መዝሙር
ሦስተኛ መጽሐፍ
(መዝሙር 73-89)
የአሳፍ+ ማህሌት።
73 አምላክ ለእስራኤል፣ ልባቸው ንጹሕ ለሆነ ሁሉ በእርግጥ ጥሩ ነው።+
2 እኔ ግን እግሮቼ ከመንገድ ሊወጡ ተቃርበው ነበር፤
አዳልጦኝ ልወድቅ ምንም አልቀረኝም።+
6 ስለዚህ ትዕቢት የአንገት ጌጣቸው ነው፤+
ዓመፅም እንደ ልብስ ይሸፍናቸዋል።
7 ከብልጽግናቸው* የተነሳ ዓይናቸው ፈጧል፤
ልባቸው ካሰበው በላይ አግኝተዋል።
8 በሌሎች ላይ ያፌዛሉ፤ ክፉ ነገርም ይናገራሉ፤+
ሌሎችን ለመጨቆን በእብሪት ይዝታሉ።+
9 የሰማይን ያህል ከፍ ያሉ ይመስል በእብሪት ይናገራሉ፤
በአንደበታቸው እንዳሻቸው እየተናገሩ በምድር ላይ ይንጎራደዳሉ።
10 በመሆኑም ሕዝቡ ወደ እነሱ ይሄዳል፤
ከእነሱ የተትረፈረፈ ውኃም ይጠጣል።
11 እነሱም “አምላክ እንዴት ያውቃል?+
ልዑሉ አምላክ በእርግጥ እውቀት አለው?” ይላሉ።
12 አዎ፣ ክፉዎች እንደዚህ ናቸው፤ ሁልጊዜ ሳይጨናነቁ ይኖራሉ።+
የሀብታቸውንም መጠን ያሳድጋሉ።+
13 በእርግጥም ልቤን ያነጻሁት፣
ንጹሕ መሆኔንም ለማሳየት እጄን የታጠብኩት በከንቱ ነው።+
15 እነዚህን ነገሮች ተናግሬ ቢሆን ኖሮ፣
ሕዝብህን* መክዳት ይሆንብኝ ነበር።
16 ይህን ለመረዳት በሞከርኩ ጊዜ፣
የሚያስጨንቅ ሆነብኝ፤
17 ይኸውም ወደ ታላቁ የአምላክ መቅደስ እስክገባና
የወደፊት ዕጣቸውን እስክረዳ ድረስ ነበር።
18 በእርግጥም በሚያዳልጥ መሬት ላይ ታስቀምጣቸዋለህ።+
ለጥፋት እንዲዳረጉም ትጥላቸዋለህ።+
19 እንዴት በቅጽበት ጠፉ!+
በአስደንጋጭ ሁኔታ ተደመሰሱ! የደረሰባቸው ጥፋት ቅጽበታዊ ነው!
20 ይሖዋ ሆይ፣ ሰው ከእንቅልፉ ሲነሳ እንደሚረሳው ሕልም፣
አንተም በምትነሳበት ጊዜ ምስላቸውን ታስወግዳለህ።*
22 እኔም ማመዛዘን የማልችልና ማስተዋል የጎደለኝ ሆኜ ነበር፤
በአንተ ፊት ማሰብ እንደማይችል እንስሳ ሆንኩ።
23 አሁን ግን ሁልጊዜ ከአንተ ጋር ነኝ፤
አንተም ቀኝ እጄን ይዘሃል።+
25 በሰማይ ማን አለኝ?
በምድርም ላይ ከአንተ ሌላ የምሻው የለም።+
26 ሰውነቴም ሆነ ልቤ ሊዝል ይችላል፤
አምላክ ግን ለዘላለም የልቤ ዓለትና ድርሻዬ ነው።+
27 ከአንተ የሚርቁ በእርግጥ ይጠፋሉ።
አንተን በመተው ብልሹ ምግባር የሚፈጽሙትን* ሁሉ ትደመስሳቸዋለህ።*+
28 እኔ ግን ወደ አምላክ መቅረብ ይበጀኛል።+
ሥራዎቹን ሁሉ እንዳውጅ+
ሉዓላዊውን ጌታ ይሖዋን መጠጊያዬ አድርጌዋለሁ።