የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • nwt ኤርምያስ 1:1-52:34
  • ኤርምያስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኤርምያስ
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኤርምያስ

ኤርምያስ

1 በቢንያም አገር በአናቶት+ ከነበሩት ካህናት አንዱ የሆነው የኬልቅያስ ልጅ የኤርምያስ* ቃል ይህ ነው። 2 የይሁዳ ንጉሥ የአምዖን+ ልጅ ኢዮስያስ+ በነገሠ በ13ኛው ዓመት የይሖዋ ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ። 3 ደግሞም በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮዓቄም+ ዘመን፣ እንዲሁም የይሁዳ ንጉሥ የኢዮስያስ ልጅ የሴዴቅያስ+ 11ኛው ዓመት የግዛት ዘመን እስካበቃበት ጊዜ ድረስ ይኸውም ኢየሩሳሌም ወደ ግዞት እስከተወሰደችበት እስከ አምስተኛው ወር+ ድረስ ቃሉ ወደ እሱ መጣ።

 4 የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦

 5 “በማህፀን ውስጥ ሳልሠራህ በፊት አውቄሃለሁ፤*+

ከመወለድህም* በፊት ቀድሼሃለሁ።*+

ለብሔራት ነቢይ አድርጌሃለሁ።”

 6 እኔ ግን “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ወዮልኝ!

እኔ ገና ልጅ* ስለሆንኩ+ ምን ብዬ እንደምናገር አላውቅም”+ አልኩ።

 7 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦

“‘እኔ ገና ልጅ ነኝ’ አትበል።

ወደምልክህ ሁሉ ትሄዳለህና፤

የማዝህንም ሁሉ ትናገራለህ።+

 8 ከቁመናቸው የተነሳ አትፍራ፤+

‘አድንህ ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና’+ ይላል ይሖዋ።”

9 ከዚያም ይሖዋ እጁን ዘርግቶ አፌን ዳሰሰ።+ ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ “ቃሌን በአፍህ አኑሬአለሁ።+ 10 እንግዲህ እንድትነቅልና እንድታፈርስ፣ እንድታጠፋና እንድታወድም፣ እንድትገነባና እንድትተክል ዛሬ በብሔራትና በመንግሥታት ላይ ሾሜሃለሁ።”+

11 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ “ኤርምያስ፣ የምታየው ምንድን ነው?” እኔም “የአልሞንድ ዛፍ* ቅርንጫፍ አያለሁ” አልኩ።

12 ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ “በትክክል አይተሃል፤ እኔ ቃሌን ለመፈጸም በከፍተኛ ንቃት እየተጠባበቅኩ ነውና።”

13 የይሖዋ ቃል ለሁለተኛ ጊዜ ወደ እኔ መጥቶ “ምን ይታይሃል?” አለኝ። እኔም “የተጣደ* ድስት* አያለሁ፤ አፉም ከሰሜን ወደ ደቡብ ያዘነበለ ነው” አልኩ። 14 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦

“በምድሪቱ ነዋሪዎች ሁሉ ላይ

ከሰሜን ጥፋት ይመጣል።+

15 ‘በሰሜን ያሉትን መንግሥታት ነገዶች ሁሉ እጠራለሁና’ ይላል ይሖዋ፤+

‘እነሱም ይመጣሉ፤ እያንዳንዱም ዙፋኑን

በኢየሩሳሌም በሮች መግቢያ፣+

በቅጥሮቿ ዙሪያ ሁሉና

በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ላይ ያደርጋል።+

16 ደግሞም እኔን ስለተዉ፣+

ለሌሎች አማልክትም የሚጨስ መሥዋዕት ስለሚያቀርቡና+

በገዛ እጃቸው ለሠሯቸው ነገሮች ስለሚሰግዱ+

በክፋታቸው ሁሉ ላይ ፍርዴን አውጃለሁ።’

17 አንተ ግን ለሥራ ተዘጋጅ፤*

ደግሞም ተነስ፤ እኔ የማዝህንም ሁሉ ንገራቸው።

እኔ ራሴ በፊታቸው እንዳላሸብርህ፣

እነሱን አትፍራቸው።+

18 ምድሪቱን ሁሉ፣ የይሁዳን ነገሥታትና መኳንንቷን፣

ካህናቷንና የምድሪቱን ሕዝብ እንድትቋቋም፣+

ዛሬ አንተን የተመሸገ ከተማ፣

የብረት ዓምድና የመዳብ ቅጥር አድርጌሃለሁ።+

19 እነሱም በእርግጥ ይዋጉሃል፤

ሆኖም አያሸንፉህም፤*

‘አድንህ ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና’+ ይላል ይሖዋ።”

2 የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “ሂድና ኢየሩሳሌም ጆሮዋ እየሰማ ይህን አውጅ፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“በወጣትነትሽ ጊዜ ለአምላክ ያደርሽ እንደነበርሽ፣*+

ደግሞም ለጋብቻ በታጨሽበት ጊዜ ያሳየሽውን ፍቅር፣+

ዘር በማይዘራበት ምድር፣ በምድረ በዳ

እንዴት እንደተከተልሽኝ በሚገባ አስታውሳለሁ።+

 3 እስራኤል ለይሖዋ የተቀደሰ፣+ የመከሩ በኩር ነበር።”’

‘እሱን የሚውጥ ሁሉ በደለኛ ይሆናል።

በእነሱም ላይ ጥፋት ይመጣል’ ይላል ይሖዋ።”+

 4 የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ የእስራኤልም ቤት ወገኖች ሁሉ፣

የይሖዋን ቃል ስሙ።

 5 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“አባቶቻችሁ ከእኔ እጅግ የራቁት፣

ከንቱ የሆኑ ጣዖቶችን የተከተሉትና+

እነሱ ራሳቸው ከንቱ የሆኑት+ ምን ጥፋት አግኝተውብኝ ነው?+

 6 እነሱ ‘ከግብፅ ምድር ያወጣን፣+

በምድረ በዳ፣ በረሃማ በሆነና+

ጉድጓድ ባለበት ምድር፣

በድርቅ በተጠቃና+ ድቅድቅ ጨለማ በዋጠው ምድር

እንዲሁም ማንም ሰው በማይጓዝበትና

ሰው በማይኖርበት ምድር

የመራን ይሖዋ የት አለ?’ ብለው አልጠየቁም።

 7 በዚያን ጊዜ እኔ ፍሬዋንና በውስጧ ያሉትን ጥሩ ጥሩ ነገሮች እንድትበሉ

የፍራፍሬ ዛፎች ወዳሉባት ምድር አመጣኋችሁ።+

እናንተ ግን መጥታችሁ ምድሬን አረከሳችሁ፤

ርስቴንም አስጸያፊ ነገር አደረጋችሁት።+

 8 ካህናቱ ‘ይሖዋ የት አለ?’ ብለው አልጠየቁም፤+

ሕጉ በአደራ የተሰጣቸውም እኔን አላወቁም፤

እረኞቹ በእኔ ላይ ዓመፁ፤+

ነቢያቱ በባአል ስም ትንቢት ተናገሩ፤+

ምንም ጥቅም የማያስገኙላቸውንም አማልክት ተከተሉ።

 9 ‘በመሆኑም ከእናንተ ጋር ገና እሟገታለሁ’+ ይላል ይሖዋ፤

‘ከልጅ ልጆቻችሁም ጋር እሟገታለሁ።’

10 ‘እስቲ ወደ ኪቲም+ የባሕር ዳርቻዎች* ተሻግራችሁ ተመልከቱ።

አዎ፣ መልእክተኞችን ወደ ቄዳር+ ልካችሁ ጉዳዩን በጥሞና መርምሩ፤

እንዲህ ያለ ነገር ተፈጽሞ እንደሆነ እዩ።

11 አማልክቱን፣ አማልክት ባልሆኑት ለውጦ የሚያውቅ ብሔር አለ?

የገዛ ሕዝቤ ግን ክብሬን ምንም ጥቅም በሌለው ነገር ለውጧል።+

12 እናንተ ሰማያት በዚህ ተደነቁ፤

በታላቅ ድንጋጤም ተርበትበቱ’ ይላል ይሖዋ፤

13 ‘ምክንያቱም ሕዝቤ ሁለት መጥፎ ነገሮች ፈጽመዋል፦

የሕያው ውኃ ምንጭ የሆንኩትን እኔን ትተው+

የውኃ ማጠራቀሚያዎችን ይኸውም ውኃ መያዝ የማይችሉና የሚያፈሱ

የውኃ ማጠራቀሚያዎችን ለራሳቸው ቆፍረዋል።’*

14 ‘እስራኤል፣ አገልጋይ ወይም የቤት ውልድ ባሪያ ነው?

ታዲያ እንዲበዘበዝ የተደረገው ለምንድን ነው?

15 ደቦል አንበሶች በእሱ ላይ አገሡ፤+

በኃይለኛ ድምፅ ጮኹበት።

ምድሩን የሚያስፈራ ቦታ አደረጉት።

ከተሞቹ ማንም እንዳይኖርባቸው በእሳት ተቃጠሉ።

16 የኖፍና*+ የጣፍነስ+ ሕዝቦች፣ መሃል አናትሽን ይበላሉ።

17 አምላክሽ ይሖዋ በመንገዱ በመራሽ ወቅት

እሱን በመተው+

ይህን በራስሽ ላይ አላመጣሽም?

18 ደግሞስ የሺሆርን ውኃዎች* ለመጠጣት

ወደ ግብፅ የሚወስደውን መንገድ የመረጥሽው ለምንድን ነው?+

የወንዙን* ውኃዎች ለመጠጣት

ወደ አሦር የሚወስደውን መንገድ የመረጥሽው ለምንድን ነው?+

19 ከክፋትሽ ትምህርት ልታገኚ ይገባል፤

ታማኝነት በማጉደል የፈጸምሻቸው ድርጊቶችም ወቀሳ ያስከትሉብሻል።

አምላክሽን ይሖዋን መተውሽ

መጥፎና መራራ እንደሆነ ማወቅና መገንዘብ ይኖርብሻል፤+

እኔን ፈጽሞ አልፈራሽም’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ።

20 ‘ከረጅም ጊዜ በፊት ቀንበርሽን ሰባበርኩ፤+

የታሰርሽበትንም ሰንሰለት በጣጠስኩ።

አንቺ ግን “አንተን አላገለግልም” አልሽ፤

ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይና ቅጠሉ በተንዠረገገ ዛፍ ሁሉ ሥር+

ለማመንዘር ተንጋለሽ ተኝተሻልና።+

21 እኔ፣ እንደ ምርጥ ቀይ የወይን ተክል፣ ሙሉ በሙሉ ንጹሕ የሆነ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር፤+

ታዲያ በፊቴ እንዲህ ተለውጠሽ የተበላሸ ባዕድ የወይን ተክል የሆንሽው እንዴት ነው?’+

22 ‘በሶዳ* ብትታጠቢና ብዛት ያለው እንዶድ* ብትጠቀሚ እንኳ

ከበደልሽ የተነሳ ዕድፍሽ በፊቴ ይኖራል’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።

23 ‘ራሴን አላረከስኩም።

ባአልንም አልተከተልኩም’ እንዴት ትያለሽ?

በሸለቆው ውስጥ ያለውን መንገድሽን ተመልከቺ።

ያደረግሽውን ነገር ልብ በይ።

በመንገዷ ላይ ወዲያና ወዲህ እንደምትፋንን

የደረሰች ፈጣን ግመል ነሽ፤

24 በምድረ በዳ መኖር እንደለመደች፣

በፍትወቷ* ነፋሱን እንደምታነፈንፍ የዱር አህያ ነሽ።

ስሜቷ ሲነሳሳ ማን ሊመልሳት ይችላል?

የሚፈልጓት ሁሉ እሷን ለማግኘት ብዙ ድካም አይጠይቅባቸውም።

በመራቢያዋ ወቅት* ያገኟታል።

25 እግርሽ እስኪነቃ አትዙሪ፤

ጉሮሮሽም በውኃ ጥም አይቃጠል።

አንቺ ግን ‘አይሆንም! ምንም ተስፋ የሌለው ነገር ነው!+

እኔ ከባዕዳን* ጋር ፍቅር ይዞኛል፤+

እነሱንም እከተላለሁ’ አልሽ።+

26 ሌባ ሲያዝ እንደሚያፍር፣

የእስራኤል ቤት ሰዎችም እንዲሁ አፍረዋል፤

እነሱም ሆኑ ነገሥታታቸው፣ መኳንንታቸው፣

ካህናታቸውና ነቢያታቸው ውርደት ተከናንበዋል።+

27 ዛፉን ‘አንተ አባቴ ነህ’፤+

ድንጋዩንም ‘የወለድከኝ አንተ ነህ’ ይላሉ።

ለእኔ ግን ፊታቸውን ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጥተውኛል።+

ጥፋት ሲመጣባቸውም

‘ተነስተህ አድነን!’ ይላሉ።+

28 ለራስህ የሠራሃቸው አማልክት ታዲያ የት አሉ?+

ጥፋት ሲደርስብህ ሊያድኑህ የሚችሉ ከሆነ ይነሱ፤

ይሁዳ ሆይ፣ አማልክትህ የከተሞችህን ያህል በዝተዋልና።+

29 ‘አሁንም ከእኔ ጋር የምትሟገቱት ለምንድን ነው?

ሁላችሁም በእኔ ላይ ያመፃችሁት ለምንድን ነው?’+ ይላል ይሖዋ።

30 ልጆቻችሁን የመታሁት በከንቱ ነው።+

ለመታረም ፈቃደኞች አይደሉም፤+

የገዛ ራሳችሁ ሰይፍ እንደሚያደባ አንበሳ

ነቢያታችሁን በልቷል።+

31 የዚህ ትውልድ ሰዎች ሆይ፣ የይሖዋን ቃል ልብ በሉ።

እኔ ለእስራኤል፣ እንደ ምድረ በዳ

ወይም ድቅድቅ ጨለማ እንደዋጠው ምድር ሆኛለሁ?

የእኔ ሕዝብ የሆኑት እነዚህ ሰዎች ‘እኛ ወደፈለግንበት እንሄዳለን።

ከእንግዲህ ወደ አንተ አንመጣም’ ለምን ይላሉ?+

32 ለመሆኑ አንዲት ድንግል ጌጣጌጧን፣

ሙሽሪትስ ጌጠኛ መቀነቷን* ትረሳለች?

የገዛ ሕዝቤ ግን ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ቀናት ረስቶኛል።+

33 አንቺ ሴት፣ ፍቅረኛ ለማግኘት መንገድሽን ምንኛ በጥበብ አመቻቸሽ!

የክፋትን መንገዶች ተምረሻል።+

34 ልብሶችሽ በንጹሐን ድሆች* ደም ቆሽሸዋል፤+

ይሁንና ይህን ያገኘሁት ቤት ሲዘረፍ አይደለም፤

ይልቁንም በልብሶችሽ ሁሉ ላይ ነው።+

35 አንቺ ግን ‘እኔ ንጹሕ ነኝ።

በእርግጥ ቁጣው ከእኔ ተመልሷል’ ትያለሽ።

‘ኃጢአት አልሠራሁም’ ስለምትዪ፣

በአንቺ ላይ ፍርድ አመጣለሁ።

36 መንገድሽን በመለዋወጥ የምትፈጽሚውን ድርጊት አቅልለሽ የምትመለከቺው ለምንድን ነው?

በአሦር እንዳፈርሽ ሁሉ+

በግብፅም ታፍሪያለሽ።+

37 በዚህም የተነሳ እጆችሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ትወጫለሽ፤+

ይሖዋ የምትተማመኚባቸውን ነገሮች አስወግዷልና፤

እነሱ ለስኬት አያበቁሽም።”

3 ሰዎች እንዲህ ብለው ይጠይቃሉ፦ “አንድ ሰው ሚስቱን ቢያሰናብታት፣ እሷም ተለይታው ብትሄድና የሌላ ሰው ሚስት ብትሆን፣ ዳግመኛ ወደ እሷ መመለስ ይኖርበታል?”

ይህች ምድር ጨርሶ ተበክላ የለም?+

“አንቺ ከብዙ ወዳጆችሽ ጋር አመነዘርሽ፤+

ታዲያ አሁን ወደ እኔ መመለስ ይገባሻል?” ይላል ይሖዋ።

 2 “ዓይንሽን አንስተሽ የተራቆቱትን ኮረብቶች ተመልከቺ።

አንቺ ያልተደፈርሽበት ቦታ ይገኛል?

በምድረ በዳ እንዳለ ዘላን*

አንቺም በመንገዶቹ ዳር ተቀምጠሽ ጠበቅሻቸው።

በዝሙትሽና በክፋትሽ

ምድሪቱን በከልሽ።+

 3 ስለዚህ ዝናብ እንዳይዘንብ ተከልክሏል፤+

የኋለኛው ዝናብም አልዘነበም።

አንቺ ዝሙት አዳሪ እንደሆነች ሚስት፣ ዓይን አውጣ ነሽ፤*

ኀፍረት የሚባል ነገር አታውቂም።+

 4 አሁን ግን ወደ እኔ ተጣርተሽ እንዲህ ትያለሽ፦

‘አባቴ፣ አንተ ከልጅነቴ ጀምሮ ወዳጄ ነህ!+

 5 ለዘላለም ቅር ትሰኛለህ?

ወይስ ቂም እንደያዝክ ትኖራለህ?’

አንቺ እንዲህ ትያለሽ፤

ይሁንና የቻልሽውን ያህል ክፉ ነገር መሥራትሽን ቀጥለሻል።”+

6 በንጉሥ ኢዮስያስ+ ዘመን ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “‘ታማኝነቷን ያጎደለችው እስራኤል ያደረገችውን አይተሃል? ከፍ ባለው ተራራ ሁሉ ላይና ቅጠሉ ከተንዠረገገው ዛፍ ሁሉ በታች ለማመንዘር ሄዳለች።+ 7 ይህን ሁሉ ነገር ካደረገች በኋላ እንኳ ወደ እኔ እንድትመለስ መወትወቴን ቀጠልኩ፤+ እሷ ግን አልተመለሰችም፤ ይሁዳም ከሃዲ የሆነችውን እህቷን ተመለከተች።+ 8 ይህን ባየሁ ጊዜ፣ በማመንዘሯ የተነሳ+ ታማኝነቷን ላጎደለችው ለእስራኤል የፍችዋን የምሥክር ወረቀት ሰጥቼ አሰናበትኳት።+ ያም ሆኖ ከሃዲ የሆነችው እህቷ ይሁዳ አልፈራችም፤ እሷም ሄዳ አመነዘረች።+ 9 አመንዝራነቷን አቅልላ ተመለከተችው፤ ምድሪቱን መበከሏን እንዲሁም ከድንጋዮችና ከዛፎች ጋር ማመንዘሯን ቀጠለች።+ 10 ይህም ሁሉ ሆኖ ከሃዲ የሆነችው እህቷ ይሁዳ ለይስሙላ እንጂ በሙሉ ልቧ ወደ እኔ አልተመለሰችም’ ይላል ይሖዋ።”

11 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ታማኝነቷን ያጎደለችው እስራኤል፣ ከሃዲ ከሆነችው ይሁዳ ይልቅ ጻድቅ ሆና* ተገኝታለች።+ 12 ሂድና እነዚህን ቃላት ወደ ሰሜን+ አውጅ፦

“‘“ከዳተኛይቱ እስራኤል ሆይ፣ ተመለሽ” ይላል ይሖዋ።’+ ‘“እኔ ታማኝ ስለሆንኩ እናንተን በቁጣ አልመለከትም”*+ ይላል ይሖዋ።’ ‘“ለዘላለም ቅር አልሰኝም። 13 ብቻ የሠራሽውን በደል አምነሽ ተቀበይ፤ በአምላክሽ በይሖዋ ላይ ዓምፀሻልና። ቅጠሉ በተንዠረገገ ዛፍ ሁሉ ሥር ከእንግዶች* ጋር አመነዘርሽ፤* ቃሌንም አትታዘዢም” ይላል ይሖዋ።’”

14 “እናንተ ከዳተኛ ልጆች፣ ተመለሱ” ይላል ይሖዋ። “እኔ እውነተኛ ጌታችሁ* ሆኛለሁና፤ ከአንድ ከተማ አንድ፣ ከአንድ ነገድም ሁለት እያደረግኩ እወስዳችኋለሁ፤ ወደ ጽዮንም አመጣችኋለሁ።+ 15 እንደ ልቤ የሆኑ እረኞችም እሰጣችኋለሁ፤+ እነሱም በእውቀትና በጥልቅ ማስተዋል ይመግቧችኋል። 16 በዚያ ዘመን በምድሪቱ ላይ ትበዛላችሁ፤ ፍሬያማም ትሆናላችሁ” ይላል ይሖዋ።+ “ከእንግዲህ ‘የይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት!’ አይሉም፤ ስለ እሱ አያስቡም፤ ጨርሶ አያስታውሱትም ወይም እንዳጎደላቸው ሆኖ አይሰማቸውም፤ ታቦቱም ዳግመኛ አይሠራም። 17 በዚያን ጊዜ ኢየሩሳሌምን የይሖዋ ዙፋን ብለው ይጠሯታል፤+ ብሔራትም ሁሉ በአንድነት የይሖዋን ስም ለማወደስ ወደ ኢየሩሳሌም ይመጣሉ፤+ ከዚያ በኋላ ግትር ሆነው የገዛ ክፉ ልባቸውን አይከተሉም።”

18 “በዚያ ዘመን የይሁዳ ቤትና የእስራኤል ቤት አብረው ይሄዳሉ፤+ በአንድነት ከሰሜን ምድር ተነስተው ለአባቶቻችሁ ርስት አድርጌ ወደሰጠኋት ምድር ይመጣሉ።+ 19 እኔም እንዲህ ብዬ አሰብኩ፦ ‘በወንዶች ልጆች መካከል ባስቀምጥሽ፣ የተወደደችውንም ምድር፣ በብሔራት መካከል የምትገኘውን እጅግ ያማረች ርስት ብሰጥሽ ምንኛ ደስ ባለኝ!’+ በተጨማሪም እናንተ ‘አባቴ!’ ብላችሁ ትጠሩኛላችሁ፤ እኔንም ከመከተል አትመለሱም ብዬ አስቤ ነበር። 20 ‘የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እናንተ ግን ባሏን* ክዳ እንደምትሄድ ሚስት በእኔ ላይ ክህደት ፈጽማችኋል’+ ይላል ይሖዋ።”

21 በተራቆቱ ኮረብቶች ላይ ድምፅ ተሰምቷል፤

አዎ፣ የእስራኤል ልጆች ለቅሶና ልመና ተሰምቷል፤

እነሱ መንገዳቸውን አጣመዋልና፤

አምላካቸውን ይሖዋን ረስተዋል።+

22 “እናንተ ከዳተኛ ልጆች፣ ተመለሱ።

ከዳተኝነታችሁን እፈውሳለሁ።”+

“እነሆ፣ እኛ ወደ አንተ መጥተናል!

ይሖዋ ሆይ፣ አንተ አምላካችን ነህና።+

23 ኮረብቶቹና በተራሮቹ ላይ የሚሰማው ሁካታ የሐሰት ናቸው።+

በእርግጥ የእስራኤል መዳን በአምላካችን በይሖዋ ነው።+

24 ይሁንና አሳፋሪው ነገር* ከልጅነታችን ጀምሮ አባቶቻችን የደከሙበትን ሁሉ፣+

መንጎቻቸውንና ከብቶቻቸውን፣

ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በልቷል።

25 ኀፍረታችንን ተከናንበን እንተኛ፤

ውርደታችንም ይሸፍነን፤

እኛና አባቶቻችን ከልጅነታችን ጀምሮ እስካሁን ድረስ

በአምላካችን በይሖዋ ላይ ኃጢአት ሠርተናልና፤+

የአምላካችንን የይሖዋን ድምፅም አልታዘዝንም።”

4 “እስራኤል ሆይ፣ ብትመለስ” ይላል ይሖዋ፣

“ወደ እኔ ብትመለስ፣

አስጸያፊ ጣዖቶችህን ከፊቴ ብታስወግድ

ተንከራታች አትሆንም።+

 2 ‘በእውነት፣ በፍትሕና በጽድቅ

ሕያው ይሖዋን!’ ብለህ ብትምል፣

ብሔራት በእሱ አማካኝነት በረከት ያገኛሉ፤

በእሱም ይኮራሉ።”+

3 ይሖዋ ለይሁዳ ሰዎችና ለኢየሩሳሌም እንዲህ ይላልና፦

“ያልለማውን መሬት እረሱ፤

በእሾህ መካከልም አትዝሩ።+

 4 እናንተ የይሁዳ ሰዎችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች፣

ለይሖዋ ተገረዙ፤

የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ፤+

አለዚያ በክፉ ሥራችሁ የተነሳ

ቁጣዬ እንደ እሳት ይነድዳል፤

ማንም ሊያጠፋው አይችልም።”+

 5 ይህን በይሁዳ ተናገሩ፤ በኢየሩሳሌምም አውጁ።

ጩኹ፤ በምድሪቱም ሁሉ ላይ ቀንደ መለከት ንፉ።+

ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ እንዲህ በሉ፦ “አንድ ላይ ተሰብሰቡ፤

ወደተመሸጉት ከተሞችም እንሽሽ።+

 6 ወደ ጽዮን የሚጠቁም ምልክት* አቁሙ።

መጠለያ ፈልጉ፤ ዝም ብላችሁም አትቁሙ።”

ከሰሜን ጥፋት ብሎም ታላቅ መዓት አመጣለሁና።+

 7 ጠላት እንደ አንበሳ ከጥሻው ውስጥ ወጥቷል፤+

ብሔራትንም የሚያጠፋው ተነስቷል።+

ምድርሽን አስፈሪ ቦታ ሊያደርግ ከቦታው ወጥቷል።

ከተሞችሽ አንድም ሰው የማይኖርባቸው የፍርስራሽ ክምር ይሆናሉ።+

 8 ስለዚህ ማቅ ልበሱ፤+

እዘኑ፤* ዋይ ዋይም በሉ፤

ምክንያቱም የሚነደው የይሖዋ ቁጣ ከእኛ አልተመለሰም።

 9 “በዚያ ቀን” ይላል ይሖዋ፣ “የንጉሡ ልብና

የመኳንንቱ ልብ ይቀልጣል፤*+

ካህናቱም ይሸበራሉ፤ ነቢያቱም ይገረማሉ።”+

10 ከዚያም እንዲህ አልኩ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ወዮ! ሰይፍ አንገታችን ላይ ተጋድሞ* እያለ ‘ሰላም ታገኛላችሁ’+ ብለህ ይህን ሕዝብና ኢየሩሳሌምን ፈጽሞ አታለሃል።”+

11 በዚያን ጊዜ ለዚህ ሕዝብና ለኢየሩሳሌም እንዲህ ይባላል፦

“የሚለበልብ ነፋስ በበረሃ ከሚገኙ ጠፍ ኮረብቶች ተነስቶ

ወደ ሕዝቤ ሴት ልጅ* በፍጥነት ይነፍሳል፤

ነፋሱ የሚነፍሰው እህል ለማዝራትም* ሆነ ለማጥራት አይደለም።

12 በእኔ ትእዛዝ ኃይለኛው ነፋስ ከእነዚህ ስፍራዎች ይመጣል።

አሁን በእነሱ ላይ ፍርድ አስተላልፋለሁ።

13 እነሆ፣ እሱ ዝናብ እንዳዘሉ ደመናት ይመጣል፤

ሠረገሎቹም እንደ አውሎ ነፋስ ናቸው።+

ፈረሶቹ ከንስር ይበልጥ ፈጣኖች ናቸው።+

ጠፍተናልና ወዮልን!

14 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ እንድትድኚ ልብሽን ከክፋት ሁሉ አጥሪ።+

እስከ መቼ በውስጥሽ ክፉ ሐሳብ ይዘሽ ትኖሪያለሽ?

15 አንድ ድምፅ ከዳን ዜናውን ይናገራልና፤+

ከኤፍሬም ተራሮችም ጥፋትን ያውጃል።

16 ይህን አሳውቁ፤ አዎ ለብሔራት ተናገሩ፤

በኢየሩሳሌም ላይ አውጁ።”

“ጠባቂዎች* ከሩቅ አገር እየመጡ ነው፤

በይሁዳ ከተሞችም ላይ ይጮኻሉ።

17 ማሳ እንደሚጠብቁ ሰዎች ከሁሉም አቅጣጫ ይመጡባታል፤+

ምክንያቱም እሷ በእኔ ላይ ዓምፃለች”+ ይላል ይሖዋ።

18 “ለተከተልሽው መንገድና ለፈጸምሽው ተግባር ዋጋሽን ትቀበያለሽ።+

የሚደርስብሽ ጥፋት ምንኛ መራራ ነው፤

ወደ ልብሽ ዘልቆ ይገባልና!”

19 ወይ አበሳዬ!* ወይ አበሳዬ!

ልቤን ሥቃይ ቀስፎታል።

ልቤ በውስጤ በኃይል ይመታል።

ዝም ማለት አልችልም፤

የቀንደ መለከት ድምፅ፣

የጦርነት ማስጠንቀቂያ ድምፅ* ሰምቻለሁና።*+

20 በጥፋት ላይ ጥፋት መድረሱ ተወርቷል፤

ምድሪቱ በሙሉ ወድማለችና።

የገዛ ድንኳኖቼ በድንገት፣

የድንኳን ሸራዎቼም በቅጽበት ጠፍተዋል።+

21 ምልክቱን* የማየውና

የቀንደ መለከቱን ድምፅ የምሰማው እስከ መቼ ድረስ ነው?+

22 “ሕዝቤ ሞኝ ነውና፤+

እነሱ ለእኔ ትኩረት አይሰጡም።

ማስተዋል የሌላቸው ቂል ልጆች ናቸው።

ክፉ ነገር ለማድረግ ብልሃተኞች* ናቸው፤

መልካም ነገር ማድረግ ግን አያውቁም።”

23 ምድሪቱን አየሁ፤ እነሆም፣ ባዶና ወና ነበረች።+

ወደ ሰማያት ተመለከትኩ፤ ብርሃናቸው ጠፍቶ ነበር።+

24 ተራሮቹን አየሁ፤ እነሆ፣ ይናወጡ ነበር፤

ኮረብቶቹም ይንቀጠቀጡ ነበር።+

25 እኔም ተመለከትኩ፤ እነሆ፣ በዚያ አንድም ሰው አልነበረም፤

የሰማይ ወፎችም ሁሉ ሸሽተው ነበር።+

26 እኔም አየሁ፤ እነሆ፣ የፍራፍሬ እርሻው ምድረ በዳ ሆኖ ነበር፤

ከተሞቹም ሁሉ ፈራርሰው ነበር።+

ይህም የሆነው በይሖዋ፣

በሚነደውም ቁጣው የተነሳ ነው።

27 ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “ምድሪቱ በሙሉ ባድማ ትሆናለች፤+

ሆኖም ፈጽሜ አላጠፋትም።

28 ከዚህ የተነሳ ምድሪቱ ታዝናለች፤+

በላይ ያሉት ሰማያትም ይጨልማሉ።+

ምክንያቱም እኔ ተናግሬአለሁ፤ ደግሞም ወስኛለሁ፤

ሐሳቤንም አለውጥም፤* ወደ ኋላም አልመለስም።+

29 ከፈረሰኞቹና ከቀስተኞቹ ድምፅ የተነሳ

ከተማዋ በሙሉ ትሸሻለች።+

ጥሻ ውስጥ ይገባሉ፤

ዓለቶቹም ላይ ይወጣሉ።+

ከተሞቹ ሁሉ ተትተዋል፤

የሚኖርባቸውም ሰው የለም።”

30 ለጥፋት ተዳርገሻል፤ ታዲያ ምን ታደርጊ ይሆን?

ደማቅ ቀይ ልብስ ትጎናጸፊ፣

በወርቅ ጌጣጌጦች ታጌጪና

ዓይኖችሽን ትኳዪ ነበር።

ይሁንና ትዋቢ የነበረው እንዲያው በከንቱ ነው፤+

በፍትወት ስሜት ይከተሉሽ የነበሩት ትተውሻልና፤

አሁን ሕይወትሽን* ይሿታል።+

31 እንደታመመች ሴት ድምፅ፣

የመጀመሪያ ልጇንም ለመውለድ እንደምታምጥ ሴት ያለ የጭንቅ ድምፅ፣

ደግሞም ትንፋሽ አጥሯት ቁና ቁና የምትተነፍሰውን የጽዮን ሴት ልጅ ድምፅ ሰምቻለሁና።

እሷም እጆቿን ዘርግታ+

“ወዮልኝ! ከገዳዮች የተነሳ ዝያለሁና”* ትላለች።

5 በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ ወዲያና ወዲህ ተመላለሱ።

ዙሪያውን ተመልከቱ፤ ልብ በሉ።

ፍትሕን የሚያደርግ፣+

ታማኝ መሆን የሚሻ ሰውም ታገኙ እንደሆነ

በአደባባዮቿ ፈልጉ፤

እኔም ይቅር እላታለሁ።

 2 “ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ!” ቢሉም

የሚምሉት ሐሰት ለሆነ ነገር ነው።+

 3 ይሖዋ ሆይ፣ ዓይኖችህ የሚመለከቱት ታማኝ የሆኑ ሰዎችን ለማግኘት አይደለም?+

አንተ መተሃቸዋል፤ በእነሱ ላይ ግን ያመጣው ለውጥ የለም።*

አንተ አድቅቀሃቸዋል፤ እነሱ ግን አልታረሙም።+

ፊታቸውን ከዓለት ይልቅ አጠነከሩ፤+

ለመመለስም አሻፈረን አሉ።+

 4 እኔ ግን ለራሴ እንዲህ አልኩ፦ “በእርግጥ እነዚህ ምስኪኖች ናቸው።

የይሖዋን መንገድ፣ የአምላካቸውንም ፍርድ ባለማወቃቸው

የሞኝነት ድርጊት ይፈጽማሉ።

 5 ታዋቂ ወደሆኑት ሰዎች ሄጄ አነጋግራቸዋለሁ፤

እነሱ የይሖዋን መንገድ፣ የአምላካቸውንም ፍርድ

አስተውለው መሆን አለበትና።+

ነገር ግን ሁሉም ቀንበሩን ሰብረዋል፤

ማሰሪያውንም በጥሰዋል።”

 6 ስለዚህ ከጫካ የወጣ አንበሳ ይሰባብራቸዋል፤

የበረሃ ተኩላም ይቦጫጭቃቸዋል፤

ነብር በከተሞቻቸው አቅራቢያ አድብቶ ይጠብቃል።

ከዚያ የሚወጣውንም ሁሉ ይዘነጣጥላል።

በደላቸው በዝቷልና፤

የክህደት ሥራቸው ተበራክቷል።+

 7 ታዲያ ይህን ነገር እንዴት ይቅር እልሻለሁ?

ወንዶች ልጆችሽ ትተውኛል፤

አምላክ ባልሆነውም ይምላሉ።+

እኔም የሚያስፈልጋቸውን ነገር አሟላሁላቸው፤

እነሱ ግን ምንዝር መፈጸማቸውን ቀጠሉ፤

ወደ ዝሙት አዳሪ ቤትም እየተንጋጉ ሄዱ።

 8 እንደሚቅበጠበጡ፣ ብርቱ ፈረሶች ናቸው፤

እያንዳንዱ የሌላውን ሰው ሚስት ተከትሎ ያሽካካል።+

 9 “ታዲያ በእነዚህ ነገሮች የተነሳ ተጠያቂ ላደርጋቸው አይገባም?” ይላል ይሖዋ።

“እንዲህ ዓይነቱን ሕዝብ ልበቀል* አይገባም?”+

10 “የወይን እርሻዋን እርከኖች ሄዳችሁ አበላሹ፤

ሆኖም ሙሉ በሙሉ አታጥፉት።+

የተንሰራፉ ቅርንጫፎቿን አስወግዱ፤

የይሖዋ አይደሉምና።

11 የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት

በእኔ ላይ ከፍተኛ ክህደት ፈጽመዋልና” ይላል ይሖዋ።+

12 “እነሱ ይሖዋን ክደዋል፤

‘እሱ ምንም ነገር አያደርግም።*+

በእኛ ላይ ምንም ጥፋት አይመጣም፤

ሰይፍም ሆነ ረሃብ አናይም’ ይላሉ።+

13 ነቢያቱ በነፋስ የተሞሉ ናቸው፤

ቃሉም* በውስጣቸው የለም።

ይህ በእነሱ ላይ ይድረስ!”

14 ስለዚህ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“እነዚህ ሰዎች እንዲህ ስለሚሉ፣

ቃሌን በአፋችሁ ውስጥ እሳት አደርጋለሁ፤+

እንጨቱ ደግሞ ይህ ሕዝብ ነው፤

እሳቱም ይበላቸዋል።”+

15 “የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እነሆ፣ በሩቅ ቦታ ያለን ብሔር አመጣባችኋለሁ”+ ይላል ይሖዋ።

“እሱም ለረጅም ጊዜ የኖረ ብሔር ነው።

ከጥንት ዘመን ጀምሮ የነበረ፣

ቋንቋውን የማታውቀውና

ንግግሩን የማትረዳው ብሔር ነው።+

16 የፍላጻ ኮሮጇቸው እንደተከፈተ መቃብር ነው፤

ሁሉም ተዋጊዎች ናቸው።

17 እነሱ አዝመራህንና ምግብህን ይበላሉ።+

ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን ይበላሉ።

መንጎችህንና ከብቶችህን ይበላሉ።

የወይን ተክሎችህንና የበለስ ዛፎችህን ይበላሉ።

የምትታመንባቸውን የተመሸጉ ከተሞችህን በሰይፍ ያወድማሉ።”

18 “ይሁንና በእነዚያ ቀናት እንኳ” ይላል ይሖዋ፣ “ሙሉ በሙሉ አላጠፋችሁም።+ 19 ‘አምላካችን ይሖዋ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ያደረገብን ለምንድን ነው?’ ብለው ሲጠይቁ ደግሞ ‘በምድራችሁ ላይ ባዕድ አምላክን ለማገልገል ስትሉ እኔን እንደተዋችሁኝ ሁሉ የራሳችሁ ባልሆነ ምድር ባዕዳንን ታገለግላላችሁ’ ትላቸዋለህ።”+

20 ይህን በያዕቆብ ቤት ተናገሩ፤

በይሁዳም እንዲህ ብላችሁ አውጁ፦

21 “እናንተ ሞኞችና የማመዛዘን ችሎታ የጎደላችሁ ሰዎች* ይህን ስሙ፦+

ዓይን አላቸው ግን አያዩም፤+

ጆሮ አላቸው ግን አይሰሙም።+

22 ‘እኔን አትፈሩም?’ ይላል ይሖዋ፤

‘በፊቴስ ልትሸበሩ አይገባም?

ውኃው አልፎ እንዳይሄድ፣ በማይሻር ድንጋጌ

አሸዋውን የባሕሩ ወሰን አድርጌ የሠራሁት እኔ ነኝ።

ሞገዶቹ ቢናወጡም ጥሰው መሄድ አይችሉም፤

ቢያስገመግሙም ከዚያ አልፈው መሄድ አይችሉም።+

23 ነገር ግን ይህ ሕዝብ ልቡ ግትርና ዓመፀኛ ነው፤

ጀርባቸውን ሰጥተው በራሳቸው መንገድ ሄደዋል።+

24 እነሱም በልባቸው

“እንግዲያው፣ ዝናቡን ይኸውም የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ

በወቅቱ የሚሰጠንን፣

የተወሰኑትን የአዝመራ ሳምንታት የሚጠብቅልንን

አምላካችንን ይሖዋን እንፍራ” አላሉም።+

25 የገዛ ራሳችሁ በደል እነዚህ ነገሮች እንዲቀሩ አድርጓል፤

የገዛ ኃጢአታችሁ መልካም የሆነ ነገር አሳጥቷችኋል።+

26 በሕዝቤ መካከል ክፉ ሰዎች አሉና።

አድብተው እንደሚጠብቁ ወፍ አዳኞች፣ በዓይነ ቁራኛ ይመለከታሉ።

ገዳይ ወጥመድ ይዘረጋሉ።

ሰዎችን ያጠምዳሉ።

27 በወፎች እንደተሞላ የወፍ ጎጆ፣

ቤቶቻቸው በማታለያ የተሞሉ ናቸው።+

ኃያላንና ሀብታም የሆኑት ለዚህ ነው።

28 ወፍረዋል፤ ቆዳቸውም ለስልሷል፤

በክፋት ተሞልተዋል።

ለራሳቸው ስኬት ሲያስቡ

አባት ለሌለው ልጅ አይሟገቱም፤+

ድሆችንም ፍትሕ ይነፍጋሉ።’”+

29 “ታዲያ በእነዚህ ነገሮች የተነሳ ተጠያቂ ላደርጋቸው አይገባም?” ይላል ይሖዋ።

“እንዲህ ዓይነቱን ሕዝብ ልበቀል* አይገባም?

30 በምድሪቱ ላይ የሚያስደነግጥና የሚያሰቅቅ ነገር ተከስቷል፦

31 ነቢያቱ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤+

ካህናቱም በራሳቸው ሥልጣን በኃይል ይገዛሉ።

የገዛ ሕዝቤም ይህን ወዶታል።+

ይሁንና መጨረሻው ሲመጣ ምን ታደርጉ ይሆን?”

6 እናንተ የቢንያም ልጆች፣ ተሸሸጉ፤ ከኢየሩሳሌም ወጥታችሁ ሽሹ።

በተቆአ+ ቀንደ መለከት ንፉ፤+

በቤትሃኬሬም እሳት በማንደድ ምልክት አሳዩ!

ከሰሜን ጥፋት፣ ይኸውም ታላቅ መዓት እያንዣበበ ነውና።+

 2 የጽዮን ሴት ልጅ ያማረችና ቅምጥል ሴት ትመስላለች።+

 3 እረኞችና መንጎቻቸው ይመጣሉ።

በዙሪያዋም ድንኳኖቻቸውን ይተክሉባታል፤+

እያንዳንዳቸውም የሚጠብቋቸውን መንጎች ያሰማራሉ።+

 4 “በእሷ ላይ ጦርነት ለማወጅ ተዘጋጁ!*

ተነሱ፣ እኩለ ቀን ላይ ጥቃት እንሰንዝርባት!”

“ወዮልን፣ ቀኑ እየመሸ፣

የምሽቱም ጥላ እየረዘመ ነውና!”

 5 “ተነሱ፣ በሌሊት ጥቃት እንሰንዝርባት፤

የማይደፈሩትንም ማማዎቿን እንደምስስ።”+

 6 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦

“እንጨት ቁረጡ፤ በኢየሩሳሌም ዙሪያም የአፈር ቁልል ደልድሉ።+

ይህች ከተማ ተጠያቂ ልትሆን ይገባል፤

በውስጧ ከግፍ በቀር ምንም አይገኝም።+

 7 የውኃ ጉድጓድ ውኃውን እንደቀዘቀዘ እንደሚያቆይ፣

እሷም ክፋቷን እንዳለ ጠብቃ አቆይታለች።

ዓመፅና ጥፋት በውስጧ ይሰማል፤+

ሕመምና ደዌ ምንጊዜም በፊቴ ናቸው።

 8 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ተጸይፌሽ ከአንቺ እንዳልርቅ* ተጠንቀቂ፤+

ባድማና ሰው የማይኖርበት ምድር አደርግሻለሁ።”+

 9 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“የእስራኤልን ቀሪዎች በወይን ተክል ላይ እንደቀሩ የመጨረሻ የወይን ፍሬዎች ምንም ሳያስቀሩ ይቃርሟቸዋል።

ከወይን ተክሎች ላይ የወይን ፍሬዎች እንደሚለቅም ሰው በድጋሚ እጅህን ዘርጋ።”

10 “ለማን ልናገር? ማንን ላስጠንቅቅ?

ማንስ ይሰማል?

እነሆ፣ ጆሮዎቻቸው ስለተዘጉ* ማዳመጥ አይችሉም።+

እነሆ፣ የይሖዋን ቃል መሳለቂያ አድርገውታል፤+

ቃሉም ደስ አያሰኛቸውም።

11 በመሆኑም በይሖዋ ቁጣ ተሞልቻለሁ፤

በውስጤ አፍኜ ስለያዝኩት ዝያለሁ።”+

“በጎዳና ባለ ልጅ፣

ተሰብስበው ባሉ ወጣቶች ላይ አፍስሰው።+

ባልም ሆነ ሚስቱ፣

አረጋውያኑም ሆኑ ያረጁት* ይያዛሉ።+

12 ቤቶቻቸው፣ እርሻዎቻቸውና ሚስቶቻቸው

ለሌሎች ይሰጣሉ።+

እጄን በምድሪቱ ነዋሪዎች ላይ እዘረጋለሁና” ይላል ይሖዋ።

13 “ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ እያንዳንዱ አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ይሯሯጣል፤+

ከነቢዩ አንስቶ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉም ያጭበረብራል።+

14 ሰላም ሳይኖር፣

‘ሰላም ነው! ሰላም ነው!’ እያሉ

የሕዝቤን ስብራት* ላይ ላዩን* ለመጠገን ይሞክራሉ።+

15 በፈጸሙት አስጸያፊ ተግባር ኀፍረት ተሰምቷቸዋል?

እነሱ እንደሆነ ጨርሶ ኀፍረት አይሰማቸውም!

ውርደት ምን ማለት እንደሆነ እንኳ አያውቁም!+

ስለዚህ ከወደቁት ጋር ይወድቃሉ።

እነሱን በምቀጣበት ጊዜ ይሰናከላሉ” ይላል ይሖዋ።

16 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“መስቀለኛ መንገዶቹ ላይ ቁሙና ተመልከቱ።

ስለ ጥንቶቹ ጎዳናዎች፣

መልካም የሆነው መንገድ የትኛው እንደሆነ ጠይቁ፤ በዚያም ሂዱ፤+

እረፍትም አግኙ።”*

እነሱ ግን “በዚያ አንሄድም” ይላሉ።+

17 “እኔም በእናንተ ላይ ጠባቂዎችን ሾምኩ፤+

ጠባቂዎቹም ‘የቀንደ መለከቱን ድምፅ በትኩረት አዳምጡ!’ አሉ”፤+

እነሱ ግን “አናዳምጥም” አሉ።+

18 “ስለዚህ እናንተ ብሔራት፣ ስሙ!

እናንተ ሰዎች ሆይ፣

ምን እንደሚደርስባቸው እወቁ።

19 ምድር ሆይ፣ ስሚ!

በእነዚህ ሰዎች ላይ የገዛ ውጥናቸውን ፍሬ፣

ጥፋትን አመጣባቸዋለሁ፤+

እነሱ ለቃሌ ምንም ትኩረት አልሰጡምና፤

ሕጌንም* አልተቀበሉም።”

20 “ነጭ ዕጣን ከሳባ፣

ጠጅ ሣር* ከሩቅ አገር ብታመጡልኝ ምን ይጠቅመኛል?

ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባችሁን አልቀበልም፤

መሥዋዕቶቻችሁም ደስ አያሰኙኝም።”+

21 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“በዚህ ሕዝብ ፊት መሰናክል አስቀምጣለሁ፤

አባቶችም ሆኑ ልጆች፣

ጎረቤትም ሆነ ባልንጀራው

በአንድነት ይሰናከላሉ፤

ሁሉም ይጠፋሉ።”+

22 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“እነሆ፣ ከሰሜን ምድር አንድ ሕዝብ እየመጣ ነው፤

ከምድር ዳርቻም ታላቅ ብሔር ይነሳል።+

23 ቀስትና ጦር ይይዛሉ።

ጨካኝና ምሕረት የለሽ ናቸው።

ድምፃቸው እንደ ባሕር ያስተጋባል፤

ፈረሶችንም ይጋልባሉ።+

የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ ልክ እንደ ተዋጊ በአንቺ ላይ ይሰለፋሉ።”

24 ወሬውን ሰምተናል።

እጆቻችንም ዝለዋል፤+

በጭንቀት ተውጠናል፤

ልትወልድ እንደተቃረበች ሴት ሥቃይ ቀስፎናል።*+

25 ወደ ውጭ አትውጡ፤

በመንገዱም ላይ አትዘዋወሩ፤

ጠላት ሰይፍ ታጥቋልና፤

በየቦታውም ሽብር ነግሦአል።

26 የሕዝቤ ሴት ልጅ ሆይ፣

ማቅ ልበሺ፤+ በአመድም ላይ ተንከባለዪ።

አንድ ልጁን እንዳጣ ሰው መራራ ለቅሶ አልቅሺ፤+

አጥፊው በእኛ ላይ በድንገት ይመጣልና።+

27 “አንተን* በሕዝቤ መካከል ብረትን እንደሚፈትን፣

በጥንቃቄም እንደሚመረምር ሰው አድርጌሃለሁ፤

አንተም ልብ በል፤ መንገዳቸውንም መርምር።

28 ሁሉም በጣም ግትር ናቸው፤+

እየዞሩ ስም ያጠፋሉ።+

እንደ መዳብና ብረት ናቸው፤

ሁሉም ምግባረ ብልሹዎች ናቸው።

29 ወናፎቹ በእሳት ተቃጠሉ።

ከእሳቱም የሚወጣው እርሳስ ነው።

አንጥረኛ በደንብ የሚያጣራው እንዲያው በከንቱ ነው፤+

መጥፎዎቹም ተለይተው አልወጡም።+

30 ሰዎች ‘የተጣለ ብር’ ብለው ይጠሯቸዋል፤

ይሖዋ ጥሏቸዋልና።”+

7 ከይሖዋ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፦ 2 “በይሖዋ ቤት በር ላይ ቆመህ በዚያ ይህን መልእክት አውጅ፦ ‘ለይሖዋ ለመስገድ በእነዚህ በሮች የምትገቡ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ፣ የይሖዋን ቃል ስሙ። 3 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “መንገዳችሁንና ተግባራችሁን አስተካክሉ፤ እኔም በዚህ ስፍራ እንድትኖሩ እፈቅድላችኋለሁ።+ 4 ‘ይህ* የይሖዋ ቤተ መቅደስ፣ የይሖዋ ቤተ መቅደስ፣ የይሖዋ ቤተ መቅደስ ነው!’ እያላችሁ በአሳሳች ቃል አትታመኑ።+ 5 በእርግጥ መንገዳችሁንና ተግባራችሁን ብታስተካክሉ፣ በሰውና በባልንጀራው መካከል ፍትሕ ብታሰፍኑ፣+ 6 ከባዕድ አገር የመጣውን ሰው፣ ወላጅ አልባ የሆኑ ልጆችንና* መበለቶችን ባትጨቁኑ፣+ በዚህ ቦታ የንጹሕ ሰው ደም ባታፈሱ እንዲሁም ጉዳት ላይ የሚጥሏችሁን ሌሎች አማልክት ባትከተሉ፣+ 7 በዚህች ስፍራ፣ ለአባቶቻችሁ በሰጠኋቸው በዚህ ምድር ለዘለቄታው እንድትኖሩ እፈቅድላችኋለሁ።”’”

8 “እናንተ ግን አሳሳች በሆነ ቃል ታምናችኋል፤+ ይህ ደግሞ ፈጽሞ አይጠቅማችሁም። 9 እየሰረቃችሁ፣+ እየገደላችሁ፣ እያመነዘራችሁ፣ በሐሰት እየማላችሁ፣+ ለባአል መሥዋዕት* እያቀረባችሁና+ የማታውቋቸውን አማልክት እየተከተላችሁ፣ 10 በስሜ ወደሚጠራው ወደዚህ ቤት መጥታችሁ በፊቴ መቆምና እነዚህን ሁሉ አስጸያፊ ነገሮች እያደረጋችሁ ‘ምንም ችግር አይደርስብንም’ ማለት ትችላላችሁ? 11 ስሜ የሚጠራበት ይህ ቤት በእናንተ ዓይን የዘራፊዎች ዋሻ ሆኗል ማለት ነው?+ እነሆ፣ እኔ ራሴ ይህን አይቻለሁ” ይላል ይሖዋ።

12 “‘አሁን ግን መጀመሪያ የስሜ ማደሪያ+ አድርጌው ወደነበረው በሴሎ+ ወዳለው ስፍራዬ ሂዱ፤ ከሕዝቤ ከእስራኤል ክፋት የተነሳም ምን እንዳደረግኩት እዩ።+ 13 እናንተ ግን እነዚህን ሁሉ ነገሮች መሥራታችሁን ቀጠላችሁ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘ለእናንተ ደግሜ ደጋግሜ* ብናገርም እንኳ አልሰማችሁም።+ ደጋግሜ ጠራኋችሁ፤ እናንተ ግን መልስ አትሰጡም።+ 14 ስለዚህ በሴሎ እንዳደረግኩት ሁሉ በስሜ በተጠራው፣+ እናንተም በምትታመኑበት በዚህ ቤት+ ላይ እንዲሁም ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጠሁት በዚህ ቦታ ላይ እንዲሁ አደርጋለሁ።+ 15 ወንድሞቻችሁን ሁሉ ይኸውም መላውን የኤፍሬም ዘር እንዳስወገድኩ እናንተንም ከፊቴ አስወግዳችኋለሁ።’+

16 “አንተም ለዚህ ሕዝብ አትጸልይ። እኔ ስለማልሰማህ+ ስለ እነሱ የልመና ጩኸትም ሆነ ጸሎት አታሰማ ወይም እኔን አትማጸን።+ 17 በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ የሚያደርጉትን አታይም? 18 እኔን ያሳዝኑ ዘንድ ‘ለሰማይ ንግሥት’* መሥዋዕት የሚሆን ቂጣ ለመጋገር ወንዶች ልጆች እንጨት ይሰበስባሉ፣ አባቶች እሳት ያቀጣጥላሉ፣ ሚስቶች ደግሞ ሊጥ ያቦካሉ፤+ ለሌሎች አማልክትም የመጠጥ መባ ያፈሳሉ።+ 19 ‘ለመሆኑ የሚጎዱት* እኔን ነው?’ ይላል ይሖዋ። ‘በራሳቸው ላይ ውርደት በማምጣት የሚጎዱት ራሳቸውን አይደለም?’+ 20 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ንዴቴና ቁጣዬ በዚህ ቦታ፣ በሰውና በእንስሳ፣ በዱር ዛፎችና በምድሪቱ ፍሬ ላይ ይፈስሳል፤+ ቁጣዬ ይነድዳል፤ ፈጽሞም አይጠፋም።’+

21 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የጀመራችሁትን ግፉበት፤ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎቻችሁን በሌሎች መሥዋዕቶቻችሁ ላይ ጨምሩ፤ ሥጋውንም ራሳችሁ ብሉ።+ 22 አባቶቻችሁን ከግብፅ ምድር ባወጣኋቸው ጊዜ ሙሉ በሙሉ ስለሚቃጠሉ መባዎችና መሥዋዕቶች አልነገርኳቸውም ወይም አላዘዝኳቸውም።+ 23 ከዚህ ይልቅ ይህን ትእዛዝ ሰጥቻቸው ነበር፦ “ድምፄን ስሙ፤ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ፤ እናንተም ሕዝቤ ትሆናላችሁ።+ መልካም እንዲሆንላችሁ በማዛችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ።”’+ 24 እነሱ ግን አልሰሙም ወይም ጆሯቸውን አልሰጡም፤+ ይልቁንም ግትር ሆነው ክፉ ልባቸውን በመከተል በገዛ ራሳቸው ዕቅድ* ሄዱ፤+ ወደ ፊት በመሄድ ፋንታ ወደ ኋላ ተመለሱ፤ 25 አባቶቻችሁ ከግብፅ ምድር ከወጡበት ጊዜ አንስቶ እስከዚህ ቀን ድረስ ይህን አደረጉ።+ በመሆኑም አገልጋዮቼ የሆኑትን ነቢያት ሁሉ ወደ እናንተ መላኬን ቀጠልኩ፤ ደግሜ ደጋግሜ በየዕለቱ* ላክኋቸው።+ 26 እነሱ ግን እኔን ለመስማት እንቢተኛ ሆኑ፤ ጆሯቸውንም አልሰጡም።+ ይልቁንም ግትር ሆኑ፤* አባቶቻቸው ከሠሩት የከፋ ነገር አደረጉ!

27 “ይህን ሁሉ ቃል ትነግራቸዋለህ፤+ እነሱ ግን አይሰሙህም፤ ትጠራቸዋለህ፤ እነሱ ግን አይመልሱልህም። 28 እንዲህም ትላቸዋለህ፦ ‘ይህ ብሔር የአምላኩን የይሖዋን ድምፅ አልሰማም፤ ተግሣጽ ለመቀበልም እንቢተኛ ሆኗል። ታማኝነት ጠፍቷል፤ በመካከላቸውም ጨርሶ አይነሳም።’*+

29 “ያልተቆረጠውን* ፀጉርሽን ሸልተሽ ጣይው፤ በተራቆቱት ኮረብቶችም ላይ ሙሾ አውርጂ፤* ይሖዋ እጅግ ያስቆጣውን ይህን ትውልድ ጥሎታልና፤ እርግፍ አድርጎም ይተወዋል። 30 ‘የይሁዳ ሰዎች በፊቴ መጥፎ ነገር ሠርተዋልና’ ይላል ይሖዋ። ‘አስጸያፊ ጣዖቶቻቸውን በስሜ በተጠራው ቤት ውስጥ በማስቀመጥ አርክሰውታል።+ 31 ያላዘዝኩትንና በልቤ እንኳ ፈጽሞ ያላሰብኩትን* ነገር ለማድረግ ይኸውም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት ለማቃጠል+ በሂኖም ልጅ ሸለቆ*+ የሚገኘውን የቶፌትን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች ሠርተዋል።’+

32 “‘ከዚህ የተነሳ፣’ ይላል ይሖዋ፣ ‘የእርድ ሸለቆ እንጂ ቶፌት ወይም የሂኖም ልጅ ሸለቆ* ተብሎ የማይጠራበት ጊዜ ይመጣል። እነሱም ቦታ እስኪታጣ ድረስ በቶፌት ይቀብራሉ።+ 33 የዚህ ሕዝብ አስከሬንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ሲሳይ ይሆናል፤ ፈርተው እንዲሸሹ የሚያደርጋቸውም የለም።+ 34 የሐሴትንና የደስታን ድምፅ እንዲሁም የሙሽራንና የሙሽሪትን ድምፅ፣ ከይሁዳ ከተሞችና ከኢየሩሳሌም ጎዳናዎች አጠፋለሁ፤+ ምድሪቱ የፍርስራሽ ክምር ትሆናለችና።’”+

8 “በዚያን ጊዜ” ይላል ይሖዋ፣ “የይሁዳ ነገሥታት አጥንቶች፣ የመኳንንቱ አጥንቶች፣ የካህናቱ አጥንቶች፣ የነቢያቱ አጥንቶችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች አጥንቶች ከየመቃብራቸው ይወሰዳሉ። 2 በወደዷቸው፣ ባገለገሏቸው፣ በተከተሏቸው፣ ባማከሯቸውና በሰገዱላቸው በፀሐይ፣ በጨረቃና በሰማያት ሠራዊት ሁሉ ፊት ይሰጣሉ።+ አይሰበሰቡም፤ እንዲሁም አይቀበሩም። በምድር ላይ እንደ ፍግ ይሆናሉ።”+

3 “ደግሞም ከዚህ ክፉ ወገን የሚተርፉት ቀሪዎች በሙሉ እኔ በምበትናቸው ቦታዎች ሁሉ ከሕይወት ይልቅ ሞትን ይመርጣሉ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።

4 “አንተም እንዲህ በላቸው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“ሰዎች ከወደቁ በኋላ ዳግመኛ አይነሱም?

አንዱ ከተመለሰ ሌላውስ አይመለስም?

 5 ታዲያ ይህ ሕዝብ፣ የኢየሩሳሌም ነዋሪ በክህደት ሥራው የጸናው ለምንድን ነው?

ተንኮልን የሙጥኝ ብለዋል፤

ለመመለስ አሻፈረን ብለዋል።+

 6 እኔም ትኩረት ሰጥቼ ማዳመጤን ቀጠልኩ፤ የሚናገሩበት መንገድ ግን ትክክል አልነበረም።

ከክፋቱ ንስሐ የገባ ወይም ‘ምን መሥራቴ ነው?’ ብሎ የጠየቀ አንድም ሰው የለም።+

እያንዳንዱ ሰው ወደ ጦርነት እንደሚገሰግስ ፈረስ ብዙኃኑ ወደሚከተለው መንገድ ይመለሳል።

 7 በሰማይ የምትበረው ራዛ* እንኳ ወቅቷን* ታውቃለች፤

ዋኖስ፣ ወንጭፊትና ጭሪ* የሚመለሱበትን* ጊዜ ያከብራሉ።

የገዛ ሕዝቤ ግን የይሖዋን ፍርድ አይገነዘብም።”’+

 8 ‘“ጥበበኞች ነን፤ የይሖዋም ሕግ* አለን” እንዴት ትላላችሁ?

እንዲያውም የጸሐፊዎቹ ሐሰተኛ* ብዕር+ ያገለገለው ውሸት ለመጻፍ ብቻ ነው።

 9 ጥበበኞቹ ለኀፍረት ተዳርገዋል።+

ተሸብረዋል፤ ደግሞም ይያዛሉ።

እነሆ፣ እነሱ የይሖዋን ቃል ንቀዋል፤

ታዲያ ምን ዓይነት ጥበብ ይኖራቸዋል?

10 ስለዚህ ሚስቶቻቸውን ለሌሎች ሰዎች፣

እርሻዎቻቸውንም ለሌሎች እሰጣለሁ፤+

ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ ሁሉም አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ይሯሯጣልና፤+

ከነቢዩ አንስቶ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉም ያጭበረብራል።+

11 ሰላም ሳይኖር፣

“ሰላም ነው! ሰላም ነው!” እያሉ

የሕዝቤን ሴት ልጅ ስብራት ላይ ላዩን* ለመጠገን ይሞክራሉ።+

12 በፈጸሙት አስጸያፊ ተግባር ኀፍረት ተሰምቷቸዋል?

እነሱ እንደሆነ ጨርሶ ኀፍረት አይሰማቸውም!

ውርደት ምን ማለት እንደሆነ እንኳ አያውቁም!+

“‘ስለዚህ ከወደቁት ጋር ይወድቃሉ።

እነሱን በምቀጣበት ጊዜ ይሰናከላሉ’+ ይላል ይሖዋ።

13 ‘በምሰበስባቸው ጊዜ አጠፋቸዋለሁ’ ይላል ይሖዋ።

‘በወይን ተክሉ ላይ የቀረ የወይን ፍሬ አይኖርም፤ በበለስ ዛፉ ላይ የበለስ ፍሬ አይገኝም፤ ቅጠሉም ይጠወልጋል።

የሰጠኋቸውም ነገር ይጠፋባቸዋል።’”

14 “እዚህ የምንቀመጠው ለምንድን ነው?

በአንድነት እንሰብሰብ፤ ወደ ተመሸጉትም ከተሞች ገብተን+ በዚያ እንጥፋ።

አምላካችን ይሖዋ ያጠፋናልና፤

የተመረዘ ውኃ እንድንጠጣ ይሰጠናል፤+

ምክንያቱም በይሖዋ ላይ ኃጢአት ሠርተናል።

15 ሰላምን ተስፋ አደረግን፤ ሆኖም መልካም ነገር አልመጣም፤

የፈውስ ጊዜ ይመጣል ብለን ጠበቅን፤ ነገር ግን ሽብር ነገሠ!+

16 የፈረሶቹ ፉርፉርታ ከዳን ተሰማ።

ድንጉላ ፈረሶቹ ሲያሽካኩ

ምድሪቱ በሙሉ ትንቀጠቀጣለች።

እነሱ መጥተው ምድሪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ፣

ከተማዋንና ነዋሪዎቿን ይበላሉ።”

17 “እነሆ፣ ድግምት የማይገታቸው እባቦችንና እፉኝቶችን

በመካከላችሁ እልካለሁ፤

እነሱም ይነድፏችኋል” ይላል ይሖዋ።

18 ማጽናኛ የማይገኝለት ሐዘን ደርሶብኛል፤

ልቤ ታሟል።

19 የሕዝቤ ሴት ልጅ “ይሖዋ በጽዮን የለም?

ወይስ ንጉሧ በዚያ የለም?”

የሚል የእርዳታ ጥሪ

ከሩቅ አገር ታሰማለች።

“በተቀረጹት ምስሎቻቸውና

ከንቱ በሆኑት ባዕዳን አማልክታቸው ያስከፉኝ ለምንድን ነው?”

20 “መከሩ አልፏል፤ በጋውም አብቅቷል፤

እኛ ግን አልዳንም!”

21 በሕዝቤ ሴት ልጅ ውድቀት የተነሳ ደቅቄአለሁ፤+

በጣም አዝኛለሁ፤

በፍርሃት ተውጫለሁ።

22 በጊልያድ የበለሳን ዘይት የለም?*+

ወይስ በዚያ ፈዋሽ* የለም?+

ታዲያ የሕዝቤ ሴት ልጅ ያላገገመችው ለምንድን ነው?+

9 ምነው ራሴ በውኃ በተሞላ!

ዓይኖቼ የእንባ ምንጭ በሆኑ!+

ለታረዱት ወገኖቼ

ቀን ከሌት ባለቀስኩ ነበር።

 2 ምነው በምድረ በዳ ለተጓዦች የሚሆን ማረፊያ ቦታ ባገኘሁ ኖሮ!

በዚያን ጊዜ ሕዝቤን ትቼና ከእነሱ ተለይቼ በሄድኩ ነበር፤

ሁሉም አመንዝሮች፣+

የከዳተኞች ጥርቅም ሆነዋልና።

 3 ምላሳቸውን እንደ ደጋን ወጠሩ፤

በምድሪቱ ላይ ታማኝነት ሳይሆን ውሸት ሰፍኗል።+

“በክፋት ላይ ክፋት እየጨመሩ ይሄዳሉ፤

እኔንም ጨርሶ አይሰሙም”+ ይላል ይሖዋ።

 4 “እያንዳንዳችሁ ራሳችሁን ከባልንጀራችሁ ጠብቁ፤

ወንድማችሁን እንኳ ሳይቀር አትመኑ።

እያንዳንዱ ወንድም ከሃዲ ነውና፤+

እያንዳንዱ ባልንጀራም ስም አጥፊ ነው።+

 5 እያንዳንዱ ባልንጀራውን ያታልላል፤

አንድም ሰው እውነትን አይናገርም።

ምላሳቸውን ውሸት መናገር አስተምረውታል።+

ትክክል ያልሆነ ነገር በማድረግ ራሳቸውን ያደክማሉ።

 6 የምትኖረው አታላይ በሆኑ ሰዎች መካከል ነው።

አታላይ ከመሆናቸውም የተነሳ እኔን ለማወቅ እንቢተኞች ሆነዋል” ይላል ይሖዋ።

 7 ስለዚህ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“እኔ አቀልጣቸዋለሁ፤ ደግሞም እፈትናቸዋለሁ፤+

ከሕዝቤ ሴት ልጅ ጋር በተያያዘ ከዚህ ሌላ ምን ማድረግ እችላለሁ?

 8 ምላሳቸው ማታለያ የሚናገር፣ ገዳይ ፍላጻ ነው።

ሰው በአፉ ለባልንጀራው ስለ ሰላም ይናገራል፤

በውስጡ ግን ለማጥቃት ያደባል።”

 9 “ታዲያ በእነዚህ ነገሮች የተነሳ ተጠያቂ ላደርጋቸው አይገባም?” ይላል ይሖዋ።

“እንዲህ ዓይነቱን ሕዝብ ልበቀል* አይገባም?+

10 በተራሮቹ የተነሳ አለቅሳለሁ፤ ዋይ ዋይም እላለሁ፤

በምድረ በዳ ባሉት ማሰማሪያዎችም የተነሳ ሙሾ አወርዳለሁ፤*

ማንም ሰው እንዳያልፍባቸው በእሳት ተቃጥለዋልና፤

የከብቶችም ድምፅ አይሰማም።

የሰማይ ወፎችና የዱር አራዊት ሸሽተዋል፤ ከአካባቢው ጠፍተዋል።+

11 ኢየሩሳሌምን የድንጋይ ክምር፣+ የቀበሮም ጎሬ አደርጋታለሁ፤+

የይሁዳንም ከተሞች ሰው የማይኖርበት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።+

12 ይህን ይረዳ ዘንድ ጥበበኛ የሆነ ማን ነው?

ይህን ያሳውቅ ዘንድ የይሖዋ አፍ የተናገረው ለማን ነው?

ምድሪቱ የጠፋችው ለምንድን ነው?

ማንም እንዳያልፍባት

እንደ ምድረ በዳ የተለበለበችው ለምንድን ነው?”

13 ይሖዋ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “በፊታቸው ያኖርኩትን ሕጌን* ስለተዉና ስላልተከተሉ እንዲሁም ድምፄን ስላልሰሙ ነው። 14 ከዚህ ይልቅ ግትር ሆነው የገዛ ልባቸውን+ እንዲሁም አባቶቻቸው ባስተማሯቸው መሠረት የባአልን ምስሎች ተከተሉ።+ 15 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ይህ ሕዝብ ጭቁኝ እንዲበላ አደርጋለሁ፤ የተመረዘም ውኃ እንዲጠጣ አደርጋለሁ።+ 16 እነሱም ሆኑ አባቶቻቸው በማያውቋቸው ብሔራት መካከል እበትናቸዋለሁ፤+ ሙሉ በሙሉ እስካጠፋቸውም ድረስ ከኋላቸው ሰይፍን እሰዳለሁ።’+

17 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

‘በማስተዋል ተመላለሱ።

ሙሾ የሚያወርዱትን* ሴቶች ጥሩ፤+

የሠለጠኑ አልቃሽ ሴቶችንም ልካችሁ አስመጡ፤

18 ዓይኖቻችን እንባ ያጎርፉ ዘንድ፣

ሽፋሽፍቶቻችንም ውኃ ያንጠባጥቡ ዘንድ

ፈጥነው እንዲመጡና የሐዘን እንጉርጉሮ እንዲያንጎራጉሩልን ጥሯቸው።+

19 ከጽዮን የሐዘን እንጉርጉሮ ድምፅ ተሰምቷልና፦+

“ከባድ ጥፋት ደርሶብናል!

ታላቅ ኀፍረት ተከናንበናል!

ምድሪቱን ጥለን ሄደናልና፤ እነሱም ቤቶቻችንን አፈራርሰዋል።”+

20 እናንተ ሴቶች፣ የይሖዋን ቃል ስሙ።

ጆሯችሁ የአፉን ቃል ያዳምጥ።

ሴቶች ልጆቻችሁን ይህን የሐዘን እንጉርጉሮ አስተምሯቸው፤

አንዳችሁም ለሌላው ይህን ሙሾ አስተምሩ።+

21 ሞት በመስኮቶቻችን በኩል ገብቷልና፤

ልጆቹን ከጎዳናዎቹ፣

ወጣቶቹንም ከአደባባዮቹ ለመውሰድ

ወደማይደፈሩት ማማዎቻችን ገብቷል።’+

22 እንዲህ በል፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ሲል አውጇል፦

“የሰዎች አስከሬን በምድር ላይ ልክ እንደ ፍግ ይወድቃል፤

አጫጅ አጭዶ እንደተወውም እህል ይሆናል፤

የሚሰበስበው አይኖርም።”’”+

23 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“ጥበበኛው በጥበቡ አይኩራራ፤+

ኃያሉ በኃያልነቱ አይኩራራ፤

ባለጸጋውም በሀብቱ አይኩራራ።”+

24 “ከዚህ ይልቅ የሚኩራራ በዚህ ነገር ይኩራራ፦

ስለ እኔ ጥልቅ ማስተዋልና እውቀት ያለው በመሆኑ+

እንዲሁም በምድር ላይ ታማኝ ፍቅር የማሳየው፣ ደግሞም ፍትሕና ጽድቅ የማሰፍነው እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ በማወቁ ይኩራራ፤+

በእነዚህ ነገሮች ደስ እሰኛለሁና”+ ይላል ይሖዋ።

25 “እነሆ፣ እንዲህ የሚሆንበት ቀን ይመጣል” ይላል ይሖዋ፣ “የተገረዘ ቢሆንም እንኳ ያልተገረዘውን ሁሉ ተጠያቂ አደርጋለሁ፤+ 26 ግብፅን፣+ ይሁዳን፣+ ኤዶምን፣+ አሞናውያንን፣+ ሞዓብንና+ በሰሪሳራቸው* ላይ ያለውን ፀጉር የሚላጩትን በምድረ በዳ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ተጠያቂ አደርጋለሁ፤+ ብሔራት ሁሉ ያልተገረዙ ናቸውና፤ የእስራኤልም ቤት ሁሉ ልባቸው ያልተገረዘ ነው።”+

10 የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ይሖዋ በእናንተ ላይ የተናገረውን ቃል ስሙ። 2 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“የብሔራትን መንገድ አትማሩ፤+

በሰማያት ምልክቶችም አትሸበሩ፤

ምክንያቱም ብሔራት በእነዚህ ነገሮች ተሸብረዋል።+

 3 የእነዚህ ሕዝቦች ልማድ ከንቱ* ነውና፤

የእጅ ጥበብ ባለሙያ ዛፍ ከጫካ ይቆርጥና

በመሣሪያው* ጠርቦ ጣዖት ይሠራል።+

 4 በብርና በወርቅ ያስጌጡታል፤+

እንዳይወድቅም በመዶሻና በምስማር ይቸነክሩታል።+

 5 እነሱ በኪያር እርሻ ውስጥ ለወፍ ማስፈራሪያነት እንደሚተከል ማስፈራርቾ መናገር አይችሉም፤+

መራመድ ስለማይችሉ ተሸካሚ ያስፈልጋቸዋል።+

ጉዳት ማድረስም ሆነ

ምንም ዓይነት መልካም ነገር መሥራት ስለማይችሉ አትፍሯቸው።”+

 6 ይሖዋ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ማንም የለም።+

አንተ ታላቅ ነህ፤ ስምህም ታላቅና ኃያል ነው።

 7 የብሔራት ንጉሥ ሆይ፣+ አንተን የማይፈራ ማን ነው? አንተ ልትፈራ ይገባሃልና፤

ምክንያቱም ከብሔራት ጠቢባን ሁሉ እንዲሁም ከመንግሥቶቻቸው ሁሉ መካከል

እንደ አንተ ያለ ማንም የለም።+

 8 ሁሉም የማመዛዘን ችሎታ የጎደላቸውና ሞኞች ናቸው።+

ከእንጨት ምስል የሚመጣ መመሪያ ፈጽሞ ከንቱ* ነው።+

 9 በእጅ ጥበብ ባለሙያና በአንጥረኛ የተሠራ

የተጠፈጠፈ ብር ከተርሴስ፣+ ወርቅም ከዑፋዝ ይመጣል።

ልብሳቸው በሰማያዊ ክርና በሐምራዊ ሱፍ የተሠራ ነው።

ሁሉም በባለሙያዎች የተሠሩ ናቸው።

10 ይሖዋ ግን እውነተኛ አምላክ ነው።

እሱ ሕያው አምላክና+ ዘላለማዊ ንጉሥ ነው።+

ከቁጣው የተነሳ ምድር ትናወጣለች፤+

የእሱን ውግዘት ሊቋቋም የሚችል አንድም ብሔር የለም።

11 * እናንተ እንዲህ በሏቸው፦

“ሰማያትንና ምድርን ያልሠሩት አማልክት

ከምድር ገጽ፣ ከእነዚህም ሰማያት በታች ይጠፋሉ።”+

12 ምድርን በኃይሉ የሠራው፣

ፍሬያማ የሆነችውን መሬት በጥበቡ የመሠረተውና+

ሰማያትን በማስተዋሉ የዘረጋው እሱ ነው።+

13 ድምፁን ሲያሰማ

በሰማያት ያሉ ውኃዎች ይናወጣሉ፤+

ደመና* ከምድር ዳርቻዎች ወደ ላይ እንዲወጣ ያደርጋል።+

በዝናብ ጊዜ መብረቅን ያበርቃል፤*

ነፋሱንም ከግምጃ ቤቱ ያወጣል።+

14 እያንዳንዱ ሰው ማስተዋልና እውቀት የጎደለው ድርጊት ይፈጽማል።

እያንዳንዱ አንጥረኛ፣ በተቀረጸው ምስል የተነሳ ኀፍረት ይከናነባል፤+

ከብረት የተሠራው ምስሉ* ሐሰት ነውና፤

በውስጣቸውም መንፈስ* የለም።+

15 እነሱ ከንቱና* መሳለቂያ ናቸው።+

የሚመረመሩበት ቀን ሲመጣ ይጠፋሉ።

16 የያዕቆብ ድርሻ ግን እንደነዚህ ነገሮች አይደለም፤

እሱ የሁሉ ነገር ሠሪ ነውና፤

እስራኤልም የርስቱ በትር ነው።+

ስሙ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ነው።+

17 አንቺ የተከበብሽ ሴት፣

ጓዝሽን ከመሬት ላይ ሰብስቢ።

18 ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦

“እነሆ፣ በዚህ ጊዜ ነዋሪዎቹን ከምድሪቱ ውጭ እወረውራቸዋለሁ፤*+

ጭንቀት እንዲይዛቸውም አደርጋለሁ።”

19 ስብራት* ደርሶብኛልና ወዮልኝ!+

ቁስሌ የማይድን ነው።

እኔም እንዲህ አልኩ፦ “በእርግጥ ይህ የእኔ ሕመም ነው፤ ልሸከመውም ይገባል።

20 ድንኳኔ ፈርሷል፤ የድንኳኔም ገመዶች ሁሉ ተበጥሰዋል።+

ወንዶች ልጆቼ ጥለውኝ ሄደዋል፤ ከዚህ በኋላ አይኖሩም።+

ድንኳኔን የሚተክልልኝ ወይም የድንኳኔን ሸራዎች የሚዘረጋልኝ አንድም ሰው የለም።

21 እረኞቹ የሞኝነት ድርጊት ፈጽመዋልና፤+

ይሖዋንም አልጠየቁም።+

ማስተዋል የጎደለው ድርጊት የፈጸሙት ለዚህ ነው፤

መንጎቻቸውም ሁሉ ተበታትነዋል።”+

22 አዳምጡ! አንድ ወሬ ስሙ! ወደዚህ እየመጣ ነው!

የይሁዳን ከተሞች ባድማና የቀበሮዎች ጎሬ ሊያደርግ+

ከሰሜን ምድር ድም፣ ድም የሚል ኃይለኛ ድምፅ እየቀረበ ነው።+

23 ይሖዋ ሆይ፣ የሰው መንገድ በራሱ እጅ እንዳልሆነ በሚገባ አውቃለሁ።

አካሄዱን እንኳ በራሱ አቃንቶ መምራት አይችልም።+

24 ይሖዋ ሆይ፣ አርመኝ፤

ሆኖም ፈጽመህ እንዳታጠፋኝ+ በፍትሕ እንጂ በቁጣህ አይሁን።+

25 አንተን ችላ በሚሉ ብሔራት+

እንዲሁም ስምህን በማይጠሩ ነገዶች ላይ ቁጣህን አፍስስ።

ያዕቆብን በልተውታልና፤+

አዎ፣ ሙሉ በሙሉ እስኪጠፋ ድረስ በልተውታል፤+

የትውልድ አገሩንም አውድመዋል።+

11 ከይሖዋ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፦ 2 “እናንተ ሰዎች፣ የዚህን ቃል ኪዳን ቃል ስሙ!

“ለይሁዳ ሰዎችና ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ቃሉን ተናገር፤* 3 እንዲህም በላቸው፦ ‘የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የዚህን ቃል ኪዳን ቃል የማይታዘዝ ሰው የተረገመ ነው፤+ 4 ይህም አባቶቻችሁን ከግብፅ ምድር፣ ከብረት ማቅለጫ ምድጃው ባወጣኋቸው ጊዜ+ እንዲህ ብዬ ያዘዝኳቸው ቃል ነው፦+ ‘ድምፄን ስሙ፤ ያዘዝኳችሁንም ነገር ሁሉ አድርጉ፤ እናንተም ሕዝቤ ትሆናላችሁ፤ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ፤+ 5 ይህም ዛሬ እንደሆነው ሁሉ ወተትና ማር የምታፈሰውን ምድር ለመስጠት ለአባቶቻችሁ የገባሁትን መሐላ ለመፈጸም ነው።’”’”+

እኔም “ይሖዋ ሆይ፣ አሜን”* ብዬ መለስኩ።

6 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “እነዚህን ቃላት ሁሉ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ አውጅ፦ ‘የዚህን ቃል ኪዳን ቃል ስሙ፤ በሥራም ላይ አውሉት። 7 አባቶቻችሁን ከግብፅ ምድር ካወጣሁበት ቀን አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ “ድምፄን ስሙ” በማለት ደግሜ ደጋግሜ* አጥብቄ ሳሳስባቸው ነበርና።+ 8 እነሱ ግን አልሰሙም ወይም ጆሯቸውን አልሰጡም፤ ከዚህ ይልቅ እያንዳንዳቸው ግትር ሆነው የገዛ ክፉ ልባቸውን ተከተሉ።+ ስለዚህ ተግባራዊ እንዲያደርጉት ያዘዝኳቸውንና እነሱ ሥራ ላይ ያላዋሉትን የዚህን ቃል ኪዳን ቃል ሁሉ በእነሱ ላይ አመጣሁባቸው።’”

9 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “የይሁዳ ሰዎችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሴራ ጠንስሰዋል። 10 ቃሌን ያልታዘዙት የቀድሞ አባቶቻቸው ይፈጽሙት ወደነበረው በደል ተመልሰዋል።+ እነሱም ሌሎች አማልክትን ተከትለዋል፤ ደግሞም አገልግለዋል።+ የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት ከአባቶቻቸው ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል።+ 11 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ማምለጥ የማይችሉትን ጥፋት አመጣባቸዋለሁ።+ እርዳታ ለማግኘት ወደ እኔ ሲጮኹ አልሰማቸውም።+ 12 ከዚያም የይሁዳ ከተሞችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች መሥዋዕት* ወደሚያቀርቡላቸው አማልክት ሄደው እርዳታ ይጠይቃሉ፤+ ሆኖም ጥፋት በሚደርስባቸው ጊዜ ፈጽሞ አያድኗቸውም። 13 ይሁዳ ሆይ፣ አማልክትህ የከተሞችህን ያህል በዝተዋልና፤ ለአሳፋሪው ነገር* ይኸውም ለባአል መሥዋዕት ለማቅረብ የኢየሩሳሌምን ጎዳናዎች ያህል ብዛት ያላቸው መሠዊያዎች ሠርታችኋል።’+

14 “አንተም* ለዚህ ሕዝብ አትጸልይ። ስለ እነሱ የልመና ጩኸትም ሆነ ጸሎት አታሰማ፤+ ጥፋት ደርሶባቸው ወደ እኔ ሲጮኹ አልሰማቸውምና።

15 ብዙዎቹ የሸረቡትን ክፉ ሐሳብ እየፈጸሙ ሳለ፣

ውዴ በቤቴ ለመገኘት ምን መብት አላት?

ጥፋት በአንቺ ላይ ሲመጣ በቅዱስ ሥጋ* ጥፋቱን ሊከላከሉልሽ ይችላሉ?

በዚያን ጊዜ ሐሴት ታደርጊ ይሆን?

16 በአንድ ወቅት ይሖዋ በመልካም ፍሬ የተዋበ፣

የለመለመ የወይራ ዛፍ ብሎ ጠርቶሽ ነበር።

በሚያስገመግም ታላቅ ድምፅ፣ በእሳት አነደዳት፤

እነሱም ቅርንጫፎቿን ሰባበሩ።

17 “የተከለሽ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣+ ለባአል መሥዋዕት በማቅረብ እኔን ያስከፉኝ የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በሠሩት ክፉ ነገር የተነሳ በአንቺ ላይ ጥፋት እንደሚመጣ አስታውቋል።”+

18 ይሖዋ ይህን እንዳውቅ ገለጠልኝ፤

አምላክ ሆይ፣ በዚያን ጊዜ የፈጸሙትን ነገር እንዳይ አደረግከኝ።

19 እኔ ለመታረድ እንደሚነዳ የዋህ የበግ ጠቦት ነበርኩ።

“ዛፉን ከነፍሬው እናጥፋው፤

ከእንግዲህም ወዲያ ስሙ እንዳይታወስ

ከሕያዋን ምድር እናስወግደው” ብለው

በእኔ ላይ ሴራ እንደጠነሰሱ አላወቅኩም ነበር።+

20 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ግን በጽድቅ ይፈርዳል፤

የውስጥ ሐሳብንና* ልብን ይመረምራል።+

አምላክ ሆይ፣ በእነሱ ላይ የምትወስደውን የበቀል እርምጃ እንዳይ አድርገኝ፤

ጉዳዬን ለአንተ አቅርቤአለሁና።

21 ስለዚህ ይሖዋ ሕይወትህን ለማጥፋት በሚሹ* በአናቶት+ ሰዎች ላይ ይህን ቃል ተናግሯል፤ እነሱ “በይሖዋ ስም ትንቢት አትናገር፤+ አለዚያ በእጃችን ትጠፋለህ” ይላሉ፤ 22 ስለዚህ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ እነሱን ተጠያቂ አደርጋለሁ። ወጣት ወንዶቹ በሰይፍ ይወድቃሉ፤+ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው በረሃብ ያልቃሉ።+ 23 እነሱን ተጠያቂ በማደርግበት ዓመት፣ በአናቶት+ ሰዎች ላይ ጥፋት ስለማመጣ ከእነሱ መካከል የሚተርፍ አንድም ሰው አይኖርም።”

12 ይሖዋ ሆይ፣ አቤቱታዬን ለአንተ ሳቀርብ፣

ከፍትሕ ጋር ስለተያያዙ ጉዳዮች ሳናግርህ እነሆ፣ አንተ ጻድቅ ነህ።+

ታዲያ የክፉዎች መንገድ ለምን ይሰምራል?+

ደግሞስ ከዳተኞች ሳይጨነቁ የሚኖሩት ለምንድን ነው?

 2 አንተ ተክለሃቸዋል፤ እነሱም ሥር ሰደዋል።

አድገዋል፤ ፍሬም አፍርተዋል።

ከከንፈራቸው አይለዩህም፤ የውስጥ ሐሳባቸው* ግን ከአንተ የራቀ ነው።+

 3 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን በሚገባ ታውቀኛለህ፤+ ታየኛለህም፤

ልቤን መረመርክ፤ ከአንተም ጋር የሚስማማ ሆኖ አገኘኸው።+

ለእርድ እንደተዘጋጁ በጎች ለያቸው፤

ለሚገደሉበትም ቀን ለይተህ አቆያቸው።

 4 ምድሪቱ ተራቁታ፣

የሜዳውም ተክል ሁሉ ደርቆ የሚቆየው እስከ መቼ ድረስ ነው?+

በምድሪቱ በሚኖሩት ሰዎች ክፋት የተነሳ

አራዊቱና ወፎቹ ተጠራርገው ጠፉ።

እነሱ፣ “ወደፊት ምን እንደሚገጥመን አያውቅም” ብለዋልና።

 5 ከእግረኞች ጋር ሮጠህ ከደከምክ፣

ከፈረሶች ጋር እንዴት ልትወዳደር ትችላለህ?+

በሰላም ምድር ተማምነህ ብትቀመጥ እንኳ

ጥቅጥቅ ባለው የዮርዳኖስ ጥሻ ውስጥ እንዴት ልትሆን ነው?

 6 የገዛ ወንድሞችህ፣

የገዛ አባትህ ቤተሰቦች እንኳ አታለውሃልና።+

እነሱ በአንተ ላይ ጮኸዋል።

መልካም ነገር ቢናገሩህ እንኳ

ፈጽሞ አትመናቸው።

 7 “ቤቴን ትቻለሁ፤+ ርስቴን ጥዬ ሄጃለሁ።+

እጅግ የምወዳትን* በጠላቶቿ እጅ አሳልፌ ሰጥቻታለሁ።+

 8 ርስቴ በጫካ ውስጥ እንዳለ አንበሳ ሆነችብኝ።

በእኔ ላይ ጮኻብኛለች።

በዚህም የተነሳ ጠላኋት።

 9 ርስቴ ለእኔ ብዙ ቀለማት እንዳለው* አዳኝ አሞራ ነች፤

ሌሎች አዳኝ አሞሮች ይከቧታል፤ ደግሞም ያጠቋታል።+

እናንተ የዱር አራዊት ሁሉ ኑ፤ በአንድነት ተሰብሰቡ፤

ትቀራመቷት ዘንድ ኑ።+

10 ብዙ እረኞች የወይን እርሻዬን አጥፍተውታል፤+

ይዞታዬንም ረግጠውታል።+

የተወደደውን ይዞታዬን ጠፍ ምድረ በዳ አድርገውታል።

11 ባድማ ሆኗል።

ደግሞም ተራቁቷል፤*

በፊቴ ወና ሆኗል።+

ምድሪቱ በሙሉ ባድማ ሆናለች፤

ይሁንና ይህን ልብ ያለ አንድም ሰው የለም።+

12 በምድረ በዳ ባሉት፣ በተበላሹ መንገዶች ሁሉ አጥፊዎች መጥተዋል፤

የይሖዋ ሰይፍ ከአንዱ ጫፍ እስከ ሌላኛው ጫፍ ድረስ ምድሪቱን ትበላለችና።+

ማንም ሰው* ሰላም የለውም።

13 ስንዴ ዘሩ፤ ሆኖም እሾህን አጨዱ።+

እስኪዝሉ ድረስ ሠሩ፤ ነገር ግን ምንም ጥቅም አላገኙም።

ከሚነደው የይሖዋ ቁጣ የተነሳ

በሚያገኙት ምርት ያፍራሉ።”

14 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ እስራኤል እንዲወርሰው ያደረግኩትን ርስት የሚነኩ ክፉ ጎረቤቶቼን ሁሉ+ ከምድራቸው እነቅላቸዋለሁ፤+ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅላለሁ። 15 ከነቀልኳቸው በኋላ ግን ዳግመኛ ምሕረት አደርግላቸዋለሁ፤ እያንዳንዳቸውን ወደየርስታቸው፣ እያንዳንዳቸውንም ወደየምድራቸው እመልሳቸዋለሁ።”

16 “ሕዝቤን በባአል እንዲምሉ እንዳስተማሩ ሁሉ እነሱም የሕዝቤን መንገድ በእርግጥ ቢማሩና ‘ሕያው ይሖዋን!’ ብለው በስሜ ቢምሉ በሕዝቤ መካከል ጸንተው ይኖራሉ። 17 ይሁንና ከእነዚህ ብሔራት መካከል የማይታዘዝ ቢኖር ያን ብሔር እነቅለዋለሁ፤ ነቅዬም አጠፋዋለሁ” ይላል ይሖዋ።+

13 ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ሂድና ከተልባ እግር የተሠራ ቀበቶ ግዛ፤ በወገብህም ላይ ታጠቀው፤ ሆኖም ፈጽሞ ውኃ አታስነካው።” 2 ስለዚህ ይሖዋ ባዘዘኝ መሠረት ቀበቶውን ገዝቼ ወገቤ ላይ ታጠቅኩት። 3 የይሖዋም ቃል ለሁለተኛ ጊዜ ወደ እኔ መጣ፦ 4 “የገዛኸውንና የታጠቅከውን ቀበቶ ይዘህ ተነስ፤ ወደ ኤፍራጥስም ሄደህ በቋጥኝ ስንጥቅ ውስጥ ደብቀው።” 5 ስለዚህ ይሖዋ ባዘዘኝ መሠረት ሄጄ በኤፍራጥስ አጠገብ ደበቅኩት።

6 ሆኖም ከብዙ ቀናት በኋላ ይሖዋ “ተነስ፤ ወደ ኤፍራጥስ ሄደህ፣ በዚያ እንድትደብቀው ያዘዝኩህን ቀበቶ አምጣ” አለኝ። 7 እኔም ወደ ኤፍራጥስ ሄጄ፣ ቀበቶውን ከደበቅኩበት ቦታ ቆፍሬ አወጣሁ፤ ቀበቶው ተበላሽቶና ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ሆኖ አገኘሁት።

8 ከዚያም የይሖዋ ቃል ወደ እኔ መጣ፦ 9 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የይሁዳን ኩራትና የኢየሩሳሌምን እብሪት ልክ እንደዚሁ አጠፋዋለሁ።+ 10 ቃሌን ለመታዘዝ አሻፈረኝ ያለው፣+ ግትር ሆኖ የገዛ ልቡን የሚከተለው+ እንዲሁም ሌሎች አማልክትን የሚከተለው፣ የሚያገለግለውና ለእነሱ የሚሰግደው ይህ ክፉ ሕዝብ ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ እንደሆነው እንደዚህ ቀበቶ ይሆናል።’ 11 ‘ቀበቶ በሰው ወገብ ላይ እንደሚጣበቅ፣ መላው የእስራኤል ቤትና መላው የይሁዳ ቤት ከእኔ ጋር እንዲጣበቅ አደረግኩ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘ይህም ሕዝቤ፣+ ስሜ፣+ ውዳሴዬና ውበቴ እንዲሆኑ ነው። እነሱ ግን አልታዘዙም።’+

12 “አንተም ይህን መልእክት አክለህ ንገራቸው፦ ‘የእስራኤል አምላክ ይሖዋ “እያንዳንዱ ትልቅ እንስራ በወይን ጠጅ ይሞላል” ይላል።’ እነሱም ‘እያንዳንዱ ትልቅ እንስራ በወይን ጠጅ እንደሚሞላ እኛ መች ጠፋን?’ ብለው ይመልሱልሃል። 13 በዚህ ጊዜ እንዲህ በላቸው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የምድሪቱን ነዋሪዎች በሙሉ፣ በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጡትን ነገሥታት፣ ካህናቱንና ነቢያቱን እንዲሁም የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች በሙሉ በስካር እሞላቸዋለሁ።+ 14 እነሱንም እርስ በርሳቸው፣ አባቶችንና ልጆችንም አጋጫለሁ” ይላል ይሖዋ።+ “ምንም ዓይነት ርኅራኄም ሆነ አዘኔታ አላሳይም፤ ምሕረትም አላደርግላቸውም፤ እነሱን ከማጥፋት ምንም ነገር አያግደኝም።”’+

15 ስሙ፤ ልብ በሉ።

ትዕቢተኞች አትሁኑ፤ ይሖዋ ተናግሯልና።

16 ጨለማን ከማምጣቱ በፊትና

ጨለምለም ባሉት ተራሮች ላይ እግሮቻችሁ ከመደናቀፋቸው በፊት

ለአምላካችሁ ለይሖዋ ክብር ስጡ።

እናንተ ብርሃንን ተስፋ ታደርጋላችሁ፤

እሱ ግን ፅልማሞትን ያመጣል፤

ወደ ድቅድቅ ጨለማም ይለውጠዋል።+

17 ለመስማት አሻፈረን ካላችሁ፣

በኩራታችሁ የተነሳ በስውር አለቅሳለሁ።*

የይሖዋ መንጋ+ በምርኮ ስለተወሰደ

እንባዬ እንደ ጎርፍ ይወርዳል፤ ዓይኔም በእንባ ይታጠባል።+

18 ንጉሡንና የንጉሡን እናት*+ እንዲህ በላቸው፦ ‘የሚያምረው አክሊላችሁ ከራሳችሁ ላይ ስለሚወድቅ፣

ዝቅ ባለ ስፍራ ተቀመጡ።’

19 የደቡብ ከተሞች ተዘግተዋል፤* የሚከፍታቸውም የለም።

መላው ይሁዳ በግዞት ተወስዷል፤ ሙሉ በሙሉም ተግዟል።+

20 ዓይንሽን አንስተሽ ከሰሜን የሚመጡትን ተመልከቺ።+

ለአንቺ የተሰጠው መንጋ፣ ያማሩት በጎችሽ የት አሉ?+

21 ከመጀመሪያው አንስቶ የተወዳጀሻቸው የቅርብ ጓደኞችሽ

አንቺን ለመቅጣት ሲነሱ ምን ትዪ ይሆን?+

ልክ እንደምትወልድ ሴት ምጥ አይዝሽም?+

22 በልብሽም ‘እነዚህ ነገሮች የደረሱብኝ ለምንድን ነው?’ በምትይበት ጊዜ፣+

ቀሚስሽን የተገፈፍሽውና+ ተረከዝሽ ለሥቃይ የተዳረገው

በፈጸምሽው ታላቅ በደል የተነሳ መሆኑን ልታውቂ ይገባል።

23 ኢትዮጵያዊ* መልኩን፣ ነብርስ ዥጉርጉርነቱን መለወጥ ይችላል?+

እንዲህ ማድረግ የሚችል ከሆነ፣

ክፉ ነገር መሥራት የለመዳችሁት እናንተም መልካም ማድረግ ትችላላችሁ ማለት ነው።

24 ስለዚህ የበረሃ ነፋስ ይዞት እንደሚሄድ ገለባ እበትናቸዋለሁ።+

25 ይህ ዕጣሽ፣ ሰፍሬም የሰጠሁሽ ድርሻሽ ነው” ይላል ይሖዋ፤

“ምክንያቱም እኔን ረስተሽኛል፤+ በሐሰትም ትታመኛለሽ።+

26 በመሆኑም ቀሚስሽን እስከ ፊትሽ እገልባለሁ፤

ኀፍረትሽም ይታያል፤+

27 የፈጸምሽው ምንዝር፣+ በፍትወት ማሽካካትሽ፣

ጸያፍ* የሆነው ዝሙት አዳሪነትሽ ይገለጣል።

አስጸያፊ ምግባርሽን

በኮረብቶቹና በሜዳው ላይ አይቼአለሁ።+

ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ወዮልሽ!

ርኩስ ሆነሽ የምትኖሪው እስከ መቼ ድረስ ነው?”+

14 ድርቅን አስመልክቶ ወደ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው፦+

 2 ይሁዳ ታለቅሳለች፤+ በሮቿም ወላልቀዋል።

በሐዘን ተውጠው መሬት ላይ ይቀመጣሉ፤

ከኢየሩሳሌምም ጩኸት ይሰማል።

 3 ጌቶቻቸውም አገልጋዮቻቸውን* ውኃ እንዲፈልጉ ላኳቸው።

እነሱም ወደ ውኃ ጉድጓዶቹ* ሄዱ፤ ውኃ ግን አላገኙም።

ባዶ ዕቃ ይዘው ተመለሱ።

በኀፍረት ተዋጡ፤ ተስፋም ቆረጡ፤

ራሳቸውንም ተከናነቡ።

 4 በምድሪቱ ላይ ዝናብ ባለመዝነቡ የተነሳ

መሬቱ ስለተሰነጣጠቀ+

ገበሬዎቹ እጅግ አዘኑ፤ ራሳቸውንም ተከናነቡ።

 5 በሜዳ ያለች እንስት ርኤም* እንኳ

ምንም ሣር ባለመኖሩ እንደወለደች ግልገሏን ጥላ ትሄዳለች።

 6 የዱር አህዮች በተራቆቱ ኮረብቶች ላይ ይቆማሉ።

እንደ ቀበሮ አየር አጥሯቸው ያለከልካሉ፤

ምንም ዓይነት ተክል ባለመኖሩ ዓይኖቻቸው ፈዘዙ።+

 7 ይሖዋ ሆይ፣ የገዛ ራሳችን በደል በእኛ ላይ የሚመሠክርብን ቢሆንም

ለስምህ ስትል እርምጃ ውሰድ።+

የክህደት ሥራችን በዝቷልና፤+

ኃጢአት የሠራነውም በአንተ ላይ ነው።

 8 አንተ የእስራኤል ተስፋ፣ በጭንቀትም ጊዜ አዳኙ+ የሆንክ ሆይ፣

በምድሪቱ እንደ እንግዳ፣

ሌሊቱን ለማሳለፍ ሲል ብቻ ጎራ እንዳለ መንገደኛ የሆንከው ለምንድን ነው?

 9 ክው ብሎ እንደቀረ ሰው፣

ማዳን እንደማይችል ኃያል ሰው የሆንከው ለምንድን ነው?

ይሖዋ ሆይ፣ አንተ በመካከላችን ነህና፤+

እኛም በስምህ ተጠርተናል።+

እባክህ አትተወን።

10 ይሖዋ ይህን ሕዝብ አስመልክቶ እንዲህ ይላል፦ “መቅበዝበዝ ይወዳሉ፤+ እግራቸውን አልሰበሰቡም።+ ስለዚህ ይሖዋ በእነሱ ደስ አይሰኝም።+ አሁን በደላቸውን ያስባል፤ በኃጢአታቸውም የተነሳ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል።”+

11 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ይህ ሕዝብ መልካም ሁኔታ እንዲገጥመው አትጸልይ።+ 12 በሚጾሙበት ጊዜ የሚያቀርቡትን ልመና አልሰማም፤+ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችና የእህል መባዎች በሚያቀርቡበት ጊዜም በእነሱ ደስ አልሰኝም፤+ በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር* አጠፋቸዋለሁና።”+

13 በዚህ ጊዜ እንዲህ አልኩ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ወዮ! እነሆ፣ ነቢያቱ ‘ሰይፍ አታዩም፤ ለረሃብም አትዳረጉም፤ ከዚህ ይልቅ በዚህ ስፍራ እውነተኛ ሰላም እሰጣችኋለሁ’ ይሏቸዋል።”+

14 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ነቢያቱ በስሜ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ።+ እኔ አልላክኋቸውም፤ አላዘዝኳቸውም ወይም አላናገርኳቸውም።+ የሐሰት ራእይን፣ ከንቱ የሆነ ሟርትንና የገዛ ልባቸውን ማታለያ ይተነብዩላችኋል።+ 15 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እኔ ሳልካቸው በስሜ የሚተነብዩትና በዚህች ምድር ላይ ሰይፍም ሆነ ረሃብ አይከሰትም የሚሉት እነዚህ ነቢያት በሰይፍና በረሃብ ይጠፋሉ።+ 16 የሚተነብዩለትም ሕዝብ ከረሃቡና ከሰይፉ የተነሳ አስከሬኑ በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ ይጣላል፤ እነሱን፣ አዎ እነሱን፣ ሚስቶቻቸውን፣ ወንዶች ልጆቻቸውንም ሆነ ሴቶች ልጆቻቸውን የሚቀብራቸው አይኖርም፤+ የሚገባቸውን ጥፋት በላያቸው ላይ አመጣለሁና።’+

17 “ይህን ቃል ንገራቸው፦

‘ዓይኖቼ ሌት ተቀን ሳያቋርጡ እንባ ያፍስሱ፤+

ድንግሊቱ የሕዝቤ ሴት ልጅ እጅግ አስከፊ በሆነ ቁስል ሙሉ በሙሉ ደቃለችና፤

ደግሞም ተሰብራለች።+

18 ወደ መስክ ብወጣ፣

እነሆ፣ በሰይፍ የተገደሉትን አያለሁ!+

ወደ ከተማም ብገባ፣

በረሃብ የተነሳ የታመሙ ሰዎችን አያለሁ!+

ነቢዩና ካህኑ በማያውቁት አገር ተቅበዝብዘዋልና።’”+

19 ይሁዳን ጨርሶ ትተኸዋል? ወይስ ጽዮንን ተጸይፈሃታል?*+

ታዲያ ፈውስ እስከማይገኝልን ድረስ የመታኸን ለምንድን ነው?+

ሰላምን ተስፋ አደረግን፤ ሆኖም መልካም ነገር አልመጣም፤

የፈውስ ጊዜ ይመጣል ብለን ጠበቅን፤ ነገር ግን ሽብር ነገሠ!+

20 ይሖዋ ሆይ፣ ክፋት መሥራታችንን፣

አባቶቻችንም በደል መፈጸማቸውን አምነን እንቀበላለን፤

በአንተ ላይ ኃጢአት ሠርተናልና።+

21 ስለ ስምህ ስትል አትናቀን፤+

ክብር የተላበሰውን ዙፋንህን አታቃልል።

ከእኛ ጋር የገባኸውን ቃል ኪዳን አስታውስ፤ አታፍርሰውም።+

22 ከንቱ ከሆኑት የአሕዛብ ጣዖቶች መካከል ዝናብ ሊያዘንብ የሚችል አለ?

ሰማያትስ በራሳቸው ዝናብ ማውረድ ይችላሉ?

አምላካችን ይሖዋ ሆይ፣ ይህን የምታደርገው አንተ ብቻ አይደለህም?+

እነዚህን ሁሉ ነገሮች ያደረግከው አንተ ብቻ ስለሆንክ

አንተን ተስፋ እናደርጋለን።

15 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙ እንኳ+ ለዚህ ሕዝብ አልራራም።* ከፊቴ አስወጣቸው። ይሂዱ። 2 እነሱም ‘ወዴት እንሂድ?’ ቢሉህ፣ እንዲህ በላቸው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“ገዳይ መቅሰፍት የሚገባው ሁሉ በመቅሰፍት እንዲሞት ይሂድ፤

ሰይፍ የሚገባው ሁሉ በሰይፍ ይሙት፤+

ረሃብ የሚገባው ሁሉ በረሃብ ይሙት፤

በምርኮ መወሰድ የሚገባው ሁሉ ደግሞ ተማርኮ ይወሰድ!”’+

3 “‘እኔም አራት ዓይነት ጥፋት* አዝባቸዋለሁ’+ ይላል ይሖዋ፤ ‘እነሱም፦ ለመግደል ሰይፍ፣ ጎትቶ ለመውሰድ ውሾች እንዲሁም ለመሰልቀጥና ለማጥፋት የሰማይ ወፎችና የምድር አራዊት ናቸው።+ 4 የይሁዳ ንጉሥ፣ የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ በኢየሩሳሌም ከፈጸመው ድርጊት የተነሳ+ ለምድር መንግሥታት ሁሉ መቀጣጫ እንዲሆኑ አደርጋቸዋለሁ።+

 5 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ማን ይራራልሻል?

ማንስ ያዝንልሻል?

ደህንነትሽንስ ማን ጎራ ብሎ ይጠይቃል?’

 6 ‘ትተሽኛል’ ይላል ይሖዋ።+

‘አሁንም ጀርባሽን ሰጥተሽኛል።*+

ስለዚህ እጄን በአንቺ ላይ ዘርግቼ አጠፋሻለሁ።+

ለአንቺ አዘኔታ ማሳየት* ታክቶኛል።

 7 በምድሪቱ በሮች፣ በመንሽ እበትናቸዋለሁ።

የወላድ መሃን አደርጋቸዋለሁ።+

ሕዝቤን አጠፋዋለሁ፤

ከመንገዱ ለመመለስ አሻፈረኝ ብሏልና።+

 8 መበለቶቻቸው በፊቴ ከባሕር አሸዋ ይልቅ ይበዛሉ።

በእነሱ ይኸውም በእናቶችና በወጣት ወንዶች ላይ በቀትር አጥፊ አመጣለሁ።

ከባድ ጭንቀትና ሽብር በድንገት አመጣባቸዋለሁ።

 9 ሰባት ልጆች የወለደችው ሴት ተዝለፍልፋለች፤

ትንፋሽ አጥሯት* ታጣጥራለች።

ገና ቀን ሳለ ፀሐይዋ ጠልቃለች፤

ይህም ኀፍረትና ውርደት አስከትሎባታል።’*

‘ከእነሱ መካከል የተረፉትንም ጥቂት ሰዎች

በጠላቶቻቸው ፊት ለሰይፍ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ’ ይላል ይሖዋ።”+

10 እናቴ ሆይ፣ ወዮልኝ!

በምድሪቱ ሁሉ ላይ የጠብና የጭቅጭቅ መንስኤ የሆንኩትን እኔን ወልደሻልና።+

እኔ ለማንም አላበደርኩም፤ ከማንም አልተበደርኩም፤

ይሁንና ሁሉም ይረግሙኛል።

11 ይሖዋ እንዲህ ብሏል፦ “እኔ በእርግጥ ለአንተ መልካም ነገር አደርግልሃለሁ፤

በጥፋትና በጭንቀት ጊዜ

በአንተና በጠላት መካከል ጣልቃ ገብቼ እረዳሃለሁ።

12 ሰው ብረትን ይኸውም ከሰሜን የመጣን ብረትና

መዳብን መሰባበር ይችላል?

13 በመላው ክልልህ ከፈጸምከው ኃጢአት ሁሉ የተነሳ

ንብረትህንና ውድ ሀብትህን፣ ያለዋጋ ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጣለሁ።+

14 እነዚህን ነገሮች ጠላቶችህ ወደማታውቀው አገር እንዲወስዷቸው

አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።+

ቁጣዬ እሳት አስነስቷልና፤

በእናንተም ላይ እየነደደ ነው።”+

15 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ታውቃለህ፤

አስበኝ፤ ትኩረትህንም ወደ እኔ አዙር።

አሳዳጆቼን ተበቀልልኝ።+

ቁጣህን በማዘግየት እንድጠፋ አታድርግ።*

ይህን ነቀፋ የተሸከምኩት ለአንተ ስል እንደሆነ እወቅ።+

16 ቃልህ ተገኝቷል፤ እኔም በልቼዋለሁ፤+

የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ በስምህ ተጠርቻለሁና፣

ቃልህ ሐሴት፣ ለልቤም ደስታ ሆነልኝ።

17 ፈንጠዝያ ከሚወዱ ሰዎች ጋር አልተቀመጥኩም፤ ከእነሱም ጋር ሐሴት አላደረግኩም።+

እጅህ በእኔ ላይ ስለሆነ ብቻዬን እቀመጣለሁ፤

በቁጣ* ሞልተኸኛልና።+

18 ሕመሜ ሥር የሰደደው፣ ቁስሌም የማይፈወስ የሆነው ለምንድን ነው?

ጨርሶ አልድን ብሏል።

እምነት ሊጣልበት እንደማይችል

የሚያታልል የውኃ ምንጭ ትሆንብኛለህ?

19 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“ብትመለስ፣ እኔም ወደ ቀድሞው ሁኔታህ እመልስሃለሁ፤

በፊቴም ትቆማለህ።

ውድ የሆነውን ነገር ከማይረባው ነገር ብትለይ፣

እንደ አፌ* ትሆናለህ።

እነሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ እንጂ

አንተ ወደ እነሱ አትመለስም።”

20 “ለዚህ ሕዝብ ጠንካራ የመዳብ ቅጥር አደርግሃለሁ።+

እነሱ በእርግጥ ይዋጉሃል፤

ሆኖም በአንተ ላይ አያይሉም፤*+

እኔ አንተን ለማዳንና ለመታደግ ከአንተ ጋር ነኝና” ይላል ይሖዋ።

21 “ከክፉዎች እጅ እታደግሃለሁ፤

ከጨካኞችም መዳፍ እቤዥሃለሁ።”

16 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “በዚህ ስፍራ ሚስት አታግባ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም አትውለድ። 3 ይሖዋ በዚህ ስለሚወለዱ ወንዶችና ሴቶች ልጆች እንዲሁም በዚህች ምድር ስለሚወልዷቸው እናቶችና አባቶች እንዲህ ይላልና፦ 4 ‘በገዳይ በሽታዎች ይሞታሉ፤+ ይሁንና ማንም አያለቅስላቸውም ወይም አይቀብራቸውም፤ በምድር ላይ እንደ ፍግ ይሆናሉ።+ በሰይፍና በረሃብ ይጠፋሉ፤+ አስከሬናቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።’

 5 ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦

‘ለለቀስተኞች ድግስ ወደተዘጋጀበት ቤት አትግባ፤

እዚያም ሄደህ አታልቅስ ወይም አታስተዛዝን።’+

‘ሰላሜን ከዚህ ሕዝብ ወስጄአለሁና’ ይላል ይሖዋ፤

‘ታማኝ ፍቅሬና ምሕረቴ ከእነሱ እንዲርቅ አድርጌአለሁ።+

 6 ታላላቆችም ሆኑ ታናናሾች በዚህች ምድር ላይ ይሞታሉ።

ደግሞም አይቀበሩም፤

ማንም ሰው አያዝንላቸውም፤

ለእነሱ ሲል ሰውነቱን የሚተለትልም ሆነ ራሱን የሚላጭ አይኖርም።*

 7 ሰው የሞተባቸውንም ለማጽናናት

የእዝን እንጀራ የሚወስድላቸው አይኖርም፤

አባት ወይም እናት ለሞተባቸውም

የመጽናኛ ጽዋ እንዲጠጡ የሚሰጣቸው አይኖርም።

 8 ከእነሱ ጋር ተቀምጠህ ለመብላትና ለመጠጣት

ግብዣ ወደተዘጋጀበት ቤት አትግባ።’

9 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘በዚህ ስፍራ፣ በእናንተ ዘመን ዓይናችሁ እያየ የሐሴትንና የደስታን ድምፅ እንዲሁም የሙሽራንና የሙሽሪትን ድምፅ አስወግዳለሁ።’+

10 “ይህን ሁሉ ቃል ለዚህ ሕዝብ በምትነግርበት ጊዜ እንዲህ ብለው ይጠይቁሃል፦ ‘ይሖዋ ይህን ሁሉ ታላቅ ጥፋት በእኛ ላይ የተናገረው ለምንድን ነው? በአምላካችን በይሖዋ ላይ የፈጸምነው በደልና ኃጢአት ምንድን ነው?’+ 11 አንተም እንዲህ ብለህ ትመልስላቸዋለህ፦ ‘“አባቶቻችሁ እኔን ስለተዉ ነው”+ ይላል ይሖዋ፤ “ደግሞም ሌሎች አማልክትን ስለተከተሉና ስላገለገሉ እንዲሁም ስለሰገዱላቸው ነው።+ እኔን ግን ትተውኛል፤ ሕጌንም አልጠበቁም።+ 12 እናንተ ደግሞ አባቶቻችሁ ከፈጸሙት የባሰ ነገር አድርጋችኋል፤+ እያንዳንዳችሁም እኔን ከመታዘዝ ይልቅ ግትር የሆነውን ክፉ ልባችሁን ተከተላችሁ።+ 13 ስለዚህ ከዚህች ምድር አስወጥቼ እናንተም ሆነ አባቶቻችሁ ወደማታውቁት ምድር እጥላችኋለሁ፤+ በዚያም ሌሎች አማልክትን ቀን ከሌት ታገለግላላችሁ፤+ ምክንያቱም እኔ ምንም ምሕረት አላሳያችሁም።”’

14 “‘ይሁን እንጂ ከዚህ በኋላ “የእስራኤልን ሕዝብ ከግብፅ ምድር ባወጣው ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ” የማይሉበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ፤+ 15 ‘ከዚህ ይልቅ “እስራኤላውያንን ከሰሜን ምድርና እነሱን ከበተነባቸው አገሮች ሁሉ ሰብስቦ ባመጣቸው ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ” ይባላል፤ እኔም ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት፣ ወደ ምድራቸው እመልሳቸዋለሁ።’+

16 ‘እነሆ፣ እኔ ብዙ ዓሣ አጥማጆችን እሰዳለሁ’ ይላል ይሖዋ፤

‘እነሱንም ያጠምዷቸዋል።

ከዚያም በኋላ ብዙ አዳኞችን እሰዳለሁ፤

እነሱም ከየተራራው፣ ከየኮረብታውና

ከየቋጥኙ ስንጣቂ አድነው ይይዟቸዋል።

17 ዓይኖቼ በሚያደርጉት ነገር ሁሉ* ላይ ነውና።

ከፊቴ አልተሸሸጉም፤

በደላቸውም ከዓይኔ አልተሰወረም።

18 በመጀመሪያ፣ ለሠሩት በደልና ኃጢአት የሚገባቸውን ሙሉ ዋጋ እከፍላቸዋለሁ፤+

ምድሬን አስጸያፊ በሆኑ ጣዖቶቻቸው በድን ምስሎች* አርክሰዋልና፤

ርስቴንም አስነዋሪ በሆኑ ነገሮች ሞልተዋል።’”+

19 ብርታቴና መጠጊያዬ፣

በጭንቀት ጊዜ መሸሸጊያዬ የሆንከው ይሖዋ ሆይ፣+

ብሔራት ከምድር ዳርቻዎች ወደ አንተ ይመጣሉ፤

እንዲህም ይላሉ፦ “አባቶቻችን ፍጹም ውሸትን፣

ከንቱ የሆኑና ምንም ጥቅም የሌላቸውን የማይረቡ ነገሮች ወርሰዋል።”+

20 ሰው ለራሱ አማልክት ሊሠራ ይችላል?

የሚሠራቸው አማልክት እውነተኛ አማልክት አይደሉም።+

21 “ስለዚህ አስተምራቸዋለሁ፤

በዚህ ጊዜ ኃይሌንና ብርታቴን እንዲያውቁ አደርጋለሁ፤

እነሱም ስሜ ይሖዋ መሆኑን ያውቃሉ።”

17 “የይሁዳ ኃጢአት በብረት ብዕር ተጽፏል።

በሾለ የአልማዝ ጫፍ በልባቸው ጽላትና

በመሠዊያዎቻቸው ቀንዶች ላይ ተቀርጿል፤

 2 ያን ጊዜ ወንዶች ልጆቻቸው ከፍ ባሉ ኮረብቶች ላይ ቅጠሉ በተንዠረገገ ዛፍ አጠገብ ያሉትን+

መሠዊያዎቻቸውንና የማምለኪያ ግንዶቻቸውን* ያስታውሳሉ፤+

 3 በአውላላ ሜዳ ላይ ባሉት ተራሮች ላይ ያሉትንም ያስባሉ።

ንብረትህን ይኸውም ውድ ሀብትህን ሁሉ ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጣለሁ፤+

አዎ፣ በመላው ክልልህ ካለው ኃጢአት የተነሳ ከፍ ያሉ ቦታዎችህ እንዲበዘበዙ አደርጋለሁ።+

 4 የሰጠሁህን ርስት በገዛ ፈቃድህ አሳልፈህ ትሰጣለህ።+

በማታውቀውም ምድር ጠላቶችህን እንድታገለግል አደርግሃለሁ፤+

ቁጣዬን እንደ እሳት አቀጣጥለሃልና።*+

እሳቱም ለዘላለም ይነዳል።”

 5 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“በሰዎች የሚታመን፣+

በሰብዓዊ ኃይል የሚመካና*+

ልቡ ከይሖዋ የራቀ ሰው* የተረገመ ነው።

 6 በበረሃ ብቻውን እንዳለ ዛፍ ይሆናል።

መልካም ነገር ሲመጣ አያይም፤

ይልቁንም በምድረ በዳ ደረቅ በሆኑ ስፍራዎች፣

ማንም መኖር በማይችልበት የጨው ምድር ይኖራል።

 7 በይሖዋ የሚታመን፣

መመኪያውም ይሖዋ የሆነ ሰው* የተባረከ ነው።+

 8 በውኃዎች አጠገብ እንደተተከለ፣

ሥሮቹን ወደ ጅረት እንደሚሰድ ዛፍ ይሆናል።

ሙቀት ሲመጣ አያስተውልም፤

ከዚህ ይልቅ ቅጠሉ ሁልጊዜ ይለመልማል።+

ድርቅ በሚከሰትበት ዓመትም ምንም አይጨነቅም፤

ፍሬ ማፍራቱንም አያቋርጥም።

 9 ልብ ከምንም ነገር በላይ ከዳተኛ* ነው፤ ማንኛውንም ነገር ከማድረግ አይመለስም።*+

ማንስ ሊያውቀው ይችላል?

10 እኔ ይሖዋ፣ ለእያንዳንዱ እንደ መንገዱ፣

እንደ ሥራውም ፍሬ ለመስጠት

ልብን እመረምራለሁ፤+

የውስጥ ሐሳብንም* እፈትናለሁ።+

11 በማጭበርበር* ሀብት የሚያከማች ሰው፣

ያልጣለችውን እንቁላል እንደምትሰበስብ ቆቅ ነው።+

በዕድሜው አጋማሽ ላይ ሀብቱ ትቶት ይሄዳል፤

በመጨረሻም የማመዛዘን ችሎታ የጎደለው ሰው መሆኑ ይረጋገጣል።”

12 ከመጀመሪያ አንስቶ ክብራማ የሆነ ዙፋን ከፍ ከፍ ብሏል፤

እሱም መቅደሳችን ነው።+

13 የእስራኤል ተስፋ የሆንከው ይሖዋ ሆይ፣

አንተን የሚተዉ ሁሉ ያፍራሉ።

አንተን* የሚክዱ ስማቸው በአፈር ላይ ይጻፋል፤+

ምክንያቱም የሕያው ውኃ ምንጭ የሆነውን ይሖዋን ትተዋል።+

14 ይሖዋ ሆይ፣ ፈውሰኝ፤ እኔም እፈወሳለሁ።

አድነኝ፤ እኔም እድናለሁ፤+

የማወድሰው አንተን ነውና።

15 እነሆ፣ “የይሖዋ ቃል የት አለ?+

እስቲ ይፈጸም!”

የሚሉኝ ሰዎች አሉ።

16 እኔ ግን እረኛ ሆኜ አንተን ከመከተል ወደኋላ አላልኩም፤

የጥፋትንም ቀን ፈጽሞ አልተመኘሁም።

አንተ ከንፈሮቼ የተናገሩትን ሁሉ በሚገባ ታውቃለህ፤

ሁሉም የተፈጸመው በፊትህ ነው!

17 ሽብር ላይ አትጣለኝ።

አንተ በጥፋት ቀን መጠጊያዬ ነህ።

18 አሳዳጆቼ ኀፍረት ይከናነቡ፤+

እኔ ግን ለኀፍረት እንድዳረግ አትፍቀድ።

እነሱ በሽብር ይዋጡ፤

እኔ ግን አልሸበር።

የጥፋት ቀን አምጣባቸው፤+

አድቅቃቸው፤ ሙሉ በሙሉም አጥፋቸው።*

19 ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ሂድና የይሁዳ ነገሥታት በሚገቡበትና በሚወጡበት በሕዝቡ ልጆች በር እንዲሁም በኢየሩሳሌም በሮች ሁሉ ቁም።+ 20 እንዲህም በላቸው፦ ‘በእነዚህ በሮች የምትገቡ፣ እናንተ የይሁዳ ነገሥታት፣ የይሁዳ ሕዝብ ሁሉና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች በሙሉ የይሖዋን ቃል ስሙ። 21 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ለራሳችሁ* ተጠንቀቁ፤ በሰንበት ቀን ምንም ዓይነት ሸክም አትሸከሙ ወይም በኢየሩሳሌም በሮች አታስገቡ።+ 22 በሰንበት ቀን ምንም ዓይነት ሸክም ከቤታችሁ ይዛችሁ አትውጡ፤ ምንም ዓይነት ሥራም አትሥሩ።+ አባቶቻችሁን እንዳዘዝኳቸው ሁሉ እናንተም የሰንበትን ቀን ቀድሱ።+ 23 ሆኖም እነሱ አልሰሙም፤ ጆሯቸውንም አልሰጡም፤ ላለመታዘዝና ተግሣጽ ላለመቀበል በእንቢተኝነታቸው ጸኑ።”’*+

24 “‘“ይሁን እንጂ በሚገባ ብትታዘዙኝ” ይላል ይሖዋ፣ “በሰንበትም ቀን በከተማዋ በሮች ሸክም ይዛችሁ ባትገቡና በሰንበት ቀን ምንም ዓይነት ሥራ ባለመሥራት ቀኑን ብትቀድሱት፣+ 25 በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጡ ነገሥታትና መኳንንት+ ይኸውም እነሱና መኳንንታቸው እንዲሁም የይሁዳ ሰዎችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች በሠረገሎችና በፈረሶች ላይ ተቀምጠው በዚህች ከተማ በሮች ይገባሉ፤+ ይህችም ከተማ ለዘለቄታው የሰው መኖሪያ ትሆናለች። 26 ሰዎችም ከይሁዳ ከተሞች፣ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ከሚገኙ ቦታዎች፣ ከቢንያም አገር፣+ ከቆላው፣+ ከተራራማው አካባቢና ከኔጌብ* ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎች፣+ መሥዋዕቶች፣+ የእህል መባዎች፣+ ነጭ ዕጣንና የምስጋና መሥዋዕቶች ይዘው ወደ ይሖዋ ቤት ይመጣሉ።+

27 “‘“የሰንበትን ቀን ሳትቀድሱ፣ በሰንበት ቀን ሸክም ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች በመግባት ትእዛዜን ብትጥሱ፣ በሮቿን በእሳት አነዳለሁ፤ እሳቱም የኢየሩሳሌምን የማይደፈሩ ማማዎች ይበላል፤+ ፈጽሞም አይጠፋም።”’”+

18 ከይሖዋ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፦ 2 “ተነሥተህ ወደ ሸክላ ሠሪው ቤት ውረድ፤+ እኔም በዚያ ቃሌን አሰማሃለሁ።”

3 ስለዚህ ወደ ሸክላ ሠሪው ቤት ወረድኩ፤ እሱም በሸክላ መዘውሮቹ ላይ እየሠራ ነበር። 4 ሆኖም ሸክላ ሠሪው በጭቃ እየሠራ የነበረው ዕቃ እጁ ላይ ተበላሸ። በመሆኑም ሸክላ ሠሪው ተስማሚ ሆኖ ባገኘው መንገድ* መልሶ ሌላ ዕቃ አድርጎ ሠራው።

5 ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 6 “‘የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ይህ ሸክላ ሠሪ እንዳደረገው እኔም በእናንተ ላይ ማድረግ አልችልም?’ ይላል ይሖዋ። ‘የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እነሆ፣ በሸክላ ሠሪ እጅ እንዳለ ጭቃ፣ እናንተም በእኔ እጅ እንዲሁ ናችሁ።+ 7 አንድን ብሔር ወይም አንድን መንግሥት እንደምነቅል፣ እንደማፈርስና እንደማጠፋ በተናገርኩ ጊዜ፣+ 8 ያ ብሔር እኔ ያወገዝኩትን ክፉ ነገር ቢተው፣ ሐሳቤን ለውጬ በእሱ ላይ ላመጣው ያሰብኩትን ጥፋት እተወዋለሁ።*+ 9 ሆኖም አንድን ብሔር ወይም አንድን መንግሥት እንደምገነባውና እንደምተክለው በተናገርኩ ጊዜ፣ 10 በፊቴ ክፉ የሆነውን ነገር ቢያደርግና ድምፄን ባይሰማ እኔም ሐሳቤን ለውጬ ለእሱ አደርገዋለሁ ብዬ ያሰብኩትን መልካም ነገር እተወዋለሁ።’*

11 “አሁንም ለይሁዳ ሰዎችና ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እባክህ እንዲህ በላቸው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በእናንተ ላይ ጥፋት ለማምጣት እየተዘጋጀሁ ነው፤* በእናንተም ላይ ክፉ ነገር እየጠነሰስኩ ነው። እባካችሁ፣ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ መንገዳችሁንና ተግባራችሁንም አስተካክሉ።”’”+

12 እነሱ ግን እንዲህ አሉ፦ “ይህ ያበቃለት ጉዳይ ነው!+ እኛ እንደሆነ በራሳችን ሐሳብ እንሄዳለን፤ እያንዳንዳችንም ግትር የሆነውን ክፉ ልባችንን እንከተላለን።”+

13 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“እስቲ ራሳችሁ ብሔራትን ጠይቁ።

እንዲህ ያለ ነገር ማን ሰምቷል?

የእስራኤል ድንግል እጅግ የሚሰቀጥጥ ነገር አድርጋለች።+

14 የሊባኖስ ዓለታማ ተረተር በረዶ ተለይቶት ያውቃል?

ወይስ ከሩቅ ስፍራ የሚፈስሱት ቀዝቃዛ ውኃዎች ይደርቃሉ?

15 ሕዝቤ ግን እኔን ረስቶኛል።+

ለማይረባ ነገር መሥዋዕት ያቀርባሉና፤+

ሰዎችም በመንገዳቸው፣ በጥንቶቹ ጎዳናዎች እንዲሰናከሉ+

ደግሞም ባልተስተካከሉና ባልተደለደሉ* ተለዋጭ መንገዶች እንዲሄዱ ያደርጋሉ፤

16 ስለዚህ ምድራቸው አስፈሪ ቦታ፣+

ለዘላለምም ማፏጫ ትሆናለች።+

በዚያ የሚያልፍ ሁሉ በፍርሃት አፍጥጦ ይመለከታል፤ ራሱንም ይነቀንቃል።+

17 እንደ ምሥራቅ ነፋስ በጠላት ፊት እበትናቸዋለሁ።

በሚጠፉበት ቀን ጀርባዬን እንጂ ፊቴን አላሳያቸውም።”+

18 እነሱም እንዲህ አሉ፦ “ኑ፣ በኤርምያስ ላይ እናሲር፤+ ሕጉ* ከካህናት፣ ምክር ከጠቢባን ወይም ቃሉ ከነቢያት አይጠፋምና። ኑና በአንደበታችን እናጥቃው፤* የሚናገረውንም ቃል አንስማ።”

19 ይሖዋ ሆይ፣ ትኩረትህን ወደ እኔ አድርግ፤

ተቃዋሚዎቼ የሚናገሩትንም ስማ።

20 ስለ መልካም ነገር ክፉ መመለስ አግባብ ነው?

እነሱ ጉድጓድ ቆፍረውልኛልና።*+

ቁጣህ ከእነሱ እንዲመለስ፣ ስለ እነሱ መልካም ነገር ለመናገር

ምን ያህል ጊዜ በፊትህ እንደቆምኩ አስብ።

21 ስለዚህ ወንዶች ልጆቻቸውን ለረሃብ ዳርጋቸው፤

ለሰይፍ ኃይል አሳልፈህ ስጣቸው።+

ሚስቶቻቸው የወላድ መሃንና መበለት ይሁኑ።+

ወንዶቻቸው በገዳይ መቅሰፍት ይሙቱ፤

ወጣቶቻቸው በጦር ሜዳ በሰይፍ ተመተው ይውደቁ።+

22 በድንገት ወራሪዎችን ስታመጣባቸው

ከየቤታቸው ጩኸት ይሰማ።

እኔን ለመያዝ ጉድጓድ ቆፍረዋልና፤

ለእግሮቼም ወጥመድ ዘርግተዋል።+

23 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን

እኔን ለመግደል የጠነሰሱትን ሴራ ሁሉ በሚገባ ታውቃለህ።+

በደላቸውን አትሸፍን፤

ኃጢአታቸውንም ከፊትህ አትደምስስ።

በቁጣ ተነሳስተህ እርምጃ ስትወስድባቸው+

በፊትህ ይሰናከሉ።+

19 ይሖዋ እንዲህ ብሏል፦ “ሄደህ፣ ከሸክላ ሠሪ ገንቦ ግዛ።+ ከሕዝቡ ሽማግሌዎችና ከካህናቱ ሽማግሌዎች መካከል የተወሰኑትን ይዘህ 2 በገል በር መግቢያ አጠገብ ወዳለው ወደ ሂኖም ልጅ ሸለቆ+ ውጣ። የምነግርህንም ቃል በዚያ አውጅ። 3 እንዲህ ትላለህ፦ ‘እናንተ የይሁዳ ነገሥታትና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች የይሖዋን ቃል ስሙ። የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“‘“በዚህ ስፍራ ላይ ጥፋት ላመጣ ነው፤ ስለሚመጣው ጥፋት የሚሰማ ሰው ሁሉ ጆሮውን ይነዝረዋል። 4 ምክንያቱም እኔን ትተውኛል፤+ ይህን ስፍራም የማይታወቅ ቦታ አድርገውታል።+ በዚህ ስፍራ እነሱም ሆኑ አባቶቻቸው እንዲሁም የይሁዳ ነገሥታት ለማያውቋቸው ሌሎች አማልክት መሥዋዕት ያቀርባሉ፤ ይህን ስፍራም በንጹሐን ደም ሞልተውታል።+ 5 እኔ ያላዘዝኩትን ወይም ያልተናገርኩትን፣ በልቤም እንኳ ፈጽሞ ያላሰብኩትን* ነገር ለማድረግ ይኸውም ወንዶች ልጆቻቸውን ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ አድርገው ለባአል በእሳት ለማቃጠል ከፍ ያሉትን የባአል የማምለኪያ ቦታዎች ሠሩ።”’+

6 “‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ስለዚህ፣ እነሆ ይህ ስፍራ የእርድ ሸለቆ እንጂ ቶፌት ወይም የሂኖም ልጅ ሸለቆ ተብሎ የማይጠራበት ጊዜ ይመጣል።+ 7 በዚህ ስፍራ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ዕቅድ አጨናግፋለሁ፤ በጠላቶቻቸው ፊት በሰይፍ እንዲወድቁ፣ ሕይወታቸውንም* በሚሹ ሰዎች እጅ እንዲጠፉ አደርጋለሁ። አስከሬናቸውንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል እንዲሆን እሰጣለሁ።+ 8 ይህችንም ከተማ አስፈሪ ቦታና ማፏጫ አደርጋታለሁ። በዚያ የሚያልፍ ሁሉ በደረሰባት መቅሰፍት የተነሳ በፍርሃት አፍጥጦ ይመለከታል፤ ደግሞም ያፏጫል።+ 9 ጠላቶቻቸውና ሕይወታቸውን ለማጥፋት የሚሹ* ሰዎች ሲከቧቸውና መፈናፈኛ አሳጥተው ሲያስጨንቋቸው የወንዶችና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ እንዲበሉ አደርጋቸዋለሁ፤ እያንዳንዳቸው የባልንጀሮቻቸውን ሥጋ ይበላሉ።”’+

10 “ከዚያም ገንቦውን ከአንተ ጋር በሚሄዱ ሰዎች ፊት ስበረው፤ 11 እንዲህም በላቸው፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አንድ ሰው የሸክላ ሠሪን ዕቃ ሊጠገን በማይችል መንገድ እንደሚሰብረው፣ እኔም ይህን ሕዝብና ይህችን ከተማ እንዲሁ እሰባብራለሁ፤ እነሱም የመቃብር ቦታ እስኪታጣ ድረስ የሞቱትን በቶፌት ይቀብራሉ።”’+

12 “‘ይህችን ከተማ እንደ ቶፌት አደርጋት ዘንድ በዚህ ስፍራና በነዋሪዎቹ ላይ ይህን እፈጽማለሁ’ ይላል ይሖዋ። 13 ‘የኢየሩሳሌም ቤቶችና የይሁዳ ነገሥታት ቤቶች፣ አዎ በጣሪያዎቻቸው ላይ ለሰማያት ሠራዊት መሥዋዕቶች ያቀረቡባቸውና+ ለሌሎች አማልክት የመጠጥ መባዎች ያፈሰሱባቸው ቤቶች ሁሉ+ እንደዚህ ስፍራ፣ እንደ ቶፌት የረከሱ ይሆናሉ።’”+

14 ኤርምያስ፣ ይሖዋ ትንቢት እንዲናገር ልኮት ከነበረበት ከቶፌት ሲመለስ በይሖዋ ቤት ግቢ ቆሞ ለመላው ሕዝብ እንዲህ አለ፦ 15 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ በዚህች ከተማና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች ሁሉ ላይ አመጣዋለሁ ብዬ የተናገርኩትን ጥፋት ሁሉ አወርድባቸዋለሁ፤ ምክንያቱም ቃሌን ለመታዘዝ በግትርነት አሻፈረን ብለዋል።’”*+

20 በይሖዋ ቤት ዋና ሹም የነበረው የኢሜር ልጅ ካህኑ ጳስኮር፣ ኤርምያስ እነዚህን ነገሮች ሲተነብይ ሰማ። 2 ጳስኮርም ነቢዩ ኤርምያስን መታው፤ ከዚያም በይሖዋ ቤት ባለው በላይኛው የቢንያም በር በእግር ግንድ ጠረቀው።+ 3 ይሁንና በማግስቱ ጳስኮር ኤርምያስን ከእግር ግንዱ ውስጥ ፈታው፤ በዚህ ጊዜ ኤርምያስ እንዲህ አለው፦

“ይሖዋ፣ ማጎርሚሳቢብ*+ ብሎ ይጠራሃል እንጂ ጳስኮር አይልህም። 4 ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘አንተም ሆንክ ወዳጆችህ እንድትሸበሩ አደርጋለሁ፤ እነሱም ዓይንህ እያየ በጠላቶቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ፤+ ይሁዳንም ሁሉ ለባቢሎን ንጉሥ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እሱም በግዞት ወደ ባቢሎን ይወስዳቸዋል፤ በሰይፍም ይገድላቸዋል።+ 5 የዚህችን ከተማ ሀብት ሁሉ፣ ጥሪቷን ሁሉ፣ ውድ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ እንዲሁም የይሁዳን ነገሥታት ውድ ሀብት ሁሉ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ።+ እነሱም ይበዘብዟቸዋል፤ ወደ ባቢሎንም ያግዟቸዋል።+ 6 ጳስኮር ሆይ፣ አንተና በቤትህ የሚኖሩ ሁሉ በግዞት ትወሰዳላችሁ። ወደ ባቢሎን ትሄዳለህ፤ በዚያም ትሞታለህ፤ ከወዳጆችህም ሁሉ ጋር በዚያ ትቀበራለህ፤ ምክንያቱም ለእነሱ የሐሰት ትንቢት ተናግረሃል።’”+

 7 ይሖዋ ሆይ፣ አሞኘኸኝ፤ እኔም ተሞኘሁ።

አንተ በእኔ ላይ በረታህ፤ አሸነፍክም።+

እኔም ቀኑን ሙሉ መሳለቂያ ሆንኩ፤

ሁሉም ያፌዙብኛል።+

 8 በተናገርኩ ቁጥር እጮኻለሁና፤

“ዓመፅና ጥፋት!” ብዬ አውጃለሁ።

የይሖዋ ቃል ቀኑን ሙሉ ስድብና ፌዝ አስከትሎብኛል።+

 9 ስለዚህ “እሱን አላነሳም፤

ከእንግዲህም በስሙ አልናገርም” አልኩ።+

ይሁንና ቃሉ በልቤ ውስጥ እንዳለ፣ በአጥንቶቼም ውስጥ እንደገባ የሚነድ እሳት ሆነብኝ፤

አፍኜ መያዝ አቃተኝ፤

ከዚህ በላይ መቋቋም አልቻልኩም።+

10 ብዙ መጥፎ ወሬ ሰምቻለሁና፤

በዙሪያዬ ያለው ሁኔታ አሸብሮኛል።+

“አውግዙት፤ እናውግዘው!”

