ኢሳይያስ
54 “አንቺ ያልወለድሽ መሃን ሴት፣ እልል በይ!+
2 “የድንኳንሽን ቦታ አስፊ።+
ታላቅ የሆነውን የማደሪያ ድንኳንሽን ሸራዎች ዘርጊ።
ፈጽሞ አትቆጥቢ፤ የድንኳንሽን ገመዶች አስረዝሚ፤
ካስማዎችሽንም አጠንክሪ።+
3 በቀኝም ሆነ በግራ ትስፋፊያለሽና።
ዘሮችሽ ብሔራትን ይወርሳሉ፤
ባድማ በሆኑትም ከተሞች ውስጥ ይኖራሉ።+
በልጅነትሽ ዘመን የደረሰብሽን ኀፍረት ትረሺዋለሽና፤
መበለትነትሽ ያስከተለብሽን ውርደትም ከእንግዲህ አታስታውሽም።”
እሱም የምድር ሁሉ አምላክ ተብሎ ይጠራል።+
7 “ለአጭር ጊዜ ተውኩሽ፤
ሆኖም በታላቅ ምሕረት መልሼ እሰበስብሻለሁ።+
9 “ይህ ለእኔ እንደ ኖኅ ዘመን ነው።+
11 “አንቺ የተጎሳቆልሽ፣+ በአውሎ ነፋስ የተናወጥሽና ማጽናኛ ያላገኘሽ ሴት ሆይ፣+
እነሆ ድንጋዮችሽን በኃይለኛ ማጣበቂያ እገነባለሁ፤
መሠረትሽንም በሰንፔር እሠራለሁ።+
14 በጽድቅ ጽኑ ሆነሽ ትመሠረቺያለሽ።+
15 ማንም ጥቃት ቢሰነዝርብሽ
እኔ አዝዤው አይደለም።
ጥቃት የሚሰነዝርብሽ ሁሉ ከአንቺ የተነሳ ይወድቃል።”+
16 “እነሆ፣ የከሰል እሳቱን በወናፍ የሚያናፋውን
የእጅ ጥበብ ባለሙያ የፈጠርኩት እኔ ነኝ፤
የሚያከናውነውም ሥራ የጦር መሣሪያ ያስገኛል።
ደግሞም ጥፋት እንዲያደርስ አጥፊውን ሰው የፈጠርኩት እኔ ራሴ ነኝ።+
17 አንቺን ለማጥቃት የተሠራ ማንኛውም መሣሪያ ይከሽፋል፤+
አንቺን ለመክሰስ የሚነሳን ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ።