መኃልየ መኃልይ
1 ከመዝሙሮች ሁሉ የሚበልጠው የሰለሞን+ መዝሙር፦*
2 “በከንፈሩ መሳም ይሳመኝ፤
የፍቅር መግለጫዎችህ ከወይን ጠጅ ይልቅ ደስ ያሰኛሉና።+
3 የዘይትህ መዓዛ ደስ ይላል።+
ስምህ ጥሩ መዓዛ እንዳለው የሚፈስ ዘይት ነው።+
ቆነጃጅት የሚወዱህ ለዚህ ነው።
4 ይዘኸኝ ሂድ፤* አብረን እንሩጥ።
ንጉሡ ወደ እልፍኞቹ አስገብቶኛል!
በአንተ ደስ ይበለን፤ ሐሴትም እናድርግ።
ከወይን ጠጅ ይልቅ የፍቅር መግለጫዎችህን እናወድስ።*
አንተን መውደዳቸው* ተገቢ ነው።
6 ጥቁር ስለሆንኩ ትኩር ብላችሁ አትዩኝ፤
ፀሐይ ፊቴን አክስሎታልና።
ወንድሞቼ በጣም ተቆጡኝ፤
የወይን እርሻዎች ጠባቂ አደረጉኝ፤
የገዛ ራሴን የወይን እርሻ ግን መጠበቅ አልቻልኩም።
በጓደኞችህ መንጎች መካከል
በመሸፈኛ* ፊቷን ተሸፋፍና እንደምትቅበዘበዝ ሴት ለምን ልሁን?”
8 “አንቺ ከሴቶች ሁሉ እጅግ የተዋብሽ ሆይ፣ የማታውቂ ከሆነ
የመንጋውን ዱካ ተከትለሽ ሂጂ፤
የፍየል ግልገሎችሽንም በእረኞቹ ድንኳኖች አጠገብ አሰማሪ።”
9 “ፍቅሬ ሆይ፣ የፈርዖንን ሠረገሎች በሚጎትቱ ፈረሶች መካከል እንዳለች ባዝራ* ውብ ነሽ።+
10 ጉንጮችሽ በማስዋቢያ ተውበዋል፤*
አንገትሽም በጨሌ ሐብል አጊጧል።
11 በብር ፈርጥ የተንቆጠቆጡ
የወርቅ ጌጦች* እንሠራልሻለን።”
13 ውዴ ለእኔ ጥሩ መዓዛ እንዳለው በከረጢት ያለ ከርቤ+ ነው፤
በጡቶቼ መካከል ያድራል።
15 “ፍቅሬ ሆይ፣ እነሆ፣ አንቺ ውብ ነሽ።
እነሆ፣ አንቺ ውብ ነሽ። ዓይኖችሽ እንደ ርግብ+ ዓይኖች ናቸው።”
16 “ውዴ ሆይ፣ እነሆ፣ አንተ ውብ* ነህ፤ ደግሞም ደስ ትላለህ።+
አልጋችን በለምለም ቅጠል መካከል ነው።
17 የቤታችን* ተሸካሚዎች አርዘ ሊባኖሶች፣
ጣሪያችንም የጥድ ዛፎች ናቸው።
2 “ፍቅሬ በሴቶች መካከል ስትታይ
በእሾህ መካከል እንዳለ አበባ ናት።”
3 “ውዴ በወንዶች መካከል ሲታይ
በዱር ዛፎች መካከል እንዳለ የፖም ዛፍ ነው።
በጥላው ሥር ለመቀመጥ እጅግ እጓጓለሁ፤
ፍሬውም ለአፌ ጣፋጭ ነው።
4 ወደ ግብዣ ቤት* ወሰደኝ፤
የፍቅር ዓርማውንም በእኔ ላይ አውለበለበ።
6 ግራ እጁን ተንተርሻለሁ፤
ቀኝ እጁም አቅፎኛል።+
7 የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣ በራሱ እስኪነሳሳ ድረስ
ፍቅርን በውስጤ እንዳትቀሰቅሱ ወይም እንዳታነሳሱ፣
በሜዳ ፍየሎችና+ በመስክ ላይ ባሉ አጋዘኖች አምላችኋለሁ።+
8 እነሆ፣ ውዴ ተራሮቹን እየወጣና
በኮረብቶቹ ላይ እየዘለለ ሲመጣ
ድምፁ ይሰማኛል!