ሰላም የሚመኝልኝ ሰው ሁሉ የእኔን ውድቀት ይጠባበቃል፦+

“ምናልባት ይታለል ይሆናል፤

እኛም እናሸንፈዋለን፤ ደግሞም እንበቀለዋለን።”

11 ይሖዋ ግን እንደ አስፈሪ ተዋጊ ከእኔ ጋር ነበር።+

ከዚህም የተነሳ የሚያሳድዱኝ ሰዎች ይሰናከላሉ እንጂ አያሸንፉም።+

ስለማይሳካላቸውም ለከፍተኛ ኀፍረት ይዳረጋሉ።

የሚደርስባቸው ዘላለማዊ ውርደት ፈጽሞ አይረሳም።+

12 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን ጻድቁን ትመረምራለህ፤

የውስጥ ሐሳብንና* ልብን ታያለህ።+

በእነሱ ላይ የምትወስደውን የበቀል እርምጃ እንዳይ አድርገኝ፤+

ጉዳዬን ለአንተ አቅርቤአለሁና።+

13 ለይሖዋ ዘምሩ! ይሖዋን አወድሱ!

እሱ ድሃውን* ከክፉ አድራጊዎች እጅ ታድጓልና።

14 የተወለድኩበት ቀን የተረገመ ይሁን!

እናቴ እኔን የወለደችበት ቀን አይባረክ!+

15 ለአባቴ “ልጅ፣ አዎ ወንድ ልጅ ተወልዶልሃል!”

የሚል ምሥራች አብስሮ እጅግ ደስ ያሰኘው

ሰው የተረገመ ይሁን።

16 ያ ሰው፣ ይሖዋ ያላንዳች ጸጸት እንደገለበጣቸው ከተሞች ይሁን።

በማለዳ ዋይታ፣ በቀትርም የጦርነት ሁካታ ይስማ።

17 እናቴ የመቃብሬ ቦታ እንድትሆን፣

ማህፀኗም ዘወትር እርጉዝ እንደሆነ ይኖር ዘንድ፣

ገና በማህፀን ሳለሁ ለምን አልገደለኝም?+

18 ችግርንና ሐዘንን እንዳይ፣

ዕድሜዬም በኀፍረት እንዲያከትም

ለምን ከማህፀን ወጣሁ?+

21 ንጉሥ ሴዴቅያስ+ የማልኪያህን ልጅ ጳስኮርንና+ የማአሴያህን ልጅ ካህኑን ሶፎንያስን+ ወደ ኤርምያስ በላካቸው ጊዜ የይሖዋ ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ፤ እነሱም እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፦ 2 “የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* ሊወጋን ስለሆነ+ እባክህ፣ ስለ እኛ ይሖዋን ጠይቅልን። ንጉሡ ከእኛ እንዲመለስ ይሖዋ እንደቀድሞው ሁሉ አሁንም ተአምር ይፈጽምልን ይሆናል።”+

3 ኤርምያስ እንዲህ አላቸው፦ “ሴዴቅያስን እንዲህ በሉት፦ 4 ‘የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የባቢሎንን ንጉሥና ከቅጥሩ ውጭ የከበቧችሁን ከለዳውያንን ለመውጋት የምትጠቀሙባቸውን በገዛ እጃችሁ ላይ ያሉትን የጦር መሣሪያዎች በእናንተው ላይ አዞራለሁ።+ በዚህችም ከተማ መሃል እሰበስባቸዋለሁ። 5 እኔ ራሴ በተዘረጋች እጅና በኃያል ክንድ እንዲሁም በመዓትና በታላቅ ቁጣ እዋጋችኋለሁ።+ 6 የዚህችን ከተማ ነዋሪዎች፣ ሰውንም ሆነ እንስሳን እመታለሁ። እነሱም በታላቅ ቸነፈር* ይሞታሉ።”’+

7 “‘“ከዚያም በኋላ” ይላል ይሖዋ፣ “የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን፣ አገልጋዮቹን እንዲሁም ከቸነፈር፣ ከሰይፍና ከረሃብ ተርፎ በከተማዋ ውስጥ የሚቀረውን ሕዝብ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር* እጅ፣ በጠላቶቻቸው እጅና ሕይወታቸውን ለማጥፋት በሚሹ* ሰዎች እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።+ እሱም በሰይፍ ይመታቸዋል። አያዝንላቸውም፤ ርኅራኄም ሆነ ምሕረት አያሳያቸውም።”’+

8 “ደግሞም ይህን ሕዝብ እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ የሕይወትን መንገድና የሞትን መንገድ በፊታችሁ አድርጌአለሁ። 9 በዚህች ከተማ የሚቀሩ ሰዎች በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር ይሞታሉ። ይሁንና ከከተማዋ ወጥቶ፣ ለከበቧችሁ ከለዳውያን እጁን የሚሰጥ በሕይወት ይኖራል፤ ሕይወቱም* እንደ ምርኮ ትሆንለታለች።”’*+

10 “‘“መልካም ነገር ሳይሆን ጥፋት ለማምጣት ፊቴን ወደዚህች ከተማ አዙሬአለሁና”+ ይላል ይሖዋ። “ለባቢሎን ንጉሥ ትሰጣለች፤+ እሱም በእሳት ያቃጥላታል።”+

11 “‘የይሁዳ ንጉሥ ቤት ሆይ፦ የይሖዋን ቃል ስሙ። 12 የዳዊት ቤት ሆይ፣ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“ከክፉ ድርጊታችሁ የተነሳ

ቁጣዬ እንደ እሳት እንዳይቀጣጠልና+

ማንም ሊያጠፋው እስከማይችል ድረስ እንዳይነድ

በየማለዳው ለፍትሕ ቁሙ፤

የተዘረፈውንም ሰው ከአጭበርባሪው እጅ ታደጉ።”’+

13 ‘አንቺ በሸለቆ ውስጥ* የምትኖሪ፣ በደልዳላው መሬት ላይ የተቀመጥሽ ዓለት ሆይ፣

እነሆ፣ እኔ በአንቺ ላይ እነሳለሁ’ ይላል ይሖዋ።

‘“በእኛ ላይ ማን ይወርዳል? ደግሞስ መኖሪያዎቻችንን ማን ይወራል?”

የምትሉ ይህን እወቁ፤

14 እንደ ሥራችሁ መጠን

ተጠያቂ አደርጋችኋለሁ’+ ይላል ይሖዋ።

‘ጫካዋን በእሳት አነዳለሁ፤

እሳቱም በዙሪያዋ ያለውን ነገር ሁሉ ይበላል።’”+

22 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ወደ ይሁዳ ንጉሥ ቤት* ወርደህ ይህን መልእክት ተናገር። 2 እንዲህ በል፦ ‘በዳዊት ዙፋን ላይ የተቀመጥከው የይሁዳ ንጉሥ ሆይ፣ አንተም ሆንክ አገልጋዮችህ እንዲሁም በእነዚህ በሮች የሚገባው ሕዝብህ የይሖዋን ቃል ስሙ። 3 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ለፍትሕና ለጽድቅ ቁሙ። የተዘረፈውን ሰው ከአጭበርባሪው እጅ ታደጉ። ከባዕድ አገር የመጣውን ሰው አታንገላቱ፤ አባት የሌለውን ልጅ* ወይም መበለቲቱን አትበድሉ።+ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደም አታፍስሱ።+ 4 ይህን ቃል በሚገባ ብትጠብቁ፣ በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጡ ነገሥታት+ በሠረገሎችና በፈረሶች ላይ ተቀምጠው ከአገልጋዮቻቸውና ከሕዝቦቻቸው ጋር በዚህ ቤት በሮች ይገባሉ።”’+

5 “‘ይህን ቃል ባትታዘዙ ግን’ ይላል ይሖዋ፣ ‘ይህ ቤት እንደሚወድም በራሴ እምላለሁ።’+

6 “ይሖዋ የይሁዳን ንጉሥ ቤት አስመልክቶ እንዲህ ይላልና፦

‘አንተ ለእኔ እንደ ጊልያድና

እንደ ሊባኖስ ተራራ አናት ነህ።

ይሁንና ምድረ በዳ አደርግሃለሁ፤

ከተሞችህን በሙሉ ሰው አልባ አደርጋቸዋለሁ።+

 7 በአንተ ላይ ጥፋት የሚያደርሱ ሰዎችን፣

እያንዳንዳቸውን ከጦር መሣሪያዎቻቸው ጋር እሾማለሁ።*+

ምርጥ የሆኑ አርዘ ሊባኖሶችህን ይቆርጣሉ፤

ለእሳትም ይማግዷቸዋል።+

8 “‘ብዙ ብሔራትም በዚህች ከተማ በኩል ያልፋሉ፤ እርስ በርሳቸውም “ይሖዋ በዚህች ታላቅ ከተማ ላይ ይህን ያደረገው ለምንድን ነው?” ይባባላሉ።+ 9 እነሱም እንዲህ ብለው ይመልሳሉ፦ “የአምላካቸውን የይሖዋን ቃል ኪዳን ትተው ለሌሎች አማልክት ስለሰገዱና እነሱን ስላገለገሉ ነው።”’+

10 ለሞተው ሰው አታልቅሱ፤

ደግሞም አትዘኑለት።

ይልቁንም በግዞት ለተወሰደው አምርራችሁ አልቅሱ፤

ከእንግዲህ የትውልድ አገሩን ለማየት አይመለስምና።

11 “በአባቱ በኢዮስያስ ፋንታ ስለነገሠው፣ ከዚህም ቦታ ስለሄደው ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ+ ስለ ሻሉም*+ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘ከእንግዲህ ወደዚያ አይመለስም። 12 በግዞት በተወሰደበት በዚያው ስፍራ ይሞታል እንጂ ይህን ምድር ዳግመኛ አያይም።’+

13 ጽድቅን በሚጻረር መንገድ ቤቱን ለሚገነባ፣

ፍትሕን በማዛባት ደርብ ለሚሠራ፣

የወገኑን ጉልበት እንዲሁ ለሚበዘብዝና

ደሞዙን ለማይከፍለው ወዮለት፤+

14 ‘ለራሴ ሰፊ ቤትና

የተንጣለለ ደርብ እገነባለሁ።

መስኮቶች እንዲኖረው አደርጋለሁ፤

በአርዘ ሊባኖስም እለብጠዋለሁ፤ ቀይ ቀለምም እቀባዋለሁ’ ለሚል ወዮለት!

15 በአርዘ ሊባኖስ እንጨት ከሌሎች ስለምትበልጥ በንግሥና የምትቀጥል ይመስልሃል?

አባትህም ቢሆን ይበላና ይጠጣ ነበር፤

ሆኖም ለፍትሕና ለጽድቅ ቆሟል፤+

እንዲህ በማድረጉም ተሳክቶለት ነበር።

16 ለተጎሳቆለው ሰውና ለድሃው ተሟግቷል፤

ስለዚህ መልካም ሆኖለት ነበር።

‘እኔን ማወቅ ማለት ይህ አይደለም?’ ይላል ይሖዋ።

17 ‘አንተ ግን ዓይንህና ልብህ ያረፈው አላግባብ በምታገኘው ጥቅም፣

ንጹሕ ደም በማፍሰስ

እንዲሁም በማጭበርበርና በቅሚያ ላይ ብቻ ነው።’

18 “ስለዚህ ይሖዋ ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ኢዮዓቄም+ እንዲህ ይላል፦

‘“ወይኔ ወንድሜን! ወይኔ እህቴን!”

ብለው አያለቅሱለትም።

“ወይኔ ጌታዬን! ክብሩ ሁሉ እንዲህ ይጥፋ!”

ብለው አያለቅሱለትም።

19 አህያ እንደሚቀበረው ይቀበራል፤+

ከኢየሩሳሌም በሮች ውጭ

ጎትተው ይጥሉታል።’+

20 ወደ ሊባኖስ ወጥተሽ ጩኺ፤

በባሳን ድምፅሽን አሰሚ፤

በአባሪም+ ሆነሽ ጩኺ፤

አጥብቀው የሚወዱሽ ሁሉ ደቀዋልና።+

21 ተማምነሽ በተቀመጥሽበት ጊዜ አነጋገርኩሽ።

አንቺ ግን ‘አልታዘዝም’ አልሽ።+

ከልጅነትሽ ጀምሮ ይህን ጎዳና ተከተልሽ፤

ቃሌን አልታዘዝሽምና።+

22 ነፋስ እረኞችሽን በሙሉ ይነዳቸዋል፤+

አጥብቀው የሚወዱሽም በግዞት ይወሰዳሉ።

በዚያን ጊዜ ከሚደርስብሽ ጥፋት ሁሉ የተነሳ ታፍሪያለሽ፤ ውርደትም ትከናነቢያለሽ።

23 አንቺ በሊባኖስ የምትኖሪ፣+

በአርዘ ሊባኖሶች መካከል ተደላድለሽ የተቀመጥሽ፣+

ጣር ሲይዝሽ፣

አዎ ልትወልድ እንደተቃረበች ሴት ጭንቅ* ሲይዝሽ ምንኛ ታቃስቺ ይሆን!”+

24 “‘በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ይሖዋ፣ ‘አንተ የይሁዳ ንጉሥ፣ የኢዮዓቄም+ ልጅ፣ ኮንያሁ*+ በቀኝ እጄ እንዳለ የማኅተም ቀለበት ብትሆን እንኳ ከዚያ አውጥቼ እጥልሃለሁ! 25 ሕይወትህን ለማጥፋት በሚሹ* ሰዎች እጅ፣ በምትፈራቸው ሰዎች እጅ፣ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር* እጅና በከለዳውያን እጅ አሳልፌ እሰጥሃለሁ።+ 26 አንተንና የወለደችህን እናትህን ወዳልተወለዳችሁበት፣ ወደ ሌላ አገር እወረውራችኋለሁ፤ በዚያም ትሞታላችሁ። 27 ወደሚናፍቋትም ምድር* ፈጽሞ አይመለሱም።+

28 ኮንያሁ የተባለው ይህ ሰው የተናቀና የተሰበረ ገንቦ፣

ማንም የማይፈልገው የሸክላ ዕቃ ነው?

እሱም ሆነ ዘሮቹ ወደማያውቋት ምድር የተወረወሩትና

የተጣሉት ለምንድን ነው?’+

29 ምድር፣* ምድር፣ አንቺ ምድር ሆይ፣ የይሖዋን ቃል ስሚ።

30 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

‘ይህን ሰው፣ ልጅ እንደሌለውና

በሕይወት ዘመኑ* ሁሉ ምንም እንደማይሳካለት አድርጋችሁ መዝግቡት፤

ከዘሮቹ መካከል አንዱም እንኳ አይሳካለትምና፤

በዳዊት ዙፋን ላይ አይቀመጥም እንዲሁም ይሁዳን ዳግመኛ አይገዛም።’”+

23 “በማሰማሪያዬ ያሉትን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው!” ይላል ይሖዋ።+

2 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሕዝቡን በሚጠብቁት እረኞች ላይ እንዲህ ይላል፦ “በጎቼን በትናችኋል፤ አባራችኋቸዋል፤ ትኩረትም አልሰጣችኋቸውም።”+

“ስለዚህ ከክፉ ድርጊታችሁ የተነሳ ትኩረቴን በእናንተ ላይ አደርጋለሁ” ይላል ይሖዋ።

3 “ከዚያም የቀሩትን በጎቼን ከበተንኩባቸው አገሮች ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፤+ ወደ መሰማሪያቸውም መልሼ አመጣቸዋለሁ፤+ እነሱም ፍሬያማ ይሆናሉ፤ ደግሞም ይበዛሉ።+ 4 እኔም በሚገባ የሚጠብቋቸውን እረኞች አስነሳላቸዋለሁ።+ ከእንግዲህ አይፈሩም፣ አይሸበሩም እንዲሁም አንዳቸውም አይጎድሉም” ይላል ይሖዋ።

5 “እነሆ፣ ለዳዊት፣ ጻድቅ ቀንበጥ* የማስነሳበት ጊዜ እየደረሰ ነው”+ ይላል ይሖዋ። “ንጉሥም ይገዛል፤+ በማስተዋል ይመላለሳል እንዲሁም በምድሪቱ ላይ ለፍትሕና ለጽድቅ ይቆማል።+ 6 በእሱ ዘመን ይሁዳ ይድናል፤+ እስራኤልም ያለስጋት ይኖራል።+ የሚጠራበትም ስም ‘ይሖዋ ጽድቃችን ነው’ የሚል ይሆናል።”+

7 “ይሁን እንጂ ከዚህ በኋላ ‘የእስራኤልን ሕዝብ ከግብፅ ምድር ባወጣው ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ!’ የማይሉበት ጊዜ ይመጣል” ይላል ይሖዋ፤+ 8 “ከዚህ ይልቅ ‘የእስራኤልን ቤት ዘሮች ከሰሜን ምድርና እነሱን ከበተነባቸው አገሮች ሁሉ ባወጣውና መልሶ ባመጣው ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ’ ይላሉ፤ እነሱም በገዛ ምድራቸው ይኖራሉ።”+

9 ነቢያቱን በተመለከተ፣

ልቤ በውስጤ ተሰብሯል።

አጥንቶቼ ሁሉ እየተንቀጠቀጡ ነው።

ከይሖዋና ከቅዱስ ቃሉ የተነሳ

እንደሰከረ ሰውና

የወይን ጠጅ እንዳሸነፈው ሰው ሆንኩ።

10 ምድሪቱ በአመንዝሮች ተሞልታለችና፤+

ከእርግማኑ የተነሳ ምድሪቱ አዝናለች፤+

በምድረ በዳ ያሉት ማሰማሪያዎችም ደርቀዋል።+

መንገዳቸው መጥፎ ነው፤ ሥልጣናቸውንም አላግባብ ይጠቀሙበታል።

11 “ነቢዩም ሆነ ካህኑ ተበክለዋል።*+

በገዛ ቤቴ እንኳ ሳይቀር የሠሩትን ክፋት አግኝቻለሁ”+ ይላል ይሖዋ።

12 “ስለሆነም መንገዳቸው የሚያዳልጥና ጨለማ ይሆናል፤+

ይገፋሉ እንዲሁም ይወድቃሉ።

በሚመረመሩበት ዓመት፣

ጥፋት አመጣባቸዋለሁና” ይላል ይሖዋ።

13 “በሰማርያ+ ነቢያት ላይ ደግሞ አስጸያፊ ነገር አይቻለሁ።

ትንቢት የሚናገሩት በባአል አነሳሽነት ነው፤

ሕዝቤ እስራኤልም እንዲባዝን አድርገዋል።

14 በኢየሩሳሌም ነቢያትም ላይ የሚዘገንኑ ነገሮች አይቻለሁ።

ያመነዝራሉ፤+ በሐሰትም ይመላለሳሉ፤+

ክፉ አድራጊዎችን ያደፋፍራሉ፤*

ከክፋታቸውም አይመለሱም።

ለእኔ ሁሉም እንደ ሰዶም፣+

ነዋሪዎቿም እንደ ገሞራ+ ናቸው።”

15 ስለዚህ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በነቢያቱ ላይ እንዲህ ይላል፦

“እነሆ፣ እኔ ጭቁኝ እንዲበሉ አደርጋቸዋለሁ፤

የተመረዘም ውኃ እንዲጠጡ እሰጣቸዋለሁ።+

የኢየሩሳሌም ነቢያት በምድሪቱ ሁሉ ላይ ክህደት አሰራጭተዋልና።”

16 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“ትንቢት የሚተነብዩላችሁ ነቢያት የሚናገሩትን ቃል አትስሙ።+

እነሱ እያሞኟችሁ ነው።*

የሚናገሩት ራእይ ከይሖዋ አፍ የወጣ ሳይሆን+

ከገዛ ልባቸው የመነጨ ነው።+

17 እነሱ እኔን ለሚንቁ ሰዎች ደግመው ደጋግመው

‘ይሖዋ “ሰላም ታገኛላችሁ” ብሏል’ ይላሉ።+

ግትር የሆነ ልባቸውን የሚከተሉትን ሁሉ

‘ጥፋት አይደርስባችሁም’ ይሏቸዋል።+

18 ቃሉን ለማየትና ለመስማት

ከይሖዋ የቅርብ ወዳጆች ጋር የቆመ ማን ነው?

ይሰማስ ዘንድ ለቃሉ ትኩረት የሰጠ ማን ነው?

19 እነሆ፣ የይሖዋ አውሎ ነፋስ በታላቅ ቁጣ ይነሳል፤

እንደሚሽከረከር ኃይለኛ ነፋስ በክፉዎች ራስ ላይ እየተሽከረከረ ይወርዳል።+

20 ይሖዋ የልቡን ሐሳብ ሳያከናውንና ሳይፈጽም

ቁጣው አይመለስም።

በዘመኑ መጨረሻ ይህን በግልጽ ትረዳላችሁ።

21 ነቢያቱን እኔ አልላክኋቸውም፤ እነሱ ግን ሮጡ።

እኔ የነገርኳቸው ነገር የለም፤ እነሱ ግን ትንቢት ተናገሩ።+

22 ከእኔ የቅርብ ወዳጆች ጋር ቢቆሙ ኖሮ

ሕዝቤ ቃሌን እንዲሰማ ባደረጉ ነበር፤

ደግሞም ከክፉ መንገዱና ከመጥፎ ድርጊቱ እንዲመለስ ባደረጉ ነበር።”+

23 “እኔ የቅርብ አምላክ ብቻ ነኝ? የሩቅስ አምላክ አይደለሁም?” ይላል ይሖዋ።

24 “እኔ እንዳላየው በስውር ቦታ መሸሸግ የሚችል ሰው ይኖራል?”+ ይላል ይሖዋ።

“ሰማያትንና ምድርን የሞላሁት እኔ አይደለሁም?”+ ይላል ይሖዋ።

25 “‘ሕልም አይቻለሁ! ሕልም አይቻለሁ!’+ እያሉ በስሜ የሐሰት ትንቢት የሚናገሩ ነቢያትን ቃል ሰምቻለሁ። 26 የሐሰት ትንቢት ይናገሩ ዘንድ ይህ ነገር በነቢያት ልብ ውስጥ የሚኖረው እስከ መቼ ነው? እነሱ ከገዛ ልባቸው ያመነጩትን ማታለያ የሚናገሩ ነቢያት ናቸው።+ 27 አባቶቻቸው በባአል የተነሳ ስሜን እንደረሱ ሁሉ፣+ እነሱም አንዳቸው ለሌላው በሚናገሩት ሕልም አማካኝነት ሕዝቤ ስሜን እንዲረሳ ማድረግ ይፈልጋሉ። 28 ሕልም ያየ ነቢይ ሕልሙን ይናገር፤ ይሁንና ቃሌ ያለው ቃሌን በእውነት ይናገር።”

“ገለባና እህል አንድ የሚያደርጋቸው ምን ነገር አለ?” ይላል ይሖዋ።

29 “ቃሌ እንደ እሳት አይደለም?”+ ይላል ይሖዋ፤ “ቋጥኝንስ እንደሚያደቅ መዶሻ አይደለም?”+

30 “ስለዚህ እርስ በርስ ቃሌን በሚሰራረቁ ነቢያት ላይ ተነስቻለሁ” ይላል ይሖዋ።+

31 “እነሆ፣ በምላሳቸው እየቀባጠሩ ‘እሱ እንዲህ ይላል!’ ብለው በሚናገሩ ነቢያት ላይ ተነስቻለሁ” ይላል ይሖዋ።+

32 “እነሆ፣ ሐሰትን በሚያልሙና በሚናገሩ እንዲሁም የሐሰት ወሬ እያናፈሱና ጉራ እየነዙ ሕዝቤን በሚያስቱ ነቢያት ላይ ተነስቻለሁ” ይላል ይሖዋ።+

“ሆኖም እኔ አልላክኋቸውም ወይም አላዘዝኳቸውም። ስለዚህ ይህን ሕዝብ ምንም አይጠቅሙትም”+ ይላል ይሖዋ።

33 “ይህ ሕዝብ ወይም አንድ ነቢይ አሊያም አንድ ካህን ‘የይሖዋ ሸክም* ምንድን ነው?’ ብለው በሚጠይቁህ ጊዜ እንዲህ ትላቸዋለህ፦ ‘“ሸክሙ እናንተ ናችሁ! እኔም እጥላችኋለሁ”+ ይላል ይሖዋ።’ 34 ነቢይ ወይም ካህን አሊያም ማንኛውም ሰው ‘ይህ የይሖዋ ሸክም* ነው!’ እያለ ቢናገር በእሱም ሆነ በቤተሰቡ ላይ ትኩረቴን አደርጋለሁ። 35 እያንዳንዳችሁ ባልንጀራችሁንና ወንድማችሁን ‘ይሖዋ የሰጠው መልስ ምንድን ነው? ይሖዋ የተናገረውስ ምንድን ነው?’ ትላላችሁ። 36 ሆኖም ከእንግዲህ የይሖዋ ሸክም* ብላችሁ አትናገሩ፤ ሸክሙ* የእያንዳንዱ ሰው የገዛ ራሱ ቃል ነውና፤ እናንተም ሕያው አምላክ የሆነውን የአምላካችንን የሠራዊት ጌታ የይሖዋን ቃል ለውጣችኋል።

37 “ነቢዩን እንዲህ ትለዋለህ፦ ‘ይሖዋ የሰጠህ መልስ ምንድን ነው? ይሖዋ የተናገረውስ ምንድን ነው? 38 “የይሖዋ ሸክም!”* ማለታችሁን የማታቆሙ ከሆነ፣ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “‘“የይሖዋ ሸክም!”* አትበሉ’ ብዬ ከነገርኳችሁ በኋላ እናንተ ‘ይህ ቃል የይሖዋ ሸክም* ነው’ በማለታችሁ፣ 39 እነሆ፣ እናንተንም ሆነ ለእናንተና ለአባቶቻችሁ የሰጠኋትን ከተማ አንስቼ ከፊቴ እወረውራችኋለሁ። 40 የማይረሳ የዘላለም ኀፍረትና የዘላለም ውርደት በእናንተ ላይ አመጣለሁ።”’”+

24 ከዚያም ይሖዋ በለስ የያዙ ሁለት ቅርጫቶችን በይሖዋ ቤተ መቅደስ ፊት ለፊት ተቀምጠው አሳየኝ፤ ይህም የሆነው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* የይሁዳን ንጉሥ የኢዮዓቄምን ልጅ+ ኢኮንያንን፣*+ ከይሁዳ መኳንንት፣ ከእጅ ጥበብ ባለሙያዎቹና ከአንጥረኞቹ* ጋር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን በግዞት ከወሰዳቸው በኋላ ነው።+ 2 በአንደኛው ቅርጫት ውስጥ ያሉት በለሶች በመጀመሪያው ወቅት ላይ እንደሚደርሱ በለሶች ጥሩ ዓይነት ነበሩ፤ በሌላኛው ቅርጫት ውስጥ ያሉት በለሶች ደግሞ መጥፎ ዓይነት ነበሩ፤ በጣም መጥፎ ከመሆናቸው የተነሳም ሊበሉ የሚችሉ አልነበሩም።

3 ከዚያም ይሖዋ “ኤርምያስ፣ የምታየው ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም እንዲህ አልኩ፦ “የበለስ ፍሬዎችን አያለሁ፤ ጥሩዎቹ በለሶች በጣም ጥሩ ዓይነት ናቸው፤ መጥፎዎቹ ደግሞ በጣም መጥፎ ዓይነት ናቸው፤ ከመጥፎነታቸውም የተነሳ ሊበሉ አይችሉም።”+

4 ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 5 “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ከዚህ ስፍራ ወደ ከለዳውያን ምድር የሰደድኳቸውን የይሁዳ ግዞተኞች እንደነዚህ ጥሩ ዓይነት በለሶች በጥሩ ዓይን እመለከታቸዋለሁ። 6 መልካም ነገር አደርግላቸው ዘንድ ዓይኔን በእነሱ ላይ አኖራለሁ፤ ወደዚህችም ምድር እንዲመለሱ አደርጋለሁ።+ እገነባቸዋለሁ እንጂ አላፈርሳቸውም፤ እተክላቸዋለሁ እንጂ አልነቅላቸውም።+ 7 እኔ ይሖዋ መሆኔን እንዲያውቁም ልብ እሰጣቸዋለሁ።+ በሙሉ ልባቸው ወደ እኔ ስለሚመለሱ+ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።+

8 “‘ይሁንና ከመጥፎነታቸው የተነሳ ሊበሉ የማይችሉትን መጥፎ በለሶች+ በተመለከተ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን፣+ መኳንንቱን፣ በዚህች ምድር ላይ የሚቀሩትን የኢየሩሳሌም ቀሪዎችና በግብፅ ምድር የሚኖሩትን በዚሁ ዓይን እመለከታቸዋለሁ።+ 9 ለምድር መንግሥታት ሁሉ መቀጣጫ እንዲሆኑ ጥፋት አመጣባቸዋለሁ፤+ በምበትናቸው ቦታም ሁሉ+ ነቀፋ እንዲደርስባቸው፣ መተረቻ እንዲሆኑ፣ እንዲፌዝባቸውና እንዲረገሙ አደርጋለሁ።+ 10 ለእነሱና ለአባቶቻቸው ከሰጠኋት ምድር ላይ እስኪጠፉ ድረስ በእነሱ ላይ ሰይፍ፣+ ረሃብና ቸነፈር* እሰዳለሁ።”’”+

25 የይሁዳ ንጉሥ የኢዮስያስ ልጅ ኢዮዓቄም+ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ይኸውም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት መላውን የይሁዳን ሕዝብ በተመለከተ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው። 2 ነቢዩ ኤርምያስ የይሁዳን ሕዝብ ሁሉና የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች በሙሉ አስመልክቶ* እንዲህ ሲል ተናገረ፦

3 “ከይሁዳ ንጉሥ ከአምዖን ልጅ ከኢዮስያስ 13ኛ ዓመት የግዛት ዘመን+ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ላለፉት 23 ዓመታት የይሖዋ ቃል ወደ እኔ መጣ፤ እኔም ደግሜ ደጋግሜ ነገርኳችሁ፤* እናንተ ግን አትሰሙም።+ 4 ይሖዋም ደግሞ ደጋግሞ* አገልጋዮቹን ነቢያትን ሁሉ ወደ እናንተ ላከ፤ እናንተ ግን አትሰሙም ወይም ጆሯችሁን አትሰጡም።+ 5 እነሱም እንዲህ ይላሉ፦ ‘እባካችሁ፣ እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ድርጊታችሁ ተመለሱ፤+ ይህን ካደረጋችሁ ይሖዋ ለብዙ ዘመን እንድትኖሩባት ሲል ከረጅም ጊዜ በፊት ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጣት ምድር ላይ ትኖራላችሁ። 6 በእጃችሁ ሥራ ታስቆጡኝ ዘንድ ሌሎች አማልክትን አትከተሉ፣ አታገልግሏቸው፣ አትስገዱላቸውም፤ አለዚያ ጥፋት አመጣባችኋለሁ።’

7 “‘እናንተ ግን እኔን አትሰሙም’ ይላል ይሖዋ። ‘ይልቁንም በራሳችሁ ላይ ጥፋት ታመጡ ዘንድ አስቆጣችሁኝ።’+

8 “ስለዚህ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘“ቃሌን ስለማትታዘዙ፣ 9 የሰሜንን ወገኖች ሁሉ እጠራለሁ”+ ይላል ይሖዋ፤ “አገልጋዬን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነጾርን* እጠራለሁ፤+ በዚህች ምድር፣ በነዋሪዎቿና በዙሪያዋ ባሉ በእነዚህ ብሔራት ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ።+ ፈጽሞ አጠፋቸዋለሁ፤ እንዲሁም መቀጣጫና ማፏጫ እንዲሆኑ ብሎም ባድማ ሆነው እንዲቀሩ አደርጋለሁ። 10 የሐሴትንና የደስታን ድምፅ፣ የሙሽራንና የሙሽሪትን ድምፅ፣ የወፍጮን ድምፅና የመብራትን ብርሃን ከመካከላቸው አስቀራለሁ።+ 11 መላ ምድሪቱ ትወድማለች፤ እንዲሁም አስፈሪ ቦታ ትሆናለች፤ እነዚህም ብሔራት የባቢሎንን ንጉሥ 70 ዓመት ያገለግሉታል።”’+

12 “‘ይሁንና ሰባው ዓመት ሲፈጸም+ በበደላቸው የተነሳ የባቢሎንን ንጉሥና ያንን ብሔር ተጠያቂ አደርጋለሁ’*+ ይላል ይሖዋ፤ ‘የከለዳውያንንም ምድር እስከ ወዲያኛው ባድማ አደርገዋለሁ።+ 13 በምድሪቱ ላይ የተናገርኩትን ቃል ሁሉ ይኸውም ኤርምያስ በሁሉም ብሔራት ላይ የተነበየውንና በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈውን ነገር ሁሉ አመጣባታለሁ። 14 ብዙ ብሔራትና ታላላቅ ነገሥታት+ ባሪያዎች ያደርጓቸዋልና፤+ እኔም እንደ ድርጊታቸውና እንደ ገዛ እጃቸው ሥራ እከፍላቸዋለሁ።’”+

15 የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ብሎኛልና፦ “የቁጣ ወይን ጠጅ ያለበትን ይህን ጽዋ ከእጄ ውሰድ፤ እኔም ወደምልክህ ብሔራት ሁሉ ሄደህ አጠጣቸው። 16 እነሱም በመካከላቸው ከምሰደው ሰይፍ የተነሳ ይጠጣሉ፣ ይንገዳገዳሉ፣ እንደ አበደ ሰውም ይሆናሉ።”+

17 ስለዚህ ከይሖዋ እጅ ጽዋውን ወሰድኩ፤ ይሖዋ ወደላከኝም ብሔራት ሁሉ ሄጄ አጠጣኋቸው፦+ 18 ዛሬ እንደሆነው ሁሉ ባድማ፣ መቀጣጫና ማፏጫ እንዲሆኑ እንዲሁም ለእርግማን እንዲዳረጉ+ በመጀመሪያ ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች፣+ ነገሥታቷንና መኳንንቷን አጠጣኋቸው፤ 19 ከዚያም የግብፅ ንጉሥ ፈርዖንና አገልጋዮቹ፣ መኳንንቱና ሕዝቡ ሁሉ፣+ 20 ድብልቅ የሆነው ሕዝባቸው ሁሉ፣ የዑጽ ምድር ነገሥታት ሁሉ፣ የፍልስጤማውያን+ ምድር ነገሥታት ሁሉ፣ አስቀሎን፣+ ጋዛ፣ ኤቅሮንና ከአሽዶድ የቀሩት ሰዎች፣ 21 ኤዶም፣+ ሞዓብና+ አሞናውያን፣+ 22 የጢሮስ ነገሥታት ሁሉ፣ የሲዶና+ ነገሥታት ሁሉና በባሕሩ ላይ ያለው ደሴት ነገሥታት፣ 23 ዴዳን፣+ ቴማ፣ ቡዝና በሰሪሳራቸው* ላይ ያለውን ፀጉር የሚላጩ ሁሉ፣+ 24 የዓረብ ነገሥታት ሁሉና+ በምድረ በዳ የሚኖሩት ድብልቅ ሕዝብ ነገሥታት ሁሉ፣ 25 የዚምሪ ነገሥታት ሁሉ፣ የኤላም+ ነገሥታት ሁሉና የሜዶናውያን ነገሥታት+ ሁሉ፣ 26 በቅርብም ሆነ በሩቅ ያሉ የሰሜን ነገሥታት ሁሉ አንድ በአንድ እንዲሁም በምድር ላይ ያሉ ሌሎች የዓለም መንግሥታት ሁሉ ጠጡ፤ ከእነሱም በኋላ የሼሻቅ*+ ንጉሥ ይጠጣል።

27 “አንተም እንዲህ በላቸው፦ ‘የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በመካከላችሁ ከምሰደው ሰይፍ የተነሳ ጠጡ፣ ስከሩ፣ አስታውኩ፣ ዳግመኛም ላትነሱ ውደቁ።”’+ 28 ጽዋውን ከእጅህ ወስደው ለመጠጣት ፈቃደኛ ባይሆኑ እንዲህ በላቸው፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በግድ ትጠጣላችሁ! 29 እነሆ፣ በመጀመሪያ የማጠፋው በስሜ የተጠራችውን ከተማ+ ከሆነ እናንተስ ከቅጣት ታመልጣላችሁ?”’+

“‘በምድር ነዋሪዎች ሁሉ ላይ ሰይፍን ስለምጠራ እናንተም ከቅጣት አታመልጡም’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።

30 “አንተም ይህን ቃል ሁሉ ትተነብይላቸዋለህ፤ እንዲህም ትላቸዋለህ፦

‘ይሖዋ ከላይ ሆኖ ይጮኻል፤

ከቅዱስ ማደሪያውም ድምፁን ያሰማል።

በመኖሪያ ስፍራውም ላይ በኃይል ይጮኻል።

ወይን መጭመቂያውን እንደሚረግጡ ሰዎች፣

በምድር ነዋሪዎች ሁሉ ላይ በድል አድራጊነት ይዘምራል።’

31 ‘ታላቅ ጩኸት እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ያስተጋባል፤

ይሖዋ ከብሔራት ጋር ሙግት አለውና።

እሱ ራሱ በሰዎች* ሁሉ ላይ ይፈርዳል።+

ክፉዎችንም ለሰይፍ ይዳርጋል’ ይላል ይሖዋ።

32 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

‘እነሆ፣ ጥፋት ብሔራትን አንድ በአንድ ያዳርሳል፤+

ታላቅ አውሎ ነፋስም ከምድር ዳርቻዎች ይነሳል።+

33 “‘በዚያም ቀን፣ ይሖዋ የገደላቸው ከምድር ዳር እስከ ምድር ዳር ድረስ ይሆናሉ። አይለቀስላቸውም፣ አይሰበሰቡም ወይም አይቀበሩም። በምድር ላይ እንደ ፍግ ይሆናሉ።’

34 እናንተ እረኞች፣ ዋይ ዋይ በሉ፤ ጩኹም!

እናንተ በመንጋው መካከል ያላችሁ ታላላቆች፣ በአመድ ላይ ተንከባለሉ፤

ምክንያቱም የምትታረዱበትና የምትበታተኑበት ጊዜ ደርሷል፤

እንደ ውድ የሸክላ ዕቃ ትከሰከሳላችሁ!

