ሕዝቅኤል
1 በ30ኛው ዓመት፣ በአራተኛው ወር፣ ከወሩም በአምስተኛው ቀን፣ በኬባር ወንዝ+ አጠገብ በግዞት በተወሰደው ሕዝብ+ መካከል ሳለሁ ሰማያት ተከፍተው አምላክ የገለጠልኝን ራእዮች ማየት ጀመርኩ። 2 ከወሩ በአምስተኛው ቀን ይኸውም ንጉሥ ዮአኪን+ በግዞት በተወሰደ በአምስተኛው ዓመት፣ 3 በከለዳውያን+ ምድር በኬባር ወንዝ አጠገብ የይሖዋ ቃል የካህኑ የቡዚ ልጅ ወደሆነው ወደ ሕዝቅኤል* መጣ። በዚያም የይሖዋ ኃይል* በእሱ ላይ ወረደ።+
4 እኔም በማየት ላይ ሳለሁ ከሰሜን ኃይለኛ አውሎ ነፋስ+ ሲመጣ ተመለከትኩ፤ በዚያም ታላቅ ደመናና በደማቅ ብርሃን የተከበበ የእሳት+ ብልጭታ* ነበር፤ ከእሳቱም መካከል የሚያብረቀርቅ ብረት*+ የሚመስል ነገር ይወጣ ነበር። 5 በመካከሉም የአራት ሕያዋን ፍጥረታት+ አምሳያ ነበር፤ የእያንዳንዳቸውም መልክ እንደ ሰው መልክ ነበር። 6 እያንዳንዳቸው አራት አራት ፊትና አራት አራት ክንፍ ነበራቸው።+ 7 እግሮቻቸው ቀጥ ያሉ ነበሩ፤ የእግራቸውም ኮቴ የጥጃ ኮቴ ይመስል ነበር፤ እግሮቻቸውም እንደተወለወለ መዳብ ያብረቀርቃሉ።+ 8 በአራቱም ጎኖቻቸው ከክንፎቻቸው ሥር የሰው እጆች ነበሯቸው፤ አራቱም ፊቶችና ክንፎች ነበሯቸው። 9 ክንፎቻቸውም እርስ በርሳቸው ይነካኩ ነበር። በሚሄዱበት ጊዜ አይዞሩም፤ እያንዳንዳቸውም ቀጥ ብለው ወደ ፊት ይሄዱ ነበር።+
10 የፊታቸው መልክ ይህን ይመስል ነበር፦ አራቱም የሰው ፊት ነበራቸው፤ በስተ ቀኝ የአንበሳ+ ፊት፣ በስተ ግራ የበሬ+ ፊት ነበራቸው፤ ደግሞም አራቱም የንስር+ ፊት ነበራቸው።+ 11 ፊታቸው ይህን ይመስላል። ክንፎቻቸው ከእነሱ በላይ ተዘርግተዋል። እያንዳንዳቸው እርስ በርሳቸው የሚነካኩ ሁለት ክንፎች ነበሯቸው፤ ሁለቱ ክንፎቻቸው ደግሞ ሰውነታቸውን ይሸፍኑ ነበር።+
12 እያንዳንዳቸው መንፈሱ ወደመራቸው አቅጣጫ ሁሉ ቀጥ ብለው ወደ ፊት ይሄዱ ነበር።+ በሚሄዱበት ጊዜ አይዞሩም። 13 የሕያዋን ፍጥረታቱ መልክ የሚነድ የከሰል ፍም ይመስላል፤ በሕያዋን ፍጥረታቱም መካከል እየነደደ ያለ ችቦ የሚመስል ነገር ወዲያና ወዲህ ይል ነበር፤ ከእሳቱም+ መካከል መብረቅ ይወጣ ነበር። 14 ሕያዋን ፍጥረታቱም ወዲያና ወዲህ ሲሄዱ እንቅስቃሴያቸው የመብረቅ ብልጭታ ይመስል ነበር።
15 እኔም ሕያዋን ፍጥረታቱን ስመለከት አራት ፊቶች ባሉት በእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር አጠገብ በምድር ላይ አንድ አንድ መንኮራኩር* አየሁ።+ 16 መንኮራኩሮቹ በአጠቃላይ ሲታዩ እንደ ክርስቲሎቤ የሚያብረቀርቅ መልክ ነበራቸው፤ አራቱም ይመሳሰላሉ። መልካቸውና አሠራራቸው ሲታይ በአንድ መንኮራኩር ውስጥ በጎን በኩል ሌላ መንኮራኩር የተሰካ ይመስላል። 17 በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ መዞር ሳያስፈልጋቸው በአራቱም ጎን በፈለጉበት አቅጣጫ መሄድ ይችላሉ። 18 የመንኮራኩሮቹም ጠርዝ እጅግ ረጅም ከመሆኑ የተነሳ የሚያስፈራ ነበር፤ የአራቱም መንኮራኩሮች ጠርዝ ዙሪያውን በዓይኖች የተሞላ ነበር።+ 19 ሕያዋን ፍጥረታቱ በተንቀሳቀሱ ቁጥር፣ መንኮራኩሮቹም ከእነሱ ጋር አብረው ይንቀሳቀሳሉ፤ ሕያዋን ፍጥረታቱ ከምድር ከፍ ከፍ ሲሉ መንኮራኩሮቹም ከፍ ከፍ ይላሉ።+ 20 መንፈሱ ወደመራቸው አቅጣጫ፣ መንፈሱ ወደሚሄድበት ቦታ ሁሉ ይሄዳሉ። መንኮራኩሮቹ ከእነሱ ጋር አብረው ከፍ ከፍ ይሉ ነበር፤ በሕያዋን ፍጥረታቱ ላይ የሚሠራው መንፈስ* በመንኮራኩሮቹም ውስጥ ነበርና። 21 ሕያዋን ፍጥረታቱ ሲንቀሳቀሱ እነሱም ይንቀሳቀሳሉ፤ ሕያዋን ፍጥረታቱ ሲቆሙ እነሱም ይቆማሉ፤ ከምድር ከፍ ከፍ ሲሉ መንኮራኩሮቹም ከእነሱ ጋር አብረው ከፍ ከፍ ይሉ ነበር፤ በሕያዋን ፍጥረታቱ ላይ የሚሠራው መንፈስ በመንኮራኩሮቹም ውስጥ ነበርና።
22 ከሕያዋን ፍጥረታቱ ራስ በላይ እጅግ አስደናቂ እንደሆነ በረዶ የሚያብረቀርቅ ጠፈር የሚመስል ነገር ነበር፤ ይህም ከራሳቸው በላይ ተዘርግቶ ነበር።+ 23 ከጠፈሩ በታች ክንፎቻቸው አንዳቸው ወደ ሌላው ቀጥ ብለው ነበር።* እያንዳንዳቸውም በዚህ ጎንና በዚያኛው ጎን ሰውነታቸውን የሚሸፍኑባቸው ሁለት ሁለት ክንፎች ነበሯቸው። 24 የክንፎቻቸውን ድምፅ ስሰማ እንደሚጎርፍ ውኃ ድምፅ፣ ደግሞም ሁሉን እንደሚችል አምላክ ድምፅ ነበር።+ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ድምፁ እንደ ሠራዊት ድምፅ ነበር። በሚቆሙበት ጊዜ ክንፎቻቸውን ወደ ታች ያደርጋሉ።
25 ከራሳቸው በላይ ካለው ጠፈር በላይ አንድ ድምፅ ይሰማ ነበር። (በሚቆሙበት ጊዜ ክንፎቻቸውን ወደ ታች ያደርጉ ነበር።) 26 ከራሳቸው በላይ ካለው ጠፈር በላይ የሰንፔር ድንጋይ+ የመሰለ እንደ ዙፋን ያለ ነገር ነበር።+ ከላይ በኩል ባለው በዙፋኑ ላይ መልኩ የሰው መልክ የሚመስል ተቀምጦ ነበር።+ 27 ወገቡ ከሚመስለው ነገር ጀምሮ ወደ ላይ፣ እሳት የሚመስል እንደ ብረት የሚያብረቀርቅ ነገር+ ሲወጣ አየሁ፤ ደግሞም ከወገቡ ጀምሮ ወደ ታች፣ እሳት የሚመስል ነገር አየሁ።+ በዙሪያውም ደማቅ ብርሃን ነበር፤ 28 ይህም ዝናባማ በሆነ ቀን በደመና ውስጥ እንደሚታይ ቀስተ ደመና ነበር።+ በዙሪያው ያለው ደማቅ ብርሃን ይህን ይመስላል። ደግሞም የይሖዋን ክብር ይመስል ነበር።+ እኔም ባየሁት ጊዜ በግንባሬ ተደፋሁ፤ ከዚያም አንዱ ሲናገር ድምፅ ሰማሁ።
2 ከዚያም “የሰው ልጅ* ሆይ፣ ተነስተህ በእግርህ ቁም፤ እኔም አናግርሃለሁ” አለኝ።+ 2 እሱም ባናገረኝ ጊዜ መንፈስ ወደ ውስጤ ገባ፤ የሚያነጋግረኝንም እሰማ ዘንድ በእግሬ አቆመኝ።+
3 ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ ወደ እስራኤል ሕዝብ፣ በእኔ ላይ ወዳመፁት ወደ ዓመፀኞቹ ብሔራት+ እልክሃለሁ።+ እነሱም ሆኑ አባቶቻቸው እስከዚህች ቀን ድረስ ሕጌን ተላልፈዋል።+ 4 ግትርና* ልበ ደንዳና+ ወደሆኑ ልጆች እልክሃለሁ፤ አንተም ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል’ በላቸው። 5 እነሱ ዓመፀኛ+ ቤት ስለሆኑ ቢሰሙም ባይሰሙም በመካከላቸው ነቢይ እንደነበረ በእርግጥ ያውቃሉ።+
6 “አንተ ግን የሰው ልጅ ሆይ፣ በአሜኬላና በእሾህ+ የተከበብክ* እንዲሁም በጊንጦች መካከል የምትኖር ቢሆንም እነሱንም ሆነ የሚናገሩትን ቃል አትፍራ።+ እነሱ ዓመፀኛ ቤት ስለሆኑ የሚናገሩትን አትፍራ፤+ ከፊታቸውም የተነሳ አትሸበር።+ 7 እነሱ ዓመፀኛ ስለሆኑ ቢሰሙም ባይሰሙም ቃሌን ንገራቸው።+
8 “አንተ ግን የሰው ልጅ ሆይ፣ የምነግርህን ስማ። እንደዚህ ዓመፀኛ ቤት፣ ዓመፀኛ አትሁን። አፍህን ክፈት፤ የምሰጥህንም ብላ።”+
9 እኔም ባየሁ ጊዜ ወደ እኔ የተዘረጋ እጅ+ ተመለከትኩ፤ ደግሞም የተጻፈበት ጥቅልል*+ አየሁ። 10 እሱም በፊቴ ጥቅልሉን ሲተረትረው፣ ከፊትና ከኋላ ተጽፎበት ነበር።+ በላዩ ላይ የሙሾ፣* የሐዘንና የዋይታ ቃላት ተጽፈውበት ነበር።+
3 ከዚያም “የሰው ልጅ ሆይ፣ በፊትህ ያለውን ብላ።* ይህን ጥቅልል ብላ፤ ሄደህም ለእስራኤል ቤት ተናገር” አለኝ።+
2 ስለዚህ አፌን ከፈትኩ፤ እሱም ጥቅልሉን እንድበላው ሰጠኝ። 3 ከዚያም “የሰው ልጅ ሆይ፣ ይህን የሰጠሁህን ጥቅልል ብላ፤ ሆድህንም ሙላ” አለኝ። እኔም ጥቅልሉን መብላት ጀመርኩ፤ በአፌም ውስጥ እንደ ማር ጣፈጠኝ።+
4 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ ወደ እስራኤል ቤት ሂድ፤ ቃሌንም ንገራቸው። 5 የተላክኸው ወደ እስራኤል ቤት እንጂ ለመረዳት የሚያዳግት ቋንቋ ወይም የማይታወቅ ልሳን ወደሚናገር ሕዝብ አይደለምና። 6 ለመረዳት የሚያዳግት ቋንቋ ወይም የማይታወቅ ልሳን ወደሚናገሩና ቃላቸው ሊገባህ ወደማይችል ብዙ ሕዝቦች አልተላክህም። ወደ እነሱ ብልክህማ ኖሮ ይሰሙህ ነበር።+ 7 የእስራኤል ቤት ግን ሊሰሙህ አይፈልጉም፤ እኔን መስማት አይፈልጉምና።+ የእስራኤል ቤት ወገኖች ሁሉ ግትርና ልበ ደንዳና ናቸው።+ 8 እነሆ፣ ፊትህን ልክ እንደ እነሱ ፊት ጠንካራ አድርጌዋለሁ፤ ግንባርህንም ልክ እንደ እነሱ ግንባር አጠንክሬዋለሁ።+ 9 ግንባርህን እንደ አልማዝ፣ ከባልጩትም ይበልጥ ጠንካራ አድርጌዋለሁ።+ አትፍራቸው፤ ከፊታቸውም የተነሳ አትሸበር፤+ እነሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና።”
10 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ የምነግርህን ቃል ሁሉ በልብህ ያዝ፤ ደግሞም አዳምጥ። 11 በምርኮ ወደተወሰዱት ወገኖችህ*+ ሄደህ ንገራቸው። ቢሰሙም ባይሰሙም ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል’ በላቸው።”+
12 ከዚያም መንፈስ ወደ ላይ አነሳኝ፤+ ከበስተ ኋላዬም ታላቅ የጉምጉምታ ድምፅ “የይሖዋ ክብር ከስፍራው ይወደስ” ሲል ሰማሁ። 13 በዚያም የሕያዋን ፍጥረታቱ ክንፎች እርስ በርስ ሲነካኩ የሚያሰሙት ድምፅ፣+ በአጠገባቸው ያሉት መንኮራኩሮች*+ የሚያሰሙት ድምፅና የታላቅ ጉምጉምታ ድምፅ ነበር። 14 መንፈስም ወደ ላይ አንስቶ ወሰደኝ፤ እኔም ተማርሬና መንፈሴ ተቆጥቶ ሄድኩ፤ የይሖዋም ብርቱ እጅ በእኔ ላይ አርፋ ነበር። 15 ስለሆነም በቴልአቢብ፣ በኬባር ወንዝ+ አቅራቢያ ይኖሩ ወደነበሩት በግዞት የተወሰዱ ሰዎች ሄድኩ፤ እነሱም በሚኖሩበት ስፍራ ተቀመጥኩ፤ በድንጋጤ ፈዝዤም+ በመካከላቸው ሰባት ቀን ቆየሁ።
16 ሰባቱ ቀናት ካለፉ በኋላ የይሖዋ ቃል ወደ እኔ መጣ፦
17 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ለእስራኤል ቤት ጠባቂ አድርጌ ሾሜሃለሁ፤+ ከአፌ የሚወጣውንም ቃል ስትሰማ ማስጠንቀቂያዬን ንገራቸው።+ 18 ክፉውን ሰው ‘በእርግጥ ትሞታለህ’ ባልኩት ጊዜ ባታስጠነቅቀው፣ ደግሞም ክፉው ሰው በሕይወት ይኖር ዘንድ ከክፉ መንገዱ እንዲመለስ ማስጠንቀቂያ ባትሰጠው፣+ እሱ ክፉ በመሆኑ በሠራው በደል ይሞታል፤+ ደሙን ግን ከአንተ እጅ እሻዋለሁ።*+ 19 ሆኖም ክፉውን ሰው አስጠንቅቀኸው ከክፋቱና ከክፉ መንገዱ ባይመለስ፣ እሱ በሠራው በደል ይሞታል፤ አንተ ግን የገዛ ሕይወትህን* በእርግጥ ታድናለህ።+ 20 ይሁንና ጻድቅ ሰው ጽድቅ ማድረጉን ቢተውና መጥፎ ነገር ቢፈጽም፣* እኔ በፊቱ መሰናክል አስቀምጣለሁ፤ እሱም ይሞታል።+ ሳታስጠነቅቀው ከቀረህ በሠራው ኃጢአት የተነሳ ይሞታል፤ ያከናወነውም የጽድቅ ሥራ አይታወስም፤ ደሙን ግን ከአንተ እጅ እሻዋለሁ።*+ 21 ሆኖም ጻድቁን ሰው ኃጢአት እንዳይሠራ ብታስጠነቅቀውና ኃጢአት ባይሠራ፣ ማስጠንቀቂያውን በመስማቱ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል፤+ አንተም የገዛ ሕይወትህን* ታድናለህ።”
22 በዚያም የይሖዋ እጅ በእኔ ላይ ሆነች፤ እሱም “ተነስተህ ወደ ሸለቋማው ሜዳ ሂድ፤ በዚያም አናግርሃለሁ” አለኝ። 23 ስለዚህ ተነስቼ ወደ ሸለቋማው ሜዳ ሄድኩ፤ እነሆም በኬባር ወንዝ+ አጠገብ ያየሁትን ክብር የሚመስል የይሖዋ ክብር በዚያ ነበር፤+ እኔም በግንባሬ ተደፋሁ። 24 ከዚያም መንፈስ ወደ ውስጤ ገብቶ በእግሬ አቆመኝ፤+ አምላክም አናገረኝ፤ እንዲህም አለኝ፦
“ወደ ቤትህ ሄደህ በርህን ዘግተህ ተቀመጥ። 25 የሰው ልጅ ሆይ፣ አንተን በገመድ ይጠፍሩሃል፤ በመካከላቸውም እንዳትመላለስ ያስሩሃል። 26 እኔም ምላስህን ከላንቃህ ጋር አጣብቃለሁ፤ ዱዳም ትሆናለህ፤ ልትወቅሳቸውም አትችልም፤ ምክንያቱም እነሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸው። 27 በማናግርህ ጊዜ ግን አፍህን እከፍታለሁ፤ አንተም ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል’ በላቸው።+ የሚሰማ ይስማ፤+ የማይሰማም አይስማ፤ ምክንያቱም እነሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸው።+
4 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ አንድ ጡብ ወስደህ በፊትህ አስቀምጥ። በላዩም ላይ የኢየሩሳሌምን ከተማ ቅረጽበት። 2 ከተማዋን ክበብ፤+ ለከበባ የሚያገለግል ግንብ ሥራባት፤+ የአፈር ቁልል ደልድልባት፤+ የጦር ሰፈሮችን ሥራባት እንዲሁም በዙሪያዋ የመደርመሻ መሣሪያዎችን ደግንባት።+ 3 የብረት ምጣድ ወስደህ በአንተና በከተማዋ መካከል እንደ ብረት ቅጥር አቁመው። ፊትህንም በእሷ ላይ አዙር፤ ከተማዋም ትከበባለች፤ አንተም ትከባታለህ። ይህ ለእስራኤል ቤት ምልክት ይሆናል።+
4 “ከዚያም በግራ ጎንህ ትተኛለህ፤ የእስራኤልንም ቤት በደል በላይህ ላይ* ታኖራለህ።+ በጎንህ በተኛህበት ቀን ቁጥር በደላቸውን ትሸከማለህ። 5 እኔም በደል በፈጸሙባቸው ዓመታት መጠን 390 ቀናት በአንተ ላይ እመድባለሁ፤+ አንተም የእስራኤልን ቤት በደል ትሸከማለህ። 6 እነዚህንም ቀናት ማጠናቀቅ ይኖርብሃል።
“ከዚያም ለሁለተኛ ጊዜ በቀኝ ጎንህ ትተኛለህ፤ የይሁዳንም ቤት በደል+ ለ40 ቀናት ትሸከማለህ። ለአንድ ዓመት አንድ ቀን፣ ለአንድ ዓመት አንድ ቀን ሰጥቼሃለሁ። 7 ክንድህን ገልጠህ ፊትህን ወደ ኢየሩሳሌም ከበባ+ ታዞራለህ፤ በእሷም ላይ ትንቢት ትናገራለህ።
8 “እነሆ፣ የከበባህን ጊዜ እስክታጠናቅቅ ድረስ ከአንዱ ጎንህ ወደ ሌላው መገላበጥ እንዳትችል በገመድ አስርሃለሁ።
9 “አንተም ስንዴ፣ ገብስ፣ ባቄላ፣ ምስር፣ ማሽላና አጃ ወስደህ በአንድ ዕቃ ውስጥ አስቀምጣቸው፤ ለራስህም ዳቦ ጋግር። በጎንህ በምትተኛባቸው 390 ቀናት ትበላዋለህ።+ 10 በየቀኑ 20 ሰቅል* እየመዘንክ ትበላለህ። በየተወሰነ ጊዜ ትበላዋለህ።
11 “ደግሞም የሂን አንድ ስድስተኛ* ለክተህ ውኃ ትጠጣለህ። በየተወሰነ ጊዜ ትጠጣዋለህ።
12 “የገብስ ሙልሙል እንደምትበላ ትበላዋለህ፤ የደረቀን የሰው ዓይነ ምድር እንደ ማገዶ ተጠቅመህ በፊታቸው ትጋግረዋለህ።” 13 ከዚያም ይሖዋ “ልክ እንደዚሁ እስራኤላውያንም እነሱን በምበትንባቸው ብሔራት መካከል የረከሰ ምግብ ይበላሉ” አለ።+
14 ከዚያም እንዲህ አልኩ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ይህስ አይሁን! እኔ* ከልጅነቴ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ሞቶ የተገኘም ሆነ አውሬ የቦጫጨቀው እንስሳ ሥጋ በልቼ የረከስኩበት ጊዜ የለም፤+ የረከሰም * ሥጋ ወደ አፌ ገብቶ አያውቅም።”+
15 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “መልካም፣ በሰው ዓይነ ምድር ፋንታ የከብት ኩበት እንድትጠቀም ፈቅጄልሃለሁ፤ የምትበላውንም ዳቦ በእሱ ትጋግራለህ።” 16 ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ በኢየሩሳሌም የምግብ አቅርቦቱ እንዲቋረጥ አደርጋለሁ፤*+ እነሱም እየተመጠነ የሚሰጣቸውን ዳቦ በሚዛን እየለኩ በከፍተኛ ጭንቀት ይበላሉ፤+ እየተመጠነ የሚሰጣቸውንም ውኃ እየለኩ በስጋት ይጠጣሉ።+ 17 ይህም የሚሆነው ምግብና ውኃ አጥተው እርስ በርስ በድንጋጤ እንዲተያዩ እንዲሁም ከበደላቸው የተነሳ እንዲመነምኑ ነው።
5 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ እንደ ፀጉር አስተካካይ ምላጭ የምትጠቀምበት ስለታም ሰይፍ ውሰድ። የራስህን ፀጉርና ጢምህን ተላጭ፤ ከዚያም ሚዛን ወስደህ ፀጉሩን መዝነውና ከፋፍለው። 2 የከበባው ጊዜ ሲፈጸም+ አንድ ሦስተኛውን በከተማዋ ውስጥ በእሳት ታቃጥለዋለህ። ከዚያም ሌላ አንድ ሦስተኛ ወስደህ በከተማዋ ዙሪያ በሰይፍ ትመታዋለህ፤+ የመጨረሻውንም አንድ ሦስተኛ ለነፋስ ትበትነዋለህ፤ እኔም እነሱን ለማሳደድ ሰይፍ እመዛለሁ።+
3 “ደግሞም ከፀጉሮቹ ላይ ጥቂት ወስደህ በልብስህ እጥፋት* ቋጥራቸው። 4 የተወሰነውን ደግሞ ወስደህ እሳት ውስጥ ጨምረው፤ ሙሉ በሙሉም በእሳት አቃጥለው። ይህ እሳት ወጥቶ በእስራኤል ቤት ሁሉ ይሰራጫል።+
5 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ይህች ኢየሩሳሌም ናት። አገሮችን በዙሪያዋ አድርጌ፣ በብሔራት መካከል አስቀምጫታለሁ። 6 እሷ ግን ከብሔራትና በዙሪያዋ ካሉ አገሮች ሁሉ የባሰ ክፋት በመሥራት በድንጋጌዎቼና ባወጣኋቸው ደንቦች ላይ ዓምፃለች።+ ሕዝቡ ድንጋጌዎቼን ወደ ጎን ገሸሽ አድርጓልና፤ ደንቦቼንም አክብሮ አልተመላለሰም።’
7 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዙሪያችሁ ካሉት ብሔራት ይበልጥ አስቸጋሪ በመሆናችሁ፣ ደንቦቼን አክብራችሁ ባለመመላለሳችሁ ወይም ድንጋጌዎቼን ባለመጠበቃችሁ፣ ይልቁንም በዙሪያችሁ ያሉትን ብሔራት ድንጋጌዎች በመከተላችሁ፣+ 8 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አንቺ ከተማ ሆይ፣ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ፤+ ደግሞም እኔ ራሴ በብሔራት ፊት በመካከልሽ ፍርዴን አስፈጽማለሁ።+ 9 በአስጸያፊ ድርጊቶችሽ ሁሉ የተነሳ ከዚህ በፊት ፈጽሞ ያላደረግኩትን፣ ከዚህም በኋላ የማልደግመውን በአንቺ ላይ አደርጋለሁ።+
10 “‘“ስለዚህ በመካከልሽ አባቶች ልጆቻቸውን ይበላሉ፤+ ልጆችም አባቶቻቸውን ይበላሉ፤ በመካከልሽ ፍርዴን አስፈጽማለሁ፤ ከአንቺ የቀሩትንም በሙሉ በየአቅጣጫው* እበትናቸዋለሁ።”’+
11 “‘ስለዚህ በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘በአስጸያፊ ጣዖቶችሽ ሁሉና ጸያፍ በሆኑ ድርጊቶችሽ ሁሉ መቅደሴን ስላረከስሽ፣+ እኔ ራሴ እተውሻለሁ፤* ዓይኔ አያዝንም ደግሞም አልራራም።+ 12 ከአንቺም አንድ ሦስተኛው በቸነፈር* ይሞታል ወይም በመካከልሽ በረሃብ ያልቃል። ሌላ አንድ ሦስተኛ ደግሞ በዙሪያሽ በሰይፍ ይወድቃል።+ የመጨረሻውን አንድ ሦስተኛ ደግሞ በየአቅጣጫው* እበትነዋለሁ፤ እነሱንም ለማሳደድ ሰይፍ እመዛለሁ።+ 13 ከዚያም ቁጣዬ ይፈጸማል፤ በእነሱም ላይ የነደደው ቁጣዬ ይበርዳል፤ እኔም እረካለሁ።+ በእነሱም ላይ ቁጣዬን ፈጽሜ ባወረድኩ ጊዜ፣ እኔ ብቻ መመለክ የምፈልገው፣+ እኔ ይሖዋ ይህን እንደተናገርኩ ያውቃሉ።
14 “‘በዙሪያሽ ባሉ ብሔራት መካከል እንዲሁም በአጠገብሽ በሚያልፉ ሁሉ ፊት ባድማና መሳለቂያ አደርግሻለሁ።+ 15 በቁጣ፣ በንዴትና በኃይለኛ ቅጣት የፍርድ እርምጃ ስወስድብሽ በዙሪያሽ ባሉ ብሔራት ዘንድ መሳለቂያና መዘባበቻ+ ደግሞም የማስጠንቀቂያ ምሳሌና ማስፈራሪያ ትሆኛለሽ። እኔ ይሖዋ ይህን ተናግሬአለሁ።
16 “‘እነሱን ለማጥፋት ገዳይ የሆኑ የረሃብ ፍላጻዎችን እሰድባቸዋለሁ። የምሰዳቸው የረሃብ ፍላጻዎች ያጠፏችኋል።+ የምግብ አቅርቦታችሁ እንዲቋረጥ በማድረግ* ረሃቡን አባብሳለሁ።+ 17 በእናንተ ላይ ረሃብንና አደገኛ የዱር አራዊትን እሰዳለሁ፤+ እነሱም የወላድ መሃን ያደርጓችኋል። ቸነፈርና ደም መፋሰስ ያጥለቀልቋችኋል፤ ሰይፍም አመጣባችኋለሁ።+ እኔ ይሖዋ ይህን ተናግሬአለሁ።’”
6 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን ወደ እስራኤል ተራሮች አዙረህ በእነሱ ላይ ትንቢት ተናገር። 3 እንዲህም በል፦ ‘የእስራኤል ተራሮች ሆይ፣ የሉዓላዊውን ጌታ የይሖዋን ቃል ስሙ፦ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ለተራሮቹ፣ ለኮረብቶቹ፣ ለጅረቶቹና ለሸለቆዎቹ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ እኔ በእናንተ ላይ ሰይፍ አመጣለሁ፤ ከፍ ያሉትን የማምለኪያ ቦታዎቻችሁንም አጠፋለሁ። 4 መሠዊያዎቻችሁ ይፈርሳሉ፤ የዕጣን ማጨሻዎቻችሁ ይሰባበራሉ፤+ የታረዱ ወገኖቻችሁንም አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻችሁ* ፊት እጥላለሁ።+ 5 የእስራኤልን ሕዝብ ሬሳ አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻቸው ፊት እጥላለሁ፤ አጥንቶቻችሁንም በመሠዊያዎቻችሁ ዙሪያ እበትናለሁ።+ 6 በምትኖሩባቸው ቦታዎች ሁሉ ያሉት ከተሞች ይወድማሉ፤+ ከፍ ያሉት የማምለኪያ ቦታዎቹም ፈራርሰው ባድማ ይሆናሉ።+ መሠዊያዎቻችሁ ፈራርሰው እንዳልነበሩ ይሆናሉ፤ አስጸያፊ የሆኑት ጣዖቶቻችሁ ይወገዳሉ፤ የዕጣን ማጨሻዎቻችሁ ተገንድሰው ይወድቃሉ፤ የሠራችኋቸው ሥራዎችም ተጠራርገው ይጠፋሉ። 7 የታረዱትም ሰዎች በመካከላችሁ ይወድቃሉ፤+ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።+
8 “‘“ይሁንና የተወሰኑ ቀሪዎች እንዲኖሩ አደርጋለሁ፤ በየአገሩ በምትበተኑበት ጊዜ፣ ከእናንተ ውስጥ አንዳንዶቻችሁ በብሔራት መካከል ስትኖሩ ከሰይፍ ታመልጣላችሁና።+ 9 የተረፉትም ሰዎች በምርኮ በተወሰዱባቸው ብሔራት መካከል ሆነው እኔን ያስታውሳሉ።+ ከእኔ በራቀው ከሃዲ* ልባቸውና+ አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቻቸውን በፍትወት ስሜት በተመለከቱት* ዓይኖቻቸው የተነሳ+ ምን ያህል ልቤ እንዳዘነ ይገነዘባሉ። በሠሯቸው መጥፎና አስነዋሪ ነገሮች ሁሉ ያፍራሉ፤ እነዚህንም ነገሮች ይጸየፋሉ።+ 10 እኔ ይሖዋ እንደሆንኩና ይህን ጥፋት እንደማመጣባቸው የዛትኩት በከንቱ እንዳልሆነ ያውቃሉ።”’+
11 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የእስራኤል ቤት ሰዎች በሠሯቸው ክፉና አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ የተነሳ በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር ስለሚወድቁ በእጅህ እያጨበጨብክ፣ በእግርህም መሬቱን እየደበደብክ አልቅስ።+ 12 በሩቅ ያለው በቸነፈር ይሞታል፤ በቅርብ ያለው በሰይፍ ይወድቃል፤ ከእነዚህ ነገሮች ያመለጠና በሕይወት የተረፈ ሁሉ በረሃብ ያልቃል፤ ቁጣዬንም ሁሉ በእነሱ ላይ አወርዳለሁ።+ 13 የታረዱት ወገኖቻቸው አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻቸው መካከል፣ በመሠዊያዎቻቸው ዙሪያ፣ ከፍ ባለ ኮረብታ ሁሉና በተራሮች አናት ሁሉ ላይ፣ ከለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች እንዲሁም በትላልቅ ዛፎች ቅርንጫፎች ሥር ይኸውም አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቻቸውን ሁሉ ቁጣ ለማብረድ፣ ደስ የሚያሰኝ ሽታ ያላቸው መባዎች*+ ባቀረቡባቸው ቦታዎች በሚወድቁበት ጊዜ+ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።+ 14 በእነሱ ላይ እጄን እዘረጋለሁ፤ ምድሪቱንም ባድማ አደርጋለሁ፤ መኖሪያ ቦታዎቻቸውም ሁሉ በዲብላ አቅራቢያ ካለው ምድረ በዳ የባሰ ባድማ ይሆናሉ። እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’”
7 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “አንተ የሰው ልጅ ሆይ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ለእስራኤል ምድር እንዲህ ይላል፦ ‘ፍጻሜ! በአራቱ የምድሪቱ ማዕዘናት ላይ ፍጻሜ መጥቷል። 3 አሁን ፍጻሜሽ ደርሷል፤ ቁጣዬንም በአንቺ ላይ አወርዳለሁ፤ እንደ መንገድሽም እፈርድብሻለሁ፤ ለፈጸምሻቸውም አስጸያፊ ድርጊቶች ሁሉ ተጠያቂ አደርግሻለሁ። 4 ዓይኔ አያዝንልሽም፤ ደግሞም አልራራልሽም፤+ የተከተልሽው መንገድ የሚያስከትለውን ውጤት አመጣብሻለሁና፤ የፈጸምሻቸው አስጸያፊ ድርጊቶች የሚያስከትሉትን መዘዝ ትቀምሻለሽ።+ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’+
5 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ ጥፋት፣ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ጥፋት እየመጣ ነው!+ 6 ፍጻሜ እየመጣ ነው፤ ፍጻሜው ይመጣል፤ በአንቺ ላይ ይነሳል።* እነሆ፣ ፍጻሜው እየመጣ ነው! 7 አንቺ በምድሪቱ የምትኖሪ፣ ተራሽ ደርሷል።* ጊዜው እየደረሰ ነው፤ ቀኑ ቀርቧል።+ በተራሮች ላይ የእልልታ ሳይሆን የሁከት ድምፅ ይሰማል።
8 “‘በቅርብ ጊዜ ውስጥ ቁጣዬን በአንቺ ላይ አወርዳለሁ፤+ ንዴቴንም ሁሉ በአንቺ ላይ እወጣለሁ፤+ እንደ መንገድሽም እፈርድብሻለሁ፤ ለፈጸምሻቸውም አስጸያፊ ድርጊቶች ሁሉ ተጠያቂ አደርግሻለሁ። 9 ዓይኔ አያዝንም፤ ደግሞም አልራራም።+ የተከተልሽው መንገድ የሚያስከትለውን ውጤት አመጣብሻለሁ፤ የፈጸምሻቸው አስጸያፊ ድርጊቶች የሚያስከትሉብሽን መዘዝ ትቀምሻለሽ። እናንተም የምመታችሁ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።+
10 “‘እነሆ ቀኑ! እነሆ ቀኑ እየመጣ ነው!+ ተራሽ ደርሷል፤* በትሩ አብቧል፤ እብሪትም አቆጥቁጧል። 11 ዓመፅ አድጎ የክፋት በትር ሆኗል።+ እነሱም ሆኑ ሀብታቸው ደግሞም ሕዝባቸውም ሆነ ታላቅነታቸው ይጠፋል። 12 ጊዜው ይደርሳል፤ ቀኑም ይመጣል። የሚገዛ አይደሰት፤ የሚሸጥም አይዘን፤ በሕዝባቸው ሁሉ ላይ ቁጣ ነዷልና።*+ 13 ሻጩ በሕይወት ቢተርፍ እንኳ ወደተሸጠው ነገር አይመለስም፤ ራእዩ በሕዝቡ ሁሉ ላይ ነውና። ማንም አይመለስም፤ ከፈጸመውም በደል የተነሳ* ማንም ሕይወቱን ማትረፍ አይችልም።
14 “‘መለከት ነፍተዋል፤+ ሁሉም ቢዘጋጁም ወደ ውጊያ የሚሄድ አንድም ሰው የለም፤ ምክንያቱም ቁጣዬ በሕዝቡ ሁሉ ላይ ነዷል።+ 15 በውጭ ሰይፍ፣+ በውስጥ ደግሞ ቸነፈርና ረሃብ አለ። በሜዳ ያለ ሁሉ በሰይፍ ይሞታል፤ በከተማዋ ውስጥ ያሉትን ደግሞ ረሃብና ቸነፈር ይፈጃቸዋል።+ 16 አምልጠው መትረፍ የቻሉት ሁሉ ወደ ተራሮች ይሄዳሉ፤ እያንዳንዳቸውም በሸለቆ ውስጥ እንዳሉ ርግቦች በበደላቸው ይቃትታሉ።+ 17 እጃቸው ሁሉ ይዝላል፤ ጉልበታቸውም ሁሉ በውኃ ይርሳል።*+ 18 ማቅ ለብሰዋል፤+ ብርክም ይዟቸዋል። ሁሉም ኀፍረት ይከናነባሉ፤ ራስም ሁሉ ይመለጣል።*+
19 “‘ብራቸውን በየጎዳናው ይጥላሉ፤ ወርቃቸውም አስጸያፊ ነገር ይሆንባቸዋል። በይሖዋ የቁጣ ቀን ብራቸውም ሆነ ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም።+ በልተው አይጠግቡም፤* ሆዳቸውንም አይሞሉም፤ በኃጢአት እንዲወድቁ እንቅፋት ሆኖባቸዋልና።* 20 በጌጦቻቸው ውበት ታበዩ፤ በእነዚህም* ጸያፍ የሆኑ ምስሎቻቸውን ይኸውም አስጸያፊ ጣዖቶቻቸውን ሠሩ።+ በዚህም ምክንያት ብሩንና ወርቁን ርኩስ ነገር አደርግባቸዋለሁ። 21 ባዕዳን የሆኑ ሰዎች እንዲዘርፉት፣ በምድር ላይ የሚኖሩ ክፉ ሰዎችም እንዲበዘብዙት አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤* እነሱም ያረክሱታል።
22 “‘ፊቴን ከእነሱ አዞራለሁ፤+ እነሱም የተሰወረውን ቦታዬን* ያረክሳሉ፤ ዘራፊዎችም ወደ እሷ ይገባሉ፤ ደግሞም ያረክሷታል።+
23 “‘ምድሪቱ ነፍስ ግድያ በሚያስከትል የተዛባ ፍርድ ስለተሞላች፣+ ከተማዋም በዓመፅ ስለተሞላች+ ሰንሰለት*+ ሥራ። 24 ከብሔራት መካከል እጅግ የከፉትን አመጣለሁ፤+ እነሱም ቤቶቻቸውን ይወርሳሉ፤+ የብርቱዎቹንም ኩራት አጠፋለሁ፤ መቅደሶቻቸውም ይረክሳሉ።+ 25 መከራ ሲመጣባቸው ሰላምን ይሻሉ፤ ሆኖም ሰላም አይኖርም።+ 26 በጥፋት ላይ ጥፋት ይመጣል፤ በወሬም ላይ ወሬ ይናፈሳል፤ ሰዎችም ከነቢይ ራእይ ይሻሉ፤+ ሆኖም ሕግ* ከካህን፣ ምክርም ከሽማግሌዎች ዘንድ ይጠፋል።+ 27 ንጉሡ ያለቅሳል፤+ አለቃውም በተስፋ መቁረጥ* ስሜት ይዋጣል፤ የምድሪቱም ሕዝብ ከመሸበሩ የተነሳ እጁ ይንቀጠቀጣል። እንደ መንገዳቸው አደርግባቸዋለሁ፤ ደግሞም እነሱ እንደፈረዱት እፈርድባቸዋለሁ። እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’”+
8 በስድስተኛውም ዓመት፣ በስድስተኛው ወር፣ ከወሩም በአምስተኛው ቀን በቤቴ ተቀምጬ ሳለሁ፣ የይሁዳም ሽማግሌዎች በፊቴ ተቀምጠው ሳሉ በዚያ የሉዓላዊው ጌታ የይሖዋ እጅ ያዘኝ። 2 እነሆም እሳት የሚመስል ነገር ተመለከትኩ፤ ወገቡ ከሚመስለው ነገር በታች እሳት ነበር፤+ ደግሞም ከወገቡ በላይ መልኩ እንደሚያብረቀርቅ ብረት* ደማቅ ነበር።+ 3 ከዚያም እጅ የሚመስል ነገር ዘርግቶ የራስ ፀጉሬን ያዘ፤ መንፈስም በምድርና በሰማይ መካከል ይዞ ወሰደኝ፤ አምላክ በገለጠልኝ ራእዮች አማካኝነት ወደ ኢየሩሳሌም ይኸውም ቅናት የሚቀሰቅሰው የቅናት ጣዖት ምልክት* ወደቆመበት+ በሰሜን ትይዩ ወደሚገኘው ወደ ውስጠኛው ግቢ በር+ አመጣኝ። 4 እነሆም፣ በሸለቋማው ሜዳ አይቼው የነበረውን የሚመስል የእስራኤል አምላክ ክብር በዚያ ነበር።+
5 ከዚያም “የሰው ልጅ ሆይ፣ እባክህ ዓይንህን አንስተህ ወደ ሰሜን ተመልከት” አለኝ። ስለዚህ ወደ ሰሜን ተመለከትኩ፤ በዚያም ከመሠዊያው በር በስተ ሰሜን በኩል መግቢያው ላይ ይህ የቅናት ምልክት* ነበር። 6 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ የእስራኤል ቤት ሰዎች በዚህ ቦታ የሚሠሯቸውን ከመቅደሴ እንድርቅ የሚያደርጉ ነገሮች+ ይኸውም የሚፈጽሟቸውን አስከፊና አስጸያፊ ነገሮች ትመለከታለህ?+ ይበልጥ አስከፊ የሆኑ አስጸያፊ ነገሮችን ገና ታያለህ።”
7 ከዚያም ወደ ቅጥር ግቢው መግቢያ አመጣኝ፤ እኔም ስመለከት በግድግዳው ላይ አንድ ቀዳዳ አየሁ። 8 እሱም “የሰው ልጅ ሆይ፣ እስቲ ግድግዳውን ንደለው” አለኝ። እኔም ግድግዳውን ነደልኩት፤ አንድ መግቢያም ተመለከትኩ። 9 እሱም “ወደ ውስጥ ግባና በዚህ ቦታ የሚሠሯቸውን ክፉና አስጸያፊ ነገሮች ተመልከት” አለኝ። 10 እኔም ገብቼ አየሁ፤ መሬት ለመሬት የሚሳቡ ፍጥረታትንና የሚያስጠሉ አራዊትን+ ሁሉ እንዲሁም አስጸያፊ የሆኑ የእስራኤል ቤት ጣዖቶችን* ሁሉ ምስል+ ተመለከትኩ፤ ምስላቸውም በግድግዳው ዙሪያ ተቀርጾ ነበር። 11 ደግሞም 70 የሚሆኑ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች በምስሎቹ ፊት ቆመው ነበር፤ የሳፋን+ ልጅ ያአዛንያህ በመካከላቸው ቆሞ ነበር። እያንዳንዳቸውም በእጃቸው ጥና የያዙ ሲሆን መልካም መዓዛ ያለው የዕጣን ጭስም እየተትጎለጎለ ይወጣ ነበር።+ 12 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች እያንዳንዳቸው ጣዖቶቻቸው ባሉባቸው* እልፍኞች ውስጥ በጨለማ ምን እንደሚያደርጉ ታያለህ? እነሱ ‘ይሖዋ አያየንም። ይሖዋ ምድሪቱን ትቷታል’ ይላሉና።”+