9 ውዴ፣ የሜዳ ፍየል ወይም የአጋዘን ግልገል+ ይመስላል።
በመስኮት በኩል ትኩር ብሎ እየተመለከተ፣
በፍርግርጉ በኩል አጮልቆ እያየ
ከግድግዳችን ጀርባ ቆሟል።
10 ውዴ እንዲህ አለኝ፦
‘ፍቅሬ ሆይ፣ ተነሽ፤
የእኔ ቆንጆ፣ ነይ አብረን እንሂድ።
11 እነሆ፣ ክረምቱ አልፏል።
ዝናቡ ቆሟል፤ ደግሞም ጠፍቷል።
13 የበለስ ዛፏ መጀመሪያ ላይ ያፈራቻቸው ፍሬዎች በስለዋል፤+
የወይን ተክሎቹም አብበው መዓዛቸውን ሰጥተዋል።
ፍቅሬ ሆይ፣ ተነሽና ነይ፤
የእኔ ቆንጆ፣ ነይ አብረን እንሂድ።
14 በዓለቶች መሃል በሚገኝ መሸሸጊያ፣
በገደላማ ስፍራ ባለ ሰዋራ ቦታ ያለሽ ርግቤ ሆይ፣+
እስቲ ልይሽ፤ ድምፅሽንም ልስማው፤+
ድምፅሽ ማራኪ፣ ቁመናሽም ያማረ ነውና።’”+
15 “ቀበሮዎቹን ይኸውም የወይን እርሻዎቹን የሚያበላሹትን
ትናንሽ ቀበሮዎች ያዙልን፤
የወይን እርሻችን አብቧልና።”
16 “ውዴ የእኔ ነው፤ እኔም የእሱ ነኝ።+
መንጋውን በአበቦች መካከል እየጠበቀ ነው።+
17 የቀኑ ነፋስ መንፈስ ከመጀመሩና ጥላው ከመሸሹ በፊት
ውዴ ሆይ፣ እንደ ሜዳ ፍየል
ፈለግኩት፤ ግን አላገኘሁትም።+
ፈለግኩት፤ ግን አላገኘሁትም።
3 በከተማዋ ውስጥ የሚዘዋወሩት ጠባቂዎች አገኙኝ።+
እኔም ‘የምወደውን* ሰው አይታችሁታል?’ ብዬ ጠየቅኳቸው።
4 ከእነሱ ገና እልፍ እንዳልኩ
የምወደውን* ሰው አገኘሁት።
5 የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣ በራሱ እስኪነሳሳ ድረስ
ፍቅርን በውስጤ እንዳትቀሰቅሱ ወይም እንዳታነሳሱ
በሜዳ ፍየሎችና በመስክ ላይ ባሉ አጋዘኖች አምላችኋለሁ።”+
7 “እነሆ፣ ይህ የሰለሞን ድንክ አልጋ ነው።
ከእስራኤል ኃያላን የተውጣጡ
ስልሳ ኃያላን አጅበውታል፤+
8 ሁሉም ሰይፍ የታጠቁና
በውጊያ የሠለጠኑ ናቸው፤
እያንዳንዳቸውም በሌሊት የሚያጋጥሙ አስፈሪ ነገሮችን ለመከላከል
ሰይፋቸውን ወገባቸው ላይ ታጥቀዋል።”
10 ዓምዶቹን የሠራው ከብር፣
መደገፊያዎቹን ደግሞ ከወርቅ ነው።
መቀመጫው በሐምራዊ ሱፍ የተሠራ ነው፤
ውስጡንም የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች
በፍቅር ተነሳስተው ለብጠውታል።”
11 “እናንተ የጽዮን ሴቶች ልጆች ሆይ፣
ወጥታችሁ ንጉሥ ሰለሞንን ተመልከቱ፤
በሠርጉ ዕለት፣