35 እረኞቹ የሚሸሹበት ቦታ የለም፤

በመንጋው መካከል ያሉት ታላላቆችም ማምለጫ የላቸውም።

36 አዳምጡ! የእረኞቹ ጩኸትና

በመንጋው መካከል ያሉ ታላላቆች ዋይታ ይሰማል፤

ይሖዋ ማሰማሪያቸውን እያወደመ ነውና።

37 ከሚነደው የይሖዋ ቁጣም የተነሳ

ሰላማዊ የሆኑት የመኖሪያ ቦታዎች ሕይወት አልባ ሆነዋል።

38 እንደ ደቦል አንበሳ ከጎሬው ወጥቷል፤+

ከጨካኙ ሰይፍና

ከሚነደው ቁጣው የተነሳ

ምድራቸው የሚያስፈራ ቦታ ሆኗልና።”

26 በኢዮስያስ ልጅ፣ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮዓቄም+ ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ ላይ ይህ ቃል ከይሖዋ ዘንድ መጣ፦ 2 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በይሖዋ ቤት ግቢ ውስጥ ቆመህ፣ ለአምልኮ* ወደ ይሖዋ ቤት ስለሚመጡት፣ በይሁዳ ከተሞች ስለሚኖሩት* ሰዎች ሁሉ ተናገር። የማዝህን ቃል ሁሉ ንገራቸው፤ አንዲትም ቃል አታስቀር። 3 ምናልባት ይሰሙና እያንዳንዳቸው ከክፉ መንገዳቸው ይመለሱ ይሆናል፤ እኔም በክፉ ሥራቸው የተነሳ በእነሱ ላይ ላመጣ ያሰብኩትን ጥፋት እተወዋለሁ።*+ 4 እንዲህ በላቸው፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የማትሰሙኝና የሰጠኋችሁን ሕግ* የማትከተሉ ከሆነ፣ 5 እንዲሁም ደግሜ ደጋግሜ* ወደ እናንተ የላክኋቸውን፣ እናንተ ያልሰማችኋቸውን የአገልጋዮቼን የነቢያትን ቃል የማትቀበሉ ከሆነ፣+ 6 ይህን ቤት እንደ ሴሎ አደርገዋለሁ፤+ ይህችንም ከተማ ለምድር ብሔራት ሁሉ እርግማን አደርጋታለሁ።’”’”+

7 ካህናቱ፣ ነቢያቱና ሕዝቡ ሁሉ ኤርምያስ በይሖዋ ቤት ይህን ቃል ሲናገር ሰሙ።+ 8 በመሆኑም ኤርምያስ፣ ይሖዋ ለሕዝቡ ሁሉ እንዲናገር ያዘዘውን ተናግሮ በጨረሰ ጊዜ ካህናቱ፣ ነቢያቱና ሕዝቡ ሁሉ ይዘው እንዲህ አሉት፦ “አንተ በእርግጥ ትሞታለህ። 9 ‘ይህ ቤት እንደ ሴሎ ይሆናል፤ ይህችም ከተማ ወድማ ሰው አልባ ትሆናለች’ ብለህ በይሖዋ ስም የተነበይከው ለምንድን ነው?” ሕዝቡም ሁሉ በይሖዋ ቤት በኤርምያስ ዙሪያ ተሰበሰበ።

10 የይሁዳ መኳንንት ይህን ቃል በሰሙ ጊዜ ከንጉሡ ቤት* ወደ ይሖዋ ቤት መጥተው በይሖዋ ቤት ባለው በአዲሱ በር መግቢያ ተቀመጡ።+ 11 ካህናቱና ነቢያቱ፣ ለመኳንንቱና ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው በሞት ሊቀጣ ይገባዋል፤+ ምክንያቱም በገዛ ጆሯችሁ እንደሰማችሁት በዚህች ከተማ ላይ ትንቢት ተናግሯል።”+

12 በዚህ ጊዜ ኤርምያስ ለመኳንንቱ ሁሉና ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አለ፦ “የሰማችሁትን ቃል ሁሉ በዚህ ቤትና በዚህች ከተማ ላይ እንድተነብይ የላከኝ ይሖዋ ነው።+ 13 እንግዲያው አሁን መንገዳችሁንና ድርጊታችሁን አስተካክሉ፤ የአምላካችሁንም የይሖዋን ቃል ስሙ፤ ይሖዋም በእናንተ ላይ አመጣዋለሁ ብሎ የተናገረውን ጥፋት ይተወዋል።*+ 14 እኔ ግን በእጃችሁ ነኝ። መልካምና ትክክል መስሎ የታያችሁን ነገር ሁሉ አድርጉብኝ። 15 ከገደላችሁኝ በራሳችሁ፣ በዚህች ከተማና በነዋሪዎቿ ላይ የንጹሕ ሰው ደም ዕዳ እንደምታመጡ በእርግጥ እወቁ፤ ይህን ሁሉ ቃል በጆሯችሁ እንድናገር የላከኝ በእርግጥ ይሖዋ ነውና።”

16 በዚህ ጊዜ መኳንንቱና ሕዝቡ ሁሉ ካህናቱንና ነቢያቱን “ይህ ሰው የተናገረን በአምላካችን በይሖዋ ስም ስለሆነ በሞት ሊቀጣ አይገባውም” አሏቸው።

17 በተጨማሪም በምድሪቱ ከሚኖሩ ሽማግሌዎች መካከል አንዳንዶቹ ተነስተው ለተሰበሰበው ሕዝብ ሁሉ እንዲህ አሉ፦ 18 “የሞረሸቱ ሚክያስ+ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ+ ዘመን ትንቢት ይናገር ነበር፤ ለይሁዳም ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ብሎ ነበር፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፤

ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤+

የቤቱም* ተራራ፣ በጫካ እንዳሉ ከፍ ያሉ ቦታዎች* ይሆናል።”’+

19 “ታዲያ በዚያ ጊዜ የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስና የይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ገደሉት? ይልቁንም ይሖዋን ፈርቶ፣ ይሖዋ እንዲራራለት አልተማጸነም? ከዚህስ የተነሳ ይሖዋ በእነሱ ላይ ሊያመጣ አስቦት የነበረውን ጥፋት አልተወውም?*+ እኛ ግን በራሳችን* ላይ ጥፋት እየጋበዝን ነው።

20 “ደግሞም በይሖዋ ስም ትንቢት የሚናገር ሌላ ሰው ነበር፤ እሱም የቂርያትየአሪም+ ሰው የሆነው የሸማያህ ልጅ ዑሪያህ ሲሆን ኤርምያስ የተናገረውን ዓይነት ቃል በመናገር በዚህች ከተማና በዚህች ምድር ላይ ተንብዮአል። 21 ንጉሥ ኢዮዓቄም፣+ ኃያል ተዋጊዎቹ ሁሉና መኳንንቱ ሁሉ እሱ የተናገረውን ቃል ሰሙ፤ ንጉሡም ሊገድለው ፈለገ።+ ዑሪያህ ይህን እንደሰማ በጣም ስለፈራ ሸሽቶ ወደ ግብፅ ሄደ። 22 በዚህ ጊዜ ንጉሥ ኢዮዓቄም የአክቦርን ልጅ ኤልናታንን+ እንዲሁም ከእሱ ጋር ሌሎች ሰዎችን ወደ ግብፅ ላከ። 23 እነሱም ዑሪያህን ከግብፅ አምጥተው ወደ ንጉሥ ኢዮዓቄም ወሰዱት፤ እሱም በሰይፍ መትቶ ገደለው፤+ አስከሬኑንም ተራ ሰዎች በሚቀበሩበት ስፍራ ጣለው።”

24 ይሁንና የሳፋን+ ልጅ አኪቃም+ ኤርምያስን ረዳው፤ በመሆኑም ኤርምያስ እንዲገደል ለሕዝቡ አልተሰጠም።+

27 በኢዮስያስ ልጅ፣ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮዓቄም* ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ ላይ ይህ የይሖዋ ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ 2 “ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘ለራስህ ማሰሪያና ቀንበር ሠርተህ አንገትህ ላይ አድርገው። 3 ከዚያም በኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሴዴቅያስ በመጡት መልእክተኞች እጅ፣ ወደ ኤዶም+ ንጉሥ፣ ወደ ሞዓብ+ ንጉሥ፣ ወደ አሞናውያን+ ንጉሥ፣ ወደ ጢሮስ+ ንጉሥና ወደ ሲዶና+ ንጉሥ ላከው። 4 ለጌቶቻቸው ይህን ትእዛዝ እንዲያስተላልፉ ንገራቸው፦

“‘“የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ለጌቶቻችሁ እንዲህ በሏቸው፦ 5 ‘ምድርን እንዲሁም በምድር ላይ ያሉትን ሰዎችና እንስሳት በታላቅ ኃይሌና በተዘረጋችው ክንዴ የሠራሁት እኔ ነኝ፤ ለወደድኩትም ሰጥቼዋለሁ።+ 6 አሁንም እነዚህን ሁሉ አገሮች ለአገልጋዬ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾር አሳልፌ ሰጥቻለሁ፤+ የዱር አራዊትም እንኳ እንዲገዙለት አድርጌአለሁ። 7 የእሱ መንግሥት የሚያበቃበት ጊዜ እስኪደርስ ድረስ+ ብሔራት ሁሉ እሱን፣ ልጁንና የልጅ ልጁን ያገለግላሉ፤ በዚያን ጊዜ ግን ብዙ ብሔራትና ታላላቅ ነገሥታት ባሪያቸው ያደርጉታል።’+

8 “‘“‘የትኛውም ብሔር ወይም መንግሥት የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነጾርን ለማገልገል ፈቃደኛ ባይሆን እንዲሁም አንገቱን በባቢሎን ንጉሥ ቀንበር ሥር ለማስገባት እንቢተኛ ቢሆን ያንን ብሔር በእሱ እጅ ፈጽሞ እስካጠፋው ድረስ በሰይፍ፣+ በረሃብና በቸነፈር* እቀጣዋለሁ’ ይላል ይሖዋ።

9 “‘“‘ስለዚህ “የባቢሎንን ንጉሥ አታገለግሉም” የሚሏችሁን በመካከላችሁ ያሉትን ነቢያት፣ ሟርተኞች፣ ሕልም አላሚዎች፣ አስማተኞችና መተተኞች አትስሙ። 10 የሚተነብዩላችሁ ነገር ሐሰት ነውና፤ እነሱን የምትሰሙ ከሆነ ከምድራችሁ ተፈናቅላችሁ ወደ ሩቅ ቦታ ትወሰዳላችሁ፤ እኔም እበትናችኋለሁ፤ እናንተም ትጠፋላችሁ።

11 “‘“‘ሆኖም አንገቱን በባቢሎን ንጉሥ ቀንበር ሥር የሚያስገባንና እሱን የሚያገለግልን ብሔር ምድሪቱን እንዲያርስና በዚያ እንዲኖር በገዛ ምድሩ እንዲቀር* አደርገዋለሁ’ ይላል ይሖዋ።”’”

12 ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስም+ ተመሳሳይ ነገር ነገርኩት፤ እንዲህም አልኩት፦ “አንገታችሁን በባቢሎን ንጉሥ ቀንበር ሥር አስገቡ፤ እሱንና ሕዝቡንም አገልግሉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ።+ 13 ይሖዋ የባቢሎንን ንጉሥ የማያገለግልን ብሔር አስመልክቶ በሰጠው ማስጠንቀቂያ መሠረት፣ አንተም ሆንክ ሕዝብህ በሰይፍ፣+ በረሃብና+ በቸነፈር ለምን ታልቃላችሁ?+ 14 ‘የባቢሎንን ንጉሥ አታገለግሉም’ የሚሏችሁን ነቢያት ቃል አትስሙ፤+ ምክንያቱም የሚተነብዩላችሁ ነገር ሐሰት ነው።+

15 “‘እኔ አልላክኋቸውምና’ ይላል ይሖዋ፤ ‘እነሱ ግን በስሜ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ እነሱን የምትሰሙ ከሆነ እናንተንና የሚተነብዩላችሁን ነቢያት እበትናለሁ፤ እናንተም ትጠፋላችሁ።’”+

16 ደግሞም ለካህናቱና ለዚህ ሕዝብ ሁሉ እንዲህ አልኩ፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘“እነሆ፣ የይሖዋ ቤት ዕቃዎች ከባቢሎን በቅርቡ ይመለሳሉ!”+ እያሉ የሚተነብዩላችሁን የነቢያታችሁን ቃል አትስሙ፤ የሚተነብዩላችሁ ነገር ሐሰት ነውና።+ 17 እነሱን አትስሟቸው። የባቢሎንን ንጉሥ አገልግሉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ።+ ይህች ከተማ ለምን ትፈራርስ? 18 ሆኖም እነሱ ነቢያት ከሆኑና የይሖዋ ቃል እነሱ ጋር ካለ፣ በይሖዋ ቤት፣ በይሁዳ ንጉሥ ቤትና* በኢየሩሳሌም የቀሩት ዕቃዎች ወደ ባቢሎን እንዳይወሰዱ እስቲ የሠራዊት ጌታ ይሖዋን ይለምኑ።’

19 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ስለ ዓምዶቹ፣+ ስለ ባሕሩ፣*+ ስለ ዕቃ ማጓጓዣ ጋሪዎቹና+ በዚህች ከተማ ስለቀሩት የተረፉ ዕቃዎች እንዲህ ይላልና፦ 20 እነዚህ፣ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር የኢዮዓቄምን ልጅ የይሁዳን ንጉሥ ኢኮንያንን ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም ታላላቅ ሰዎች ሁሉ ጋር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ባጋዘበት ወቅት ሳይወስዳቸው የቀሩ ነገሮች ናቸው፤+ 21 አዎ፣ የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ በይሖዋ ቤት፣ በይሁዳ ንጉሥ ቤትና* በኢየሩሳሌም ስለቀሩት ዕቃዎች እንዲህ ይላል፦ 22 ‘“ትኩረቴን ወደ እነሱ እስከማዞርበት ጊዜ ድረስ ወደ ባቢሎን ይወሰዳሉ፤+ በዚያም ይቆያሉ” ይላል ይሖዋ። “ከዚያ በኋላ አመጣቸዋለሁ፤ ወደዚህ ስፍራም እመልሳቸዋለሁ።”’”+

28 በዚያው ዓመት፣ በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ+ ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ፣ በአራተኛው ዓመት፣ በአምስተኛው ወር፣ የገባኦን+ ሰው የሆነው የአዙር ልጅ ነቢዩ ሃናንያህ፣ በይሖዋ ቤት ውስጥ በካህናቱና በሕዝቡ ሁሉ ፊት እንዲህ አለኝ፦ 2 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር እሰብራለሁ።+ 3 በሁለት ዓመት* ጊዜ ውስጥ፣ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር ከዚህ ስፍራ ወደ ባቢሎን የወሰዳቸውን የይሖዋን ቤት ዕቃዎች ሁሉ ወደዚህ ቦታ መልሼ አመጣለሁ።’”+ 4 “‘የኢዮዓቄምን+ ልጅ፣ የይሁዳን ንጉሥ ኢኮንያንን+ እንዲሁም ወደ ባቢሎን በግዞት የተወሰዱትን የይሁዳ ሰዎች ሁሉ+ ወደዚህ ቦታ መልሼ አመጣለሁ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር እሰብራለሁና።’”

5 ከዚያም ነቢዩ ኤርምያስ በካህናቱ ፊትና በይሖዋ ቤት ቆመው በነበሩት ሕዝብ ሁሉ ፊት ነቢዩ ሃናንያህን አናገረው። 6 ነቢዩ ኤርምያስ እንዲህ አለ፦ “አሜን! ይሖዋ ይህን ያድርግ! የይሖዋን ቤት ዕቃዎችና በግዞት የተወሰዱትን ሰዎች ሁሉ ከባቢሎን ወደዚህ ስፍራ እንዲመለሱ በማድረግ ይሖዋ የተነበይከውን ቃል ይፈጽም! 7 ይሁንና እባክህ፣ በጆሮህና በሕዝቡ ሁሉ ጆሮ የምናገረውን ይህን መልእክት ስማ። 8 በጥንት ዘመን ከእኔና ከአንተ በፊት የነበሩት ነቢያት፣ ብዙ አገሮችና ታላላቅ መንግሥታት ስለሚያጋጥማቸው ጦርነት እንዲሁም ስለሚደርስባቸው ጥፋትና ቸነፈር* ይተነብዩ ነበር። 9 አንድ ነቢይ ስለ ሰላም ትንቢት ከተናገረና ነቢዩ የተናገረው ቃል ከተፈጸመ ይሖዋ ይህን ነቢይ በእርግጥ እንደላከው ይታወቃል።”

10 በዚህ ጊዜ ነቢዩ ሃናንያህ ቀንበሩን ከነቢዩ ኤርምያስ አንገት ላይ ወስዶ ሰበረው።+ 11 ከዚያም ሃናንያህ በሕዝቡ ሁሉ ፊት እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ልክ እንዲሁ እኔም በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የባቢሎንን ንጉሥ የናቡከደነጾርን ቀንበር ከብሔራት ሁሉ አንገት ላይ እሰብራለሁ።’”+ ነቢዩ ኤርምያስም ትቶት ሄደ።

12 ነቢዩ ሃናንያህ ቀንበሩን ከነቢዩ ኤርምያስ አንገት ላይ ወስዶ ከሰበረው በኋላ ይህ የይሖዋ መልእክት ወደ ኤርምያስ መጣ፦ 13 “ሄደህ ሃናንያህን እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አንተ የእንጨት ቀንበር ሰብረሃል፤+ ይሁንና በእሱ ምትክ የብረት ቀንበር ትሠራለህ።” 14 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነጾርን እንዲያገለግሉ በእነዚህ ሁሉ ብሔራት አንገት ላይ የብረት ቀንበር አደርጋለሁ፤ እነሱም ያገለግሉታል።+ የዱር አራዊትንም እንኳ እሰጠዋለሁ።”’”+

15 ከዚያም ነቢዩ ኤርምያስ ነቢዩ ሃናንያህን+ እንዲህ አለው፦ “ሃናንያህ ሆይ፣ እባክህ ስማ! ይሖዋ ሳይልክህ ይህ ሕዝብ በሐሰት እንዲታመን አድርገሃል።+ 16 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ከምድር ገጽ አስወግድሃለሁ። በይሖዋ ላይ ዓመፅ ስላነሳሳህ በዚህ ዓመት ትሞታለህ።’”+

17 በመሆኑም ነቢዩ ሃናንያህ በዚያው ዓመት በሰባተኛው ወር ሞተ።

29 ነቢዩ ኤርምያስ፣ በግዞት ከተወሰዱት ሰዎች መካከል በሕይወት ለቀሩት ሽማግሌዎች፣ ለካህናቱ፣ ለነቢያቱና ናቡከደነጾር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን በግዞት ለወሰደው ሕዝብ ሁሉ ከኢየሩሳሌም የላከው ደብዳቤ ቃል ይህ ነው፦ 2 ይህም የሆነው ንጉሥ ኢኮንያን፣+ የንጉሡ እናት፣*+ ባለሥልጣናቱ፣ የይሁዳና የኢየሩሳሌም መኳንንት፣ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎቹና አንጥረኞቹ* ከኢየሩሳሌም ከሄዱ በኋላ ነው።+ 3 ደብዳቤውን የላከው፣ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ+ ወደ ባቢሎን ይኸውም የባቢሎን ንጉሥ ወደሆነው ወደ ናቡከደነጾር በላካቸው በሳፋን+ ልጅ በኤልዓሳና በኬልቅያስ ልጅ በገማርያህ እጅ ነው። ደብዳቤውም እንዲህ የሚል ነበር፦

4 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን በግዞት እንዲወሰዱ ላደረጋቸው ለተማረኩት ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ይላል፦ 5 ‘ቤት ሠርታችሁ በዚያ ኑሩ። አትክልት ተክላችሁ ፍሬውን ብሉ። 6 ሚስት አግብታችሁ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ውለዱ፤ እነሱም ወንዶችና ሴቶች ልጆች እንዲወልዱ፣ ወንዶች ልጆቻችሁንና ሴቶች ልጆቻችሁን ዳሩ። በዚያም ቁጥራችሁ ይብዛ እንጂ አይነስ። 7 በግዞት ተወስዳችሁ እንድትኖሩባት ላደረግኳት ከተማም ሰላምን ፈልጉ፤ ስለ እሷም ወደ ይሖዋ ጸልዩ፤ እሷ ሰላም ከሰፈነባት እናንተም በሰላም ትኖራላችሁና።+ 8 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “በመካከላችሁ ያሉት ነቢያትና ሟርተኞች አያታሏችሁ፤+ የሚያልሙትንም ሕልም አትስሙ። 9 ‘በስሜ የሚተነብዩላችሁ ሐሰት ነውና። እኔ አልላክኋቸውም’+ ይላል ይሖዋ።”’”

10 “ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘በባቢሎን የምትኖሩበት 70 ዓመት ሲፈጸም ትኩረቴን ወደ እናንተ አዞራለሁ፤+ ወደዚህም ስፍራ መልሼ በማምጣት፣ የገባሁትን ቃል እፈጽማለሁ።’+

11 “‘ለእናንተ የማስበውን ሐሳብ በሚገባ አውቀዋለሁና’ ይላል ይሖዋ፤ ‘ለእናንተ የማስበው ጥፋትን ሳይሆን ሰላምን+ እንዲሁም የተሻለ ሕይወትንና ተስፋን ነው።+ 12 እናንተም ትጠሩኛላችሁ፤ ወደ እኔም ቀርባችሁ ትጸልያላችሁ፤ እኔም እሰማችኋለሁ።’+

13 “‘እኔን ትሻላችሁ፤ በሙሉ ልባችሁ ስለምትፈልጉኝ ታገኙኛላችሁ።+ 14 እኔም እገኝላችኋለሁ’+ ይላል ይሖዋ። ‘በምርኮ የተወሰዱትን ወገኖቻችሁን እሰበስባለሁ፤ እናንተን ከበተንኩባቸው ብሔራትና ቦታዎች ሁሉ እሰበስባችኋለሁ’+ ይላል ይሖዋ። ‘በግዞት እንድትወሰዱ ባደረግኩ ጊዜ ትታችሁት ወደሄዳችሁት ቦታ መልሼ አመጣችኋለሁ።’+

15 “እናንተ ግን ‘ይሖዋ በባቢሎን ነቢያት አስነስቶልናል’ ብላችኋል።

16 “ይሖዋ በዳዊት ዙፋን ላይ ለተቀመጠው ንጉሥና+ በዚህች ከተማ ውስጥ ለሚኖረው ሕዝብ ሁሉ ይኸውም ከእናንተ ጋር በግዞት ላልተወሰዱት ወንድሞቻችሁ እንዲህ ይላልና፦ 17 ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በእነሱ ላይ ሰይፍን፣ ረሃብንና ቸነፈርን* እሰዳለሁ፤+ በጣም መጥፎ ከመሆናቸው የተነሳ ሊበሉ እንደማይችሉ የበሰበሱ* በለሶች አደርጋቸዋለሁ።”’+

18 “‘በሰይፍ፣+ በረሃብና በቸነፈር አሳድዳቸዋለሁ፤ በምድር ላይ ላሉ መንግሥታትም ሁሉ መቀጣጫ አደርጋቸዋለሁ፤+ እነሱን በምበትንባቸው ብሔራት ሁሉ መካከልም ለእርግማን አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ ደግሞም መደነቂያ፣ ማፏጫና+ መሳለቂያ አደርጋቸዋለሁ፤+ 19 ምክንያቱም ደግሜ ደጋግሜ* በላክኋቸው አገልጋዮቼ ይኸውም በነቢያት አማካኝነት ያስተላለፍኩትን ቃል አልሰሙም’+ ይላል ይሖዋ።

“‘ይሁንና እናንተም አልሰማችሁም’+ ይላል ይሖዋ።

20 “ስለዚህ ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን የሰደድኳችሁ እናንተ ግዞተኞች ሁሉ የይሖዋን ቃል ስሙ። 21 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በስሜ የሐሰት ትንቢት ስለሚተነብዩላችሁ+ ስለ ቆላያህ ልጅ ስለ አክዓብና ስለ ማአሴያህ ልጅ ስለ ሴዴቅያስ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር* እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እሱም በፊታችሁ ይገድላቸዋል። 22 በእነሱ ላይ የሚደርሰውንም ነገር በባቢሎን ያሉ የይሁዳ ግዞተኞች ሁሉ እንደ እርግማን ይጠቀሙበታል፤ “ይሖዋ፣ የባቢሎን ንጉሥ በእሳት እንደጠበሳቸው እንደ ሴዴቅያስና እንደ አክዓብ ያድርግህ!” ይላሉ፤ 23 ከባልንጀሮቻቸው ሚስቶች ጋር በማመንዘርና እኔ ያላዘዝኳቸውን ቃል በስሜ በሐሰት በመናገር+ በእስራኤል የሚያሳፍር ድርጊት ፈጽመዋልና።+

“‘“እኔ ይህን አውቃለሁ፤ ለዚህም ነገር ምሥክር ነኝ”+ ይላል ይሖዋ።’”

24 “ኔሄላማዊውን ሸማያህን+ እንዲህ ትለዋለህ፦ 25 ‘የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በኢየሩሳሌም ላሉት ሰዎች ሁሉና ለማአሴያህ ልጅ ለካህኑ ሶፎንያስ+ እንዲሁም ለካህናቱ ሁሉ፣ በገዛ ስምህ እንዲህ ብለህ ደብዳቤዎችን ልከሃልና፦ 26 ‘በይሖዋ ቤት የበላይ ተመልካች እንድትሆን፣ እንደ ነቢይ የሚያደርገውን ማንኛውንም ያበደ ሰው እንድትይዝ እንዲሁም በእግር ግንድ ብሎም በአንገትና በእጅ መጠረቂያ* እንድታስር ይሖዋ በካህኑ በዮዳሄ ምትክ ካህን አድርጎሃል፤+ 27 ታዲያ ነቢይ ነኝ የሚላችሁን የአናቶቱን+ ኤርምያስን ለምን አልገሠጽከውም?+ 28 በባቢሎን ላለነው ሰዎችም እንኳ ሳይቀር እንዲህ የሚል መልእክት ልኮብናል፦ “በግዞት የምትቆዩበት ጊዜ ረጅም ነው! ቤት ሠርታችሁ በዚያ ኑሩ። አትክልት ተክላችሁ ፍሬውን ብሉ፤+ . . .”’”’”

29 ካህኑ ሶፎንያስ+ ይህን ደብዳቤ ነቢዩ ኤርምያስ እየሰማ ባነበበ ጊዜ 30 የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ 31 “በግዞት ወዳሉት ሁሉ እንዲህ የሚል መልእክት ላክ፦ ‘ይሖዋ ስለ ኔሄላማዊው ሸማያህ እንዲህ ይላል፦ “ሸማያህ እኔ ሳልከው ስለተነበየላችሁና በሐሰት እንድትታመኑ ለማድረግ ስለሞከረ፣+ 32 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ትኩረቴን በኔሄላማዊው ሸማያህና በዘሮቹ ላይ አደርጋለሁ።’ በዚህ ሕዝብ መካከል የእሱ ዘር የሆነ አንድም ሰው አይተርፍም፤ ለሕዝቤ የማደርገውንም መልካም ነገር አያይም’ ይላል ይሖዋ፤ ‘በይሖዋ ላይ ዓመፅ አነሳስቷልና።’”’”

30 ከይሖዋ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፦ 2 “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የምነግርህን ቃል ሁሉ በመጽሐፍ ጻፈው። 3 “እነሆ፣ ተማርከው የተወሰዱትን ሕዝቤን፣ እስራኤልንና ይሁዳን የምሰበስብበት ጊዜ ይመጣል”+ ይላል ይሖዋ፤ “ደግሞም ለአባቶቻቸው ወደሰጠኋት ምድር መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ እነሱም ዳግመኛ ይወርሷታል” ይላል ይሖዋ።’”+

4 ይሖዋ ለእስራኤልና ለይሁዳ የተናገረው ቃል ይህ ነው።

 5 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“የሚንቀጠቀጡ ሰዎችን ድምፅ ሰምተናል፤

ሽብር ነግሦአል፤ ሰላምም የለም።

 6 ወንድ፣ መውለድ ይችል እንደሆነ እስቲ ጠይቁ።

ታዲያ ብርቱ የሆነ ወንድ ሁሉ፣

ልትወልድ እንደተቃረበች ሴት+ እጁን ሆዱ* ላይ አድርጎ የማየው ለምንድን ነው?

የሰዉ ሁሉ ፊት የገረጣው ለምንድን ነው?

 7 ወዮ! ያ ቀን አስፈሪ* ነውና።+

በዓይነቱ ልዩ የሆነ ቀን ነው፤

ለያዕቆብ የጭንቅ ጊዜ ይሆናል።

ሆኖም ከዚያ ቀን ይተርፋል።”

8 “በዚያም ቀን፣” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ “ቀንበሩን ከአንገትህ ላይ እሰብራለሁ፤ ማሰሪያህንም እበጥሳለሁ፤ ከእንግዲህ እንግዶች* ባሪያቸው አያደርጉትም።* 9 እነሱም አምላካቸውን ይሖዋንና የማስነሳላቸውን ንጉሣቸውን ዳዊትን ያገለግላሉ።”+

10 “አንተም አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፣ አትፍራ” ይላል ይሖዋ፤

“እስራኤል ሆይ፣ አትሸበር።+

አንተን ከሩቅ አገር፣

ዘርህንም ተማርኮ ከተወሰደበት ምድር እታደጋለሁና።+

ያዕቆብ ይመለሳል፤ ሳይረበሽም ተረጋግቶ ይቀመጣል፤

የሚያስፈራቸው አይኖርም።”+

11 “እኔ አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋር ነኝና” ይላል ይሖዋ።

“አንተን የበተንኩባቸውን ብሔራት ሁሉ ግን ፈጽሞ አጠፋቸዋለሁ፤+

ይሁን እንጂ አንተን ሙሉ በሙሉ አላጠፋህም።+

በተገቢው መጠን እገሥጽሃለሁ* እንጂ

በምንም ዓይነት ሳልቀጣ አልተውህም።”+

12 ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦

“ስብራትሽ ፈውስ የለውም።+

ቁስልሽ የማይድን ነው።

13 የሚሟገትልሽ የለም፤

ቁስልሽ በምንም መንገድ ሊድን አይችልም።

ለአንቺ የሚሆን ፈውስ የለም።

14 አጥብቀው የሚወዱሽ ሁሉ ረስተውሻል።+

ከእንግዲህ አይፈልጉሽም።

ከባድ በደል ስለፈጸምሽና ብዙ ኃጢአት ስለሠራሽ

ጠላት በሚማታበት መንገድ መትቼሻለሁና፤+

እንደ ጨካኝ ቀጥቼሻለሁ።+

15 ከስብራትሽ የተነሳ የምትጮኺው ለምንድን ነው?

ሕመምሽ የማይፈወስ ሆኗል!

ከባድ በደል ስለፈጸምሽና ብዙ ኃጢአት ስለሠራሽ+

ይህን አድርጌብሻለሁ።

16 በእርግጥ የሚውጡሽ ሁሉ ይዋጣሉ፤+

ጠላቶችሽም ሁሉ በምርኮ ይወሰዳሉ።+

የሚዘርፉሽ ሁሉ ይዘረፋሉ፤

የሚበዘብዙሽንም ሁሉ ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጣለሁ።”+

17 “ይሁንና ጤንነትሽን እመልስልሻለሁ፤ ቁስሎችሽንም እፈውሳለሁ”+ ይላል ይሖዋ፤

“እነሱ ግን የተገለለች፣

‘ማንም የማይፈልጋት ጽዮን’ ብለውሻል።”+

18 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“እነሆ፣ ከያዕቆብ ድንኳኖች የተማረኩትን እሰበስባለሁ፤+

ለማደሪያ ድንኳኖቹም እራራለሁ።

ከተማዋ በጉብታዋ ላይ ዳግም ትገነባለች፤+

የማይደፈረውም ማማ በተገቢው ቦታ ላይ ይቆማል።

19 ከእነሱም የምስጋናና የሳቅ ድምፅ ይሰማል።+

እኔ አበዛቸዋለሁ፤ እነሱም ጥቂት አይሆኑም፤+

ቁጥራቸው እንዲጨምር* አደርጋለሁ፤

የተናቁም አይሆኑም።+

20 ወንዶች ልጆቹ እንደቀድሞው ጊዜ ይሆናሉ፤

ጉባኤውም በፊቴ ጸንቶ ይመሠረታል።+

እሱን በሚጨቁኑት ሁሉ ላይ ትኩረቴን አደርጋለሁ።+

21 ታላቅ ግርማ የተላበሰው መሪ ከራሱ ወገን ይገኛል፤

ገዢውም ከመካከሉ ይወጣል።

ወደ እኔ እንዲቀርብ እፈቅድለታለሁ፤ እሱም ወደ እኔ ይቀርባል።”

“አለዚያ ወደ እኔ ለመቅረብ የሚደፍር* ማን ነው?” ይላል ይሖዋ።

22 “እናንተም ሕዝቤ ትሆናላችሁ፤+ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ።”+

23 እነሆ፣ የይሖዋ አውሎ ነፋስ በታላቅ ቁጣ ይነሳል፤+

በክፉዎች ራስ ላይ እየተሽከረከረ የሚወርድ ኃይለኛ ነፋስ ይነፍሳል።

24 ይሖዋ የልቡን ሐሳብ ሳያከናውንና ሳይፈጽም፣

የሚነደው ቁጣው አይመለስም።+

በዘመኑ መጨረሻ ይህን ትረዳላችሁ።+

31 “በዚያን ጊዜ” ይላል ይሖዋ፣ “ለእስራኤል ወገኖች ሁሉ አምላክ እሆናለሁ፤ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።”+

 2 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“እስራኤል ወደ ማረፊያ ቦታው በሄደ ጊዜ፣

ከሰይፍ የተረፉት ሰዎች በምድረ በዳ የአምላክን ሞገስ አገኙ።”

 3 ይሖዋ ከሩቅ ተገለጠልኝ፤ እንዲህም አለኝ፦

“በዘላለማዊ ፍቅር ወድጄሻለሁ።

ከዚህም የተነሳ በታማኝ ፍቅር ወደ እኔ ሳብኩሽ።*+

 4 አሁንም መልሼ እገነባሻለሁ፤ አንቺም ዳግመኛ ትገነቢያለሽ።+

የእስራኤል ድንግል ሆይ፣ አታሞዎችሽን እንደገና አንስተሽ

በደስታ እየጨፈርሽ* ትወጫለሽ።+

 5 በሰማርያ ተራሮች ላይ እንደገና የወይን ተክሎችን ትተክያለሽ፤+

አትክልተኞቹ ይተክላሉ፤ ፍሬውንም ይበላሉ።+

 6 በኤፍሬም ተራሮች የሚገኙ ጠባቂዎች

‘ተነሱ፤ ወደ ጽዮን፣ ወደ አምላካችን ወደ ይሖዋ እንውጣ’ ብለው የሚጮኹበት ቀን ይመጣልና።”+

 7 ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦

“በታላቅ ደስታ ወደ ያዕቆብ ጩኹ።

ከብሔራት በላይ ስለሆናችሁ እልል በሉ።+

ይህን አውጁ፤ ውዳሴ አቅርቡ፤

ደግሞም ‘ይሖዋ ሆይ፣ ሕዝብህን፣ የእስራኤልን ቀሪዎች አድን’ በሉ።+

 8 ከሰሜን ምድር መልሼ አመጣቸዋለሁ።+

ከምድር ዳርቻዎች እሰበስባቸዋለሁ።+

በመካከላቸው ዓይነ ስውርና አንካሳ፣+

ነፍሰ ጡርና ልትወልድ የተቃረበች ሴት በአንድነት ይገኛሉ።

ታላቅ ጉባኤ ሆነው ወደዚህ ይመለሳሉ።+

 9 እያለቀሱ ይመጣሉ።+

ሞገስ ለማግኘት ሲለምኑ እየመራሁ አመጣቸዋለሁ።

ወደ ውኃ ጅረቶች* እመራቸዋለሁ፤+

በማይሰናከሉበት ደልዳላ መንገድ እወስዳቸዋለሁ።

እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፤ ኤፍሬምም የበኩር ልጄ ነው።”+

10 እናንተ ብሔራት፣ የይሖዋን ቃል ስሙ፤

ርቀው በሚገኙ ደሴቶችም ቃሉን አውጁ፦+

“እስራኤልን የበተነው እሱ ይሰበስበዋል።

መንጋውን እንደሚጠብቅ እረኛ ይጠብቀዋል።+

11 ይሖዋ ያዕቆብን ይዋጀዋልና፤+

ከእሱም ከሚበረታው እጅ ይታደገዋል።*+

12 እነሱም መጥተው በጽዮን ከፍ ያለ ቦታ በደስታ እልል ይላሉ፤+

ደግሞም በይሖዋ ጥሩነት፣*

በእህሉ፣ በአዲሱ የወይን ጠጅ፣+ በዘይቱ

እንዲሁም በመንጎቹ ግልገሎችና በከብቶቹ ጥጆች የተነሳ ፊታቸው ይፈካል።+

ውኃ እንደጠገበ የአትክልት ቦታ ይሆናሉ፤*+

ከእንግዲህም ወዲህ አይደክሙም።”+

13 “በዚያን ጊዜ ድንግሊቱ በደስታ ትጨፍራለች፤

ወጣቶቹና ሽማግሌዎቹም በአንድነት በደስታ ይጨፍራሉ።+

ሐዘናቸውን ወደ ሐሴት እለውጠዋለሁ።+

ከሐዘናቸው ተላቀው እንዲጽናኑና ደስ እንዲሰኙ አደርጋለሁ።+

14 ካህናቱን* በተትረፈረፈ ምግብ* አጠግባለሁ፤

ሕዝቤም በጥሩነቴ ይረካል”+ ይላል ይሖዋ።

15 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

‘የዋይታና የመራራ ለቅሶ ድምፅ በራማ+ ተሰማ፦

ራሔል ስለ ወንዶች ልጆቿ* አለቀሰች።+

ወንዶች ልጆቿ ስለሌሉ

ከደረሰባት ሐዘን ለመጽናናት እንቢ አለች።’”+

16 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“‘አታልቅሺ፤ ዓይኖችሽም እንባ አያፍስሱ፤

ሥራሽ ወሮታ አለውና’ ይላል ይሖዋ።

‘ከጠላት ምድር ይመለሳሉ።’+

17 ‘አንቺም ብሩህ ተስፋ ይጠብቅሻል’+ ይላል ይሖዋ።

‘ወንዶች ልጆችሽ ወደ ገዛ ምድራቸው ይመለሳሉ።’”+

18 “የኤፍሬምን ሲቃ በእርግጥ ሰምቻለሁ፤

‘እንዳልተገራ ጥጃ አረምከኝ፤

እኔም ታረምኩ።

መልሰኝ፤ እኔም ወዲያውኑ እመለሳለሁ፤

አንተ አምላኬ ይሖዋ ነህና።

19 ከተመለስኩ በኋላ ተጸጽቻለሁና፤+

እንዳስተውል ከተደረግኩ በኋላ በሐዘን ጭኔን መታሁ።

አፈርኩ፤ ተዋረድኩም፤+

በወጣትነቴ የደረሰብኝን ነቀፋ ተሸክሜአለሁና።’”

20 “ኤፍሬም ከፍ አድርጌ የምመለከተው ውድ ልጄ አይደለም?+

ብዙ ጊዜ እሱን ተቃውሜ የምናገረውን ያህል፣ አሁንም አስበዋለሁና።

አንጀቴ ለእሱ የሚንሰፈሰፈው ለዚህ ነው።+

ደግሞም እራራለታለሁ” ይላል ይሖዋ።+

21 “የጎዳና ምልክቶችን ለራስሽ አቁሚ፤

መንገድ የሚጠቁሙ ዓምዶችን ትከዪ።+

የምትሄጂበትን አውራ ጎዳና ልብ ብለሽ ተመልከቺ።+

የእስራኤል ድንግል ሆይ፣ ተመለሽ፤ የራስሽ ወደሆኑት ወደነዚህ ከተሞች ተመለሽ።

22 ከዳተኛዪቱ ሴት ልጅ ሆይ፣ የምትወላውዪው እስከ መቼ ድረስ ነው?

ይሖዋ በምድር ላይ አዲስ ነገር ፈጥሯልና፦

ሴት ወንድን አጥብቃ ታሳድዳለች።”

23 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የተማረኩባቸውን ሰዎች በምሰበስብበት ጊዜ በይሁዳ ምድርና በከተሞቹ ‘አንተ ጻድቅ መኖሪያ፣+ አንተ ቅዱስ ተራራ፣+ ይሖዋ ይባርክህ’ የሚል ቃል እንደገና ይናገራሉ። 24 በእሷም ውስጥ ይሁዳና ከተሞቹ ሁሉ እንዲሁም ገበሬዎችና የመንጋ እረኞች በአንድነት ይኖራሉ።+ 25 የዛለውን* አድሳለሁና፤ የደከመውንም* ሁሉ አበረታለሁ።”+

26 በዚህ ጊዜ ነቃሁ፤ ዓይኔንም ገለጥኩ፤ እንቅልፌም ጣፋጭ ሆኖልኝ ነበር።

27 “እነሆ፣ በእስራኤል ቤትና በይሁዳ ቤት የሰውን ዘርና የከብትን ዘር የምዘራበት ጊዜ ይመጣል” ይላል ይሖዋ።+

28 “እነሱን ለመንቀል፣ ለማፍረስ፣ ለማውደም፣ ለማጥፋትና ለመደምሰስ እከታተላቸው እንደነበረ ሁሉ፣+ እነሱን ለመገንባትና ለመትከልም እከታተላቸዋለሁ”+ ይላል ይሖዋ። 29 “በዚያም ዘመን ‘የሚጎመዝዝ ወይን የበሉት አባቶች ሆነው ሳለ የልጆቹ ጥርስ ጠረሰ’*+ ብለው ዳግመኛ አይናገሩም። 30 ከዚህ ይልቅ በዚያ ጊዜ እያንዳንዱ ሰው በገዛ በደሉ ይሞታል። የሚጎመዝዝ ወይን የሚበላ ሰው ሁሉ፣ የገዛ ራሱ ጥርስ ይጠርሳል።”

31 “እነሆ፣ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ጊዜ ይመጣል” ይላል ይሖዋ።+ 32 “ይህም ቃል ኪዳን አባቶቻቸውን እጃቸውን ይዤ ከግብፅ ምድር እየመራሁ ባወጣኋቸው ቀን ከእነሱ ጋር እንደገባሁት ዓይነት ቃል ኪዳን አይሆንም፤+ ‘እኔ እውነተኛ ጌታቸው* ብሆንም እንኳ እነሱ ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋል’ ይላል ይሖዋ።”+

33 “ከዚያ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና” ይላል ይሖዋ። “ሕጌን በውስጣቸው አኖራለሁ፤+ በልባቸውም እጽፈዋለሁ።+ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።”+

34 “እነሱም እያንዳንዳቸው ባልንጀራቸውን፣ እያንዳንዳቸውም ወንድማቸውን ‘ይሖዋን እወቅ!’ ብለው ከእንግዲህ አያስተምሩም፤+ ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ ሁሉም ያውቁኛልና”+ ይላል ይሖዋ። “በደላቸውን ይቅር እላለሁና፤ ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ አላስታውስም።”+

35 ስሙ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ የሆነው፣

በቀን እንድታበራ ፀሐይን የሰጠው፣

በሌሊትም እንዲያበሩ የጨረቃንና የከዋክብትን ሕጎች ያወጣው፣*

ባሕሩን የሚያናውጠውና ኃይለኛ ማዕበል የሚያስነሳው

ይሖዋ እንዲህ ይላል፦+

36 “‘የእስራኤል ዘር ምንጊዜም በፊቴ የሚኖር ብሔር መሆኑ የሚያከትመው’ ይላል ይሖዋ፣

‘ይህ ሥርዓት ከተሻረ ብቻ ነው።’”+

37 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “‘መላውን የእስራኤል ዘር፣ በሠሩት ነገር ሁሉ የተነሳ ልተዋቸው የምችለው፣ በላይ ያሉትን ሰማያት መለካት፣ በታች ያሉትንም የምድር መሠረቶች መመርመር የሚቻል ከሆነ ብቻ ነው’ ይላል ይሖዋ።”+

38 “እነሆ፣ ከተማዋ ከሃናንኤል ማማ+ እስከ ማዕዘን በር+ ድረስ ለይሖዋ የምትገነባበት ጊዜ ይመጣል”+ ይላል ይሖዋ። 39 “የመለኪያ ገመዱም+ በቀጥታ ወደ ጋሬብ ኮረብታ ይዘረጋል፤ ደግሞም ወደ ጎዓ ይዞራል። 40 ሬሳና አመድ* ያለበት ሸለቆ* ሁሉ እንዲሁም የቄድሮንን ሸለቆ+ ይዞ በምሥራቅ በኩል እስካለው እስከ ፈረስ በር+ ማዕዘን ድረስ ያለው ደልዳላ ቦታ ሁሉ ለይሖዋ የተቀደሰ ይሆናል።+ ከእንግዲህ ወዲህ አይነቀልም ወይም አይወድምም።”

32 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በነገሠ በ10ኛው ዓመት ይኸውም ናቡከደነጾር* በነገሠ በ18ኛው ዓመት ወደ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው።+ 2 በዚያን ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት ኢየሩሳሌምን ከቦ ነበር፤ ነቢዩ ኤርምያስም በይሁዳ ንጉሥ ቤት፣* በክብር ዘቦቹ ግቢ+ ታስሮ ነበር። 3 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ እንዲህ በማለት አስሮት ነበርና፦+ “እንዲህ ብለህ ትንቢት የምትናገረው ለምንድን ነው? አንተ እንዲህ ትላለህ፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ይህችን ከተማ በባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣታለሁ፤ እሱም ይይዛታል፤+ 4 የይሁዳም ንጉሥ ሴዴቅያስ ከከለዳውያን እጅ አያመልጥም፤ ያላንዳች ጥርጥር በባቢሎን ንጉሥ እጅ አልፎ ይሰጣል፤ ከንጉሡም ጋር ፊት ለፊት ይነጋገራል፤ በዓይኖቹም ያየዋል።”’+ 5 ‘ሴዴቅያስን ወደ ባቢሎን ይወስደዋል፤ ትኩረቴን ወደ እሱ እስካዞር ድረስም በዚያ ይቆያል’ ይላል ይሖዋ። ‘ከከለዳውያን ጋር መዋጋታችሁን ብትቀጥሉም እንኳ አይሳካላችሁም።’”+

6 ኤርምያስ እንዲህ አለ፦ “የይሖዋ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ 7 ‘እነሆ፣ የአጎትህ* የሻሉም ልጅ ሃናምኤል ወደ አንተ መጥቶ “የመቤዠት መብት ያለህ የመጀመሪያው ሰው አንተ ስለሆንክ+ በአናቶት+ የሚገኘውን መሬቴን ለራስህ ግዛው” ይልሃል።’”

8 ይሖዋ በተናገረው መሠረት የአጎቴ ልጅ ሃናምኤል እኔ ወዳለሁበት ወደ ክብር ዘቦቹ ግቢ መጥቶ እንዲህ አለኝ፦ “በቢንያም አገር፣ በአናቶት የሚገኘውን መሬቴን እባክህ ግዛኝ፤ የመውረስና የመቤዠት መብት ያለህ አንተ ነህና። ስለዚህ መሬቱን ለራስህ ግዛው።” ይህ የሆነው ይሖዋ በተናገረው ቃል መሠረት እንደሆነ ተረዳሁ።

9 በመሆኑም በአናቶት ያለውን መሬት ከአጎቴ ልጅ ከሃናምኤል ላይ ገዛሁ። እኔም ሰባት ሰቅልና* አሥር የብር ሰቅል ገንዘብ መዝኜ ሰጠሁት።+ 10 ከዚያም የውል ሰነድ+ ካዘጋጀሁ በኋላ በማኅተም አሸግኩት፤ ምሥክሮችንም ጠርቼ+ ገንዘቡን በሚዛን መዘንኩ። 11 በመመሪያውና በሕጉ መሠረት የታሸገውን እንዲሁም ያልታሸገውን የግዢውን የውል ሰነድ ወሰድኩ፤ 12 ከዚያም የግዢውን የውል ሰነድ በአጎቴ ልጅ በሃናምኤል፣ በግዢው ውል ላይ በፈረሙት ምሥክሮች እንዲሁም በክብር ዘቦቹ ግቢ+ ተቀምጠው በነበሩት አይሁዳውያን ሁሉ ፊት ለማህሴያህ ልጅ፣ ለነሪያህ+ ልጅ ለባሮክ+ ሰጠሁት።

13 ባሮክንም በእነሱ ፊት እንዲህ ብዬ አዘዝኩት፦ 14 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነዚህን የውል ሰነዶች፣ የታሸገውንም ሆነ ያልታሸገውን የግዢ የውል ሰነድ ወስደህ ለረጅም ጊዜ እንዲቆዩ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አስቀምጣቸው።’ 15 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘በዚህች ምድር፣ ቤቶችና የእርሻ ቦታዎች እንዲሁም የወይን እርሻዎች እንደገና ይገዛሉ።’”+

16 የግዢውን የውል ሰነድ ለነሪያህ ልጅ ለባሮክ ከሰጠሁት በኋላ እንዲህ ብዬ ወደ ይሖዋ ጸለይኩ፦ 17 “አቤቱ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ! እነሆ፣ አንተ ሰማያትንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ሠርተሃል።+ አንተ ምንም የሚሳንህ ነገር የለም፤ 18 ለሺዎች ታማኝ ፍቅር ታሳያለህ፤ ይሁንና የአባቶችን በደል ከእነሱ በኋላ በሚመጡት ልጆቻቸው ላይ* ትመልሳለህ፤+ አንተ እውነተኛ፣ ታላቅና ኃያል አምላክ ነህ፤ ስምህም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ነው። 19 በምክር ታላቅ፣* በሥራም ኃያል ነህ፤+ ለእያንዳንዱ እንደ መንገዱና እንደ ሥራው ለመክፈል+ ዓይኖችህ የሰው ልጆችን መንገዶች ሁሉ ያያሉ።+ 20 እስከ ዛሬ ድረስ የሚነገርላቸውን ምልክቶችና ተአምራት በግብፅ ምድር አደረግክ፤ በዚህም መንገድ አሁን እየሆነ እንዳለው ሁሉ በእስራኤልና በሰው ልጆች መካከል ለራስህ ስም አተረፍክ።+ 21 ሕዝብህን እስራኤልን በምልክቶች፣ በተአምራት፣ በኃያል እጅ፣ በተዘረጋች ክንድና አስፈሪ በሆኑ ክንውኖች ከግብፅ ምድር አወጣህ።+

22 “ከጊዜ በኋላም ለአባቶቻቸው ለመስጠት የማልክላቸውን+ ወተትና ማር የምታፈሰውን ይህችን ምድር ሰጠሃቸው።+ 23 እነሱም ገብተው ምድሪቱን ወረሷት፤ ሆኖም ቃልህን አልታዘዙም ወይም በሕግህ አልተመላለሱም። እንዲያደርጉ ያዘዝካቸውን ነገር ሁሉ አላደረጉም፤ ከዚህም የተነሳ ይህን ሁሉ ጥፋት በላያቸው አመጣህ።+ 24 እነሆ፣ ከተማዋን ለመያዝ ሰዎች በዙሪያዋ የአፈር ቁልል ደልድለዋል፤+ ከሰይፉ፣+ ከረሃቡና ከቸነፈሩ*+ የተነሳ ከተማዋ እየወጓት ባሉት ከለዳውያን እጅ መውደቋ አይቀርም፤ አሁን እንደምታየው አንተ ያልከው ሁሉ ተፈጽሟል። 25 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን ከተማዋ በከለዳውያን እጅ መውደቋ የማይቀር ቢሆንም ‘መሬቱን ለራስህ በምሥክሮች ፊት በገንዘብ ግዛ’ አልከኝ።”

