መዝሙር
א [አሌፍ]
3 ክፉ ነገር አያደርጉም፤
በመንገዶቹ ይሄዳሉ።+
4 አንተ መመሪያዎችህን
በጥብቅ እንድንከተል አዘኸናል።+
6 ይህ ቢሆንልኝ፣
ትእዛዛትህን ሁሉ በትኩረት ስመለከት አላፍርም።+
7 የጽድቅ ፍርዶችህን በተማርኩ ጊዜ
በቀና ልብ አወድስሃለሁ።
8 ሥርዓትህን አከብራለሁ።
አቤቱ እርግፍ አድርገህ አትተወኝ።
ב [ቤት]
9 ወጣቶች በንጽሕና መመላለስ የሚችሉት እንዴት ነው?
በቃልህ መሠረት ራሳቸውን በመጠበቅ ነው።+
10 በሙሉ ልቤ አንተን እሻለሁ።
ከትእዛዛትህ እንድርቅ አትፍቀድ።+
12 ይሖዋ ሆይ፣ ውዳሴ ይድረስህ፤
ሥርዓትህን አስተምረኝ።
13 የተናገርካቸውን ፍርዶች ሁሉ
በከንፈሮቼ አስታውቃለሁ።
16 ያወጣሃቸውን ደንቦች እወዳቸዋለሁ።
ቃልህን አልረሳም።+
ג [ጊሜል]
17 በሕይወት መኖርና ቃልህን መጠበቅ እችል ዘንድ፣
ለአገልጋይህ ደግነት አሳይ።+
18 በሕግህ ውስጥ ያሉትን አስደናቂ ነገሮች
አጥርቼ እንዳይ ዓይኖቼን ክፈት።
19 በምድሪቱ ላይ የባዕድ አገር ሰው ነኝ።+
ትእዛዛትህን ከእኔ አትሰውር።
20 እኔ* ፍርዶችህን
ዘወትር ከመናፈቄ የተነሳ ዛልኩ።
21 እብሪተኛ የሆኑትን፣
ከትእዛዛትህ የራቁትን የተረገሙ ሰዎች ትገሥጻለህ።+
22 ማሳሰቢያዎችህን ጠብቄአለሁና፣
ዘለፋንና ንቀትን ከእኔ አስወግድ።*
23 መኳንንትም እንኳ አንድ ላይ ተቀምጠው ስለ እኔ መጥፎ ነገር ሲያወሩ፣
አገልጋይህ በሥርዓትህ ላይ ያሰላስላል።*
ד [ዳሌት]
በቃልህ መሠረት በሕይወት አቆየኝ።+
26 መንገዶቼን ለአንተ ተናገርኩ፤ አንተም መለስክልኝ፤
ሥርዓትህን አስተምረኝ።+
28 ከሐዘን የተነሳ እንቅልፍ አጣሁ።*
በቃልህ መሠረት አበርታኝ።
29 የአታላይነትን መንገድ ከእኔ አርቅ፤+
ሕግህንም በማሳወቅ ሞገስ አሳየኝ።
30 የታማኝነትን ጎዳና መርጫለሁ።+
ፍርዶችህ ትክክል እንደሆኑ እገነዘባለሁ።
31 ማሳሰቢያዎችህን የሙጥኝ እላለሁ።+
ה [ሄ]
34 ሕግህን እንዳከብርና
በሙሉ ልቤ እንድጠብቅ
ማስተዋል ስጠኝ።
37 ከንቱ ነገር እንዳያዩ ዓይኖቼን መልስ፤+
በመንገድህ ላይ በሕይወት እንድቀጥል አድርገኝ።
39 በጣም የምፈራውን ውርደት ከእኔ አርቅ፤
ፍርዶችህ ጥሩ ናቸውና።+
40 መመሪያዎችህን ምን ያህል እንደናፈቅኩ ተመልከት።
በጽድቅህ ሕያው ሆኜ እንድኖር አድርገኝ።
ו [ዋው]