ልቡ ሐሴት ባደረገበት በዚያ ቀን፣
4 “ፍቅሬ ሆይ፣ እነሆ፣ አንቺ ውብ ነሽ።
እነሆ፣ አንቺ ውብ ነሽ።
ዓይኖችሽ በፊትሽ መሸፈኛ ውስጥ ሲታዩ እንደ ርግብ ዓይኖች ናቸው።
ፀጉርሽ ከጊልያድ+ ተራሮች
እየተግተለተለ እንደሚወርድ የፍየል መንጋ ነው።
2 ጥርሶችሽ ገና ተሸልተውና
ታጥበው እንደወጡ፣
ሁሉም መንታ መንታ እንደወለዱ የበግ መንጋ ናቸው፤
ደግሞም ከመካከላቸው ግልገሉን ያጣ የለም።
3 ከንፈሮችሽ እንደ ደማቅ ቀይ ፈትል ናቸው፤
ንግግርሽም አስደሳች ነው።
በመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ጉንጮችሽ*
የተከፈለ ሮማን ይመስላሉ።
4 አንገትሽ+ አንድ ሺህ ጋሻዎች፣
ይኸውም ኃያላን ሰዎች የሚይዟቸው ክብ ጋሻዎች+ ሁሉ የተንጠለጠሉበትንና
በንብርብር ድንጋዮች የተገነባውን
የዳዊት ማማ+ ይመስላል።
7 “ፍቅሬ ሆይ፣ ሁለንተናሽ ውብ ነው፤+
እንከንም የለብሽም።
8 ሙሽራዬ ሆይ፣ ተያይዘን ከሊባኖስ እንሂድ፤
አዎ፣ ከሊባኖስ+ አብረን እንሂድ።
10 እህቴ፣ ሙሽራዬ ሆይ፣ የፍቅር መግለጫዎችሽ እንዴት ደስ ያሰኛሉ!+
11 ሙሽራዬ ሆይ፣ ከንፈሮችሽ የማር እንጀራ ወለላ ያንጠባጥባሉ።+
ከምላስሽ ሥር ማርና ወተት ይፈልቃል፤+
የልብሶችሽም ጠረን እንደ ሊባኖስ መዓዛ ነው።
12 እህቴ፣ ሙሽራዬ፣ የተቆለፈ የአትክልት ቦታ፣
አዎ የተቆለፈ የአትክልት ቦታ፣ የታሸገም ምንጭ ናት።
13 ቡቃያሽ* ሮማንና ምርጥ ፍራፍሬዎች
ደግሞም የሂና እና የናርዶስ ተክሎች የበቀሉበት ገነት* ነው፤
14 በተጨማሪም ናርዶስ፣+ ሳፍሮን፣* ጠጅ ሣር፣+ ቀረፋ፣+
ነጭ ዕጣን የሚገኝባቸው የተለያዩ ዛፎች፣ ከርቤ፣ እሬትና*+
ሁሉም ዓይነት ምርጥ ሽቶዎች+ ያሉበት ገነት ነው።
15 አንቺ በአትክልት ቦታ ያለ ምንጭ፣ ንጹሕ ውኃ የሚገኝበት ጉድጓድና
ከሊባኖስ የሚፈስሱ ጅረቶች ነሽ።+
16 የሰሜን ነፋስ ሆይ፣ ንቃ፤
የደቡብ ነፋስ ሆይ፣ ና።
በአትክልት ቦታዬ ላይ ንፈስ።*
መዓዛውም አካባቢውን ያውደው።”
“ውዴ ወደ አትክልት ቦታው ይግባና
ምርጥ የሆኑትን ፍራፍሬዎች ይብላ።”
5 “እህቴ፣ ሙሽራዬ ሆይ፣
ወደ አትክልት ቦታዬ ገብቻለሁ።+
ከርቤዬንና ቅመሜን+ ወስጃለሁ።
የማር እንጀራዬንና ወለላውን በልቻለሁ፤
የወይን ጠጄንና ወተቴን ጠጥቻለሁ።”+
“ውድ ጓደኞቼ፣ ብሉ!
