ኢሳይያስ
51 “እናንተ ጽድቅን የምትከታተሉ፣
ይሖዋንም የምትፈልጉ ስሙኝ።
ተፈልፍላችሁ የወጣችሁበትን ዓለት፣
ተቆፍራችሁ የወጣችሁበትንም ካባ ተመልከቱ።
3 ይሖዋ ጽዮንን ያጽናናታልና።+
በእሷም ውስጥ ሐሴትና ታላቅ ደስታ
እንዲሁም ምስጋናና ደስ የሚያሰኝ መዝሙር ይገኛሉ።+
4 ሕዝቤ ሆይ፣ በጥሞና አዳምጡኝ፤
አንተም የእኔ ብሔር፣ ጆሮህን ስጠኝ።+
5 ጽድቄ ቀርቧል።+
6 ዓይኖቻችሁን ወደ ሰማያት አንሱ፤
ወደታችም ወደ ምድር ተመልከቱ።
ሰማያት እንደ ጭስ በነው ይጠፋሉና፤
ምድርም እንደ ልብስ ታረጃለች፤
ነዋሪዎቿም እንደ ትንኝ ይረግፋሉ።
ሟች የሆኑ ሰዎች የሚሰነዝሩትን ትችት አትፍሩ፤
ስድባቸውም አያሸብራችሁ።
ሆኖም ጽድቄ ለዘላለም፣
ማዳኔም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።”+
9 የይሖዋ ክንድ ሆይ፣+
ተነስ! ተነስ! ብርታትንም ልበስ!
ከረጅም ጊዜ በፊት፣ በጥንቶቹ ትውልዶች ዘመን እንደሆነው ተነስ።
10 ባሕሩን፣ የተንጣለለውን የጥልቁን ውኃ ያደረቅከው አንተ አይደለህም?+
የተቤዠሃቸው ሰዎች እንዲሻገሩ ጥልቁን ባሕር መንገድ ያደረግከው አንተ አይደለህም?+
11 ይሖዋ የዋጃቸው ይመለሳሉ።+
ሐሴት ያደርጋሉ፤ ታላቅ ደስታም ያገኛሉ፤
ሐዘንና ሲቃም ከእነሱ ይሸሻሉ።+
12 “የማጽናናችሁ እኔ ራሴ ነኝ።+
ሟች የሆነውን ሰው፣
እንደ ሣርም የሚጠወልገውን የሰው ልጅ የምትፈሪው ለምንድን ነው?+
ደግሞም ጨቋኙ* ሊያጠፋህ የተዘጋጀ ይመስል
ከእሱ ቁጣ የተነሳ ቀኑን ሙሉ በፍርሃት ተውጠህ ነበር።
ታዲያ አሁን የጨቋኙ ቁጣ የት አለ?
17 ከይሖዋ እጅ የቁጣውን ጽዋ የጠጣሽ
ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ተነሺ! ተነሺ! ቁሚ።+
ዋንጫውን ጠጥተሻል፤
የሚያንገዳግደውን ጽዋ ጨልጠሻል።+
18 ከወለደቻቸው ወንዶች ልጆች ሁሉ መካከል አንድም የሚመራት የለም፤
ካሳደገቻቸውም ወንዶች ልጆች ሁሉ መካከል እጇን ይዞ የወሰዳት ማንም የለም።
19 እነዚህ ሁለት ነገሮች ደርሰውብሻል።
ማን ያስተዛዝንሻል?
ጥፋትና ውድመት እንዲሁም ረሃብና ሰይፍ መጥቶብሻል!+
ማንስ ያጽናናሻል?+
20 ወንዶች ልጆችሽ ራሳቸውን ስተዋል።+
በመረብ እንደተያዘ የዱር በግ
በየመንገዱ ማዕዘን ላይ* ይተኛሉ።
የይሖዋ ቁጣ፣ የአምላክሽም ተግሣጽ ሙሉ በሙሉ ወርዶባቸዋል።”
21 ስለዚህ አንቺ የተጎሳቆልሽና ያለወይን ጠጅ የሰከርሽ ሴት ሆይ፣
እባክሽ ይህን ስሚ።
22 ለሕዝቡ የሚሟገተው ጌታሽና አምላክሽ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
አንቺም ጀርባሽን እንደ መሬት፣
እንደሚሄዱበትም መንገድ አደረግሽላቸው።”