13 ደግሞም “እነሱ የሚሠሯቸውን ይበልጥ አስከፊ የሆኑ አስጸያፊ ነገሮች ታያለህ” አለኝ። 14 በመሆኑም በሰሜን በኩል ወዳለው ወደ ይሖዋ ቤት በር መግቢያ አመጣኝ፤ በዚያም ሴቶች ተቀምጠው ታሙዝ ለተባለው አምላክ ሲያለቅሱ አየሁ።
15 እሱም በመቀጠል “የሰው ልጅ ሆይ፣ ይህን ታያለህ? ከእነዚህ የባሰ አስከፊ የሆኑ አስጸያፊ ነገሮች ታያለህ” አለኝ።+ 16 በመሆኑም ወደ ይሖዋ ቤት ውስጠኛው ግቢ+ አመጣኝ። በዚያም በይሖዋ ቤተ መቅደስ መግቢያ ላይ በበረንዳውና በመሠዊያው መካከል 25 ያህል ወንዶች ነበሩ፤ እነሱም ጀርባቸውን ለይሖዋ ቤተ መቅደስ ሰጥተው ፊታቸውን ወደ ምሥራቅ አዙረው ነበር፤ ደግሞም በምሥራቅ አቅጣጫ ለፀሐይ ይሰግዱ ነበር።+
17 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ ይህን ታያለህ? የይሁዳ ቤት እነዚህን አስጸያፊ ነገሮች መፈጸማቸው፣ ምድሪቱን በዓመፅ መሙላታቸውና+ እኔን ማስቆጣታቸው ቀላል ነገር ነው? እነሆ፣ ቅርንጫፉን* ወደ አፍንጫዬ አቅርበዋል። 18 በመሆኑም በቁጣ እርምጃ እወስዳለሁ። ዓይኔ አያዝንም፤ ደግሞም አልራራም።+ በታላቅ ድምፅ ወደ ጆሮዬ ቢጮኹም አልሰማቸውም።”+
9 ከዚያም በጆሮዬ እየሰማሁ ድምፁን ከፍ አድርጎ “ከተማዋን የሚቀጡት፣ እያንዳንዳቸው አጥፊ መሣሪያቸውን በእጃቸው ይዘው እንዲመጡ ጥሯቸው!” አለ።
2 እኔም እያንዳንዳቸው በእጃቸው የማጥፊያ መሣሪያ የያዙ ስድስት ሰዎች በሰሜን ትይዩ ባለው በላይኛው በር+ በኩል ሲመጡ አየሁ፤ ከእነሱም ጋር በፍታ የለበሰ፣ በወገቡ ላይም የጸሐፊ የቀለም ቀንድ* የያዘ አንድ ሰው ነበር፤ እነሱም መጥተው ከመዳብ በተሠራው መሠዊያ+ አጠገብ ቆሙ።
3 ከዚያም የእስራኤል አምላክ ክብር፣+ አርፎበት ከነበረው ከኪሩቦቹ በላይ ተነስቶ ወደ ቤተ መቅደሱ በር ደጃፍ ሄደ፤+ አምላክም በፍታ የለበሰውንና በወገቡ ላይ የጸሐፊ የቀለም ቀንድ የያዘውን ሰው ጠራው። 4 ይሖዋም እንዲህ አለው፦ “በከተማዋ መካከል ይኸውም በኢየሩሳሌም መካከል እለፍ፤ በከተማዋ ውስጥ እየተፈጸሙ ባሉት አስጸያፊ ነገሮች+ ሁሉ እያዘኑና እየቃተቱ ባሉት ሰዎች+ ግንባር ላይም ምልክት አድርግ።”
5 ሌሎቹን ደግሞ እኔ እየሰማሁ እንዲህ አላቸው፦ “እሱን ተከትላችሁ በከተማዋ መካከል እለፉ፤ ሰዉንም ግደሉ። ዓይናችሁ አይዘን፤ ደግሞም አትራሩ።+ 6 ሽማግሌውን፣ ወጣቱን፣ ድንግሊቱን፣ ሕፃኑንና ሴቶቹን ፈጽማችሁ ግደሉ።+ ምልክቱ ወዳለበት ወደ ማንኛውም ሰው ግን አትቅረቡ።+ ከመቅደሴም ጀምሩ።”+ ስለዚህ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት በነበሩት ሽማግሌዎች ጀመሩ።+ 7 ከዚያም “ቤተ መቅደሱን አርክሱ፤ ግቢዎቹንም ሬሳ በሬሳ አድርጓቸው።+ ሂዱ!” አላቸው። ስለዚህ ሄደው የከተማዋን ሕዝብ ገደሉ።
8 እነሱ ሰዉን እየገደሉ ሳሉ ብቻዬን ቀረሁ፤ በግንባሬም ተደፍቼ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ወዮ! በኢየሩሳሌም ላይ ቁጣህን በማፍሰስ የእስራኤልን ቀሪዎች ሁሉ ልታጠፋ ነው?” በማለት ጮኽኩ።+
9 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የእስራኤልና የይሁዳ ቤት በደል እጅግ በጣም ታላቅ ነው።+ ምድሪቱ በደም ተጥለቅልቃለች፤+ ከተማዋም በክፋት ተሞልታለች።+ ‘ይሖዋ ምድሪቱን ትቷታል፤ ይሖዋም አያይም’ ይላሉና።+ 10 እኔ ግን ዓይኔ አያዝንም፤ ደግሞም አልራራም።+ የተከተሉት መንገድ የሚያስከትለውን መዘዝ በራሳቸው ላይ አመጣባቸዋለሁ።”
11 ከዚያም በፍታ የለበሰውና በወገቡ ላይ የጸሐፊ የቀለም ቀንድ የያዘው ሰው ተመልሶ መጥቶ “ልክ እንዳዘዝከኝ አድርጌአለሁ” አለ።
10 እኔም እያየሁ ሳለ ከኪሩቦቹ ራስ በላይ ካለው ጠፈር በላይ እንደ ሰንፔር ድንጋይ ያለ ነገር ተገለጠ፤ መልኩም ዙፋን ይመስል ነበር።+ 2 ከዚያም አምላክ በፍታ የለበሰውን ሰው+ “በኪሩቦቹ ሥር ወደሚገኙት የሚሽከረከሩ መንኮራኩሮች*+ መሃል ግባና በኪሩቦቹ መካከል ካለው ፍም+ በእጆችህ ዘግነህ በከተማዋ ላይ በትነው”+ አለው። እሱም እኔ እያየሁት ገባ።
3 ሰውየው ወደዚያ ሲገባ ኪሩቦቹ ከቤተ መቅደሱ በስተ ቀኝ ቆመው ነበር፤ ደመናውም የውስጠኛውን ግቢ ሞላው። 4 የይሖዋም ክብር+ ከኪሩቦቹ ላይ ተነስቶ ወደ ቤተ መቅደሱ በር ደጃፍ ሄደ፤ ቤተ መቅደሱም ቀስ በቀስ በደመናው ተሞላ፤+ ግቢውም በይሖዋ ክብር ብርሃን ተሞላ። 5 የኪሩቦቹም ክንፎች ድምፅ ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ሲናገር እንደሚሰማው ድምፅ እስከ ውጨኛው ግቢ ድረስ ይሰማ ነበር።+
6 ከዚያም አምላክ፣ በፍታ የለበሰውን ሰው “ከሚሽከረከሩት መንኮራኩሮች መካከልና ከኪሩቦቹ መሃል እሳት ውሰድ” ብሎ አዘዘው፤ ሰውየውም ገብቶ ከመንኮራኩሩ አጠገብ ቆመ። 7 ከዚያም አንዱ ኪሩብ፣ በኪሩቦቹ መካከል ወዳለው እሳት+ እጁን ዘረጋ። የተወሰነ እሳት ወስዶ በፍታ በለበሰው ሰው+ እጆች ላይ አደረገ፤ እሱም እሳቱን ይዞ ወጣ። 8 ኪሩቦቹ ከክንፎቻቸው ሥር የሰው እጅ የሚመስል ነገር ነበራቸው።+
9 እኔም እያየሁ ሳለ በኪሩቦቹ አጠገብ አራት መንኮራኩሮች ተመለከትኩ፤ በእያንዳንዱ ኪሩብ አጠገብ አንድ መንኮራኩር ነበር፤ መንኮራኩሮቹም እንደ ክርስቲሎቤ ድንጋይ የሚያብረቀርቅ መልክ ነበራቸው።+ 10 የአራቱም መልክ ይመሳሰል ነበር፤ በአንድ መንኮራኩር ውስጥ በጎን በኩል ሌላ መንኮራኩር የተሰካ ይመስል ነበር። 11 በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ መዞር ሳያስፈልጋቸው በአራቱም አቅጣጫ መሄድ ይችሉ ነበር፤ ምክንያቱም መዞር ሳያስፈልጋቸው ፊታቸው ወደሚያይበት* አቅጣጫ ሁሉ ይሄዱ ነበር። 12 ሰውነታቸው ሁሉ፣ ጀርባቸው፣ እጃቸው፣ ክንፋቸው እንዲሁም መንኮራኩሮቹ ይኸውም የአራቱም መንኮራኩሮች ሁለመና በዓይን የተሞላ ነበር።+ 13 አንድ ድምፅ መንኮራኩሮቹን “ተሽከርካሪ መንኮራኩሮች!” ብሎ ሲጠራቸው ሰማሁ።
14 እያንዳንዳቸው* አራት አራት ፊት ነበራቸው። የመጀመሪያው ፊት የኪሩብ ፊት፣ ሁለተኛው ፊት የሰው ፊት፣ ሦስተኛውም የአንበሳ ፊት፣ አራተኛው ደግሞ የንስር ፊት ነበር።+
15 ኪሩቦቹም ወደ ላይ ተነሱ፤ በኬባር ወንዝ+ ያየኋቸው ሕያዋን ፍጥረታት እነዚሁ ነበሩ፤* 16 ኪሩቦቹ ሲንቀሳቀሱ፣ መንኮራኩሮቹም አጠገባቸው ሆነው ይንቀሳቀሱ ነበር፤ ኪሩቦቹ ከምድር በላይ ከፍ ከፍ ለማለት ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ሲዘረጉ መንኮራኩሮቹ ከአጠገባቸው አይለዩም ወይም አይርቁም ነበር።+ 17 እነሱ ሲቆሙ፣ መንኮራኩሮቹም ይቆማሉ፤ እነሱ ከፍ ከፍ ሲሉ መንኮራኩሮቹም አብረዋቸው ከፍ ከፍ ይሉ ነበር፤ በሕያዋን ፍጥረታቱ ላይ የሚሠራው መንፈስ* በውስጣቸው ነበርና።
18 ከዚያም የይሖዋ ክብር+ ከቤተ መቅደሱ በር ደጃፍ ተነስቶ በመሄድ ከኪሩቦቹ በላይ ቆመ።+ 19 ኪሩቦቹ እኔ እያየኋቸው ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ዘርግተው ከምድር ተነሱ። እነሱ ሲሄዱ መንኮራኩሮቹም አብረዋቸው ነበሩ። በይሖዋ ቤት በስተ ምሥራቅ በሚገኘው በር መግቢያም ላይ ቆሙ፤ የእስራኤል አምላክ ክብርም በላያቸው ነበር።+
20 እነዚህ በኬባር ወንዝ አቅራቢያ ከእስራኤል አምላክ በታች ያየኋቸው ሕያዋን ፍጥረታት ናቸው፤+ በመሆኑም ኪሩቦች መሆናቸውን አወቅኩ። 21 አራቱም፣ አራት አራት ፊትና አራት አራት ክንፍ ነበራቸው፤ ከክንፎቻቸውም ሥር የሰው እጆች የሚመስሉ ነገሮች ነበሯቸው።+ 22 የፊታቸውም መልክ በኬባር ወንዝ አቅራቢያ እንዳየኋቸው ፊቶች ነበር።+ እያንዳንዳቸው ቀጥ ብለው ወደ ፊት ይሄዱ ነበር።+
11 መንፈስም ወደ ላይ አንስቶ በምሥራቅ ትይዩ ወዳለው የይሖዋ ቤት የምሥራቅ በር+ አመጣኝ። በዚያም በበሩ መግቢያ ላይ 25 ሰዎች አየሁ፤ ከእነሱም መካከል የሕዝቡ አለቆች+ የሆኑት የአዙር ልጅ ያአዛንያህና የበናያህ ልጅ ጰላጥያህ ነበሩ። 2 ከዚያም አምላክ እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ እነዚህ ሰዎች ክፋትን የሚያቅዱና በዚህች ከተማ* መጥፎ ምክር የሚመክሩ ናቸው። 3 እነሱ ‘አሁን ቤት የምንሠራበት ጊዜ አይደለም?+ ከተማዋ* ድስት ናት፤+ እኛ ደግሞ ሥጋ* ነን’ ይላሉ።
4 “ስለዚህ በእነሱ ላይ ትንቢት ተናገር። የሰው ልጅ ሆይ፣ ትንቢት ተናገር።”+
5 ከዚያም የይሖዋ መንፈስ በእኔ ላይ መጣ፤+ እንዲህም አለኝ፦ “እንዲህ በላቸው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ቤት ሆይ፣ የተናገራችሁት ነገር ትክክል ነው፤ የምታስቡትን ነገር* አውቃለሁ። 6 በዚህች ከተማ ብዙዎች እንዲሞቱ አድርጋችኋል፤ ጎዳናዎቿንም በሙታን ሞልታችኋል።”’”+ 7 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እናንተ በከተማዋ ዙሪያ የጣላችኋቸው ሬሳዎች፣ እነሱ ሥጋው ናቸው፤ ከተማዋ ደግሞ ድስቱ ናት።+ እናንተ ግን ከውስጧ ትወሰዳላችሁ።’”
8 “‘ሰይፍን ፈርታችኋል፤+ እኔም ሰይፍ አመጣባችኋለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 9 ‘ከእሷ አውጥቼ ለባዕዳን አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ የፍርድ እርምጃም እወስድባችኋለሁ።+ 10 በሰይፍ ትወድቃላችሁ።+ በእስራኤል ድንበር ላይ እፈርድባችኋለሁ፤+ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።+ 11 ከተማዋ ድስት አትሆንላችሁም፤ እናንተም በውስጧ እንዳለ ሥጋ አትሆኑም፤ በእስራኤል ድንበር ላይ እፈርድባችኋለሁ፤ 12 እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ። በሥርዓቴ አልተመላለሳችሁምና፤ ድንጋጌዎቼንም አላከበራችሁም፤+ ይልቁንም በዙሪያችሁ ያሉትን ብሔራት ድንጋጌዎች ተከተላችሁ።’”+
13 ትንቢት ተናግሬ እንደጨረስኩ የበናያህ ልጅ ጰላጥያህ ሞተ፤ እኔም በግንባሬ ተደፍቼ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ወዮ! የእስራኤልን ቀሪዎች ፈጽመህ ልታጠፋ ነው?” በማለት በታላቅ ድምፅ ጮኽኩ።+
14 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 15 “የሰው ልጅ ሆይ፣ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች፣ ወንድሞችህን ይኸውም የመቤዠት መብት ያላቸውን ወንድሞችህንና የእስራኤልን ቤት ሁሉ ‘ከይሖዋ ራቁ። ምድሪቱ የእኛ ናት፤ ለእኛ ርስት ሆና ተሰጥታለች’ ብለዋቸዋል። 16 ስለዚህ እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በሩቅ ወዳሉ ብሔራት በግዞት እንዲወሰዱና በብዙ አገሮች መካከል እንዲበተኑ ባደርግም+ በሄዱባቸው አገሮች ውስጥ ለጥቂት ጊዜ መቅደስ እሆናቸዋለሁ።”’+
17 “ስለዚህ እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ደግሞም ከሕዝቦች መካከል እሰበስባችኋለሁ፤ ከተበተናችሁባቸውም አገሮች አመጣችኋለሁ፤ የእስራኤልንም ምድር እሰጣችኋለሁ።+ 18 እነሱም ወደዚያ ይመለሳሉ፤ በላይዋም ላይ ያሉትን አስጸያፊ ነገሮች ሁሉና ጸያፍ የሆኑ ልማዶች ሁሉ ያስወግዳሉ።+ 19 እኔም አንድ ልብ እሰጣቸዋለሁ፤+ በውስጣቸውም አዲስ መንፈስ አኖራለሁ፤+ ድንጋይ የሆነውንም ልብ ከሰውነታቸው አውጥቼ+ የሥጋ ልብ* እሰጣቸዋለሁ፤+ 20 ይህም ደንቦቼን አክብረው እንዲመላለሱ እንዲሁም ድንጋጌዎቼን እንዲጠብቁና እንዲታዘዙ ነው። በዚህ ጊዜ እነሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።”’
21 “‘“ሆኖም አስጸያፊ ነገሮቻቸውንና ጸያፍ የሆኑ ልማዶቻቸውን አጥብቀው ለመከተል በልባቸው ቆርጠው የተነሱትን በተመለከተ፣ መንገዳቸው የሚያስከትለውን መዘዝ በራሳቸው ላይ አመጣባቸዋለሁ” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።’”
22 በዚህ ጊዜ ኪሩቦቹ ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ዘረጉ፤ መንኮራኩሮቹም* በአጠገባቸው ነበሩ፤+ የእስራኤል አምላክ ክብርም በላያቸው ነበር።+ 23 ከዚያም የይሖዋ ክብር+ ከከተማዋ ተነስቶ ወደ ላይ ወጣ፤ ከከተማዋ በስተ ምሥራቅ ባለው ተራራም ላይ ቆመ።+ 24 ከዚያም መንፈስ፣ በአምላክ ኃይል* አማካኝነት በተሰጠኝ ራእይ ወደ ላይ አነሳኝ፤ ደግሞም በከለዳውያን ምድር ወዳሉት ግዞተኞች አመጣኝ። ከዚያም ያየሁት ራእይ ከእኔ ተለየ። 25 እኔም ይሖዋ ያሳየኝን ነገር ሁሉ በግዞት ላሉት ሰዎች መናገር ጀመርኩ።
12 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ የምትኖረው በዓመፀኛ ሕዝብ መካከል ነው። እነሱ የሚያዩበት ዓይን አላቸው፣ ግን አያዩም፤ የሚሰሙበት ጆሮ አላቸው፣ ነገር ግን አይሰሙም፤+ እነሱ ዓመፀኛ ሕዝብ ናቸውና።+ 3 የሰው ልጅ ሆይ፣ አንተ ግን በግዞት እንደሚወሰድ ሰው ለመሄድ ጓዝህን አዘጋጅ። ከዚያም እነሱ እያዩህ በቀን ጉዞ ጀምር። እነሱ እያዩህ ከቤትህ ተነስተህ ወደ ሌላ ቦታ እንደ ግዞተኛ ሂድ። ዓመፀኛ ሕዝብ ቢሆኑም እንኳ ትርጉሙ ምን እንደሆነ ይገባቸው ይሆናል። 4 በቀን እነሱ እያዩህ በግዞት እንደሚወሰድ ሰው ለመሄድ ጓዝህን አዘጋጅተህ አውጣ፤ ከዚያም ምሽት ላይ እነሱ እያዩህ በግዞት እንደሚወሰድ ሰው ውጣ።+
5 “እነሱ እያዩ ግንቡን ነድለህ በዚያ በኩል ጓዝህን ተሸክመህ ውጣ።+ 6 እነሱ እያዩ ጓዝህን በትከሻህ ተሸክመህ በጨለማ ይዘኸው ውጣ። መሬቱን እንዳታይ ፊትህን ሸፍን፤ ለእስራኤል ቤት ምልክት አደርግሃለሁና።”+
7 እኔም ልክ እንደታዘዝኩት አደረግኩ። ቀን ላይ በግዞት እንደሚሄድ ሰው ጓዝ፣ ጓዜን ጠቅልዬ አወጣሁ፤ ከዚያም ምሽት ላይ ግንቡን በእጄ ነደልኩት። ሲጨልምም ዓይናቸው እያየ ጓዜን በትከሻዬ ተሸክሜ ወጣሁ።
8 ጠዋት ላይ የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 9 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ዓመፀኛ ሕዝብ የሆኑት የእስራኤል ቤት ሰዎች ‘ምን እያደረግክ ነው?’ ብለው አልጠየቁህም? 10 እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ቃል የተነገረው በኢየሩሳሌም ለሚኖረው አለቃና+ በከተማዋ ውስጥ ለሚኖረው የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ነው።”’
11 “እንዲህ በል፦ ‘እኔ ለእናንተ ምልክት ነኝ።+ ልክ እኔ እንዳደረግኩት በእነሱም ላይ እንዲሁ ይደረግባቸዋል። ተማርከው በግዞት ይወሰዳሉ።+ 12 በመካከላቸው ያለው አለቃ በጨለማ ጓዙን በትከሻው ተሸክሞ ይወጣል። ግንቡን ይነድልና ጓዙን ተሸክሞ በዚያ በኩል ይወጣል።+ መሬቱን እንዳያይ ፊቱን ይሸፍናል።’ 13 መረቤን በእሱ ላይ እዘረጋለሁ፤ እሱም በማጥመጃ መረቤ ይያዛል።+ ከዚያም ወደ ከለዳውያን ምድር ወደ ባቢሎን አመጣዋለሁ፤ ምድሪቱን ግን አያይም፤ በዚያም ይሞታል።+ 14 በእሱም ዙሪያ ያሉትን ሁሉ ይኸውም ረዳቶቹንና ወታደሮቹን በየአቅጣጫው እበትናቸዋለሁ፤+ እነሱንም ለማሳደድ ሰይፍ እመዛለሁ።+ 15 በብሔራት መካከል ስበትናቸውና በአገሮችም መካከል ስዘራቸው እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። 16 ይሁንና በሚሄዱባቸው ብሔራት መካከል አስጸያፊ ስለሆኑት ልማዶቻቸው ሁሉ እንዲናገሩ ከእነሱ መካከል ጥቂት ሰዎች ከሰይፍ፣ ከረሃብና ከቸነፈር እንዲተርፉ አደርጋለሁ፤ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”
17 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 18 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ምግብህን እየተንቀጠቀጥክ ብላ፤ ውኃህንም በስጋትና በጭንቀት ጠጣ።+ 19 ለምድሪቱም ሕዝብ እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ በእስራኤል ምድር ላሉት የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እንዲህ ይላል፦ “ምግባቸውን በጭንቀት ይበላሉ፤ ውኃቸውንም በፍርሃት ይጠጣሉ፤ በምድሪቱ ላይ የሚኖሩት ሰዎች ሁሉ ከሚፈጽሙት ዓመፅ የተነሳ ምድራቸው ፈጽማ ባድማ ትሆናለችና።+ 20 ሰው ይኖርባቸው የነበሩት ከተሞች ባድማ ይሆናሉ፤ ምድሪቱም ወና ትሆናለች፤+ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።”’”+
21 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 22 “የሰው ልጅ ሆይ፣ በእስራኤል ምድር ‘ዘመኑ አልፏል፤ ራእይም ሁሉ መና ቀርቷል’ የምትሉት ይህ አባባል ምንድን ነው?+ 23 ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ይህን አባባል አስቀራለሁ፤ በእስራኤልም ምድር ይህን አባባል ዳግመኛ አይጠቀሙበትም።”’ ሆኖም እንዲህ በላቸው፦ ‘ዘመኑ ቀርቧል፤+ እያንዳንዱም ራእይ ይፈጸማል።’ 24 በእስራኤል ቤት መካከል ከእንግዲህ የሐሰት ራእይ ወይም አሳሳች* ሟርት አይኖርምና።+ 25 ‘“እኔ ይሖዋ እናገራለሁና። የተናገርኩት ቃል ሁሉ ከእንግዲህ ሳይዘገይ ይፈጸማል።+ ዓመፀኛው ቤት ሆይ፣ በእናንተ ዘመን+ እኔ እናገራለሁ፤ የተናገርኩትንም እፈጽማለሁ” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።’”
26 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 27 “የሰው ልጅ ሆይ፣ የእስራኤል ሰዎች* ‘እሱ የሚያየው ራእይ የሚፈጸመው ከብዙ ጊዜ በኋላ ነው፤ ትንቢት የሚናገረውም በጣም ሩቅ ስለሆነ ጊዜ ነው’ ይላሉ።+ 28 ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “‘ከተናገርኩት ቃል ውስጥ የሚዘገይ አይኖርም፤ የተናገርኩት ቃል ሁሉ ይፈጸማል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”’”
13 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ በእስራኤል ነቢያት ላይ ትንቢት ተናገር፤+ የገዛ ራሳቸውን ትንቢት ፈጥረው የሚናገሩትንም*+ እንዲህ በላቸው፦ ‘የይሖዋን ቃል ስሙ። 3 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ምንም ያዩት ነገር ሳይኖር የገዛ መንፈሳቸውን ለሚከተሉት ሞኝ ነቢያት ወዮላቸው!+ 4 እስራኤል ሆይ፣ ነቢያትህ በፍርስራሽ መካከል እንደሚኖሩ ቀበሮዎች ሆነዋል። 5 እስራኤል፣ በይሖዋ ቀን በሚኖረው ውጊያ+ ጸንቶ ይቆም ዘንድ በድንጋይ ቅጥሩ ላይ የሚገኙትን የፈረሱ ቦታዎች ለእስራኤል ቤት መልሳችሁ ለመገንባት ወደዚያ አትሄዱም።”+ 6 “ይሖዋ ሳይልካቸው ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል’ የሚሉ ሰዎች ያዩአቸው ራእዮች ውሸት ናቸው፤ ትንቢታቸውም ሐሰት ነው፤ ይሁንና ቃላቸው እንዲፈጸም ይጠብቃሉ።+ 7 እኔ የተናገርኩት ነገር ሳይኖር ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል’ ስትሉ ያያችሁት ራእይ ውሸት፣ የተናገራችሁትም ትንቢት ሐሰት መሆኑ አይደለም?”’
8 “‘ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “‘ውሸት ስለተናገራችሁና ያያችኋቸው ራእዮች ሐሰት ስለሆኑ እኔ በእናንተ ላይ ተነስቻለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”+ 9 እጄ የውሸት ራእዮች በሚያዩና የሐሰት ትንቢት በሚናገሩ ነቢያት ላይ ተነስታለች።+ ሚስጥሬን ከማካፍላቸው ሰዎች መካከል አይሆኑም፤ በእስራኤል ቤት መዝገብም ላይ አይጻፉም፤ ወደ እስራኤልም ምድር አይመለሱም፤ እናንተም እኔ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።+ 10 ይህ ሁሉ የሚሆነው ሰላም ሳይኖር “ሰላም አለ!” እያሉ ሕዝቤን በማሳታቸው ነው።+ ሕዝቡ ጥንካሬ የሌለው ግድግዳ ሲሠራ እነሱ በኖራ ይለስኑታል።’*+
11 “በኖራ የሚለስኑትን ሰዎች ’ግድግዳው ይፈርሳል’ በላቸው። ከባድ ዶፍ ይጥላል፤ የበረዶ ድንጋይ ይወርዳል፤ ኃይለኛ አውሎ ነፋስም ግድግዳውን ያፈርሰዋል።+ 12 ግድግዳው በሚወድቅበት ጊዜም ‘የለሰናችሁት ልስን የት አለ?’ ብለው ይጠይቋችኋል።+
13 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በታላቅ ቁጣዬ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ እንዲነሳ አደርጋለሁ፤ በቁጣዬም ከባድ ዶፍ አዘንባለሁ፤ ደግሞም ጥፋት በሚያስከትል ታላቅ ንዴት የበረዶ ድንጋይ አወርዳለሁ። 14 እናንተ በኖራ የለሰናችሁትን ግድግዳ አፍርሼ ከመሬት እደባልቀዋለሁ፤ መሠረቱም ይታያል። ከተማዋ ስትወድቅ በውስጧ ትጠፋላችሁ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’
15 “‘ቁጣዬን ሁሉ በግድግዳውና ግድግዳውን በኖራ በለሰኑት ሰዎች ላይ በማወርድበት ጊዜ እንዲህ እላችኋለሁ፦ “ግድግዳው ፈርሷል፤ በኖራ የለሰኑት ሰዎችም የሉም።+ 16 ለኢየሩሳሌም ትንቢት የሚናገሩትና ሰላም ሳይኖር የሰላም ራእዮች የሚያዩላት የእስራኤል ነቢያት ጠፍተዋል”’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
17 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ የገዛ ራሳቸውን ትንቢት ፈጥረው ወደሚናገሩት የሕዝብህ ሴቶች ልጆች ፊትህን አዙር፤ በእነሱም ላይ ትንቢት ተናገር። 18 እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የሰዎችን ሕይወት* ለማደን፣ በክንድ* ሁሉ ላይ የሚታሰር ቀጭን ጨርቅ ለሚሰፉና ለሰው እንደየቁመቱ የራስ መሸፈኛ ለሚሠሩ ሴቶች ወዮላቸው! የሕዝቤን ሕይወት* እያደናችሁ የራሳችሁን ሕይወት* ለማዳን ትጥራላችሁ? 19 የእናንተን ውሸት ለሚያዳምጠው ሕዝቤ ውሸት እየተናገራችሁ+ መሞት የማይገባቸውን ሰዎች* በመግደልና መኖር የማይገባቸውን ሰዎች* በሕይወት በማቆየት፣ ለጥቂት እፍኝ ገብስና ለቁርስራሽ ዳቦ ብላችሁ+ በሕዝቤ መካከል ታረክሱኛላችሁ?”’
20 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እናንተ ሴቶች፣ እነሆ ሰዎችን* እንደ ወፎች ለማደን በምትጠቀሙበት ጨርቅ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ፤ ከክንዳችሁም ላይ እቀደዋለሁ፤ እንደ ወፎች ያደናችኋቸውንም ሰዎች ነፃ አወጣለሁ። 21 የራስ መሸፈኛችሁን እቀዳለሁ፤ ሕዝቤንም ከእጃችሁ እታደጋለሁ፤ ከእንግዲህ አድናችሁ አትይዟቸውም፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።+ 22 እኔ እንዲያዝን* ያላደረግኩትን ጻድቅ ሰው ሐሰት በመናገር+ ተስፋ እንዲቆርጥ አድርጋችኋልና፤ ደግሞም ክፉው ሰው ከክፋት መንገዱ ተመልሶ በሕይወት እንዳይኖር+ እጁን አበርትታችኋል።+ 23 ስለዚህ እናንተ ሴቶች፣ ከእንግዲህ የውሸት ራእዮች አታዩም፤ ሟርትም አታሟርቱም፤+ ሕዝቤንም ከእጃችሁ እታደጋለሁ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’”
14 ከእስራኤል ሽማግሌዎች መካከል አንዳንዶቹ ወደ እኔ መጥተው በፊቴ ተቀመጡ።+ 2 ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 3 “የሰው ልጅ ሆይ፣ እነዚህ ሰዎች አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቻቸውን* ለመከተል ቆርጠው ተነስተዋል፤ ሰዎች ኃጢአት እንዲሠሩ የሚያደርግ የማሰናከያ ድንጋይ አስቀምጠዋል። ታዲያ እኔን እንዲጠይቁኝ ልፈቅድላቸው ይገባል?+ 4 እንግዲህ ንገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አንድ እስራኤላዊ አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቹን ለመከተል ቆርጦ ተነስቶና ሰዎች ኃጢአት እንዲሠሩ የሚያደርግ የማሰናከያ ድንጋይ አስቀምጦ አንድን ነቢይ ለመጠየቅ ቢመጣ እኔ ይሖዋ፣ እንደ አስጸያፊ ጣዖቶቹ ብዛት በተገቢው መንገድ እመልስለታለሁ። 5 የእስራኤልን ቤት ሰዎች ልብ አሸብራለሁና፤* ምክንያቱም ሁሉም ከእኔ ርቀዋል፤ እንዲሁም አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቻቸውን ተከትለዋል።”’+
6 “ስለሆነም የእስራኤልን ቤት ሰዎች እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ተመለሱ፤ አስጸያፊ ከሆኑት ጣዖቶቻችሁ ራቁ፤ ቀፋፊ ከሆኑት ልማዶቻችሁ ሁሉ ፊታችሁን መልሱ።+ 7 ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በእስራኤል የሚኖር የባዕድ አገር ሰው ከእኔ በመለየት አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቹን ለመከተል ቆርጦ ተነስቶና ሰዎች ኃጢአት እንዲሠሩ የሚያደርግ የማሰናከያ ድንጋይ አስቀምጦ የእኔን ነቢይ ለመጠየቅ ቢመጣ+ እኔ ይሖዋ፣ አዎ እኔ ራሴ እመልስለታለሁ። 8 ፊቴን ወደዚህ ሰው አዞራለሁ፤ መቀጣጫና መተረቻ አደርገዋለሁ፤ ከሕዝቤም መካከል አስወግደዋለሁ፤+ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።”’
9 “‘ይሁንና ነቢዩ ቢሞኝና ምላሽ ቢሰጥ፣ ያንን ነቢይ ያሞኘሁት እኔ ይሖዋ ነኝ።+ ከዚያም እጄን በእሱ ላይ ዘርግቼ ከሕዝቤ ከእስራኤል መካከል አጠፋዋለሁ። 10 የፈጸሙት በደል የሚያስከትልባቸውን መዘዝ ይሸከማሉ፤ ነቢዩን ሊጠይቅ የመጣው ሰው በደል ነቢዩ ከፈጸመው በደል ጋር አንድ ዓይነት ይሆናል፤ 11 ይህም የሚሆነው የእስራኤል ቤት ሰዎች ከእኔ ርቀው እንዳይባዝኑና በሚፈጽሙት በደል ሁሉ ራሳቸውን ከማርከስ እንዲቆጠቡ ነው። እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
12 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 13 “የሰው ልጅ ሆይ፣ አንድ አገር ታማኝ ሳይሆን ቀርቶ በእኔ ላይ ኃጢአት ቢፈጽም እጄን በእሱ ላይ እዘረጋለሁ፤ የምግብ አቅርቦቱም እንዲቋረጥ አደርጋለሁ፤*+ ረሃብም እሰድበታለሁ+ እንዲሁም ሰውንም ሆነ እንስሳን ከዚያ አጠፋለሁ።”+ 14 “‘እነዚህ ሦስት ሰዎች ይኸውም ኖኅ፣+ ዳንኤልና+ ኢዮብ+ በዚያ ቢኖሩ እንኳ በጽድቃቸው የሚያድኑት ራሳቸውን* ብቻ ነው’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
15 “‘ወይም አደገኛ የዱር አራዊትን ወደዚያ አገር ብሰድ፣ በአገሩ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ቢፈጁና* አገሩ በዱር አራዊቱ የተነሳ ማንም ሰው የማያልፍበት ወና እንዲሆን ቢያደርጉ፣+ 16 በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘እነዚህ ሦስት ሰዎች በዚያ ቢኖሩ እንኳ ወንዶችንም ሆነ ሴቶች ልጆቻቸውን ማዳን አይችሉም፤ የሚያድኑት ራሳቸውን ብቻ ነው፤ አገሩም ባድማ ይሆናል።’”
17 “‘ወይም ደግሞ በአገሩ ላይ ሰይፍ ባመጣና+ “በአገሩ መካከል ሰይፍ ይለፍ” ብል፣ በአገሩም ላይ ያለውን ሰውም ሆነ እንስሳ ባጠፋ፣+ 18 እነዚህ ሦስት ሰዎች በዚያ ቢኖሩ እንኳ፣ በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ወንዶችንም ሆነ ሴቶች ልጆቻቸውን ማዳን አይችሉም፤ የሚያድኑት ራሳቸውን ብቻ ነው።’”
19 “‘ወይም በአገሩ ላይ ቸነፈር ብሰድና+ ሰውንም ሆነ እንስሳን ለማጥፋት ደም በማፍሰስ በአገሩ ላይ ቁጣዬን ባወርድ፣ 20 ኖኅ፣+ ዳንኤልና+ ኢዮብ+ በዚያ ቢኖሩ እንኳ፣ በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ወንዶችንም ሆነ ሴቶች ልጆቻቸውን ማዳን አይችሉም፤ በጽድቃቸው የሚያድኑት ራሳቸውን* ብቻ ነው።’”+
21 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሰውንም ሆነ እንስሳን ለማጥፋት+ በኢየሩሳሌም ላይ አራት ቅጣቶቼን*+ ይኸውም ሰይፍን፣ ረሃብን፣ አደገኛ የዱር አራዊትንና ቸነፈርን በምሰድበት ጊዜ+ ምንኛ የከፋ ይሆን! 22 ሆኖም በዚያ የሚቀሩ አንዳንድ ወንዶችና ሴቶች ልጆች በሕይወት ይተርፋሉ፤ ደግሞም ከዚያ ይወሰዳሉ።+ ወደ እናንተ ይመጣሉ፤ መንገዳቸውንና ሥራቸውንም በምታዩበት ጊዜ በኢየሩሳሌም ላይ ካመጣሁት ጥፋት፣ በእሷም ላይ ካደረስኩት ነገር ሁሉ በእርግጥ ትጽናናላችሁ።’”
23 “‘መንገዳቸውንና ሥራቸውን ስታዩ ያጽናኗችኋል፤ በእሷም ላይ ላደርገው የሚገባኝን ነገር ያደረግኩት ያለምክንያት አለመሆኑን ትገነዘባላችሁ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
15 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ የወይን ተክል እንጨት በጫካ ዛፎች መካከል ካለ ከየትኛውም ዛፍ ወይም ቅርንጫፍ ከተወሰደ እንጨት ጋር እንዴት ሊወዳደር ይችላል? 3 ከወይን ተክል የሚገኝ ግንድ ሥራ ላይ ሊውል ይችላል? ወይስ ሰዎች ግንዱን ተጠቅመው ዕቃ ለማንጠልጠል የሚያገለግል ኩላብ ይሠራሉ? 4 እነሆ፣ ማገዶ እንዲሆን እሳት ውስጥ ይጣላል፤ እሳቱ ጫፍና ጫፉን ይበላዋል፤ መሃሉንም ይለበልበዋል። ከዚህ በኋላ ሥራ ላይ ሊውል ይችላል? 5 ምንም ነገር ሳይነካውም እንኳ ለምንም ነገር ሊያገለግል አይችልም። እሳት ሲበላውና ሲለበልበውማ ጨርሶ ከጥቅም ውጭ ይሆናል!”