ጠጥታችሁም በፍቅር መግለጫዎች ስከሩ!”+
2 “እኔ ተኝቻለሁ፤ ልቤ ግን ነቅቷል።+
ውዴ በሩን ሲያንኳኳ ይሰማኛል!
‘እህቴ ሆይ፣ የእኔ ፍቅር፣
እንከን የለሽ ርግቤ ሆይ፣ ክፈቺልኝ!
ራሴ በጤዛ፣
ፀጉሬም በሌሊቱ እርጥበት ርሷል።’+
3 ልብሴን አውልቄአለሁ።
መልሼ መልበስ ሊኖርብኝ ነው?
እግሬን ታጥቤአለሁ።
እንደገና ላቆሽሸው ነው?
4 ውዴ እጁን ከበሩ ቀዳዳ መለሰ፤
ለእሱ ያለኝ ስሜትም ተነሳሳ።
5 እኔም ለውዴ በሩን ለመክፈት ተነሳሁ፤
የመዝጊያው እጀታ ላይ
እጆቼ ከርቤ፣
ጣቶቼም የከርቤ ፈሳሽ አንጠባጠቡ።
6 ለውዴ በሩን ከፈትኩለት፤
ውዴ ግን በዚያ አልነበረም፤ ሄዶ ነበር።
በመሄዱም ተስፋ ቆረጥኩ።*
ፈለግኩት፤ ግን አላገኘሁትም።+
ጠራሁት፤ እሱ ግን አልመለሰልኝም።
7 ከተማዋን እየተዘዋወሩ የሚጠብቁት ሰዎች አገኙኝ።
መቱኝ፤ አቆሰሉኝ።
የቅጥሩ ጠባቂዎች ነጠላዬን* ገፈፉኝ።
8 የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣
ውዴን ካገኛችሁት በፍቅሩ ተይዤ መታመሜን
እንድትነግሩት አምላችኋለሁ።”
9 “አንቺ ከሴቶች ሁሉ እጅግ የተዋብሽ ሆይ፣
ውድሽ ሌሎች ከሚያፈቅሯቸው ወንዶች ሁሉ እንዴት ቢበልጥ ነው?
እንዲህ ያለ መሐላ ያስገባሽን፣
ለመሆኑ ውድሽ ሌሎች ከሚያፈቅሯቸው ወንዶች ሁሉ እንዴት ቢበልጥ ነው?”
10 “ውዴ በጣም ቆንጆና ቀይ ነው፤
በአሥር ሺህ ሰዎች መካከል እንኳ ጎልቶ ይታያል።
11 ራሱ እንደ ወርቅ፣ አዎ እንደጠራ ወርቅ ነው።
ፀጉሩ እንደሚወዛወዝ የዘንባባ ዝንጣፊ* ነው፤
እንደ ቁራም ጥቁር ነው።
13 ጉንጮቹ የቅመማ ቅመም መደብ፣+
ጥሩ መዓዛ ያላቸው ዕፀዋት ክምር ይመስላሉ።
ከንፈሮቹ ፈሳሽ ከርቤ የሚያንጠባጥቡ አበቦች ናቸው።+
14 የእጆቹ ጣቶች ወርቅ፣ የጣቶቹም ጫፎች ክርስቲሎቤ ናቸው።
ሆዱ በሰንፔር የተሸፈነ የተወለወለ የዝሆን ጥርስ ነው።
15 እግሮቹ ከምርጥ ወርቅ በተሠሩ መሰኪያዎች ላይ የቆሙ የእብነ በረድ ዓምዶች ናቸው።
መልኩ እንደ ሊባኖስ ያማረ ነው፤ እንደ አርዘ ሊባኖስም አቻ የለውም።+
የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣ ውዴ ይህ ነው፤ ፍቅሬ እንዲህ ያለ ነው።”
6 “ከሴቶች ሁሉ እጅግ የተዋብሽ ሆይ፣
ውድሽ የት ሄደ?
