ኢሳይያስ
60 “አንቺ ሴት ሆይ፣ ተነሺ፣+ ብርሃን አብሪ፤ ብርሃንሽ መጥቷልና።
የይሖዋ ክብር በአንቺ ላይ ያበራል።+
2 እነሆ፣ ጨለማ ምድርን፣
ድቅድቅ ጨለማም ብሔራትን ይሸፍናል፤
በአንቺ ላይ ግን ይሖዋ ያበራል፤
ክብሩም በአንቺ ላይ ይታያል።
4 ዓይንሽን አንስተሽ ዙሪያሽን ተመልከቺ!
ሁሉም አንድ ላይ ተሰብስበዋል፤ ወደ አንቺም እየመጡ ነው።
5 በዚያን ጊዜ ታያለሽ፤ ፊትሽም ይፈካል፤+
ልብሽ በኃይል ይመታል፤ በደስታም ይሞላል፤
ምክንያቱም የባሕር ብልጽግና ወደ አንቺ ይጎርፋል፤
የብሔራትም ሀብት ወደ አንቺ ይመጣል።+
ሁሉም ወርቅና ነጭ ዕጣን ይዘው
ከሳባ ይመጣሉ።
የይሖዋንም ውዳሴ ያውጃሉ።+
7 የቄዳር+ መንጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ።
የነባዮት+ አውራ በጎች ያገለግሉሻል።
8 እንደ ደመና፣ ወደ ቤታቸውም* እንደሚተሙ ርግቦች
እየበረሩ የሚመጡት እነዚህ እነማን ናቸው?
9 ደሴቶች እኔን ተስፋ ያደርጋሉና፤+
የተርሴስ መርከቦችም ከሩቅ ወንዶች ልጆችሽን
ከነብራቸውና ከነወርቃቸው
ለአምላክሽ ለይሖዋ ስምና ለእስራኤል ቅዱስ ለማምጣት+
ቀዳሚ ሆነው* ይወጣሉ፤
12 አንቺን የማያገለግል ማንኛውም ብሔርም ሆነ ማንኛውም መንግሥት ይጠፋልና፤
ብሔራትም ፈጽመው ይደመሰሳሉ።+
13 የመቅደሴን ስፍራ አስውብ ዘንድ
የሊባኖስ ክብር፣+ ጥዱ፣ የአሽ ዛፉና* የፈረንጅ ጥዱ
በአንድነት ወደ አንቺ ይመጣሉ፤+
እግሬ የሚያርፍበትንም ስፍራ አከብራለሁ።+
14 የጨቋኞችሽ ወንዶች ልጆች መጥተው በፊትሽ ይሰግዳሉ፤
የሚያዋርዱሽ ሁሉ እግርሽ ሥር ይደፋሉ፤
ደግሞም የይሖዋ ከተማ፣
የእስራኤልም ቅዱስ አምላክ ንብረት የሆንሽ ጽዮን ብለው ይጠሩሻል።+
16 አንቺም የብሔራትን ወተት ትጠጫለሽ፤+
የነገሥታትን ጡት ትጠቢያለሽ፤+
እኔ ይሖዋ አዳኝሽ እንደሆንኩ፣
ደግሞም የያዕቆብ ኃያል አምላክ የሆንኩት እኔ እንደምቤዥሽ በእርግጥ ታውቂያለሽ።+
17 በመዳብ ፋንታ ወርቅ፣
በብረት ፋንታ ብር፣
በእንጨት ፋንታ መዳብ፣
በድንጋዮችም ፋንታ ብረት አመጣለሁ፤
ሰላምንም የበላይ ተመልካቾችሽ፣
ጽድቅንም አሠሪዎችሽ አድርጌ እሾማለሁ።+
18 ከዚህ በኋላ በምድርሽ ውስጥ ዓመፅ፣
ወይም በክልልሽ ውስጥ ጥፋትና ውድመት አይሰማም።+
ቅጥሮችሽን መዳን፣+ በሮችሽንም ውዳሴ ብለሽ ትጠሪያቸዋለሽ።
21 ሕዝቦችሽም ሁሉ ጻድቃን ይሆናሉ፤
ምድሪቱን ለዘላለም ይወርሳሉ።
እነሱ፣ ውበት እጎናጸፍ ዘንድ የተከልኳቸው ችግኞች፣
የእጆቼም ሥራ ናቸው።+
22 ጥቂት የሆነው ሺህ፣
ትንሽ የሆነውም ኃያል ብሔር ይሆናል።
እኔ ይሖዋ፣ ይህን በራሱ ጊዜ አፋጥነዋለሁ።”