6 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ማገዶ እንዲሆን ለእሳት አሳልፌ እንደሰጠሁት በጫካ ዛፎች መካከል እንዳለ የወይን ተክል እንጨት ሁሉ፣ በኢየሩሳሌም ነዋሪዎችም ላይ እንዲሁ አደርጋለሁ።+ 7 ፊቴን በእነሱ ላይ አድርጌአለሁ። ከእሳቱ ቢያመልጡም እሳት ይበላቸዋል። ፊቴንም በእነሱ ላይ በማደርግበት ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’”+
8 “‘ታማኝ ሳይሆኑ በመቅረታቸውም+ ምድሪቱን ባድማ አደርጋታለሁ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
16 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ለኢየሩሳሌም አስጸያፊ ልማዶቿን አሳውቃት።+ 3 እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ለኢየሩሳሌም እንዲህ ይላል፦ “መገኛሽና ትውልድሽ በከነአናውያን ምድር ነው። አባትሽ አሞራዊ፣+ እናትሽም ሂታዊት ነበሩ።+ 4 አወላለድሽንም በተመለከተ፣ በተወለድሽበት ቀን እትብትሽ አልተቆረጠም፤ ንጹሕም እንድትሆኚ በውኃ አልታጠብሽም፤ በጨውም አልታሸሽም፤ ደግሞም በጨርቅ አልተጠቀለልሽም። 5 ለአንቺ አዝኖ ከእነዚህ ነገሮች አንዱንም እንኳ ያደረገልሽ የለም። የራራልሽም የለም። ይልቁንም በተወለድሽበት ቀን ስለተጠላሽ* አውላላ ሜዳ ላይ ተጣልሽ።
6 “‘“በአጠገብሽ ሳልፍ በደምሽ ላይ ስትንፈራገጪ አየሁሽ፤ ደግሞም በደምሽ ላይ ተኝተሽ ሳለ ‘በሕይወት ኑሪ!’ አልኩሽ። አዎ፣ በደምሽ ላይ ተኝተሽ ሳለ ‘በሕይወት ኑሪ!’ አልኩሽ። 7 በሜዳ ላይ እንደሚበቅሉ ዕፀዋት እጅግ እንድትበዢ አደረግኩ፤ አንቺም አደግሽ፤ ደግሞም ሙሉ ሰው ሆንሽ፤ እጅግ ያማረ ጌጥም አደረግሽ። ጡቶችሽ አጎጠጎጡ፤ ፀጉርሽም አደገ፤ ይሁንና በዚህ ጊዜም እርቃንሽንና ራቁትሽን ነበርሽ።”’
8 “‘በአጠገብሽ ሳልፍ አየሁሽ፤ የፍቅር ግንኙነት ለመጀመር ዕድሜሽ እንደደረሰ አስተዋልኩ። ስለዚህ ልብሴን* በአንቺ ላይ ዘርግቼ+ እርቃንሽን ሸፈንኩ፤ ደግሞም ማልኩልሽ፤ ከአንቺም ጋር ቃል ኪዳን አደረግኩ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፤ ‘አንቺም የእኔ ሆንሽ። 9 በተጨማሪም በውኃ አጠብኩሽ፤ ከደምሽም አነጻሁሽ፤ ዘይትም ቀባሁሽ።+ 10 ከዚያም የተጠለፈ ሸማ አለበስኩሽ፤ ከጥሩ ቆዳ* የተሠራ ጫማም ሰጠሁሽ፤ በጥሩ በፍታም ጠቀለልኩሽ፤ እጅግ ውድ የሆነ ልብስም አለበስኩሽ። 11 በጌጣጌጥ አንቆጠቆጥኩሽ፤ በእጆችሽ አምባር፣ በአንገትሽም ሐብል አጠለቅኩልሽ። 12 በተጨማሪም በአፍንጫሽ ቀለበት፣ በጆሮዎችሽ ጉትቻ፣ በራስሽም ላይ የሚያምር አክሊል አደረግኩልሽ። 13 ራስሽን በወርቅና በብር አስጌጥሽ፤ ልብስሽም ጥሩ በፍታ፣ እጅግ ውድ በሆነ ጨርቅ የተሠራና የተጠለፈ ሸማ ነበር። ምግብሽም የላመ ዱቄት፣ ማርና ዘይት ነበር፤ እጅግ ውብ ሆንሽ፤+ ንግሥት ለመሆንም* በቃሽ።’”
14 “‘ከውበትሽ የተነሳ ዝናሽ* በብሔራት መካከል ገነነ፤+ ውበትሽ በአንቺ ላይ ካኖርኩት ግርማዬ የተነሳ ፍጹም ሆኖ ነበርና’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
15 “‘ሆኖም አንቺ በውበትሽ መመካት ጀመርሽ፤+ ዝናሽንም ለዝሙት አዳሪነት ተጠቀምሽበት።+ ከአላፊ አግዳሚው ጋር ያለገደብ አመነዘርሽ፤+ ውበትሽንም ለማንም አሳልፈሽ ሰጠሽ። 16 የተለያዩ ቀለማት ካሏቸው ልብሶችሽ አንዳንዶቹን ወስደሽ የምታመነዝሪባቸውን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎችሽን አስጌጥሽባቸው፤+ እነዚህ ነገሮች መሆን የለባቸውም፤ ጨርሶ ሊፈጸሙም አይገባም። 17 ደግሞም በሰጠሁሽ ወርቅና ብር የተሠሩትን ያማሩ ጌጣጌጦችሽን ወስደሽ ለራስሽ የወንድ ምስሎች ሠራሽ፤ ከእነሱም ጋር አመነዘርሽ።+ 18 የተጠለፉ ሸማዎችሽንም ወስደሽ አለበስሻቸው፤* ዘይቴንና ዕጣኔንም አቀረብሽላቸው።+ 19 ደግሞም እንድትበዪው የሰጠሁሽን ከላመ ዱቄት፣ ከዘይትና ከማር የተዘጋጀ ምግብ ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ አድርገሽ አቀረብሽላቸው።+ የተፈጸመው ነገር ይኸው ነው’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
20 “‘ለእኔ የወለድሻቸውን ወንዶችና ሴቶች ልጆችሽን+ ወስደሽ መብል ይሆኑ ዘንድ ለጣዖቶቹ ሠዋሽላቸው፤+ የምትፈጽሚው ምንዝር እጅግ አልበዛም? 21 ወንዶች ልጆቼን አረድሽ፤ በእሳትም አሳልፈሽ መሥዋዕት አድርገሽ አቀረብሻቸው።+ 22 አስጸያፊ ልማዶችሽንና ምንዝርሽን ሁሉ ስትፈጽሚ እርቃንሽንና ራቁትሽን ሆነሽ በገዛ ደምሽ ላይ ስትንፈራገጪ የነበርሽበትን የልጅነትሽን ጊዜ አላስታወስሽም። 23 ይህን ሁሉ ክፋት ከፈጸምሽ በኋላ ወዮ፣ ወዮልሽ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 24 ‘ለራስሽ ጉብታ አበጀሽ፤ በየአደባባዩም ከፍ ያለ ቦታ ሠራሽ። 25 በየመንገዱ ላይ በሚገኝ የታወቀ ስፍራ ሁሉ ከፍ ያለ ቦታ ሠራሽ፤ ለአላፊ አግዳሚው ሁሉ ራስሽን በመስጠት*+ ውበትሽን ወደ አስጸያፊ ነገር ለወጥሽ፤ የምትፈጽሚውንም ምንዝር አበዛሽ።+ 26 በፍትወት ከተቃጠሉ ጎረቤቶችሽ* ይኸውም ከግብፅ ወንዶች ልጆች ጋር አመነዘርሽ፤+ ገደብ በሌለው ምንዝርሽ አስቆጣሽኝ። 27 አሁን እጄን በአንቺ ላይ እዘረጋለሁ፤ ቀለብሽንም እቀንሳለሁ፤+ በጸያፍ ተግባርሽ የተነሳ የሚሸማቀቁትና የሚጠሉሽ ሴቶች ይኸውም የፍልስጤም ሴቶች ልጆች ያሻቸውን እንዲያደርጉብሽ አሳልፌ እሰጥሻለሁ።+
28 “‘እርካታ ባለማግኘትሽ ከአሦር ወንዶች ልጆች ጋር ደግሞ አመነዘርሽ፤+ ሆኖም ከእነሱ ጋር ካመነዘርሽ በኋላም እንኳ አልረካሽም። 29 ስለዚህ ምንዝርሽን በነጋዴዎች* ምድርና በከለዳውያን ምድር አበዛሽ፤+ ያም ሆኖ እንኳ አልረካሽም። 30 ዓይን አውጣ እንደሆነች ዝሙት አዳሪ+ ይህን ሁሉ ነገር የፈጸምሽው ልብሽ ምንኛ ታማሚ* ቢሆን ነው!’* ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 31 ‘ይሁንና በየመንገዱ ላይ በሚገኝ የታወቀ ስፍራ ሁሉ ጉብታሽን ስታበጂና በየአደባባዩ ለራስሽ ከፍ ያለ ቦታ ስትሠሪ እንደ ዝሙት አዳሪ አልሆንሽም፤ ምክንያቱም ምንም ዓይነት ክፍያ አትቀበዪም። 32 አንቺ በባሏ ፋንታ እንግዳ የሆኑ ሰዎችን የምታስተናግድ አመንዝራ ሚስት ነሽ!+ 33 ሰዎች ለዝሙት አዳሪዎች ሁሉ ስጦታ ይሰጣሉ፤+ በፍትወት ለሚመኙሽ ሁሉ ስጦታ የሰጠሽው ግን አንቺ ነሽ፤+ ደግሞም ከየቦታው መጥተው ከአንቺ ጋር እንዲያመነዝሩ ጉቦ ትሰጫቸዋለሽ።+ 34 አንቺ ከሌሎች ዝሙት አዳሪ ሴቶች ፈጽሞ የተለየሽ ነሽ። አንቺ የፈጸምሽው ዓይነት ምንዝር የፈጸመ ሰው ታይቶ አይታወቅም! አንቺ ትከፍያቸዋለሽ እንጂ እነሱ አይከፍሉሽም። የአንቺ አድራጎት ተቃራኒ ነው።’
35 “በመሆኑም አንቺ ዝሙት አዳሪ፣+ የይሖዋን ቃል ስሚ። 36 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ከፍቅረኞችሽና የወንዶች ልጆችሽን ደም መሥዋዕት አድርገሽ ካቀረብሽላቸው+ አስጸያፊና ቀፋፊ ጣዖቶችሽ*+ ሁሉ ጋር ባመነዘርሽ ጊዜ ከልክ በላይ በፍትወት ስለተቃጠልሽና እርቃንሽ ስለተገለጠ፣ 37 እኔ ደስ ያሰኘሻቸውን ፍቅረኞችሽን ሁሉ፣ የወደድሻቸውንም ሆነ የጠላሻቸውን ሁሉ አንድ ላይ እሰበስባለሁ። እነሱን ከየቦታው በአንቺ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፤ እርቃንሽን ለእነሱ እገልጣለሁ፤ እነሱም ሙሉ በሙሉ እርቃንሽን ሆነሽ ያዩሻል።+
38 “‘አመንዝሮችና ደም የሚያፈሱ ሴቶች+ ሊፈረድባቸው በሚገባው ፍርድ እቀጣሻለሁ፤+ ደግሞም በቁጣና በቅናት ደምሽ ይፈስሳል።+ 39 በእጃቸው አሳልፌ እሰጥሻለሁ፤ እነሱም ጉብታዎችሽን ያፈርሳሉ፤ ከፍ ያሉ ቦታዎችሽንም ያወድማሉ፤+ ልብሶችሽንም ይገፉሻል፤+ ያማሩ ጌጣጌጦችሽንም ይወስዳሉ፤+ እርቃንሽንና ራቁትሽንም ያስቀሩሻል። 40 ብዙ ሰዎችን ያነሳሱብሻል፤+ በድንጋይም ይወግሩሻል፤+ በሰይፋቸውም ያርዱሻል።+ 41 ቤቶችሽን በእሳት ያቃጥላሉ፤+ በብዙ ሴቶችም ፊት በአንቺ ላይ ፍርዴን ይፈጽማሉ፤ ምንዝርሽንም አስተውሻለሁ፤+ ከእንግዲህም ወዲህ ዋጋ አትከፍዪም። 42 በአንቺ ላይ የነበረው ቁጣዬ ይበርዳል፤+ ንዴቴም ከአንቺ ይርቃል።+ እኔም እረጋጋለሁ፤ ከእንግዲህም አልቆጣም።’
43 “‘የልጅነት ጊዜሽን ስላላስታወስሽና+ እነዚህን ነገሮች ሁሉ በማድረግ ስላስቆጣሽኝ እኔም የተከተልሽው መንገድ የሚያስከትለውን መዘዝ በራስሽ ላይ አመጣብሻለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፤ ‘አንቺም ከእንግዲህ ወዲህ አስነዋሪ ምግባርሽንና አስጸያፊ የሆኑ ልማዶችሽን ሁሉ አትፈጽሚም።
44 “‘እነሆ፣ ምሳሌያዊ አባባል የሚጠቀም ሁሉ “ልጅቷም በእናቷ ወጣች!”+ እያለ ይተርትብሻል። 45 አንቺ የእናትሽ ልጅ ነሽ፤ እሷ ባሏንና ልጆቿን ትንቃለች። ደግሞም ባሎቻቸውንና ልጆቻቸውን የናቁት የእህቶችሽ እህት ነሽ። እናታችሁ ሂታዊት፣ አባታችሁ ደግሞ አሞራዊ ነበሩ።’”+
46 “‘ታላቅ እህትሽ ከሴቶች ልጆቿ*+ ጋር ከአንቺ በስተ ሰሜን* የምትኖረው ሰማርያ ናት፤+ ታናሽ እህትሽም ከሴቶች ልጆቿ ጋር ከአንቺ በስተ ደቡብ* የምትኖረው ሰዶም ናት።+ 47 በእነሱ መንገድ መሄድና የእነሱን አስጸያፊ ልማዶች መከተል ብቻ ሳይሆን በጥቂት ጊዜ ውስጥ በምግባርሽ ሁሉ ከእነሱ ይበልጥ ብልሹ ሆንሽ።+ 48 በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘አንቺና ሴቶች ልጆችሽ ያደረጋችሁትን እህትሽ ሰዶምና ሴቶች ልጆቿ አላደረጉትም። 49 እነሆ፣ የእህትሽ የሰዶም በደል ይህ ነበር፦ እሷና ሴቶች ልጆቿ+ ኩራተኞች ነበሩ፤+ የተትረፈረፈ ምግብ የነበራቸው+ ሲሆን ያለጭንቀት ተረጋግተው ይኖሩ ነበር፤+ ይሁንና ጎስቋላውንና ድሃውን አልደገፉም።+ 50 እነሱም ትዕቢታቸውን አላስወገዱም፤+ በፊቴም አስጸያፊ የሆኑ ልማዶችን መፈጸማቸውን ቀጠሉ፤+ በመሆኑም እነሱን ማስወገድ ተገቢ ሆኖ አገኘሁት።+
51 “‘ሰማርያም+ ብትሆን አንቺ የሠራሽውን ኃጢአት ግማሹን እንኳ አልሠራችም። አንቺ ከምትፈጽሚያቸው አስጸያፊ ልማዶች ሁሉ የተነሳ እህቶችሽ ጻድቃን መስለው እስኪታዩ ድረስ ከእነሱ ይበልጥ ብዙ አስጸያፊ ልማዶች መፈጸምሽን ቀጠልሽ።+ 52 የእህቶችሽ ምግባር ተገቢ መስሎ እንዲታይ ስላደረግሽ* አሁን ኀፍረትሽን ተከናነቢ። ከእነሱ ይበልጥ አስጸያፊ በሆነ መንገድ ከፈጸምሽው ኃጢአት የተነሳ እነሱ ከአንቺ ይልቅ ጻድቃን ሆነዋል። እንግዲህ እህቶችሽን ጻድቃን ስላስመሰልሻቸው ኀፍረት ተከናነቢ፤ ውርደትሽንም ተሸከሚ።’
53 “‘በምርኮ የተወሰዱባቸውን ይኸውም ከሰዶምና ከሴቶች ልጆቿ የተማረኩትን እንዲሁም ከሰማርያና ከሴቶች ልጆቿ የተማረኩትን እሰበስባለሁ፤ በተጨማሪም ከአንቺ የተማረኩትን ከእነሱ ጋር እሰበስባለሁ፤+ 54 ይህም የሚሆነው ውርደትሽን እንድትሸከሚ ነው፤ ደግሞም እነሱን በማጽናናት ባደረግሽው ነገር የተነሳ ውርደት ትከናነቢያለሽ። 55 የገዛ እህቶችሽ፣ ሰዶምና ሴቶች ልጆቿ ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው ይመለሳሉ፤ እንዲሁም ሰማርያና ሴቶች ልጆቿ ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው ይመለሳሉ፤ አንቺና ሴቶች ልጆችሽም ቀድሞ ወደነበራችሁበት ሁኔታ ትመለሳላችሁ።+ 56 ኩሩ በነበርሽበት ቀን እህትሽ ሰዶም በአንደበትሽ ለመጠራት እንኳ የምትበቃ አልነበረችም፤ 57 ይህም የሆነው ክፋትሽ ከመጋለጡ በፊት ነበር።+ አሁን ግን የሶርያ ሴቶች ልጆችና ጎረቤቶቿ በአንቺ ላይ ነቀፋ ይሰነዝራሉ፤ እንዲሁም የፍልስጤማውያን+ ሴቶች ልጆች፣ በዙሪያሽም ያሉ ሁሉ በንቀት ያዩሻል። 58 አስነዋሪ ምግባርሽና አስጸያፊ ልማዶችሽ የሚያስከትሉብሽን መዘዝ ትቀበያለሽ’ ይላል ይሖዋ።”
59 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘እንግዲህ ቃል ኪዳኔን በማፍረስ መሐላውን ስለናቅሽ+ እኔም እንዳደረግሽው አደርግብሻለሁ።+ 60 ይሁንና እኔ ራሴ በልጅነትሽ ጊዜ ከአንቺ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ፤ ደግሞም ከአንቺ ጋር ዘላቂ ቃል ኪዳን አደርጋለሁ።+ 61 ታላላቆችሽና ታናናሾችሽ የሆኑትን እህቶችሽን ስትቀበዪ ምግባርሽን ታስታውሻለሽ፤ ደግሞም ታፍሪያለሽ፤+ እኔም እነሱን ሴቶች ልጆች አድርጌ እሰጥሻለሁ፤ ይህን የማደርገው ግን ከአንቺ ጋር በገባሁት ቃል ኪዳን የተነሳ አይደለም።’
62 “‘እኔ ራሴም ከአንቺ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አጸናለሁ፤ አንቺም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቂያለሽ። 63 ከዚያም፣ ያን ሁሉ ነገር ብታደርጊም እንኳ ለአንቺ ባስተሰረይኩልሽ ጊዜ ሥራሽን ታስታውሻለሽ፤+ ከደረሰብሽም ውርደት የተነሳ አፍሽን ለመክፈት እጅግ ታፍሪያለሽ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
17 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ስለ እስራኤል ቤት እንቆቅልሽና ምሳሌ ተናገር።+ 3 እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ትላልቅ ክንፎችና ረጃጅም ማርገብገቢያዎች ያሉት እንዲሁም መላ አካሉ ዥጉርጉር በሆኑ ላባዎች የተሸፈነው ታላቁ ንስር+ ወደ ሊባኖስ+ መጥቶ የአርዘ ሊባኖስን ጫፍ ያዘ።+ 4 አናቱ ላይ ያለውን ቀንበጥ ቀጥፎ ወደ ነጋዴዎች* ምድር አመጣው፤ በነጋዴዎችም ከተማ ተከለው።+ 5 ከዚያም ከምድሪቱ ዘር የተወሰነውን ወስዶ+ ለም በሆነ መሬት ላይ ዘራው። እንደ ሪጋ* ዛፍ ብዙ ውኃ ባለበት ቦታ አጠገብ ተከለው። 6 በመሆኑም ዘሩ በቀለ፤ አጭርና የተንሰራፋ እንዲሁም ወደ ራሱ አቅጣጫ የበቀሉ ቅጠሎች ያሉት የወይን ተክል ሆነ፤+ ሥሮቹም ከበታቹ አደጉ። በዚህ ሁኔታ የወይን ተክል ሆነ፤ ቀንበጦችና ቅርንጫፎችም አወጣ።+
7 “‘“ደግሞም ትላልቅ ክንፎች ያሉትና የክንፎቹ ላባዎች ረጃጅም የሆኑ ሌላ ታላቅ ንስር መጣ።+ ከዚያም ይህ የወይን ተክል ሥሮቹን ከተተከለበት የአትክልት መደብ አሻግሮ በታላቅ ጉጉት ወደ እሱ ዘረጋ፤ ውኃ ያጠጣውም ዘንድ ቅርንጫፎቹን ወደ እሱ ሰደደ።+ 8 ቅርንጫፎችን እንዲያወጣና ፍሬ እንዲያፈራ እንዲሁም ያማረ የወይን ተክል እንዲሆን ብዙ ውኃ ባለበት አቅራቢያ መልካም መሬት ላይ ተተክሎ ነበር።”’+
9 “እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ያድግ ይሆን? ሰው ሥሮቹን ነቅሎ አይጥልም?+ ፍሬው እንዲበሰብስ አያደርግም? ቀንበጦቹስ እንዲጠወልጉ አያደርግም?+ የወይኑ ተክል በጣም ስለሚደርቅ ከሥሩ ለመንቀል ብርቱ ክንድም ሆነ ብዙ ሰው አያስፈልግም። 10 ተነቅሎ በሌላ ቦታ ቢተከልስ ያድግ ይሆን? የምሥራቅ ነፋስ ሲነፍስበት ሙሉ በሙሉ አይደርቅም? በበቀለበት የአትክልት መደብ ላይ ይደርቃል።”’”
11 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 12 “እባክህ፣ ለዓመፀኛው ቤት ይህን ተናገር፦ ‘የእነዚህ ነገሮች ትርጉም ምን እንደሆነ አትገነዘቡም?’ እንዲህ በል፦ ‘እነሆ፣ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ንጉሥዋንና መኳንንቷን ማረከ፤ ወደ ባቢሎንም ይዟቸው ተመለሰ።+ 13 በተጨማሪም ከንጉሣውያን ዘር አንዱን ወስዶ+ ከእሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፤ በመሐላም ቃል አስገባው።+ ከዚያም የምድሪቱን ታላላቅ ሰዎች ወሰደ፤+ 14 ይህም መንግሥቲቱ ዝቅ እንድትልና ማንሰራራት እንዳትችል እንዲሁም የእሱን ቃል ኪዳን በመጠበቅ ብቻ እንድትኖር ለማድረግ ነው።+ 15 ንጉሡ ግን በመጨረሻ ፈረሶችና+ ብዙ ሠራዊት እንዲልኩለት መልእክተኞቹን ወደ ግብፅ በመስደድ+ በእሱ ላይ ዓመፀ።+ ታዲያ ይሳካለት ይሆን? እነዚህን ነገሮች ያደረገው ከቅጣት ያመልጣል? ቃል ኪዳኑንስ አፍርሶ ማምለጥ ይችላል?’+
16 “‘“በሕያውነቴ እምላለሁ” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ “እሱን ንጉሥ* አድርጎ የሾመው ንጉሥ* በሚኖርበት ቦታ ይኸውም በባቢሎን ይሞታል፤ ይህ ሰው መሐላውን አቃሎበታል፤ ቃል ኪዳኑንም አፍርሶበታል።+ 17 ብዙ ሕይወት* ለማጥፋት የአፈር ቁልል በሚደለደልበትና ለከበባ የሚያገለግል ግንብ በሚሠራበት ጊዜ የፈርዖን ታላቅ ሠራዊትና ስፍር ቁጥር የሌላቸው ወታደሮች ሊረዱት አይችሉም።+ 18 እሱ መሐላውን አቃሏል፤ ቃል ኪዳኑንም አፍርሷል። ቃል ቢገባለትም* እንኳ እነዚህን ነገሮች ሁሉ አድርጓል፤ ስለዚህ ፈጽሞ አያመልጥም።”’
19 “‘በመሆኑም ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በሕያውነቴ እምላለሁ፤ መሐላዬን መናቁና ቃል ኪዳኔን ማፍረሱ የሚያስከትልበትን መዘዝ በራሱ ላይ አመጣበታለሁ።+ 20 መረቤን በላዩ ላይ እዘረጋለሁ፤ እሱም በማጥመጃ መረቤ ይያዛል።+ ወደ ባቢሎን አመጣዋለሁ፤ በእኔ ላይ ክህደት ስለፈጸመ በዚያ እፋረደዋለሁ።+ 21 ከወታደሮቹ መካከል የሸሹት ሁሉ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ በሕይወት የተረፉትም በየአቅጣጫው* ይበታተናሉ።+ በዚህ ጊዜም እኔ ይሖዋ ራሴ እንደተናገርኩ ታውቃላችሁ።”’+
22 “‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ከረጅሙ አርዘ ሊባኖስ ጫፍ ላይ ቀንበጥ+ ቀጥፌ እተክለዋለሁ፤ ከቀንበጦቹም ጫፍ ላይ ለጋ የሆነውን ቀጥፌ+ ረጅምና ግዙፍ በሆነ ተራራ ላይ እኔ ራሴ እተክለዋለሁ።+ 23 ረጅም በሆነ የእስራኤል ተራራ ላይ እተክለዋለሁ፤ ቅርንጫፎቹም ያድጋሉ፤ ፍሬም ያፈራል፤ ደግሞም የሚያምር አርዘ ሊባኖስ ይሆናል። በሥሩም የወፍ ዓይነቶች ሁሉ ይኖራሉ፤ በቅጠሎቹም ጥላ ሥር ያርፋሉ። 24 የዱር ዛፎች ሁሉ፣ ከፍ ያለውን ዛፍ ዝቅ ዝቅ ያደረግኩት፣ ዝቅ ያለውን ዛፍ ደግሞ ከፍ ከፍ ያደረግኩት እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ፤+ ለምለሙን ዛፍ አድርቄአለሁ፤ ደረቁም ዛፍ እንዲለመልም አድርጌአለሁ።+ እኔ ይሖዋ ራሴ ይህን ተናግሬአለሁ፤ ደግሞም አድርጌአለሁ።”’”
18 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “በእስራኤል ምድር ‘ጎምዛዛ ወይን የበሉት አባቶች ሆነው ሳለ የልጆቹ ጥርስ ጠረሰ’ የሚለውን ምሳሌያዊ አባባል የምትጠቅሱት ምን ለማለት ነው?+
3 “‘በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ከእንግዲህ በእስራኤል ይህን ምሳሌ አትጠቅሱም። 4 እነሆ፣ ነፍስ* ሁሉ የእኔ ነው። የአባት ነፍስ የእኔ እንደሆነች ሁሉ የልጅም ነፍስ የእኔ ናት። ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ እሷ ትሞታለች።*
5 “‘አንድ ሰው ጻድቅ ነው እንበል፤ ይህ ሰው ፍትሐዊና ትክክል የሆነውን ነገር ያደርጋል። 6 በተራሮች ላይ ለጣዖት የተሠዋውን+ አይበላም፤ አስጸያፊ ወደሆኑት የእስራኤል ቤት ጣዖቶች* አይመለከትም፤ የባልንጀራውን ሚስት አያባልግም+ ወይም ከሴት ጋር በወር አበባዋ ጊዜ ግንኙነት አይፈጽምም፤+ 7 ማንንም ሰው አይበድልም፤+ ይልቁንም ተበዳሪ መያዣ አድርጎ የሰጠውን ይመልሳል፤+ ማንንም ሰው አይዘርፍም፤+ ይልቁንም ለተራበ ሰው የራሱን ምግብ ይሰጣል፤+ እንዲሁም የተራቆተውን ያለብሰዋል፤+ 8 ወለድ አይጠይቅም ወይም በአራጣ አያበድርም፤+ ይልቁንም ፍትሕ የጎደለው ድርጊት ከመፈጸም ይቆጠባል፤+ በሰዎች መካከል እውነተኛ ፍትሕ ያሰፍናል፤+ 9 ያወጣኋቸውን ደንቦች ይከተላል፤ እንዲሁም በታማኝነት ይመላለስ ዘንድ ድንጋጌዎቼን ይጠብቃል። እንዲህ ያለው ሰው ጻድቅ ነው፤ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
10 “‘ይሁንና ይህ ሰው ዘራፊ+ ወይም ነፍሰ ገዳይ*+ የሆነ ወይም ከእነዚህ ነገሮች አንዱን የሚያደርግ ልጅ አለው እንበል፤ 11 (አባቱ ከእነዚህ ነገሮች መካከል አንዱንም ባያደርግ እንኳ) ልጁ በተራሮች ላይ ለጣዖት የተሠዋውን ይበላል፤ የባልንጀራውን ሚስት ያባልጋል፤ 12 የተቸገረውንና ድሃውን ይበድላል፤+ ሰዎችን ይዘርፋል፤ መያዣ አድርጎ የወሰደውን አይመልስም፤ አስጸያፊ ወደሆኑት ጣዖቶች ይመለከታል፤+ ጸያፍ የሆኑ ልማዶችን ይፈጽማል፤+ 13 በአራጣ ያበድራል፤ እንዲሁም ወለድ ይቀበላል፤+ በመሆኑም ይህ ልጅ ፈጽሞ በሕይወት አይኖርም። እነዚህን ሁሉ አስጸያፊ ነገሮች በመሥራቱ በእርግጥ ይሞታል። ደሙ በገዛ ራሱ ላይ ይሆናል።
14 “‘ይሁንና አንድ አባት የተለያዩ ኃጢአቶች ሲሠራ ልጁ ይመለከተዋል እንበል፤ ልጁ ይህን ቢመለከትም እንዲህ ያሉ ነገሮች አይሠራም። 15 በተራሮች ላይ ለጣዖት የተሠዋውን አይበላም፤ አስጸያፊ ወደሆኑት የእስራኤል ቤት ጣዖቶች አይመለከትም፤ የባልንጀራውን ሚስት አያባልግም፤ 16 ማንንም ሰው አይበድልም፤ መያዣ እንዲሆን የተሰጠውን አይወስድም፤ ከሰው ላይ ምንም ነገር አይዘርፍም፤ ለተራበ ሰው የራሱን ምግብ ይሰጣል፤ እንዲሁም የተራቆተውን ያለብሰዋል፤ 17 ድሃውን ሰው ከመጨቆን ይቆጠባል፤ በአራጣ አያበድርም ወይም ወለድ አይጠይቅም፤ ድንጋጌዎቼንም ያከብራል፤ እንዲሁም ያወጣኋቸውን ደንቦች ይከተላል። እንዲህ ያለ ሰው አባቱ በፈጸመው በደል የተነሳ አይሞትም። በእርግጥ በሕይወት ይኖራል። 18 አባቱ ግን የማጭበርበር ድርጊት በመፈጸሙ፣ ወንድሙን በመዝረፉና በሕዝቡ መካከል መጥፎ የሆነ ነገር በመሥራቱ በፈጸመው በደል የተነሳ ይሞታል።
19 “‘እናንተ ግን “ልጅ፣ አባቱ በሠራው በደል ተጠያቂ የማይሆነው ለምንድን ነው?” ትላላችሁ። ልጁ ፍትሐዊና ጽድቅ የሆነ ነገር ስላደረገ፣ ያወጣኋቸውን ደንቦች ሁሉ ስለጠበቀና በሥራ ላይ ስላዋለ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል።+ 20 ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ እሷ ትሞታለች።*+ ልጅ፣ አባቱ በሠራው በደል ተጠያቂ አይሆንም፤ አባትም ልጁ በሠራው በደል ተጠያቂ አይሆንም። የጻድቁ ሰው ጽድቅ የሚታሰብለት ለራሱ ብቻ ነው፤ የክፉውም ሰው ክፋት የሚታሰበው በራሱ ላይ ብቻ ነው።+
21 “‘ክፉ ሰው ከሠራው ኃጢአት ሁሉ ቢመለስ፣ ያወጣኋቸውን ደንቦች ቢጠብቅ እንዲሁም ፍትሐዊና ጽድቅ የሆነ ነገር ቢያደርግ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል። ፈጽሞ አይሞትም።+ 22 ከሠራው በደል ውስጥ አንዱም አይታሰብበትም።*+ በሠራው ጽድቅ የተነሳ በሕይወት ይኖራል።’+
23 “‘እኔ በክፉ ሰው ሞት ደስ እሰኛለሁ?’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘እኔ ደስ የምሰኘው ከመንገዱ ቢመለስና በሕይወት ቢኖር አይደለም?’+
24 “‘ይሁንና ጻድቅ ሰው ጽድቅ ማድረጉን ቢተውና መጥፎ* ነገር ቢፈጽም፣ ደግሞም ክፉው ሰው እንደሚያደርገው አስጸያፊ ነገሮችን ሁሉ ቢሠራ በሕይወት ይኖራል? ካከናወነው የጽድቅ ሥራ መካከል አንዱም አይታወስም።+ ታማኝነቱን በማጉደሉና ኃጢአት በመሥራቱ የተነሳ ይሞታል።+
25 “‘ይሁንና እናንተ “የይሖዋ መንገድ ፍትሐዊ አይደለም” ትላላችሁ።+ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እባካችሁ ስሙ! በእርግጥ መንገዴ ፍትሐዊ አይደለም?+ ይልቁንስ ፍትሐዊ ያልሆነው የእናንተ መንገድ አይደለም?+
26 “‘ጻድቅ ሰው ጽድቅ ማድረጉን ቢተውና መጥፎ ነገር ቢፈጽም፣ በዚህም የተነሳ ቢሞት፣ የሚሞተው በገዛ ራሱ በደል ነው።
27 “‘ክፉ ሰው ከሠራው ክፉ ድርጊት ቢመለስና ፍትሐዊና ጽድቅ የሆነ ነገር ማድረግ ቢጀምር የራሱን ሕይወት* ያድናል።+ 28 የሠራውን በደል ሁሉ ተገንዝቦ ከዚያ ቢመለስ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል። ፈጽሞ አይሞትም።
29 “‘ይሁንና የእስራኤል ቤት ሰዎች “የይሖዋ መንገድ ፍትሐዊ አይደለም” ይላሉ። የእስራኤል ቤት ሆይ፣ በእርግጥ መንገዴ ፍትሐዊ አይደለም?+ ይልቁንስ ፍትሐዊ ያልሆነው የእናንተ መንገድ አይደለም?’
30 “‘ስለዚህ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ በእያንዳንዳችሁ ላይ እንደየመንገዳችሁ እፈርዳለሁ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘ተመለሱ፤ አዎ፣ ተጠያቂ እንድትሆኑ የሚያደርግ የማሰናከያ ድንጋይ እንዳይሆንባችሁ ከሠራችሁት በደል ሁሉ ሙሉ በሙሉ ተመለሱ። 31 የፈጸማችሁትን በደል ሁሉ ከራሳችሁ ላይ አስወግዱ፤+ ደግሞም አዲስ ልብና አዲስ መንፈስ ይኑራችሁ፤*+ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ለምን ትሞታላችሁ?’+
32 “‘እኔ በማንም ሰው ሞት ደስ አልሰኝም’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ።’”+
19 “ስለ እስራኤል አለቆች ሙሾ አውጣ፤* 2 እንዲህም በል፦
‘እናትህ ምን ነበረች? በአንበሶች መካከል ያለች እንስት አንበሳ ነበረች።
በብርቱ ደቦል አንበሶች መሃል ተኛች፤ ግልገሎቿንም በዚያ አሳደገች።
3 ከግልገሎቿ መካከል አንዱን ተንከባክባ አሳደገችው፤ እሱም ብርቱ ደቦል አንበሳ ሆነ።+
አድኖ መብላት ተማረ፤
ሰዎችንም እንኳ ሳይቀር በላ።
4 ብሔራት ስለ እሱ ሰሙ፤ ጉድጓዳቸው ውስጥ ገብቶም ያዙት፤
በስናግም እየጎተቱ ወደ ግብፅ ምድር አመጡት።+
5 እሷም በትዕግሥት ስትጠባበቅ ከቆየች በኋላ የመመለስ ተስፋ እንደሌለው ተገነዘበች።
በመሆኑም ከግልገሎቿ መካከል ሌላውን ወስዳ እንደ ብርቱ ደቦል አንበሳ አድርጋ ላከችው።
6 እሱም በአንበሶች መካከል ይጎማለል ጀመር፤ ብርቱ ደቦል አንበሳም ሆነ።
አድኖ መብላት ተማረ፤ ሰዎችንም እንኳ ሳይቀር በላ።+
7 በማይደፈሩት ማማዎቻቸው መካከል አደባ፤ ከተሞቻቸውንም አወደመ፤
ከዚህም የተነሳ ግሳቱ ወና በሆነችው ምድር ላይ አስተጋባ።+
8 በዙሪያው ባሉ ግዛቶች ያሉ ብሔራት መረባቸውን በእሱ ላይ ለመዘርጋት ተነሱበት፤
እሱም ጉድጓዳቸው ውስጥ ገብቶ ተያዘ።
9 በስናግ ጎትተው በእንስሳት ጎጆ ውስጥ በመክተት ወደ ባቢሎን ንጉሥ አመጡት።
ከዚያ በኋላ ድምፁ በእስራኤል ተራሮች ላይ እንዳይሰማ በዚያ አሰሩት።
10 እናትህ በውኃዎች አጠገብ እንደተተከለ፣ በደምህ ውስጥ ያለ የወይን ተክል* ነበረች።+
ከውኃው ብዛት የተነሳ ፍሬ አፈራች፤ ብዙ ቅርንጫፎችም ነበሯት።
11 ለገዢዎች በትረ መንግሥት የሚሆኑ ጠንካራ ቅርንጫፎች* አወጣች።
አድጋ ከሌሎች ዛፎች ይበልጥ ረጅም ሆነች፤
ደግሞም ከርዝመቷና ከቅጠሎቿ ብዛት የተነሳ ጎልታ ታየች።
12 ሆኖም በቁጣ ተነቀለች፤+ ወደ ምድርም ተጣለች፤
የምሥራቅም ነፋስ ፍሬዋን አደረቀው።
ጠንካራ ቅርንጫፎቿ ተሰብረው ደረቁ፤+ እሳትም በላቸው።+
13 በዚህ ጊዜ በምድረ በዳ፣
ውኃ በሌለበት ደረቅ ምድር ተተከለች።+
“‘ይህ ሙሾ ነው፤ ሙሾ ሆኖም ያገለግላል።’”
20 በሰባተኛው ዓመት፣ በአምስተኛው ወር፣ ከወሩም በአሥረኛው ቀን ከእስራኤል ሽማግሌዎች መካከል አንዳንዶቹ ይሖዋን ለመጠየቅ መጥተው በፊቴ ተቀመጡ። 2 ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 3 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ለእስራኤል ሽማግሌዎች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የመጣችሁት እኔን ለመጠየቅ ነው? ‘በሕያውነቴ እምላለሁ፤ ለጥያቄያችሁ ምላሽ አልሰጥም’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”’
4 “የሰው ልጅ ሆይ፣ በእነሱ ላይ ለመፍረድ* ተዘጋጅተሃል? በእነሱ ላይ ለመፍረድ ተዘጋጅተሃል? አባቶቻቸው የሠሯቸውን አስጸያፊ ነገሮች አሳውቃቸው።+ 5 እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እስራኤልን በመረጥኩበት ቀን፣+ ለያዕቆብ ቤት ዘሮች ማልኩላቸው፤* በግብፅም ምድር ራሴን አሳወቅኳቸው።+ አዎ፣ ማልኩላቸው፤ ደግሞም ‘እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ’ አልኳቸው። 6 በዚያ ቀን፣ ከግብፅ ምድር አውጥቼ ለእነሱ ወደመረጥኳት* ወተትና ማር ወደምታፈሰው ምድር እንደማስገባቸው ማልኩላቸው።+ እሷም ከሌሎች አገሮች ሁሉ ይበልጥ ውብ* ነበረች። 7 ከዚያም እንዲህ አልኳቸው፦ ‘እያንዳንዳችሁ በዓይናችሁ ፊት ያሉትን ጸያፍ ነገሮች አስወግዱ፤ አስጸያፊ በሆኑት የግብፅ ጣዖቶች* ራሳችሁን አታርክሱ።+ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።’+
8 “‘“እነሱ ግን በእኔ ላይ ዓመፁ፤ እኔን ለመስማትም ፈቃደኞች አልነበሩም። በፊታቸው ያሉትን ጸያፍ ነገሮች አላስወገዱም፤ እንዲሁም አስጸያፊ የሆኑትን የግብፅ ጣዖቶች አልተዉም።+ በመሆኑም በግብፅ ምድር ንዴቴን በላያቸው ለማፍሰስና ቁጣዬን በእነሱ ላይ ሙሉ በሙሉ ለማውረድ ቃል ገባሁ። 9 ይሁንና እነሱ በሚኖሩባቸው ብሔራት ፊት ስሜ እንዳይረክስ ስል ስለ ስሜ እርምጃ ወሰድኩ።+ እነሱን* ከግብፅ ምድር ባወጣሁበት ጊዜ በእነዚህ ብሔራት ፊት ማንነቴን አሳውቄአቸዋለሁና።*+ 10 ስለሆነም ከግብፅ ምድር አውጥቼ ወደ ምድረ በዳ መራኋቸው።+
11 “‘“ከዚያም ደንቦቼን ሰጠኋቸው፤ ድንጋጌዎቼንም አሳወቅኳቸው፤+ ይህን ያደረግኩት እነሱን የሚከተል ሰው በእነሱ አማካኝነት በሕይወት እንዲኖር ነው።+ 12 ደግሞም በእኔና በእነሱ መካከል ምልክት እንዲሆን+ ሰንበቶቼን ሰጠኋቸው፤+ ይህን ያደረግኩት የምቀድሳቸው እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ እንዲያውቁ ነው።
13 “‘“ሆኖም የእስራኤል ቤት ሰዎች በምድረ በዳ በእኔ ላይ ዓመፁ።+ ደንቦቼን አክብረው አልተመላለሱም፤ ሰው ቢከተላቸው በሕይወት እንዲኖር የሚያደርጉትን ድንጋጌዎቼን አቃለዋል። ሰንበቶቼንም ፈጽሞ አረከሱ። በመሆኑም ጨርሶ አጠፋቸው ዘንድ በምድረ በዳ በእነሱ ላይ ታላቅ ቁጣዬን ለማፍሰስ ቃል ገባሁ።+ 14 እነሱን* ሳወጣቸው ባዩት ብሔራት ፊት ስሜ እንዳይረክስ ስል ስለ ስሜ እርምጃ ወሰድኩ።+ 15 ደግሞም ለእነሱ ወደሰጠኋት ወተትና ማር ወደምታፈሰው፣+ ከሌሎች አገሮች ሁሉ ይበልጥ ውብ* ወደሆነችው ምድር እንደማላስገባቸው በምድረ በዳ ማልኩ፤+ 16 ምክንያቱም እነሱ ድንጋጌዎቼን አቃለዋል፤ ደንቦቼንም አክብረው አልተመላለሱም፤ ሰንበቶቼንም አርክሰዋል፤ ልባቸው አስጸያፊ የሆኑትን ጣዖቶቻቸውን ተከትሏልና።+
17 “‘“እኔ* ግን እንዳላጠፋቸው ራራሁላቸው፤ ደግሞም አላጠፋኋቸውም፤ በምድረ በዳም ፈጽሜ አልፈጀኋቸውም። 18 በምድረ በዳ ልጆቻቸውን እንዲህ አልኳቸው፦+ ‘የአባቶቻችሁን ሥርዓት አትከተሉ፤+ ድንጋጌዎቻቸውንም አታክብሩ፤ ወይም አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻቸው ራሳችሁን አታርክሱ። 19 እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። ደንቦቼን አክብራችሁ ተመላለሱ፤ ድንጋጌዎቼንም ጠብቁ፤ በሥራም አውሏቸው።+ 20 ደግሞም ሰንበቶቼን ቀድሱ፤+ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቁ ዘንድ በእኔና በእናንተ መካከል ምልክት ሆነው ያገለግላሉ።’+
21 “‘“ሆኖም ልጆቹ በእኔ ላይ ያምፁ ጀመር።+ ደንቦቼን አክብረው አልተመላለሱም፤ ሰው ቢከተላቸው በሕይወት እንዲኖር የሚያደርጉትን ድንጋጌዎቼን አላከበሩም፤ ደግሞም በሥራ ላይ አላዋሉም። ሰንበቶቼን አረከሱ። በመሆኑም በምድረ በዳ ንዴቴን በላያቸው ለማፍሰስና ቁጣዬን በእነሱ ላይ ሙሉ በሙሉ ለማውረድ ቃል ገባሁ።+ 22 ይሁንና እነሱን* ሳወጣቸው ባዩት ብሔራት ፊት ስሜ እንዳይረክስ ስል እጄን መለስኩ፤+ ስለ ስሜም ስል እርምጃ ወሰድኩ።+ 23 ደግሞም በብሔራት መካከል እንደምበታትናቸውና ወደተለያዩ አገሮች እንደምሰዳቸው በምድረ በዳ ማልኩ፤+ 24 ምክንያቱም እነሱ ድንጋጌዎቼን አላከበሩም፤ ደንቦቼንም አቃለዋል፤+ ሰንበቶቼን አርክሰዋል፤ ደግሞም እነሱ* አስጸያፊ የሆኑትን የአባቶቻቸውን ጣዖቶች ተከትለዋል።+ 25 እኔም ጥሩ ባልሆነ ሥርዓት እንዲመላለሱና ሕይወት የማያስገኙላቸውን ድንጋጌዎች እንዲከተሉ ተውኳቸው።+ 26 አስከፊ ሁኔታ ይደርስባቸው ዘንድ እያንዳንዱን የበኩር ልጅ ለእሳት አሳልፈው ሲሰጡ+ በገዛ መሥዋዕታቸው እንዲረክሱ አደረግኩ፤ ይህም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቁ ዘንድ ነው።”’
27 “ስለዚህ የሰው ልጅ ሆይ፣ ለእስራኤል ቤት ሰዎች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በዚህም መንገድ አባቶቻችሁ ለእኔ ያላቸውን ታማኝነት በማጉደል ሰደቡኝ። 28 ለእነሱ ለመስጠት ወደማልኩላቸው ምድር አመጣኋቸው።+ ከፍ ያለ ኮረብታና የለመለመ ዛፍ ሁሉ ባዩ ጊዜ+ በዚያ መሥዋዕታቸውንና ቁጣ የሚያነሳሳ መባቸውን ያቀርቡ ጀመር። በዚያም ደስ የሚያሰኘውን* የመሥዋዕቶቻቸውን መዓዛ አቀረቡ፤ የመጠጥ መባቸውንም አፈሰሱ። 29 እኔም እንዲህ አልኳቸው፦ ‘እናንተ የምትሄዱበት ይህ ከፍ ያለ የማምለኪያ ቦታ ምንድን ነው? (ይህ ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ ባማ * ተብሎ ይጠራል።)’”’+
30 “እንግዲህ ለእስራኤል ቤት ሰዎች እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አባቶቻችሁ አስጸያፊ ከሆኑ ጣዖቶቻቸው ጋር መንፈሳዊ ምንዝር ለመፈጸም ሲሉ እነሱን በመከተል ራሳቸውን እንዳረከሱ ሁሉ እናንተም ራሳችሁን ታረክሳላችሁ?+ 31 አስጸያፊ ለሆኑት ጣዖቶቻችሁ ሁሉ መሥዋዕት በማቅረብ ይኸውም ልጆቻችሁን ለእሳት አሳልፋችሁ በመስጠት እስከ ዛሬ ድረስ ራሳችሁን እያረከሳችሁ ነው?+ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ታዲያ እንዲህ እያደረጋችሁ ለጥያቄያችሁ ምላሽ መስጠት ይኖርብኛል?”’+
“‘በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ለጥያቄያችሁ ምላሽ አልሰጥም።+ 32 “እንጨትና ድንጋይ እንደሚያመልኩት* ብሔራት፣ እንደ ሌሎቹም አገሮች ሕዝቦች እንሁን”+ በማለት የምታውጠነጥኑት ሐሳብ* ፈጽሞ አይሳካም።’”
33 “‘በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘በኃያል እጅና በተዘረጋች ክንድ እንዲሁም ታላቅ ቁጣ በማፍሰስ በእናንተ ላይ ንጉሥ ሆኜ እገዛለሁ።+ 34 በኃያል እጅና በተዘረጋች ክንድ እንዲሁም ታላቅ ቁጣ በማፍሰስ ከሕዝቦች መካከል አወጣችኋለሁ፤ ከተበተናችሁባቸውም አገሮች እሰበስባችኋለሁ።+ 35 ወደ ሕዝቦች ምድረ በዳ አመጣችኋለሁ፤ በዚያም ፊት ለፊት እፋረዳችኋለሁ።+
36 “‘አባቶቻችሁን በግብፅ ምድረ በዳ እንደተፋረድኳቸው ሁሉ እናንተንም እፋረዳችኋለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 37 ‘ከእረኛ በትር በታች አሳልፋችኋለሁ፤+ ደግሞም በቃል ኪዳኑ ግዴታ ውስጥ* እንድትገቡ አደርጋለሁ። 38 ሆኖም በእኔ ላይ የሚያምፁትንና በደል የሚፈጽሙትን ከመካከላችሁ አስወግዳለሁ።+ የባዕድ አገር ሰው ሆነው ከሚኖሩበት ምድር አወጣቸዋለሁና፤ ወደ እስራኤል ምድር ግን አይገቡም፤+ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’
39 “የእስራኤል ቤት ሰዎች ሆይ፣ እናንተን በተመለከተ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እያንዳንዳችሁ ሄዳችሁ አስጸያፊ የሆኑትን ጣዖቶቻችሁን አገልግሉ።+ ከዚያ በኋላ ግን እኔን ባለመስማታችሁ መዘዙን ትቀበላላችሁ፤ በመሥዋዕቶቻችሁና አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻችሁ ከእንግዲህ ወዲህ ቅዱስ ስሜን አታረክሱም።’+
40 “‘በቅዱሱ ተራራዬ፣ ከፍ ባለውም የእስራኤል ተራራ ላይ፣’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘መላው የእስራኤል ቤት ሰዎች፣ አዎ ሁሉም በዚያ በምድሪቱ ላይ ያገለግሉኛልና።+ በዚያም በእነሱ ደስ እሰኛለሁ፤ ደግሞም ቅዱስ ከሆኑት ነገሮቻችሁ ሁሉ መዋጮዎቻችሁንና የመባችሁን የፍሬ በኩራት እሻለሁ።+ 41 ከሕዝቦች መካከል በማወጣችሁና ከተበተናችሁባቸው አገሮች በምሰበስባችሁ ጊዜ+ ደስ በሚያሰኘው* መዓዛ የተነሳ በእናንተ እረካለሁ፤ በብሔራትም ፊት በእናንተ መካከል እቀደሳለሁ።’+
42 “‘ለአባቶቻችሁ ለመስጠት ወደማልኩላቸው አገር፣ ወደ እስራኤል ምድር ሳመጣችሁ+ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።+ 43 በዚያም ራሳችሁን ያረከሳችሁባቸውን ምግባራችሁንና ድርጊቶቻችሁን ሁሉ ታስታውሳላችሁ፤+ በሠራችኋቸውም መጥፎ ነገሮች ሁሉ የተነሳ ራሳችሁን* ትጸየፋላችሁ።+ 44 የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እንደ ክፉ ምግባራችሁ ወይም እንደ ብልሹ ተግባራችሁ ሳይሆን፣ ስለ ስሜ ስል እርምጃ በምወስድበት ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
45 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 46 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን በስተ ደቡብ አቅጣጫ አዙረህ ወደ ደቡብ ተናገር፤ በደቡብም ምድር ባለው ደን ላይ ትንቢት ተናገር። 47 በደቡብ ለሚገኘው ደን እንዲህ በል፦ ‘የይሖዋን ቃል ስማ። ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በአንተ ላይ እሳት አነዳለሁ፤+ እሳቱም በአንተ ውስጥ ያለውን የለመለመውንና ደረቁን ዛፍ ሁሉ ይበላል። የሚንቦገቦገው ነበልባል አይጠፋም፤+ እሱም ከደቡብ እስከ ሰሜን ያለውን ፊት* ሁሉ ይለበልባል። 48 ሥጋ ለባሽም* ሁሉ እሳቱን ያነደድኩት እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያያል፤ በመሆኑም እሳቱ አይጠፋም።”’”+
49 እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ወዮ! እነሱ ስለ እኔ ‘ሁልጊዜ የሚናገረው እንቆቅልሽ* ነው’ ይላሉ።”
21 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን ወደ ኢየሩሳሌም አዙረህ ቅዱስ በሆኑት ስፍራዎች ላይ አውጅ፤ በእስራኤልም ምድር ላይ ትንቢት ተናገር። 3 ለእስራኤል ምድር እንዲህ በል፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ፤ ሰይፌንም ከሰገባው መዝዤ+ ጻድቁንም ሆነ ክፉውን ከአንቺ አስወግዳለሁ። 4 ጻድቁንም ሆነ ክፉውን ከአንቺ ስለማስወግድ ሰይፌ ከደቡብ እስከ ሰሜን ድረስ በሥጋ ለባሽ* ሁሉ ላይ ከሰገባው ይመዘዛል። 5 ሰዎች ሁሉ ሰይፌን ከሰገባው የመዘዝኩት እኔ ይሖዋ ራሴ እንደሆንኩ ያውቃሉ። ዳግመኛ ወደ ሰገባው አይመለስም።”’+
6 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ እየተንቀጠቀጥክ* አቃስት፤ አዎ፣ በፊታቸው በምሬት አቃስት።+ 7 ‘የምታቃስተው ለምንድን ነው?’ ቢሉህ ‘ከሰማሁት ወሬ የተነሳ ነው’ ትላለህ። በእርግጥ ይመጣልና፤ ልብም ሁሉ በፍርሃት ይቀልጣል፤ እጅ ሁሉ ይዝላል፤ መንፈስ ሁሉ ያዝናል፤ ጉልበትም ሁሉ በውኃ ይርሳል።*+ ‘እነሆ፣ በእርግጥ ይመጣል! ደግሞም ይፈጸማል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
8 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 9 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “‘ሰይፍ! ሰይፍ+ ተስሏል፤ ደግሞም ተወልውሏል። 10 የተሳለው ታላቅ እልቂት ለማስከተል ነው፤ የተወለወለውም እንደ መብረቅ እንዲያበራ ነው’ በል።”’”
“ታዲያ ደስ ሊለን አይገባም?”
“‘ማንኛውንም ዛፍ እንደሚንቅ* ሁሉ የገዛ ልጄን በትረ መንግሥት+ ይንቃል?