ለመሆኑ ውድሽ የሄደው በየት በኩል ነው?
አብረንሽ እንፈልገው።”
3 እኔ የውዴ ነኝ፤
ውዴም የእኔ ነው።+
እሱ መንጋውን በአበቦች መካከል እየጠበቀ ነው።”+
5 ስሜቴን አውከውታልና፣
ዓይኖችሽን+ ከእኔ ላይ አንሺ።
ፀጉርሽ ከጊልያድ እየተግተለተለ እንደሚወርድ
የፍየል መንጋ ነው።+
6 ጥርሶችሽ ታጥበው እንደወጡ፣
ሁሉም መንታ መንታ እንደወለዱ
የበግ መንጋ ናቸው፤
ከመካከላቸውም ግልገሉን ያጣ የለም።
7 በመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ጉንጮችሽ*
የተከፈለ ሮማን ይመስላሉ።
9 እንከን የሌለባት ርግቤ+ ግን አንድ ብቻ ናት።
እሷ ለእናቷ ብርቅዬ ልጅ ናት።
በወለደቻት ዘንድ እጅግ ተወዳጅ* ናት።
ሴቶች ልጆች አይተዋት ‘የታደልሽ ነሽ’ ይሏታል፤
ንግሥቶችና ቁባቶችም ያወድሷታል።
10 ‘እንደ ማለዳ ወጋገን የምታበራ፣*
እንደ ሙሉ ጨረቃ ውብ የሆነች፣
እንደ ፀሐይ ብርሃን የጠራች፣
በዓርማዎቻቸው ዙሪያ እንደተሰለፉ ወታደሮች እጅግ የምታምረው ይህች ሴት ማን ናት?’”+
11 “በሸለቆው* ውስጥ ያቆጠቆጡትን ተክሎች ለማየት፣
ደግሞም ወይኑ ለምልሞ፣*
የሮማን ዛፎቹም አብበው እንደሆነ ለመመልከት
የገውዝ ዛፎች ወዳሉበት ወደ አትክልት ቦታው ወረድኩ።+
13 “አንቺ ሱላማዊት፣ ተመለሺ፤ ተመለሺ!
እናይሽ ዘንድ
ተመለሺ፤ ተመለሺ!”
“በሱላማዊቷ ላይ የምታፈጡት ለምንድን ነው?”+
“እሷ የመሃናይምን ጭፈራ* ትመስላለች!”
7 “አንቺ የተከበርሽ ልጃገረድ ሆይ፣
እግሮችሽ በነጠላ ጫማሽ ውስጥ ሲታዩ እንዴት ያምራሉ!
የዳሌዎችሽ ቅርጽ
የእጅ ባለሙያ የተጠበበባቸው ጌጦች ይመስላሉ።
2 እምብርትሽ እንደ ክብ ሳህን ነው።
የተደባለቀ ወይን ጠጅ ከእሱ አይታጣ።
ሆድሽ ዙሪያውን በአበቦች እንደታጠረ
የስንዴ ክምር ነው።
3 ሁለቱ ጡቶችሽ ሁለት ግልገሎችን፣
የሜዳ ፍየል መንታዎችን ይመስላሉ።+
4 አንገትሽ+ በዝሆን ጥርስ የተሠራ ማማ ይመስላል።+
አፍንጫሽ ወደ ደማስቆ አቅጣጫ እንደሚመለከት
የሊባኖስ ማማ ነው።
ንጉሡ በዘንፋላው ፀጉርሽ ተማርኳል።*
6 አንቺ የተወደድሽ ልጃገረድ ሆይ፣ ምንኛ ውብ ነሽ! እንዴትስ ደስ ታሰኛለሽ!