43 የእውነትን ቃል ከአፌ አታርቅ፤
በፍርድህ ተስፋ አድርጌአለሁና።*
44 እኔ ሕግህን ዘወትር፣
አዎ፣ ለዘላለም እጠብቃለሁ።+
46 ስለ ማሳሰቢያዎችህ በነገሥታት ፊት እናገራለሁ፤
ደግሞም አላፍርም።+
47 ትእዛዛትህ ደስ ያሰኙኛል፤
አዎ፣ እወዳቸዋለሁ።+
ז [ዛየን]
50 በመከራዬ ወቅት መጽናኛ የማገኘው በዚህ ነው፤+
የተናገርከው ቃል በሕይወት አቆይቶኛልና።
51 እብሪተኞች እጅግ ይሳለቁብኛል፤
እኔ ግን ከሕግህ ንቅንቅ አልልም።+
53 ሕግህን ከተዉ ክፉ ሰዎች የተነሳ
በቁጣ በገንኩ።+
54 በምኖርበት ቦታ* ሁሉ
ሥርዓትህ መዝሙር ሆነልኝ።
55 ይሖዋ ሆይ፣ ሕግህን እጠብቅ ዘንድ
በሌሊት ስምህን አስታውሳለሁ።+
56 ይህን ልማድ አድርጌዋለሁ፤
ምክንያቱም መመሪያዎችህን ጠብቄአለሁ።
ח [ኼት]
59 እግሮቼን ወደ ማሳሰቢያዎችህ እመልስ ዘንድ
መንገዴን መረመርኩ።+
60 ትእዛዛትህን ለመጠበቅ ፈጠንኩ፤
ፈጽሞ አልዘገየሁም።+
61 የክፉዎች ገመድ ተተበተበብኝ፤
ሆኖም ሕግህን አልረሳሁም።+
62 ስለ ጽድቅ ፍርዶችህ አንተን ለማመስገን
እኩለ ሌሊት ላይ እነሳለሁ።+
63 አንተን ለሚፈሩ ሁሉ፣
መመሪያዎችህንም ለሚጠብቁ ባልንጀራ ነኝ።+
64 ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህ ምድርን ይሞላል፤+
ሥርዓትህን አስተምረኝ።
ט [ቴት]
65 ይሖዋ ሆይ፣ በቃልህ መሠረት
ለአገልጋይህ መልካም ነገር አድርገህለታል።
66 ማስተዋልንና እውቀትን አስተምረኝ፤+
በትእዛዛትህ ታምኛለሁና።
68 አንተ ጥሩ ነህ፤+ ሥራህም ጥሩ ነው።
ሥርዓትህን አስተምረኝ።+
69 እብሪተኞች በውሸት ስሜን ያጎድፋሉ፤
እኔ ግን በሙሉ ልቤ መመሪያዎችህን እጠብቃለሁ።
71 ሥርዓትህን እማር ዘንድ
በመከራ ውስጥ ማለፌ ጥሩ ሆነልኝ።+
י [ዮድ]
73 እጆችህ ሠሩኝ፤ ደግሞም አበጁኝ።
ትእዛዛትህን እማር ዘንድ
ማስተዋል ስጠኝ።+
78 እብሪተኞች ኀፍረት ይከናነቡ፤
ያላንዳች ምክንያት* በድለውኛልና።
79 አንተን የሚፈሩ፣ ማሳሰቢያዎችህንም የሚያውቁ፣
ወደ እኔ ይመለሱ።
80 ለኀፍረት እንዳልዳረግ፣
ልቤ ነቀፋ በሌለበት መንገድ ሥርዓትህን ይከተል።+
כ [ካፍ]
83 ጭስ እንዳደረቀው አቁማዳ ሆኛለሁና፤
ሆኖም ሥርዓትህን አልረሳም።+
84 ባሪያህ በሕይወት የሚቆየው እስከ መቼ ነው?