26 በዚህ ጊዜ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ 27 “እነሆ፣ እኔ የሰው ዘር* ሁሉ አምላክ፣ ይሖዋ ነኝ። ለመሆኑ እኔ የሚሳነኝ ነገር አለ? 28 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ይህችን ከተማ ለከለዳውያንና ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾር* እሰጣታለሁ፤ እሱም ይይዛታል።+ 29 ይህችን ከተማ የሚወጓት ከለዳውያንም ይገባሉ፤ በእሳትም ያቃጥሏታል፤+ ደግሞም ከተማዋን እንዲሁም ሕዝቡ እኔን ለማስቆጣት ሲሉ በጣሪያዎቻቸው ላይ ለባአል መሥዋዕቶች ያቀረቡባቸውንና ለሌሎች አማልክት የመጠጥ መባ ያፈሰሱባቸውን ቤቶች+ በእሳት ያቃጥሏቸዋል።’

30 “‘የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ ከልጅነታቸው ጀምሮ በፊቴ ክፉ የሆነውን ነገር ብቻ አድርገዋልና፤+ የእስራኤል ሕዝብ በእጃቸው ሥራ እኔን ማስቆጣታቸውን አልተዉም’ ይላል ይሖዋ። 31 ‘ይህች ከተማ ከገነቧት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ ቁጣዬንና ንዴቴን ከማነሳሳት በስተቀር ምንም የፈየደችው ነገር የለም፤+ በመሆኑም ከፊቴ አስወግዳታለሁ፤+ 32 ይህም የሆነው የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ ይኸውም እነሱ፣ ነገሥታታቸው፣+ መኳንንታቸው፣+ ካህናታቸው፣ ነቢያታቸው፣+ የይሁዳ ሰዎችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እኔን ለማስቆጣት በሠሩት ክፉ ነገር ሁሉ የተነሳ ነው። 33 ለእኔ ፊታቸውን ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጡ፤+ ደግሜ ደጋግሜ* ላስተምራቸው ብሞክርም፣ አንዳቸውም ተግሣጼን ለመቀበል ፈቃደኛ አይደሉም።+ 34 ስሜ የተጠራበትንም ቤት ለማርከስ አስጸያፊ ጣዖቶቻቸውን በዚያ አስቀመጡ።+ 35 በተጨማሪም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለሞሎክ በእሳት አሳልፈው ለመስጠት በሂኖም ልጅ ሸለቆ*+ ያሉትን የባአልን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች ሠርተዋል፤+ ይሁዳን ኃጢአት ለማሠራት ይህን አስጸያፊ ነገር እንዲፈጽሙ እኔ አላዘዝኩም፤+ ፈጽሞም በልቤ አላሰብኩም።’*

36 “ስለዚህ እናንተ በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር ለባቢሎን ንጉሥ አልፋ ትሰጣለች ስለምትሏት ስለዚህች ከተማ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ 37 ‘እነሆ፣ እነሱን በመዓቴና በታላቅ ቁጣዬ ከበተንኩባቸው አገሮች ሁሉ አንድ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፤+ ወደዚህም ቦታ መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ ያለስጋት እንዲኖሩም አደርጋለሁ።+ 38 እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።+ 39 ለእነሱም ሆነ ከእነሱ በኋላ ለሚመጡት ልጆቻቸው መልካም ይሆንላቸው ዘንድ ዘወትር እኔን እንዲፈሩ+ አንድ ልብና አንድ መንገድ እሰጣቸዋለሁ።+ 40 ደግሞም ለእነሱ መልካም ነገር ከማድረግ እንዳልቆጠብ+ ከእነሱ ጋር ዘላለማዊ ቃል ኪዳን እገባለሁ፤+ ከእኔም እንዳይርቁ በልባቸው ውስጥ እኔን የመፍራት መንፈስ አሳድራለሁ።+ 41 ለእነሱ መልካም በማድረግ እጅግ ደስ እሰኛለሁ፤+ በሙሉ ልቤና በሙሉ ነፍሴም* በዚህች ምድር ላይ አጽንቼ እተክላቸዋለሁ።’”+

42 “ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘በዚህ ሕዝብ ላይ ይህን ሁሉ ታላቅ ጥፋት እንዳመጣሁ፣ ልክ እንዲሁ ቃል የገባሁላቸውን መልካም ነገር ሁሉ አመጣላቸዋለሁ።+ 43 እናንተ “ሰውም ሆነ እንስሳ የማይኖርባት ጠፍ መሬት ናት፤ ለከለዳውያንም ተሰጥታለች” ብትሉም በዚህች ምድር ላይ እንደገና መሬት ይገዛል።’+

44 “‘ተማርከው የተወሰዱባቸውን ሰዎች መልሼ ስለማመጣቸው፣+ በቢንያም አገር፣ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ባሉ ቦታዎች፣ በይሁዳ ከተሞች፣+ በተራራማው ምድር ባሉ ከተሞች፣ በዝቅተኛው ስፍራ ባሉ ከተሞችና+ በደቡብ በሚገኙ ከተሞች መሬት በገንዘብ ይገዛል፤ የግዢ ውል ተዘጋጅቶ በማኅተም ይታሸጋል፤ ምሥክሮችም ይጠራሉ’+ ይላል ይሖዋ።”

33 ኤርምያስ በክብር ዘቦቹ ግቢ+ ታስሮ ሳለ የይሖዋ ቃል ለሁለተኛ ጊዜ እንዲህ ሲል ወደ እሱ መጣ፦ 2 “ምድርን የሠራት ይሖዋ፣ አዎ፣ ያበጃትና አጽንቶ የመሠረታት ይሖዋ እንዲህ ይላል፤ ስሙ ይሖዋ ነው፤ 3 ‘ጥራኝ፤ እኔም እመልስልሃለሁ፤ አንተ የማታውቀውን ታላቅና ለመረዳት አዳጋች የሆነ ነገር ወዲያውኑ እነግርሃለሁ።’”+

4 “እኔ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ፣ በዙሪያዋ በተደለደለው የአፈር ቁልልና በሰይፍ የተነሳ ስለፈረሱት የዚህች ከተማ ቤቶችና የይሁዳ ነገሥታት ቤቶች እንዲህ እላለሁ፤+ 5 ደግሞም ከከለዳውያን ጋር ሊዋጉ የሚመጡትን ሰዎች እንዲሁም ከክፋታቸው የተነሳ ፊቴን ከዚህች ከተማ እንድሰውር ባደረጉኝና በታላቅ ቁጣዬ በመታኋቸው ሰዎች ሬሳ የሚሞሉትን ቦታዎች በተመለከተ እንዲህ እላለሁ፦ 6 ‘እነሆ፣ ከተማዋ እንድታገግም አደርጋለሁ፤ ጤናም እሰጣታለሁ፤+ እኔም እፈውሳቸዋለሁ እንዲሁም የተትረፈረፈ ሰላምና እውነት እሰጣቸዋለሁ።+ 7 ከይሁዳ የተማረኩትንና ከእስራኤል የተማረኩትን እመልሳለሁ፤+ እንደቀድሞውም እገነባቸዋለሁ።+ 8 እኔንም ከበደሉበት ኃጢአት ሁሉ አነጻቸዋለሁ፤+ በእኔ ላይ የሠሩትን ኃጢአትና በደል ሁሉ ይቅር እላለሁ።+ 9 እሷም የማደርግላቸውን መልካም ነገር በሙሉ በሚሰሙ የምድር ብሔራት ሁሉ ፊት የሐሴት ስም፣ ውዳሴና ውበት ትሆንልኛለች።+ በማደርግላት መልካም ነገር ሁሉና በምሰጣት ሰላም ሁሉ የተነሳ በፍርሃት ይርዳሉ፤ ይንቀጠቀጣሉም።’”+

10 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሰውም ሆነ ከብት የማይኖርበት ጠፍ መሬት በምትሉት በዚህ ቦታ እንዲሁም ሰው ወይም ነዋሪ ወይም ከብት በሌለባቸው ወና የሆኑ የይሁዳ ከተሞችና የኢየሩሳሌም ጎዳናዎች እንደገና ድምፅ ይሰማል፤ 11 አዎ፣ የሐሴት ድምፅ፣ የደስታ ድምፅ፣+ የሙሽራና የሙሽሪት ድምፅ እንዲሁም “ይሖዋ ጥሩ ስለሆነ+ የሠራዊት ጌታ ይሖዋን አመስግኑ፤ ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል!”+ የሚሉ ሰዎች ድምፅ ይሰማል።’

“‘ቀድሞ እንደነበረው ከምድሪቱ ተማርከው የተወሰዱትን ስለምመልስ ወደ ይሖዋ ቤት የምሥጋና መባዎች ይዘው ይመጣሉ’+ ይላል ይሖዋ።”

12 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሰው ወይም ከብት በሌለበት በዚህ ጠፍ መሬት እንዲሁም በከተሞቹ ሁሉ እረኞች መንጎቻቸውን የሚያሳርፉበት የግጦሽ መሬት ዳግመኛ ያገኛሉ።’+

13 “‘በተራራማው ምድር በሚገኙ ከተሞች፣ በዝቅተኛው ስፍራ በሚገኙ ከተሞች፣ በደቡብ ባሉ ከተሞች፣ በቢንያም አገር፣ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ባሉ ቦታዎችና+ በይሁዳ ከተሞች፣+ እረኞች በጎቻቸውን የሚቆጥሩበት ጊዜ ዳግመኛ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ።”

14 “‘እነሆ፣ ስለ እስራኤል ቤትና ስለ ይሁዳ ቤት የገባሁትን የተስፋ ቃል የምፈጽምበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ።+ 15 ‘በዚያ ዘመንና በዚያ ጊዜ ለዳዊት ቀንበጥ* ይኸውም ጻድቅ ቀንበጥ አበቅላለሁ፤+ እሱም በምድሪቱ ላይ ፍትሕንና ጽድቅን ያሰፍናል።+ 16 በዚያ ዘመን ይሁዳ ትድናለች፤+ ኢየሩሳሌምም ያለስጋት ትቀመጣለች።+ እሷም “ይሖዋ ጽድቃችን ነው” ተብላ ትጠራለች።’”+

17 “ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘ከዳዊት ዘር፣ በእስራኤል ቤት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ፈጽሞ አይታጣም፤+ 18 ከሌዋውያን ካህናትም መካከል ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችን ለማቅረብ፣ የእህል መባዎችን ለማቃጠልና መሥዋዕቶችን ለማቅረብ በፊቴ የሚቆም ሰው ጨርሶ አይታጣም።’”

19 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ 20 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ቀንና ሌሊት በተወሰነላቸው ጊዜ እንዳይፈራረቁ፣ የቀን ቃል ኪዳኔንና የሌሊት ቃል ኪዳኔን ማፍረስ የምትችሉ ከሆነ፣+ 21 ያን ጊዜ ከአገልጋዬ ከዳዊት ጋር የገባሁት ቃል ኪዳኔ ሊፈርስ ይችላል፤+ ያን ጊዜ በዙፋኑ ላይ የሚነግሥ ልጅ አይኖረውም፤+ አገልጋዮቼ ከሆኑት ከሌዋውያን ካህናት+ ጋር የገባሁት ቃል ኪዳንም ይፈርሳል። 22 የሰማያት ሠራዊት ሊቆጠር፣ የባሕርም አሸዋ ሊሰፈር እንደማይችል ሁሉ የአገልጋዬን የዳዊትን ዘርና አገልጋዮቼን ሌዋውያንን እንዲሁ አበዛቸዋለሁ።’”

23 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ 24 “እነዚህ ሰዎች፣ ‘ይሖዋ የመረጣቸውን ሁለቱን ወገኖች ይተዋቸዋል’ እንደሚሉ አላስተዋልክም? የገዛ ሕዝቤንም ይንቃሉ፤ እነሱን እንደ ብሔር አድርገው መመልከት አቁመዋል።

25 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የቀንና የሌሊት ቃል ኪዳኔን ማቋቋሜ+ እንዲሁም የሰማይንና የምድርን ሕግ* መደንገጌ የተረጋገጠ እንደሆነ ሁሉ፣+ 26 በአብርሃም፣ በይስሐቅና በያዕቆብ ልጆች* ላይ የሚነግሡ ገዢዎች ከዘሩ እንዳይታጡ የያዕቆብንና የአገልጋዬን የዳዊትን ዘር ፈጽሞ አልጥልም። ተማርከው የተወሰዱባቸውን መልሼ እሰበስባለሁና፤+ ርኅራኄም አሳያቸዋለሁ።’”+

34 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር፣* ሠራዊቱ ሁሉ፣ በእሱ ግዛት ሥር ያሉ የምድር መንግሥታት ሁሉ እንዲሁም ሕዝቡ ሁሉ ኢየሩሳሌምንና በዙሪያዋ ያሉትን ከተሞች በሙሉ እየወጉ ሳሉ ወደ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው፦+

2 “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሂድና የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን+ አናግረው፤ እንዲህም በለው፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ይህችን ከተማ ለባቢሎን ንጉሥ አሳልፌ እሰጣታለሁ፤ እሱም በእሳት ያቃጥላታል።+ 3 አንተም ከእጁ አታመልጥም፤ ያለጥርጥር ትያዛለህና፤ በእጁም አልፈህ ትሰጣለህ።+ የባቢሎንንም ንጉሥ በዓይኖችህ ታየዋለህ፤ ፊት ለፊትም ያነጋግርሃል፤ ወደ ባቢሎንም ትወሰዳለህ።’+ 4 ይሁንና የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ሆይ፣ የይሖዋን ቃል ስማ፤ ‘ይሖዋ ስለ አንተ እንዲህ ይላል፦ “በሰይፍ አትሞትም። 5 በሰላም ትሞታለህ፤+ ለአባቶችህ ይኸውም ከአንተ ቀድሞ ለነበሩት ነገሥታት እንዳደረጉት ለክብርህ እሳት ያነዱልሃል፤ ‘ወዮ፣ ጌታችን!’ እያሉም ያለቅሱልሃል፤ ‘እኔ ይህን ቃል ተናግሬአለሁና’ ይላል ይሖዋ።”’”’”

6 ከዚያም ነቢዩ ኤርምያስ በኢየሩሳሌም ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስ ይህን ሁሉ ቃል ነገረው፤ 7 በዚህ ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት ኢየሩሳሌምንና የቀሩትን የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ይኸውም ለኪሶንና+ አዜቃን+ እየወጋ ነበር፤+ ከይሁዳ ከተሞች መካከል ድል ሳይደረጉ የቀሩት እነዚህ የተመሸጉ ከተሞች ብቻ ነበሩና።

8 ንጉሥ ሴዴቅያስ ነፃነት ለማወጅ+ በኢየሩሳሌም ከነበረው ሕዝብ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን ከገባ በኋላ የይሖዋ ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ፤ 9 ቃል ኪዳኑ፣ እያንዳንዱ ሰው ዕብራውያን የሆኑ ወንድና ሴት ባሪያዎቹን በነፃ እንዲለቅ፣ ደግሞም ማንኛውም ሰው ወገኑ የሆነውን አይሁዳዊ፣ ባሪያው አድርጎ እንዳያሠራ የሚያዝዝ ነበር። 10 በመሆኑም መኳንንቱና ሕዝቡ ሁሉ እንደተባሉት አደረጉ። እያንዳንዳቸው ወንድና ሴት ባሪያዎቻቸውን በነፃ ለመልቀቅና ከዚያ በኋላ ባሪያ አድርገው ላለማሠራት ቃል ኪዳን ገቡ። እንደተባሉት በማድረግ ባሪያዎቻቸውን አሰናበቷቸው። 11 በኋላ ግን ነፃ ለቀዋቸው የነበሩትን ወንድና ሴት ባሪያዎቻቸውን መለሷቸው፤ እንደገናም አስገድደው በባርነት ገዟቸው። 12 ስለዚህ የይሖዋ ቃል ከይሖዋ ዘንድ እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦

13 “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አባቶቻችሁን ከግብፅ ምድር፣ ከባርነት ቤት ባወጣኋቸው ጊዜ+ እንዲህ ስል ከእነሱ ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ፦+ 14 “እያንዳንዳችሁ የተሸጠላችሁንና ስድስት ዓመት ሲያገለግላችሁ የቆየውን ዕብራዊ የሆነውን ወንድማችሁን በሰባተኛው ዓመት ማብቂያ ላይ ልቀቁት፤ በነፃ ልታሰናብቱት ይገባል።”+ አባቶቻችሁ ግን አልሰሙኝም ወይም ጆሯቸውን አልሰጡኝም። 15 እናንተም በቅርቡ* ተመልሳችሁ ለወገኖቻችሁ ነፃነት በማወጅ በፊቴ ትክክል የሆነውን ነገር አደረጋችሁ፤ ስሜ በተጠራበትም ቤት በፊቴ ቃል ኪዳን ገባችሁ። 16 በኋላ ግን ሐሳባችሁን ቀይራችሁ፣ እንደ ፍላጎታቸው* በነፃ የለቀቃችኋቸውን ወንድና ሴት ባሪያዎቻችሁን መልሳችሁ በማምጣት ስሜን አረከሳችሁ፤+ አስገድዳችሁም ወደ ባርነት መለሳችኋቸው።’

17 “ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እያንዳንዳችሁ ለወንድማችሁና ለወገናችሁ ነፃነት በማወጅ አልታዘዛችሁኝም።+ በመሆኑም እኔ ለእናንተ ያወጅኩት ነፃነት ይህ ነው’ ይላል ይሖዋ፤ ‘በሰይፍ፣ በቸነፈርና* በረሃብ ታልቃላችሁ፤+ ለምድር መንግሥታትም ሁሉ መቀጣጫ አደርጋችኋለሁ።+ 18 ጥጃውን ሁለት ቦታ ከፍለው በመካከሉ ባለፉ ጊዜ በፊቴ የገቡትን ቃል ኪዳን+ ባለማክበር ቃል ኪዳኔን የጣሱት ሰዎች የሚደርስባቸው ነገር ይህ ነው፤ 19 ይኸውም የይሁዳ መኳንንት፣ የኢየሩሳሌም መኳንንት፣ የቤተ መንግሥቱ ባለሥልጣናት፣ ካህናቱና ለሁለት በተከፈለው ጥጃ መካከል ያለፈው የምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ ይህ ነገር ይደርስባቸዋል፦ 20 ለጠላቶቻቸውና ሕይወታቸውን ማጥፋት ለሚሹ* ሰዎች አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።+ 21 የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስንና መኳንንቱን ሁሉ ለጠላቶቻቸው፣ ሕይወታቸውን ማጥፋት ለሚሹ* ሰዎችና እናንተን መውጋት ትቶ ለተመለሰው+ የባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት አሳልፌ እሰጣለሁ።’+

22 “‘እነሆ፣ እኔ ይህን ትእዛዝ አስተላልፋለሁ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘እነሱንም ወደዚህች ከተማ መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ እነሱም ይወጓታል፣ ይይዟታል፣ በእሳትም ያቃጥሏታል፤+ የይሁዳንም ከተሞች ማንም የማይኖርበት ጠፍ መሬት አደርጋቸዋለሁ።’”+

35 በኢዮስያስ ልጅ፣ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮዓቄም+ የግዛት ዘመን የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ 2 “ወደ ሬካባውያን+ ቤት ሄደህ አነጋግራቸው፤ ወደ ይሖዋም ቤት አምጥተህ ወደ አንዱ መመገቢያ ክፍል አስገባቸው፤ ከዚያም የሚጠጡትን የወይን ጠጅ አቅርብላቸው።”

3 ስለዚህ የሃባጺንያን ልጅ፣ የኤርምያስን ልጅ፣ ያአዛንያህን፣ ወንድሞቹን፣ ወንዶች ልጆቹን ሁሉና የሬካባውያንን ወገን ሁሉ ወሰድኩ፤ 4 ወደ ይሖዋ ቤትም አመጣኋቸው። የእውነተኛው አምላክ ሰው፣ የይግዳልያ ልጅ፣ የሃናን ልጆች መመገቢያ ወደሆነው ክፍል አስገባኋቸው፤ ክፍሉም የሚገኘው ከበር ጠባቂው ከሻሉም ልጅ፣ ከማአሴያህ መመገቢያ ክፍል በላይ ካለው ከመኳንንቱ መመገቢያ ክፍል አጠገብ ነው። 5 ከዚያም ከሬካባውያን ወገን በሆኑት ሰዎች ፊት በወይን ጠጅ የተሞሉ ጽዋዎችንና ዋንጫዎችን አቅርቤ “የወይን ጠጅ ጠጡ” አልኳቸው።

6 እነሱ ግን እንዲህ አሉ፦ “የወይን ጠጅ አንጠጣም፤ ምክንያቱም አባታችን የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ*+ እንዲህ ሲል አዞናል፦ ‘እናንተም ሆናችሁ ወንዶች ልጆቻችሁ መቼም ቢሆን የወይን ጠጅ አትጠጡ። 7 ቤት አትሥሩ፤ ዘር አትዝሩ፤ ወይን አትትከሉ ወይም የወይን እርሻ አይኑራችሁ። ይልቁንም የባዕድ አገር ሰዎች ሆናችሁ በተቀመጣችሁበት ምድር ረጅም ዘመን እንድትኖሩ ምንጊዜም በድንኳን ውስጥ ተቀመጡ።’ 8 ስለዚህ እኛም ሆንን ሚስቶቻችን እንዲሁም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን የአባታችን የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ ያዘዘንን ቃል ሁሉ በማክበር የወይን ጠጅ የሚባል ነገር መቼም ቢሆን አንጠጣም። 9 መኖሪያ ቤትም አንሠራም፤ የወይን እርሻ፣ መሬትም ሆነ የእህል ዘር የለንም። 10 በድንኳን ውስጥ መኖራችንንና አባታችን ኢዮናዳብ* የሰጠንን ትእዛዝ ማክበራችንን እንቀጥላለን። 11 ሆኖም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* ምድሪቱን ሊወጋ በመጣ ጊዜ+ እንዲህ አልን፦ ‘ኑ፣ ከከለዳውያንና ከሶርያውያን ሠራዊት ለማምለጥ ወደ ኢየሩሳሌም እንግባ’፤ በመሆኑም አሁን በኢየሩሳሌም እየኖርን ነው።”

12 የይሖዋም ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ 13 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሂድና ለይሁዳ ሰዎችና ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እንዲህ በል፦ “ቃሌን እንድትታዘዙ በተደጋጋሚ ጊዜ ማሳሰቢያ አልተሰጣችሁም?”+ ይላል ይሖዋ። 14 “የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ፣ ዘሮቹ የወይን ጠጅ እንዳይጠጡ አዝዞ ነበር፤ እነሱም እስከ ዛሬ ድረስ የወይን ጠጅ ባለመጠጣት ቃሉን ጠብቀዋል፤ በዚህም መንገድ የአባታቸውን ትእዛዝ አክብረዋል።+ ይሁንና እኔ ደግሜ ደጋግሜ ብነግራችሁም* አልታዘዛችሁኝም።+ 15 እኔም አገልጋዮቼን ነቢያትን ሁሉ ወደ እናንተ መላኬን ቀጠልኩ፤ እንዲህ በማለትም ደግሜ ደጋግሜ* ላክኋቸው፦+ ‘እባካችሁ፣ እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤+ ትክክል የሆነውንም ነገር አድርጉ! ሌሎችን አማልክት አትከተሉ፤ ደግሞም አታገልግሏቸው። እንዲህ ካደረጋችሁ ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጠኋት ምድር ትኖራላችሁ።’+ እናንተ ግን ጆሯችሁን አልሰጣችሁም፤ እኔንም አልሰማችሁም። 16 የሬካብ ልጅ የኢዮናዳብ ዘሮች አባታቸው የሰጣቸውን ትእዛዝ ፈጽመዋል፤+ እነዚህ ሰዎች ግን እኔን አልሰሙም።”’”

17 “ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ ላይ አደርሳለሁ ያልኩትን ጥፋት ሁሉ አመጣባቸዋለሁ፤+ ብነግራቸውም እንኳ አይሰሙኝምና፤ ደጋግሜ ብጠራቸውም አይመልሱልኝም።’”+

18 ኤርምያስም ለሬካባውያን ወገኖች እንዲህ አላቸው፦ “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የአባታችሁን የኢዮናዳብን ትእዛዝ ስላከበራችሁ እንዲሁም ትእዛዙን ሁሉ ስለጠበቃችሁና ያዘዛችሁን በትክክል ስለፈጸማችሁ፣ 19 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ከሬካብ ልጅ ከኢዮናዳብ* ዘር በፊቴ የሚያገለግል ሰው ፈጽሞ አይታጣም።”’”

36 የኢዮስያስ ልጅ የሆነው የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓቄም+ በነገሠ በአራተኛው ዓመት የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ 2 “አንድ ጥቅልል* ውሰድና በኢዮስያስ ዘመን ለአንተ መናገር ከጀመርኩበት ቀን አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ+ በእስራኤል፣ በይሁዳና በብሔራት ሁሉ+ ላይ አመጣዋለሁ ብዬ የነገርኩህን ቃል በሙሉ ጻፍበት።+ 3 ምናልባት የይሁዳ ቤት ሰዎች በእነሱ ላይ ላመጣ ያሰብኩትን ጥፋት ሁሉ ሲሰሙ ከክፉ መንገዳቸው ይመለሱ ይሆናል፤ እኔም በደላቸውንና ኃጢአታቸውን ይቅር እላለሁ።”+

4 ከዚያም ኤርምያስ የነሪያህን ልጅ ባሮክን+ ጠራው፤ ይሖዋ የነገረውንም ቃል ሁሉ በቃሉ አስጻፈው፤ ባሮክም በጥቅልሉ* ላይ ጻፈው።+ 5 ኤርምያስም ባሮክን እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “እኔ ታግጃለሁ፤ ወደ ይሖዋ ቤትም መግባት አልችልም። 6 ስለዚህ ገብተህ እኔ ያስጻፍኩህን የይሖዋን ቃል ከጥቅልሉ ላይ ጮክ ብለህ ማንበብ ያለብህ አንተ ነህ። በጾም ቀን በይሖዋ ቤት የተሰበሰቡ ሰዎች እየሰሙ አንብበው፤ በዚህ መንገድ፣ ከየከተሞቻቸው ለመጡት የይሁዳ ሰዎች ሁሉ ታነብላቸዋለህ። 7 ምናልባት ሞገስ ለማግኘት የሚያቀርቡት ልመና ወደ ይሖዋ ሊደርስና እያንዳንዳቸው ከክፉ መንገዳቸው ሊመለሱ ይችላሉ፤ ይሖዋ በዚህ ሕዝብ ላይ የተናገረው ቁጣና መዓት ታላቅ ነውና።”

8 በመሆኑም የነሪያህ ልጅ ባሮክ ነቢዩ ኤርምያስ ያዘዘውን ሁሉ አደረገ፤ በይሖዋ ቤት የይሖዋን ቃል ከጥቅልሉ* ላይ ጮክ ብሎ አነበበ።+

9 የኢዮስያስ ልጅ የሆነው የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓቄም+ በነገሠ በአምስተኛው ዓመት፣ በዘጠነኛው ወር በኢየሩሳሌም ያለው ሕዝብ ሁሉና ከይሁዳ ከተሞች ወደ ኢየሩሳሌም የመጣው ሕዝብ ሁሉ በይሖዋ ፊት ጾም አወጀ።+ 10 ከዚያም ባሮክ በይሖዋ ቤት በላይኛው ግቢ ይኸውም በይሖዋ ቤት በአዲሱ በር መግቢያ+ አጠገብ ባለው፣ የቅዱሳን መጻሕፍት ገልባጭ* በሆነው በሳፋን+ ልጅ በገማርያህ+ ክፍል* ሕዝቡ ሁሉ እየሰማ የኤርምያስን ቃል ከጥቅልሉ* ላይ አነበበ።

11 የሳፋን ልጅ፣ የገማርያህ ልጅ ሚካያህ ከጥቅልሉ* ላይ የተነበበውን የይሖዋን ቃል ሁሉ በሰማ ጊዜ 12 ወደ ንጉሡ ቤት፣* ወደ ጸሐፊው ክፍል ወረደ። መኳንንቱ* ሁሉ ይኸውም ጸሐፊው ኤሊሻማ፣+ የሸማያህ ልጅ ደላያህ፣ የአክቦር+ ልጅ ኤልናታን፣+ የሳፋን ልጅ ገማርያህ፣ የሃናንያህ ልጅ ሴዴቅያስና ሌሎቹ መኳንንት ሁሉ በዚያ ተቀምጠው ነበር። 13 ሚካያህ፣ ባሮክ ሕዝቡ እየሰማ ከጥቅልሉ* ላይ ሲያነብ ያዳመጠውን ቃል ሁሉ ነገራቸው።

14 በዚህ ጊዜ መኳንንቱ ሁሉ የኩሺ ልጅ፣ የሸሌምያህ ልጅ፣ የነታንያህ ልጅ የሆነውን የሁዲን “ሕዝቡ እየሰማህ ያነበብከውን ጥቅልል ይዘህ ና” ብሎ እንዲነግረው ወደ ባሮክ ላኩት። የነሪያህ ልጅ ባሮክም ጥቅልሉን ይዞ ወደ እነሱ ሄደ። 15 እነሱም “እባክህ ተቀመጥና ጥቅልሉን ጮክ ብለህ አንብብልን” አሉት። ባሮክም አነበበላቸው።

16 እነሱም ቃሉን ሁሉ እንደሰሙ በፍርሃት ተውጠው እርስ በርስ ተያዩ፤ ከዚያም ባሮክን “ይህን ቃል ሁሉ ለንጉሡ ልንነግረው ይገባል” አሉት። 17 ደግሞም ባሮክን “ይህን ሁሉ ቃል የጻፍከው እንዴት እንደሆነ እስቲ ንገረን። በቃሉ ነው ያስጻፈህ?” ብለው ጠየቁት። 18 ባሮክም “ይህን ሁሉ በቃሉ አስጻፈኝ፤ እኔም በጥቅልሉ* ላይ በቀለም ጻፍኩት” ብሎ መለሰላቸው። 19 መኳንንቱ ባሮክን “ሂድ፣ አንተና ኤርምያስ ተደበቁ፤ ያላችሁበትንም ማንም ሰው አይወቅ” አሉት።+

20 ከዚያም ንጉሡ ወደሚገኝበት ግቢ ሄዱ፤ ጥቅልሉንም በጸሐፊው በኤሊሻማ ክፍል አስቀመጡት፤ የሰሙትንም ነገር ሁሉ ለንጉሡ ነገሩት።

21 ንጉሡም ጥቅልሉን እንዲያመጣ የሁዲን+ ላከው፤ እሱም ጥቅልሉን ከጸሐፊው ከኤሊሻማ ክፍል ይዞት መጣ። የሁዲም ንጉሡና በንጉሡ አጠገብ ቆመው የነበሩት መኳንንት ሁሉ እየሰሙ ያነበው ጀመር። 22 ንጉሡ በዘጠነኛው ወር* የክረምቱን ወቅት በሚያሳልፍበት ቤት ተቀምጦ ነበር፤ በፊቱም በምድጃ የሚነድ እሳት ነበር። 23 የሁዲ ሦስት ወይም አራት ዓምድ ካነበበ በኋላ ንጉሡ የተነበበውን ክፍል በጸሐፊ ቢላ እየቀደደ በምድጃ ውስጥ ወዳለው እሳት ይወረውረው ነበር፤ ጥቅልሉ ሙሉ በሙሉ ተቃጥሎ እስኪያልቅ ድረስ እንዲሁ አደረገ። 24 ይህን ሁሉ ቃል ሲሰሙ የነበሩት ንጉሡም ሆነ አገልጋዮቹ በሙሉ ምንም ፍርሃት አልተሰማቸውም፤ ልብሳቸውንም አልቀደዱም። 25 ኤልናታን፣+ ደላያህና+ ገማርያህ+ ንጉሡ ጥቅልሉን እንዳያቃጥለው ቢለምኑትም እንኳ አልሰማቸውም። 26 በተጨማሪም ንጉሡ ጸሐፊውን ባሮክንና ነቢዩን ኤርምያስን እንዲይዟቸው የንጉሡን ልጅ የራህምኤልን፣ የአዝርዔልን ልጅ ሰራያህንና የአብድዔልን ልጅ ሸሌምያህን አዘዘ፤ ይሖዋ ግን ሰውሯቸው ነበር።+

27 ንጉሡ፣ ባሮክ ከኤርምያስ አፍ እየሰማ የጻፈውን ቃል የያዘውን ጥቅልል+ ካቃጠለው በኋላ የይሖዋ ቃል እንደገና እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ 28 “ሌላ ጥቅልል ውሰድና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓቄም ባቃጠለው በመጀመሪያው ጥቅልል+ ላይ የነበረውን ያንኑ ቃል ሁሉ ጻፍበት። 29 የይሁዳን ንጉሥ ኢዮዓቄምንም እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ይህን ጥቅልል አቃጥለሃል፤ ደግሞም ‘“የባቢሎን ንጉሥ ያላንዳች ጥርጥር መጥቶ ይህችን ምድር ያወድማል፤ ሰውንና እንስሳንም ከምድሪቱ ላይ ያጠፋል” ብለህ በጥቅልሉ ላይ የጻፍከው ለምንድን ነው?’ ብለሃል።+ 30 ስለዚህ ይሖዋ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮዓቄም ላይ እንዲህ ይላል፦ ‘በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው አይኖረውም፤+ ሬሳውም የቀን ሐሩርና የሌሊት ቁር ይፈራረቅበታል።+ 31 እሱን፣ ልጆቹንና* አገልጋዮቹን ለፈጸሙት በደል ተጠያቂ አደርጋቸዋለሁ፤ ደግሞም በእነሱ፣ በኢየሩሳሌም ነዋሪዎችና በይሁዳ ሰዎች ላይ አመጣባቸዋለሁ ብዬ የተናገርኩትን ጥፋት ሁሉ አወርድባቸዋለሁ፤+ እነሱ ግን አልሰሙም።’”’”+

32 ከዚያም ኤርምያስ ሌላ ጥቅልል ወስዶ ለነሪያህ ልጅ ለጸሐፊው ለባሮክ ሰጠው፤+ እሱም ኤርምያስ በቃል እያስጻፈው የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓቄም በእሳት ባቃጠለው ጥቅልል*+ ላይ የነበረውን ቃል ሁሉ ጻፈበት። ደግሞም ከዚያ ጋር የሚመሳሰል ብዙ ቃል ተጨመረበት።

37 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* የኢዮስያስን ልጅ ንጉሥ ሴዴቅያስን+ በይሁዳ ምድር ስላነገሠው በኢዮአቄም ልጅ በኮንያሁ*+ ፋንታ መግዛት ጀመረ።+ 2 ይሁንና እሱም ሆነ አገልጋዮቹ እንዲሁም የምድሪቱ ሕዝብ ይሖዋ በነቢዩ ኤርምያስ በኩል የተናገረውን ቃል አልሰሙም።

3 ንጉሥ ሴዴቅያስም የሸሌምያህን ልጅ የሁካልንና+ የካህኑን የማአሴያህን ልጅ ሶፎንያስን+ “እባክህ፣ ስለ እኛ ወደ አምላካችን ወደ ይሖዋ ጸልይ” ብለው እንዲነግሩት ወደ ነቢዩ ኤርምያስ ላካቸው። 4 በዚያ ወቅት ኤርምያስ ገና እስር ቤት ስላላስገቡት በሕዝቡ መካከል በነፃነት ይገባና ይወጣ ነበር።+ 5 በዚህ ጊዜ የፈርዖን ሠራዊት ከግብፅ ወጥቶ ነበር፤+ ኢየሩሳሌምን ከበው የነበሩት ከለዳውያንም ይህን ሰሙ። በመሆኑም ኢየሩሳሌምን ለቀው ሄዱ።+ 6 ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ነቢዩ ኤርምያስ መጣ፦ 7 “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እኔን እንድትጠይቁ ወደ እኔ የላካችሁን የይሁዳን ንጉሥ እንዲህ በሉት፦ “እነሆ፣ እናንተን ለመርዳት የመጣው የፈርዖን ሠራዊት ወደ አገሩ ወደ ግብፅ ይመለሳል።+ 8 ከለዳውያኑም ተመልሰው መጥተው ይህችን ከተማ ይወጓታል፤ ይይዟታልም፤ በእሳትም ያቃጥሏታል።”+ 9 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “‘ከለዳውያን ያላንዳች ጥርጥር ትተውን ይሄዳሉ’ እያላችሁ ራሳችሁን አታታሉ፤* ምክንያቱም ትተዋችሁ አይሄዱም። 10 እናንተን የሚወጋችሁን መላውን የከለዳውያን ሠራዊት ብትመቱና ቁስለኞቻቸው ብቻ ቢቀሩ እንኳ ከድንኳናቸው ተነስተው ይህችን ከተማ በእሳት ያቃጥሏታል።”’”+

11 የከለዳውያን ሠራዊት ከፈርዖን ሠራዊት የተነሳ ኢየሩሳሌምን ትቶ በተመለሰ ጊዜ፣+ 12 ኤርምያስ ወደ ቢንያም አገር+ ሄዶ በሕዝቡ መካከል ድርሻውን ለመውሰድ ከኢየሩሳሌም ተነሳ። 13 ይሁንና ወደ ቢንያም በር በደረሰ ጊዜ የሃናንያህ ልጅ፣ የሸሌምያህ ልጅ ይሪያህ የተባለ የጠባቂዎች አለቃ ነቢዩ ኤርምያስን ይዞ “ከድተህ ወደ ከለዳውያን ልትሄድ ነው!” አለው። 14 ኤርምያስ ግን “በፍጹም! ከድቼ ወደ ከለዳውያን ልሄድ አይደለም” አለ። እሱ ግን አልሰማውም። በመሆኑም ይሪያህ ኤርምያስን ይዞ ወደ መኳንንቱ ወሰደው። 15 መኳንንቱ ኤርምያስን እጅግ ተቆጥተው+ መቱት፤ ከዚያም በወቅቱ እስር ቤት አድርገውት በነበረው በጸሐፊው በየሆናታን ቤት አሰሩት።*+ 16 ኤርምያስ በምድር ቤት* ውስጥ ወደሚገኝ የእስረኞች ክፍል እንዲገባ ተደረገ፤ በዚያም ለብዙ ቀናት ቆየ።

17 ከዚያም ንጉሥ ሴዴቅያስ ልኮ አስመጣው፤ ንጉሡም በቤቱ* ውስጥ በሚስጥር ጠየቀው።+ “ከይሖዋ የመጣ ቃል አለ?” አለው። ኤርምያስም “አዎ፣ አለ!” ሲል መለሰለት፤ አክሎም “በባቢሎን ንጉሥ እጅ አልፈህ ትሰጣለህ!” አለው።+

18 በተጨማሪም ኤርምያስ ንጉሥ ሴዴቅያስን እንዲህ አለው፦ “እስር ቤት ያስገባችሁኝ በአንተ፣ በአገልጋዮችህና በዚህ ሕዝብ ላይ ምን የሠራሁት በደል ቢኖር ነው? 19 ‘የባቢሎን ንጉሥ እናንተንና ይህችን ምድር ለመውጋት አይመጣም’ ብለው የተነበዩላችሁ ነቢያታችሁ አሁን የት አሉ?+ 20 አሁንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ እባክህ ስማኝ። በፊትህ ሞገስ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና እባክህ ተቀበል። ወደ ጸሐፊው ወደ የሆናታን ቤት+ መልሰህ አትላከኝ፤ ካልሆነ ግን በዚያ እሞታለሁ።”+ 21 በመሆኑም ንጉሥ ሴዴቅያስ፣ ኤርምያስ በክብር ዘቦቹ ግቢ+ እንዲታሰር አዘዘ፤ ዳቦ ከከተማዋ እስኪጠፋ ድረስም+ ከዳቦ ጋጋሪዎች ጎዳና በየዕለቱ አንድ አንድ ዳቦ ይሰጠው ነበር።+ ኤርምያስም በክብር ዘቦቹ ግቢ ተቀመጠ።

38 የማታን ልጅ ሰፋጥያህ፣ የጳስኮር ልጅ ጎዶልያስ፣ የሸሌምያህ ልጅ ዩካልና+ የማልኪያህ ልጅ ጳስኮር፣+ ኤርምያስ ለሕዝቡ ሁሉ የተናገረውን የሚከተለውን ቃል ሰሙ፦ 2 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዚህች ከተማ የሚቀር በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር* ይሞታል።+ ለከለዳውያን እጁን የሚሰጥ* ግን ይተርፋል፤ ሕይወቱ * እንደ ምርኮ ትሆንለታለች፤* በሕይወትም ይኖራል።’+ 3 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ይህች ከተማ ለባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት መሰጠቷ አይቀርም፤ እሱም ይይዛታል።’”+

4 መኳንንቱ ንጉሡን እንዲህ አሉት፦ “ይህ ሰው እንዲህ ያለ ቃል በመናገር በዚህች ከተማ ውስጥ የቀሩትን ወታደሮችና የሕዝቡን ሁሉ ወኔ* እያዳከመ ስለሆነ እባክህ አስገድለው።+ ይህ ሰው ለዚህ ሕዝብ ጥፋትን እንጂ ሰላምን አይመኝምና።” 5 ንጉሥ ሴዴቅያስም “እነሆ፣ እሱ በእጃችሁ ነው፤ ንጉሡ እናንተን ለማስቆም ምንም ነገር ሊያደርግ አይችልምና” ሲል መለሰላቸው።

6 እነሱም ኤርምያስን ወስደው በክብር ዘቦቹ ግቢ+ በሚገኘው በንጉሡ ልጅ በማልኪያህ የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት። ኤርምያስን በገመድ ወደ ጉድጓዱ አወረዱት። በጉድጓዱ ውስጥም ጭቃ ብቻ እንጂ ውኃ አልነበረም፤ ኤርምያስም ጭቃው ውስጥ መስመጥ ጀመረ።

7 በንጉሡ ቤት* የነበረው ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ* ኤቤድሜሌክ+ ኤርምያስን በውኃ ማጠራቀሚያው ጉድጓድ ውስጥ እንደጣሉት ሰማ። በዚህ ጊዜ ንጉሡ በቢንያም በር ተቀምጦ ነበር፤+ 8 በመሆኑም ኤቤድሜሌክ ከንጉሡ ቤት* ወጥቶ ንጉሡን እንዲህ አለው፦ 9 “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ እነዚህ ሰዎች በነቢዩ ኤርምያስ ላይ ክፉ ነገር ፈጽመዋል! በውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ውስጥ ጥለውታል፤ ከረሃቡም የተነሳ እዚያው ይሞታል፤ በከተማዋ ውስጥ ዳቦ የሚባል ነገር የለምና።”+

10 ከዚያም ንጉሡ ኢትዮጵያዊውን ኤቤድሜሌክን እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “ከዚህ 30 ሰዎች ይዘህ ሂድ፤ ነቢዩ ኤርምያስንም ከመሞቱ በፊት ከውኃ ማጠራቀሚያው ጉድጓድ ውስጥ ጎትተህ አውጣው።” 11 በመሆኑም ኤቤድሜሌክ ሰዎቹን ይዞ በንጉሡ ቤት* ከግምጃ ቤቱ+ ሥር ወዳለው ቦታ ሄደ፤ ከዚያም የተቦጫጨቀ ጨርቅና ያረጀ ልብስ ከዚያ ወስደው በውኃ ማጠራቀሚያው ጉድጓድ ውስጥ ላለው ለኤርምያስ በገመድ አወረዱለት። 12 ኢትዮጵያዊው ኤቤድሜሌክ ኤርምያስን “ይህን የተቦጫጨቀ ጨርቅና ያረጀ ልብስ በብብትህና በገመዱ መካከል አድርገው” አለው። ኤርምያስም እንደተባለው አደረገ፤ 13 እነሱም ኤርምያስን በገመዱ ጎትተው ከውኃ ማጠራቀሚያው ጉድጓድ ውስጥ አወጡት። ኤርምያስም በክብር ዘቦቹ ግቢ+ ተቀመጠ።

14 ንጉሥ ሴዴቅያስ ሰው ልኮ ነቢዩ ኤርምያስን እሱ ወዳለበት፣ በይሖዋ ቤት ወደሚገኘው ወደ ሦስተኛው መግቢያ አስመጣው፤ ንጉሡም ኤርምያስን “አንድ ነገር ልጠይቅህ እፈልጋለሁ። ምንም ነገር እንዳትደብቀኝ” አለው። 15 በዚህ ጊዜ ኤርምያስ ሴዴቅያስን “ብነግርህ ትገድለኛለህ። ብመክርህም አትሰማኝም” አለው። 16 ንጉሥ ሴዴቅያስም በሚስጥር ለኤርምያስ እንዲህ ሲል ማለለት፦ “ይህን ሕይወት በሰጠን* ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፣ አልገድልህም፤ ሕይወትህን ለማጥፋት ለሚሹት* ለእነዚህ ሰዎችም አሳልፌ አልሰጥህም።”

