ኢሳይያስ
45 ይሖዋ ለቀባው ለቂሮስ+ እንዲህ ይላል፦
ብሔራትን በፊቱ ለማስገዛት፣+
ነገሥታትን ትጥቅ ለማስፈታት*
እንዲሁም የከተማው በሮች እንዳይዘጉ
መዝጊያዎቹን በፊቱ ለመክፈት ስል
ቀኝ እጁን ለያዝኩት+ ለቂሮስ፦
2 “እኔ በፊትህ እሄዳለሁ፤+
ኮረብቶቹንም ደልዳላ አደርጋለሁ።
የመዳብ በሮቹን እሰባብራለሁ፤
የብረት መቀርቀሪያዎቹንም እቆርጣለሁ።+
4 ለአገልጋዬ ለያዕቆብ፣ ለመረጥኩትም ለእስራኤል ስል
በስምህ እጠራሃለሁ።
አንተ ባታውቀኝም እንኳ የክብር ስም እሰጥሃለሁ።
5 እኔ ይሖዋ ነኝ፤ ከእኔም ሌላ ማንም የለም።
ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም።+
አንተ ባታውቀኝም እንኳ አበረታሃለሁ፤*
6 ይኸውም ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ* ያሉ ሕዝቦች
ከእኔ በቀር ሌላ እንደሌለ እንዲያውቁ ነው።+
እኔ ይሖዋ ነኝ፤
ከእኔም ሌላ ማንም የለም።+
8 እናንተ ሰማያት፣ ከላይ አዝንቡ፤+
ደመናት ጽድቅን እንደ ዶፍ ያውርዱ።
ምድር ትከፈት፤ መዳንንም ታፍራ፤
ጽድቅንም በአንድነት ታብቅል።+
እኔ ይሖዋ ፈጥሬዋለሁ።”
ሸክላ፣ ሠሪውን* “የምትሠራው ምንድን ነው?” ይለዋል?+
የሠራኸውስ ነገር “እሱ እጅ የለውም” ይላል?*
10 አንድን አባት “ምን ልትወልድ ነው?” ብሎ ለሚጠይቅ፣
ሴትንም “ምን ልትወልጂ ነው?”* ለሚል ወዮለት!
11 የእስራኤል ቅዱስ፣+ ሠሪው የሆነው ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“ወደፊት ስለሚሆኑት ነገሮች ልትጠይቁኝ፣
ደግሞስ ልጆቼንና+ የእጆቼን ሥራ በተመለከተ ልታዙኝ ትፈልጋላችሁ?
12 እኔ ምድርን ሠርቻለሁ፤+ በላይዋም ላይ ሰውን ፈጥሬአለሁ።+
13 “እኔ አንድን ሰው በጽድቅ አስነስቻለሁ፤+
መንገዱንም ሁሉ ቀና አደርጋለሁ።
14 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
በሰንሰለት ታስረው ከኋላሽ ይሄዳሉ።
መጥተው ይሰግዱልሻል።+
ደግሞም በጸሎት ‘አምላክ በእርግጥ ከአንቺ ጋር ነው፤+
ከእሱም በቀር ሌላ የለም፤ ሌላም አምላክ የለም’ ይሉሻል።”
15 አዳኝ የሆንከው የእስራኤል አምላክ ሆይ፣+
በእርግጥ አንተ ራስህን የምትሰውር አምላክ ነህ።
16 ሁሉም ያፍራሉ፤ ይዋረዳሉም፤
ጣዖቶችን የሚሠሩ ሁሉ ውርደት ተከናንበው ይሄዳሉ።+
17 እስራኤል ግን በይሖዋ ዘላለማዊ መዳን ያገኛል።+
እናንተም ለዘላለም አታፍሩም ወይም አትዋረዱም።+
“እኔ ይሖዋ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለም።
እኔ ይሖዋ ጽድቅ የሆነውን እናገራለሁ፤ ቅን የሆነውንም አወራለሁ።+
20 ተሰብስባችሁ ኑ።
እናንተ ከብሔራት ያመለጣችሁ፣ በአንድነት ቅረቡ።+
የተቀረጹ ምስሎቻቸውን ተሸክመው የሚዞሩም ሆኑ
ሊያድናቸው ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ+ ምንም እውቀት የላቸውም።
21 ጉዳያችሁን ተናገሩ፤ እንዲሁም ሙግታችሁን አቅርቡ።
ተሰብስበው በአንድነት ይማከሩ።
ከረጅም ጊዜ በፊት ይህን አስቀድሞ የተናገረ ማን ነው?
ከጥንትስ ጀምሮ ይህን ያወጀ ማን ነው?
ይህን ያደረግኩት እኔ ይሖዋ አይደለሁም?
በእሱ ላይ የተቆጡ ሁሉ ኀፍረት ተከናንበው ወደ እሱ ይመጣሉ።
25 የእስራኤል ዘር ሁሉ በይሖዋ ትክክለኛ ሆኖ ይገኛል፤+
በእሱም ይኮራል።’”