መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የይሖዋ አገልጋይ የሆነው ዳዊት፣ ይሖዋ ከጠላቶቹ ሁሉ እጅና ከሳኦል እጅ ባዳነው ቀን ለይሖዋ የዘመረው መዝሙር፦+
18 ብርታቴ ይሖዋ ሆይ፣+ እወድሃለሁ።
2 ይሖዋ ቋጥኜ፣ ምሽጌና ታዳጊዬ ነው።+
3 ውዳሴ የሚገባውን ይሖዋን እጠራለሁ፤
ከጠላቶቼም እድናለሁ።+
6 በጭንቅ ውስጥ ሳለሁ ይሖዋን ጠራሁት፤
እርዳታ ለማግኘት አምላኬን አጥብቄ ተማጸንኩት።
10 በኪሩብ ላይ ተቀምጦ እየበረረ መጣ።+
12 በፊቱ ካለው ብርሃን፣
ከደመናቱ መካከል በረዶና ፍም ወጣ።
16 ከላይ ሆኖ እጁን ሰደደ፤
ከጥልቅ ውኃ ውስጥም አወጣኝ።+
18 ችግር ላይ በወደቅኩበት ቀን ተነሱብኝ፤+
ይሖዋ ግን ድጋፍ ሆነልኝ።
21 የይሖዋን መንገድ ጠብቄአለሁና፤
አምላኬን በመተው ክፉ ድርጊት አልፈጸምኩም።
22 ፍርዱ ሁሉ በፊቴ ነው፤
ደንቦቹን ቸል አልልም።
25 ታማኝ ለሆነ ሰው ታማኝ ትሆናለህ፤+
እንከን የለሽ ለሆነ ሰው እንከን የለሽ ትሆናለህ፤+
26 ከንጹሕ ሰው ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፤+
ጠማማ ለሆነ ሰው ግን ብልህ መሆንህን ታሳያለህ።+
28 ይሖዋ ሆይ፣ መብራቴን የምታበራው አንተ ነህና፤
አምላኬ ሆይ፣ ጨለማዬን ብርሃን የምታደርገው አንተ ነህ።+
እሱ መጠጊያ ለሚያደርጉት ሁሉ ጋሻቸው ነው።+
31 ደግሞስ ከይሖዋ ሌላ አምላክ ማን ነው?+
ከአምላካችንስ ሌላ ዓለት ማን ነው?+
33 እግሮቼን እንደ ዋልያ እግሮች ያደርጋል፤
በከፍታ ቦታዎች ላይ ያቆመኛል።+
34 እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናል፤
ክንዶቼ የመዳብ ደጋን ማጠፍ ይችላሉ።
37 ጠላቶቼን አሳድጄ እደርስባቸዋለሁ፤
ተጠራርገው እስኪጠፉ ድረስ ወደ ኋላ አልመለስም።
38 እንዳያንሰራሩ አድርጌ አደቃቸዋለሁ፤+
እግሬ ሥር ይወድቃሉ።
39 ለውጊያው ብርታት ታስታጥቀኛለህ፤
ጠላቶቼ ሥሬ እንዲወድቁ ታደርጋለህ።+
41 እርዳታ ለማግኘት ይጮኻሉ፤ ሆኖም የሚያድናቸው የለም፤
ወደ ይሖዋም ይጮኻሉ፤ እሱ ግን አይመልስላቸውም።
42 በነፋስ ፊት እንዳለ አቧራ ፈጽሜ አደቃቸዋለሁ፤
በመንገድ ላይ እንዳለ ጭቃ አውጥቼ እጥላቸዋለሁ።
43 ስህተት ከሚለቃቅሙ ሰዎች ታድነኛለህ።+
የብሔራት መሪ አድርገህ ትሾመኛለህ።+
የማላውቀው ሕዝብ ያገለግለኛል።+
44 ስለ እኔ በሰሙት ነገር ብቻ ይታዘዙኛል፤
የባዕድ አገር ሰዎችም አንገታቸውን ደፍተው ወደ ፊቴ ይቀርባሉ።+
45 የባዕድ አገር ሰዎች ወኔ ይከዳቸዋል፤*
ከምሽጎቻቸው እየተንቀጠቀጡ ይወጣሉ።
46 ይሖዋ ሕያው ነው! ዓለቴ+ ይወደስ!
የመዳኔ አምላክ ከፍ ከፍ ይበል።+
47 እውነተኛው አምላክ ይበቀልልኛል፤+
ሕዝቦችንም ከበታቼ ያስገዛልኛል።