17 ከዚያም ኤርምያስ ሴዴቅያስን እንዲህ አለው፦ “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ለባቢሎን ንጉሥ መኳንንት እጅህን ብትሰጥ* ሕይወትህ ትተርፋለች፤* ይህችም ከተማ በእሳት አትቃጠልም፤ አንተም ሆንክ ቤተሰብህ በሕይወት ትተርፋላችሁ።+ 18 ለባቢሎን ንጉሥ መኳንንት እጅህን የማትሰጥ ከሆነ* ግን ይህች ከተማ ለከለዳውያን አልፋ ትሰጣለች፤ እነሱም በእሳት ያቃጥሏታል፤+ አንተም ከእጃቸው አታመልጥም።’”+

19 ከዚያም ንጉሥ ሴዴቅያስ ኤርምያስን “ወደ ከለዳውያን የኮበለሉትን አይሁዳውያን እፈራለሁ፤ ለእነሱ አሳልፈው የሰጡኝ እንደሆነ ሊያሠቃዩኝ ይችላሉ” አለው። 20 ኤርምያስ ግን እንዲህ አለው፦ “ለእነሱ አሳልፈው አይሰጡህም። እባክህ የምነግርህን የይሖዋን ቃል ታዘዝ፤ መልካምም ይሆንልሃል፤ በሕይወትም ትኖራለህ።* 21 እጅህን ለመስጠት* ፈቃደኛ ካልሆንክ ግን ይሖዋ የገለጠልኝ ነገር ይህ ነው፦ 22 እነሆ፣ በይሁዳ ንጉሥ ቤት* የቀሩት ሴቶች ሁሉ ወደ ባቢሎን ንጉሥ መኳንንት ይወሰዳሉ፤+ እነሱም እንዲህ ይላሉ፦

‘ተማምነህባቸው የነበሩት ሰዎች* አታለውሃል፤ ደግሞም አሸንፈውሃል።+

እግርህ ጭቃ ውስጥ እንዲሰምጥ አድርገዋል።

አሁን አፈግፍገው ተመልሰዋል።’

23 “ሚስቶችህንና ወንዶች ልጆችህን ሁሉ ለከለዳውያን ይሰጣሉ፤ አንተም ከእጃቸው አታመልጥም፤ ይልቁንም የባቢሎን ንጉሥ ይይዝሃል፤+ በአንተም ምክንያት ይህች ከተማ በእሳት ትቃጠላለች።”+

24 ከዚያም ሴዴቅያስ ኤርምያስን እንዲህ አለው፦ “ስለዚህ ጉዳይ ማንም ሰው እንዳይሰማ፤ አለዚያ ትሞታለህ። 25 መኳንንቱ ከአንተ ጋር እንደተነጋገርኩ ሰምተው ወደ አንተ ቢመጡና ‘ለንጉሡ የነገርከውን ነገር እስቲ ንገረን። ምንም ነገር አትደብቀን፤ እኛም አንገድልህም።+ ንጉሡ የነገረህ ምንድን ነው?’ ቢሉህ፣ 26 ‘በዚያ እንዳልሞት ንጉሡ ወደ የሆናታን ቤት መልሶ እንዳይልከኝ ስለምነው ነበር’ በላቸው።”+

27 በኋላም መኳንንቱ ሁሉ ወደ ኤርምያስ መጥተው ጠየቁት። እሱም ንጉሡ እንዲናገር ያዘዘውን ቃል ሁሉ ነገራቸው። እነሱም ከዚያ በኋላ ምንም አላሉትም፤ ያደረጉትን ውይይት የሰማ ሰው አልነበረምና። 28 ኤርምያስ ኢየሩሳሌም እስከተያዘችበት ጊዜ ድረስ በክብር ዘቦቹ ግቢ+ ተቀመጠ፤ ኢየሩሳሌም በተያዘችበት ጊዜም እዚያው ነበር።+

39 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት፣ በአሥረኛው ወር፣ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾርና* መላው ሠራዊቱ መጥተው ኢየሩሳሌምን ከበቧት።+

2 በሴዴቅያስ ዘመነ መንግሥት በ11ኛው ዓመት፣ በአራተኛው ወር፣ ከወሩም በዘጠነኛው ቀን የከተማዋን ቅጥር ነደሉ።+ 3 የባቢሎን ንጉሥ መኳንንት ሁሉ ይኸውም ሳምጋሩ ኔርጋልሻሬጸር፣ ራብሳሪስ የሆነው ነቦሳርሰኪም፣* ራብማግ* የሆነው ኔርጋልሻሬጸርና የቀሩት የባቢሎን ንጉሥ መኳንንት ሁሉ ገብተው በመካከለኛው በር አጠገብ ተቀመጡ።+

4 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስና ወታደሮቹ ሁሉ ባዩአቸው ጊዜ፣ በንጉሡ የአትክልት ቦታ ባለው መንገድ፣ በሁለቱ ቅጥሮች መካከል በሚገኘው በር በኩል በሌሊት ከከተማዋ ወጥተው ሸሹ፤+ ወደ አረባ የሚወስደውንም መንገድ ተከትለው ሄዱ።+ 5 የከለዳውያን ሠራዊት ግን አሳደዳቸው፤ ሴዴቅያስንም በኢያሪኮ በረሃማ ሜዳ ላይ ደረሱበት።+ ከያዙት በኋላ በሃማት+ ምድር በሪብላ+ ወደነበረው ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነጾር* አመጡት፤ እሱም በዚያ ፈረደበት። 6 የባቢሎን ንጉሥ በሪብላ የሴዴቅያስን ወንዶች ልጆች ዓይኑ እያየ አሳረዳቸው፤ በተጨማሪም የባቢሎን ንጉሥ የይሁዳን ታላላቅ ሰዎች ሁሉ አሳረደ።+ 7 የሴዴቅያስንም ዓይን አሳወረ፤ ከዚያም ወደ ባቢሎን ለመውሰድ በመዳብ የእግር ብረት አሰረው።+

8 ከለዳውያንም የንጉሡን ቤትና* የሕዝቡን ቤቶች አቃጠሉ፤+ የኢየሩሳሌምንም ቅጥሮች አፈረሱ።+ 9 የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን+ በከተማዋ ውስጥ የቀሩትን በሕይወት የተረፉ ሰዎችና ከድተው ለእሱ እጃቸውን የሰጡትን ሰዎች እንዲሁም የቀሩትን ሁሉ በግዞት ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው።

10 ሆኖም የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን ምንም ነገር ያልነበራቸውን አንዳንድ ያጡ የነጡ ድሆች በይሁዳ ምድር እንዲኖሩ ተዋቸው። ደግሞም በዚያ ቀን የወይን እርሻዎችና የሚያርሱት የእርሻ መሬት* ሰጣቸው።+

11 በዚህ ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* ኤርምያስን አስመልክቶ የዘቦች አለቃ ለሆነው ለናቡዛራዳን እንዲህ የሚል መመሪያ ሰጠ፦ 12 “ወስደህ የሚያስፈልገውን እንክብካቤ አድርግለት፤ ክፉ ነገር አታድርግበት፤ የሚጠይቅህንም ነገር ሁሉ አድርግለት።”+

13 በመሆኑም የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን፣ ራብሳሪስ* የሆነው ናቡሻዝባን፣ ራብማግ* የሆነው ኔርጋልሻሬጸር እንዲሁም የባቢሎን ንጉሥ ሹማምንት ሁሉ ልከው 14 ኤርምያስን ከክብር ዘቦቹ ግቢ+ አስወጡት፤ ደግሞም ወደ ቤቱ እንዲወስደው ለሳፋን+ ልጅ፣ ለአኪቃም+ ልጅ፣ ለጎዶልያስ+ ሰጡት። በመሆኑም ኤርምያስ በሕዝቡ መካከል ተቀመጠ።

15 ኤርምያስ በክብር ዘቦቹ ግቢ+ ተዘግቶበት በነበረ ጊዜ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እሱ መጣ፦ 16 “ሂድና ለኢትዮጵያዊው ለኤቤድሜሌክ+ እንዲህ በለው፦ ‘የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በዚህች ከተማ ላይ ለመልካም ሳይሆን ለጥፋት ቃሌን እፈጽማለሁ፤ በዚያም ቀን ይህ ሲፈጸም ታያለህ።”’

17 “‘አንተን ግን በዚያ ቀን እታደግሃለሁ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘ለምትፈራቸውም ሰዎች አልፈህ አትሰጥም።’

18 “‘የምታመልጥበትን መንገድ አዘጋጅልሃለሁ፤ በሰይፍም አትወድቅም። በእኔ ስለታመንክ+ ሕይወትህ* እንደ ምርኮ ትሆንልሃለች’*+ ይላል ይሖዋ።”

40 የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን+ ኤርምያስን ከራማ+ በነፃ ከለቀቀው በኋላ ወደ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው። ናቡዛራዳን ኤርምያስን ወደዚያ ሲወስደው እጆቹ በሰንሰለት ታስረው ነበር፤ ደግሞም ወደ ባቢሎን በግዞት እየተወሰዱ ከነበሩት የኢየሩሳሌምና የይሁዳ ግዞተኞች ሁሉ መካከል ነበር። 2 ከዚያም የዘቦቹ አለቃ ኤርምያስን ወስዶ እንዲህ አለው፦ “አምላክህ ይሖዋ በዚህ ስፍራ ላይ ይህ ጥፋት እንደሚመጣ አስቀድሞ ተናግሯል፤ 3 በይሖዋ ላይ ኃጢአት ስለሠራችሁና ቃሉን ስላልታዘዛችሁ ይሖዋ በተናገረው መሠረት ይህን ጥፋት አመጣ። ይህ ነገር በእናንተ ላይ የደረሰው ለዚህ ነው።+ 4 እጆችህ የታሰሩበትን ሰንሰለት ዛሬ እፈታልሃለሁ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መሄድ መልካም መስሎ ከታየህ መሄድ ትችላለህ፤ እኔም እንከባከብሃለሁ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መሄድ ካልፈለግክ ግን መቅረት ትችላለህ። እነሆ፣ ምድሪቱ ሁሉ በፊትህ ናት። ወደመረጥከው ቦታ መሄድ ትችላለህ።”+

5 ኤርምያስ ከመመለሱ በፊት ናቡዛራዳን እንዲህ አለው፦ “የባቢሎን ንጉሥ በይሁዳ ከተሞች ላይ ወደ ሾመው ወደ ሳፋን+ ልጅ፣ ወደ አኪቃም+ ልጅ ወደ ጎዶልያስ+ ተመለስ፤ በሕዝቡም መካከል ከእሱ ጋር ተቀመጥ፤ ወይም ደግሞ ወደመረጥከው ቦታ ሂድ።”

ከዚያም የዘቦቹ አለቃ ስንቅና ስጦታ ሰጥቶ አሰናበተው። 6 በመሆኑም ኤርምያስ በምጽጳ+ ወደሚገኘው ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ ሄዶ በምድሪቱ በቀሩት ሕዝብ መካከል ከእሱ ጋር መኖር ጀመረ።

7 በኋላም ከሰዎቻቸው ጋር በየቦታው የነበሩት የሠራዊቱ አለቆች የባቢሎን ንጉሥ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በምድሪቱ ላይ እንደሾመው እንዲሁም ወደ ባቢሎን በግዞት ባልተወሰዱትና በምድሪቱ ላይ በሚገኙት ድሆች የሆኑ ወንዶች፣ ሴቶችና ልጆች ላይ እንደሾመው ሰሙ።+ 8 ስለሆነም በምጽጳ+ ወደሚገኘው ወደ ጎዶልያስ መጡ። እነሱም የነታንያህ ልጅ እስማኤል፣+ የቃሬሃ ልጆች የሆኑት ዮሃናን+ እና ዮናታን፣ የታንሁመት ልጅ ሰራያህ፣ የነጦፋዊው የኤፋይ ልጆችና የማአካታዊው ልጅ የዛንያህ+ እንዲሁም አብረዋቸው የነበሩት ሰዎች ናቸው። 9 የሳፋን ልጅ፣ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ለእነሱና አብረዋቸው ለነበሩት ሰዎች እንዲህ ብሎ ማለላቸው፦ “ከለዳውያንን ማገልገል አያስፈራችሁ። በምድሪቱ ላይ ኑሩ፤ የባቢሎንንም ንጉሥ አገልግሉ፤ መልካምም ይሆንላችኋል።+ 10 እኔም ወደ እኛ በሚመጡት ከለዳውያን ፊት እናንተን ወክዬ ለመቅረብ* በምጽጳ እቀመጣለሁ። እናንተ ግን ወይን፣ የበጋ ፍሬዎችና* ዘይት አከማቹ፤ በማጠራቀሚያ ዕቃዎቻችሁም ውስጥ ክተቱ፤ በያዛችኋቸው ከተሞችም ውስጥ ኑሩ።”+

11 በሞዓብ፣ በአሞንና በኤዶም እንዲሁም በሌሎች አገሮች ሁሉ የነበሩት አይሁዳውያንም በሙሉ የባቢሎን ንጉሥ የተወሰኑ ቀሪዎች በይሁዳ ምድር እንዲኖሩ እንደፈቀደላቸውና የሳፋንን ልጅ፣ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በእነሱ ላይ እንደሾመ ሰሙ። 12 በመሆኑም አይሁዳውያኑ በሙሉ ከተበተኑባቸው ቦታዎች ሁሉ ይመለሱ ጀመር፤ በይሁዳ ምድር በምጽጳ ወዳለው ወደ ጎዶልያስ መጡ። እነሱም ወይንና የበጋ ፍሬዎችን በብዛት አከማቹ።

13 የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን እና በየቦታው የነበሩት የሠራዊቱ አለቆች ሁሉ በምጽጳ ወዳለው ወደ ጎዶልያስ መጡ። 14 እንዲህም አሉት፦ “የአሞናውያን+ ንጉሥ ባአሊስ አንተን ለመግደል* የነታንያህን ልጅ እስማኤልን እንደላከው አታውቅም?”+ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ግን አላመናቸውም።

15 ከዚያም የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን፣ ጎዶልያስን በምጽጳ በሚስጥር እንዲህ አለው፦ “ሄጄ የነታንያህን ልጅ እስማኤልን ልግደለው፤ ማንም አያውቅም። ለምን ይግደልህ?* ወደ አንተ የተሰበሰቡት የይሁዳ ሰዎች ሁሉ ለምን ይበተኑ? የይሁዳ ቀሪዎችስ ለምን ይጥፉ?” 16 የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ+ ግን የቃሬሃን ልጅ ዮሃናንን “ስለ እስማኤል የምትነግረኝ ነገር እውነት ስላልሆነ እንዲህ አታድርግ” አለው።

41 በሰባተኛው ወር፣ ከንጉሣውያን ቤተሰብ* የሆነውና ከንጉሡ ባለሥልጣናት አንዱ የነበረው የኤሊሻማ ልጅ፣ የነታንያህ ልጅ እስማኤል+ ከሌሎች አሥር ሰዎች ጋር ሆኖ በምጽጳ+ ወዳለው ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ መጣ። በምጽጳ አንድ ላይ ምግብ እየበሉ ሳለ 2 የነታንያህ ልጅ እስማኤልና ከእሱ ጋር የነበሩት አሥሩ ሰዎች ተነስተው የሳፋንን ልጅ፣ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በሰይፍ መተው ገደሉት። በዚህ መንገድ እስማኤል የባቢሎን ንጉሥ በምድሪቱ ላይ የሾመውን ሰው ገደለው። 3 በተጨማሪም እስማኤል በምጽጳ ከጎዶልያስ ጋር የነበሩትን አይሁዳውያን በሙሉ እንዲሁም በዚያ የነበሩትን ከለዳውያን ወታደሮች ገደላቸው።

4 ጎዶልያስ በተገደለ በሁለተኛው ቀን ስለ ሁኔታው ማንም ሰው ከማወቁ በፊት፣ 5 ከሴኬም፣+ ከሴሎና+ ከሰማርያ+ 80 ሰዎች መጡ። ጢማቸውን ላጭተው፣ ልብሳቸውን ቀደውና ሰውነታቸውን ተልትለው+ የነበረ ሲሆን በይሖዋ ቤት የሚያቀርቧቸውን የእህል መባዎችና ነጭ ዕጣን+ ይዘው ነበር። 6 የነታንያህ ልጅ እስማኤልም ከእነሱ ጋር ለመገናኘት ከምጽጳ ወጥቶ እያለቀሰ ሄደ። ባገኛቸው ጊዜ “ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ ኑ” አላቸው። 7 ሆኖም ወደ ከተማዋ ሲገቡ የነታንያህ ልጅ እስማኤልና ከእሱ ጋር የነበሩት ሰዎች አረዷቸው፤ ወደ ውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድም ጣሏቸው።

8 ይሁንና በመካከላቸው የነበሩ አሥር ሰዎች እስማኤልን “በእርሻ ውስጥ የደበቅነው የተከማቸ እህል ይኸውም ስንዴ፣ ገብስ፣ ዘይትና ማር ስላለን አትግደለን” አሉት። ስለዚህ ከወንድሞቻቸው ጋር አልገደላቸውም። 9 እስማኤል የገደላቸውን ሰዎች አስከሬን በሙሉ በአንድ ትልቅ የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ውስጥ ጣለ፤ ይህ ጉድጓድ ንጉሥ አሳ የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ ባስፈራራው ጊዜ የሠራው ነበር።+ የነታንያህ ልጅ እስማኤል ይህን ጉድጓድ ባረዳቸው ሰዎች አስከሬን ሞላው።

10 እስማኤል በምጽጳ+ የቀረውን ሕዝብ በሙሉ ይኸውም የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን+ በላያቸው ገዢ አድርጎ የሾመባቸውን፣ የንጉሡን ሴቶች ልጆችና በምጽጳ የቀሩትን ሰዎች ሁሉ ማረከ። የነታንያህ ልጅ እስማኤል እነሱን ማርኮ ወደ አሞናውያን ለመሻገር ጉዞ ጀመረ።+

11 የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን+ እና ከእሱ ጋር የነበሩት የሠራዊቱ አለቆች የነታንያህ ልጅ እስማኤል ስላደረገው ክፉ ነገር ሁሉ በሰሙ ጊዜ፣ 12 ከእነሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች በሙሉ ይዘው ከነታንያህ ልጅ ከእስማኤል ጋር ለመዋጋት ሄዱ፤ እሱንም በገባኦን ባለው በታላቁ ውኃ* አጠገብ አገኙት።

13 ከእስማኤል ጋር የነበሩት ሰዎች ሁሉ የቃሬሃን ልጅ ዮሃናንን እና ከእሱ ጋር የነበሩትን የሠራዊቱን አለቆች ሁሉ ባዩ ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው። 14 ከዚያም እስማኤል ከምጽጳ+ ማርኮ የወሰዳቸው ሰዎች ሁሉ ዞረው ከቃሬሃ ልጅ ከዮሃናን ጋር ተመለሱ። 15 የነታንያህ ልጅ እስማኤልና ከእሱ ጋር የነበሩት ስምንት ሰዎች ግን ከዮሃናን ፊት ሸሽተው ወደ አሞናውያን ሄዱ።

16 የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን እና ከእሱ ጋር የነበሩት የሠራዊቱ አለቆች ሁሉ ከምጽጳ የተወሰዱትን የቀሩትን ሰዎች ይዘዋቸው ሄዱ፤ እነዚህ ሰዎች የነታንያህ ልጅ እስማኤል፣ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን ከገደለው በኋላ+ ዮሃናን እና የሠራዊቱ አለቆች ከእሱ የታደጓቸው ናቸው። ወንዶቹን፣ ወታደሮቹን፣ ሴቶቹንና ልጆቹን እንዲሁም የቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱን ከገባኦን መልሰው አመጧቸው። 17 ከዚያም ተነስተው ሄዱ፤ ወደ ግብፅ ለመሄድ+ ስላሰቡም በቤተልሔም+ አጠገብ በሚገኘው በኪምሃም ማረፊያ ቦታ ቆዩ፤ 18 ይህን ያደረጉት ከከለዳውያን የተነሳ ነው። የነታንያህ ልጅ እስማኤል የባቢሎን ንጉሥ በምድሪቱ ላይ ሾሞት የነበረውን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን ስለገደለው ከለዳውያንን ፈርተዋቸው ነበር።+

42 ከዚያም የሠራዊቱ አለቆች ሁሉ፣ የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን፣+ የሆሻያህ ልጅ የዛንያህ* እና ሕዝቡ ሁሉ ከትንሹ እስከ ትልቁ ቀርበው 2 ነቢዩ ኤርምያስን እንዲህ አሉት፦ “ሞገስ ለማግኘት የምናቀርበውን ልመና እባክህ ስማ፤ ስለ እኛና ስለ እነዚህ ቀሪዎች ሁሉ ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ጸልይ፤ ይኸው እንደምታየው ከብዙዎች መካከል የቀረነው ጥቂቶች ብቻ ነን።+ 3 አምላክህ ይሖዋ በየት መሄድ እንደሚገባንና ምን ማድረግ እንዳለብን ይንገረን።”

4 ነቢዩ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እሺ፣ ሰምቻችኋለሁ፤ በጠየቃችሁኝ መሠረት ወደ አምላካችሁ ወደ ይሖዋ እጸልያለሁ፤ ይሖዋ የሚመልስላችሁንም ቃል ሁሉ እነግራችኋለሁ። አንድም ቃል አላስቀርባችሁም።”

5 እነሱም ለኤርምያስ እንዲህ ብለው መለሱለት፦ “አምላክህ ይሖዋ በአንተ በኩል እንዳዘዘን ባናደርግ፣ ይሖዋ በእኛ ላይ እውነተኛና ታማኝ ምሥክር ይሁን። 6 የአምላካችንን የይሖዋን ቃል በመታዘዝ መልካም እንዲሆንልን፣ ነገሩ ቢስማማንም ባይስማማንም፣ ወደ እሱ የምንልክህ አምላካችን ይሖዋ የሚለውን ሁሉ እንፈጽማለን።”

7 ከአሥር ቀን በኋላ የይሖዋ ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ። 8 ስለዚህ የቃሬሃን ልጅ ዮሃናንን፣ ከእሱ ጋር የነበሩትን የሠራዊቱን አለቆች ሁሉ እንዲሁም ሕዝቡን ሁሉ ከትንሹ እስከ ትልቁ ድረስ ጠራ።+ 9 እንዲህም አላቸው፦ “ሞገስ ለማግኘት ያሰማችሁትን ልመና በፊቱ እንዳቀርብ ወደ እሱ የላካችሁኝ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ 10 ‘በእርግጥ በዚህች ምድር ላይ የምትኖሩ ከሆነ፣ እገነባችኋለሁ እንጂ አላፈርሳችሁም፤ እተክላችኋለሁ እንጂ አልነቅላችሁም፤ በእናንተ ላይ ባመጣሁት ጥፋት እጸጸታለሁና።*+ 11 ከምትፈሩት ከባቢሎን ንጉሥ የተነሳ አትሸበሩ።’+

“‘ከእሱ የተነሳ አትፍሩ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘አድናችሁና ከእጁ እታደጋችሁ ዘንድ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና። 12 ምሕረት አደርግላችኋለሁ፤+ እሱም ምሕረት ያደርግላችኋል፤ ወደ ገዛ ምድራችሁም ይመልሳችኋል።

13 “‘እናንተ ግን “አይሆንም፤ በዚህች ምድር ላይ አንኖርም!” ብትሉና የአምላካችሁን የይሖዋን ቃል ባትታዘዙ፣ 14 ደግሞም “አይሆንም፤ ጦርነት ወደማናይበት፣ የቀንደ መለከት ድምፅ ወደማንሰማበት ወይም ምግብ አጥተን ወደማንራብበት ወደ ግብፅ ምድር እንሄዳለን፤+ በዚያም እንኖራለን” ብትሉ፣ 15 እናንተ የይሁዳ ቀሪዎች ሆይ፣ እንግዲህ የይሖዋን ቃል ስሙ። የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ወደ ግብፅ ለመግባት ቆርጣችሁ ከተነሳችሁና በዚያ ለመኖር* ከሄዳችሁ፣ 16 የፈራችሁት ሰይፍ ራሱ በግብፅ ምድር ያገኛችኋል፤ የፈራችሁትም ረሃብ ወደ ግብፅ ተከትሏችሁ ይሄዳል፤ በዚያም ትሞታላችሁ።+ 17 በዚያ ለመኖር ሲሉ ወደ ግብፅ ለመሄድ ቆርጠው የተነሱ ሰዎች ሁሉ በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር* ይሞታሉ። በእነሱ ላይ ከማመጣው ጥፋት ከመካከላቸው የሚተርፍ ወይም የሚያመልጥ አይኖርም።”’

18 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘ወደ ግብፅ ከሄዳችሁ፣ ቁጣዬና ንዴቴ በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ እንደወረደ ሁሉ+ በእናንተም ላይ ቁጣዬ ይወርዳል፤ እናንተም ለእርግማን፣ ለውርደትና ለነቀፋ ትዳረጋላችሁ፤ መቀጣጫም ትሆናላችሁ፤+ ይህን ቦታም ዳግመኛ አታዩትም።’

19 “የይሁዳ ቀሪዎች ሆይ፣ ይሖዋ በእናንተ ላይ ተናግሯል። ወደ ግብፅ አትሂዱ። ዛሬ እንዳስጠነቀቅኳችሁ በእርግጥ እወቁ፤ 20 በደላችሁም ሕይወታችሁን* እንደሚያሳጣችሁ እወቁ። እንዲህ ስትሉ ወደ ይሖዋ አምላካችሁ ልካችሁኝ ነበርና፦ ‘ወደ አምላካችን ወደ ይሖዋ ስለ እኛ ጸልይ፤ አምላካችን ይሖዋም የሚለውን ነገር ሁሉ ንገረን፤ እኛም የተባልነውን እናደርጋለን።’+ 21 እኔም ዛሬ ነግሬአችኋለሁ፤ እናንተ ግን የአምላካችሁን የይሖዋን ቃልም ሆነ ወደ እናንተ ልኮኝ የነገርኳችሁን ሁሉ አትታዘዙም።+ 22 ስለዚህ ሄዳችሁ ልትኖሩበት በፈለጋችሁት ቦታ በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር እንደምትሞቱ በእርግጥ እወቁ።”+

43 ኤርምያስ አምላካቸው ይሖዋ ለእነሱ እንዲነግራቸው የላከውን የአምላካቸውን የይሖዋን ቃል ሁሉ፣ አንድም ሳያስቀር ለሕዝቡ በሙሉ ተናግሮ ሲጨርስ 2 የሆሻያህ ልጅ አዛርያስ፣ የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን+ እና እብሪተኛ የሆኑት ሰዎች ሁሉ ኤርምያስን እንዲህ አሉት፦ “የምትናገረው ነገር ውሸት ነው! አምላካችን ይሖዋ ‘በግብፅ ለመኖር ወደዚያ አትሂዱ’ ብሎ አላከህም። 3 ከዚህ ይልቅ ከለዳውያን እንዲገድሉን ወይም ወደ ባቢሎን በግዞት እንዲወስዱን በእጃቸው አሳልፈህ ትሰጠን ዘንድ በእኛ ላይ ያነሳሳህ የነሪያህ ልጅ ባሮክ+ ነው።”+

4 በመሆኑም የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን፣ የሠራዊቱ አለቆች ሁሉና ሕዝቡ በሙሉ በይሁዳ ምድር እንዲቀመጡ ያዘዛቸውን የይሖዋን ቃል አልሰሙም። 5 እንዲያውም የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን እና የሠራዊቱ አለቆች በሙሉ፣ በይሁዳ ምድር ለመኖር ከተበተኑባቸው ብሔራት ሁሉ የተመለሱትን የይሁዳ ቀሪዎች በሙሉ ይዘው ሄዱ።+ 6 ወንዶቹን፣ ሴቶቹን፣ ልጆቹን፣ የንጉሡን ሴቶች ልጆችና የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን+ ከሳፋን+ ልጅ፣ ከአኪቃም+ ልጅ ከጎዶልያስ+ ጋር የተዋቸውን ሁሉ* እንዲሁም ነቢዩን ኤርምያስንና የነሪያህን ልጅ ባሮክን ይዘው ሄዱ። 7 የይሖዋን ቃል ባለመታዘዝ ወደ ግብፅ ምድር ገቡ፤ እስከ ጣፍነስ+ ድረስም ሄዱ።

8 ከዚያም የይሖዋ ቃል በጣፍነስ እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ 9 “ትላልቅ ድንጋዮችን ውሰድና አይሁዳውያኑ እያዩ በጣፍነስ በሚገኘው በፈርዖን ቤት መግቢያ፣ ከጡብ ከተሠራው መደብ ሥር ሸሽገህ በቅጥራን ለስናቸው። 10 ከዚያም እንዲህ በላቸው፦ ‘የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ አገልጋዬን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነጾርን* እጠራዋለሁ፤+ ዙፋኑንም እኔ ከሸሸግኳቸው ከእነዚህ ድንጋዮች በላይ አስቀምጣለሁ፤ ንጉሣዊ ድንኳኑንም በእነሱ ላይ ይዘረጋል።+ 11 እሱም መጥቶ የግብፅን ምድር ይመታል።+ ገዳይ መቅሰፍት የሚገባው ሁሉ ለገዳይ መቅሰፍት፣ በምርኮ መወሰድ የሚገባው ሁሉ ለምርኮ እንዲሁም ሰይፍ የሚገባው ሁሉ ለሰይፍ ይሰጣል።+ 12 የግብፅን አማልክት ቤቶችም* በእሳት አያይዛለሁ፤+ እሱም ያቃጥላቸዋል፤ ማርኮም ይወስዳቸዋል። እረኛ ልብሱን እንደሚጎናጸፍ የግብፅን ምድር ይጎናጸፋል፤ ከዚያም ቦታ በሰላም* ይሄዳል። 13 በግብፅም ምድር የሚገኙትን የቤትሼሜሽን* ዓምዶች* ይሰባብራል፤ የግብፅን አማልክት ቤቶችም* በእሳት ያቃጥላል።”’”

44 በግብፅ ምድር+ ይኸውም በሚግዶል፣+ በጣፍነስ፣+ በኖፍ*+ እና በጳትሮስ+ ምድር ለሚኖሩ አይሁዳውያን ሁሉ እንዲነገር ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፦ 2 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ከተሞች በሙሉ ያመጣሁትን ጥፋት ሁሉ አይታችኋል፤+ ዛሬ ማንም የማይኖርባቸው የፍርስራሽ ክምር ሆነዋል።+ 3 ይህም የሆነው እናንተም ሆነ አባቶቻችሁ ወደማታውቋቸው ሌሎች አማልክት+ ሄደው ለእነሱ መሥዋዕት በማቅረብና እነሱን በማገልገል እኔን ለማስቆጣት በፈጸሙት ክፉ ድርጊት የተነሳ ነው።+ 4 አገልጋዮቼን ነቢያትን ሁሉ ወደ እናንተ ላክኋቸው፤ “እባካችሁ፣ እኔ የምጠላውን ይህን አስጸያፊ ነገር አታድርጉ” በማለት ደግሜ ደጋግሜ* ላክኋቸው።+ 5 እነሱ ግን አልሰሙም፤ ለሌሎች አማልክት መሥዋዕት ከማቅረብ+ በመቆጠብም ከክፉ መንገዳቸው ለመመለስ ጆሯቸውን አልሰጡም። 6 በመሆኑም ቁጣዬና ንዴቴ ፈሰሰ፤ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎችም ላይ ነደደ፤ እነሱም ዛሬ እንደሚታዩት የፍርስራሽ ክምርና ጠፍ መሬት ሆነዋል።’+

7 “አሁንም የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ወንዶችና ሴቶች፣ ልጆችና ሕፃናት ሁሉ ከይሁዳ ጠፍተው ለራሳችሁ አንድም ቀሪ እንዳይተርፍ በራሳችሁ* ላይ ለምን ታላቅ ጥፋት ታመጣላችሁ? 8 ለመኖር በሄዳችሁባት በግብፅ ምድር ለሌሎች አማልክት መሥዋዕት በማቅረብ በእጃችሁ ሥራ የምታስቆጡኝ ለምንድን ነው? ትጠፋላችሁ፤ በምድር ብሔራትም ሁሉ መካከል ለእርግማንና ለነቀፋ ትዳረጋላችሁ።+ 9 በይሁዳ ምድርና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች አባቶቻችሁ የሠሩትን ክፉ ሥራ፣ የይሁዳ ነገሥታት የሠሩትን ክፉ ሥራና+ ሚስቶቻቸው የሠሩትን ክፉ ሥራ+ እንዲሁም እናንተ ራሳችሁ የሠራችሁትን ክፉ ሥራና ሚስቶቻችሁ የሠሩትን ክፉ ሥራ ረሳችሁት?+ 10 እነሱ እስከ ዛሬ ድረስ ራሳቸውን ዝቅ አላደረጉም፤* የፍርሃትም ስሜት አላደረባቸውም፤+ በእናንተና በአባቶቻችሁ ፊት ያኖርኩትን ሕጌንና ሥርዓቴንም አልተከተሉም።’+

11 “ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ በእናንተ ላይ ጥፋት ለማምጣትና ይሁዳን ሁሉ ለመደምሰስ ቆርጬ ተነስቻለሁ። 12 በግብፅ ምድር ለመኖር ወደዚያ ለመሄድ ቆርጠው የተነሱትንም የይሁዳ ቀሪዎች እወስዳለሁ፤ ሁሉም በግብፅ ምድር ይጠፋሉ።+ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ከትንሹ እስከ ትልቁ ድረስ በረሃብ ያልቃሉ፤ በሰይፍና በረሃብ ይሞታሉ። ለእርግማን፣ ለውርደትና ለነቀፋ ይዳረጋሉ፤ መቀጣጫም ይሆናሉ።+ 13 ኢየሩሳሌምን እንደቀጣሁ ሁሉ በግብፅ ምድር የሚኖሩትንም በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር* እቀጣለሁ።+ 14 በግብፅ ምድር ለመኖር የሄዱት የይሁዳ ቀሪዎችም አምልጠው ወይም በሕይወት ተርፈው ወደ ይሁዳ ምድር አይመለሱም። ወደዚያ ለመመለስና በዚያ ለመኖር ቢመኙም እንኳ* ከጥቂት ሰዎች በስተቀር አምልጦ የሚመለስ አይኖርም።’”

15 ሚስቶቻቸው ለሌሎች አማልክት መሥዋዕት ያቀርቡ እንደነበረ የሚያውቁ ወንዶች ሁሉ፣ ብዙ ሆነው የተሰበሰቡት ሚስቶቻቸው ሁሉ እንዲሁም በግብፅ ምድር+ ይኸውም በጳትሮስ+ የሚኖሩት ሰዎች ሁሉ ለኤርምያስ እንዲህ ሲሉ መለሱለት፦ 16 “በይሖዋ ስም የነገርከንን ቃል አንሰማም። 17 ይልቁንም አፋችን የተናገረውን ቃል ሁሉ መፈጸማችን አይቀርም፤ እኛና አባቶቻችን እንዲሁም ነገሥታታችንና መኳንንታችን በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ እናደርግ እንደነበረው ‘ለሰማይ ንግሥት’* መሥዋዕት እናቀርባለን፤ ለእሷም የመጠጥ መባ እናፈሳለን፤+ በዚያን ጊዜ እስክንጠግብ ድረስ እንበላና ተመችቶን እንኖር ነበር፤ ጥፋት የሚባል ነገርም አልገጠመንም። 18 ‘ለሰማይ ንግሥት’* መሥዋዕት ማቅረብና የመጠጥ መባ ማፍሰስ ካቆምንበት ጊዜ ጀምሮ ግን ሁሉን ነገር አጥተናል፤ እንዲሁም በሰይፍና በረሃብ አልቀናል።”

19 ሴቶቹም አክለው እንዲህ አሉ፦ “ደግሞስ ‘ለሰማይ ንግሥት’* መሥዋዕት እናቀርብና የመጠጥ መባ እናፈስ በነበረበት ጊዜ፣ በእሷ ምስል የመሥዋዕት ቂጣ የምንጋግረውና ለእሷ የመጠጥ መባ የምናፈሰው ባሎቻችንን ሳናማክር ነበር?”

20 በዚህ ጊዜ ኤርምያስ ለሕዝቡ ሁሉ ይኸውም ለወንዶቹ፣ ለሚስቶቻቸውና እያናገሩት ለነበሩት ሰዎች ሁሉ እንዲህ አለ፦ 21 “እናንተ፣ አባቶቻችሁ፣ ነገሥታታችሁ፣ መኳንንታችሁና በምድሪቱ የሚኖረው ሕዝብ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ ያቀረባችኋቸውን መሥዋዕቶች+ ይሖዋ አልዘነጋም፤ በልቡም አኑሯቸዋል! 22 በመጨረሻም ይሖዋ የፈጸማችኋቸውን ክፉ ድርጊቶችና የሠራችኋቸውን አስጸያፊ ነገሮች ሊታገሥ አልቻለም፤ ምድራችሁም ዛሬ እንደምታዩት ባድማ ስፍራ፣ አስፈሪ ቦታና ሰው የማይኖርባት ቦታ ሆነች፤ ለእርግማንም ተዳረገች።+ 23 እነዚህን መሥዋዕቶች ስላቀረባችሁ፣ ደግሞም የይሖዋን ቃል ባለመታዘዝ እንዲሁም የእሱን ሕግ፣ ደንብና ማሳሰቢያ ባለመከተል በይሖዋ ላይ ኃጢአት ስለሠራችሁ ዛሬ እንደምታዩት ይህ ጥፋት ደርሶባችኋል።”+

24 ኤርምያስ ለሕዝቡ ሁሉና ለሴቶቹ ሁሉ እንዲህ ሲል አክሎ ተናገረ፦ “በግብፅ ምድር የምትኖሩ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ፣ የይሖዋን ቃል ስሙ። 25 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እናንተና ሚስቶቻችሁ በአፋችሁ የተናገራችሁትን በእጃችሁ ፈጽማችሁታል፤ እንዲህ ብላችኋልና፦ “‘ለሰማይ ንግሥት’* መሥዋዕት ለማቅረብና ለእሷ የመጠጥ መባ ለማፍሰስ የተሳልነውን ስእለት በእርግጥ እንፈጽማለን።”+ እናንተ ሴቶች የገባችሁትን ስእለት በእርግጥ ታደርሳላችሁ፤ ስእለታችሁንም ትፈጽማላችሁ።’

26 “ስለዚህ በግብፅ ምድር የምትኖሩ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ የይሖዋን ቃል ስሙ፦ ‘“እነሆ፣ በገዛ ራሴ ታላቅ ስም እምላለሁ” ይላል ይሖዋ፤ “በመላው የግብፅ ምድር፣ የትኛውም የይሁዳ ሰው ‘ሕያው በሆነው በሉዓላዊው ጌታ በይሖዋ እምላለሁ’+ በማለት ከእንግዲህ ስሜን በመሐላ አይጠራም።+ 27 መልካም ነገር ሳይሆን ጥፋት ለማምጣት እከታተላቸዋለሁ፤+ በግብፅ ምድር የሚኖሩ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ ፈጽሞ እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍና በረሃብ ያልቃሉ።+ 28 ጥቂት ሰዎች ብቻ ከሰይፍ አምልጠው ከግብፅ ምድር ወደ ይሁዳ ምድር ይመለሳሉ።+ ከዚያም በግብፅ ምድር ለመኖር ወደዚያ የመጡት የይሁዳ ቀሪዎች ሁሉ ከእኔ ወይም ከእነሱ፣ የማን ቃል እንደተፈጸመ ያውቃሉ!”’”

29 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በእናንተ ላይ ጥፋት ለማምጣት የተናገርኩት ቃል መፈጸሙ እንደማይቀር ታውቁ ዘንድ በዚህ ስፍራ እንደምቀጣችሁ ይህ ምልክት ይሆናችኋል። 30 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን ጠላቱ ለሆነውና ሕይወቱን ሊያጠፋ ይፈልግ* ለነበረው ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾር* አሳልፌ እንደሰጠሁ ሁሉ የግብፁን ንጉሥ፣ ፈርዖን ሆፍራንም ለጠላቶቹና ሕይወቱን ለማጥፋት ለሚፈልጉት* ሰዎች አሳልፌ እሰጣለሁ።”’”+

45 የኢዮስያስ ልጅ፣ የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓቄም በነገሠ በአራተኛው ዓመት፣+ የነሪያህ ልጅ ባሮክ+ ይህን ቃል ከኤርምያስ አፍ እየሰማ በመጽሐፍ በጻፈበት ጊዜ፣+ ነቢዩ ኤርምያስ ለባሮክ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦

2 “ባሮክ፣ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ አንተን በተመለከተ እንዲህ ይላል፦ 3 ‘አንተ “ወዮልኝ፣ ይሖዋ በሥቃዬ ላይ ሐዘን ጨምሮብኛልና! ከማሰማው ሲቃ የተነሳ ዝያለሁ፤ ማረፊያ ቦታም አላገኘሁም” ብለሃል።’

4 “እሱን እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ የገነባሁትን አፈርሳለሁ፤ የተከልኩትንም እነቅላለሁ፤ ምድሪቱን በሙሉ አወድማለሁ።+ 5 አንተ ግን ለራስህ ታላላቅ ነገሮችን ትፈልጋለህ።* እንዲህ ያሉ ነገሮችን ፈጽሞ አትፈልግ።”’*

“‘በሥጋ ለባሽ* ሁሉ ላይ ጥፋት ላመጣ ነውና’+ ይላል ይሖዋ፤ ‘በምትሄድበትም ቦታ ሁሉ ሕይወትህን* እንደ ምርኮ አድርጌ እሰጥሃለሁ።’”*+

46 ብሔራትን አስመልክቶ ወደ ነቢዩ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው፦+ 2 የኢዮስያስ ልጅ የሆነው የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓቄም+ በነገሠ በአራተኛው ዓመት በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ የነበረውንና የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* በካርከሚሽ ድል ያደረገውን የግብፅን ንጉሥ የፈርዖን ኒካዑን+ ሠራዊት በተመለከተ ለግብፅ+ የተነገረ መልእክት፦

 3 “ትንሹንና* ትልቁን ጋሻችሁን አዘጋጁ፤

ለውጊያም ውጡ።

 4 እናንተ ፈረሰኞች፣ ፈረሶችን ጫኑ፤ በላያቸውም ተቀመጡ።

ቦታ ቦታችሁን ያዙ፤ የራስ ቁራችሁንም አድርጉ።

ጦሩን ወልውሉ፤ ጥሩራችሁንም ልበሱ።

 5 ‘እንዲህ ተሸብረው ያየኋቸው ለምንድን ነው?

እያፈገፈጉ ነው፤ ተዋጊዎቻቸው ተፍረክርከዋል።

በድንጋጤ እግሬ አውጪኝ ብለዋል፤ ተዋጊዎቻቸው ወደ ኋላ አልተመለከቱም።

በየቦታው ሽብር ነግሦአል’ ይላል ይሖዋ።

 6 ‘ፈጣን የሆኑት መሸሽ አይችሉም፤ ተዋጊዎቹም ማምለጥ አይችሉም።

በሰሜን በኤፍራጥስ ወንዝ ዳርቻ

ተሰናክለው ወድቀዋል።’+

 7 እንደ አባይ ወንዝ፣

እንደሚናወጥም የወንዝ ውኃ ሆኖ የሚመጣው ይህ ማን ነው?

 8 ግብፅ እንደ አባይ ወንዝና+

እንደሚናወጥ የወንዝ ውኃ ሆኖ ይመጣል፤

ደግሞም ‘እወጣለሁ፤ ምድርንም እሸፍናለሁ።

ከተማዋንና ነዋሪዎቿን አጠፋለሁ’ ይላል።

 9 እናንተ ፈረሶች፣ ወደ ላይ ውጡ!

እናንተ ሠረገሎች፣ በፍጥነት ገስግሱ!

ተዋጊዎቹ ይውጡ፤

ጋሻ የሚያነግቡት የኢትዮጵያ* እና የፑጥ ሰዎች+

እንዲሁም ደጋን የመወጠርና*+ በጥበብ የመጠቀም ችሎታ ያላቸው የሉድ+ ሰዎች ይውጡ።

10 “ያ ቀን የሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ነው፤ ጠላቶቹን የሚበቀልበት የበቀል ቀን ነው። ሰይፉ ይበላል፤ ይጠግባልም፤ ደማቸውንም እስኪረካ ድረስ ይጠጣል፤ ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ በኤፍራጥስ ወንዝ+ አጠገብ በሚገኘው የሰሜን ምድር መሥዋዕት* አዘጋጅቷልና።

11 ድንግሊቱ የግብፅ ሴት ልጅ ሆይ፣

ወደ ጊልያድ ወጥተሽ በለሳን አምጪ።+

መድኃኒት የምታበዢው እንዲያው በከንቱ ነው፤

ፈውስ አታገኚምና።+

12 ብሔራት በአንቺ ላይ የደረሰውን ውርደት ሰምተዋል፤+

ጩኸትሽም አገር ምድሩን አናውጧል።

ተዋጊ በተዋጊው ይሰናከላልና፤

ሁለቱም በአንድነት ተያይዘው ወድቀዋል።”

13 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* የግብፅን ምድር ለመምታት ስለመምጣቱ ይሖዋ ለነቢዩ ኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦+

14 “ይህን በግብፅ ተናገሩ፤ በሚግዶል+ አውጁት።

በኖፍ* እና በጣፍነስ+ አውጁት።

እንዲህም በሉ፦ ‘ቦታ ቦታችሁን ያዙ፤ ተዘጋጁም፤

ሰይፍ በዙሪያችሁ ያለውን ሁሉ ይበላልና።

15 ኃያላኖቻችሁ ተጠራርገው የጠፉት ለምንድን ነው?

ጸንተው መቆም አልቻሉም፤

ይሖዋ ገፍትሮ ጥሏቸዋልና።

16 ብዙዎቹ ይሰናከላሉ፤ ደግሞም ይወድቃሉ።

እርስ በርሳቸውም “ተነሱ!