በጣም ከሚያስደስቱ ነገሮች ሁሉ በላይ ትማርኪያለሽ!
7 ቁመናሽ የዘንባባ ዛፍ ይመስላል፤
ጡቶችሽ ደግሞ የቴምር ዘለላ ይመስላሉ።+
8 እኔም እንዲህ አልኩ፦ ‘የቴምር ዘለላዎቹን መያዝ እንድችል
ዛፉ ላይ እወጣለሁ።’
“ይህ የወይን ጠጅ ለውዴ እየተንቆረቆረ ይውረድ፤
በተኙ ሰዎች ከንፈር በቀስታ ይፍሰስ።
10 እኔ የውዴ ነኝ፤+
እሱም የሚመኘው እኔን ነው።
እኔም በዚያ ለአንተ ያለኝን ፍቅር እገልጽልሃለሁ።+
ውዴ ሆይ፣ አዲሶቹንም ሆነ በፊት የተቀጠፉትን ፍሬዎች
ለአንተ አስቀምጬልሃለሁ።
8 “ምነው አንተ፣ የእናቴን ጡት እንደጠባ፣
እንደ ወንድሜ በሆንክ!
እንዲህ ቢሆን ኖሮ ውጭ ሳገኝህ በሳምኩህ ነበር፤+
ማንም ባልናቀኝ ነበር።
ትጠጣው ዘንድ ቅመም የተጨመረበት ወይን ጠጅና
የሮማን ጭማቂ በሰጠሁህ ነበር።
3 ግራ እጁን በተንተራስኩ፣
ቀኝ እጁም ባቀፈኝ ነበር።+
4 የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣
በራሱ እስኪነሳሳ ድረስ ፍቅርን በውስጤ እንዳትቀሰቅሱ ወይም እንዳታነሳሱ አምላችኋለሁ።”+
5 “ውዷን ደገፍ ብላ
ከምድረ በዳ የምትመጣው ይህች ማን ናት?”
“ከፖም ዛፍ ሥር ቀሰቀስኩህ።
በዚያ እናትህ አንተን ለመውለድ አማጠች።
በዚያም ወላጅ እናትህ ምጥ ይዟት ነበር።
የፍቅር ወላፈን የእሳት ወላፈን ነው፤ የያህም* ነበልባል ነው።+
አንድ ሰው ለፍቅር ሲል የቤቱን ሀብት ሁሉ ለመስጠት ቢያቀርብ
ሰዎች በጣም ይንቁበታል።”*
8 “ገና ጡት ያላወጣች
ትንሽ እህት አለችን።+
እሷን በሚጠይቁን ቀን
ለእህታችን ምን ብናደርግ ይሻላል?”