11 “‘እንዲወለወልና በእጅ እንዲያዝ ተሰጥቷል። ገዳዩ በእጁ እንዲይዘው ይህ ሰይፍ ተስሏል፤ ደግሞም ተወልውሏል።+
12 “‘የሰው ልጅ ሆይ፣ ሰይፍ በሕዝቤ ላይ ስለመጣ ጩኽ፤ ደግሞም ዋይ ዋይ በል፤+ በእስራኤል አለቆች ሁሉ ላይ ተነስቷል።+ እነዚህ ሰዎች ከሕዝቤ ጋር በአንድ ላይ የሰይፍ ሰለባ ይሆናሉ። ስለዚህ ጭንህን በሐዘን ምታ። 13 ሰይፉ ተፈትሿልና፤+ ደግሞስ በትረ መንግሥቱን ከናቀው ምን ይሆናል? ከሕልውና ውጭ ይሆናል’*+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
14 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ ትንቢት ተናገር፤ በእጅህም አጨብጭብ፤ ደግሞም ‘ሰይፍ!’ የሚለውን ቃል ሦስት ጊዜ ደጋግመህ ተናገር። ሰለባዎቹን የሚገድልና ታላቅ እልቂት የሚያስከትል፣ እነሱን የሚከብ ሰይፍ ነው።+ 15 ልባቸው በፍርሃት ይቀልጣል፤+ ብዙዎችም በከተሞቻቸው በር ላይ ይወድቃሉ፤ እኔም በሰይፉ እገድላለሁ። አዎ፣ ሰይፉ እንደ መብረቅ ያበራል፤ ለመግደልም ተወልውሏል! 16 በስተ ቀኝ በኩል በኃይል ቁረጥ! በስተ ግራ በኩል ተንቀሳቀስ! ስለትህ በዞረበት አቅጣጫ ሁሉ ሂድ! 17 እኔም በእጄ አጨበጭባለሁ፤ ቁጣዬንም አበርዳለሁ።+ እኔ ይሖዋ ራሴ ይህን ተናግሬአለሁ።”
18 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 19 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ የባቢሎን ንጉሥ ሰይፍ የሚመጣባቸውን ሁለት መንገዶች ንድፍ አውጣ። ሁለቱም መንገዶች የሚነሱት ከአንድ ምድር ነው፤ መንገዱ ወደ ሁለቱ ከተሞች የሚገነጠልበት ቦታ ላይ ምልክት አድርግ። 20 ሰይፍ በአሞናውያን ከተማ በራባ+ ላይ ይመጣ ዘንድ አንደኛውን መንገድ አመልክት፤ እንዲሁም በይሁዳ በምትገኘው በተመሸገችው ኢየሩሳሌም+ ላይ ይመጣ ዘንድ ሌላኛውን መንገድ አመልክት። 21 የባቢሎን ንጉሥ ያሟርት ዘንድ በመንታ መንገድ ይኸውም በሁለቱ መንገዶች መገንጠያ ላይ ይቆማልና። ፍላጾችን ይወዘውዛል። ጣዖቶቹን* ያማክራል፤ ጉበት ይመረምራል። 22 በቀኝ እጁ የወጣው ሟርት የመደርመሻ መሣሪያዎችን ለመደገን፣ የግድያ ትእዛዝ ለማስተላለፍ፣ የጦርነት ሁካታ ለማሰማት፣ በበሮቿ ላይ የመደርመሻ መሣሪያዎች ለመደገን፣ በዙሪያዋ የአፈር ቁልል ለመደልደልና ለከበባ የሚያገለግል ግንብ ለመሥራት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሄድ አመለከተው።+ 23 ቃለ መሐላዎች የገቡላቸው ሰዎች* ግን ይህ የሐሰት ሟርት ይመስላቸዋል።+ ይሁንና እሱ በደላቸውን በማስታወስ ማርኮ ይወስዳቸዋል።+
24 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በምትፈጽሙት ድርጊት ሁሉ መተላለፋችሁ እንዲገለጥና ኃጢአታችሁ እንዲታይ በማድረግ በደላችሁ እንዲታሰብ አድርጋችኋል። እናንተም አሁን ስለታሰባችሁ በኃይል* ትወሰዳላችሁ።’
25 “አንተ ክፉኛ የቆሰልከው፣ መጥፎው የእስራኤል አለቃ፣+ ቀንህ ይኸውም የመጨረሻ ቅጣት የምትቀበልበት ጊዜ ደርሷል። 26 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ጥምጥሙን ፍታ፤ አክሊሉንም አንሳ።+ ይህ እንደ በፊቱ አይሆንም።+ ዝቅ ያለውን ከፍ አድርግ፤+ ከፍ ያለውን ደግሞ ዝቅ አድርግ።+ 27 ባድማ፣ ባድማ፣ ባድማ አደርጋታለሁ። እሷም ሕጋዊ መብት ያለው እስኪመጣ ድረስ+ ለማንም አትሆንም፤ ለእሱም እሰጣታለሁ።’+
28 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ስለ አሞናውያንና ስለ ስድባቸው እንዲህ ይላል።’ እንዲህ በል፦ ‘ሰይፍ! ሰይፍ ለግድያ ተመዟል፤ እንዲበላና እንደ መብረቅ እንዲያበራ ተወልውሏል። 29 ስለ ራስሽ የሐሰት ራእዮች ያየሽና የውሸት ሟርት ያሟረትሽ ቢሆንም ቀናቸው፣ የመጨረሻ ቅጣት የሚቀበሉበት ጊዜ በደረሰባቸው ክፉዎች ማለትም በሚገደሉት ሰዎች* ላይ ትከመሪያለሽ። 30 ሰይፉ ወደ ሰገባው ይመለስ። በተፈጠርሽበት ስፍራ፣ በተገኘሽበትም ምድር እፈርድብሻለሁ። 31 ቁጣዬን በአንቺ ላይ አወርዳለሁ። የታላቅ ቁጣዬን እሳት በላይሽ ላይ አነዳለሁ፤ በማጥፋትም ለተካኑ ጨካኝ ሰዎች አሳልፌ እሰጥሻለሁ።+ 32 ለእሳት ማገዶ ትሆኛለሽ፤+ የገዛ ደምሽ በምድሪቱ ላይ ይፈስሳል፤ ደግሞም ከእንግዲህ ወዲህ አትታወሺም፤ እኔ ይሖዋ ራሴ ይህን ተናግሬአለሁና።’”
22 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ አንተስ የደም ዕዳ ባለባት ከተማ ላይ ፍርድ ለማወጅና+ አስጸያፊ ነገሮቿን ሁሉ+ ለማሳወቅ ተዘጋጅተሃል? 3 እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በመካከልሽ ደም የምታፈሺ፣+ ፍርድ የምትቀበዪበት ጊዜ የደረሰብሽ፣+ ትረክሺም ዘንድ አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶች* የምትሠሪ ከተማ ሆይ፣+ 4 ያፈሰስሽው ደም በደለኛ አድርጎሻል፤+ ደግሞም አስጸያፊ ጣዖቶችሽ አርክሰውሻል።+ የቀኖችሽን መጨረሻ አፋጥነሻል፤ የዘመኖችሽም መጨረሻ ደርሷል። ስለዚህ ብሔራት ነቀፋ እንዲሰነዝሩብሽ፣ አገሩም ሁሉ እንዲሳለቅብሽ አደርጋለሁ።+ 5 አንቺ ስምሽ ርኩስ የሆነና ሽብር የሞላብሽ ከተማ ሆይ፣ በቅርብም ሆነ በሩቅ ያሉት አገሮች ይሳለቁብሻል።+ 6 እነሆ፣ በመካከልሽ ያለ እያንዳንዱ የእስራኤል አለቃ ሥልጣኑን ደም ለማፍሰስ ይጠቀምበታል።+ 7 በአንቺ ውስጥ ያሉት ሰዎች አባቶቻቸውንና እናቶቻቸውን ያቃልላሉ።+ ከባዕድ አገር የመጣውን ሰው ያጭበረብራሉ፤ ደግሞም አባት የሌለውን ልጅና* መበለቲቱን ይበድላሉ።”’”+
8 “‘ቅዱስ ስፍራዎቼን ታቃልያለሽ፤ ሰንበቶቼንም ታረክሻለሽ።+ 9 በአንቺ ውስጥ ደም የማፍሰስ ዓላማ ያላቸው ስም አጥፊዎች አሉ።+ በአንቺ ውስጥ በተራሮች ላይ መሥዋዕቶችን ይበላሉ፤ በመካከልሽም ጸያፍ ምግባር ይፈጽማሉ።+ 10 በአንቺ ውስጥ የአባታቸውን መኝታ ያረክሳሉ፤*+ ደግሞም በወር አበባዋ የረከሰችን ሴት አስገድደው ይደፍራሉ።+ 11 በአንቺ ውስጥ አንዱ ከባልንጀራው ሚስት ጋር አስጸያፊ ነገር ይሠራል፤+ ሌላው ጸያፍ ምግባር በመፈጸም የገዛ ምራቱን ያረክሳታል፤+ ሌላው ደግሞ የገዛ አባቱ ልጅ የሆነችውን እህቱን አስገድዶ ይደፍራል።+ 12 በአንቺ ውስጥ ያሉ ሰዎች ደም ለማፍሰስ ጉቦ ይቀበላሉ።+ ወለድና ትርፍ ለማግኘት* ታበድሪያለሽ፤+ የባልንጀሮችሽንም ገንዘብ ትቀሚያለሽ።+ አዎ፣ እኔን ጨርሶ ረስተሻል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
13 “‘እነሆ፣ ያገኘሽውን አግባብ ያልሆነ ጥቅምና በመካከልሽ ያፈሰስሽውን ደም በመጸየፍ አጨበጭባለሁ። 14 በአንቺ ላይ እርምጃ በምወስድበት ጊዜ ልብሽ ሊጸና፣ እጆችሽስ ብርቱ ሆነው ሊቀጥሉ ይችላሉ?+ እኔ ይሖዋ ራሴ ተናግሬአለሁ፤ ደግሞም አደርገዋለሁ። 15 በብሔራት መካከል እበትንሻለሁ፤ በየአገሩም እዘራሻለሁ፤+ ርኩሰትሽንም አስወግዳለሁ።+ 16 አንቺም በብሔራት ፊት ትዋረጃለሽ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቂያለሽ።’”+
17 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 18 “የሰው ልጅ ሆይ፣ የእስራኤል ቤት ሰዎች ከላይ እንደሚሰፍ የማይረባ ቆሻሻ ሆነውብኛል። ሁሉም ምድጃ ውስጥ ያለ መዳብ፣ ቆርቆሮ፣ ብረትና እርሳስ ናቸው። ብር ሲቀልጥ ከላይ እንደሚሰፍ ቆሻሻ ሆነዋል።+
19 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሁላችሁም ከላይ እንደሚሰፍ የማይረባ ቆሻሻ+ ስለሆናችሁ በኢየሩሳሌም ውስጥ እሰበስባችኋለሁ። 20 እሳት በላያቸው ላይ እንዲነድባቸውና እንዲቀልጡ ብር፣ መዳብ፣ ብረት፣ እርሳስና ቆርቆሮ በምድጃ ውስጥ እንደሚሰበሰቡ ሁሉ እኔም እናንተን በንዴትና በታላቅ ቁጣ እሰበስባችኋለሁ፤ በእናንተም ላይ እሳት በማንደድ አቀልጣችኋለሁ።+ 21 አንድ ላይ እሰበስባችኋለሁ፤ በላያችሁም ላይ የቁጣዬን እሳት አነዳለሁ፤+ እናንተም በውስጧ ትቀልጣላችሁ።+ 22 ብር በምድጃ ውስጥ እንደሚቀልጥ ሁሉ እናንተም በውስጧ ትቀልጣላችሁ፤ በእናንተ ላይ ቁጣዬን ያፈሰስኩት እኔ ይሖዋ ራሴ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’”
23 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 24 “የሰው ልጅ ሆይ፣ እንዲህ በላት፦ ‘አንቺ በቁጣ ቀን የማትጸጂ ወይም ዝናብ የማይዘንብብሽ ምድር ነሽ። 25 ነቢያቷ ያደነውን እንስሳ እንደሚቦጫጭቅ የሚያገሳ አንበሳ+ በውስጧ ሴራ ጠንስሰዋል።+ ሰዎችን* ይውጣሉ። ውድ ሀብትንና የከበሩ ነገሮችን ይነጥቃሉ። በውስጧ ያሉትን ብዙ ሴቶች መበለት አድርገዋል። 26 ካህናቷ ሕጌን ጥሰዋል፤+ ቅዱስ ስፍራዎቼንም ያረክሳሉ።+ ቅዱስ በሆነውና ተራ በሆነው ነገር መካከል ምንም ልዩነት አያደርጉም፤+ ደግሞም ንጹሕ ባልሆነውና ንጹሕ በሆነው ነገር መካከል ያለውን ልዩነት አያስታውቁም፤+ ሰንበቶቼንም ለማክበር አሻፈረኝ ይላሉ፤ እኔም በመካከላቸው ረከስኩ። 27 በመካከሏ ያሉት አለቆቿ ያደኑትን እንስሳ እንደሚቦጫጭቁ ተኩላዎች ናቸው፤ አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ደም ያፈሳሉ፤ የሰዎችንም ሕይወት* ያጠፋሉ።+ 28 ነቢያቷ ግን እነሱ የሚያደርጉትን ነገር በኖራ ይለስናሉ። የሐሰት ራእዮች ያያሉ፤ የውሸት ሟርትም ያሟርታሉ፤+ ደግሞም ይሖዋ ራሱ ምንም ሳይናገር “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል” ይላሉ። 29 የምድሪቱ ሰዎች የማጭበርበር ድርጊት ፈጽመዋል፤ ሌሎችን ዘርፈዋል፤+ ችግረኛውንና ድሃውን በድለዋል፤ ደግሞም ከባዕድ አገር የመጣውን ሰው አጭበርብረዋል፤ ፍትሕንም ነፍገውታል።’
30 “‘ከመካከላቸው የድንጋይ ቅጥሩን የሚጠግን ወይም ምድሪቱ እንዳትጠፋ በፈረሰው ቦታ ላይ በፊቴ የሚቆምላት ሰው ይኖር እንደሆነ ተመለከትኩ፤+ ሆኖም አንድም ሰው አላገኘሁም። 31 ስለዚህ ቁጣዬን በእነሱ ላይ አወርዳለሁ፤ በታላቅ ቁጣዬም እሳት ፈጽሜ አጠፋቸዋለሁ። የመረጡት መንገድ የሚያስከትለውን መዘዝ በራሳቸው ላይ አመጣባቸዋለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
23 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ከአንድ እናት የተወለዱ ሁለት ሴቶች ነበሩ።+ 3 እነሱም በግብፅ ዝሙት አዳሪዎች ሆኑ፤+ ከወጣትነታቸው ጊዜ ጀምሮ አመነዘሩ። በዚያም ጡታቸው ተሻሸ፤ የድንግልናቸውም ጉያ ተዳበሰ። 4 የታላቂቱ ስም ኦሆላ፣* የእህቷም ስም ኦሆሊባ* ነበር። እነሱም የእኔ ሆኑ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ወለዱ። ስማቸውን በተመለከተ፣ ኦሆላ ሰማርያ+ ስትሆን ኦሆሊባ ደግሞ ኢየሩሳሌም ናት።
5 “ኦሆላ የእኔ ሆና ሳለች ታመነዝር ጀመር።+ ጎረቤቶቿ የሆኑትን ፍቅረኞቿን+ አሦራውያንን በፍትወት ተመኘች።+ 6 እነሱ ሰማያዊ ልብስ የለበሱ ገዢዎችና የበታች ገዢዎች ሲሆኑ ሁሉም መልከ ቀና ወጣቶች እንዲሁም ፈረሰኞች ነበሩ። 7 እሷ ምርጥ ከሆኑት የአሦር ልጆች ሁሉ ጋር ማመንዘሯን ቀጠለች፤ ደግሞም በፍትወት የምትመኛቸው ሰዎች በሚያመልኳቸው አስጸያፊ ጣዖቶች* ራሷን አረከሰች።+ 8 በግብፅ ትፈጽመው የነበረውን ምንዝር አልተወችም፤ እነሱ በወጣትነቷ ከእሷ ጋር ተኝተዋልና፤ የድንግልናዋን ጉያ ዳብሰዋል እንዲሁም ፍትወታቸውን በእሷ ላይ አፍስሰዋል።*+ 9 ስለዚህ በፍትወት ለተመኘቻቸው፣ ፍቅረኞቿ ለሆኑት አሦራውያን አሳልፌ ሰጠኋት።+ 10 እነሱ እርቃኗን ገለጡ፤+ ወንዶችና ሴቶች ልጆቿን ማረኩ፤+ እሷንም በሰይፍ ገደሏት። በሴቶች መካከል መጥፎ ስም አተረፈች፤ እነሱም የፍርድ እርምጃ ወሰዱባት።
11 “እህቷ ኦሆሊባ ይህን ስትመለከት ፍትወቷ እጅግ የከፋ ሆነ፤ አመንዝራነቷም ከእህቷ የባሰ ሆነ።+ 12 ጎረቤቶቿ የሆኑትን የአሦርን ልጆች በፍትወት ተመኘች፤+ እነሱ ያማረ ልብስ የለበሱ ገዢዎችና የበታች ገዢዎች እንዲሁም ፈረሰኞች ሲሆኑ ሁሉም መልከ ቀና ወጣቶች ነበሩ። 13 እሷ ራሷን ባረከሰች ጊዜ ሁለቱም በአንድ መንገድ እንደሄዱ ተገነዘብኩ።+ 14 ይሁን እንጂ እሷ በአመንዝራነቷ ገፋችበት። በግድግዳው ላይ የተቀረጹትን የወንድ ምስሎች ይኸውም ቀይ ቀለም የተቀቡትን የከለዳውያን የተቀረጹ ምስሎች አየች፤ 15 እነሱ ወገባቸው ላይ ቀበቶ ታጥቀዋል፤ በራሳቸውም ላይ የተንዘረፈፈ ጥምጥም አድርገዋል፤ ደግሞም ተዋጊዎች ይመስላሉ፤ ሁሉም በከለዳውያን ምድር የተወለዱትን ባቢሎናውያን ያመለክታሉ። 16 እሷም እነሱን እንዳየቻቸው በፍትወት ትመኛቸው ጀመር፤ ወደ ከለዳውያንም ምድር መልእክተኞች ላከችባቸው።+ 17 በመሆኑም የባቢሎን ልጆች ከእሷ ጋር ለመተኛት ወደ እሷ መምጣታቸውን ቀጠሉ፤ በፍትወታቸውም* አረከሷት። በእነሱ ከረከሰች በኋላ ተጸይፋቸው* ከእነሱ ራቀች።
18 “በማንአለብኝነት ማመንዘሯንና እርቃኗን መግለጧን በቀጠለች ጊዜ+ እህቷን ተጸይፌ* እንደራቅኳት ሁሉ እሷንም ተጸይፌ ራቅኳት።+ 19 እሷ ግን በግብፅ ምድር ስታመነዝር+ የነበረበትን የወጣትነቷን ዘመን በማስታወስ በአመንዝራነቷ ይባስ ገፋችበት።+ 20 ብልታቸው እንደ አህያ ብልት፣ አባለዘራቸውም እንደ ፈረስ አባለዘር በሆኑ ወንዶች የተያዙ ቁባቶች እንደሚያደርጉት እሷም በፍትወት ተመኘቻቸው። 21 በግብፅ ምድር ጉያሽን በዳበሱበት፣ የወጣትነትሽንም ጡቶች ባሻሹበት ጊዜ በወጣትነትሽ ትፈጽሚው የነበረውን ጸያፍ ምግባር ተመኘሽ።+
22 “ስለዚህ ኦሆሊባ ሆይ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ተጸይፈሽ* የራቅሻቸውን ፍቅረኞችሽን በአንቺ ላይ አስነሳለሁ፤+ እነሱንም ከየአቅጣጫው አመጣብሻለሁ፤+ 23 እነሱም የባቢሎን ልጆችና+ ከለዳውያን+ ሁሉ እንዲሁም የአሦርን ልጆች ሁሉ ጨምሮ የጰቆድ፣+ የሾአ እና የቆአ ሰዎች ናቸው። ሁሉም መልከ ቀና ወጣቶች፣ ገዢዎችና የበታች ገዢዎች፣ ተዋጊዎችና የተመረጡ አማካሪዎች እንዲሁም ፈረሰኞች ናቸው። 24 እነሱም የጦር ሠረገሎችንና መንኮራኩሮችን* ሁሉ እያንጋጉ፣ ትልቅና ትንሽ* ጋሻ የያዘ እንዲሁም የራስ ቁር የደፋ ብዙ ሠራዊት አስከትለው ጥቃት ይሰነዝሩብሻል። በዙሪያሽም ይሰለፋሉ፤ እኔም የመፍረድ ሥልጣን እሰጣቸዋለሁ፤ እነሱም ትክክል መስሎ በታያቸው መንገድ ይፈርዱብሻል።+ 25 እኔም ቁጣዬን በአንቺ ላይ እገልጣለሁ፤ እነሱም በታላቅ ቁጣ እርምጃ ይወስዱብሻል። አፍንጫሽንና ጆሮዎችሽን ይቆርጣሉ፤ ከአንቺም የቀሩት በሰይፍ ይወድቃሉ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችሽን ይወስዳሉ፤ ከአንቺም የቀሩት በእሳት ይበላሉ።+ 26 ልብሶችሽን ይገፉሻል፤+ ያማሩ ጌጣጌጦችሽንም ይነጥቁሻል።+ 27 በግብፅ ምድር የጀመርሽው+ ጸያፍ ምግባርና አመንዝራነትሽ እንዲያበቃ አደርጋለሁ።+ ከእንግዲህ ዓይንሽን ወደ እነሱ አታነሺም፤ ግብፅንም አታስታውሺም።’
28 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘እነሆ፣ ለጠላሻቸው ሰዎች፣ ተጸይፈሽ* ለራቅሻቸው ሰዎች አሳልፌ ልሰጥሽ ነው።+ 29 እነሱ በጥላቻ እርምጃ ይወስዱብሻል፤ የደከምሽበትን ነገር ሁሉ ይወስዳሉ፤+ ራቁትሽንና እርቃንሽን ያስቀሩሻል። የፆታ ብልግና ስትፈጽሚ የተገለጠው አሳፋሪ የሆነው እርቃንሽ፣ ጸያፍ ምግባርሽና አመንዝራነትሽ ይፋ ይወጣል።+ 30 እንደ ዝሙት አዳሪ ብሔራትን ተከትለሽ ስለሄድሽና+ አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻቸው ራስሽን ስላረከስሽ+ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ይፈጸሙብሻል። 31 የእህትሽን መንገድ ተከትለሻል፤+ ስለዚህ የእሷን ጽዋ አስጨብጥሻለሁ።’+
32 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
34 ትጠጪዋለሽ፤ ትጨልጪዋለሽ፤+ የጽዋውንም ስብርባሪዎች ትቆረጣጥሚያለሽ፤
ከዚያም ጡቶችሽን ትቆርጫለሽ።
“እኔ ራሴ ተናግሬአለሁና” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።’
35 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ስለረሳሽኝና ጨርሶ ቸል ስላልሽኝ*+ ጸያፍ ምግባርሽና አመንዝራነትሽ የሚያስከትለውን መዘዝ ትቀበያለሽ።’”
36 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ በኦሆላና በኦሆሊባ+ ላይ ትፈርዳለህ? አስጸያፊ ተግባራቸውንስ ፊት ለፊት ትነግራቸዋለህ? 37 እነሱ አመንዝረዋል፤*+ እጃቸውም በደም ተበክሏል። አስጸያፊ ከሆኑት ጣዖቶቻቸው ጋር ከማመንዘራቸውም በተጨማሪ ለእኔ የወለዷቸውን ልጆች ለጣዖቶቻቸው መብል እንዲሆኑ ለእሳት አሳልፈው ሰጥተዋል።+ 38 በተጨማሪም በእኔ ላይ እንዲህ አድርገዋል፦ በዚያ ቀን መቅደሴን አርክሰዋል፤ ሰንበቶቼንም አቃለዋል። 39 ልጆቻቸውን አስጸያፊ ለሆኑት ጣዖቶቻቸው ከሠዉ+ በኋላ በዚያው ቀን ወደ መቅደሴ መጥተው አረከሱት።+ እንግዲህ በቤቴ ውስጥ ይህን አድርገዋል። 40 አልፎ ተርፎም ከሩቅ ቦታ ወንዶች እንዲመጡላቸው መልእክተኛ ላኩ።+ እነሱ በመጡ ጊዜ ገላሽን ታጠብሽ፤ ዓይንሽን ተኳልሽ፤ በጌጣጌጥም ተዋብሽ።+ 41 እጅግ ባማረ ድንክ አልጋ ላይ ተቀመጥሽ፤+ በፊቱም በተሰናዳ ማዕድ+ ላይ ዕጣኔንና+ ዘይቴን አኖርሽ።+ 42 በዚያም በፈንጠዝያ ላይ ያሉ ብዙ ወንዶች ሁካታ ይሰማ ነበር፤ በመካከላቸውም ከምድረ በዳ የመጡ ሰካራሞች ነበሩ። እነሱም በሴቶቹ እጆች ላይ አምባር አጠለቁ፤ በራሳቸውም ላይ የተዋበ አክሊል አደረጉላቸው።
43 “ከዚያም እኔ ሰውነቷ በምንዝር ስላለቀው ሴት፣ ‘አሁንም ማመንዘሯን ትቀጥላለች’ አልኩ። 44 ሰው ወደ ዝሙት አዳሪ እንደሚሄድ ሁሉ እነሱም ወደ እሷ መሄዳቸውን ቀጠሉ። በዚህ መንገድ፣ ባለጌ ወደሆኑት ወደ ኦሆላና ወደ ኦሆሊባ ገቡ። 45 ጻድቃን ግን ለምንዝርና ለደም አፍሳሽነት የሚገባውን ፍርድ ይፈርዱባታል፤+ እነሱ አመንዝሮች ናቸውና፤ እጃቸውም በደም ተበክሏል።+
46 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘መቀጣጫ ያደርጋቸውና ለብዝበዛ ይዳርጋቸው ዘንድ በእነሱ ላይ ብዙ ሠራዊት ይሰበሰባል።+ 47 ሠራዊቱ ድንጋይ ይወረውርባቸዋል፤+ በሰይፉም ይቆራርጣቸዋል። ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ይገድላል፤+ ቤቶቻቸውንም በእሳት ያቃጥላል።+ 48 በምድሪቱ ላይ የሚፈጸመው ጸያፍ ምግባር እንዲወገድ አደርጋለሁ፤ ሴቶቹም ሁሉ ከዚህ ይማራሉ፤ የእናንተንም ጸያፍ ምግባር ከመከተል ይርቃሉ።+ 49 የፈጸማችሁት ጸያፍ ምግባር እንዲሁም አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻችሁ የሠራችሁት ኃጢአት የሚያስከትለውን መዘዝ እንድትቀበሉ ያደርጋሉ፤ እኔም ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’”+
24 የይሖዋ ቃል በዘጠነኛው ዓመት፣ በአሥረኛው ወር፣ ከወሩም በአሥረኛው ቀን እንዲህ ሲል ዳግመኛ ወደ እኔ መጣ፦ 2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ይህን ቀን፣* አዎ ይህንኑ ቀን መዝግብ። የባቢሎን ንጉሥ በዚሁ ቀን በኢየሩሳሌም ላይ ጥቃት መሰንዘር ጀምሯል።+ 3 ዓመፀኛውን ቤት አስመልክቶ ምሳሌ* ተናገር፤ ስለ እነሱም እንዲህ በል፦
“‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“ድስቱን* ጣደው፤ እሳት ላይ ጣደው፤ ውኃም ጨምርበት።+
4 ጭኑንና ወርቹን ጨምሮ ጥሩ ጥሩ የሆነውን ሙዳ ሥጋ ሁሉ ሰብስበህ ጨምርበት፤+
ምርጥ የሆኑ አጥንቶችንም ሙላበት።
5 ከመንጋው ምርጥ የሆነውን በግ ውሰድ፤+ በድስቱም ሥር ዙሪያውን ማገዶ ጨምር።
ሥጋውን ቀቅለው፤ በውስጡ ያለውንም አጥንት አብስለው።”’
6 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
‘የዛገ ድስት ለሆነችውና ዝገቷ ላለቀቀው እንዲሁም ደም አፍሳሽ ለሆነችው ከተማ ወዮላት!+
ሥጋውን አንድ በአንድ አውጣ፤+ ዕጣ መጣል አያስፈልግህም።
7 ያፈሰሰችው ደም በውስጧ ይገኛልና፤+ በገላጣ ዓለት ላይ አፍስሳዋለች።
በአፈር እንዲሸፈን መሬት ላይ አላፈሰሰችውም።+
9 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
‘ደም አፍሳሽ ለሆነችው ከተማ ወዮላት!+
ማገዶውን እቆልለዋለሁ።
10 እንጨቱን ከምር፤ እሳቱን አቀጣጥል፤
ሥጋውን በደንብ ቀቅል፤ መረቁን አፍስ፤ አጥንቶቹም ይረሩ።
11 ባዶውን ድስት እንዲግል ፍሙ ላይ ጣደው፤
መዳቡም በጣም ይግላል።
ቆሻሻው በውስጡ ይቀልጣል፤+ ዝገቱንም እሳት ይበላዋል።
12 ድስቱ በጣም ከመዛጉ የተነሳ ስለማይለቅ ከንቱ ልፋት ነው፤
ደግሞም እንዲሁ ድካም ብቻ ነው።+
ከነዝገቱ እሳት ውስጥ ጣለው!’
13 “‘በጸያፍ ምግባርሽ የተነሳ ረክሰሻል።+ ላነጻሽ ሞክሬ ነበር፤ አንቺ ግን ከርኩሰትሽ ንጹሕ ልትሆኚ አትችዪም። በአንቺ ላይ ያደረብኝ ቁጣ እስኪበርድ ድረስ ንጹሕ አትሆኚም።+ 14 እኔ ይሖዋ ራሴ ይህን ተናግሬአለሁ። በእርግጥ ይፈጸማል። ምንም ሳላቅማማ፣ ያላንዳች ሐዘንና ጸጸት እርምጃ እወስዳለሁ።+ እንደ መንገድሽና እንደ ሥራሽ ይፈርዱብሻል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
15 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 16 “የሰው ልጅ ሆይ፣ በፊትህ ተወዳጅ የሆነውን በአንድ ምት ልወስድብህ ነው።+ አንተም ዋይታ አታሰማ* ወይም አታልቅስ ወይም ደግሞ እንባህን አታፍስ። 17 ሐዘንህን በውስጥህ አምቀህ ያዝ፤ ለሞተው በወጉ መሠረት ሐዘንህን አትግለጽ።+ ጥምጥምህን እሰር፤+ ጫማህንም አድርግ።+ ሪዝህን* አትሸፍን፤+ ሰዎች የሚያመጡልህንም ምግብ* አትብላ።”+
18 እኔም በጠዋት ለሕዝቡ ተናገርኩ፤ ሚስቴም ማታ ላይ ሞተች። ስለሆነም ጠዋት፣ ልክ እንደታዘዝኩት አደረግኩ። 19 ሕዝቡም “ይህ የምታደርገው ነገር ለእኛ ምን መልእክት እንዳለው አትነግረንም?” አሉኝ። 20 እኔም እንዲህ አልኳቸው፦ “የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 21 ‘ለእስራኤል ቤት ሰዎች እንዲህ በል፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እጅግ የምትኮሩበትን፣ በፊታችሁ ተወዳጅ የሆነውንና የልባችሁ ምኞት የሆነውን* መቅደሴን ላረክስ ነው።+ ትታችኋቸው የሄዳችሁት ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።+ 22 ከዚያም እኔ እንዳደረግኩት ታደርጋላችሁ። ሪዛችሁን አትሸፍኑም፤ ሰዎች የሚያመጡላችሁንም ምግብ አትበሉም።+ 23 ጥምጥማችሁ አይፈታም፤ ጫማችሁ ከእግራችሁ ላይ አይወልቅም። ዋይታ አታሰሙም ወይም አታለቅሱም። ይልቁንም በበደላችሁ ትመነምናላችሁ፤+ አንዳችሁ ለሌላው እሮሮ ታሰማላችሁ። 24 ሕዝቅኤል ምልክት ይሆንላችኋል።+ እሱ እንዳደረገው ሁሉ ታደርጋላችሁ። ይህ በሚሆንበት ጊዜ እኔ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’”’”
25 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ ምሽጋቸውን ይኸውም ደስ የሚሰኙበትን ያማረ ነገር፣ በፊታቸው ተወዳጅ የሆነውን ነገርና የልባቸውን* ምኞት እንዲሁም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በምወስድባቸው ቀን፣+ 26 አምልጦ የመጣ ሰው ወሬውን ይነግርሃል።+ 27 በዚያን ቀን አፍህን ከፍተህ፣ ካመለጠው ሰው ጋር ትነጋገራለህ፤ ከዚያ በኋላ ዱዳ አትሆንም።+ ምልክት ትሆንላቸዋለህ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”
25 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን ወደ አሞናውያን+ አዙረህ በእነሱ ላይ ትንቢት ተናገር።+ 3 አሞናውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘የሉዓላዊውን ጌታ የይሖዋን ቃል ስሙ። ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “መቅደሴ በረከሰ ጊዜና የእስራኤል ምድር ባድማ በሆነ ጊዜ እንዲሁም የይሁዳ ቤት ሰዎች በግዞት በተወሰዱ ጊዜ ‘እሰይ!’ ስላላችሁ 4 ለምሥራቅ ሰዎች ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ። እነሱ በእናንተ ውስጥ ይሰፍራሉ፤* ድንኳኖቻቸውንም በመካከላችሁ ይተክላሉ። ፍሬያችሁን ይበላሉ፤ ወተታችሁንም ይጠጣሉ። 5 ራባን+ የግመሎች መሰማሪያ፣ የአሞናውያንን ምድርም መንጋ የሚያርፍበት ስፍራ አደርጋለሁ፤ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።”’”
6 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘በእጅህ ስላጨበጨብክና+ በእግርህ መሬቱን ስለመታህ እንዲሁም በእስራኤል ምድር ላይ የደረሰውን ሁኔታ ስታይ በንቀት ተሞልተህ* ሐሴት ስላደረግክ፣+ 7 ብሔራት እንዲበዘብዙህ ለእነሱ አሳልፌ እሰጥህ ዘንድ እጄን በአንተ ላይ እዘረጋለሁ። ከሕዝቦች መካከል አስወግድሃለሁ፤ ከአገራትም መካከል ለይቼ አጠፋሃለሁ።+ እደመስስሃለሁ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃለህ።’
8 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሞዓብና+ ሴይር+ “እነሆ፣ የይሁዳ ቤት ልክ እንደ ሌሎቹ ብሔራት ነው” ስላሉ፣ 9 በድንበሩ ላይ የሚገኙትና የምድሪቱ ውበት* የሆኑት ከተሞች ማለትም ከቤትየሺሞትና ከበዓልመዖን አንስቶ እስከ ቂርያታይም+ ድረስ ያለው የሞዓብ ክንፍ* ለጠላት እንዲጋለጥ አደርጋለሁ። 10 ከአሞናውያን ጋር ለምሥራቅ ሰዎች ርስት አድርጌ እሰጠዋለሁ፤+ ይህም አሞናውያን በብሔራት መካከል እንዳይታወሱ ለማድረግ ነው።+ 11 በሞዓብም ላይ የፍርድ እርምጃ እወስዳለሁ፤+ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’
12 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ኤዶም በቂም በቀል ተነሳስቶ በይሁዳ ቤት ላይ እርምጃ ወስዷል፤ ደግሞም እነሱን በመበቀል ከፍተኛ በደል ፈጽሟል፤+ 13 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እጄን በኤዶምም ላይ እዘረጋለሁ፤ ከምድሪቱም ላይ ሰውንም ሆነ ከብትን አጠፋለሁ፤ ባድማም አደርጋታለሁ።+ ከቴማን አንስቶ እስከ ዴዳን ድረስ በሰይፍ ይወድቃሉ።+ 14 ‘በሕዝቤ በእስራኤል እጅ ኤዶምን እበቀላለሁ።+ እነሱም፣ ኤዶም የምወስደውን የበቀል እርምጃ ይቀምስ ዘንድ ቁጣዬንና መዓቴን በኤዶም ላይ ያወርዳሉ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”’
15 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ፍልስጤማውያን በማይበርድ የጠላትነት ስሜት ተነሳስተው በክፋት* የበቀል እርምጃ ለመውሰድና ጥፋት ለማድረስ ጥረት አድርገዋል።+ 16 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በፍልስጤማውያን ላይ እጄን እዘረጋለሁ፤+ ከሪታውያንንም አጠፋለሁ፤+ በባሕሩ ዳርቻ ላይ የቀሩትንም ነዋሪዎች እደመስሳለሁ።+ 17 ኃይለኛ ቅጣት በመቅጣት ታላቅ የበቀል እርምጃ እወስድባቸዋለሁ፤ በምበቀላቸውም ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”’”
26 በ11ኛው ዓመት፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ጢሮስ ስለ ኢየሩሳሌም+ ‘እሰይ! የሕዝቦች በር ተሰበረች!+ አሁን እሷ ስለጠፋች ሁሉም ነገር ይሳካልኛል፤ ደግሞም እበለጽጋለሁ’ ስላለች፣ 3 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ጢሮስ ሆይ፣ እነሆ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ፤ ባሕር ሞገዱን እንደሚያስነሳ ብዙ ብሔራትን በአንቺ ላይ አስነሳለሁ። 4 እነሱ የጢሮስን ቅጥሮች ያፈርሳሉ፤ ማማዎቿንም ያወድማሉ፤+ አፈሯን ከላይዋ ጠርጌ አስወግዳለሁ፤ የሚያንጸባርቅ ገላጣ ዓለትም አደርጋታለሁ። 5 በባሕር መካከል የመረብ ማስጫ ቦታ ትሆናለች።’+
“‘እኔ ራሴ ተናግሬአለሁና፣’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ብሔራትም ይበዘብዟታል። 6 በገጠር ያሉ ሰፈሮቿም* በሰይፍ ይመታሉ፤ ሰዎችም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’
7 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘እነሆ፣ በጢሮስ ላይ የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነጾርን* ከሰሜን አመጣለሁ፤+ እሱ ፈረሶችን፣+ የጦር ሠረገሎችን፣+ ፈረሰኞችንና ብዙ ወታደሮችን* ያቀፈ ሠራዊት ያለው የነገሥታት ንጉሥ ነው።+ 8 በገጠር ያሉ ሰፈሮችሽን በሰይፍ ያወድማል፤ በአንቺም ላይ ለከበባ የሚያገለግል ግንብ ይገነባል፤ የአፈር ቁልልም ይደለድላል፤ በአንቺም ላይ ትልቅ ጋሻ ያነሳል። 9 ቅጥሮችሽን በግንብ መደርመሻ መሣሪያ* ይደበድባል፤ ማማዎችሽንም በመጥረቢያ* ያፈርሳል። 10 ፈረሶቹ እጅግ ብዙ ከመሆናቸው የተነሳ አቧራ ያለብሱሻል፤ ሰዎች ቅጥሮቿ ወደፈረሱባት ከተማ እንደሚገቡ ሁሉ እሱም በበሮችሽ በሚገባበት ጊዜ የፈረሰኞቹ፣ የመንኮራኩሮቹና* የሠረገሎቹ ድምፅ ቅጥሮችሽን ያናውጣል። 11 የፈረሶቹ ኮቴዎች ጎዳናዎችሽን ሁሉ ይረግጣሉ፤+ ሕዝብሽን በሰይፍ ይገድላል፤ ግዙፍ የሆኑት ዓምዶችሽ መሬት ላይ ይንኮታኮታሉ። 12 ሀብትሽን ይበዘብዛሉ፤ ሸቀጥሽን ይዘርፋሉ፤+ ቅጥሮችሽን ያፈርሳሉ፤ የሚያማምሩ ቤቶችሽንም ያወድማሉ፤ ከዚያም ድንጋዮችሽን፣ ሳንቃዎችሽንና አፈርሽን ወደ ባሕር ይጥላሉ።’
13 “‘የዘፈንሽ ጩኸት ጸጥ እንዲል አደርጋለሁ፤ የበገናሽም ድምፅ ከእንግዲህ አይሰማም።+ 14 የሚያንጸባርቅ ገላጣ ዓለትም አደርግሻለሁ፤ የመረብ ማስጫ ቦታ ትሆኛለሽ።+ ዳግመኛ አትገነቢም፤ እኔ ይሖዋ ራሴ ተናግሬአለሁና’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
15 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ጢሮስን እንዲህ ይላል፦ ‘ሞት አፋፍ ላይ ያሉት* ሲያቃስቱና በመካከልሽ ጭፍጨፋ ሲካሄድ፣ ከውድቀትሽ ድምፅ የተነሳ ደሴቶች አይናወጡም?+ 16 የባሕርም ገዢዎች* ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ፤ ልብሳቸውንም * ያወልቃሉ፤ የተጠለፉ ሸማዎቻቸውንም አውልቀው ይጥላሉ፤ ደግሞም በጣም ይንቀጠቀጣሉ።* መሬት ላይ ተቀምጠው ያለማቋረጥ ይንቀጠቀጣሉ፤ በመገረምም አተኩረው ይመለከቱሻል።+ 17 በአንቺም ላይ ሙሾ ያወርዳሉ፤*+ እንዲህም ይሉሻል፦
“ባሕር አቋርጠው የመጡ ሰዎች የሰፈሩብሽ፣ የተወደስሽ ከተማ ሆይ፣ እንዴት ጠፋሽ!+
አንቺም ሆንሽ ነዋሪዎችሽ በምድር ነዋሪዎች ሁሉ ላይ
ሽብር የምትነዙ የባሕር ላይ ኃያላን ነበራችሁ።+
18 በምትወድቂበት ቀን ደሴቶች ይንቀጠቀጣሉ፤
ጥፋት በሚደርስብሽ ጊዜ በባሕር ላይ ያሉ ደሴቶች ይሸበራሉ።”’+
19 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘ሰው እንደማይኖርባቸው ከተሞች ባድማ ሳደርግሽ፣ የሚያጥለቀልቅ ውኃ ሳመጣብሽና ኃይለኛ ውኃ ሲሸፍንሽ፣+ 20 አንቺንም ሆነ ከአንቺ ጋር ወደ ጉድጓድ* የሚወርዱትን፣ የጥንት ዘመን ሰዎች ወዳሉበት አወርዳችኋለሁ፤ ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱት ጋር፣ ጥንት እንደወደሙት ቦታዎች እጅግ ዝቅተኛ በሆነ ምድር እንድትኖሪ አደርጋለሁ፤+ ይህም የሚሆነው ሰው እንዳይኖርብሽ ነው። ከዚያ በኋላ የሕያዋንን ምድር ከፍ ከፍ አደርጋለሁ።*
21 “‘በአንቺ ላይ ድንገተኛ ሽብር አመጣለሁ፤ ከእንግዲህም አትኖሪም።+ ይፈልጉሻል ግን ፈጽሞ አትገኚም’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
27 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ በጢሮስ ላይ ሙሾ አውርድ፤*+ 3 ጢሮስንም እንዲህ በላት፦
‘አንቺ በባሕሩ መግቢያዎች ላይ የምትኖሪና
በብዙ ደሴቶች ላይ ከሚኖሩ ሕዝቦች ጋር የንግድ ልውውጥ የምታደርጊ፣
ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“ጢሮስ ሆይ፣ አንቺ ራስሽ ‘ፍጹም ውብ ነኝ’ ብለሻል።+
4 ግዛትሽ በባሕሩ መካከል ነው፤
የገነቡሽ ሰዎችም ውበትሽን ፍጹም አድርገውታል።
6 በባሳን የባሉጥ ዛፎች መቅዘፊያዎችሽን ሠሩ፤
የፊተኛውን ክፍልሽንም ከኪቲም+ ደሴቶች በመጣ በዝሆን ጥርስ በተለበጠ የጥድ እንጨት ሠሩ።
7 ከግብፅ የመጣው የተለያየ ቀለም ያለው በፍታ የመርከብ ሸራሽን ለመሥራት አገልግሏል፤
የላይኛው መድረክ መሸፈኛዎችሽም ከኤሊሻ+ ደሴቶች በመጣ ሰማያዊ ክርና ሐምራዊ ሱፍ የተሠሩ ናቸው።
8 ቀዛፊዎችሽ የሲዶና እና የአርዋድ+ ነዋሪዎች ነበሩ።
ጢሮስ ሆይ፣ የገዛ ራስሽ ባለሙያዎች መርከበኞችሽ ነበሩ።+
9 ልምድ ያካበቱት* የጌባል+ ባለሙያዎች ስንጥቆችሽን ይደፍናሉ።+
በባሕር ላይ የሚጓዙ መርከቦችና ባሕረኞቻቸው ሁሉ ሸቀጣ ሸቀጦችን ለመገበያየት ወደ አንቺ ይመጡ ነበር።
10 የፋርስ፣ የሉድና የፑጥ+ ሰዎች ተዋጊዎች ሆነው በጦር ሠራዊትሽ ውስጥ ያገለግሉ ነበር።
ጋሻቸውንና የራስ ቁራቸውን በአንቺ ውስጥ ሰቀሉ፤ ደግሞም ግርማ ሞገስ አጎናጸፉሽ።
11 በሠራዊትሽ ውስጥ ያሉት የአርዋድ ሰዎች በቅጥሮችሽ ላይ ዙሪያውን ቆመው ነበር፤
ጀግኖችም በማማዎችሽ ላይ ነበሩ።
ክብ የሆኑ ጋሻዎቻቸውን በቅጥሮችሽ ዙሪያ ሰቀሉ፤
ውበትሽንም ፍጹም አደረጉ።
12 “‘“ከተትረፈረፈው ውድ ሀብትሽ የተነሳ ተርሴስ+ ከአንቺ ጋር የንግድ ልውውጥ ታደርግ ነበር።+ ሸቀጣ ሸቀጦችሽን በብር፣ በብረት፣ በቆርቆሮና በእርሳስ ይለውጡ ነበር።+ 13 ያዋን፣ ቱባልና+ መሼቅ+ ከአንቺ ጋር ይገበያዩ ነበር፤ ሸቀጦችሽን በባሪያዎችና በመዳብ ዕቃዎች ይለውጡ ነበር።+ 14 የቶጋርማ+ ሰዎች ደግሞ ሸቀጦችሽን በጭነት ፈረሶች፣ በጦር ፈረሶችና በበቅሎዎች ይለውጡ ነበር። 15 የዴዳን+ ሰዎች ከአንቺ ጋር ይገበያዩ ነበር፤ በብዙ ደሴቶች ላይ ነጋዴዎች ቀጠርሽ፤ የዝሆን ጥርስና+ ዞጲ* በግብር መልክ ያመጡልሽ ነበር። 16 ከምታመርቻቸው ዕቃዎች ብዛት የተነሳ ኤዶም ከአንቺ ጋር ትነግድ ነበር። ሸቀጦችሽን በበሉር፣ በሐምራዊ ሱፍ፣ የተለያዩ ቀለማት ባላቸው ጥልፎች፣ ጥራት ባለው ልብስ፣ በዛጎልና በሩቢ ይለውጡ ነበር።
17 “‘“ይሁዳና የእስራኤል ምድር ከአንቺ ጋር ይገበያዩ ነበር፤ ሸቀጦችሽን በሚኒት+ ስንዴ፣ ምርጥ በሆኑ ምግቦች፣ በማር፣+ በዘይትና በበለሳን+ ይለውጡ ነበር።+
18 “‘“ደማስቆ+ ከተትረፈረፈው ምርትሽና ከሀብትሽ የተነሳ ከአንቺ ጋር ትነግድ ነበር፤ የሄልቦን የወይን ጠጅና የዛሃር ሱፍ* ጨርቅ ትሸጥልሽ ነበር። 19 በዑዛል አቅራቢያ የሚገኙት ዌዳንና ያዋን ሸቀጦችሽን በሚተጣጠፍ ብረት፣ በብርጉድና* በጠጅ ሣር ይለውጡ ነበር። 20 ዴዳን፣+ በከብት ላይ ለመቀመጥ የሚያገለግል ግላስ* በማቅረብ ከአንቺ ጋር የንግድ ልውውጥ ታደርግ ነበር። 21 የጠቦቶች፣ የአውራ በጎችና የፍየሎች+ ነጋዴ የሆኑ ዓረቦችንና የቄዳር+ አለቆችን ሁሉ ቀጠርሽ። 22 የሳባና የራአማ+ ነጋዴዎች ከአንቺ ጋር ይገበያዩ ነበር፤ ሸቀጦችሽን በሁሉም ዓይነት ምርጥ የሆኑ ሽቶዎች፣ የከበሩ ድንጋዮችና በወርቅ ይለውጡ ነበር።+ 23 ካራን፣+ ካኔህና ኤደን+ እንዲሁም የሳባ፣+ የአሹርና+ የኪልማድ ነጋዴዎች ከአንቺ ጋር ይገበያዩ ነበር። 24 በገበያ ቦታሽ ያማሩ ልብሶችን፣ በሰማያዊ ጨርቅና የተለያዩ ቀለማት ባለው ጥልፍ የተሠራን ካባ እንዲሁም ብዙ ዓይነት ቀለም ያላቸውን ምንጣፎች ይነግዱ የነበረ ሲሆን ሁሉም በገመድ በጥብቅ የታሰሩ ነበሩ።
26 ቀዛፊዎችሽ ወደ ታላቅ ባሕር አምጥተውሻል፤
የምሥራቁ ነፋስ በተንጣለለው ባሕር መካከል ሰባብሮሻል።
27 ውድቀት በሚደርስብሽ ቀን ሀብትሽ፣ ሸቀጦችሽ፣ የምትነግጃቸው ዕቃዎች፣ ባሕረኞችሽ፣ መርከበኞችሽ፣
ስንጥቆችሽን የሚደፍኑልሽ ሰዎች፣ ነጋዴዎችሽና+ ተዋጊዎችሽ ሁሉ+
ይኸውም በአንቺ ውስጥ ያለው ሕዝብ* ሁሉ
በተንጣለለው ባሕር መካከል ይሰምጣል።+
28 መርከበኞችሽ ሲጮኹ የባሕሩ ጠረፍ ይናወጣል።
29 ቀዛፊዎቹ፣ ባሕረኞቹና መርከበኞቹ ሁሉ
ከመርከቦቻቸው ይወርዳሉ፤ መሬት ላይም ይቆማሉ።
30 በአንቺ የተነሳ በራሳቸው ላይ አቧራ እየነሰነሱና በአመድ ላይ እየተንከባለሉ
ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይጮኻሉ፤ ምርር ብለውም ያለቅሳሉ።+
31 በአንቺ የተነሳ ራሳቸውን ይላጫሉ፣ ማቅ ይለብሳሉ
እንዲሁም ዋይ ዋይ እያሉ አምርረው * ያለቅሳሉ።
32 ለአንቺም በሚያለቅሱበት ጊዜ ሙሾ ያወርዳሉ፤ የሐዘን እንጉርጉሮም ያንጎራጉራሉ፦
‘በባሕር መካከል ጸጥ እንዳለችው እንደ ጢሮስ ያለ ማን ነው?+
33 ሸቀጥሽ ከተንጣለለው ባሕር በመጣ ጊዜ ብዙ ሕዝቦችን አጥግበሻል።+
የተትረፈረፈው ሀብትሽና ሸቀጣ ሸቀጥሽ የምድርን ነገሥታት አበልጽጓል።+
36 በብሔራት መካከል ያሉ ነጋዴዎች በአንቺ ላይ ከደረሰው ነገር የተነሳ ያፏጫሉ።
ፍጻሜሽ ድንገተኛና አስከፊ ይሆናል፤
ደግሞም ለዘላለም ከሕልውና ውጭ ትሆኛለሽ።’”’”+
28 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ የጢሮስን ገዢ እንዲህ በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“ልብህ ከመታበዩ የተነሳ+ ‘እኔ አምላክ ነኝ።
በባሕሩ መካከል በአምላክ ዙፋን ላይ እቀመጣለሁ’ ትላለህ።+
በልብህ አምላክ እንደሆንክ የምታስብ ቢሆንም
አንተ ሰው እንጂ አምላክ አይደለህም።
3 እነሆ፣ አንተ ከዳንኤል+ ይበልጥ ጥበበኛ እንደሆንክ ይሰማሃል።
ከአንተ የተሰወረ ሚስጥር እንደሌለ አድርገህ ታስባለህ።
4 በጥበብህና በማስተዋልህ ራስህን አበልጽገሃል፤
በግምጃ ቤቶችህም ውስጥ ወርቅና ብር ማከማቸትህን ቀጥለሃል።+
5 በንግድህ ስኬታማ ከመሆንህ የተነሳ ብዙ ሀብት አፈራህ፤+
ካካበትከውም ሀብት የተነሳ ልብህ ታበየ።”’
6 “‘ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“በልብህ አምላክ እንደሆንክ ስለተሰማህ፣
7 ከብሔራት መካከል እጅግ ጨካኝ የሆኑትን ባዕዳን አመጣብሃለሁ፤+
እነሱም በጥበብህ ውበት ላይ ሰይፋቸውን ይመዛሉ፤
ታላቅ ግርማህንም ያረክሳሉ።+
9 ያም ሆኖ በገዳይህ ፊት ‘እኔ አምላክ ነኝ’ ትላለህ?