ስደት በሚያደርሱብኝ ላይ የምትፈርደው መቼ ነው?+
85 ሕግህን የሚጥሱ
እብሪተኛ ሰዎች እኔን ለማጥመድ ጉድጓድ ይቆፍራሉ።
86 ትእዛዛትህ ሁሉ አስተማማኝ ናቸው።
ሰዎች ያለምክንያት ያሳድዱኛል፤ አቤቱ እርዳኝ!+
87 ከምድር ገጽ ሊያጠፉኝ ምንም ያህል አልቀራቸውም ነበር፤
እኔ ግን መመሪያዎችህን አልተውኩም።
88 የተናገርካቸውን ማሳሰቢያዎች እጠብቅ ዘንድ፣
ከታማኝ ፍቅርህ የተነሳ በሕይወት አቆየኝ።
ל [ላሜድ]
89 ይሖዋ ሆይ፣ ቃልህ በሰማያት፣
ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።+
90 ታማኝነትህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው።+
ምድር ለዘለቄታው እንድትኖር በጽኑ መሠረትካት።+
91 በፍርዶችህ መሠረት እስከ ዛሬ ጸንተው ኖረዋል፤*
ሁሉም አገልጋዮችህ ናቸውና።
92 ሕግህን ባልወድ ኖሮ፣
በደረሰብኝ ጉስቁልና በጠፋሁ ነበር።+
93 መመሪያዎችህን ፈጽሞ አልረሳም፤
ምክንያቱም በእነሱ አማካኝነት በሕይወት አቆይተኸኛል።+
95 ክፉዎች እኔን ለማጥፋት ያደባሉ፤
እኔ ግን ለማሳሰቢያዎችህ ትኩረት እሰጣለሁ።
96 ፍጽምና ሁሉ ገደብ እንዳለው አይቻለሁ።
ትእዛዝህ ግን ገደብ የለውም።*
מ [ሜም]
97 ሕግህን ምንኛ ወደድኩ!+
98 ትእዛዝህ ለዘላለም ስለማይለየኝ፣
ከጠላቶቼ ይበልጥ ጥበበኛ ያደርገኛል።+
100 መመሪያዎችህን ስለማከብር፣
ከሽማግሌዎች ይበልጥ በማስተዋል እመላለሳለሁ።
101 ቃልህን እጠብቅ ዘንድ፣
በየትኛውም ክፉ መንገድ ከመሄድ እቆጠባለሁ።+
102 አንተ አስተምረኸኛልና፣
ከፍርዶችህ ፈቀቅ አልልም።
103 የተናገርከው ነገር ለምላሴ እጅግ ጣፋጭ ነው፤
ለአፌም ከማር የበለጠ ይጥማል!+
104 ከመመሪያዎችህ የተነሳ በማስተዋል እመላለሳለሁ።+
ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ሁሉ እጠላለሁ።+
נ [ኑን]
105 ቃልህ ለእግሬ መብራት፣
ለመንገዴም ብርሃን ነው።+
106 የጽድቅ ፍርዶችህን ለመጠበቅ ምያለሁ፤
ደግሞም እፈጽመዋለሁ።
107 ከፍተኛ ጉስቁልና ደርሶብኛል።+
ይሖዋ ሆይ፣ በቃልህ መሠረት በሕይወት አቆየኝ።+
110 ክፉዎች ወጥመድ ዘረጉብኝ፤
እኔ ግን ከመመሪያዎችህ ዝንፍ አላልኩም።+
112 ሥርዓትህን በሕይወቴ ዘመን ሁሉ፣
እስከ መጨረሻው ለመጠበቅ ቆርጫለሁ።*
ס [ሳሜኽ]
115 እናንተ ክፉዎች፣
የአምላኬን ትእዛዛት መጠበቅ እንድችል ከእኔ ራቁ።+
118 ከሥርዓትህ የሚርቁትን ሁሉ ገሸሽ ታደርጋቸዋለህ፤+
ውሸታሞችና አታላዮች ናቸውና።
119 በምድር ላይ ያሉ ክፉዎችን ሁሉ ከላይ እንደሚሰፍ የማይረባ ቆሻሻ ታስወግዳቸዋለህ።+
ስለዚህ ማሳሰቢያዎችህን እወዳለሁ።
120 አንተን እጅግ ከመፍራቴ የተነሳ ሰውነቴ* ይንቀጠቀጣል፤
ፍርዶችህን እፈራለሁ።
ע [አይን]
121 ትክክልና ጽድቅ የሆነውን አድርጌአለሁ።
ለሚጨቁኑኝ አሳልፈህ አትስጠኝ!
122 ለአገልጋይህ ደህንነት ዋስትና ስጥ፤
እብሪተኞች እንዲጨቁኑኝ አትፍቀድ።
125 እኔ አገልጋይህ ነኝ፤
ማሳሰቢያዎችህን እንዳውቅ ማስተዋል ስጠኝ።+
126 ይሖዋ ሆይ፣ እርምጃ የምትወስድበት ጊዜ ደርሷል፤+
ሰዎች ሕግህን ጥሰዋልና።
פ [ፔ]
129 ማሳሰቢያዎችህ ድንቅ ናቸው።
ስለዚህ እጠብቃቸዋለሁ።*
134 ጨቋኝ ከሆኑ ሰዎች ታደገኝ፤*
እኔም መመሪያዎችህን እጠብቃለሁ።
136 ሰዎች ሕግህን ስለማያከብሩ
እንባ ከዓይኖቼ እንደ ውኃ ፈሰሰ።+
צ [ጻዴ]
138 የምትሰጣቸው ማሳሰቢያዎች በጽድቅ ላይ የተመሠረቱና
ሙሉ በሙሉ አስተማማኝ ናቸው።
139 ጠላቶቼ ቃልህን ስለረሱ
ቅንዓቴ ይበላኛል።+
141 እኔ በሌሎች ዘንድ የተናቅኩና የማልረባ ነኝ፤+
ሆኖም መመሪያዎችህን አልረሳሁም።
143 ጭንቀትና ችግር ቢደርስብኝም
ትእዛዛትህን ምንጊዜም እወዳለሁ።
144 ማሳሰቢያህ ለዘላለም ጽድቅ ነው።
በሕይወት መኖሬን እንድቀጥል ማስተዋል ስጠኝ።+
ק [ኮፍ]
145 በሙሉ ልቤ እጣራለሁ። ይሖዋ ሆይ፣ መልስልኝ።
ሥርዓትህን እጠብቃለሁ።
146 አንተን እጣራለሁ፤ አቤቱ አድነኝ!