9 “እሷ ቅጥር ብትሆን
በላይዋ ላይ የብር ጉልላት እንሠራለን፤
በር ብትሆን ግን
ከአርዘ ሊባኖስ በተሠራ ሳንቃ እናሽጋታለን።”
10 “እኔ ቅጥር ነኝ፤
ጡቶቼም እንደ ማማ ናቸው።
በእሱም ፊት
ሰላም እንዳገኘች ሴት ሆንኩ።
11 ሰለሞን በበዓልሃሞን የወይን እርሻ ነበረው።+
እሱም የወይን እርሻውን ለጠባቂዎች በአደራ ሰጠ።
እያንዳንዳቸውም ለሚያገኙት ፍሬ አንድ ሺህ የብር ሰቅል ያመጡ ነበር።
12 የራሴ የሆነ የወይን እርሻ አለኝ።
ሰለሞን ሆይ፣ አንድ ሺው የብር ሰቅል* የአንተ ነው፤
ሁለት መቶው ደግሞ ፍሬውን ለሚጠብቁት ነው።”
እስቲ እኔም ልስማው።”+
መኃልየ መኃልይ የሚለው የመጽሐፉ ስም “ከመዝሙሮች ሁሉ የሚበልጥ መዝሙር” የሚል ትርጉም አለው።
ቃል በቃል “እየሳብክ ውሰደኝ።”
ወይም “ከወይን ጠጅ ይልቅ ስለ ፍቅር መግለጫዎችህ እናውራ።”
ቆነጃጅቱን ያመለክታል።
ወይም “ነፍሴ እጅግ የምትወድህ።”
ወይም “በሐዘን መሸፈኛ።”
ወይም “ባዝራዬ።”
“በሹሩባዎች መካከል ሲታዩ ያምራሉ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ክብ የወርቅ ጌጦች።”
ቃል በቃል “የናርዶሴ።”
ወይም “አንተ መልከ መልካም።”
ወይም “የታላቁ ቤታችን።”
ቃል በቃል “ሳፍሮን።”
ቃል በቃል “ወይን ጠጅ ቤት።”
“ክፍተት ባላቸው ተራሮች” ማለትም ሊሆን ይችላል። ወይም “በቤተር ተራሮች።”
ወይም “ነፍሴ የምትወደውን።”
ወይም “ነፍሴ የምትወደውን።”
ወይም “ነፍሴ የምትወደውን።”
ወይም “ነፍሴ የምትወደውን።”
ከፍተኛ ሥልጣን ያለውን ሰው ተሸክሞ ለመውሰድ የሚያገለግል መሸፈኛ ያለው ድንክ አልጋ።
ወይም “የአበባ ጉንጉን።”
ወይም “ሰሪሳራዎችሽ።” በዓይንና በጆሮ መካከል ያለውን የአካል ክፍል ያመለክታል።
“ገላሽ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “የአትክልት ስፍራ።”
የአበባ ዓይነት ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ሽቶ ለመሥራት የሚያገለግል ጥሩ መዓዛ ያለው ንጥረ ነገር የሚገኝበትን ዛፍ ያመለክታል።
ወይም “በቀስታ ንፈስ።”
ወይም “ነፍሴ ሄደች።” “እሱ በተናገረ ጊዜ ነፍሴ ትታኝ ሄደች” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “መሸፈኛዬን።”
“እንደ ቴምር ዘለላ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
“በምንጩ ዳርቻ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “ላንቃው።”
ወይም “ውብ ከተማ።”
ወይም “ሰሪሳራዎችሽ።” በዓይንና በጆሮ መካከል ያለውን የአካል ክፍል ያመለክታል።
ቃል በቃል “የጠራች።”
ቃል በቃል “ወደ ታች የምትመለከት።”
ወይም “በደረቁ ወንዝ።”
ወይም “አቆጥቁጦ።”
ወይም “ነፍሴ።”
ወይም “ፈቃደኛ የሆኑ።”
ወይም “የሁለት ቡድኖች ጭፈራ።”
ቃል በቃል “ራስሽ።”
ወይም “ታስሮ ተይዟል።”
ቃል በቃል “ላንቃሽም።”
ወይም “አቆጥቁጦ።”
እንግሊዝኛ፣ ማንድሬክ። ከድንች ዝርያ የሚመደብ ተክል ሲሆን ብርቱካንማ ቀለም ያለው ፍሬ ያፈራል።
ወይም “ሙሉ በሙሉ ያደሩ መሆንም።”
ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
“ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።
“ይንቁታል” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “አንድ ሺው።”
“ጓደኞችሽ” ማለትም ሊሆን ይችላል።