በሚያረክሱህ ሰዎች እጅ ሰው እንጂ አምላክ አይደለህም።”’
10 ‘በባዕዳን እጅ፣ ያልተገረዙ ሰዎችን አሟሟት ትሞታለህ፤
እኔ ራሴ ተናግሬአለሁና’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
11 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 12 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ስለ ጢሮስ ንጉሥ ሙሾ አውርድ፤* እንዲህም በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
13 በአምላክ የአትክልት ስፍራ በኤደን ነበርክ።
በከበሩ ድንጋዮች ሁሉ
ይኸውም በሩቢ፣ በቶጳዝዮን፣ በኢያስጲድ፣ በክርስቲሎቤ፣ በኦኒክስ፣ በጄድ፣ በሰንፔር፣ በበሉርና+ በመረግድ አጊጠህ ነበር፤
እነዚህ የከበሩ ድንጋዮች የተሰኩባቸው ማቀፊያዎችም ከወርቅ የተሠሩ ነበሩ።
በተፈጠርክበት ቀን ተዘጋጅተው ነበር።
14 የተቀባህ፣ የምትጋርድ ኪሩብ አድርጌ ሾምኩህ።
በአምላክ ቅዱስ ተራራ ላይ ነበርክ፤+ በእሳታማ ድንጋዮችም መካከል ትመላለስ ነበር።
15 ከተፈጠርክበት ቀን አንስቶ ዓመፅ እስከተገኘብህ ጊዜ ድረስ
በመንገድህ ሁሉ ምንም እንከን አልነበረብህም።+
የምትጋርድ ኪሩብ ሆይ፣ እንደ ርኩስ ቆጥሬ ከአምላክ ተራራ እጥልሃለሁ፤
ከእሳታማዎቹ ድንጋዮች መካከልም አስወግድሃለሁ።+
17 በውበትህ+ ምክንያት ልብህ ታበየ።
ከታላቅ ግርማህ የተነሳ ጥበብህን አበላሸህ።+
ወደ ምድር እጥልሃለሁ።+
በነገሥታት ፊት ትዕይንት አደርግሃለሁ።
18 ታላቅ በደል በመፈጸምና በንግድ ሥራ በማጭበርበር መቅደሶችህን አረከስክ።
እኔም ከመካከልህ እሳት እንዲወጣ አደርጋለሁ፤ እሳቱም ይበላሃል።+
በሚያዩህ ሁሉ ፊት በምድር ላይ አመድ አደርግሃለሁ።
19 ከሕዝቦች መካከል የሚያውቁህ ሁሉ በመገረም አተኩረው ያዩሃል።+
ፍጻሜህ ድንገተኛና አስከፊ ይሆናል፤
ደግሞም ለዘላለም ከሕልውና ውጭ ትሆናለህ።”’”+
20 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 21 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን ወደ ሲዶና+ አዙረህ በእሷ ላይ ትንቢት ተናገር። 22 እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“ሲዶና ሆይ፣ እነሆ እኔ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ፤ በመካከልሽም እከበራለሁ፤
ደግሞም በእሷ ላይ የፍርድ እርምጃ በምወስድበትና በእሷ አማካኝነት በምቀደስበት ጊዜ ሰዎች እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።
23 በእሷ ላይ ቸነፈር እሰዳለሁ፤ በጎዳናዎቿም ላይ ደም ይፈስሳል።
ከየአቅጣጫው ሰይፍ በሚመጣባት ጊዜ የታረዱት ሰዎች በመካከሏ ይወድቃሉ፤
እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።+
24 “‘“ከዚያ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ አደገኛ በሆነ አሜኬላና በሚያሠቃይ እሾህ+ ይኸውም በሚንቁት ብሔራት ዳግመኛ አይከበብም፤ ሰዎችም እኔ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”’
25 “‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤልን ቤት ሰዎች ከተበተኑባቸው ሕዝቦች መካከል ዳግመኛ በምሰበስባቸው ጊዜ+ በብሔራት ፊት በእነሱ መካከል እቀደሳለሁ።+ እነሱም ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት+ ምድራቸው ላይ ይኖራሉ።+ 26 በላይዋ ላይ ያለስጋት ይቀመጣሉ፤+ ቤቶችንም ይሠራሉ፤ ወይንንም ይተክላሉ፤+ ደግሞም በዙሪያቸው ባሉት በሚንቋቸው ሁሉ ላይ የፍርድ እርምጃ በምወስድበት ጊዜ ያለስጋት ይኖራሉ፤+ እኔም አምላካቸው ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”’”
29 በአሥረኛው ዓመት፣ በአሥረኛው ወር፣ ከወሩም በ12ኛው ቀን የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ፈርዖን አዙረህ በእሱና በመላዋ ግብፅ ላይ ትንቢት ተናገር።+ 3 እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
አንተ ግዙፍ የባሕር ፍጥረት፣ የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን፣ በአንተ ላይ ተነስቻለሁ።+
4 በመንጋጋህ መንጠቆ አስገባለሁ፤ በአባይ ወንዝህ ውስጥ ያሉት ዓሣዎች ከቅርፊትህ ጋር እንዲጣበቁ አደርጋለሁ።
ቅርፊትህ ላይ ከተጣበቁት የአባይ ዓሣዎች ሁሉ ጋር ከአባይ ወንዝህ መካከል አወጣሃለሁ።
5 አንተንም ሆነ በአባይ ወንዝህ ውስጥ ያሉትን ዓሣዎች ሁሉ በረሃ ላይ እጥላለሁ።
አውላላ ሜዳ ላይ ትወድቃለህ፤ የሚሰበስብህም ሆነ የሚያነሳህ አይኖርም።+
ለምድር አራዊትና ለሰማይ ወፎች መብል አድርጌ እሰጥሃለሁ።+
7 እጅህን ሲይዙህ ተሰበርክ፤
ትከሻቸውንም ወጋህ።
8 “‘ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ ሰይፍ አመጣብሃለሁ፤+ በአንተ ዘንድ የሚገኘውን ሰውም ሆነ እንስሳ አጠፋለሁ። 9 የግብፅ ምድር ባድማና ወና ይሆናል፤+ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ፤ አንተ ‘የአባይ ወንዝ የእኔ ነው፤ የሠራሁት እኔ ነኝ’ ብለሃልና።*+ 10 ስለዚህ በአንተና በአባይ ወንዝህ ላይ ተነስቻለሁ፤ የግብፅንም ምድር ከሚግዶል+ እስከ ሰዌኔ+ ብሎም እስከ ኢትዮጵያ ድንበር ድረስ ባድማ፣ ደረቅና ወና አደርጋለሁ።+ 11 የሰው እግርም ሆነ የከብት ኮቴ አያልፍባትም፤+ ለ40 ዓመትም ማንም አይኖርባትም። 12 የግብፅን ምድር ከሌሎች አገሮች በከፋ ሁኔታ ባድማ አደርጋታለሁ፤ ከተሞቿም ከሌሎች ከተሞች በከፋ ሁኔታ ለ40 ዓመት ያህል ባድማ ይሆናሉ፤+ ግብፃውያንንም በብሔራት መካከል እበትናቸዋለሁ፤ በአገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ።”+
13 “‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “ከ40 ዓመት በኋላ ግብፃውያንን ከተበተኑባቸው ሕዝቦች መካከል እሰበስባቸዋለሁ፤+ 14 የተማረኩትን ግብፃውያን ወደ ትውልድ አገራቸው ወደ ጳትሮስ+ ምድር መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ በዚያም ደካማ መንግሥት ይሆናሉ። 15 ግብፅ ከሌሎቹ መንግሥታት ያነሰች ትሆናለች፤ ከእንግዲህ ሌሎች ብሔራትን አትጨቁንም፤+ ደግሞም በጣም ትንሽ ስለማደርጋቸው ሌሎች ብሔራትን መግዛት አይችሉም።+ 16 ግብፅ ለእስራኤል ቤት ዳግመኛ መታመኛ አትሆንም፤+ ይልቁንም ከግብፃውያን እርዳታ በመሻት ለሠሩት ስህተት መታሰቢያ ትሆናለች። እነሱም እኔ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”’”
17 በ27ኛው ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 18 “የሰው ልጅ ሆይ፣ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር*+ ሠራዊቱ በጢሮስ ላይ ታላቅ ግዳጅ እንዲፈጽም አደረገ።+ ራስ ሁሉ ተመልጧል፤ ትከሻም ሁሉ ተልጧል። ይሁን እንጂ እሱም ሆነ ሠራዊቱ በጢሮስ ላይ ላፈሰሱት ጉልበት ያገኙት ዋጋ የለም።
19 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ የግብፅን ምድር ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾር* እሰጣለሁ፤+ እሱም ሀብቷን ያግዛል፤ በእጅጉ ይበዘብዛል እንዲሁም ይመዘብራል፤ ይህም ለሠራዊቱ ደሞዝ ይሆናል።’
20 “‘በእሷ* ላይ ላፈሰሰው ጉልበት የግብፅን ምድር ካሳ አድርጌ እሰጠዋለሁ፤ ምክንያቱም ይህን ያደረጉት ለእኔ ነው’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
21 “በዚያ ቀን ለእስራኤል ቤት ቀንድ እንዲበቅል አደርጋለሁ፤*+ ለአንተም በእነሱ መካከል መናገር የምትችልበት አጋጣሚ እከፍትልሃለሁ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”
30 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“ዋይ ዋይ በሉ፤ ‘ቀኑ ስለቀረበ ወዮ!’
3 ቀኑ ቀርቧልና፤ አዎ፣ የይሖዋ ቀን ቀርቧል።+
የደመናት ቀን፣+ በብሔራትም ላይ የሚፈረድበት ቀን ይሆናል።+
4 ሰይፍ በግብፅ ላይ ይመጣል፤ የታረዱት በግብፅ ሲወድቁ፣
ሀብቷ ሲወሰድ እንዲሁም መሠረቶቿ ሲፈራርሱ ኢትዮጵያ በሽብር ትዋጣለች።+
6 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
‘ለግብፅ ድጋፍ የሚሰጡም ይወድቃሉ፤
የምትታበይበት ኃይሏም ይወገዳል።’+
“‘ከሚግዶል+ እስከ ሰዌኔ+ በምድሪቱ ላይ በሰይፍ ይወድቃሉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 7 ‘ከሌሎች አገሮች በከፋ ሁኔታ ባድማ ይሆናሉ፤ ከተሞቿም ከሌሎች ከተሞች በከፋ ሁኔታ ይወድማሉ።+ 8 በግብፅም ላይ እሳት በማነድበትና ተባባሪዎቿ ሁሉ በሚደቁበት ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። 9 በዚያን ቀን በራሷ የምትታመነውን ኢትዮጵያን ለማንቀጥቀጥ መልእክተኞችን በመርከብ እልካለሁ፤ ግብፅ በምትጠፋበት ቀን በሽብር ይዋጣሉ፤ ቀኑ በእርግጥ ይመጣልና።’
10 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ስፍር ቁጥር የሌለውን የግብፅ ሕዝብ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር* እጅ አጠፋለሁ።+ 11 ከብሔራት መካከል እጅግ ጨካኝ የሆኑት፣ እሱና ሠራዊቱ+ ምድሪቱን ለማውደም ይመጣሉ። እነሱም በግብፅ ላይ ሰይፋቸውን ይመዛሉ፤ ምድሪቱንም ሬሳ በሬሳ ያደርጋሉ።+ 12 የአባይን የመስኖ ቦዮች አደርቃለሁ፤+ ምድሪቱንም ለክፉ ሰዎች እሸጣለሁ። ምድሪቱና በውስጧ ያለው ሁሉ በባዕዳን እጅ እንዲጠፉ አደርጋለሁ።+ እኔ ይሖዋ ራሴ ይህን ተናግሬአለሁ።’
13 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አስጸያፊ የሆኑትንም ጣዖቶች* አጠፋለሁ፤ ከንቱ የሆኑትንም የኖፍ*+ አማልክት አስወግዳለሁ። ከእንግዲህ ከግብፅ ምድር የሚወጣ ገዢ* አይኖርም፤ በግብፅም ምድር ፍርሃት እሰዳለሁ።+ 14 ጳትሮስን+ ባድማ አደርጋለሁ፤ በጾዓን እሳት አነዳለሁ፤ ደግሞም በኖእ*+ ላይ የፍርድ እርምጃ እወስዳለሁ። 15 የግብፅ ምሽግ በሆነችው በሲን ላይ ቁጣዬን አፈስሳለሁ፤ የኖእንም ሕዝብ አጠፋለሁ። 16 በግብፅ ላይ እሳት አነዳለሁ፤ ሲን በሽብር ትዋጣለች፤ ኖእ ቅጥሯ ይፈርሳል፤ ኖፍ* ደግሞ በጠራራ ፀሐይ ጥቃት ይሰነዘርባታል! 17 የኦንና* የጲበሰት ወጣቶች በሰይፍ ይወድቃሉ፤ የከተሞቹም ነዋሪዎች በግዞት ይወሰዳሉ። 18 በዚያ የግብፅን ቀንበር በምሰብርበት ጊዜ በጣፍነስ ቀኑ ይጨልማል።+ የምትታበይበት ኃይሏ ይጠፋል፤+ ደመናት ይሸፍኗታል፤ የከተሞቿም ነዋሪዎች በግዞት ይወሰዳሉ።+ 19 በግብፅ ላይ የፍርድ እርምጃ እወስዳለሁ፤ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’”
20 በ11ኛውም ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በሰባተኛው ቀን፣ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 21 “የሰው ልጅ ሆይ፣ የግብፅን ንጉሥ የፈርዖንን ክንድ ሰብሬአለሁ፤ እንዲድን አይታሰርም፤ ወይም ጠንክሮ ሰይፍ እንዲይዝ በጨርቅ አይጠቀለልም።”
22 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ እኔ በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ላይ ተነስቻለሁ፤+ ብርቱውንና የተሰበረውን፣ ሁለቱንም ክንዶቹን እሰብራለሁ፤+ ሰይፉም ከእጁ ላይ እንዲወድቅ አደርጋለሁ።+ 23 ከዚያም ግብፃውያንን በብሔራት መካከል እበትናቸዋለሁ፤ በአገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ።+ 24 የባቢሎንን ንጉሥ ክንዶች አበረታለሁ፤*+ ሰይፌንም አስጨብጠዋለሁ፤+ የፈርዖንን ክንዶች እሰብራለሁ፤ እሱም ሊሞት እያጣጣረ እንዳለ ሰው በፊቱ* እጅግ ያቃስታል። 25 የባቢሎንን ንጉሥ ክንዶች አበረታለሁ፤ የፈርዖን ክንዶች ግን ይዝላሉ፤ ሰይፌንም ለባቢሎን ንጉሥ ሳስጨብጠውና በግብፅ ምድር ላይ ሲሰነዝረው እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።+ 26 ግብፃውያንንም በብሔራት መካከል እበትናቸዋለሁ፤ በአገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ፤+ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’”
31 በ11ኛው ዓመት፣ በሦስተኛው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖንና ስፍር ቁጥር ለሌለው ሕዝቡ እንዲህ በል፦+
‘በታላቅነትህ ከማን ጋር ትመሳሰላለህ?
3 አንድ አሦራዊ፣ በሊባኖስ ያደገ አርዘ ሊባኖስ ነበር፤
አርዘ ሊባኖሱ ጥላ እንደሚሰጡ ችፍግ ብለው ያደጉ ዛፎች፣ የሚያማምሩ ቅርንጫፎች ያሉት እጅግ ረጅም ዛፍ ሲሆን
ጫፉም ደመናትን ይነካ ነበር።
4 ውኃዎቹ ትልቅ ዛፍ እንዲሆን አደረጉት፤ ጥልቅ ከሆኑት ምንጮች የተነሳ ዛፉ በጣም ረጅም ሆነ።
በተተከለበት ቦታ ዙሪያ ጅረቶች ነበሩ፤
የውኃ መውረጃዎቻቸውም በሜዳ ያሉትን ዛፎች ሁሉ ያጠጡ ነበር።
5 ከዚህም የተነሳ ቁመቱ በሜዳ ካሉት ከሌሎቹ ዛፎች ሁሉ ረዘመ።
ብዙ ቅርንጫፎች አወጣ፤ ጅረቶቹ ብዙ ውኃ ስለነበራቸው
ቅርንጫፎቹ ረጃጅም ሆኑ።
6 የሰማይ ወፎች ሁሉ በቅርንጫፎቹ ላይ ጎጇቸውን ሠሩ፤
የዱር እንስሳትም ሁሉ ከቅርንጫፎቹ ሥር ግልገሎቻቸውን ወለዱ፤
ከጥላውም ሥር ብዙ ሕዝብ ያላቸው ብሔራት ሁሉ ሰፈሩ።
7 ከውበቱና ከቅርንጫፎቹ ርዝመት የተነሳ ግርማ ሞገስ ተላበሰ፤
ሥሮቹን ብዙ ውኃ ወዳለበት ስፍራ ሰዶ ነበርና።
8 በአምላክ የአትክልት ስፍራ+ ያሉ ሌሎች አርዘ ሊባኖሶች ሊተካከሉት አልቻሉም።
ከጥድ ዛፎች መካከል የእሱ ዓይነት ቅርንጫፎች ያሉት አንድም ዛፍ የለም፤
የአርሞን ዛፎችም* ከእሱ ቅርንጫፎች ጋር ሊወዳደሩ አይችሉም።
በአምላክ የአትክልት ስፍራ ያለ የትኛውም ዛፍ በውበቱ አይወዳደረውም።
9 ብዙ ቅጠሎች ያሉት ውብ ዛፍ አድርጌ ሠራሁት፤
በእውነተኛው አምላክ የአትክልት ስፍራ በኤደን ያሉ ሌሎች ዛፎችም ሁሉ ቀኑበት።’
10 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ቁመቱ* እጅግ ከመርዘሙ የተነሳ ጫፉን በደመናት መካከል ከፍ ስላደረገና በቁመቱ የተነሳ ልቡ ስለታበየ፣ 11 ኃያል ለሆነ የብሔራት ገዢ አሳልፌ እሰጠዋለሁ።+ እሱም በእርግጥ ይነሳበታል፤ በክፋቱም የተነሳ እጥለዋለሁ። 12 ከብሔራት መካከል እጅግ ጨካኝ የሆኑት ባዕዳን ቆርጠው ይጥሉታል፤ በተራሮችም ላይ ጥለውት ይሄዳሉ፤ ቅጠሎቹም በየሸለቆው ይረግፋሉ፤ ቅርንጫፎቹም በምድሪቱ ላይ ባሉ ጅረቶች ሁሉ ላይ ተሰባብረው ይወድቃሉ።+ የምድር ሕዝቦች ሁሉ ከጥላው ሥር ወጥተው ትተውት ይሄዳሉ። 13 የሰማይ ወፎች ሁሉ በወደቀው ግንዱ ላይ ይሰፍራሉ፤ የዱር እንስሳትም ሁሉ በቅርንጫፎቹ ላይ ይኖራሉ።+ 14 ይህም የሚሆነው በውኃዎች አጠገብ ካሉ ዛፎች መካከል አንዳቸውም ቁመታቸው በጣም እንዳይረዝም ወይም ጫፋቸውን በደመናት መካከል ከፍ እንዳያደርጉ እንዲሁም ውኃ የጠገበ አንድም ዛፍ ቁመቱ እነሱ ጋ እንዳይደርስ ነው። ሁሉም ለሞት ይዳረጋሉና፤ ወደ ጉድጓድ* ከሚወርዱት የሰው ልጆች ጋር በአንድነት ከምድር በታች ይወርዳሉ።’
15 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ወደ መቃብር* በሚወርድበት ቀን ሰዎች እንዲያዝኑ አደርጋለሁ። ስለዚህ ጥልቅ የሆኑትን ውኃዎች እሸፍናለሁ፤ ጅረቶቹንም እገታለሁ፤ ይህም በገፍ የሚፈስሱት ውኃዎች ይቋረጡ ዘንድ ነው። ከእሱ የተነሳ ሊባኖስን አጨልማለሁ፤ በሜዳም ያሉ ዛፎች ሁሉ ይጠወልጋሉ። 16 ወደ ጉድጓድ* ከሚወርዱት ሁሉ ጋር ወደ መቃብር* በማወርደው ጊዜ ሲወድቅ በሚሰማው ድምፅ ብሔራት እንዲናወጡ አደርጋለሁ፤ ከምድርም በታች የኤደን ዛፎች ሁሉ፣+ ምርጥና ግሩም የሆኑት የሊባኖስ ዛፎች ሁሉ እንዲሁም ውኃ የጠገቡት ዛፎች ሁሉ ይጽናናሉ። 17 ከእሱ ጋር እንዲሁም በብሔራት መካከል በጥላው ሥር ይኖሩ ከነበሩት ደጋፊዎቹ* ጋር በሰይፍ የታረዱት ወዳሉበት ወደ መቃብር* ወርደዋል።’+
18 “‘በኤደን ካሉት ዛፎች መካከል የአንተ ዓይነት ክብርና ታላቅነት ያለው የትኛው ነው?+ ይሁንና ከኤደን ዛፎች ጋር ከምድር በታች ትወርዳለህ። ባልተገረዙት መካከል፣ በሰይፍ ከታረዱት ጋር ትጋደማለህ። ይህ በፈርዖንና ስፍር ቁጥር በሌለው ሕዝቡ ላይ ይፈጸማል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
32 በ12ኛውም ዓመት፣ በ12ኛው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ስለ ግብፅ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ሙሾ አውርድ፤* እንዲህም በለው፦
‘በብሔራት መካከል እንደ ብርቱ ደቦል አንበሳ ነበርክ፤
አሁን ግን አክትሞልሃል።
3 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
‘በብዙ ብሔራት ጉባኤ አማካኝነት መረቤን በአንተ ላይ እዘረጋለሁ፤
እነሱም በማጥመጃ መረቤ ጎትተው ያወጡሃል።
4 በምድር ላይ እተውሃለሁ፤
አውላላ ሜዳ ላይ እጥልሃለሁ።
የሰማይ ወፎች ሁሉ በአንተ ላይ እንዲሰፍሩ አደርጋለሁ፤
በመላው ምድር የሚገኙትን የዱር እንስሳትም በአንተ አጠግባለሁ።+
5 ሥጋህን በተራሮች ላይ እጥላለሁ፤
ከሬሳህ በተረፉት ነገሮችም ሸለቆዎቹን እሞላለሁ።+
6 ምድሪቷ እስከ ተራሮች ድረስ በሚፈሰው ደምህ እንድትርስ አደርጋለሁ፤
ጅረቶችም በደምህ ይሞላሉ።’*
7 ‘አንተም በምትጠፋበት ጊዜ ሰማያትን እሸፍናለሁ፤ ከዋክብታቸውንም አጨልማለሁ።
ፀሐይን በደመና እሸፍናለሁ፤
ጨረቃም ብርሃኗን አትፈነጥቅም።+
8 በሰማያት ያሉትን ብርሃን ሰጪ አካላት ሁሉ ከአንተ የተነሳ አጨልማቸዋለሁ፤
ምድርህንም ጨለማ አለብሳለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
9 ‘ከአንተ የተማረኩትን ወደ ሌሎች ብሔራት ይኸውም ወደማታውቃቸው አገሮች በምወስድበት ጊዜ+
የብዙ ሰዎችን ልብ አስጨንቃለሁ።
10 ብዙ ሕዝቦች እንዲደነግጡ አደርጋለሁ፤
ሰይፌንም በፊታቸው ሳወዛውዝ ከአንተ የተነሳ ንጉሦቻቸው በፍርሃት ይርዳሉ።
አንተ በምትወድቅበት ቀን
እያንዳንዳቸው ለሕይወታቸው በመፍራት ያለማቋረጥ ይንቀጠቀጣሉ።’
11 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦
‘የባቢሎን ንጉሥ ሰይፍ ይመጣብሃል።+
12 ስፍር ቁጥር የሌለው ሕዝብህ በኃያላን ተዋጊዎች ሰይፍ እንዲወድቅ አደርጋለሁ፤
ሁሉም ከብሔራት መካከል እጅግ ጨካኞች ናቸው።+
እነሱም የግብፅን ኩራት ያንኮታኩታሉ፤ ስፍር ቁጥር የሌለው ሕዝቧም ሁሉ ይደመሰሳል።+
14 ‘በዚያን ጊዜ ውኃዎቻቸውን አጠራለሁ፤
ወንዞቻቸውም እንደ ዘይት እንዲፈስሱ አደርጋለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
15 ‘ግብፅን ባድማና ወና በማድረግ ምድሪቱን የሞላውን ነገር ሁሉ በማስወግድበት ጊዜ፣+
ነዋሪዎቿንም ሁሉ በምመታበት ጊዜ
እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።+
16 ይህ ሙሾ ነው፤ ሰዎችም ያንጎራጉሩታል፤
የብሔራት ሴቶች ልጆች ያንጎራጉሩታል።
በግብፅና ስፍር ቁጥር በሌለው ሕዝቧ ሁሉ የተነሳ ያንጎራጉሩታል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
17 ከዚያም በ12ኛው ዓመት፣ ከወሩም በ15ኛው ቀን፣ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 18 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ስፍር ቁጥር ለሌለው የግብፅ ሕዝብ ዋይ ዋይ በል፤ እሷንና የኃያላን ብሔራትን ሴቶች ልጆች ወደ ጉድጓድ* ከሚወርዱት ጋር ከምድር በታች አውርዳቸው።
19 “‘በውበት ማንን ትበልጣለህ? ወደ ታች ውረድ፤ ካልተገረዙትም ጋር ተጋደም!’
20 “‘በሰይፍ በታረዱት መካከል ይወድቃሉ።+ እሷ ለሰይፍ ተሰጥታለች፤ እሷንም ሆነ ስፍር ቁጥር የሌለውን ሕዝቧን ሁሉ ጎትቱ።
21 “‘ኃያላኑ ተዋጊዎች እሱንና ረዳቶቹን ከጥልቅ መቃብር* ውስጥ ያነጋግሯቸዋል። እነሱ በእርግጥ ወደ ታች ይወርዳሉ፤ ደግሞም በሰይፍ ታርደው፣ እንዳልተገረዙት ሰዎች ይጋደማሉ። 22 አሦር ከመላ ጉባኤዋ ጋር በዚያ ትገኛለች። መቃብሮቻቸው በእሱ ዙሪያ ናቸው፤ ሁሉም በሰይፍ ወድቀዋል።+ 23 መቃብሮቿ በጥልቅ ጉድጓድ* ውስጥ ይገኛሉ፤ ጉባኤዋም በመቃብሯ ዙሪያ አለ፤ ሁሉም በሰይፍ ተመትተው ወድቀዋል፤ ምክንያቱም በሕያዋን ምድር ሽብር ፈጥረው ነበር።
24 “‘ኤላም+ ስፍር ቁጥር ከሌለው ሕዝቧ ሁሉ ጋር በመቃብሯ ዙሪያ ትገኛለች፤ ሁሉም በሰይፍ ወድቀዋል። በሕያዋን ምድር ሽብር የፈጠሩት እነዚህ ሰዎች ሳይገረዙ ከምድር በታች ወርደዋል። ወደ ጉድጓድ* ከሚወርዱት ጋር ኀፍረታቸውን ይከናነባሉ። 25 በመቃብሯ ዙሪያ ከሚገኘው ስፍር ቁጥር የሌለው ሕዝቧ ሁሉ ጋር፣ በታረዱት መካከል መኝታ አዘጋጅተውላታል። ሁሉም ያልተገረዙና በሰይፍ የታረዱ ናቸው፤ ምክንያቱም በሕያዋን ምድር ሽብር ፈጥረው ነበር፤ ወደ ጉድጓድ* ከሚወርዱት ጋር ኀፍረታቸውን ይከናነባሉ። እሱ በታረዱት መካከል እንዲቀመጥ ተደርጓል።
26 “‘መሼቅና ቱባል+ እንዲሁም ስፍር ቁጥር የሌለው ሕዝባቸው ሁሉ* በዚያ ይገኛሉ። መቃብሮቻቸው* በዙሪያው ናቸው። ሁሉም ያልተገረዙና በሰይፍ የተወጉ ናቸው፤ ምክንያቱም በሕያዋን ምድር ሽብር ፈጥረዋል። 27 እነሱ፣ ከወደቁትና ከጦር መሣሪያዎቻቸው ጋር ወደ መቃብር* ከወረዱት ያልተገረዙ ኃያላን ተዋጊዎች ጋር ይጋደሙ የለም? ሰይፎቻቸውን ከራሳቸው በታች ያደርጋሉ፤* በኃጢአታቸውም የተነሳ የሚደርስባቸው ቅጣት በአጥንታቸው ላይ ይሆናል፤ ምክንያቱም እነዚህ ኃያላን ተዋጊዎች የሕያዋንን ምድር አሸብረዋል። 28 አንተ ግን ባልተገረዙት መካከል ትደቅቃለህ፤ በሰይፍ ከታረዱትም ጋር ትጋደማለህ።
29 “‘ኤዶም፣+ ነገሥታቷና አለቆቿ ሁሉ በዚያ ይገኛሉ፤ ኃያላን ሆነው ሳለ በሰይፍ በታረዱት መካከል ተጋድመዋል፤ እነሱም ካልተገረዙትና+ ወደ ጉድጓድ* ከሚወርዱት ጋር ይጋደማሉ።
30 “‘የሰሜን ገዢዎች* በሙሉ ከሲዶናውያን+ ሁሉ ጋር በዚያ ይገኛሉ፤ ኃይላቸው ሽብር የፈጠረ ቢሆንም ከታረዱት ሰዎች ጋር ኀፍረት ተከናንበው ወርደዋል። በሰይፍ ከታረዱት ጋር ሳይገረዙ ይጋደማሉ፤ ወደ ጉድጓድ* ከሚወርዱትም ጋር ኀፍረታቸውን ይከናነባሉ።
31 “‘ፈርዖን እነዚህን ሁሉ ነገሮች ይመለከታል፤ ደግሞም ስፍር ቁጥር በሌለው ሕዝቡ ላይ ከደረሰው ነገር ሁሉ ይጽናናል፤+ ፈርዖንና ሠራዊቱ ሁሉ በሰይፍ ይታረዳሉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
32 “‘በሕያዋን ምድር ሽብር ስለፈጠረ ፈርዖንና ስፍር ቁጥር የሌለው ሕዝቡ ሁሉ በሰይፍ ከታረዱት፣ ካልተገረዙት ሰዎች ጋር ለማረፍ ይጋደማሉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
33 የይሖዋም ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ለሕዝብህ ልጆች ተናገር፤+ እንዲህም በላቸው፦
“‘በአንድ አገር ላይ ሰይፍ አመጣሁ እንበል፤+ በዚህ ጊዜ የአገሪቱ ሕዝብ ሁሉ አንድ ሰው በመምረጥ ጠባቂ አድርጎ ሾመው፤ 3 እሱም በአገሪቱ ላይ ሰይፍ ሲመጣ አይቶ ቀንደ መለከት በመንፋት ሕዝቡን አስጠነቀቀ።+ 4 አንድ ሰው የቀንደ መለከቱን ድምፅ ሰምቶ ማስጠንቀቂያውን ተግባራዊ ሳያደርግ ቢቀር፣+ ሰይፍም መጥቶ ሕይወቱን ቢያጠፋ፣* ደሙ በገዛ ራሱ ላይ ይሆናል።+ 5 የቀንደ መለከቱን ድምፅ ቢሰማም ማስጠንቀቂያውን ተግባራዊ አላደረገም። ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል። ቢጠነቀቅ ኖሮ ሕይወቱ* በተረፈ ነበር።
6 “‘ነገር ግን ጠባቂው ሰይፍ ሲመጣ አይቶ ቀንደ መለከት ባይነፋና+ ሕዝቡን ባያስጠነቅቅ፣ ሰይፍም መጥቶ ከመካከላቸው የአንዱን ሰው ሕይወት* ቢያጠፋ፣ ይህ ሰው በገዛ በደሉ ይሞታል፤ ደሙን ግን ከጠባቂው እጅ እሻለሁ።’*+
7 “የሰው ልጅ ሆይ፣ አንተን ለእስራኤል ቤት ጠባቂ አድርጌ ሾሜሃለሁ፤ ከአፌ የሚወጣውንም ቃል ስትሰማ ማስጠንቀቂያዬን ንገራቸው።+ 8 ክፉውን ሰው ‘አንተ ክፉ ሰው፣ በእርግጥ ትሞታለህ!’ ባልኩት ጊዜ፣+ ክፉውን ሰው አካሄዱን እንዲያስተካክል ባታስጠነቅቀው፣ እሱ ክፉ በመሆኑ ከሠራው በደል የተነሳ ይሞታል፤+ ደሙን ግን ከአንተ እጅ እሻዋለሁ። 9 ሆኖም ክፉውን ሰው ከመንገዱ እንዲመለስ አስጠንቅቀኸው አካሄዱን ለማስተካከል ፈቃደኛ ባይሆን፣ እሱ በሠራው በደል ይሞታል፤+ አንተ ግን የገዛ ሕይወትህን* በእርግጥ ታድናለህ።+
10 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፦ ‘እናንተ እንዲህ ብላችኋል፦ “ዓመፃችንና ኃጢአታችን እጅግ ከብዶናል፤ በዚህም የተነሳ እየመነመንን ሄደናል፤+ ታዲያ እንዴት በሕይወት መቀጠል እንችላለን?”’+ 11 እንዲህ በላቸው፦ ‘“በሕያውነቴ እምላለሁ” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ “በክፉው ሰው ሞት ደስ አልሰኝም፤+ ይልቁንም ክፉው ሰው አካሄዱን አስተካክሎ+ በሕይወት እንዲኖር እፈልጋለሁ።+ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ተመለሱ፤ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤+ ለምን ትሞታላችሁ?”’+
12 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ ለሕዝብህ ልጆች እንዲህ በላቸው፦ ‘ጻድቁ ሰው በሚያምፅበት ጊዜ ጽድቁ አያድነውም፤+ ክፉውም ሰው ከክፋቱ በሚመለስበት ጊዜ በክፋቱ አይሰናከልም፤+ ደግሞም ጻድቅ የሆነ ማንኛውም ሰው ኃጢአት በሚሠራበት ቀን በጽድቁ በሕይወት ሊኖር አይችልም።+ 13 ጻድቁን ሰው “በእርግጥ በሕይወት ትኖራለህ” ባልኩት ጊዜ በገዛ ጽድቁ ታምኖ መጥፎ* ነገር ቢፈጽም፣+ ከጽድቅ ሥራው መካከል አንዱም አይታሰብም፤ ይልቁንም መጥፎ ነገር በመፈጸሙ ይሞታል።+
14 “‘እንዲሁም ክፉውን ሰው “በእርግጥ ትሞታለህ” ባልኩት ጊዜ ከኃጢአቱ ቢመለስና ፍትሐዊና ጽድቅ የሆነ ነገር ቢያደርግ፣+ 15 ደግሞም ክፉው ሰው መያዣ አድርጎ የወሰደውን ቢመልስ፣+ የሰረቀውን መልሶ ቢሰጥና+ መጥፎ ነገር ከመፈጸም ተቆጥቦ ሕይወት የሚያስገኙትን ደንቦች ቢከተል፣ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል።+ ፈጽሞ አይሞትም። 16 ከሠራቸው ኃጢአቶች ውስጥ አንዱም አይታወስበትም።*+ ፍትሕና ጽድቅ የሆነውን ነገር ስላደረገ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል።’+
17 “ይሁንና ወገኖችህ ፍትሐዊ ያልሆነው የእነሱ መንገድ ሆኖ ሳለ ‘የይሖዋ መንገድ ፍትሐዊ አይደለም’ ብለዋል።
18 “ጻድቅ ሰው ጽድቅ ማድረጉን ቢተውና መጥፎ ነገር ቢፈጽም፣ በዚህ የተነሳ ይሞታል።+ 19 ሆኖም ክፉ ሰው ከክፋቱ ቢመለስና ፍትሐዊና ጽድቅ የሆነ ነገር ቢያደርግ፣ ይህን በማድረጉ በሕይወት ይኖራል።+
20 “ይሁንና እናንተ ‘የይሖዋ መንገድ ፍትሐዊ አይደለም’ ብላችኋል።+ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ በእያንዳንዳችሁ ላይ እንደ መንገዳችሁ እፈርድባችኋለሁ።”
21 ከረጅም ጊዜ በኋላ ይኸውም በተማረክን በ12ኛው ዓመት፣ በአሥረኛው ወር፣ ከወሩም በአምስተኛው ቀን ከኢየሩሳሌም ያመለጠ ሰው ወደ እኔ መጥቶ+ “ከተማዋ ተመታች!” አለኝ።+
22 ያመለጠው ሰው ከመምጣቱ በፊት በነበረው ምሽት የይሖዋ እጅ በእኔ ላይ ነበረች፤ ሰውየው ጠዋት ወደ እኔ ከመምጣቱ በፊት፣ አምላክ አፌን ከፈተልኝ። እኔም አፌ ተከፍቶ በድጋሚ መናገር ቻልኩ።+
23 ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 24 “የሰው ልጅ ሆይ፣ በእነዚህ የፈራረሱ ቦታዎች የሚኖሩ ሰዎች+ ስለ እስራኤል ምድር እንዲህ በማለት ይናገራሉ፦ ‘አብርሃም አንድ ራሱ ብቻ ነበር፤ ይሁንና ምድሪቱን ወረሰ።+ እኛ ግን ብዙ ነን፤ በእርግጥ ምድሪቱ ርስት ሆና ተሰጥታናለች።’
25 “ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሥጋውን ከነደሙ ትበላላችሁ፤+ ዓይኖቻችሁን አስጸያፊ ወደሆኑት ጣዖቶቻችሁ* ታነሳላችሁ፤ ደምም ታፈሳላችሁ።+ ታዲያ ምድሪቱን ልትወርሱ ይገባችኋል? 26 በሰይፋችሁ ታምናችኋል፤+ አስጸያፊ ልማዶች ትፈጽማላችሁ፤ እያንዳንዳችሁም የባልንጀራችሁን ሚስት አርክሳችኋል።+ ታዲያ ምድሪቱን ልትወርሱ ይገባችኋል?”’+
27 “አንተም እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በሕያውነቴ እምላለሁ፤ በፈራረሱት ቦታዎች የሚኖሩት ሰዎች በሰይፍ ይወድቃሉ፤ አውላላ ሜዳ ላይ ያሉትንም ለዱር አራዊት መብል አድርጌ እሰጣቸዋለሁ፤ በምሽጎችና በዋሻዎች ውስጥ ያሉትም በበሽታ ይሞታሉ።+ 28 ምድሪቱን ፈጽሞ ባድማ አደርጋታለሁ፤+ ከልክ ያለፈ ኩራቷም ይጠፋል፤ የእስራኤልም ተራሮች ባድማ ይሆናሉ፤+ የሚያልፍባቸውም አይኖርም። 29 ደግሞም በፈጸሟቸው አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ የተነሳ+ ምድሪቱን ፈጽሞ ባድማ በማደርግበት ጊዜ+ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”’
30 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ወገኖችህ በየግድግዳው ሥርና በየቤቱ በራፍ ላይ ሆነው እርስ በርሳቸው ስለ አንተ ይነጋገራሉ።+ አንዱ ሌላውን፣ እያንዳንዱም ወንድሙን፣ ‘ና፣ ከይሖዋ የመጣውን ቃል እንስማ’ ይለዋል። 31 እንደ ሕዝቤ በፊትህ ለመቀመጥ ተሰብስበው ወደ አንተ ይመጣሉ፤ ቃልህን ይሰማሉ፤ ሆኖም በተግባር አያውሉትም።+ በአፋቸው ይሸነግሉሃልና፤* ልባቸው ግን አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ይስገበገባል። 32 እነሆ፣ አንተ ለእነሱ ባማረ ድምፅ እንደሚዘፈንና በባለ አውታር መሣሪያ አሳምረው እንደሚጫወቱት የፍቅር ዘፈን ሆነህላቸዋል። ቃልህን ይሰማሉ፤ ሆኖም አንዳቸውም አያደርጉትም። 33 ይህ በሚፈጸምበት ጊዜ፣ ደግሞም ይፈጸማል፣ በመካከላቸው ነቢይ እንደነበረ ያውቃሉ።”+
34 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ በእስራኤል እረኞች ላይ ትንቢት ተናገር። ትንቢት ተናገር፤ እረኞቹንም እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ራሳቸውን ለሚመግቡ የእስራኤል እረኞች ወዮላቸው!+ እረኞቹ ሊመግቡ የሚገባው መንጋውን አይደለም?+ 3 ጮማውን ትበላላችሁ፤ ሱፉን ትለብሳላችሁ፤ የሰባውንም እንስሳ ታርዳላችሁ፤+ መንጋውን ግን አትመግቡም።+ 4 የደከመውን አላበረታችሁም፣ የታመመውን አልፈወሳችሁም፣ የተጎዳውን በጨርቅ አላሰራችሁትም፣ የባዘኑትን መልሳችሁ አላመጣችሁም ወይም የጠፋውን አልፈለጋችሁም፤+ ከዚህ ይልቅ በጭካኔና በግፍ ገዛችኋቸው።+ 5 በጎቹ እረኛ በማጣታቸው ተበታተኑ፤+ ተበታትነው ለዱር አራዊት ሁሉ መብል ሆኑ። 6 በጎቼ በየተራራውና ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ባዘኑ፤ በምድር ሁሉ ላይ ተበተኑ፤ የፈለጋቸው ወይም እነሱን ለማግኘት የጣረ አንድም ሰው የለም።
7 “‘“ስለዚህ እናንተ እረኞች፣ የይሖዋን ቃል ስሙ፦ 8 ‘“በሕያውነቴ እምላለሁ” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ “በጎቼ እረኛ ስላጡና እረኞቼ በጎቼን ስላልፈለጉ፣ ይልቁንም እረኞቹ ራሳቸውን ስለመገቡና በጎቼን ስላልመገቡ፣ በጎቼ ለአደን ተዳርገዋል፤ ለዱር አራዊትም ሁሉ መብል ሆነዋል፤”’ 9 ስለዚህ እናንተ እረኞች፣ የይሖዋን ቃል ስሙ። 10 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እኔ በእረኞቹ ላይ ተነስቻለሁ፤ ስለ በጎቼ እጠይቃቸዋለሁ፤* በጎቼን እንዳያሰማሩም* እከለክላቸዋለሁ፤+ እረኞቹም ከእንግዲህ ራሳቸውን አይመግቡም። በጎቼን ከአፋቸው አስጥላለሁ፤ ከእንግዲህ ለእነሱ መብል አይሆኑም።’”
11 “‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “እነሆኝ፣ እኔ ራሴ በጎቼን እፈልጋለሁ፤ ደግሞም እንከባከባቸዋለሁ።+ 12 የተበታተኑትን በጎቹን አግኝቶ እንደሚመግብ እረኛ በጎቼን እንከባከባለሁ።+ በደመናትና በድቅድቅ ጨለማ ቀን ከተበተኑባቸው ቦታዎች ሁሉ እታደጋቸዋለሁ።+ 13 ከሕዝቦች መካከል አወጣቸዋለሁ፤ ከየአገሩም እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደ ምድራቸውም አመጣቸዋለሁ፤ በእስራኤል ተራሮች፣ በየጅረቱ ዳርና በምድሪቱ ላይ በሚገኙት መኖሪያ ስፍራዎች ሁሉ አሰማራቸዋለሁ።+ 14 ጥሩ በሆነ መስክ ላይ አሰማራቸዋለሁ፤ ከፍ ያሉት የእስራኤል ተራሮችም የግጦሽ መሬት ይሆኗቸዋል።+ በዚያም ጥሩ በሆነ የግጦሽ መሬት ላይ ያርፋሉ፤+ በእስራኤልም ተራሮች ላይ በለመለመ መስክ ይሰማራሉ።”
15 “‘“በጎቼን እኔ ራሴ አሰማራለሁ፤+ እኔ ራሴም አሳርፋቸዋለሁ”+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 16 “የጠፋውን እፈልጋለሁ፤+ የባዘነውን መልሼ አመጣለሁ፤ የተጎዳውን በጨርቅ አስራለሁ፤ የደከመውን አበረታለሁ፤ የወፈረውንና ጠንካራ የሆነውን ግን አጠፋለሁ። እፈርድበታለሁ፤ ተገቢውንም ቅጣት እሰጠዋለሁ።”
17 “‘በጎቼ ስለሆናችሁት ስለ እናንተ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በበግና በበግ መካከል እንዲሁም በአውራ በጎችና በአውራ ፍየሎች መካከል ልፈርድ ነው።+ 18 እናንተ ምርጥ ከሆነው የግጦሽ ስፍራ መመገባችሁ አነሳችሁ? የቀሩትን የግጦሽ ስፍራዎች ደግሞ በእግራችሁ መረጋገጥ ይገባችኋል? እጅግ የጠራውን ውኃ ከጠጣችሁ በኋላስ ውኃውን በእግራችሁ እየመታችሁ ማደፍረሳችሁ ተገቢ ነው? 19 ታዲያ በጎቼ በእግራችሁ በረጋገጣችሁት የግጦሽ መስክ ላይ መሰማራትና በእግራችሁ እየመታችሁ ያደፈረሳችሁትን ውኃ መጠጣት ይኖርባቸዋል?”