ማሳሰቢያዎችህን እጠብቃለሁ።
149 ከታማኝ ፍቅርህ የተነሳ ድምፄን ስማ።+
ይሖዋ ሆይ፣ ከአንተ ፍትሕ ጋር በሚስማማ መንገድ በሕይወት አቆየኝ።
150 አሳፋሪ በሆነ ድርጊት* የተጠመዱ ሰዎች ወደ እኔ ቀርበዋል፤
ከሕግህም ርቀዋል።
152 በቀድሞው ዘመን ስለ ማሳሰቢያዎችህ ተምሬአለሁ፤
ለዘላለም ይጸኑ ዘንድ እንደመሠረትካቸው ተረድቻለሁ።+
ר [ረሽ]
153 የደረሰብኝን ጉስቁልና ተመልከት፤ ደግሞም ታደገኝ፤+
ሕግህን አልረሳሁምና።
155 ክፉዎች ሥርዓትህን ስላልፈለጉ
መዳን ከእነሱ ርቋል።+
156 ይሖዋ ሆይ፣ ምሕረትህ ታላቅ ነው።+
ከአንተ ፍትሕ ጋር በሚስማማ መንገድ በሕይወት አቆየኝ።
157 አሳዳጆቼና ጠላቶቼ ብዙ ናቸው፤+
እኔ ግን ከማሳሰቢያዎችህ ፈቀቅ አላልኩም።
158 ከዳተኛ የሆኑ ሰዎችን ተጸየፍኩ፤
ምክንያቱም አንተ የተናገርከውን አይጠብቁም።+
159 መመሪያዎችህን ምን ያህል እንደምወድ ተመልከት!
ይሖዋ ሆይ፣ ከታማኝ ፍቅርህ የተነሳ በሕይወት አቆየኝ።+
160 የቃልህ ፍሬ ነገር እውነት ነው፤+
በጽድቅ ላይ የተመሠረተው ፍርድህ ሁሉ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።
ש [ሲን] ወይም [ሺን]
162 ብዙ ምርኮ እንዳገኘ ሰው፣
እኔም አንተ በተናገርከው ነገር ሐሴት አደርጋለሁ።+
164 በጽድቅ ላይ ከተመሠረቱት ፍርዶችህ የተነሳ
በቀን ሰባት ጊዜ አወድስሃለሁ።
166 ይሖዋ ሆይ፣ የማዳን ሥራህን ተስፋ አደርጋለሁ፤
ትእዛዛትህንም እፈጽማለሁ።
168 መመሪያዎችህንና ማሳሰቢያዎችህን እጠብቃለሁ፤
የማደርገውን ነገር ሁሉ ታውቃለህና።+
ת [ታው]
169 ይሖዋ ሆይ፣ እርዳታ ለማግኘት የማሰማው ጩኸት ወደ አንተ ይድረስ።+
እንደ ቃልህ ማስተዋል ስጠኝ።+
170 ሞገስ ለማግኘት የማቀርበው ልመና ወደ አንተ ይድረስ።
ቃል በገባኸው* መሠረት አድነኝ።
171 ሥርዓትህን ስለምታስተምረኝ
ከንፈሮቼ ውዳሴን ያፍልቁ።+
172 አንደበቴ ስለተናገርከው ቃል ይዘምር፤+
ትእዛዛትህ ሁሉ ጽድቅ ናቸውና።
174 ይሖዋ ሆይ፣ ማዳንህን እናፍቃለሁ፤
ሕግህንም እወዳለሁ።+