ኢሳይያስ
42 እነሆ፣ ደግፌ የያዝኩት፣
2 አይጮኽም ወይም ድምፁን ከፍ አያደርግም፤
ድምፁንም በጎዳና ላይ አያሰማም።+
3 የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም፤
የሚጨስንም የጧፍ ክር አያጠፋም።+
ፍትሕን በታማኝነት ያመጣል።+
5 ሰማያትን የፈጠረውና የዘረጋው፣+
ምድርንና በውስጧ ያሉትን ነገሮች ሁሉ የሠራው፣+
በላይዋም ለሚኖሩ ሰዎች እስትንፋስን፣+
በእሷም ላይ ለሚመላለሱ መንፈስን የሰጠው+
እውነተኛው አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
6 “እኔ ይሖዋ በጽድቅ ጠርቼሃለሁ፤
እጅህን ይዣለሁ።
እጠብቅሃለሁ፤ እንዲሁም ለሰዎች ቃል ኪዳን፣
ለብሔራትም ብርሃን አድርጌ እሰጥሃለሁ፤+
7 አንተም የዓይነ ስውራንን ዓይን ታበራለህ፤+
እስረኛውን ከወህኒ ቤት፣
በጨለማ ውስጥ የተቀመጡትንም ከእስር ቤት ታወጣለህ።+
9 እነሆ፣ የቀደሙት ነገሮች ተፈጽመዋል፤
አሁን ደግሞ አዳዲስ ነገሮችን እናገራለሁ።
ገና ከመከሰታቸው በፊት ስለ እነሱ እነግራችኋለሁ።”+
10 እናንተ በባሕር ላይና በውስጡ ባሉት ፍጥረታት መካከል የምትጓዙ፣
እናንተ ደሴቶችና በእነሱ ላይ የምትኖሩ ሁሉ፣+
ለይሖዋ አዲስ መዝሙር ዘምሩ፤+
ከምድር ዳርቻም ውዳሴውን አሰሙ።+
ዓለታማ በሆኑ ቦታዎች የሚኖሩ ሰዎች በደስታ እልል ይበሉ፤
በተራሮችም አናት ላይ ሆነው ይጩኹ።
12 ለይሖዋ ክብር ይስጡ፤
በደሴቶችም ላይ ውዳሴውን ያውጁ።+
13 ይሖዋ እንደ ኃያል ሰው ይወጣል።+
እንደ ተዋጊ ቅንዓቱን ይቀሰቅሳል።+
ይጮኻል፤ አዎ፣ ቀረርቶ ያሰማል፤
ከጠላቶቹ ይበልጥ ኃያል መሆኑን ያሳያል።+
14 “ለረጅም ጊዜ ዝም አልኩ።
ጸጥ ብዬ ቆየሁ፤ ራሴንም ገታሁ።
ምጥ እንደያዛት ሴት
እቃትታለሁ፣ አለከልካለሁ እንዲሁም ቁና ቁና እተነፍሳለሁ።
15 ተራሮችንና ኮረብቶችን አወድማለሁ፤
ደግሞም በላያቸው ላይ ያለውን ተክል ሁሉ አደርቃለሁ።
ይህን አደርግላቸዋለሁ፤ ደግሞም አልተዋቸውም።”
18 እናንተ ደንቆሮዎች፣ ስሙ፤
እናንተ ዕውሮች እዩ፤ ተመልከቱም።+
19 ከአገልጋዬ በቀር የታወረ፣
እንደምልከው መልእክተኛዬም ደንቆሮ የሆነ ማን አለ?
ብድራት እንደተከፈለው ሰው ዕውር የሆነ
ወይም እንደ ይሖዋ አገልጋይ የታወረ ማን ነው?+
20 ብዙ ነገሮች ብታዩም ልብ የምትሉት ነገር የለም።
ጆሮዎቻችሁን ብትከፍቱም ምንም አትሰሙም።+
21 ይሖዋ ለጽድቁ ሲል
ሕጉን* ታላቅና ክብራማ በማድረግ ደስ ተሰኝቷል።
የሚታደጋቸው በሌለበት ተበዝብዘዋል፤+
“መልሷቸው!” የሚል በሌለበትም ተዘርፈዋል።
23 ከእናንተ መካከል ይህን የሚሰማ ማን ነው?
በትኩረት የሚያዳምጥና ለወደፊቱ ጊዜ ትምህርት የሚወስድ ማን ነው?
24 ያዕቆብን ለዘረፋ፣
እስራኤልንም ለበዝባዦች አሳልፎ የሰጠ ማን ነው?
በእሱ ላይ ኃጢአት በመፈጸም የበደልነው ይሖዋ አይደለም?
25 ስለዚህ ንዴቱን፣ ቁጣውንና የጦርነቱን መዓት
በእስራኤል ላይ አፈሰሰ።+
የጦርነቱም እሳት በዙሪያው ያለውን ሁሉ በላው፤ እሱ ግን አላስተዋለም።+
አቃጠለው፤ እሱ ግን ጨርሶ ልብ አላለም።+