20 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላቸዋል፦ “እነሆኝ፣ እኔ ራሴ በሰባው በግና ከሲታ በሆነው በግ መካከል እፈርዳለሁ፤ 21 እናንተ የታመሙት ሁሉ በየአቅጣጫው እስኪበታተኑ ድረስ በጎናችሁና በትከሻችሁ ገፍታችኋቸዋልና፤ በቀንዳችሁም ገፍትራችኋቸዋል። 22 በጎቼንም አድናለሁ፤ እነሱም ከእንግዲህ ለአደን አይዳረጉም፤+ እኔም በበግና በበግ መካከል እፈርዳለሁ። 23 በእነሱ ላይ አንድ እረኛ ይኸውም አገልጋዬን ዳዊትን* አስነሳለሁ፤+ እሱም ይመግባቸዋል። እሱ ራሱ ያሰማራቸዋል፤ እረኛቸውም ይሆናል።+ 24 ደግሞም እኔ ይሖዋ አምላካቸው እሆናለሁ፤+ አገልጋዬ ዳዊት ደግሞ በመካከላቸው አለቃ ይሆናል።+ እኔ ይሖዋ ራሴ ተናግሬአለሁ።
25 “‘“ከእነሱም ጋር የሰላም ቃል ኪዳን እገባለሁ፤+ አደገኛ የሆኑ የዱር አራዊትንም ከምድሪቱ ላይ አጠፋለሁ፤+ በመሆኑም በምድረ በዳ ያለስጋት ይኖራሉ፤ በጫካዎችም ውስጥ ይተኛሉ።+ 26 እነሱንና በኮረብታዬ ዙሪያ ያለውን ቦታ በረከት አደርጋቸዋለሁ፤+ ዝናብም በወቅቱ እንዲዘንብ አደርጋለሁ። በረከት እንደ ዝናብ ይወርዳል።+ 27 የሜዳው ዛፎች ፍሬያቸውን ይሰጣሉ፤ መሬቱም ፍሬ ይሰጣል፤+ እነሱም በምድሪቱ ላይ ያለስጋት ይቀመጣሉ። ቀንበራቸውን በምሰብርበትና ባሪያ አድርገው ከሚገዟቸው እጅ በማድናቸው ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።+ 28 ከእንግዲህ ወዲህ ብሔራት እነሱን ለማደን አይነሱም፤ የምድር አራዊትም አይበሏቸውም፤ ያለስጋትም ይኖራሉ፤ የሚያስፈራቸውም የለም።+
29 “‘“ዝና የሚያስገኝ* የእርሻ ቦታ እሰጣቸዋለሁ፤ ከእንግዲህ በምድሪቱ ላይ በረሃብ አያልቁም፤+ ደግሞም ከእንግዲህ ወዲህ ብሔራት አያዋርዷቸውም።+ 30 ‘በዚህ ጊዜ እኔ አምላካቸው ይሖዋ ከእነሱ ጋር እንደሆንኩና እነሱ ይኸውም የእስራኤል ቤት ሕዝቤ እንደሆኑ ያውቃሉ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”’
31 “‘እናንተ በጎቼ፣+ የምንከባከባችሁ በጎች፣ ከአፈር የተሠራችሁ ሰዎች ናችሁ፤ እኔም አምላካችሁ ነኝ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
35 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን ተራራማ ወደሆነው የሴይር+ ምድር አዙረህ በእሱ ላይ ትንቢት ተናገር።+ 3 እንዲህም በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የሴይር ተራራማ ምድር ሆይ፣ እነሆ በአንተ ላይ ተነስቻለሁ፤ እጄን በአንተ ላይ እዘረጋለሁ፤ ባድማና ወና አደርግሃለሁ።+ 4 ከተሞችህን አፈራርሳለሁ፤ አንተም ባድማና ወና ትሆናለህ፤+ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃለህ። 5 የእስራኤል ልጆች ጥፋት በደረሰባቸውና የመጨረሻውን ቅጣት በተቀበሉበት ጊዜ የማያባራ የጠላትነት ስሜት በማሳየት+ ለሰይፍ አሳልፈህ ሰጥተሃቸዋልና።”’+
6 “‘ስለዚህ በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ለእርድ አዘጋጅሃለሁ፤ ደምህም ይፈስሳል።+ ደም ጠልተህ ስለነበር ደምህ ይፈስሳል።+ 7 የሴይርን ተራራማ ምድር ባድማና ወና አደርጋለሁ፤+ በዚያ የሚያልፈውንም ሆነ የሚመለሰውን ማንኛውንም ሰው አጠፋለሁ። 8 ተራሮቹን በታረዱ ሰዎች እሞላለሁ፤ በሰይፍ የታረዱት በኮረብቶችህ፣ በሸለቆዎችህና በጅረቶችህ ላይ ይወድቃሉ። 9 ለዘላለም ባድማ አደርግሃለሁ፤ ከተሞችህም ሰው አልባ ይሆናሉ፤+ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’
10 “ይሖዋ ራሱ በዚያ ቢኖርም እንኳ፣ አንተ ‘እነዚህ ሁለት ብሔራትና ሁለት አገሮች የእኔ ይሆናሉ፤ እኛም ሁለቱን አገሮች እንወርሳለን’+ ስላልክ፣ 11 ‘በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ለእነሱ ካደረብህ የጥላቻ ስሜት የተነሳ በእነሱ ላይ በገለጥከው በዚያው ዓይነት ቁጣና ቅናት እኔም እርምጃ እወስድብሃለሁ፤+ በአንተም ላይ በምፈርድበት ጊዜ በእነሱ መካከል ማንነቴ እንዲታወቅ አደርጋለሁ። 12 አንተ “ወና ሆነዋል፤ ለእኛም እንደ መብል ተሰጥተዋል” ባልክ ጊዜ በእስራኤል ተራሮች ላይ በንቀት የተናገርከውን ነገር ሁሉ እኔ ይሖዋ ራሴ እንደሰማሁ በዚያን ጊዜ ታውቃለህ።” 13 እናንተ በእኔ ላይ በእብሪት ተናግራችኋል፤ ደግሞም በእኔ ላይ ብዙ ነገር ተናግራችኋል።+ የተናገራችሁትን ሁሉ ሰምቻለሁ።’
14 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አንተን ባድማና ወና በማደርግበት ጊዜ መላዋ ምድር ሐሴት ታደርጋለች። 15 የእስራኤል ቤት ርስት ባድማ በሆነበት ጊዜ ስለተደሰትክ እኔም እንዲሁ አደርግብሃለሁ።+ የሴይር ተራራማ ምድር ሆይ፣ አንተም ሆንክ መላው የኤዶም ምድር ሙሉ በሙሉ ባድማ ትሆናላችሁ፤+ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’”
36 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ ስለ እስራኤል ተራሮች ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፦ ‘የእስራኤል ተራሮች ሆይ፣ የይሖዋን ቃል ስሙ። 2 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ጠላት ስለ እናንተ ‘እሰይ! የጥንቶቹ ከፍ ያሉ ቦታዎች ሳይቀሩ የእኛ ርስት ሆነዋል!’ ብሏል።”’+
3 “ስለዚህ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ከብሔራት መካከል ለተረፉት* ርስት እንድትሆኑ ባድማ ስላደረጓችሁና ከየአቅጣጫው ጥቃት ስለሰነዘሩባችሁ እንዲሁም ሰው አፍ ውስጥ ስለገባችሁና ሰዎች ስማችሁን ስላጠፉ፣+ 4 የእስራኤል ተራሮች ሆይ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ የተናገረውን ቃል ስሙ! ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ለተራሮችና ለኮረብቶች፣ ለጅረቶችና ለሸለቆዎች፣ ፈራርሰው ባድማ ለሆኑት ቦታዎችና+ በዙሪያቸው ባሉት ከጥፋት የተረፉ ብሔራት ለተበዘበዙት እንዲሁም መሳለቂያ ለሆኑት የተተዉ ከተሞች ይህን ቃል ተናግሯል፤+ 5 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እነሱን በተመለከተ እንዲህ ይላል፦ ‘የግጦሽ ቦታዎቿን ለመውሰድና ምድሪቱን ለመበዝበዝ ሲሉ በታላቅ ደስታና በከፍተኛ ንቀት*+ ምድሬን የገዛ ርስታቸው እንደሆነ አድርገው በተናገሩት፣ ከጥፋት በተረፉት ብሔራትና በመላዋ ኤዶም ላይ በቅንዓቴ እሳት+ እናገራለሁ።’”’+
6 “ስለዚህ ስለ እስራኤል ምድር ትንቢት ተናገር፤ ለተራሮችና ለኮረብቶች፣ ለጅረቶችና ለሸለቆዎች እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ ብሔራት ያደረሱባችሁን ውርደት ስለተሸከማችሁ በቅንዓቴና በቁጣዬ እናገራለሁ።”’+
7 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዙሪያችሁ ያሉት ብሔራት የገዛ ራሳቸውን ኀፍረት ይሸከማሉ ብዬ እጄን አንስቼ ምያለሁ።+ 8 የእስራኤል ተራሮች ሆይ፣ እናንተ ግን ለሕዝቤ ለእስራኤል ቅርንጫፍ ታወጣላችሁ፤ ፍሬም ታፈራላችሁ፤+ እነሱ በቅርቡ ይመለሳሉና። 9 እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ ፊቴንም ወደ እናንተ እመልሳለሁ፤ እናንተም ትታረሳላችሁ፤ ደግሞም ዘር ይዘራባችኋል። 10 ሕዝባችሁን ይኸውም መላውን የእስራኤል ቤት አበዛለሁ፤ ከተሞቹም የሰው መኖሪያ ይሆናሉ፤+ የፈራረሱትም ስፍራዎች ዳግመኛ ይገነባሉ።+ 11 አዎ፣ ሕዝባችሁንና ከብቶቻችሁን አበዛለሁ፤+ እነሱም ይበዛሉ፤ ፍሬያማም ይሆናሉ። እንደቀድሞው ዘመን ሰዎች እንዲኖሩባችሁ አደርጋለሁ፤+ ደግሞም ከበፊቱ የበለጠ አበለጽጋችኋለሁ፤+ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።+ 12 በእናንተ ላይ ሰዎች ይኸውም ሕዝቤ እስራኤል እንዲመላለሱ አደርጋለሁ፤ እነሱም ይወርሷችኋል።+ የእነሱ ርስት ትሆናላችሁ፤ ከእንግዲህ ልጅ አልባ አታደርጓቸውም።’”+
13 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘“ሰዎችን የምትበላና በላይዋ ያሉትን ብሔራት የወላድ መሃን የምታደርግ ምድር ናችሁ” ስለሚሏችሁ፣’ 14 ‘ከእንግዲህ ሰው አትበሉም ወይም በምድሪቱ ላይ ያሉትን ብሔራት ልጅ አልባ አታደርጉም’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 15 ‘ከእንግዲህ ብሔራት እናንተን እንዲሰድቡ ወይም ሰዎች የሚሰነዝሩባችሁን ዘለፋ እንድትሸከሙ አልፈቅድም፤+ ደግሞም በምድሪቱ ላይ ላሉት ብሔራት መሰናክል አትሆኑም’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
16 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 17 “የሰው ልጅ ሆይ፣ የእስራኤል ቤት ሰዎች በምድራቸው ላይ ይኖሩ በነበረበት ጊዜ በመንገዳቸውና በሥራቸው ምድሪቱን አረከሷት።+ መንገዳቸው በፊቴ እንደ ወር አበባ ርኩሰት ነበር።+ 18 በምድሪቱ ላይ ደም ስላፈሰሱና ምድሪቱን አስጸያፊ በሆኑ ጣዖቶቻቸው* ስላረከሱ+ ቁጣዬን አፈሰስኩባቸው።+ 19 ደግሞም በብሔራት መካከል በተንኳቸው፤ በየአገሩም ዘራኋቸው።+ እንደ መንገዳቸውና እንደ ሥራቸው ፈረድኩባቸው። 20 ሆኖም ወደ እነዚህ ብሔራት በመጡ ጊዜ ሰዎች ስለ እነሱ ‘እነዚህ የይሖዋ ሕዝብ ናቸው፤ ይሁን እንጂ ከእሱ ምድር ለመፈናቀል ተገደዱ’ እያሉ ቅዱስ ስሜን አረከሱ።+ 21 በመሆኑም የእስራኤል ቤት በሄዱባቸው ብሔራት መካከል ያረከሱት ቅዱስ ስሜ ያሳስበኛል።”+
22 “ስለዚህ ለእስራኤል ቤት ሰዎች እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ቤት ሰዎች ሆይ፣ እርምጃ የምወስደው ለእናንተ ብዬ ሳይሆን በሄዳችሁባቸው ብሔራት መካከል ላረከሳችሁት ቅዱስ ስሜ ስል ነው።”’+ 23 ‘በብሔራት መካከል የረከሰውን፣ ይኸውም በእነሱ መካከል ያረከሳችሁትን ታላቅ ስሜን በእርግጥ እቀድሰዋለሁ፤+ ዓይኖቻቸው እያዩ በመካከላችሁ በምቀደስበት ጊዜ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ብሔራት እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።+ 24 ከብሔራት መካከል አወጣችኋለሁ፤ ከየአገሩም ሁሉ ሰብስቤ ወደ ምድራችሁ አመጣችኋለሁ።+ 25 ንጹሕ ውኃ እረጫችኋለሁ፤ እናንተም ንጹሕ ትሆናላችሁ፤+ ከርኩሰታችሁ ሁሉና አስጸያፊ ከሆኑት ጣዖቶቻችሁ ሁሉ+ አነጻችኋለሁ።+ 26 አዲስ ልብ እሰጣችኋለሁ፤+ በውስጣችሁም አዲስ መንፈስ አሳድራለሁ።+ የድንጋይ ልባችሁን+ ከሰውነታችሁ አስወግጄ የሥጋ ልብ* እሰጣችኋለሁ። 27 መንፈሴን በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ በሥርዓቴም እንድትመላለሱ አደርጋለሁ፤+ ድንጋጌዎቼንም ትጠብቃላችሁ፣ በተግባርም ታውሏቸዋላችሁ። 28 በዚያን ጊዜ ለአባቶቻችሁ በሰጠኋት ምድር ላይ ትኖራላችሁ፤ ሕዝቤም ትሆናላችሁ፤ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ።’+
29 “‘ከርኩሰታችሁ ሁሉ አድናችኋለሁ፤ እህሉን እጠራዋለሁ፤ ደግሞም አበዛዋለሁ፤ ረሃብም አላመጣባችሁም።+ 30 በረሃብ የተነሳ በብሔራት መካከል ዳግመኛ ውርደት እንዳይደርስባችሁ፣ የዛፉን ፍሬና የእርሻውን ምርት አበዛለሁ።+ 31 በዚያን ጊዜ ክፉ መንገዳችሁንና መጥፎ ሥራችሁን ታስታውሳላችሁ፤ በበደላችሁና በምትፈጽሟቸው አስጸያፊ ልማዶች የተነሳ ራሳችሁን ትጸየፋላችሁ።+ 32 ይሁንና ይህን እወቁ፦ ይህን የማደርገው ለእናንተ ብዬ አይደለም’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘ይልቁንም የእስራኤል ቤት ሰዎች ሆይ፣ ከመንገዳችሁ የተነሳ እፈሩ፤ ደግሞም ተሸማቀቁ።’
33 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ከበደላችሁ ሁሉ በማነጻችሁ ቀን ከተሞቹ የሰው መኖሪያ እንዲሆኑ፣ የፈራረሱትም ቦታዎች እንደገና እንዲገነቡ አደርጋለሁ።+ 34 አላፊ አግዳሚው ሁሉ ጠፍ ሆኖ ሲያየው የነበረው ባድማ መሬት ይታረሳል። 35 ሰዎችም እንዲህ ይላሉ፦ “ባድማ የነበረው ምድር እንደ ኤደን የአትክልት ስፍራ+ ሆነ፤ ፈራርሰው ባድማና ወና ሆነው የነበሩት ከተሞችም አሁን የተመሸጉ ከተሞችና የሰው መኖሪያ ሆነዋል።”+ 36 ደግሞም ከጥፋት የተረፉት በዙሪያችሁ ያሉት ብሔራት፣ የፈረሰውን የገነባሁትና ባድማ የሆነውን ምድር ያለማሁት እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። እኔ ይሖዋ ተናግሬአለሁ፤ ደግሞም አድርጌዋለሁ።’+
37 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የእስራኤል ቤት ሰዎችም ይህን እንዳደርግላቸው እንዲጠይቁኝ እፈቅድላቸዋለሁ፦ ሕዝባቸውን እንደ መንጋ አበዛዋለሁ። 38 እንደ ቅዱሳን መንጋና በበዓል ወቅት+ በኢየሩሳሌም ውስጥ እንደሚገኘው መንጋ፣* ፈራርሰው የነበሩት ከተሞችም በሰው መንጋ ይሞላሉ፤+ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’”
37 የይሖዋ እጅ በእኔ ላይ ነበረች፤ ይሖዋም በመንፈሱ ወሰደኝ፤ በሸለቋማው ሜዳ መካከልም አኖረኝ፤+ ስፍራውም በአጥንቶች ተሞልቶ ነበር። 2 እሱም በዙሪያቸው እንዳልፍ አደረገኝ፤ በሸለቋማው ሜዳ ላይ በጣም ብዙ አጥንቶች ወድቀው አየሁ፤ አጥንቶቹም በጣም ደርቀው ነበር።+ 3 እሱም “የሰው ልጅ ሆይ፣ እነዚህ አጥንቶች ሕያው ሊሆኑ ይችላሉ?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ የምታውቀው አንተ ነህ” አልኩ።+ 4 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “ስለ እነዚህ አጥንቶች ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘እናንተ ደረቅ አጥንቶች፣ የይሖዋን ቃል ስሙ፦
5 “‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ለእነዚህ አጥንቶች እንዲህ ይላል፦ “እስትንፋስ እንዲገባባችሁ አደርጋለሁ፤ እናንተም ሕያው ትሆናላችሁ።+ 6 ጅማት አደርግላችኋለሁ፤ ሥጋም አለብሳችኋለሁ፤ በቆዳም እሸፍናችኋለሁ፤ እስትንፋስም አስገባባችኋለሁ፤ እናንተም ሕያው ትሆናላችሁ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።”’”
7 ከዚያም በታዘዝኩት መሠረት ትንቢት ተናገርኩ። ትንቢቱን እንደተናገርኩ የሚንኮሻኮሽ ድምፅ ተሰማ፤ አጥንቶቹም እርስ በርስ መገጣጠም ጀመሩ። 8 ከዚያም አጥንቶቹ ጅማትና ሥጋ ሲለብሱ አየሁ፤ በቆዳም ተሸፈኑ። ሆኖም በውስጣቸው ገና እስትንፋስ አልነበረም።
9 ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “ለነፋሱ ትንቢት ተናገር። የሰው ልጅ ሆይ፣ ትንቢት ተናገር፤ ነፋሱንም እንዲህ በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ነፋስ* ሆይ፣ ከአራቱ ነፋሳት ዘንድ ና፤ ሕያው እንዲሆኑም በእነዚህ በተገደሉት ሰዎች ላይ ንፈስ።”’”
10 ስለዚህ ባዘዘኝ መሠረት ትንቢት ተናገርኩ፤ እስትንፋስም* ገባባቸው፤ እነሱም ሕያው ሆነው በእግራቸው ቆሙ፤+ እጅግ ታላቅ ሠራዊትም ሆኑ።
11 ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ እነዚህ አጥንቶች መላው የእስራኤል ቤት ናቸው።+ እነሱ ‘አጥንቶቻችን ደርቀዋል፤ ተስፋችንም ጨልሟል።+ ከሌሎች ጋር ሙሉ በሙሉ ተቆራርጠናል’ ይላሉ። 12 ስለዚህ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ ሆይ፣ መቃብሮቻችሁን እከፍታለሁ፤+ ከመቃብሮቻችሁም ውስጥ አስነሳችኋለሁ፤ ወደ እስራኤልም ምድር አመጣችኋለሁ።+ 13 ሕዝቤ ሆይ፣ መቃብሮቻችሁን ስከፍትና ከመቃብሮቻችሁ ውስጥ ሳስነሳችሁ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።”’+ 14 ‘መንፈሴን በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ እናንተም ሕያው ትሆናላችሁ፤+ በምድራችሁም ላይ አሰፍራችኋለሁ፤ እናንተም እኔ ይሖዋ ራሴ እንደተናገርኩና ይህን እንዳደረግኩ ታውቃላችሁ’ ይላል ይሖዋ።”
15 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 16 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ በትር ወስደህ ‘ለይሁዳና ከእሱ ጋር ላሉት* የእስራኤል ሰዎች’+ ብለህ ጻፍበት። ከዚያም ሌላ በትር ወስደህ ‘ለዮሴፍ ይኸውም ኤፍሬምን ለሚወክለው በትርና ከእሱ ጋር ላሉት* የእስራኤል ቤት ሰዎች ሁሉ’+ ብለህ ጻፍበት። 17 ከዚያም በእጅህ ውስጥ አንድ በትር ይሆኑ ዘንድ ሁለቱንም አንድ ላይ ያዛቸው።+ 18 ወገኖችህ* ‘የእነዚህ ነገሮች ትርጉም ምን እንደሆነ አትነግረንም?’ ብለው ሲጠይቁህ፣ 19 እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በኤፍሬም እጅ ውስጥ ያለውን የዮሴፍንና ከእሱ ጋር ያሉትን የእስራኤልን ነገዶች በትር ወስጄ ከይሁዳ በትር ጋር አያይዘዋለሁ፤ አንድ በትርም አደርጋቸዋለሁ፤+ እነሱም በእጄ ላይ አንድ በትር ይሆናሉ።”’ 20 የጻፍክባቸውን በትሮች ማየት እንዲችሉ በእጅህ ያዝ።
21 “ከዚያም እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እስራኤላውያንን ከሄዱባቸው ብሔራት መካከል አመጣቸዋለሁ፤ ከየአቅጣጫውም ሰብስቤ ወደ ምድራቸው እመልሳቸዋለሁ።+ 22 በምድሪቱ፣ በእስራኤል ተራሮች ላይ አንድ ብሔር አደርጋቸዋለሁ፤+ በሁሉም ላይ አንድ ንጉሥ ይገዛል፤+ ከእንግዲህ ሁለት ብሔራት አይሆኑም፤ ደግሞም ተከፍለው ሁለት መንግሥታት አይሆኑም።+ 23 ከእንግዲህ ወዲህ አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻቸው፣* ጸያፍ በሆኑት ልማዶቻቸውና በሚፈጽሟቸው በደሎች ሁሉ ራሳቸውን አያረክሱም።+ ታማኝነት በማጉደል ከሠሩት ኃጢአት ሁሉ እታደጋቸዋለሁ፤ ደግሞም አነጻቸዋለሁ። እነሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔ ራሴም አምላካቸው እሆናለሁ።+
24 “‘“አገልጋዬ ዳዊት ንጉሣቸው ይሆናል፤+ ሁሉም አንድ እረኛ ይኖራቸዋል።+ ድንጋጌዎቼን አክብረው ይመላለሳሉ፤ ደንቦቼንም በጥንቃቄ ይጠብቃሉ።+ 25 አባቶቻችሁ በኖሩባት፣ ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት ምድር ይቀመጣሉ፤+ እነሱና ልጆቻቸው* እንዲሁም የልጅ ልጆቻቸው በእሷ ላይ ለዘላለም ይኖራሉ፤+ አገልጋዬም ዳዊት ለዘላለም አለቃቸው* ይሆናል።+
26 “‘“ከእነሱም ጋር የሰላም ቃል ኪዳን እገባለሁ፤+ ከእነሱ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ዘላለማዊ ይሆናል። እነሱንም አጸናቸዋለሁ፤ አበዛቸዋለሁ+ እንዲሁም መቅደሴን በመካከላቸው ለዘላለም አኖራለሁ። 27 ድንኳኔ* ከእነሱ ጋር* ይሆናል፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።+ 28 መቅደሴም ለዘላለም በመካከላቸው በሚሆንበት ጊዜ፣ ብሔራት እስራኤልን የቀደስኩት እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”’”+
38 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን የመሼቅና የቱባል+ ዋና አለቃ* በሆነውና በማጎግ ምድር በሚገኘው በጎግ ላይ አድርገህ+ በእሱ ላይ ትንቢት ተናገር።+ 3 እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የመሼቅና የቱባል ዋና አለቃ* የሆንከው ጎግ ሆይ፣ እኔ በአንተ ላይ ተነስቻለሁ። 4 እመልስሃለሁ፤ በመንጋጋህም መንጠቆ አስገባለሁ፤+ ከመላው ሠራዊትህ ይኸውም ከፈረሶች፣ ያማረ ልብስ ከለበሱ ፈረሰኞች፣ ትልቅ ጋሻና ትንሽ ጋሻ* ከያዘ እንዲሁም ሰይፍ ከሚመዝ ታላቅ ጉባኤ ጋር አወጣሃለሁ፤+ 5 ትንሽ ጋሻ የያዙና የራስ ቁር የደፉ የፋርስ፣ የኢትዮጵያና የፑጥ+ ሰዎች ከእነሱ ጋር አሉ፤ 6 ጎሜርንና ወታደሮቹን ሁሉ፣ ራቅ ባለው የሰሜን ምድር የሚገኙትን የቶጋርማ+ ቤት ሰዎችንና ወታደሮቻቸውን ሁሉ ጨምሮ ብዙ ሕዝቦች ከአንተ ጋር አሉ።+
7 “‘“አንተም ሆንክ ከአንተ ጋር የተሰበሰበው ሠራዊትህ ሁሉ ተነሡ፣ ተዘጋጁም፤ አንተም አዛዣቸው* ትሆናለህ።
8 “‘“ከብዙ ቀናት በኋላ በአንተ ላይ ትኩረት ይደረጋል።* በመጨረሻዎቹ ዓመታት ከሰይፍ ጥቃት የተረፈውንና ከብዙ ሕዝቦች መካከል ተሰብስቦ ለብዙ ጊዜ ባድማ ሆነው ወደቆዩት የእስራኤል ተራሮች የተመለሰውን ሕዝብ ምድር ትወራለህ። የምድሪቱ ነዋሪዎች ከተለያዩ ሕዝቦች መካከል ተመልሰው የመጡ ናቸው፤ ደግሞም ሁሉም ያለስጋት ተቀምጠዋል።+ 9 አንተም በእነሱ ላይ እንደ አውሎ ነፋስ ትመጣለህ፤ አንተና ወታደሮችህ ሁሉ እንዲሁም ከአንተ ጋር ያሉት ብዙ ሕዝቦች ምድሪቱን እንደ ደመና ትሸፍናላችሁ።”’
10 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዚያ ቀን ሐሳብ ወደ ልብህ ይገባል፤ ክፉ ዕቅድም ታወጣለህ፤ 11 እንዲህ ትላለህ፦ “ከለላ የሌላቸው ሰፈሮች* የሚገኙበትን ምድር እወራለሁ።+ ያለስጋት ተረጋግተው በሚኖሩት ላይ እመጣለሁ፤ ሁሉም የሚኖሩት ቅጥር፣ መቀርቀሪያና በር በሌላቸው ሰፈሮች ነው።” 12 ዓላማህ ብዙ ሀብት መበዝበዝና መዝረፍ፣ ደግሞም አሁን የሰው መኖሪያ የሆኑትን ባድማ የነበሩ ስፍራዎችና+ ከብሔራት ሁሉ መካከል ዳግመኛ የተሰበሰበውን ሕዝብ+ ማጥቃት ነው፤ ይህ ሕዝብ ሀብትና ንብረት አከማችቷል፤+ በምድርም እምብርት ላይ ይኖራል።
13 “‘ሳባ፣+ ዴዳን፣+ የተርሴስ+ ነጋዴዎችና ተዋጊዎቹ* ሁሉ እንዲህ ይሉሃል፦ “ወረራ የምታካሂደው ብዙ ሀብት ለመበዝበዝና ለመዝረፍ ነው? ሠራዊትህን የሰበሰብከው ብርና ወርቅ ለማጋበስ፣ ሀብትና ንብረት ለመውሰድ እንዲሁም ብዙ ምርኮ ለመንጠቅ ነው?”’
14 “ስለዚህ የሰው ልጅ ሆይ፣ ትንቢት ተናገር፤ ጎግንም እንዲህ በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ እስራኤል ያለስጋት በሚቀመጥበት ጊዜ፣ አንተ በዚያን ቀን ይህን ማወቅህ ይቀራል?+ 15 አንተ ከስፍራህ ይኸውም ርቆ ከሚገኘው የሰሜን ምድር ትመጣለህ፤+ አንተና ከአንተ ጋር ያሉ ብዙ ሕዝቦች ትመጣላችሁ፤ ሁሉም በፈረሶች ላይ የተቀመጡ፣ ታላቅ ጉባኤና ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሠራዊት ናቸው።+ 16 ምድርን እንደሚሸፍን ደመና ሆነህ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ትመጣለህ። ጎግ ሆይ፣ በዘመኑ መጨረሻ በአንተ አማካኝነት በፊታቸው ራሴን በምቀድስበት ጊዜ ብሔራት ያውቁኝ ዘንድ በምድሬ ላይ አመጣሃለሁ።”’+
17 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አንተን በእነሱ ላይ እንደማመጣ ለብዙ ዓመታት ትንቢት በተናገሩትና አገልጋዮቼ በሆኑት የእስራኤል ነቢያት አማካኝነት በቀድሞ ዘመን የተናገርኩት ስለ አንተው አይደለም?’
18 “‘በዚያ ቀን፣ ጎግ የእስራኤልን ምድር በሚወርበት ቀን’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ታላቅ ቁጣዬ ይነድዳል።+ 19 በቅንዓቴና በቁጣዬ እሳት እናገራለሁ፤ ደግሞም በዚያ ቀን በእስራኤል ምድር ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ ይከሰታል። 20 የባሕር ዓሣዎች፣ የሰማይ ወፎች፣ የዱር አራዊት፣ በምድር ላይ የሚሳቡ እንስሳት ሁሉና በምድር ላይ ያሉ ሰዎች በሙሉ ከእኔ የተነሳ ይንቀጠቀጣሉ፤ ተራሮችም ይናዳሉ፤+ ገደላማ ቦታዎችም ይደረመሳሉ፤ ቅጥሩም ሁሉ ይፈርሳል።’
21 “‘በተራሮቼ ሁሉ፣ በጎግ ላይ ሰይፍ እጠራለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘የእያንዳንዱ ሰው ሰይፍ በገዛ ወንድሙ ላይ ይሆናል።+ 22 እኔም በቸነፈርና+ በደም መፋሰስ እፈርድበታለሁ፤* በእሱ፣ በወታደሮቹና ከእሱ ጋር ባሉ ብዙ ሕዝቦች ላይ ኃይለኛ ዶፍ፣ በረዶ፣+ እሳትና+ ድኝ+ አዘንባለሁ።+ 23 ደግሞም ራሴን ገናና አደርጋለሁ፤ እንዲሁም ራሴን እቀድሳለሁ፤ በብዙ ብሔራትም ፊት ማንነቴ እንዲታወቅ አደርጋለሁ፤ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’
39 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ በጎግ ላይ ትንቢት ተናገር፤+ እንዲህም በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የመሼቅና የቱባል+ ዋና አለቃ* የሆንከው ጎግ ሆይ፣ እኔ በአንተ ላይ ተነስቻለሁ። 2 እመልስሃለሁ፤ ደግሞም እነዳሃለሁ፤ ራቅ ካለውም የሰሜን ምድር አምጥቼ+ ወደ እስራኤል ተራሮች እወስድሃለሁ። 3 በግራ እጅህ ያለውን ደጋንህንም ሆነ በቀኝ እጅህ የያዝካቸውን ፍላጻዎችህን አስጥልሃለሁ። 4 አንተና ወታደሮችህ ሁሉ እንዲሁም ከአንተ ጋር የሚሆኑት ሕዝቦች በእስራኤል ተራሮች ላይ ትወድቃላችሁ።+ ለተለያዩ አዳኝ አሞሮች ሁሉና ለዱር አራዊት መብል አድርጌ እሰጥሃለሁ።”’+
5 “‘አውላላ ሜዳ ላይ ትወድቃለህ፤+ እኔ ራሴ ተናግሬአለሁና’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
6 “‘በማጎግና ያለስጋት በደሴቶች በሚኖሩት ላይም እሳት እሰዳለሁ፤+ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። 7 ቅዱስ ስሜ በሕዝቤ በእስራኤል መካከል እንዲታወቅ አደርጋለሁ፤ ከእንግዲህ ቅዱስ ስሜ እንዲረክስ አልፈቅድም፤ ብሔራትም እኔ ይሖዋ፣ የእስራኤል ቅዱስ+ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’+
8 “‘አዎ፣ በትንቢት የተነገረው ነገር ይመጣል፤ ደግሞም ይፈጸማል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘ያ ያልኩት ቀን ይህ ነው። 9 በእስራኤል ከተሞች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ወጥተው፣ የጦር መሣሪያዎቹን ይኸውም ትናንሾቹንና* ትላልቆቹን ጋሻዎች፣ ደጋኖቹን፣ ፍላጻዎቹን፣ የጦር ቆመጦቹንና* ጦሮቹን እሳት ያነዱባቸዋል። ለሰባት ዓመታትም እሳት ለማንደድ ይጠቀሙባቸዋል።+ 10 የጦር መሣሪያዎቹን እሳት ለማንደድ ስለሚጠቀሙባቸው ከሜዳ እንጨት መልቀም ወይም ከጫካ ማገዶ መሰብሰብ አያስፈልጋቸውም።’
“‘የበዘበዟቸውን ይበዘብዛሉ፤ የመዘበሯቸውንም ይመዘብራሉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
11 “‘በዚያ ቀን በእስራኤል ምድር፣ ከባሕሩ በስተ ምሥራቅ በሚጓዙት ሰዎች ሸለቆ ለጎግ+ የመቃብር ቦታ እሰጠዋለሁ፤ በዚያ የሚያልፉትንም ሰዎች መንገድ ይዘጋል። ጎግንና ስፍር ቁጥር የሌለውን ሠራዊቱን ሁሉ በዚያ ይቀብራሉ፤ ሸለቆውንም የሃሞን ጎግ ሸለቆ*+ ብለው ይጠሩታል። 12 የእስራኤል ቤት ሰዎች እነሱን ቀብረው ምድሪቱን ለማንጻት ሰባት ወር ይፈጅባቸዋል።+ 13 የምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ እነሱን ይቀብራል፤ ይህም ራሴን በማስከብርበት ቀን ዝና ያስገኝላቸዋል’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
14 “‘ምድሪቱ ትነጻ ዘንድ፣ ሰዎች በየጊዜው በምድሪቱ ላይ እንዲያልፉና በምድሪቱ ላይ የቀሩትን አስከሬኖች እንዲቀብሩ ይመደባሉ። ለሰባት ወራትም ፍለጋቸውን ይቀጥላሉ። 15 በምድሪቱ ላይ የሚያልፉት ሰዎች የሰው አፅም ሲያዩ በአጠገቡ ምልክት ያደርጋሉ። ከዚያም እንዲቀብሩ የተመደቡት አፅሙን በሃሞን ጎግ ሸለቆ+ ይቀብሩታል። 16 በዚያም ሃሞና* ተብላ የምትጠራ ከተማ ትኖራለች። እነሱም ምድሪቱን ያነጻሉ።’+
17 “አንተም፣ የሰው ልጅ ሆይ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ለተለያዩ ወፎችና ለዱር አራዊት ሁሉ እንዲህ በል፦ “አንድ ላይ ተሰብስባችሁ ኑ። ለእናንተ በማዘጋጀው መሥዋዕቴ ዙሪያ ተሰብሰቡ፤ ይህም በእስራኤል ተራሮች ላይ የሚዘጋጅ ታላቅ መሥዋዕት ነው።+ ሥጋ ትበላላችሁ፤ ደምም ትጠጣላችሁ።+ 18 የኃያላንን ሥጋ ትበላላችሁ፤ የምድርንም አለቆች ደም ትጠጣላችሁ፤ እነሱ አውራ በጎች፣ ጠቦቶች፣ አውራ ፍየሎችና ወይፈኖች ሲሆኑ ሁሉም የሰቡ የባሳን ከብቶች ናቸው። 19 እናንተም እኔ ከማዘጋጅላችሁ መሥዋዕት፣ እስክትጠግቡ ድረስ ስብ ትሰለቅጣላችሁ፤ እስክትሰክሩም ደም ትጠጣላችሁ።”’
20 “‘በማዕዴም ፈረሶችንና ሠረገለኞችን እንዲሁም ኃያላን ሰዎችንና ሁሉንም ዓይነት ተዋጊዎች እስክትጠግቡ ትበላላችሁ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
21 “‘በብሔራት መካከል ክብሬን እገልጣለሁ፤ ብሔራት ሁሉ የወሰድኩትን የፍርድ እርምጃና በእነሱ መካከል የገለጥኩትን ኃይል* ያያሉ።+ 22 ከዚያ ቀን አንስቶ የእስራኤል ቤት ሰዎች እኔ አምላካቸው ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። 23 ብሔራትም የእስራኤል ቤት ሰዎች በግዞት የተወሰዱት በገዛ ራሳቸው በደል ይኸውም ለእኔ ታማኝ ሳይሆኑ በመቅረታቸው እንደሆነ ያውቃሉ።+ ስለዚህ ፊቴን ከእነሱ ሰወርኩ፤+ ለጠላቶቻቸውም አሳልፌ ሰጠኋቸው፤+ ሁሉም በሰይፍ ወደቁ። 24 እንደ ርኩሰታቸውና እንደ በደላቸው መጠን አደረግኩባቸው፤ ፊቴንም ከእነሱ ሰወርኩ።’
25 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በምርኮ የተወሰዱትን የያዕቆብ ወገኖች እመልሳለሁ፤+ ለእስራኤል ቤት ሰዎች ሁሉ ምሕረት አደርግላቸዋለሁ፤+ የስሜንም ቅድስና አስከብራለሁ።*+ 26 ለእኔ ታማኝ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ውርደት ከደረሰባቸው+ በኋላ የሚያስፈራቸው ሳይኖር በምድራቸው ላይ ያለስጋት ይኖራሉ።+ 27 ከሕዝቦች መካከል መልሼ ሳመጣቸውና ከጠላቶቻቸው አገሮች ስሰበስባቸው፣+ በብዙ ብሔራት ፊት፣ በመካከላቸው ራሴን እቀድሳለሁ።’+
28 “‘በብሔራት መካከል በግዞት እንዲኖሩ ሳደርግና ከዚያም አንዳቸውንም ሳላስቀር ወደ ገዛ ምድራቸው መልሼ ሳመጣቸው፣ እኔ አምላካቸው ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።+ 29 ከእንግዲህ ፊቴን ከእስራኤል ቤት ሰዎች አልሰውርም፤+ በእነሱ ላይ መንፈሴን አፈሳለሁና’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
40 በግዞት በተወሰድን+ በ25ኛው ዓመት፣ በዓመቱ መጀመሪያ፣ በወሩ አሥረኛ ቀን፣ ከተማዋ በወደቀች+ በ14ኛው ዓመት፣ በዚያው ዕለት የይሖዋ እጅ በእኔ ላይ ነበረች፤ እሱም ወደ ከተማዋ ወሰደኝ።+ 2 አምላክ በገለጠልኝ ራእዮች አማካኝነት ወደ እስራኤል ምድር አመጣኝ፤ በአንድ ትልቅ ተራራም+ ላይ አስቀመጠኝ፤ በዚያም በስተ ደቡብ በኩል ከተማ የሚመስል ሕንፃ ነበር።
3 ወደዚያ በወሰደኝ ጊዜ መዳብ የሚመስል መልክ ያለው አንድ ሰው አየሁ።+ በእጁም ከተልባ እግር የተሠራ ገመድና የመለኪያ ዘንግ* ይዞ+ መግቢያው ላይ ቆሞ ነበር። 4 ሰውየው እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ በደንብ ተመልከት፤ በጥሞና አዳምጥ፤ የማሳይህንም ሁሉ በትኩረት ተመልከት፤* እዚህ የመጣኸው ለዚህ ነውና። የምታየውን ነገር ሁሉ ለእስራኤል ቤት ሰዎች ተናገር።”+
5 ከቤተ መቅደሱ* ውጭ በዙሪያው ያለውን ቅጥር አየሁ። ሰውየው ስድስት ክንድ ርዝመት ያለው የመለኪያ ዘንግ ይዞ ነበር፤ እያንዳንዱ ክንድ አንድ ጋት ተጨምሮበት ነበር።* እሱም ቅጥሩን መለካት ጀመረ፤ የቅጥሩ ውፍረት አንድ ዘንግ፣ ቁመቱም አንድ ዘንግ ነበር።
6 ከዚያም በምሥራቅ ትይዩ ወዳለው በር+ መጣ፤ በደረጃዎቹም ወጣ። የበሩን ደፍ ሲለካ ወርዱ አንድ ዘንግ ነበር፤ የሌላኛውም ደፍ ወርድ አንድ ዘንግ ነበር። 7 እያንዳንዱ የዘብ ጠባቂ ክፍል ርዝመቱ አንድ ዘንግ፣ ወርዱም አንድ ዘንግ ነበር፤ በዘብ ጠባቂ ክፍሎቹ+ መካከል ደግሞ አምስት ክንድ ስፋት ነበር። ከበሩ በረንዳ አጠገብ በውስጥ በኩል ያለው የበሩ ደፍ አንድ ዘንግ ነበር።
8 በውስጥ በኩል ያለውን የበሩን በረንዳ ለካ፤ አንድ ዘንግም ሆነ። 9 ከዚያም የበሩን በረንዳ ሲለካ ስምንት ክንድ ሆነ፤ በጎን በኩል ያሉትን ዓምዶችም ሲለካ ሁለት ክንድ ሆኑ፤ የበሩም በረንዳ በውስጥ በኩል ነበር።
10 በምሥራቁ በር ግራና ቀኝ ሦስት ሦስት የዘብ ጠባቂ ክፍሎች ነበሩ። ሦስቱም መጠናቸው እኩል ነበር፤ በሁለቱም በኩል ያሉት ዓምዶችም መጠናቸው እኩል ነበር።
11 ከዚያም የበሩን መግቢያ ወርድ ሲለካ 10 ክንድ ሆነ፤ የበሩ ስፋት ከውጭ በኩል 13 ክንድ ነበር።
12 ከዘብ ጠባቂ ክፍሎቹ ፊት ለፊት ያለው የተከለለ ቦታ በሁለቱም በኩል አንድ አንድ ክንድ ነበር። የዘብ ጠባቂ ክፍሎቹ በሁለቱም በኩል ስድስት ስድስት ክንድ ነበሩ።
13 ከዚያም በሩን ከአንዱ የዘብ ጠባቂ ክፍል ጣሪያ* እስከ ሌላኛው የዘብ ጠባቂ ክፍል ጣሪያ ድረስ ለካ፤ ወርዱም 25 ክንድ ነበር፤ አንደኛው መግቢያ ከሌላኛው መግቢያ ትይዩ ነበር።+ 14 ከዚያም በጎንና በጎን በኩል ያሉትን ዓምዶች ቁመት ሲለካ 60 ክንድ ሆነ፤ በግቢው ዙሪያ በሚገኙት በሮች ላይ ያሉትንም ዓምዶች ለካ። 15 ከመግቢያው በር ፊት አንስቶ በበሩ ውስጠኛ ክፍል በኩል እስካለው በረንዳ ፊት ድረስ 50 ክንድ ነበር።
16 ከበሩ በውስጥ በኩል በግራና በቀኝ፣ የዘብ ጠባቂ ክፍሎቹና በጎን ያሉት ዓምዶቻቸው እየጠበቡ የሚሄዱ ክፈፎች ያሏቸው መስኮቶች* ነበሯቸው።+ በረንዳዎቹም በውስጥ በኩል፣ በግራም በቀኝም መስኮቶች ነበሯቸው፤ በጎን ያሉት ዓምዶች ደግሞ የዘንባባ ዛፍ ምስሎች ተቀርጸውባቸው ነበር።+
17 ከዚያም ወደ ውጨኛው ግቢ አመጣኝ፤ በግቢውም ዙሪያ የመመገቢያ ክፍሎችና*+ መመላለሻ መንገድ አየሁ። በመንገዱ ላይ 30 የመመገቢያ ክፍሎች ነበሩ። 18 በበሮቹ ጎን ያለው መመላለሻ መንገድ ከበሮቹ ርዝመት ጋር እኩል ነበር፤ ይህም የታችኛው መመላለሻ መንገድ ነበር።
19 ከዚያም ከታችኛው በር አንስቶ ወደ ውስጠኛው ግቢ እስከሚያስገባው በር ድረስ ያለውን ርቀት* ለካ። በምሥራቅም ሆነ በሰሜን በኩል ያለው ርቀት 100 ክንድ ነበር።
20 የውጨኛው ግቢ ከሰሜን ጋር ትይዩ የሆነ በር ነበረው፤ እሱም ርዝመቱንና ወርዱን ለካ። 21 በሁለቱም ጎን ሦስት ሦስት የዘብ ጠባቂ ክፍሎች ነበሩ። በጎን ያሉት ዓምዶቹና በረንዳው መጠናቸው ከመጀመሪያው በር ጋር እኩል ነበር። ርዝመቱ 50 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 25 ክንድ ነበር። 22 የመስኮቶቹ፣ የበረንዳውና የዘንባባ ዛፍ ምስሎቹ+ መጠን በምሥራቁ በር ካሉት ጋር እኩል ነበር። ሰዎች ሰባት ደረጃዎች ወጥተው ወደዚያ መግባት ይችላሉ፤ በረንዳውም ከፊት ለፊታቸው ነበር።
23 በውስጠኛው ግቢ፣ ከሰሜኑ በር ትይዩ አንድ በር፣ ከምሥራቁ በር ትይዩ ደግሞ ሌላ በር ነበር። እሱም ከአንደኛው በር እስከ ሌላኛው በር ሲለካ 100 ክንድ ሆነ።
24 ከዚያም ወደ ደቡብ አቅጣጫ አመጣኝ፤ በስተ ደቡብ በኩል አንድ በር አየሁ።+ እሱም በጎን ያሉትን ዓምዶቹንና በረንዳውን ለካ፤ መጠናቸውም ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር። 25 በበሩና በበረንዳው ግራና ቀኝ እንደ ሌሎቹ ዓይነት መስኮቶች ነበሩ። ርዝመቱ 50 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 25 ክንድ ነበር። 26 ወደዚያ የሚወስዱ ሰባት ደረጃዎች ነበሩ፤+ በረንዳውም ከፊት ለፊታቸው ነበር። በግራና በቀኝ ባሉት ዓምዶች ላይ አንድ አንድ የዘንባባ ዛፍ ምስል ተቀርጾ ነበር።
27 የውስጠኛው ግቢ ከደቡብ ጋር ትይዩ የሆነ በር ነበረው፤ እሱም ወደ ደቡብ አቅጣጫ ከአንደኛው በር እስከ ሌላኛው በር ለካ፤ ርቀቱም 100 ክንድ ሆነ። 28 ከዚያም በደቡብ በር በኩል ወደ ውስጠኛው ግቢ ወሰደኝ፤ የደቡቡን በር ሲለካ መጠኑ ከሌሎቹ ጋር እኩል ሆነ። 29 የዘብ ጠባቂ ክፍሎቹ፣ በጎን ያሉት ዓምዶቹና በረንዳው መጠናቸው ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር። በበሩና በበረንዳው ግራና ቀኝ መስኮቶች ነበሩ። ርዝመቱ 50 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 25 ክንድ ነበር።+ 30 ዙሪያውን በረንዳዎች ነበሩ፤ ርዝመታቸው 25 ክንድ፣ ወርዳቸው ደግሞ 5 ክንድ ነበር። 31 በረንዳው ከውጨኛው ግቢ ጋር ትይዩ ነበር፤ በጎን ባሉት ዓምዶቹም ላይ የዘንባባ ዛፍ ምስሎች ነበሩ፤+ ወደዚያም የሚወስዱ ስምንት ደረጃዎች ነበሩ።+
32 በምሥራቅ በኩል ወደ ውስጠኛው ግቢ ሲወስደኝ በሩን ለካ፤ መጠኑም ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር። 33 የዘብ ጠባቂ ክፍሎቹ፣ በጎን ያሉት ዓምዶቹና በረንዳው መጠናቸው ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር፤ በበሩና በበረንዳው ግራና ቀኝ መስኮቶች ነበሩ። ርዝመቱ 50 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 25 ክንድ ነበር። 34 በረንዳው ከውጨኛው ግቢ ጋር ትይዩ ነበር፤ በግራና በቀኝ ባሉት ዓምዶች ላይ የዘንባባ ዛፍ ምስሎች ተቀርጸው ነበር፤ ወደዚያም የሚወስዱ ስምንት ደረጃዎች ነበሩ።
35 ከዚያም ወደ ሰሜን በር+ ወሰደኝና ለካው፤ መጠኑ ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር። 36 የዘብ ጠባቂ ክፍሎቹ፣ በጎን ያሉት ዓምዶቹና በረንዳው መጠናቸው ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር። በግራና በቀኝ መስኮቶች ነበሩት። ርዝመቱ 50 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 25 ክንድ ነበር። 37 በጎን ያሉት ዓምዶቹ ከውጨኛው ግቢ ጋር ትይዩ ነበሩ፤ በግራና በቀኝ ባሉት ዓምዶቹ ላይ የዘንባባ ዛፍ ምስሎች ተቀርጸው ነበር፤ ወደዚያም የሚወስዱ ስምንት ደረጃዎች ነበሩ።
38 በበሮቹ ጎንና ጎን ባሉት ዓምዶች አጠገብ የመመገቢያ ክፍል ነበር፤ መግቢያም ነበረው፤ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠለውን መባ የሚያጥቡት በዚያ ነበር።+
39 በበሩም በረንዳ ላይ በግራና በቀኝ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ፣+ የኃጢአት መባና+ የበደል መባ+ የሚታረድባቸው ሁለት ሁለት ጠረጴዛዎች ነበሩ። 40 ወደ ሰሜን በር በሚወስደው መንገድ ላይ ከመግቢያው ውጭ ሁለት ጠረጴዛዎች ነበሩ። በተጨማሪም ከበሩ በረንዳ በሌላኛው በኩል ሁለት ጠረጴዛዎች ነበሩ። 41 በበሩ ግራና ቀኝ አራት አራት ጠረጴዛዎች፣ በድምሩ መሥዋዕት የታረደባቸው ስምንት ጠረጴዛዎች ነበሩ። 42 ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ ለማቅረብ የሚያገለግሉት አራቱ ጠረጴዛዎች ከተጠረበ ድንጋይ የተሠሩ ነበሩ። ርዝመታቸው አንድ ክንድ ተኩል፣ ወርዳቸው አንድ ክንድ ተኩል፣ ቁመታቸው ደግሞ አንድ ክንድ ነበር። በእነሱም ላይ የሚቃጠለውን መባና መሥዋዕቱን ለማረድ የሚያገለግሉ መሣሪያዎች ተቀምጠው ነበር። 43 ከውስጠኛው ግንብ ጋር ተያይዘው ዙሪያውን የተሠሩ መደርደሪያዎች የነበሩ ሲሆን ወርዳቸው አንድ ጋት ነበር፤ በጠረጴዛዎቹም ላይ የስጦታ መባው ሥጋ ይቀመጥ ነበር።
44 ከውስጠኛው በር ውጭ የዘማሪዎቹ መመገቢያ ክፍሎች ነበሩ፤+ ክፍሎቹ ከደቡብ ትይዩ ባለው የሰሜን በር አጠገብ በሚገኘው በውስጠኛው ግቢ ውስጥ ነበሩ። ከሰሜን ትይዩ ባለው የምሥራቅ በር አጠገብ ሌላ የመመገቢያ ክፍል ነበር።
45 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “በደቡብ ትይዩ ያለው ይህ የመመገቢያ ክፍል የቤተ መቅደሱን አገልግሎት እንዲያከናውኑ ኃላፊነት ለተጣለባቸው ካህናት የተመደበ ነው።+ 46 በሰሜን ትይዩ ያለው የመመገቢያ ክፍል ከመሠዊያው ጋር የተያያዘ አገልግሎት እንዲያከናውኑ ኃላፊነት ለተጣለባቸው ካህናት የተመደበ ነው።+ እነዚህ የሳዶቅ+ ልጆች ሲሆኑ ከሌዋውያን መካከል ይሖዋን ለማገልገል ወደ እሱ እንዲቀርቡ የተመደቡ ናቸው።”+
47 ከዚያም የውስጠኛውን ግቢ ለካ። ርዝመቱ 100 ክንድ፣ ወርዱም 100 ክንድ የሆነ አራት ማዕዘን ነበር። መሠዊያው ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ነበር።
48 ከዚያም ወደ ቤተ መቅደሱ በረንዳ+ አመጣኝ፤ በጎን በኩል ያለውንም የበረንዳውን ዓምድ ለካ፤ ዓምዱም በአንደኛው ጎን አምስት ክንድ፣ በሌላኛውም ጎን አምስት ክንድ ነበር። የበሩ ወርድ በአንደኛው ጎን ሦስት ክንድ፣ በሌላኛውም ጎን ሦስት ክንድ ነበር።
49 የበረንዳው ርዝመት 20 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 11* ክንድ ነበር። ሰዎች ወደዚያ የሚወጡት በደረጃዎች ነበር። በጎንና በጎን ባሉት ምሰሶዎች አጠገብ በግራና በቀኝ አንድ አንድ ዓምድ ነበር።+
41 ከዚያም ወደ ውጨኛው መቅደስ* አስገባኝ፤ በጎንና በጎን ያሉትንም ዓምዶች ለካ፤ የዓምዶቹ ወርድ በአንደኛው ጎን ስድስት ክንድ፣* በሌላኛውም ጎን ስድስት ክንድ ሆነ። 2 የመግቢያው ወርድ አሥር ክንድ ነበር፤ በመግቢያው ግራና ቀኝ ያሉት ግንቦች* አምስት አምስት ክንድ ነበሩ። የውጨኛውን መቅደስ ርዝመት ሲለካ 40 ክንድ ሆነ፤ ወርዱ ደግሞ 20 ክንድ ሆነ።
3 ከዚያም ወደ ውስጥ* ገብቶ በመግቢያው ጎን ላይ ያለውን ዓምድ ውፍረት ሲለካ ሁለት ክንድ ሆነ፤ የመግቢያውም ወርድ ስድስት ክንድ ነበር። በመግቢያው ግራና ቀኝ ያሉት ግንቦች ሰባት ክንድ ነበሩ።* 4 ከዚያም ከውጨኛው መቅደስ ትይዩ ያለውን ክፍል ለካ፤ ርዝመቱም 20 ክንድ፣ ወርዱም 20 ክንድ ሆነ።+ እሱም “ይህ ቅድስተ ቅዱሳኑ+ ነው” አለኝ።
5 ከዚያም የቤተ መቅደሱን ግንብ ሲለካ ውፍረቱ ስድስት ክንድ ሆነ። በቤተ መቅደሱ ጎን ዙሪያውን ያሉት ክፍሎች ወርድ አራት ክንድ ነበር።+ 6 በጎን በኩል ያሉት ክፍሎች ከበላያቸው ሁለት ፎቅ ነበራቸው፤ በእያንዳንዱ ፎቅ ላይ 30 ክፍሎች ነበሩ። በቤተ መቅደሱ ግንብ ዙሪያ፣ በጎን በኩል ያሉትን ክፍሎች ደግፈው የሚይዙ ተሸካሚዎች ነበሩ፤ በመሆኑም እነዚህ ተሸካሚዎች ወደ ቤተ መቅደሱ ግንብ ዘልቀው አልገቡም።+ 7 በቤተ መቅደሱ ግራና ቀኝ ጠመዝማዛ መተላለፊያ* ነበር፤ ላይ ወደሚገኙት ክፍሎች ሲወጣ የመወጣጫዎቹ ወርድ ይጨምር ነበር።+ አንድ ሰው ከታች ተነስቶ በመካከለኛው ፎቅ በኩል ወደ መጨረሻው ፎቅ ሲወጣ ፎቁ እየሰፋ ይሄድ ነበር።
8 በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ከፍ ያለ መሠረት መኖሩን አየሁ፤ በጎን በኩል ያሉት ክፍሎች መሠረትም እስከ ማዕዘኑ ድረስ ሙሉ ዘንግ ይኸውም ስድስት ክንድ ነበር። 9 በጎን በኩል ያሉት ክፍሎች የውጨኛው ግንብ ወርድ አምስት ክንድ ነበር። በጎን ካሉት ክፍሎች አጠገብ የቤተ መቅደሱ ክፍል የሆነ ክፍት ቦታ* ነበር።
10 በቤተ መቅደሱና በመመገቢያ ክፍሎቹ*+ መካከል በሁለቱም በኩል ወርዱ 20 ክንድ የሆነ ቦታ ነበር። 11 በሰሜን አቅጣጫ፣ በጎን በኩል ባሉት ክፍሎችና ክፍት በሆነው ቦታ መካከል መግቢያ ነበር፤ በደቡብ አቅጣጫም ሌላ መግቢያ ነበር። ክፍት የሆነው ቦታ በሁሉም አቅጣጫ ወርዱ አምስት ክንድ ነበር።
12 በምዕራብ በኩል ክፍት ከሆነው ስፍራ ትይዩ ያለው ሕንፃ ወርዱ 70 ክንድ፣ ርዝመቱ ደግሞ 90 ክንድ ነበር፤ የሕንፃው ግንብ ውፍረት ዙሪያውን አምስት ክንድ ነበር።
13 ቤተ መቅደሱን ሲለካ ርዝመቱ 100 ክንድ ሆነ። ክፍት የሆነው ስፍራ፣ ሕንፃውና* ግንቦቹ ርዝመታቸው 100 ክንድ ነበር። 14 ከምሥራቅ ትይዩ የሆነው የቤተ መቅደሱ የፊተኛው ክፍልና ክፍት የሆነው ስፍራ ወርድ 100 ክንድ ነበር።
15 በሁለቱም ጎን ያሉትን መተላለፊያዎቹን ጨምሮ በጀርባ በኩል ክፍት ከሆነው ስፍራ ጋር ትይዩ የሆነውን ሕንፃ ርዝመት ሲለካ 100 ክንድ ሆነ።
እንዲሁም ውጨኛውን መቅደስ፣ ውስጠኛውን መቅደስና+ የግቢውን በረንዳዎች ለካ፤ 16 ደግሞም በሦስቱም ቦታዎች ያሉትን ደፎች፣ እየጠበቡ የሚሄዱ ክፈፎች ያሏቸው መስኮቶችና+ መተላለፊያዎች ለካ። ከደፉ አጠገብ ከወለሉ አንስቶ እስከ መስኮቶቹ ድረስ የእንጨት ማስጌጫዎች ነበሩ፤+ መስኮቶቹም ተሸፍነው ነበር። 17 ከመግቢያው በላይ ያለው፣ የቤተ መቅደሱ ውስጥና ውጭ እንዲሁም በዙሪያው ያለው ግንብ ሁሉ ተለካ። 18 ግንቡ ኪሩቤልና+ የዘንባባ ዛፍ ምስል ተቀርጸውበት ነበር፤+ በሁለት ኪሩቤል መካከል የዘንባባ ዛፍ ምስል ነበር፤ እያንዳንዱ ኪሩብ ሁለት ፊት ነበረው። 19 ሰው የሚመስለው ፊት በአንድ በኩል ወዳለው የዘንባባ ዛፍ ምስል የዞረ ሲሆን፣ አንበሳ* የሚመስለው ፊት ደግሞ በሌላ በኩል ወዳለው የዘንባባ ዛፍ ዞሮ ነበር።+ በዚህ መንገድ በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ተቀርጸው ነበር። 20 በመቅደሱ ግድግዳ ላይ ከወለሉ አንስቶ ከመግቢያው በላይ እስካለው ስፍራ ድረስ ኪሩቤልና የዘንባባ ዛፍ ምስሎች ተቀርጸው ነበር።
21 የመቅደሱ መቃኖች አራት ማዕዘን ናቸው።*+ ከቅዱሱ ስፍራ* ፊት ለፊት 22 ቁመቱ ሦስት ክንድ፣ ርዝመቱ ደግሞ ሁለት ክንድ የሆነ ከእንጨት የተሠራ መሠዊያ+ የሚመስል ነገር ነበር። የማዕዘን ቋሚዎች ነበሩት፤ መሠረቱና* ጎኖቹ ከእንጨት የተሠሩ ነበሩ። እሱም “በይሖዋ ፊት ያለው ጠረጴዛ ይህ ነው”+ አለኝ።
23 የውጨኛው መቅደስና ቅዱሱ ስፍራ እያንዳንዳቸው ሁለት በሮች ነበሯቸው።+ 24 በሮቹ ታጣፊ የሆኑ ሁለት ሳንቃዎች ነበሯቸው፤ እያንዳንዱ በር ሁለት ሳንቃዎች ነበሩት። 25 በግድግዳው ላይ ያሉት ዓይነት ኪሩቦችና የዘንባባ ዛፍ ምስሎች በመቅደሱ በሮች ላይ ተቀርጸው ነበር።+ በተጨማሪም በውጭ በኩል ከፊት ለፊት በረንዳው ላይ ከእንጨት የተሠራ ወጣ ያለ ነገር* ነበር። 26 እንዲሁም በበረንዳው ግራና ቀኝ፣ ከቤተ መቅደሱ ጎን ባሉት ክፍሎች ላይና በታዛው አካባቢ እየጠበቡ የሚሄዱ ክፈፎች ያሏቸው መስኮቶችና+ የዘንባባ ዛፍ ምስሎች ነበሩ።
42 ከዚያም በስተ ሰሜን ወዳለው ወደ ውጨኛው ግቢ ወሰደኝ።+ ደግሞም በአቅራቢያው ከሚገኘው ሕንፃ+ በስተ ሰሜን፣ ክፍት ከሆነው ስፍራ አጠገብ ወዳሉት የመመገቢያ ክፍሎች ያሏቸው ሕንፃዎች+ አመጣኝ። 2 ሕንፃዎቹ በሰሜኑ መግቢያ በኩል ርዝመታቸው 100 ክንድ* ነበር፤ ወርዳቸው ደግሞ 50 ክንድ ነበር። 3 ሕንፃዎቹ የሚገኙት ወርዱ 20 ክንድ በሆነው በውስጠኛው ግቢና+ በውጨኛው ግቢ መመላለሻ መንገድ መካከል ነበር። ሕንፃዎቹ ባለ ሁለት ፎቅ ሲሆኑ ትይዩ ሆነው የተሠሩ ሰገነቶች ነበሯቸው። 4 በመመገቢያ ክፍሎቹ ፊት* ወርዱ 10 ክንድ፣ ርዝመቱ ደግሞ 100 ክንድ የሆነ መተላለፊያ* በውስጥ በኩል ነበር፤+ የክፍሎቹም መግቢያዎች የሚገኙት በስተ ሰሜን በኩል ነበር። 5 ከላይ ያሉት የመመገቢያ ክፍሎች ከታች ካሉትና መካከል ላይ ካሉት የሕንፃው ክፍሎች ይልቅ ጠበብ ያሉ ነበሩ፤ ምክንያቱም ሰገነቶቹ ሰፋ ያለ ቦታ ይዘውባቸው ነበር። 6 የመመገቢያ ክፍሎቹ ባለ ሁለት ፎቅ ነበሩ፤ ይሁንና በግቢው ውስጥ እንዳሉት ዓይነት ዓምዶች አልነበሯቸውም። ከታች ካሉትና መካከል ላይ ካሉት ይበልጥ ከላይኛው ፎቅ ክፍሎች ሰፊ ቦታ የተወሰደው ለዚህ ነው።
7 ከሌሎቹ የመመገቢያ ክፍሎች ጋር ትይዩ ከሆኑትና በውጨኛው ግቢ በኩል ካሉት የመመገቢያ ክፍሎች አጠገብ የሚገኘው የውጨኛው የድንጋይ ቅጥር ርዝመት 50 ክንድ ነበር። 8 በውጨኛው ግቢ በኩል ያሉት የመመገቢያ ክፍሎች ርዝመት 50 ክንድ ሲሆን ከመቅደሱ ትይዩ ያሉት የመመገቢያ ክፍሎች ርዝመት ግን 100 ክንድ ነበር። 9 የመመገቢያ ክፍሎቹ በስተ ምሥራቅ በኩል፣ ከውጨኛው ግቢ ወደ ክፍሎቹ የሚወስድ መግቢያ ነበራቸው።
10 በደቡብም በኩል ክፍት በሆነው ስፍራና በሕንፃው አቅራቢያ፣ በስተ ምሥራቅ ባለው የግቢው የድንጋይ ቅጥር ውስጥ* የመመገቢያ ክፍሎች ነበሩ።+ 11 በስተ ሰሜን እንዳሉት የመመገቢያ ክፍሎች ሁሉ በእነዚህ የመመገቢያ ክፍሎች ፊትም መተላለፊያ ነበር።+ ክፍሎቹ ተመሳሳይ ርዝመትና ወርድ ነበራቸው፤ መውጫዎቻቸውም ሆኑ ንድፎቻቸው ተመሳሳይ ነበሩ። መግቢያዎቻቸው 12 በደቡብ በኩል ከሚገኙት የመመገቢያ ክፍሎች መግቢያዎች ጋር ተመሳሳይ ነበሩ። በስተ ምሥራቅ በኩል በአቅራቢያው ካለው የድንጋይ ቅጥር ፊት፣ በመተላለፊያው መንገድ መነሻ ላይ ሰው ሊገባበት የሚችል መግቢያ ነበር።+
13 ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “ክፍት ከሆነው ስፍራ አጠገብ የሚገኙት በስተ ሰሜን ያሉት የመመገቢያ ክፍሎችና በስተ ደቡብ ያሉት የመመገቢያ ክፍሎች፣+ ወደ ይሖዋ የሚቀርቡት ካህናት እጅግ ቅዱስ የሆኑትን መባዎች የሚበሉባቸው የተቀደሱ መመገቢያ ክፍሎች ናቸው።+ በዚያም እጅግ ቅዱስ የሆኑትን መባዎች፣ የእህል መባ፣ የኃጢአት መባና የበደል መባ ያስቀምጣሉ፤ ምክንያቱም ቦታው ቅዱስ ነው።+ 14 ካህናቱ በሚገቡበት ጊዜ፣ ሲያገለግሉ የሚለብሱትን ልብስ ሳያወልቁ ከቅዱሱ ስፍራ ወደ ውጨኛው አደባባይ መውጣት አይችሉም፤+ ልብሶቹ ቅዱስ ናቸውና። ለሕዝቡ ወደተፈቀዱት ቦታዎች ከመሄዳቸው በፊት ልብሳቸውን ይቀይሩ ነበር።”
15 የቤተ መቅደሱን የውስጠኛውን ስፍራ ለክቶ* ሲጨርስ ከምሥራቅ ትይዩ ወደሆነው በር+ በሚወስደው መተላለፊያ በኩል ይዞኝ ወጣ፤ ከዚያም ስፍራውን በጠቅላላ ለካ።
16 በስተ ምሥራቅ በኩል ያለውን በመለኪያ ዘንግ* ለካ። በመለኪያ ዘንጉ ከአንዱ ጎን እስከ ሌላው ጎን ርዝመቱ 500 ዘንግ ሆነ።
17 በስተ ሰሜን በኩል ያለውን ለካ፤ በመለኪያ ዘንጉም ርዝመቱ 500 ዘንግ ሆነ።
18 በስተ ደቡብ በኩል ያለውን ለካ፤ በመለኪያ ዘንጉም ርዝመቱ 500 ዘንግ ሆነ።
19 ከዚያም ወደ ምዕራብ ዞረ። በመለኪያ ዘንጉ ሲለካ ርዝመቱ 500 ዘንግ ሆነ።
20 ስፍራውን በአራቱም ጎን ለካ። ቅዱስ የሆነውንና ቅዱስ ያልሆነውን ስፍራ ለመለየት የሚያገለግል+ ርዝመቱ 500 ዘንግ፣ ወርዱም 500 ዘንግ+ የሆነ ቅጥር በዙሪያው ነበር።+
43 ከዚያም ከምሥራቅ ትይዩ ወደሆነው በር ወሰደኝ።+ 2 በዚያም የእስራኤል አምላክ ክብር ከምሥራቅ ሲመጣ አየሁ፤+ ድምፁም እንደሚጎርፍ ውኃ ድምፅ ነበር፤+ ከክብሩም የተነሳ ምድር አበራች።+ 3 ያየሁት ነገር ከተማዋን ለማጥፋት* በመጣሁ* ጊዜ ያየሁትን ራእይ ይመስል ነበር፤ ደግሞም በኬባር ወንዝ+ አቅራቢያ አይቼው ከነበረው ነገር ጋር ይመሳሰል ነበር፤ እኔም መሬት ላይ በግንባሬ ተደፋሁ።
4 ከዚያም የይሖዋ ክብር ከምሥራቅ ትይዩ በሆነው በር በኩል ወደ ቤተ መቅደሱ* ገባ።+ 5 መንፈስም አንስቶ ወደ ውስጠኛው ግቢ አመጣኝ፤ እኔም ቤተ መቅደሱ በይሖዋ ክብር ተሞልቶ አየሁ።+ 6 ከዚያም አንድ ሰው ከቤተ መቅደሱ ውስጥ ሲያናግረኝ ሰማሁ፤ ሰውየውም መጥቶ አጠገቤ ቆመ።+ 7 አምላክም እንዲህ አለኝ፦
“የሰው ልጅ ሆይ፣ ይህ የዙፋኔ መቀመጫ፣+ የእግሬ ማሳረፊያና+ በእስራኤል ልጆች መካከል ለዘላለም የምኖርበት ስፍራ ነው።+ የእስራኤል ቤት ሰዎች፣ እነሱም ሆኑ ንጉሦቻቸው በሚፈጽሙት መንፈሳዊ ምንዝርና በሞቱት ንጉሦቻቸው* ሬሳ ከእንግዲህ ቅዱስ ስሜን አያረክሱም።+ 8 በእኔና በእነሱ መካከል ግንቡ ብቻ ሲቀር፣ ደፋቸውን ከቤቴ ደፍ አጠገብ፣ መቃናቸውንም ከቤቴ መቃን አጠገብ በማድረግ+ በሠሯቸው አስጸያፊ ነገሮች ቅዱስ ስሜን አርክሰዋል፤ ስለዚህ በቁጣዬ አጠፋኋቸው።+ 9 ከእንግዲህ የሚፈጽሙትን መንፈሳዊ ምንዝር ያስወግዱ፤ የንጉሦቻቸውንም ሬሳ ከእኔ ያርቁ፤ እኔም በመካከላቸው ለዘላለም እኖራለሁ።+
10 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ ከሠሩት በደል የተነሳ ኀፍረት እንዲሰማቸው+ ለእስራኤል ቤት ሰዎች ስለ ቤተ መቅደሱ ግለጽላቸው፤+ ንድፉንም ያጥኑ።* 11 በሠሩት ነገር ሁሉ ኀፍረት ከተሰማቸው የቤተ መቅደሱን ንድፍ፣ አቀማመጡን፣ መውጫዎቹንና መግቢያዎቹን አሳውቃቸው።+ አጠቃላይ ንድፉንና ደንቦቹን፣ ንድፉንና ሕጎቹን አሳያቸው፤ ደግሞም እነሱ እያዩ ጻፋቸው፤ ይህን የምታደርገው አጠቃላይ ንድፉንና ደንቦቹን አስተውለው በተግባር እንዲያውሉ ነው።+ 12 የቤተ መቅደሱ ሕግ ይህ ነው። በተራራው አናት ዙሪያ ያለው ቦታ ሁሉ እጅግ ቅዱስ ነው።+ እነሆ፣ የቤተ መቅደሱ ሕግ ይህ ነው።
13 “የመሠዊያው ልክ በክንድ* ሲለካ መጠኑ ይህ ነው፤+ እያንዳንዱ ክንድ አንድ ጋት ተጨምሮበት ነበር። የመሠዊያው መሠረት አንድ ክንድ ነው፤ ወርዱም አንድ ክንድ ነው። በጠርዙ ዙሪያ፣ ወርዱ አንድ ስንዝር* የሆነ ክፈፍ አለው። ይህ የመሠዊያው መሠረት ነው። 14 መሬት ላይ ካረፈው መሠረት አንስቶ በዙሪያው እስካለው የታችኛው እርከን ድረስ ሁለት ክንድ ሲሆን ወርዱ ደግሞ አንድ ክንድ ነው። በዙሪያው ካለው ከትንሹ እርከን እስከ ትልቁ እርከን ድረስ አራት ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ አንድ ክንድ ነው። 15 የመሠዊያው ምድጃ ከፍታ አራት ክንድ ሲሆን ከምድጃው በላይ ወጣ ወጣ ያሉ አራት ቀንዶች አሉ።+ 16 የመሠዊያው ምድጃ አራት ማዕዘን ሲሆን ርዝመቱ 12 ክንድ፣ ወርዱም 12 ክንድ ነው።+ 17 በዙሪያው ያለው እርከን አራቱም ጎኖች ርዝመታቸው 14 ክንድ፣ ወርዳቸውም 14 ክንድ ነው፤ በዙሪያውም ያለው ክፈፍ ግማሽ ክንድ ሲሆን መሠረቱም በሁሉም ጎኖች አንድ ክንድ ነው።
“ደረጃዎቹም ከምሥራቅ ትይዩ ነበሩ።”
18 ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በመሠዊያው ላይ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ እንዲቀርብና በላዩ ላይ ደም እንዲረጭበት፣ መሠዊያው ሲሠራ ሊከተሏቸው የሚገቡት መመሪያዎች እነዚህ ናቸው።’+
19 “‘እኔን ለማገልገል በፊቴ ለሚቀርቡት የሳዶቅ ዘር ለሆኑት ሌዋውያን ካህናት፣+ ከመንጋው መካከል ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ ወይፈን ትሰጣቸዋለህ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 20 ‘ከደሙ ጥቂት ወስደህ በመሠዊያው አራት ቀንዶች፣ በዙሪያው ባለው እርከን አራት ጎኖችና በዙሪያው ባለው ጠርዝ ላይ አድርግ፤ ይህን የምታደርገው መሠዊያውን ከኃጢአት ለማንጻትና ለመሠዊያው ማስተሰረያ ለማቅረብ ነው።+ 21 ከዚያም ከመቅደሱ ውጭ፣ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ለዚህ ተብሎ በተመደበው ቦታ ታቃጥለው ዘንድ የኃጢአት መባ የሆነውን ወይፈን ውሰድ።+ 22 በሁለተኛው ቀን የኃጢአት መባ የሚሆን እንከን የሌለበት ተባዕት ፍየል ታቀርባለህ፤ እነሱም በወይፈኑ መሠዊያውን ከኃጢአት እንዳነጹት ሁሉ በዚህም መሠዊያውን ከኃጢአት ያነጹታል።’
23 “‘መሠዊያውን ከኃጢአት ካነጻህ በኋላ ከከብቶቹ መካከል እንከን የሌለበት አንድ ወይፈንና ከመንጋው መካከል እንከን የሌለበት አንድ አውራ በግ ታቀርባለህ። 24 ለይሖዋ ታቀርባቸዋለህ፤ ካህናቱም ጨው ከነሰነሱባቸው+ በኋላ ለይሖዋ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ አድርገው ያቀርቧቸዋል። 25 በየዕለቱ፣ ለሰባት ቀናት አንድ አውራ ፍየል የኃጢአት መባ አድርገህ ታቀርባለህ፤+ እንዲሁም ከከብቶቹ መካከል አንድ ወይፈንና ከመንጋው መካከል አንድ አውራ በግ ታቀርባለህ፤ የምታቀርባቸው እንስሳት እንከን የሌለባቸው* ይሁኑ። 26 ለሰባት ቀናት ለመሠዊያው ማስተሰረያ ያቀርባሉ፤ መሠዊያውንም ያነጹታል እንዲሁም ለአገልግሎት ያዘጋጁታል። 27 እነዚህ ቀናት ከተፈጸሙ በኋላ ከስምንተኛው ቀን+ አንስቶ ካህናቱ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባችሁንና* የኅብረት መሥዋዕቶቻችሁን በመሠዊያው ላይ ያቀርባሉ፤ እኔም በእናንተ ደስ እሰኛለሁ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
44 ከምሥራቅ ትይዩ ወደሆነው ወደ ውጨኛው የመቅደሱ በር ወደሚወስደው መንገድ መልሶ አመጣኝ፤+ በሩም ዝግ ነበር።+ 2 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ይህ በር እንደተዘጋ ይኖራል። መከፈት የለበትም፤ ደግሞም ማንም ሰው አይገባበትም፤ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ በዚያ በኩል ገብቷልና፤+ ስለዚህ እንደተዘጋ ይኖራል። 3 አለቃው ግን አለቃ ስለሆነ በይሖዋ ፊት ምግብ ለመብላት በዚያ ይቀመጣል።+ በበሩ መተላለፊያ በረንዳ በኩል ይገባል፤ በዚያም ይወጣል።”+
4 ከዚያም በስተ ሰሜን በሚገኘው በር በኩል ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ወዳለው ቦታ አመጣኝ። እኔም ባየሁ ጊዜ የይሖዋ ክብር፣ የይሖዋን ቤተ መቅደስ ሞልቶት ተመለከትኩ።+ በዚህ ጊዜ በግንባሬ መሬት ላይ ተደፋሁ።+ 5 ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ ስለ ይሖዋ ቤተ መቅደስ ደንቦችና ሕጎች የምነግርህን ሁሉ በትኩረት ተከታተል፤ በዓይኖችህም ተመልከት እንዲሁም በጥሞና አዳምጥ። የቤተ መቅደሱን መግቢያና የመቅደሱን መውጫዎች ሁሉ ልብ በል።+ 6 ዓመፀኛ ለሆኑት የእስራኤል ቤት ሰዎች እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ቤት ሰዎች ሆይ፣ አስጸያፊ ልማድ መፈጸማችሁ ከእንግዲህ ይብቃ! 7 ልባቸውንና ሥጋቸውን ያልተገረዙትን የባዕድ አገር ሰዎች ወደ መቅደሴ ስታመጧቸው ቤተ መቅደሴን ያረክሳሉ። በምትፈጽሟቸው አስጸያፊ ልማዶች ሁሉ የተነሳ ቃል ኪዳኔ እየፈረሰ ሳለ እናንተ ግን ምግቤን ይኸውም ስቡንና ደሙን ታቀርባላችሁ። 8 ቅዱስ ከሆኑት ነገሮቼ ጋር በተያያዘ ያለባችሁን ኃላፊነት አልተወጣችሁም።+ ይልቁንም በመቅደሴ ውስጥ ያሉትን ሥራዎች እንዲያከናውኑ ሌሎች ሰዎችን መደባችሁ።”’
9 “‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ልቡንና ሥጋውን ያልተገረዘ በእስራኤል የሚኖር ማንኛውም የባዕድ አገር ሰው ወደ መቅደሴ አይግባ።”’
10 “‘ይሁንና እስራኤላውያን አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቻቸውን* ለመከተል ሲሉ ከእኔ በራቁ ጊዜ ከእኔ የራቁት ሌዋውያን+ በደላቸው የሚያስከትልባቸውን መዘዝ ይቀበላሉ። 11 ከዚያም በመቅደሴ የቤተ መቅደሱን በሮች የሚቆጣጠሩ+ እንዲሁም በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚያገለግሉ አገልጋዮች ይሆናሉ። ሙሉ በሙሉ የሚቃጠለውን መባና መሥዋዕት ለሕዝቡ ያርዳሉ፤ ደግሞም ሕዝቡን ለማገልገል በፊታቸው ይቆማሉ። 12 አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻቸው ፊት ስላገለገሏቸውና የእስራኤል ቤት ሰዎች ኃጢአት እንዲሠሩ የማሰናከያ ድንጋይ ስለሆኑባቸው+ በመሐላ እጄን በእነሱ ላይ አንስቻለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፤ ‘እነሱም የሠሩት በደል የሚያስከትልባቸውን መዘዝ ይሸከማሉ። 13 ካህናቴ ሆነው ለማገልገል ወደ እኔ አይቀርቡም፤ ደግሞም ቅዱስ ወይም እጅግ ቅዱስ ወደሆኑት ነገሮቼ አይቀርቡም፤ በሠሯቸውም አስጸያፊ ነገሮች የተነሳ የሚደርስባቸውን ኀፍረት ይሸከማሉ። 14 ይሁንና በቤተ መቅደሱ ውስጥ በኃላፊነት እንዲሠሩ ይኸውም በውስጡ የሚካሄደውን አገልግሎትና መሠራት ያለበትን ሥራ ሁሉ እንዲያከናውኑ አደርጋለሁ።’+
15 “‘እስራኤላውያን ከእኔ በራቁ ጊዜ+ የመቅደሴን አገልግሎት ያከናውኑ የነበሩት የሳዶቅ+ ልጆች የሆኑት ሌዋውያን ካህናት ያገለግሉኝ ዘንድ ወደ እኔ ይቀርባሉ፤ ለእኔም ስቡንና+ ደሙን ለማቅረብ በፊቴ ይቆማሉ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 16 ‘ወደ መቅደሴ የሚገቡት እነሱ ናቸው፤ እኔን ለማገልገልም ወደ ገበታዬ* ይቀርባሉ፤+ በእኔ ፊት ያለባቸውንም ኃላፊነት ይወጣሉ።+
17 “‘ወደ ውስጠኛው ግቢ በሚያስገቡት በሮች በሚገቡበት ጊዜ በፍታ መልበስ ይኖርባቸዋል።+ በውስጠኛው ግቢ በሮች ወይም በውስጥ ባሉት ቦታዎች ሲያገለግሉ የሱፍ ልብስ መልበስ የለባቸውም። 18 በራሳቸው ላይ ከበፍታ የተሠራ ጥምጥም ያድርጉ፤ በወገባቸውም ላይ የበፍታ ቁምጣ ይታጠቁ።+ እንዲያልባቸው የሚያደርግ ማንኛውም ዓይነት ልብስ መልበስ የለባቸውም። 19 ወደ ውጨኛው ግቢ ይኸውም ሕዝቡ ወዳለበት ግቢ ከመውጣታቸው በፊት አገልግሎታቸውን ሲያከናውኑ ለብሰውት የነበረውን ልብስ አውልቀው+ ቅዱስ በሆኑት የመመገቢያ ክፍሎች*+ ውስጥ ማስቀመጥ አለባቸው። ከዚያም ቅድስናን ወደ ሕዝቡ እንዳያስተላልፉ* ሌላ ልብስ ይለብሳሉ። 20 ራሳቸውን አይላጩ፤+ ወይም ፀጉራቸውን አያስረዝሙ። ይልቁንም ፀጉራቸውን ይከርክሙ። 21 ካህናቱ ወደ ውስጠኛው ግቢ በሚገቡበት ጊዜ የወይን ጠጅ አይጠጡ።+ 22 መበለት የሆነች ወይም ከባሏ የተፋታች ሴት አያግቡ፤+ ይሁንና የእስራኤል ዘር የሆነች ድንግል ወይም የካህን ሚስት የነበረች መበለት ማግባት ይችላሉ።’+
23 “‘ቅዱስ በሆነና ተራ በሆነ ነገር መካከል ያለውን ልዩነት ለሕዝቤ ያስተምሩ፤ ንጹሕ ባልሆነውና ንጹሕ በሆነው ነገር መካከል ያለውንም ልዩነት ያሳውቋቸው።+ 24 ፍርድ ነክ ጉዳዮችን ይዳኙ፤+ በድንጋጌዎቼ መሠረት ይፍረዱ።+ ከሁሉም በዓሎቼ ጋር የተያያዙትን ሕጎቼንና ደንቦቼን ይጠብቁ፤+ እንዲሁም ሰንበቶቼን ይቀድሱ። 25 ወደ ሞተ ሰው አይቅረቡ፤ አለዚያ ይረክሳሉ። ሆኖም ለአባታቸው፣ ለእናታቸው፣ ለወንድ ወይም ለሴት ልጃቸው፣ ለወንድማቸው ወይም ላላገባች እህታቸው ሲሉ ራሳቸውን ሊያረክሱ ይችላሉ።+ 26 ደግሞም አንድ ካህን ከነጻ በኋላ ለሰባት ቀን ሊያቆዩት ይገባል። 27 በተቀደሰው ስፍራ ለማገልገል፣ በውስጠኛው ግቢ ወደሚገኘው ቅዱስ ስፍራ በሚገባበት ቀን የኃጢአት መባውን ያቅርብ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
28 “‘የእነሱም ውርሻ ይህ ይሆናል፦ ውርሻቸው እኔ ነኝ።+ በእስራኤል ምንም ዓይነት ርስት አትስጧቸው፤ ርስታቸው እኔ ነኝና። 29 የእህሉን መባ፣+ የኃጢአቱን መባና የበደሉን መባ ይበላሉ፤+ በእስራኤል ምድር ቅዱስ ለሆነ ነገር የተለየ ሁሉ የእነሱ ይሆናል።+ 30 መጀመሪያ ላይ ከደረሱት ፍሬዎች ሁሉና መዋጮ አድርጋችሁ ከምትሰጡት ነገር ሁሉ ምርጥ የሆነው ለካህናቱ ይሆናል።+ የተፈጨውንም የእህል በኩር ለካህኑ ስጡ።+ እንዲህ የምታደርጉ ከሆነ ቤተሰቦቻችሁ ይባረካሉ።+ 31 ካህናቱ ሞቶ የተገኘውንም ሆነ በአራዊት የተዘነጠለውን ማንኛውም ወፍ ወይም እንስሳ መብላት የለባቸውም።’+
45 “‘ምድሪቱን ርስት አድርጋችሁ በምትከፋፈሉበት ጊዜ+ ከምድሪቱ ላይ ቅዱስ የሆነ ድርሻ ለይሖዋ መዋጮ አድርጋችሁ ስጡ።+ ርዝመቱ 25,000 ክንድ፣* ወርዱ ደግሞ 10,000 ክንድ ይሁን።+ ስፍራው በሙሉ* ቅዱስ ድርሻ ይሆናል። 2 በዚህ ቦታ ውስጥ ለቅዱሱ ስፍራ የሚያገለግል 500 ክንድ በ500 ክንድ*+ የሆነ አራት ማዕዘን ቦታ ይኖራል፤ በሁሉም በኩል 50 ክንድ የሆነ የግጦሽ መሬት ይኖረዋል።+ 3 ከተለካው መሬት ላይ ርዝመቱ 25,000፣ ወርዱ ደግሞ 10,000 የሆነ ስፍራ ለካ፤ እጅግ ቅዱስ የሆነውም መቅደስ በዚያ ውስጥ ይሆናል። 4 ይሖዋን ለማገልገል ለሚቀርቡትና በመቅደሱ ለሚያገለግሉት ካህናት ቅዱስ ድርሻ ይሆናል።+ ለቤቶቻቸው እንዲሁም ለመቅደሱ የሚሆን ቅዱስ ስፍራ ይሆናል።
5 “‘በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚያገለግሉት ሌዋውያን ርዝመቱ 25,000 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 10,000 ክንድ የሆነ ድርሻ ይኖራቸዋል፤+ እነሱም 20 የመመገቢያ ክፍሎችን*+ ርስት አድርገው ይወስዳሉ።
6 “‘እናንተም ለከተማዋ እንደ ርስት እንዲሆን ርዝመቱ 25,000 ክንድ (መዋጮ ሆኖ ከተሰጠው ቅዱስ ስፍራ ትይዩ የሆነ) ወርዱ ደግሞ 5,000 ክንድ የሆነ ቦታ ትሰጣላችሁ።+ ይህም ለእስራኤል ቤት ሁሉ ይሆናል።
7 “‘አለቃው መዋጮ ሆኖ ከተሰጠው ቅዱስ ስፍራና ለከተማዋ ከተሰጠው ቦታ ግራና ቀኝ መሬት ይኖረዋል። መሬቱ መዋጮ ሆኖ ከተሰጠው ቅዱስ ስፍራና ከከተማዋ ይዞታ አጠገብ ይሆናል። ደግሞም በስተ ምዕራብና በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ ይሆናል። ከምዕራቡ ወሰን እስከ ምሥራቁ ወሰን ድረስ ያለው ርዝመት ለአንዱ ነገድ ከተሰጠው ድርሻ ጋር ተመሳሳይ ነው።+ 8 ይህ መሬት በእስራኤል ምድር የእሱ ርስት ይሆናል። ከእንግዲህ አለቆቼ በሕዝቤ ላይ ግፍ አይፈጽሙም፤+ ምድሪቱንም ለእስራኤል ቤት ሰዎች በየነገዳቸው ይሰጧቸዋል።’+
9 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እናንተ የእስራኤል አለቆች፣ በጣም አብዝታችሁታል!’
“‘ግፍና ጭቆና መፈጸማችሁን አቁሙ፤ ፍትሕንና ጽድቅን አድርጉ።+ የሕዝቤን ንብረት መቀማታችሁን ተዉ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 10 ‘ትክክለኛ ሚዛን፣ ትክክለኛ የኢፍ መስፈሪያና* ትክክለኛ የባዶስ መስፈሪያ* ተጠቀሙ።+ 11 ለኢፍ መስፈሪያና ለባዶስ መስፈሪያ ቋሚ የሆነ መመዘኛ መኖር አለበት። የባዶስ መስፈሪያው አንድ አሥረኛ ሆሜር* የሚይዝ ይሁን፤ የኢፍ መስፈሪያውም አንድ አሥረኛ ሆሜር የሚይዝ ይሁን። ሆሜር መደበኛ መመዘኛ ይሆናል። 12 አንድ ሰቅል*+ 20 ጌራ* ይሁን። ደግሞም 20 ሰቅል፣ 25 ሰቅልና 15 ሰቅል አንድ ላይ ሲደመር አንድ ማኔህ* ይሁንላችሁ።’
13 “‘የምትሰጡት መዋጮ ይህ ነው፦ ከእያንዳንዱ ሆሜር ስንዴ የኢፍ አንድ ስድስተኛ፣ ከእያንዳንዱ ሆሜር ገብስ ደግሞ የኢፍ አንድ ስድስተኛ መዋጮ ታደርጋላችሁ። 14 የሚሰጠው ዘይት የሚለካው በባዶስ መስፈሪያ ይሆናል። አንድ ባዶስ፣ የቆሮስ* አንድ አሥረኛ ነው፤ አሥር ባዶስ ደግሞ አንድ ሆሜር ነው፤ አሥር ባዶስ ከአንድ ሆሜር ጋር እኩል ነውና። 15 ደግሞም ከእስራኤል መንጎች መካከል ከየሁለት መቶው አንድ በግ ስጡ። እነዚህ ስጦታዎች ለሕዝቡ ማስተሰረያ እንዲሆኑ+ ለእህል መባ፣+ ሙሉ በሙሉ ለሚቃጠል መባና+ ለኅብረት መሥዋዕት+ ይውላሉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
16 “‘የምድሪቱ ነዋሪ ሁሉ ይህን መዋጮ ለእስራኤል አለቃ ይሰጣል።+ 17 አለቃውም በበዓላት፣ አዲስ ጨረቃ በምትወጣበት ወቅት፣ በየሰንበቱና+ ለእስራኤል ቤት ሰዎች በተወሰኑት በዓላት ወቅት ሁሉ+ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠለውን መባ፣+ የእህሉን መባና+ የመጠጡን መባ የማቅረብ ኃላፊነት አለበት።+ ለእስራኤል ቤት ሰዎች ማስተሰረያ እንዲሆን የኃጢአት መባ፣ የእህል መባ፣ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባና የኅብረት መሥዋዕት የሚያቀርበው እሱ ነው።’
18 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ከከብቶቹ መካከል ምንም እንከን የሌለበት አንድ ወይፈን ወስደህ መቅደሱን ከኃጢአት አንጻው።+ 19 ካህኑ የኃጢአት መባ ሆኖ ከቀረበው ደም የተወሰነውን ወስዶ በቤተ መቅደሱ መቃን፣+ በመሠዊያው ዙሪያ ባለው እርከን አራት ማዕዘኖችና በውስጠኛው ግቢ በር መቃን ላይ ያድርግ። 20 አንድ ሰው በስህተትና ባለማወቅ ኃጢአት ቢሠራ+ ከወሩ በሰባተኛው ቀን እንዲሁ አድርግ፤ እናንተም ለቤተ መቅደሱ ማስተሰረያ ታቀርባላችሁ።+
21 “‘በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በ14ኛው ቀን የፋሲካን በዓል ታከብራላችሁ።+ ለሰባት ቀን ቂጣ* ትበላላችሁ።+ 22 በዚያም ቀን አለቃው ለራሱና ለምድሩ ነዋሪ ሁሉ የኃጢአት መባ እንዲሆን አንድ ወይፈን ያቀርባል።+ 23 በዓሉ በሚከበርባቸው በሰባቱ ቀናት፣ በእያንዳንዱ ቀን፣ እንከን የሌለባቸውን ሰባት ወይፈኖችና እንከን የሌለባቸውን ሰባት አውራ በጎች ለይሖዋ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ አድርጎ ያቀርባል፤+ ደግሞም ለኃጢአት መባ በየዕለቱ አንድ አውራ ፍየል ያቀርባል። 24 በተጨማሪም ለእያንዳንዱ ወይፈን አንድ ኢፍ፣ ለእያንዳንዱም አውራ በግ አንድ ኢፍ የእህል መባ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ኢፍ አንድ ሂን* ዘይት ያቅርብ።
25 “‘በሰባተኛው ወር፣ ከወሩም በ15ኛው ቀን፣ በበዓሉ ወቅት ለሰባት ቀናት+ ይህንኑ የኃጢአት መባ፣ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ፣ የእህል መባና ዘይት ያቅርብ።’”
46 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ከምሥራቅ ትይዩ የሆነው የውስጠኛው ግቢ በር+ በስድስቱ የሥራ ቀናት+ ዝግ እንደሆነ ይቆይ፤+ ሆኖም በሰንበት ቀንና አዲስ ጨረቃ በምትወጣበት ቀን ይከፈት። 2 አለቃው ከውጭ በኩል በበሩ በረንዳ ገብቶ+ በበሩ መቃን አጠገብ ይቆማል። ካህናቱ የእሱን ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባና የኅብረት መሥዋዕት ያቀርባሉ፤ እሱም በበሩ ደፍ ላይ ይሰግዳል፤ ከዚያም ይወጣል። በሩ ግን እስከ ምሽት ድረስ አይዘጋ። 3 የምድሪቱም ነዋሪዎች በየሰንበቱና አዲስ ጨረቃ በምትወጣበት ቀን+ በበሩ መግቢያ ላይ በይሖዋ ፊት ይሰግዳሉ።
4 “‘አለቃው በሰንበት ቀን እንከን የሌለባቸው ስድስት ተባዕት የበግ ጠቦቶችና እንከን የሌለበት አንድ አውራ በግ ለይሖዋ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ አድርጎ ማቅረብ ይኖርበታል።+ 5 ለአውራ በጉ አንድ ኢፍ* የእህል መባ፣ ለተባዕት የበግ ጠቦቶቹም መስጠት የሚችለውን ያህል የእህል መባ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ኢፍ አንድ ሂን* ዘይት ያቀርባል።+ 6 አዲስ ጨረቃ በምትወጣበት ቀን ከከብቶቹ መካከል እንከን የሌለበት አንድ ወይፈን፣ ስድስት ተባዕት የበግ ጠቦቶችና አንድ አውራ በግ ያቀርባል፤ ሁሉም እንከን የሌለባቸው ይሁኑ።+ 7 ለወይፈኑ አንድ ኢፍ፣ ለአውራ በጉም አንድ ኢፍ፣ ለተባዕት የበግ ጠቦቶቹ ደግሞ መስጠት የሚችለውን ያህል እንደ እህል መባ አድርጎ ያቅርብ። እንዲሁም ለእያንዳንዱ ኢፍ አንድ ሂን ዘይት ያቅርብ።
8 “‘አለቃው ሲገባ፣ በበሩ በረንዳ በኩል ይግባ፤ ሲወጣም በዚያው በኩል ይውጣ።+ 9 የምድሪቱም ነዋሪዎች በበዓል ወቅቶች በይሖዋ ፊት በሚቀርቡበት ጊዜ፣+ የአምልኮ ሥርዓት ለመፈጸም በሰሜን በር+ የሚገቡ፣ በደቡብ በር ይውጡ፤ በደቡብ በር+ የሚገቡ ደግሞ በሰሜን በር ይውጡ። ማንም ሰው በገባበት በር ተመልሶ አይውጣ፤ ይልቁንም በተቃራኒ አቅጣጫ ባለው በር ይውጣ። 10 በመካከላቸው ያለው አለቃ እነሱ በሚገቡበት ጊዜ ይግባ፤ እነሱ በሚወጡበት ጊዜም ይውጣ። 11 በበዓላትና በተወሰኑት የበዓል ወቅቶች፣ ለወይፈኑ አንድ ኢፍ፣ ለአውራ በጉ አንድ ኢፍ፣ ለተባዕት የበግ ጠቦቶቹ ደግሞ መስጠት የሚችለውን ያህል የእህል መባ ያቅርብ፤ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ኢፍ አንድ ሂን ዘይት ያቅርብ።+
12 “‘አለቃው ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባን+ ወይም የኅብረት መሥዋዕትን የፈቃደኝነት መባ አድርጎ ለይሖዋ የሚያቀርብ ከሆነ በምሥራቅ ትይዩ ያለው በር ይከፈትለታል፤ በሰንበት ቀን እንደሚያደርገው ሁሉ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠለውን መባውንና የኅብረት መሥዋዕቱን ያቀርባል።+ ከወጣ በኋላ በሩ ይዘጋ።+
13 “‘በየዕለቱ፣ እንከን የሌለበትን የአንድ ዓመት ተባዕት የበግ ጠቦት ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ አድርገህ ለይሖዋ አቅርብ።+ ይህን በየማለዳው አድርግ። 14 ከዚህም ጋር በየማለዳው የኢፍ አንድ ስድስተኛ የእህል መባ እንዲሁም በላመው ዱቄት ላይ የሚፈስ የሂን አንድ ሦስተኛ ዘይት የዘወትር የእህል መባ አድርገህ ለይሖዋ አቅርብ። ይህ የዘላለም ደንብ ነው። 15 ተባዕቱን የበግ ጠቦት፣ የእህል መባውንና ዘይቱን ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል የዘወትር መባ አድርገው በየማለዳው ያቅርቡ።’
16 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አለቃው ለወንዶች ልጆቹ፣ ለእያንዳንዳቸው ውርስ አድርጎ ስጦታ ቢሰጣቸው፣ ስጦታው የልጆቹ ንብረት ይሆናል። ይህ በውርስ ያገኙት ንብረታቸው ነው። 17 ሆኖም ከአገልጋዮቹ ለአንዱ ከርስቱ ላይ ስጦታ ቢሰጥ፣ ነፃ እስከሚወጣበት ዓመት+ ድረስ ስጦታው የእሱ ይሆናል፤ ከዚያም ለአለቃው ይመለስለታል። ርስቱን ለዘለቄታው የራሳቸው አድርገው መያዝ የሚችሉት ወንዶች ልጆቹ ብቻ ናቸው። 18 አለቃው ሕዝቡን ከይዞታቸው በማፈናቀል የትኛውንም ርስት ሊወስድባቸው አይገባም። ከሕዝቤ መካከል አንዳቸውም ከይዞታቸው እንዳይፈናቀሉ ለወንዶች ልጆቹ ርስት መስጠት ያለበት ከራሱ ይዞታ ላይ ነው።’”
19 ከዚያም ከሰሜን ትይዩ ወደሚገኙት ቅዱስ ወደሆኑት የካህናቱ መመገቢያ ክፍሎች*+ ከሚወስደው በር አጠገብ ባለው መግቢያ+ በኩል አድርጎ አመጣኝ፤ በዚያም በምዕራብ በኩል ከበስተ ኋላ አንድ ቦታ አየሁ። 20 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “ካህናቱ አንድም ነገር ወደ ውጨኛው ግቢ ይዘው በመውጣት ቅድስናን ወደ ሕዝቡ እንዳያስተላልፉ*+ ሲባል የበደል መባውንና የኃጢአት መባውን የሚቀቅሉት እንዲሁም የእህል መባውን የሚጋግሩት+ በዚህ ቦታ ነው።”
21 ከዚያም ወደ ውጨኛው ግቢ ከወሰደኝ በኋላ በአራቱ የግቢው ማዕዘኖች በኩል አዞረኝ፤ በውጨኛው ግቢ በአራቱም ማዕዘኖች በኩል ግቢ አየሁ። 22 በአራቱም የግቢው ማዕዘኖች፣ ርዝመታቸው 40 ክንድ፣* ወርዳቸው 30 ክንድ የሆኑ ትናንሽ ግቢዎች ነበሩ። አራቱም መጠናቸው እኩል ነበር።* 23 በአራቱም ዙሪያ እርከን* የነበረ ሲሆን ከእርከኑ ሥር መባዎቹ የሚቀቀሉባቸው ቦታዎች ተሠርተው ነበር። 24 ከዚያም “እነዚህ፣ የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች የሕዝቡን መሥዋዕት የሚቀቅሉባቸው+ ቦታዎች ናቸው” አለኝ።
47 ከዚያም ወደ ቤተ መቅደሱ መግቢያ+ መልሶ አመጣኝ፤ በዚያም ከቤተ መቅደሱ ደፍ ሥር ወደ ምሥራቅ የሚፈስ ውኃ ተመለከትኩ፤+ የቤተ መቅደሱ ፊት ከምሥራቅ ትይዩ ነበር። ውኃው ከቤተ መቅደሱ በስተ ቀኝ ከሥር ወጥቶ ከመሠዊያው በስተ ደቡብ ይወርድ ነበር።
2 ከዚያም ወደ ሰሜን በር+ በሚወስደው መንገድ በኩል አምጥቶ ወደ ውጭ ካወጣኝ በኋላ ከምሥራቅ ትይዩ ወዳለው የውጨኛው በር+ አዙሮ አመጣኝ፤ እኔም በስተ ቀኝ በኩል ቀስ እያለ የሚፈስ ውኃ አየሁ።
3 ሰውየው መለኪያ ገመድ በእጁ ይዞ+ ወደ ምሥራቅ በመሄድ 1,000 ክንድ* ለካ፤ ከዚያም በውኃው መካከል እንዳልፍ አደረገኝ፤ ውኃው እስከ ቁርጭምጭሚት ይደርስ ነበር።
4 ከዚያም 1,000 ክንድ ለካ፤ በውኃውም መካከል እንዳልፍ አደረገኝ፤ ውኃውም እስከ ጉልበት ደረሰ።
ደግሞም 1,000 ክንድ ለካ፤ በውኃውም መካከል እንዳልፍ አደረገኝ፤ ውኃውም እስከ ወገብ ደረሰ።
5 እንደገናም 1,000 ክንድ በለካ ጊዜ ውኃው ልሻገረው የማልችል ወንዝ ሆነ፤ እጅግ ጥልቅ ከመሆኑ የተነሳ በዋና ካልሆነ በስተቀር በእግር ሊሻገሩት የማይቻል ወንዝ ሆኖ ነበር።
6 እሱም “የሰው ልጅ ሆይ፣ ይህን ታያለህ?” ሲል ጠየቀኝ።
ከዚያም መልሶ ወደ ጅረቱ ዳርቻ ወሰደኝ። 7 በተመለስኩ ጊዜ በጅረቱ ዳርቻ፣ በግራና በቀኝ በጣም ብዙ ዛፎች አየሁ።+ 8 ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “ይህ ውኃ በስተ ምሥራቅ ወዳለው ምድር ይፈስሳል፤ አረባን*+ አቋርጦም ይወርዳል፤ ወደ ባሕሩም* ይገባል። ወደ ባሕሩ በሚገባበት ጊዜ+ በዚያ ያለው ውኃ ይፈወሳል። 9 ውኃዎቹ* በሚፈስሱበት ቦታ ሁሉ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሕያዋን ፍጥረታት* በሕይወት መኖር ይችላሉ። ይህ ውኃ ወደዚያ ስለሚፈስ በዚያ እጅግ ብዙ ዓሣዎች ይኖራሉ። የባሕሩ ውኃ ይፈወሳል፤ ጅረቱ በሚፈስበት ቦታ ያለው ነገር ሁሉ በሕይወት ይኖራል።
10 “ከኤንገዲ+ እስከ ኤንዔግላይም ድረስ ዓሣ አጥማጆች በዳርቻው ይቆማሉ፤ በዚያም መረባቸውን የሚያሰጡበት ቦታ ይኖራል። በታላቁ ባሕር*+ እንዳሉት ዓሣዎች በዚያም ስፍር ቁጥር የሌላቸው ብዙ ዓይነት ዓሣዎች ይኖራሉ።
11 “ረግረጋማ የሆኑና ውኃ ያቆሩ ቦታዎች ይኖሩታል፤ እነዚህ ቦታዎች አይፈወሱም። ጨዋማ እንደሆኑ ይቀራሉ።+
12 “በወንዙ ዳርና ዳር ለመብል የሚሆኑ ብዙ ዓይነት ዛፎች ይበቅላሉ። ቅጠላቸው አይጠወልግም፤ ፍሬ ማፍራትም አያቆሙም። ከመቅደሱ የሚወጣውን ውኃ+ ስለሚጠጡ በየወሩ አዲስ ፍሬ ይሰጣሉ። ፍሬያቸው ለመብል፣ ቅጠላቸውም ለመድኃኒት ይሆናል።”+
13 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ለ12ቱ የእስራኤል ነገዶች ርስት አድርጋችሁ የምታከፋፍሏት ክልል ይህች ናት፤ ዮሴፍ ሁለት ድርሻ ይኖረዋል።+ 14 እናንተ ትወርሷታላችሁ፤ እኩል ድርሻም ታገኛላችሁ።* ለአባቶቻችሁ ይህችን ምድር እንደምሰጣቸው ምዬላቸው ነበር፤+ አሁንም ይህች ምድር ርስት ሆና ተሰጥታችኋለች።*
15 “በስተ ሰሜን በኩል የምድሪቱ ወሰን ይህ ነው፦ ከታላቁ ባሕር ተነስቶ ወደ ሄትሎን+ በሚወስደው መንገድ በኩል እስከ ጼዳድ+ ይደርሳል፤ 16 ከዚያም እስከ ሃማት፣+ እስከ ቤሮታ+ እንዲሁም በደማስቆ ክልልና በሃማት ክልል መካከል እስካለው እስከ ሲብራይም ብሎም በሃውራን+ ወሰን እስከሚገኘው እስከ ሃጸርሃቲኮን ይዘልቃል። 17 ስለዚህ ወሰኑ ከባሕሩ በመነሳት በስተ ሰሜን በደማስቆ ድንበርና በሃማት+ ድንበር በኩል እስከ ሃጻርኤናን+ ድረስ ይዘልቃል። በሰሜን በኩል ወሰኑ ይህ ነው።
18 “በምሥራቅ በኩል ወሰኑ ከሃውራን እስከ ደማስቆ እንዲሁም በዮርዳኖስ አጠገብ ከጊልያድ+ እስከ እስራኤል ምድር ይዘልቃል። ከወሰኑ አንስቶ እስከ ምሥራቁ ባሕር* ድረስ ትለካላችሁ። በምሥራቅ በኩል ወሰኑ ይህ ነው።
19 “በደቡብ በኩል ያለው ወሰን* ከትዕማር ተነስቶ እስከ መሪባትቃዴስ+ ውኃዎች፣ ከዚያም እስከ ደረቁ ወንዝና* እስከ ታላቁ ባሕር+ ይደርሳል። በደቡብ በኩል ወሰኑ* ይህ ነው።
20 “በምዕራብ በኩል ታላቁ ባሕር የሚገኝ ሲሆን ይህም ከወሰኑ አንስቶ ከሌቦሃማት*+ ትይዩ እስካለው ቦታ ድረስ ይዘልቃል። በምዕራብ በኩል ወሰኑ ይህ ነው።”
21 “ይህችን ምድር ለእናንተ ይኸውም ለ12ቱ የእስራኤል ነገዶች ታከፋፍላላችሁ። 22 ምድሪቱን ለእናንተ እንዲሁም በመካከላችሁ በመኖር ልጆች ለወለዱት፣ አብረዋችሁ ለሚኖሩት የባዕድ አገር ሰዎች ርስት አድርጋችሁ አከፋፍሉ፤ እነሱም የአገሪቱ ተወላጆች እንደሆኑት እስራኤላውያን ይሆናሉ። እንደ እስራኤል ነገዶች ከእናንተ ጋር ርስት ያገኛሉ። 23 ከባዕድ አገር ለመጣው ሰው በሚኖርበት ነገድ ክልል ውስጥ ርስት ልትሰጡት ይገባል” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
48 “ከሰሜናዊ ጫፍ አንስቶ የነገዶቹ ስም ይህ ነው፦ የዳን ድርሻ+ የሄትሎንን መንገድ ተከትሎ እስከ ሌቦሃማት*+ እንዲሁም በስተ ሰሜን በደማስቆ ድንበር በኩል፣ ከሃማት+ አጠገብ እስካለው እስከ ሃጻርኤናን ድረስ ይዘልቃል፤ ድርሻውም ከምሥራቁ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። 2 የአሴር ድርሻ+ ከዳን ምድር ጋር የሚዋሰን ሲሆን ከምሥራቁ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። 3 የንፍታሌም ድርሻ+ ከአሴር ምድር ጋር የሚዋሰን ሲሆን ከምሥራቁ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። 4 የምናሴ ድርሻ+ ከንፍታሌም ምድር ጋር የሚዋሰን ሲሆን ከምሥራቁ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። 5 የኤፍሬም ድርሻ ከምናሴ ምድር ጋር የሚዋሰን+ ሲሆን ከምሥራቁ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። 6 የሮቤል ድርሻ ከኤፍሬም ምድር ጋር የሚዋሰን+ ሲሆን ከምሥራቁ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። 7 የይሁዳ ድርሻ ከሮቤል ምድር ጋር የሚዋሰን+ ሲሆን ከምሥራቁ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። 8 በይሁዳ ድንበር፣ ከምሥራቁ ወሰን አንስቶ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ መዋጮ አድርጋችሁ ለመስጠት የምትለዩት መሬት ወርዱ 25,000 ክንድ* ይሁን፤+ ደግሞም ይህ መሬት ከምሥራቁ ወሰን አንስቶ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ርዝመቱ ከሌሎቹ ነገዶች ድርሻ ጋር እኩል ይሁን። መቅደሱ በመካከሉ ይሆናል።
9 “መዋጮ አድርጋችሁ በመስጠት ለይሖዋ የምትለዩት መሬት ርዝመቱ 25,000 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 10,000 ክንድ ይሆናል። 10 ይህ ለካህናቱ መዋጮ ሆኖ የሚሰጥ ቅዱስ ስፍራ ይሆናል።+ በሰሜን በኩል 25,000 ክንድ፣ በምዕራብ በኩል 10,000፣ በምሥራቅ በኩል 10,000፣ በደቡብ በኩል ደግሞ 25,000 ይሆናል። የይሖዋ መቅደስ በመካከሉ ይሆናል። 11 ይህ የሳዶቅ ልጆች+ ለሆኑት የተቀደሱ ካህናት ይሆናል፤ እነሱ በእኔ ፊት ያለባቸውን ኃላፊነት ተወጥተዋል፤ እንዲሁም እስራኤላውያንና ሌዋውያን በባዘኑ ጊዜ+ ከእነሱ ጋር አልባዘኑም። 12 በሌዋውያን ድንበር በኩል፣ እጅግ ቅዱስ ተደርጎ ከተለየውና መዋጮ ሆኖ ከተሰጠው መሬት ላይ ድርሻ ያገኛሉ።
13 ሌዋውያኑ ከካህናቱ መሬት አጠገብ ርዝመቱ 25,000 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 10,000 ክንድ የሆነ ድርሻ ይኖራቸዋል። (አጠቃላይ ርዝመቱ 25,000፣ ወርዱ ደግሞ 10,000 ይሆናል።) 14 ምርጥ ከሆነው ከዚህ የመሬቱ ድርሻ ላይ የትኛውንም ቦታ መሸጥ፣ መለወጥ ወይም ለሌሎች አሳልፈው መስጠት የለባቸውም፤ ለይሖዋ የተቀደሰ ነውና።
15 “ደግሞም 25,000 ክንድ ከሆነው ወሰን አጠገብ የሚገኘው፣ ወርዱ 5,000 ክንድ የሆነው የቀረው ቦታ ለከተማዋ ቅዱስ ያልሆነ አገልግሎት+ ይኸውም ለመኖሪያ ቤትና ለግጦሽ መሬት ይውላል። ከተማዋ በመካከሉ ትሆናለች።+ 16 የከተማዋም መጠን ይህ ነው፦ የሰሜኑ ወሰን 4,500፣ የደቡቡ ወሰን 4,500፣ የምሥራቁ ወሰን 4,500 እንዲሁም የምዕራቡ ወሰን 4,500 ክንድ ነው። 17 የከተማዋ የግጦሽ መሬት በስተ ሰሜን 250፣ በስተ ደቡብ 250፣ በስተ ምሥራቅ 250 እና በስተ ምዕራብ 250 ክንድ ይሆናል።
18 “የቀረው ድርሻ ርዝመቱ፣ መዋጮ ሆኖ ከተሰጠው ቅዱስ ስፍራ+ ጋር እኩል ይሆናል፤ ይኸውም በስተ ምሥራቅ 10,000፣ በስተ ምዕራብም 10,000 ክንድ ይሆናል። ርዝመቱ መዋጮ ሆኖ ከተሰጠው ቅዱስ ስፍራ ጋር እኩል ይሆናል፤ በዚያም የሚመረተው ከተማዋን ለሚያገለግሉ ምግብ ይሆናል። 19 ከተማዋን የሚያገለግሉ ከሁሉም የእስራኤል ነገዶች የተውጣጡ ሰዎች መሬቱን ያርሳሉ።+
20 “በመዋጮ የተሰጠው መሬት በአጠቃላይ አራቱም ማዕዘኑ እኩል ሲሆን እያንዳንዱ ማዕዘን 25,000 ክንድ ነው። መዋጮ ሆኖ የተሰጠ ቅዱስ ስፍራና የከተማዋ ይዞታ አድርጋችሁ ትለዩታላችሁ።
21 “መዋጮ ሆኖ ከተሰጠው ቅዱስ ስፍራና ከከተማዋ ይዞታ ግራና ቀኝ ያለው የቀረው ቦታ የአለቃው ይሆናል።+ ይህ ቦታ በመዋጮ ከተሰጠው መሬት በስተ ምሥራቅና በስተ ምዕራብ ከሚገኙት 25,000 ክንድ ከሆኑት ወሰኖች አጠገብ ይሆናል። በአቅራቢያው ካሉት የነገዶቹ ድርሻዎች ጋር ይዋሰናል፤ ይህም ለአለቃው ይሆናል። መዋጮ ሆኖ የተሰጠው ቅዱስ ስፍራና የቤተ መቅደሱ መቅደስ በመካከሉ ይሆናል።
22 “የሌዋውያኑ ይዞታና የከተማዋ ይዞታ በአለቃው ክልል መካከል ይሆናል። የአለቃው ክልል በይሁዳ ድንበርና+ በቢንያም ድንበር መካከል ይሆናል።
23 “የቀሩትን ነገዶች በተመለከተ፣ የቢንያም ድርሻ ከምሥራቁ ወሰን እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው።+ 24 የስምዖን ድርሻ ከቢንያም ምድር ጋር የሚዋሰን+ ሲሆን ከምሥራቁ ወሰን እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። 25 የይሳኮር ድርሻ+ ከስምዖን ምድር ጋር የሚዋሰን ሲሆን ከምሥራቁ ወሰን እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። 26 የዛብሎን ድርሻ ከይሳኮር ምድር ጋር የሚዋሰን+ ሲሆን ከምሥራቁ ወሰን እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው።+ 27 የጋድ ድርሻ ከዛብሎን ምድር ጋር የሚዋሰን+ ሲሆን ከምሥራቁ ወሰን እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። 28 በጋድ ወሰን በኩል ያለው ደቡባዊ ድንበር ከትዕማር+ እስከ የመሪባትቃዴስ ውኃዎች፣+ እስከ ደረቁ ወንዝና*+ እስከ ታላቁ ባሕር* ይዘልቃል።
29 “ለእስራኤል ነገዶች ርስት አድርጋችሁ የምታከፋፍሏት ምድር ይህች ናት፤+ ይህም ድርሻቸው ይሆናል”+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
30 “የከተማዋ መውጫዎች እነዚህ ይሆናሉ፦ በሰሜን በኩል ያለው 4,500 ክንድ ነው።+
31 “የከተማዋ በሮች በእስራኤል ነገዶች ስም ይሰየማሉ። በስተ ሰሜን ሦስት በሮች ያሉ ሲሆን አንዱ በር ለሮቤል፣ አንዱ በር ለይሁዳ፣ አንዱ በር ደግሞ ለሌዊ ይሆናል።
32 “ምሥራቃዊው አቅጣጫ 4,500 ክንድ ርዝመት የሚኖረው ሲሆን ሦስት በሮች ይኖሩታል፦ አንዱ በር ለዮሴፍ፣ አንዱ በር ለቢንያም፣ አንዱ በር ደግሞ ለዳን ይሆናል።
33 “ደቡባዊው አቅጣጫ 4,500 ክንድ ርዝመት የሚኖረው ሲሆን ሦስት በሮች ይኖሩታል፦ አንዱ በር ለስምዖን፣ አንዱ በር ለይሳኮር፣ አንዱ በር ደግሞ ለዛብሎን ይሆናል።
34 “ምዕራባዊው አቅጣጫ 4,500 ክንድ ርዝመት የሚኖረው ሲሆን ሦስት በሮች ይኖሩታል፦ አንዱ በር ለጋድ፣ አንዱ በር ለአሴር፣ አንዱ በር ደግሞ ለንፍታሌም ይሆናል።
35 “ዙሪያውን መጠኑ 18,000 ክንድ ይሆናል። ከዚያን ቀን ጀምሮ ከተማዋ ‘ይሖዋ በዚያ አለ’ ተብላ ትጠራለች።”+
“አምላክ ያበረታል” የሚል ትርጉም አለው።
ቃል በቃል “እጅ።”
ወይም “መብረቅ።”
የሚያብረቀርቅ የወርቅና የብር ቅይጥ።
የሠረገላ ተሽከርካሪ እግር።
ቃል በቃል “የሕያው ፍጡሩ መንፈስ።”
“ቀጥ ብለው ተዘርግተው ነበር” ማለትም ሊሆን ይችላል።
“የሰው ልጅ” የሚለው አገላለጽ በሕዝቅኤል መጽሐፍ ውስጥ 93 ጊዜ የሚገኝ ሲሆን ይህ የመጀመሪያው ነው።
ወይም “ፊታቸውን ወደማይመልሱና።”
“ሕዝቡ ልበ ደንዳኖችና እንደሚዋጉ ነገሮች ቢሆኑም” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “የመጽሐፍ ጥቅልል።”
ወይም “የሐዘን እንጉርጉሮ።”
ቃል በቃል “ያገኘኸውን ብላ።”
ቃል በቃል “የሕዝብህ ወንዶች ልጆች።”
የሠረገላ ተሽከርካሪ እግር።
ወይም “ይሁንና ስለ ደሙ አንተን ተጠያቂ አደርግሃለሁ።”
ወይም “ነፍስህን።”
ወይም “ኢፍትሐዊ ድርጊት ቢፈጽም።”
ወይም “ይሁንና ስለ ደሙ አንተን ተጠያቂ አደርግሃለሁ።”
ወይም “ነፍስህን።”
ቃል በቃል “በላዩ ላይ።” የሕዝቅኤልን ግራ ጎን ያመለክታል።
ወደ 230 ግራም ገደማ ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
ወደ 0.6 ሊትር ገደማ ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
ወይም “ነፍሴ . . . በልታ የረከሰችበት ጊዜ የለም።”
ወይም “የገማም።”
ቃል በቃል “የዳቦ በትሮቹን እሰብራለሁ።” ዳቦ ለማስቀመጥ የሚያገለግሉ በትሮችን የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።
ወይም “በቀሚስህ።”
ቃል በቃል “ወደ ነፋስ ሁሉ።”
ወይም “አሳንስሻለሁ።”
ወይም “በበሽታ።”
ቃል በቃል “ወደ ነፋስ ሁሉ።”
ቃል በቃል “የዳቦ በትሮቻችሁን በመስበር።” ዳቦ ለማስቀመጥ የሚያገለግሉ በትሮችን የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።
እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል “ፋንድያ” ከሚለው ቃል ጋር ዝምድና ሊኖረው የሚችል ሲሆን ንቀትን ለማመልከት ተሠርቶበታል።
ወይም “ሥነ ምግባር የጎደለው፤ ሴሰኛ።”
ወይም “ሥነ ምግባር በጎደለው መንገድ በተከተሉት።”
ወይም “ደስ የሚያሰኙ መዓዛዎች።”
ቃል በቃል “ይነቃል።”
“የአበባው ጉንጉን መጥቷል” ማለትም ሊሆን ይችላል።
“የአበባው ጉንጉን መጥቷል” ማለትም ሊሆን ይችላል።
በሁሉም ላይ ጥፋት ስለሚመጣ የሚገዛም ሆነ የሚሸጥ የሚያገኘው ጥቅም እንደሌለ ያመለክታል።
“በበደሉም” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ከፍርሃት የተነሳ ሽንታቸውን እንደሚለቁ ያመለክታል።
በሐዘን ምክንያት ፀጉራቸውን እንደሚላጩ ያመለክታል።
ወይም “ነፍሳቸው በልታ አትጠግብም።”
ብራቸውንና ወርቃቸውን ያመለክታል።
ከወርቅና ከብር የተሠሩ ዕቃዎቻቸውን ያመለክታል።
ጣዖቶች ለመሥራት የተጠቀሙባቸውን ብራቸውንና ወርቃቸውን ያመለክታል።
የይሖዋን መቅደስ ቅድስተ ቅዱሳን የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።
በግዞት ሲወሰዱ የሚታሰሩበትን ሰንሰለት ያመለክታል።
ወይም “መመሪያ፤ ትምህርት።”
ወይም “በባዶነት።”
የሚያብረቀርቅ የወርቅና የብር ቅይጥ።
ወይም “ምስል።”
ወይም “ምስል።”
እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል “ፋንድያ” ከሚለው ቃል ጋር ዝምድና ሊኖረው የሚችል ሲሆን ንቀትን ለማመልከት ተሠርቶበታል።
ወይም “የተቀረጹ ምስሎቻቸው በሚገኙባቸው።”
ለጣዖት አምልኮ ይጠቀሙበት የነበረ ቅርንጫፍ እንደሆነ ይታመናል።
ወይም “የጸሐፊ ቀለም መያዣ።”
የሠረገላ ተሽከርካሪ እግር።
ቃል በቃል “ራስ ወዳለበት።”
እያንዳንዱን ኪሩብ ያመለክታል።
ቃል በቃል “ያየሁት ሕያው ፍጡር ይኸው ነበር።”
ቃል በቃል “የሕያው ፍጡሩ መንፈስ።”
ወይም “ከተማ ላይ።”
ቃል በቃል “እሷ።” የኢየሩሳሌምን ከተማ የሚያመለክት ሲሆን አይሁዳውያን በእሷ ውስጥ ጥበቃ እናገኛለን ብለው ያስቡ ነበር።
በውስጡ በጥሩ ሁኔታ የተቀመጠን ሥጋ ያመለክታል።
ወይም “በመንፈሳችሁ የመጡትን ነገሮች።”
ለአምላክ አመራር ፈጣን ምላሽ የሚሰጥን ልብ ያመለክታል።
የሠረገላ ተሽከርካሪ እግር።
ቃል በቃል “መንፈስ።”
ወይም “አታላይ።”
ቃል በቃል “ቤት።”
ወይም “ከገዛ ልባቸው አመንጭተው ትንቢት የሚናገሩትንም።”
ጥንካሬ የሌለው የውስጥ ግድግዳ ከገነቡ በኋላ ጠንካራ እንዲመስል ኖራ መቀባታቸውን ያመለክታል።
ወይም “ነፍሳት።”
በክርን ወይም በእጅ አንጓ ላይ የሚታሰሩ ለአስማት የሚያገለግሉ ጨርቆችን ያመለክታል።
ወይም “ነፍሳት።”
ወይም “ነፍሳት።”
ወይም “ነፍሳት።”
ወይም “ነፍሳት።”
ወይም “ነፍሳትን።”
ወይም “እንዲሠቃይ።”
እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል “ፋንድያ” ከሚለው ቃል ጋር ዝምድና ሊኖረው የሚችል ሲሆን ንቀትን ለማመልከት ተሠርቶበታል።
ቃል በቃል “የእስራኤልን ቤት በልባቸው እይዛለሁና።”
ቃል በቃል “የዳቦ በትሮቹንም እሰብራለሁ።” ዳቦ ለማስቀመጥ የሚያገለግሉ በትሮችን የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።
ወይም “ነፍሳቸውን።”
ወይም “ልጆች ቢጨርሱና።”
ወይም “ነፍሳቸውን።”
ወይም “አደገኛ የሆኑትን አራት የፍርድ እርምጃዎቼን።”
ወይም “ነፍስሽ ስለተጠላች።”
ወይም “ቀሚሴን።”
ወይም “የአቆስጣ ቆዳ።”
ወይም “ንጉሣዊ ሥልጣን ለመቀበልም።”
ቃል በቃል “ስምሽ።”
የወንድ ጣዖቶቹን ያመለክታል።
ወይም “የሚያረጋጋ፤ የሚያበርድ።” ቃል በቃል “እረፍት የሚሰጥ።”
ቃል በቃል “እግሮችሽን በመክፈት።”
ቃል በቃል “ትልቅ ሥጋ ካላቸው ጎረቤቶችሽ።”
ቃል በቃል “በከነአን።”
ወይም “ደካማ።”
“ይህን ሁሉ ነገር ስትፈጽሚ በአንቺ ላይ ምንኛ እቆጣ!” ማለትም ሊሆን ይችላል።
እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል “ፋንድያ” ከሚለው ቃል ጋር ዝምድና ሊኖረው የሚችል ሲሆን ንቀትን ለማመልከት ተሠርቶበታል።
በዙሪያዋ ያሉትን ከተሞች ሊያመለክት ይችላል።
ቃል በቃል “በስተ ግራሽ።”
ቃል በቃል “በስተ ቀኝሽ።”
ወይም “ለእነሱ ስለተከራከርሽ።”
ቃል በቃል “ከነአን።”
የአኻያ ዛፍ የሚመስል።
ሴዴቅያስን ያመለክታል።
ናቡከደነጾርን ያመለክታል።
ወይም “ነፍስ።”
ቃል በቃል “እጁን ቢሰጠውም።”
ቃል በቃል “ወደ ነፋስ ሁሉ።”
ወይም “ሕይወት።” የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “ኃጢአት የሚሠራ ሰው ይሞታል።” የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል “ፋንድያ” ከሚለው ቃል ጋር ዝምድና ሊኖረው የሚችል ሲሆን ንቀትን ለማመልከት ተሠርቶበታል።
ቃል በቃል “ደም አፍሳሽ።”
ወይም “ኃጢአት የሚሠራ ሰው ይሞታል።”
ቃል በቃል “አይታወስበትም።”
ወይም “ፍትሕ የጎደለው።”
ወይም “ነፍስ።” የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ቃል በቃል “ለራሳችሁ ፍጠሩ።”
ወይም “የሐዘን እንጉርጉሮ አሰማ።”
“በወይን እርሻህ ውስጥ እንዳለ የወይን ተክል” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ዘንጎች።”
ወይም “እሳት ከዘንጎቿ።”
ወይም “የፍርድ ውሳኔ ለማስተላለፍ።”
ቃል በቃል “እጄን አነሳሁ።”
ወይም “ለእነሱ ወደሰለልኳት።”
ወይም “የምድር ሁሉ ጌጥ።”
እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል “ፋንድያ” ከሚለው ቃል ጋር ዝምድና ሊኖረው የሚችል ሲሆን ንቀትን ለማመልከት ተሠርቶበታል።
እስራኤልን ያመለክታል።
እስራኤልን ያመለክታል።
እስራኤልን ያመለክታል።
ወይም “የምድር ሁሉ ጌጥ።”
ቃል በቃል “ዓይኔ . . . ራራላቸው።”
እስራኤልን ያመለክታል።
ቃል በቃል “ዓይናቸው።”
ወይም “የሚያረጋጋውን፤ የሚያበርደውን።” ቃል በቃል “እረፍት የሚሰጠውን።”
“ከፍ ያለ የማምለኪያ ቦታ” ወይም የሐሰት ሃይማኖት የአምልኮ ቦታ የሚል ትርጉም ያለው የዕብራይስጥ ቃል ነው።
ወይም “እንደሚያገለግሉት።”
ቃል በቃል “ወደ መንፈሳችሁ የመጣው ነገር።”
ቃል በቃል “እስራት ውስጥ።”
ወይም “በሚያረጋጋው፤ በሚያበርደው።” ቃል በቃል “እረፍት በሚሰጠው።”
ቃል በቃል “ፊታችሁን።”
ወይም “የምድር ገጽ።”
ወይም “ሰውም።”
ወይም “ምሳሌያዊ አባባል።”
ወይም “በሰው።”
ቃል በቃል “ዳሌዎችህ እየተንቀጠቀጡ።”
ከፍርሃት የተነሳ ሽንታቸውን እንደሚለቁ ያመለክታል።
የይሖዋን ሰይፍ ያመለክታል።
ወይም “በትረ መንግሥቱ ከሕልውና ውጭ ይሆናል።”
ቃል በቃል “ተራፊሙን።”
የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች ያመለክታል።
ቃል በቃል “በእጅ።”
ቃል በቃል “በታረዱት አንገቶች።”
እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል “ፋንድያ” ከሚለው ቃል ጋር ዝምድና ሊኖረው የሚችል ሲሆን ንቀትን ለማመልከት ተሠርቶበታል።
ወይም “ወላጅ አልባ የሆነውን ልጅና።”
ቃል በቃል “የአባታቸውን እርቃን ይገልጣሉ።”
ወይም “በወለድና በአራጣ።”
ወይም “ነፍሳትን።”
ወይም “ነፍሳትንም።”
“የእሷ ድንኳን” የሚል ትርጉም አለው።
“ድንኳኔ በእሷ ውስጥ ነው” የሚል ትርጉም አለው።
እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል “ፋንድያ” ከሚለው ቃል ጋር ዝምድና ሊኖረው የሚችል ሲሆን ንቀትን ለማመልከት ተሠርቶበታል።
ወይም “ከእሷ ጋር የፆታ ብልግና ፈጽመዋል።”
ወይም “የፆታ ብልግና በመፈጸምም።”
ወይም “ነፍሷ ተጸይፋቸው።”
ወይም “ነፍሴ ተጸይፋት።”
ወይም “ነፍስሽ ተጸይፋ።”
የሠረገላ ተሽከርካሪ እግር።
አብዛኛውን ጊዜ ቀስተኞች የሚይዙት ትንሽ ጋሻ።
ወይም “ነፍስሽ ተጸይፋ።”
ቃል በቃል “ትሞያለሽ።”
ቃል በቃል “ወደ ኋላሽ ስለጣልሽኝ።”
መንፈሳዊ ምንዝርን ያመለክታል።
ቃል በቃል “የቀኑን ስም።”
ወይም “ውስጠ ወይራ ንግግር።”
ወይም “አፉ ሰፊ የሆነውን ድስት።”
ወይም “ደረትህን አትምታ።”
ወይም “የላይኛውን ከንፈርህን።”
ቃል በቃል “የሰዎችን ዳቦ።”
ወይም “ነፍሳችሁ የሚራራለትን።”
ወይም “የነፍሳቸውን።”
ወይም “በግንብ የታጠሩ ሰፈሮቻቸውን ይመሠርታሉ።”
ወይም “ነፍስህ በንቀት ተሞልታ።”
ወይም “ጌጥ።”
ወይም “የሞዓብ አቀበት።”
ወይም “በነፍሳቸው ንቀት።”
ቃል በቃል “ሴቶች ልጆቿም።”
ቃል በቃል “ናቡከደረጾርን።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።
ቃል በቃል “ሰዎችን።”
ወይም “በማጥቂያ መሣሪያ።”
ወይም “በሰይፍ።”
የሠረገላ ተሽከርካሪ እግር።
ቃል በቃል “የታረዱት።”
ወይም “አለቆች።”
ወይም “እጅጌ የሌለው ቀሚሳቸውንም።”
ቃል በቃል “መንቀጥቀጥን እንደ ልብስ ይለብሳሉ።”
ወይም “የሐዘን እንጉርጉሮ ያሰማሉ።”
ወይም “መቃብር።”
ወይም “አስጌጣለሁ።”
ወይም “የሐዘን እንጉርጉሮ አሰማ።”
ዘዳ 3:8, 9 ላይ የተጠቀሰውን “የሄርሞን ተራራ” ያመለክታል።
ቃል በቃል “ሽማግሌዎቹ።”
በጣም ተፈላጊ የሆነ ጥቁር እንጨት። እንግሊዝኛ፣ ኢቦኒ።
ወይም “ቀላ ያለ ግራጫ ሱፍ።”
ከቀረፋ ዛፍ ጋር የሚዛመድ ዛፍ ነው።
ወይም “የተሸመነ የኮርቻ ልብስ።”
“ክብር ተላብሰሽ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “ጉባኤ።”
ወይም “ከነፍሳቸው ምሬት የተነሳ።”
ወይም “ወደ መቃብር።”
ወይም “የሐዘን እንጉርጉሮ አሰማ።”
ቃል በቃል “በማኅተም የጸደቀ ንድፍ።”
እዚህ ላይም ሆነ ቀጥሎ ባሉት ቁጥሮች ላይ “አባይ” የሚለው ቃል ወንዙንና የመስኖ ቦዮቹን ያመለክታል።
ቃል በቃል “ከሸምበቆ።”
ቃል በቃል “ዳሌዎቻቸውም እንዲብረከረኩ።”
ቃል በቃል “እሱ . . . ብሏልና።”
ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።
ቃል በቃል “ለናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።
ጢሮስን ያመለክታል።
ወይም “ለእስራኤል ቤት ብርታት እሰጣለሁ።”
ወይም “ከሌሎች ብሔራት የተውጣጡ ሁሉ።”
ከግብፅ ጋር የተባበሩትን እስራኤላውያን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “በናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።
እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል “ፋንድያ” ከሚለው ቃል ጋር ዝምድና ሊኖረው የሚችል ሲሆን ንቀትን ለማመልከት ተሠርቶበታል።
ወይም “የሜምፊስ።”
ወይም “አለቃ።”
ቴብስን ያመለክታል።
ወይም “ሜምፊስ።”
ሂልያፖሊስን ያመለክታል።
ወይም “ለባቢሎን ንጉሥ ኃይል እጨምርለታለሁ።”
በባቢሎን ንጉሥ ፊት ማለት ነው።
የተንዠረገጉ ቅርንጫፎችና እየተቀረፈ የሚወድቅ ቅርፊት ያለው ዛፍ።
ቃል በቃል “ቁመትህ።”
ወይም “መቃብር።”
ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “መቃብር።”
ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ቃል በቃል “(በጥላው ሥር ይኖር ከነበረው) ክንዱ።”
ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “የሐዘን እንጉርጉሮ አሰማ።”
ቃል በቃል “ወንዞቻቸውንም።”
ቃል በቃል “የጅረቶቹም ወለል ከአንተ (በአንተ) ይሞላሉ።”
ወይም “መቃብር።”
ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “መቃብር።”
ወይም “መቃብር።”
ወይም “መቃብር።”
ቃል በቃል “ሕዝቧ ሁሉ።”
ቃል በቃል “መቃብሮቿ።”
ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ተዋጊዎች ወታደራዊ ክብር እንዲያገኙ ሲባል ከሰይፋቸው ጋር መቀበራቸውን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል።
ወይም “መቃብር።”
ወይም “መሪዎች።”
ወይም “መቃብር።”
ቃል በቃል “እሱን ቢያስወግደው።”
ወይም “ነፍሱ።”
ወይም “ነፍስ።”
ወይም “ይሁንና ስለ ደሙ ጠባቂውን ተጠያቂ አደርገዋለሁ።”
ወይም “የገዛ ነፍስህን።”
ወይም “ፍትሕ የጎደለው።”
ወይም “አይያዝበትም።”
እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል “ፋንድያ” ከሚለው ቃል ጋር ዝምድና ሊኖረው የሚችል ሲሆን ንቀትን ለማመልከት ተሠርቶበታል።
ወይም “በጣም እንደጓጉ በሚያሳይ ሁኔታ ይናገራሉና።”
ወይም “በጎቼን ከእጃቸው እሻለሁ።”
ወይም “እንዳያግዱም።”
የዳዊትን ዘር ያመለክታል።
ቃል በቃል “ለስም የሚሆን።”
ቃል በቃል “ለቀሩት።”
ወይም “በነፍሳቸው ንቀት።”
እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል “ፋንድያ” ከሚለው ቃል ጋር ዝምድና ሊኖረው የሚችል ሲሆን ንቀትን ለማመልከት ተሠርቶበታል።
ለአምላክ አመራር ፈጣን ምላሽ የሚሰጥን ልብ ያመለክታል።
“በኢየሩሳሌም ለመሥዋዕት እንደሚቀርቡ የበግ መንጋዎች” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “እስትንፋስ፤ መንፈስ።”
ወይም “መንፈስም።”
ወይም “አጋሮቹ ለሆኑት።”
ወይም “አጋሮቹ ለሆኑት።”
ቃል በቃል “የሕዝብህ ወንዶች ልጆች።”
እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል “ፋንድያ” ከሚለው ቃል ጋር ዝምድና ሊኖረው የሚችል ሲሆን ንቀትን ለማመልከት ተሠርቶበታል።
ቃል በቃል “ወንዶች ልጆቻቸው።”
ወይም “ገዢያቸው።”
ወይም “መኖሪያ ስፍራዬ፤ ቤቴ።”
ወይም “በእነሱ ላይ።”
ወይም “ዋነኛ ገዢ።”
ወይም “ዋነኛ ገዢ።”
አብዛኛውን ጊዜ ቀስተኞች የሚይዙት ትንሽ ጋሻ።
ቃል በቃል “ጠባቂያቸው።”
ወይም “ትጠራለህ።”
ወይም “ቅጥር የሌላቸው ገጠራማ ቦታዎች።”
ወይም “ደቦል አንበሶቹ።”
ወይም “እፋረደዋለሁ።”
ወይም “ዋነኛ ገዢ።”
አብዛኛውን ጊዜ ቀስተኞች የሚይዙት ትንሽ ጋሻ።
“የጦር ዱላዎቹንና” ማለትም ሊሆን ይችላል። ጫፉ ሹል የሆነ የጦር መሣሪያ ነው።
ወይም “ስፍር ቁጥር የሌለው የጎግ ሠራዊት ሸለቆ።”
“ስፍር ቁጥር የሌለው ሠራዊት” የሚል ትርጉም አለው።
ቃል በቃል “እጅ።”
ወይም “ለቅዱስ ስሜ እቀናለሁ።”
ቃል በቃል “ሸምበቆ።” ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
ቃል በቃል “በማሳይህም ነገር ሁሉ ላይ ልብህን አድርግ።”
ቃል በቃል “ከቤቱ።” ከሕዝቅኤል ምዕራፍ 40 እስከ 48 ድረስ “ቤት” የሚለው ቃል የቤተ መቅደሱን ሕንፃዎች በአጠቃላይ ወይም ራሱን ቤተ መቅደሱን ለማመልከት በተሠራባቸው ቦታዎች ሁሉ ላይ “ቤተ መቅደስ” ተብሎ ተተርጉሟል።
ቃል በቃል “ስድስት ክንድ የሆነ የመለኪያ ሸምበቆ፣ አንድ ክንድ ከጋት።” ይህ ረጅም ክንድ የሚባለውን መለኪያ ያመለክታል። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
የዘብ ጠባቂውን ክፍል ግድግዳ አናት የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።
ወይም “በአንድ በኩል ጠባብ (በሌላ በኩል ደግሞ ሰፊ) ክፍተት ያላቸው መስኮቶች።”
ወይም “በግቢውም ዙሪያ ክፍሎችና።”
ቃል በቃል “ወርድ።”
“ወርዱ ደግሞ 12” ሊሆንም ይችላል።
ቃል በቃል “ቤተ መቅደስ።” በሕዝቅኤል ምዕራፍ 41 እና 42 ላይ ይህ ቃል የውጨኛውን መቅደስ (ቅድስት) ወይም መላውን መቅደስ (ቅድስቱንና ቅድስተ ቅዱሳኑን ጨምሮ ቤተ መቅደሱን) ያመለክታል።
ይህ ረጅም ክንድ የሚባለውን መለኪያ ያመለክታል። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
ቃል በቃል “ጎኖች።”
ውስጠኛውን መቅደስ ወይም ቅድስተ ቅዱሳኑን ያመለክታል።
ቃል በቃል “የመግቢያው ወርድ ሰባት ክንድ ነበር።”
ክብ የሆኑ ደረጃዎችን የሚያመለክት ይመስላል።
በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ያለ ጠባብ መመላለሻ ሳይሆን አይቀርም።
ወይም “በቤተ መቅደሱና በክፍሎቹ።”
ከመቅደሱ በስተ ምዕራብ የሚገኘውን ሕንፃ ያመለክታል።
ወይም “ደቦል አንበሳ።”
ቃል በቃል “መቃን አራት ማዕዘን ነው።” ወደ ቅድስት የሚያስገባውን በር የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።
ቅድስተ ቅዱሳኑን የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።
ቃል በቃል “ርዝመቱና።”
ወይም “ታዛ።”
ይህ ረጅም ክንድ የሚባለውን መለኪያ ያመለክታል። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
ወይም “በክፍሎቹ ፊት።”
በግሪክኛው ሰብዓ ሊቃናት መሠረት “100 ክንድ የሆነ መተላለፊያ” ነው። የዕብራይስጡ ጽሑፍ “አንድ ክንድ የሆነ መንገድ” ይላል። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
ቃል በቃል “በድንጋይ ቅጥሩ ወርድ ውስጥ።”
ቃል በቃል “የውስጠኛውን ቤት ለክቶ።”
ቃል በቃል “ሸምበቆ።” ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
እንዲህ ያደረገው ስለ ከተማዋ ጥፋት ትንቢት በመናገር ነው።
“በመጣ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “ቤቱ።”
ንጉሦቻቸው አድርገው የሚመለከቷቸውን ጣዖቶች የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።
ቃል በቃል “ንድፉን ይለኩ።”
ይህ ረጅም ክንድ የሚባለውን መለኪያ ያመለክታል። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
አንድ ስንዝር 22.2 ሴንቲ ሜትር ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
ወይም “ፍጹም።”
ሕዝቡ የሚያቀርበውን ማለት ነው።
እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል “ፋንድያ” ከሚለው ቃል ጋር ዝምድና ሊኖረው የሚችል ሲሆን ንቀትን ለማመልከት ተሠርቶበታል።
ወይም “መሠዊያዬ።”
ወይም “ቅዱስ በሆኑት ክፍሎች።”
ቃል በቃል “ሕዝቡን እንዳይቀድሱ።”
ይህ ረጅም ክንድ የሚባለውን መለኪያ ያመለክታል። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
ወይም “በወሰኑ ውስጥ ያለው በሙሉ።”
ቃል በቃል “500 በ500።”
ወይም “20 ክፍሎችን።”
ለ14ን ተመልከት።
ለ14ን ተመልከት።
ለ14ን ተመልከት።
ለ14ን ተመልከት።
ለ14ን ተመልከት።
ወይም “ምናን።” ለ14ን ተመልከት።
ለ14ን ተመልከት።
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ለ14ን ተመልከት።
ለ14ን ተመልከት።
ለ14ን ተመልከት።
ወይም “ቅዱስ ወደሆኑት የካህናቱ ክፍሎች።”
ቃል በቃል “ሕዝቡን እንዳይቀድሱ።”
ይህ ረጅም ክንድ የሚባለውን መለኪያ ያመለክታል። ለ14ን ተመልከት።
ወይም “አራቱም እንዲሁም የማዕዘን ግንቦቻቸው መጠናቸው እኩል ነው።”
ወይም “ካብ።”
ይህ ረጅም ክንድ የሚባለውን መለኪያ ያመለክታል። ለ14ን ተመልከት።
ወይም “በረሃማውን ሜዳ።”
ሙት ባሕርን ያመለክታል።
ቃል በቃል “ሁለቱ ጅረቶች።”
ወይም “ነፍሳት።”
ሜድትራንያንን ያመለክታል።
ቃል በቃል “ትወርሷታላችሁ፤ እያንዳንዱም እንደ ወንድሙ ያገኛል።”
ቃል በቃል “ወጥታላችኋለች።”
ሙት ባሕርን ያመለክታል።
ቃል በቃል “በስተ ደቡብ ያለው የደቡቡ ጎን።”
የግብፅን ደረቅ ወንዝ ያመለክታል።
ቃል በቃል “በስተ ደቡብ ያለው የደቡቡ ጎን።”
ወይም “ከሃማት መግቢያ።”
ወይም “ሃማት መግቢያ።”
ይህ ረጅም ክንድ የሚባለውን መለኪያ ያመለክታል። ለ14ን ተመልከት።
የግብፅን ደረቅ ወንዝ ያመለክታል።
ሜድትራንያንን ያመለክታል።