ከጨካኙ ሰይፍ የተነሳ

ወደ ሕዝባችንና ወደ ትውልድ አገራችን እንመለስ” ይባባላሉ።’

17 በዚያም ‘ያገኘውን አጋጣሚ* ያልተጠቀመበት

የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን

ጉራውን የሚነዛው በከንቱ ነው’ ብለዋል።+

18 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ተብሎ የተጠራው ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ‘በሕያውነቴ እምላለሁ፤

እሱ* በተራሮች መካከል እንዳለው እንደ ታቦርና+

በባሕር አጠገብ እንዳለው እንደ ቀርሜሎስ+ ሆኖ ይመጣል።

19 አንቺ በግብፅ የምትኖሪ ሴት ልጅ ሆይ፣

በግዞት ለመሄድ ጓዝሽን አሰናጂ።

ኖፍ* አስፈሪ ቦታ ትሆናለችና፤

በእሳት ትጋያለች፤* ማንም ሰው የማይኖርባትም ምድር ትሆናለች።+

20 ግብፅ እንደምታምር ጊደር ናት፤

ሆኖም ከሰሜን ተናዳፊ ዝንቦች ይመጡባታል።

21 በመካከሏ ያሉት ቅጥረኛ ወታደሮችም እንኳ እንደሰቡ ጥጆች ናቸው፤

ይሁንና እነሱም ጭምር ወደ ኋላ ተመልሰው በአንድነት ሸሽተዋል።

ጸንተው መቆም አልቻሉም፤+

የሚጠፉበት ቀን፣

የሚመረመሩበትም ጊዜ ደርሶባቸዋልና።’

22 ‘ድምፅዋ እየተጥመዘመዘ እንደሚሄድ እባብ ድምፅ ነው፤

ዛፍ እንደሚቆርጡ* ሰዎች

መጥረቢያ ይዘው በኃይል ይመጡባታልና።

23 በውስጡ ማለፍ የማይቻል ቢመስልም ጫካዋን ይመነጥራሉ’ ይላል ይሖዋ።

‘ቁጥራቸው ከአንበጣ ይበልጥ ይበዛልና፤ ስፍር ቁጥርም የላቸውም።

24 የግብፅ ሴት ልጅ ለኀፍረት ትዳረጋለች።

ለሰሜን ሰዎች ትሰጣለች።’+

25 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አሁን ትኩረቴን በኖእ*+ ከተማ ወደሚገኘው ወደ አምዖን፣+ ወደ ፈርዖን፣ ወደ ግብፅ፣ ወደ አማልክቷና+ ወደ ነገሥታቷ፣ አዎ በፈርዖንና በእሱ ወደሚታመኑት ሰዎች ሁሉ አደርጋለሁ።’+

26 “‘ሕይወታቸውን ማጥፋት ለሚሹ* ሰዎች፣ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾርና* ለአገልጋዮቹ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።+ ከዚያ በኋላ ግን እንደቀድሞው ዘመን የሰው መኖሪያ ትሆናለች’ ይላል ይሖዋ።+

27 ‘አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፣ አትፍራ፤

እስራኤልም ሆይ፣ አትሸበር።+

አንተን ከሩቅ ቦታ፣

ዘሮችህንም ተማርከው ከተወሰዱበት ምድር አድናለሁና።+

ያዕቆብ ይመለሳል፤ የሚያስፈራውም ሳይኖር

ተረጋግቶና ሰላም አግኝቶ ይቀመጣል።+

28 ስለዚህ አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፣ አትፍራ’ ይላል ይሖዋ፤

‘እኔ ከአንተ ጋር ነኝና።

አንተን የበተንኩባቸውን ብሔራት ሁሉ ፈጽሞ አጠፋቸዋለሁ፤+

አንተን ግን ሙሉ በሙሉ አላጠፋህም።+

በተገቢው መጠን እገሥጽሃለሁ* እንጂ+

በምንም ዓይነት ሳልቀጣ አልተውህም።’”

47 ፈርዖን ጋዛን ከመውጋቱ በፊት ፍልስጤማውያንን+ በተመለከተ ወደ ነቢዩ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው። 2 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“እነሆ፣ ከሰሜን ውኃ እየመጣ ነው።

የሚያጥለቀልቅም ወንዝ ይሆናል።

ምድሪቱንና በውስጧ ያሉትን ሁሉ፣

ከተማዋንና ነዋሪዎቿን ያጥለቀልቃል።

ሰዎቹ ይጮኻሉ፤

በምድሪቱም የሚኖሩ ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ።

 3 ከድንጉላ ፈረሶቹ ኃይለኛ የኮቴ ድምፅ፣

ከሚንገጫገጩት የጦር ሠረገሎቹ ድምፅና

ከመንኮራኩሮቹ* የማያባራ ድምፅ የተነሳ

አባቶች እጃቸው ስለሚዝል

ልጆቻቸውን ለመርዳት እንኳ ወደ ኋላ አይዞሩም፤

 4 ምክንያቱም የሚመጣው ቀን ፍልስጤማውያንን+ ሁሉ ያጠፋል፤

በሕይወት ተርፈው ጢሮስንና+ ሲዶናን+ የሚረዱትን ሁሉ ያስወግዳል።

ይሖዋ ፍልስጤማውያንን

ይኸውም ከካፍቶር*+ ደሴት የመጡ ቀሪዎችን ያጠፋልና።

 5 ጋዛ ትመለጣለች።*

አስቀሎን ጸጥ ትላለች።+

ሸለቋሟ በሆነው ሜዳቸው* የምትኖሩ ቀሪዎች ሆይ፣

ሰውነታችሁን የምትቆርጡት እስከ መቼ ነው?+

 6 አንተ የይሖዋ ሰይፍ!+

የማታርፈው እስከ መቼ ነው?

ወደ ሰገባህ ግባ።

እረፍ፤ ጸጥ ብለህም ተቀመጥ።

 7 ይሖዋ ትእዛዝ ሰጥቶት እያለ

እንዴት አርፎ ሊቀመጥ ይችላል?

ትእዛዝ የተሰጠው በአስቀሎንና በባሕሩ ዳርቻ ላይ ነው፤+

በዚያ መድቦታል።”

48 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ስለ ሞዓብ+ እንዲህ ይላል፦

“ወዮ፣ ነቦ+ ጠፍታለችና!

ቂርያታይም+ ኀፍረት ተከናንባለች፤ ደግሞም ተይዛለች።

አስተማማኝ የሆነው መጠጊያ ተዋርዷል፤ ፈራርሷልም።+

 2 ከእንግዲህ ሞዓብን አያወድሷትም።

ለውድቀት ትዳረግ ዘንድ፣

‘ኑ ብሔር መሆኗ እንዲያከትም እንደምስሳት’ ብለው በሃሽቦን+ ይዶልቱባታል።

አንቺም ማድመን ሆይ፣ ዝም በይ፤

ከኋላሽ ሰይፍ ይከተልሻልና።

 3 ከሆሮናይም+ የጩኸት ድምፅ

እንዲሁም የጥፋትና የታላቅ ውድቀት ድምፅ ይሰማል።

 4 ሞዓብ ጠፍታለች።

ልጆቿ ይጮኻሉ።

 5 ወደ ሉሂት በሚወስደው አቀበት እያለቀሱ ይወጣሉ።

በደረሰው ጥፋት የተነሳ፣ ከሆሮናይም ቁልቁል በሚወስደው መንገድ ሲወርዱም የጭንቅ ጩኸት ይሰማሉ።+

 6 ሽሹ፤ ሕይወታችሁን አትርፉ!*

በምድረ በዳ እንዳለ የጥድ ዛፍ ሁኑ።

 7 ምክንያቱም አንቺ በሥራሽና ውድ በሆነ ሀብትሽ ትታመኛለሽ፤

ደግሞም ትያዣለሽ።

ከሞሽ+ ከካህናቱና ከመኳንንቱ ጋር

በአንድነት በግዞት ይወሰዳል።

 8 አጥፊው በእያንዳንዱ ከተማ ላይ ይመጣል፤

አንድም ከተማ አያመልጥም።+

ይሖዋ በተናገረው መሠረት

ሸለቆው* ይጠፋል፤ ደልዳላውም መሬት* እንዳልነበረ ይሆናል።

 9 ለሞዓብ ምልክት አቁሙ፤

ስትፈራርስ ትሸሻለችና፤

ከተሞቿም አስፈሪ ቦታ ይሆናሉ፤

የሚቀመጥባቸውም ሰው አይኖርም።+

10 ይሖዋ የሰጠውን ተልእኮ በግድየለሽነት የሚያከናውን የተረገመ ነው!

ሰይፉን ደም ከማፍሰስ የሚመልስ ሰው የተረገመ ነው!

11 ሞዓባውያን ከልጅነታቸው ጀምሮ

በአምቡላው ላይ እንደረጋ ወይን ጠጅ ተረጋግተው ተቀምጠዋል።

ከአንዱ ዕቃ ወደ ሌላው ዕቃ አልተገላበጡም፤

በግዞትም ተወስደው አያውቁም።

በዚህም ምክንያት ቃናቸው እንዳለ ነው፤

መዓዛቸውም አልተለወጠም።

12 “‘ስለዚህ፣ እነሆ እነሱን እንዲገለብጡ ሰዎችን የምልክበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ። ‘እነሱም ይገለብጧቸዋል፤ ዕቃዎቻቸውንም ባዶ ያስቀራሉ፤ ትላልቅ እንስራዎቻቸውንም ይሰባብራሉ። 13 የእስራኤል ቤት ይተማመንበት በነበረው በቤቴል እንዳፈረ ሁሉ ሞዓባውያንም በከሞሽ ያፍራሉ።+

14 “እኛ ለውጊያ የተዘጋጀን ኃያላን ተዋጊዎች ነን” በማለት እንዴት በድፍረት ትናገራላችሁ?’+

15 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ተብሎ የሚጠራው ንጉሥ+ እንዲህ ይላል፦

‘ሞዓብ ጠፍታለች፤

ከተሞቿ ተወረዋል፤+

ምርጥ የሆኑት ወጣቶቻቸውም ታርደዋል።’+

16 በሞዓባውያን ላይ የሚደርሰው ጥፋት ቀርቧል፤

ውድቀታቸውም በፍጥነት እየቀረበ ነው።+

17 በዙሪያቸው ያሉ ሁሉ፣

ስማቸውን የሚያውቁ ሁሉ አብረዋቸው ያዝናሉ።

‘ኃያሉ በትር፣ የውበትም ዘንግ እንዴት ተሰበረ!’ በሏቸው።

18 አንቺ በዲቦን+ የምትኖሪ ሴት ልጅ ሆይ፣

ከክብርሽ ውረጂ፤ ተጠምተሽም* ተቀመጪ፤

የሞዓብ አጥፊ በአንቺ ላይ መጥቶብሻልና፤

የተመሸጉ ቦታዎችሽንም ያፈራርሳል።+

19 አንቺ በአሮዔር+ የምትኖሪ፣ መንገዱ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ።

የሚሸሸውን ወንድና የምታመልጠውን ሴት ‘ምን ተፈጠረ?’ ብለሽ ጠይቂ።

20 ሞዓብ ኀፍረት ተከናነበች፤ በሽብርም ተውጣለች።

ዋይ ዋይ በሉ፤ እንዲሁም ጩኹ።

ሞዓብ መጥፋቷን በአርኖን+ አውጁ።

21 “ፍርድ ወደ ደልዳላው መሬት* መጥቷል፤+ በሆሎን፣ በያሃጽና+ በመፋአት፣+ 22 በዲቦን፣+ በነቦና+ በቤትዲብላታይም፣ 23 በቂርያታይም፣+ በቤትጋሙልና በቤትምዖን፣+ 24 በቀሪዮትና+ በቦስራ እንዲሁም በሩቅና በቅርብ ባሉ የሞዓብ ከተሞች ሁሉ ላይ መጥቷል።

25 ‘የሞዓብ ብርታት* ተቆርጧል፤

ክንዱም ተሰብሯል’ ይላል ይሖዋ።

26 ‘በይሖዋ ላይ ስለ ታበየ+ አስክሩት።+

ሞዓብ በትፋቱ ላይ ይንከባለላል፤

መሳለቂያም ሆኗል።

27 እስራኤል የአንተ መሳለቂያ ሆኖ አልነበረም?+

ራስህን የምትነቀንቀውና እሱን የምትቃወመው

እስራኤል ከሌቦች ጋር ተገኝቶ ነው?

28 እናንተ የሞዓብ ነዋሪዎች፣ ከከተሞቹ ወጥታችሁ በቋጥኝ ላይ ኑሩ፤

በገደል አፋፍ ጎጆዋን እንደምትሠራ ርግብም ሁኑ።’”

29 “ስለ ሞዓብ ኩራት ሰምተናል፤ እሱ በጣም ትዕቢተኛ ነው፤

ስለ እብሪቱ፣ ስለ ኩራቱ፣ ስለ ትዕቢቱና ስለ ልቡ ማበጥ ሰምተናል።”+

30 “‘ቁጣውን አውቃለሁ’ ይላል ይሖዋ፤

‘ሆኖም ጉራው ከንቱ ይሆናል።

አንዳች ነገር አያደርጉም።

31 ከዚህ የተነሳ ለሞዓብ አለቅሳለሁ፤

ለሞዓብ ምድር ሁሉ እጮኻለሁ፤

ለቂርሄረስ+ ነዋሪዎችም እቃትታለሁ።

32 የሲብማ+ ወይን ሆይ፣ ለያዜር+ ከተለቀሰው በበለጠ

ለአንቺ አለቅሳለሁ።

የተንዠረገጉት ቅርንጫፎችሽ ባሕሩን ተሻግረዋል።

እስከ ባሕሩ፣ እስከ ያዜርም ደርሰዋል።

አጥፊው በበጋ ፍሬሽና*

ለመከር በደረሰው ወይንሽ ላይ መጥቷል።+

33 ከፍራፍሬ እርሻውና ከሞዓብ ምድር

ሐሴትና ደስታ ጠፍቷል።+

ከወይን መጭመቂያዎቹ የወይን ጠጅ መፍሰሱን እንዲያቆም አድርጌአለሁ።

በእልልታ ወይን የሚረግጥ ሰው አይኖርም።

ጩኸቱ ለየት ያለ ጩኸት ይሆናል።’”+

34 “‘በሃሽቦን+ የሚያስተጋባው ጩኸት እስከ ኤልዓሌ+ ድረስ ይሰማል።

እስከ ያሃጽ+ ድረስ ድምፃቸውን ያሰማሉ፤

በዞአር የሚያስተጋባው ጩኸት እስከ ሆሮናይምና+ እስከ ኤግላት ሸሊሺያ ድረስ ይሰማል።

የኒምሪም ውኃዎች እንኳ ይደርቃሉ።+

35 ከፍ ባለ የማምለኪያ ቦታ ላይ መባ የሚያቀርበውንና

ለአምላኩ መሥዋዕት የሚያቀርበውን ሰው

ከሞዓብ አጠፋለሁ’ ይላል ይሖዋ።

36 ‘ስለዚህ ልቤ ለሞዓብ እንደ ዋሽንት* በሐዘን ያንጎራጉራል፤*+

ለቂርሄረስ ሰዎችም ልቤ እንደ ዋሽንት* በሐዘን ያንጎራጉራል።*

ያከማቸው ሀብት ይጠፋልና።

37 ራስ ሁሉ ተመልጧል፤+

ጢምም ሁሉ ተላጭቷል።

እጅ ሁሉ ተሸንትሯል፤+

በወገባቸውም ላይ ማቅ ታጥቀዋል!’”+

38 “‘በሞዓብ ጣሪያዎች ሁሉና

በአደባባዮቿ ሁሉ ላይ

ከዋይታ ሌላ የሚሰማ ነገር የለም።

ሞዓብን እንደተጣለ እንስራ

ሰባብሬአታለሁና’ ይላል ይሖዋ።

39 ‘እጅግ ተሸብራለች! ዋይ ዋይ በሉ!

ሞዓብ ኀፍረት ተከናንቦ ጀርባውን አዙሯል!

ሞዓብ መሳለቂያ ሆኗል፤

በዙሪያው ያሉት ሁሉ ከእሱ የተነሳ ይደነግጣሉ።’”

40 “ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦

‘እነሆ፣ ተወንጭፎ እንደሚወርድ ንስር፣+

እሱም በሞዓብ ላይ ክንፎቹን ይዘረጋል።+

41 ከተሞቹ ይወረራሉ፤

ምሽጎቿም ይያዛሉ።

በዚያ ቀን የሞዓብ ተዋጊዎች ልብ

ምጥ እንደያዛት ሴት ልብ ይሆናል።’”

42 “‘ሞዓብም ሕዝብ መሆኑ ያከትማል፤+

በይሖዋ ላይ ታብዮአልና።+

43 የሞዓብ ነዋሪ ሆይ፣

ሽብር፣ ጉድጓድና ወጥመድ ይጠብቅሃል’ ይላል ይሖዋ።

44 ‘ከሽብር የሚሸሽ ሁሉ ጉድጓዱ ውስጥ ይወድቃል፤

ከጉድጓዱም የሚወጣ ሁሉ በወጥመዱ ይያዛል።’

‘የሚቀጡበትን ዓመት በሞዓብ ላይ አመጣለሁና’ ይላል ይሖዋ።

45 ‘የሚሸሹት ሰዎች ኃይላቸው ተሟጦ በሃሽቦን ጥላ ሥር ይቆማሉ።

ከሃሽቦን እሳት፣

ከሲሖን መካከልም ነበልባል ይወጣልና።+

የሞዓብን ግንባርና

የሁከት ልጆችን ራስ ቅል ይበላል።’+

46 ‘ሞዓብ ሆይ፣ ወዮልህ!

የከሞሽ+ ሰዎች ጠፍተዋል።

ወንዶች ልጆችህ ተማርከዋልና፤

ሴቶች ልጆችህም በግዞት ተወስደዋል።+

47 በዘመኑ መጨረሻ ግን፣ ከሞዓብ የተማረኩትን እሰበስባለሁ’ ይላል ይሖዋ።

‘በሞዓብ ላይ የተላለፈው የፍርድ መልእክት እዚህ ላይ ይደመደማል።’”+

49 ይሖዋ፣ ስለ አሞናውያን+ እንዲህ ይላል፦

“እስራኤል ወንዶች ልጆች የሉትም?

ወራሽስ የለውም?

ታዲያ ማልካም፣+ ጋድን የወረሰው ለምንድን ነው?+

ሕዝቦቹስ በእስራኤል ከተሞች ውስጥ የሚኖሩት ለምንድን ነው?”

 2 “‘ስለዚህ እነሆ፣ አሞናውያን በሚኖሩባት በራባ+ ላይ

የጦርነት ማስጠንቀቂያ ድምፅ* የማሰማበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ።

‘የፍርስራሽ ቁልል ትሆናለች፤

በእሷም ሥር* ያሉት ከተሞች በእሳት ይቃጠላሉ።’

‘እስራኤልም የቀሙትን መልሶ በእጁ ያስገባል’+ ይላል ይሖዋ።

 3 ‘ሃሽቦን ሆይ፣ ጋይ ስለወደመች ዋይ ዋይ በዪ!

በራባ ሥር ያላችሁ ከተሞች ሆይ፣ ጩኹ።

ማቅ ልበሱ።

ማልካም ከካህናቱና ከመኳንንቱ ጋር

በግዞት ስለሚወሰድ+

ከድንጋይ በተሠራ የእንስሳት ማጎሪያ* ውስጥ ወዲያ ወዲህ እያላችሁ አልቅሱ።

 4 አንቺ በውድ ሀብቶችሽ የምትታመኚ፣

“ማን ይነካኛል?” የምትዪ

ከዳተኛ የሆንሽ ሴት ልጅ ሆይ፣

በሸለቆዎችሽ* ይኸውም ውኃ በሚንዶለዶልበት ሜዳሽ የምትኩራሪው ለምንድን ነው?’”

 5 “‘እነሆ፣ በዙሪያሽ ካሉት ሁሉ፣

በአንቺ ላይ የሚያስፈራ ነገር አመጣለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ።

‘እናንተም በየአቅጣጫው ትበታተናላችሁ፤

የሚሸሹትንም የሚሰበስብ አይኖርም።’”

 6 “‘ከዚያ በኋላ ግን ተማርከው የተወሰዱትን አሞናውያንን እሰበስባለሁ’ ይላል ይሖዋ።”

7 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ስለ ኤዶም እንዲህ ይላል፦

“ጥበብ ከቴማን+ ጠፍቷል?

ጥሩ ምክርስ ከአስተዋዮች ጠፍቷል?

ጥበባቸውስ ተበላሽቷል?

 8 የዴዳን+ ነዋሪዎች ሆይ፣ ሽሹ! ወደ ኋላ ተመለሱ!

ወደ ጥልቁ ወርዳችሁ ተደበቁ!

ትኩረቴን ወደ እሱ በማዞርበት ጊዜ

በኤሳው ላይ ጥፋት አመጣለሁና።

 9 ወይን ለቃሚዎች ወደ አንተ ቢመጡ

ጥቂት ቃርሚያ አያስቀሩም?

ሌቦች በሌሊት ቢመጡ፣

የሚዘርፉት የሚፈልጉትን ያህል ብቻ ነው።+

10 እኔ ግን ኤሳውን እርቃኑን አስቀረዋለሁ።

መደበቅ እንዳይችል

መሸሸጊያ ቦታዎቹን እገልጣለሁ።

ልጆቹ፣ ወንድሞቹና ጎረቤቶቹ በሙሉ ይጠፋሉ፤+

እሱም ከሕልውና ውጭ ይሆናል።+

11 አባት የሌላቸው ልጆችህን ተዋቸው፤

እኔ በሕይወት አኖራቸዋለሁ፤

መበለቶችህም በእኔ ይታመናሉ።”

12 ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “እነሆ፣ ጽዋውን እንዲጠጡ ያልተፈረደባቸውም እንኳ ለመጠጣት የሚገደዱ ከሆነ አንተ እንዴት ከቅጣት ታመልጣለህ? ከቅጣት አታመልጥም፤ ጽዋውን ትጠጣለህና።”+

13 “በራሴ ምያለሁና” ይላል ይሖዋ፤ “ቦስራ አስፈሪ ቦታ ትሆናለች፤+ ለነቀፋ፣ ለጥፋትና ለእርግማንም ትዳረጋለች፤ ከተሞቿም ሁሉ ለዘለቄታው ባድማ ይሆናሉ።”+

14 ከይሖዋ የመጣ አንድ መልእክት ሰምቻለሁ፤

በብሔራት መካከል አንድ መልእክተኛ ተልኳል፦

“በአንድነት ተሰብሰቡ፤ በእሷም ላይ ውጡ፤

ለጦርነት ተዘጋጁ።”+

15 “እነሆ፣ በብሔራት መካከል ከቁብ የማትቆጠር፣

በሰዎችም መካከል የተናቅክ አድርጌሃለሁና።+

16 አንተ በቋጥኝ መሸሸጊያ ውስጥ የምትኖር፣

በጣም ረጅሙን ኮረብታ የያዝክ ሆይ፣

የነዛኸው ሽብርና

የልብህ እብሪት አታሎሃል።

ጎጆህን እንደ ንስር በከፍታ ቦታ ላይ ብትሠራም፣

እኔ ከዚያ አወርድሃለሁ” ይላል ይሖዋ።

17 “ኤዶምም አስፈሪ ቦታ ትሆናለች።+ በእሷ አጠገብ የሚያልፍ ሁሉ በፍርሃት አፍጥጦ ይመለከታል፤ በደረሱባት መቅሰፍቶች ሁሉ የተነሳም ያፏጫል። 18 ሰዶምና ገሞራ እንዲሁም በአካባቢያቸው ያሉት ከተሞች በተደመሰሱ ጊዜ እንደሆነው ሁሉ”+ ይላል ይሖዋ፤ “በዚያ ማንም አይኖርም፤ አንድም ሰው በዚያ አይቀመጥም።+

19 “እነሆ፣ አንድ ሰው፣ እንደ አንበሳ በዮርዳኖስ ዳርቻ ከሚገኙ ጥቅጥቅ ያሉ ጥሻዎች ወጥቶ+ አስተማማኝ በሆነው መሰማሪያ ላይ ይመጣል፤ እኔ ግን ወዲያውኑ ከእሷ አባርረዋለሁ። የተመረጠውን በእሷ ላይ እሾማለሁ። እንደ እኔ ያለ ማነው? ማንስ ሊሟገተኝ ይችላል? በእኔ ፊት ሊቆም የሚችል እረኛ የትኛው ነው?+ 20 ስለዚህ እናንተ ሰዎች፣ ይሖዋ በኤዶም ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔና* በቴማን+ ነዋሪዎች ላይ ያሰበውን ሐሳብ ስሙ፦

ከመንጋው መካከል ትናንሽ የሆኑት ተጎትተው መወሰዳቸው አይቀርም።

ከእነሱ የተነሳ መሰማሪያቸውን ባድማ ያደርጋል።+

21 እነሱ ሲወድቁ ከሚሰማው ታላቅ ድምፅ የተነሳ ምድር ተናወጠች።

ጩኸት ይሰማል!

ድምፁም እስከ ቀይ ባሕር+ ድረስ አስተጋብቷል።

22 እነሆ፣ ልክ እንደ ንስር ወደ ላይ ይወጣና ተወንጭፎ ይወርዳል፤+

በቦስራም ላይ ክንፎቹን ይዘረጋል።+

በዚያ ቀን የኤዶም ተዋጊዎች ልብ፣

ምጥ እንደያዛት ሴት ልብ ይሆናል።”

23 ስለ ደማስቆ+ የተነገረ መልእክት፦

“ሃማትና+ አርጳድ

ክፉ ወሬ በመስማታቸው አፍረዋል።

በፍርሃት ይቀልጣሉ።

ባሕሩ ታውኳል፤ ጸጥ ሊል አይችልም።

24 ደማስቆ ወኔ ከዳት።

ለመሸሽ ወደ ኋላ ዞረች፤ ይሁንና ብርክ ያዛት።

ልትወልድ እንደተቃረበች ሴት

ጭንቅና ሥቃይ ያዛት።

25 የምትወደሰው ከተማ፣ በሐሴትም የተሞላችው መዲና

እንዴት ሳትተው ቀረች?

26 ወጣቶቿ በአደባባዮቿ ይወድቃሉና፤

በዚያም ቀን ወታደሮቿ ሁሉ ይጠፋሉ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።

27 “የደማስቆን ቅጥር በእሳት አነዳለሁ፤

እሳቱም የቤንሃዳድን የማይደፈሩ ማማዎች ይበላል።”+

28 ይሖዋ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* ስለመታቸው ስለ ቄዳርና+ ስለ ሃጾር መንግሥታት እንዲህ ይላል፦

“ተነሱ፤ ወደ ቄዳር ውጡ፤

የምሥራቅንም ሰዎች አጥፉ።

29 ድንኳኖቻቸውና መንጎቻቸው፣

የድንኳን ሸራዎቻቸውና ዕቃዎቻቸው ሁሉ ይወሰዳሉ።

ግመሎቻቸውን ይነጠቃሉ፤

‘ሽብር በየቦታው ነግሦአል!’ ብለው ወደ እነሱ ይጮኻሉ።”

30 “እናንተ የሃጾር ነዋሪዎች፣ ሽሹ፤ ወደ ሩቅ ቦታም ተሰደዱ!

ወደ ጥልቁ ወርዳችሁ ተደበቁ” ይላል ይሖዋ።

“የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* በእናንተ ላይ የጦር ስልት ነድፏልና፤

በእናንተም ላይ አንድ ዕቅድ አቅዷል።”

31 “በሰላም፣ ተረጋግቶ በተቀመጠው ብሔር ላይ

ተነሱ፣ ውጡ!” ይላል ይሖዋ።

“በሮችም ሆነ መቀርቀሪያዎች የሉትም፤ ብቻቸውንም ይኖራሉ።

32 ግመሎቻቸው ይበዘበዛሉ፤

ብዛት ያላቸው ከብቶቻቸውም በምርኮ ይወሰዳሉ።

በሰሪሳራቸው* ላይ ያለውን ፀጉር የሚላጩትን ሰዎች+

ነፋስ ወደሚነፍስበት አቅጣጫ ሁሉ* እበትናቸዋለሁ፤

ከሁሉም አቅጣጫ ጥፋት አመጣባቸዋለሁ” ይላል ይሖዋ።

33 “ሃጾርም የቀበሮዎች ጎሬ፣

ለዘለቄታውም ባድማ ትሆናለች።

በዚያ ማንም ሰው አይኖርም፤

አንድም ሰው በእሷ ውስጥ አይቀመጥም።”

34 በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ+ ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ ላይ ኤላምን+ አስመልክቶ ወደ ነቢዩ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው፦ 35 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ የብርታታቸው ምንጭ* የሆነውን የኤላምን+ ቀስት እሰብራለሁ። 36 ከአራቱ የሰማያት ዳርቻዎች፣ አራቱን ነፋሳት በኤላም ላይ አመጣለሁ፤ እኔም እነዚህ ነፋሳት በሚነፍሱበት አቅጣጫ ሁሉ እበትናቸዋለሁ። ከኤላም የተበተኑት ሰዎችም የማይሄዱበት ብሔር አይኖርም።’”

37 “ኤላማውያንን በጠላቶቻቸውና ሕይወታቸውን ማጥፋት በሚሹ* ሰዎች ፊት አሸብራለሁ፤ በእነሱም ላይ ጥፋትን ይኸውም የሚነድ ቁጣዬን አመጣለሁ” ይላል ይሖዋ። “ፈጽሞ እስካጠፋቸውም ድረስ ከኋላቸው ሰይፍ እሰዳለሁ።”

38 “እኔም ዙፋኔን በኤላም+ አደርጋለሁ፤ ከዚያም ስፍራ ንጉሡንና መኳንንቱን አስወግዳለሁ” ይላል ይሖዋ።

39 “በዘመኑ መጨረሻ ግን ከኤላም ተማርከው የተወሰዱትን እሰበስባለሁ” ይላል ይሖዋ።

50 ይሖዋ በነቢዩ ኤርምያስ በኩል ስለ ባቢሎን+ ይኸውም ስለ ከለዳውያን ምድር የተናገረው ቃል ይህ ነው፦

 2 “በብሔራት መካከል ይህን ተናገሩ፤ ደግሞም አውጁ።

ምልክት* አቁሙ፤ ይህን አውጁ።

ምንም ነገር አትደብቁ!

እንዲህም በሉ፦ ‘ባቢሎን ተይዛለች።+

ቤል ኀፍረት ተከናንቧል።+

ሜሮዳክ በፍርሃት ርዷል።

ምስሎቿ ተዋርደዋል።

አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቿ* ተሸብረዋል።’

 3 ከሰሜን አንድ ብሔር በእሷ ላይ ተነስቷልና።+

እሱም ምድሪቷን አስፈሪ ቦታ ያደርጋታል፤

በእሷ ውስጥ የሚኖር ሰው የለም።

ሰውም ሆነ እንስሳ ሸሽቷል፤

አካባቢውን ለቀው ሄደዋል።”

4 “በእነዚያ ቀናትና በዚያ ጊዜ” ይላል ይሖዋ፣ “የእስራኤል ሕዝብም ሆነ የይሁዳ ሕዝብ በአንድነት ይመጣሉ።+ እያለቀሱ ይሄዳሉ፤+ በአንድነትም አምላካቸውን ይሖዋን ይፈልጋሉ።+ 5 ወደ ጽዮን የሚወስደውን መንገድ ይጠይቃሉ፤+ ፊታቸውንም ወደዚያ አቅጣጫ አዙረው ‘ኑ፣ ከይሖዋ ጋር የማይረሳ ዘላለማዊ ቃል ኪዳን እንግባ’ ይላሉ።+ 6 ሕዝቤ የጠፉ በጎች መንጋ ሆኗል።+ የገዛ እረኞቻቸው እንዲባዝኑ አድርገዋቸዋል።+ ወደ ተራሮች ነዷቸው፤ እነሱም በየተራራውና በየኮረብታው ተቅበዘበዙ። ማረፊያ ቦታቸውን ረሱ። 7 ያገኟቸውም ሁሉ ዋጧቸው፤+ ጠላቶቻቸውም ‘በይሖዋ ይኸውም የጽድቅ መኖሪያና የአባቶቻቸው ተስፋ በሆነው በይሖዋ ላይ ኃጢአት ስለሠሩ እኛ በደለኞች አይደለንም’ ብለዋል።”

 8 “ከባቢሎን መካከል ወጥታችሁ ሽሹ፤

ከከለዳውያንም ምድር ውጡ፤+

መንጋውንም እንደሚመሩ እንስሳት* ሁኑ።

 9 እነሆ፣ እኔ ከሰሜን ምድር የታላላቅ ብሔራትን ጉባኤ አስነስቼ

በባቢሎን ላይ አመጣባታለሁና።+

እነሱም እሷን ለመውጋት ይሰለፋሉ፤

በዚያም በኩል ትያዛለች።

ፍላጻዎቻቸው እንደ ተዋጊ ፍላጻዎች ናቸው፤

ወላጆችን የወላድ መሃን ያደርጋሉ፤+

ዓላማቸውን ሳይፈጽሙ አይመለሱም።

10 የከለዳውያን ምድር ትበዘበዛለች።+

የሚበዘብዟትም ሁሉ እስኪበቃቸው ድረስ ይመዘብሯታል”+ ይላል ይሖዋ።

11 “እናንተ እጅግ ደስ ብሏችኋልና፤+

የገዛ ርስቴን ስትመዘብሩ ሐሴት አድርጋችኋል።+

በለምለም ሣር ላይ እንዳለች ጊደር ፈንጭታችኋልና፤

እንደ ድንጉላ ፈረሶችም አሽካክታችኋል።

12 እናታችሁ ለኀፍረት ተዳርጋለች።+

የወለደቻችሁም እጅግ አዝናለች።

እነሆ፣ ከብሔራት ሁሉ ያነሰች፣

ውኃ የሌለባት ምድረ በዳና በረሃ ሆናለች።+

13 ከይሖዋ ቁጣ የተነሳ ሰው የማይኖርባት ምድር ትሆናለች፤+

ሙሉ በሙሉ ባድማ ትሆናለች።+

በባቢሎን በኩል የሚያልፍ ሁሉ በፍርሃት አፍጥጦ ይመለከታታል፤

ከደረሱባትም መቅሰፍቶች ሁሉ የተነሳ ያፏጫል።+

14 እናንተ ደጋን የምትወጥሩ* ሁሉ፣

ባቢሎንን ለመውጋት በዙሪያዋ ተሰለፉ።

ፍላጻ ወርውሩባት፤ በይሖዋ ላይ ኃጢአት ስለሠራች+

አንድም ፍላጻ አታስቀሩ።+

15 በዙሪያዋ ሁሉ ቀረርቶ አሰሙ።

እጇን ሰጥታለች።

ዓምዶቿ ወድቀዋል፤ ቅጥሮቿ ፈርሰዋል፤+

ይህ የይሖዋ በቀል ነውና።+

እሷን ተበቀሏት።

እንዳደረገችው አድርጉባት።+

16 ዘር የሚዘራውንና

በመከር ወቅት ማጭድ የሚይዘውን ከባቢሎን አስወግዱ።+

ከጨካኙ ሰይፍ የተነሳ እያንዳንዱ ወደ ገዛ ሕዝቡ ይመለሳል፤

እያንዳንዱም ወደ ገዛ ምድሩ ይሸሻል።+

17 “የእስራኤል ሕዝብ የባዘነ በግ ነው።+ እንዲባዝን ያደረጉት አንበሶች ናቸው።+ በመጀመሪያ የአሦር ንጉሥ በላው፤+ ከዚያም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* አጥንቱን ቆረጣጠመው።+ 18 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ በአሦር ንጉሥ ላይ እንዳደረግኩት ሁሉ በባቢሎን ንጉሥና በምድሩ ላይ እንዲሁ አደርጋለሁ።+ 19 እስራኤልንም ወደ መሰማሪያው እመልሰዋለሁ፤+ እሱም በቀርሜሎስና በባሳን ይሰማራል፤+ በኤፍሬምና+ በጊልያድ+ ተራሮችም ላይ እስኪጠግብ ድረስ ይመገባል።’”*

20 “በእነዚያ ቀናትና በዚያ ጊዜ” ይላል ይሖዋ፣

“የእስራኤል በደል ይፈለጋል፤

ሆኖም አይገኝም፤

የይሁዳም ኃጢአት አይገኝም፤

እንዲተርፉ ያደረግኳቸውን ይቅር እላቸዋለሁና።”+

21 “በመረታይም ምድር ላይ ውጣ፤ በጰቆድ+ ነዋሪዎችም ላይ ተነሳ።

ነዋሪዎቹ ይጨፍጨፉ፤ ሙሉ በሙሉም ይጥፉ”* ይላል ይሖዋ።

“ያዘዝኩህንም ሁሉ አድርግ።

22 በምድሪቱ ላይ የጦርነትና

የታላቅ ጥፋት ድምፅ ይሰማል።

23 የምድር ሁሉ መዶሻ እንዴት ተቆረጠ! እንዴትስ ተሰበረ!+

ባቢሎን በብሔራት መካከል እንዴት መቀጣጫ ሆነች!+

24 ባቢሎን ሆይ፣ በአንቺ ላይ ወጥመድ ዘርግቻለሁ፤ ደግሞም ተይዘሻል፤

አንቺ ግን አልታወቀሽም።

ተገኘሽ፤ እንዲሁም ተያዝሽ፤+

የተቃወምሽው ይሖዋን ነውና።

25 ይሖዋ ግምጃ ቤቱን ከፍቷል፤

የቁጣ የጦር መሣሪያዎቹንም ያወጣል።+

ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ

በከለዳውያን ምድር የሚሠራው ሥራ አለና።

26 ከሩቅ ቦታ መጥታችሁ በእሷ ላይ ውጡ።+

ጎተራዎቿን ክፈቱ።+

እንደ እህል ክምር ከምሯት።

ፈጽማችሁ አጥፏት።+

አንድም ሰው አታስቀሩላት።

27 ወይፈኖቿን ሁሉ እረዱ፤+

ወደ እርድ ቦታ ይውረዱ።

ቀናቸው ይኸውም የሚመረመሩበት ጊዜ

ስለደረሰ ወዮላቸው!

28 የአምላካችንን የይሖዋን በቀል፣

ስለ ቤተ መቅደሱ ሲል የወሰደውን የበቀል እርምጃ+ በጽዮን ለማወጅ

ከባቢሎን ምድር የሚሸሹና

አምልጠው የሚሄዱ ሰዎች ድምፅ ይሰማል።

29 ቀስተኞችን፣ ደጋን የሚወጥሩትንም* ሁሉ

በባቢሎን ላይ ጥሩ።+

በዙሪያዋም ስፈሩ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ።

እንደ ሥራዋ መልሱላት።+

እሷ እንዳደረገችው ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉባት።+

በይሖዋ ላይ ይኸውም በእስራኤል ቅዱስ ላይ

የእብሪት ድርጊት ፈጽማለችና።+

30 በመሆኑም ወጣቶቿ በአደባባዮቿ ይወድቃሉ፤+

በዚያም ቀን ወታደሮቿ ሁሉ ይጠፋሉ”* ይላል ይሖዋ።

31 “አንቺ ዓመፀኛ፣+ እነሆ፣ እኔ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ”+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤

“ቀንሽ ይኸውም አንቺን ተጠያቂ የማደርግበት ጊዜ ይመጣልና።

32 አንቺ ዓመፀኛ ተሰናክለሽ ትወድቂያለሽ፤

የሚያነሳሽም አይኖርም።+

ከተሞችሽንም በእሳት አነዳለሁ፤

በዙሪያሽም ያለውን ሁሉ ይበላል።”

33 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“የእስራኤል ሕዝብና የይሁዳ ሕዝብ ተጨቁነዋል፤

ማርከው የወሰዷቸውም ሁሉ ጠፍረው ይዘዋቸዋል።+

እነሱን ለመልቀቅ ፈቃደኞች አልሆኑም።+

34 ይሁንና የሚቤዣቸው ብርቱ ነው።+

ስሙ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ነው።+

ለምድሪቱ እረፍት ለመስጠትና+

የባቢሎንን ነዋሪዎች ለማሸበር+

ያላንዳች ጥርጥር ይሟገትላቸዋል።”+

35 “በከለዳውያን፣ በባቢሎን ነዋሪዎች፣ በመኳንንቷ

እንዲሁም በጥበበኞቿ ላይ ሰይፍ ተመዟል” ይላል ይሖዋ።+

36 “ከንቱ ነገር በሚናገሩ ሰዎች* ላይ ሰይፍ ተመዟል፤ እነሱም የሞኝነት ድርጊት ይፈጽማሉ።

በተዋጊዎቿ ላይ ሰይፍ ተመዟል፤ እነሱም በሽብር ይዋጣሉ።+

37 በፈረሶቻቸው፣ በጦር ሠረገሎቻቸውና

በመካከሏ በሚኖሩ ድብልቅ ሕዝብ ሁሉ ላይ ሰይፍ ተመዟል፤

እነሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ።+

ውድ በሆኑ ሀብቶቿ ላይ ሰይፍ ተመዟል፤ እነሱም ይዘረፋሉ።+

38 ውኃዎቿ ይበከላሉ፤ ይደርቃሉም።+

የተቀረጹ ምስሎች ምድር ናትና፤+

አስፈሪ በሆኑት ራእዮቻቸው የተነሳ እንደ እብድ ያደርጋቸዋል።

39 ስለዚህ የበረሃ ፍጥረታት ከሚያላዝኑ እንስሳት ጋር ይኖራሉ፤

በእሷም ውስጥ ሰጎኖች ይኖራሉ።+

ከዚህ በኋላ የሚኖርባት አይገኝም፤

ከትውልድ እስከ ትውልድም ማንም አይቀመጥባትም።”+

40 “አምላክ ሰዶምንና ገሞራን+ እንዲሁም በአካባቢያቸው ያሉትን ከተሞች በደመሰሰ ጊዜ+ እንደሆነው ሁሉ” ይላል ይሖዋ፣ “በዚያ ማንም አይኖርም፤ አንድም ሰው በዚያ አይቀመጥም።+

41 እነሆ፣ አንድ ሕዝብ ከሰሜን ይመጣል፤

አንድ ታላቅ ብሔርና ታላላቅ ነገሥታት+

ከምድር ዳርቻዎች ይነሳሉ።+

42 ቀስትና ጦር ይይዛሉ።+

ጨካኝና ምሕረት የለሽ ናቸው።+

ፈረሶቻቸውን እየጋለቡ ሲመጡ

ድምፃቸው እንደሚጮኽ ባሕር ነው።+

የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ፣ አንቺን ለመውጋት በአንድ ልብ ሆነው ይሰለፉብሻል።+

43 የባቢሎን ንጉሥ ስለ እነሱ ወሬ ሰምቷል፤+

እጆቹም ይዝለፈለፋሉ።+

ጭንቀት ይይዘዋል፤

ልትወልድ እንደተቃረበች ሴት ይሠቃያል።

44 “እነሆ፣ አንድ ሰው፣ እንደ አንበሳ በዮርዳኖስ ዳርቻ ከሚገኙ ጥቅጥቅ ያሉ ጥሻዎች ወጥቶ አስተማማኝ በሆነው መሰማሪያ ላይ ይመጣል፤ እኔ ግን ወዲያውኑ ከእሷ አባርራቸዋለሁ። የተመረጠውን በእሷ ላይ እሾማለሁ።+ እንደ እኔ ያለ ማነው? ማንስ ሊሟገተኝ ይችላል? በእኔ ፊት ሊቆም የሚችል እረኛ የትኛው ነው?+ 45 ስለዚህ እናንተ ሰዎች፣ ይሖዋ በባቢሎን ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔና*+ በከለዳውያን ምድር ላይ ያሰበውን ሐሳብ ስሙ።

ከመንጋው መካከል ትናንሽ የሆኑት ተጎትተው መወሰዳቸው አይቀርም።

ከእነሱ የተነሳ መሰማሪያቸውን ባድማ ያደርጋል።+

46 ባቢሎን ስትያዝ ከሚሰማው ድምፅ የተነሳ ምድር ትናወጣለች፤

ከብሔራትም መካከል ጩኸት ይሰማል።”+

51 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“እነሆ፣ በባቢሎንና+ በሌብቃማይ* ነዋሪዎች ላይ

አጥፊ ነፋስ አስነሳለሁ።

 2 እህል የሚያዘሩ* ሰዎችን ወደ ባቢሎን እሰዳለሁ፤

እነሱም ያዘሯታል፤ ምድሯንም ባዶ ያደርጋሉ፤

በጥፋት ቀን ከሁሉም አቅጣጫ ይመጡባታል።+

 3 ቀስተኛው ደጋኑን አይወጥር።*

በተጨማሪም ማንም ሰው ጥሩሩን ለብሶ አይነሳ።

ለወጣቶቿ ምንም ዓይነት ርኅራኄ አታሳዩ።+

ሠራዊቷን ሁሉ ፈጽማችሁ አጥፉ።

 4 እነሱም በከለዳውያን ምድር ታርደው፣

በጎዳናዎቿም ላይ ክፉኛ ቆስለው ይወድቃሉ።+

 5 እስራኤልና ይሁዳ ከአምላካቸው፣ ከሠራዊት ጌታ ከይሖዋ ተለይተው መበለት አልሆኑም።+

ምድራቸው* ግን በእስራኤል ቅዱስ ፊት በበደል ተሞልታለች።

 6 ከባቢሎን መካከል ሸሽታችሁ ውጡ፤

ሕይወታችሁን* አድኑ።+

በእሷ በደል የተነሳ አትጥፉ።

ይህ የይሖዋ የበቀል ጊዜ ነውና።

ላደረገችው ነገር የእጇን ይከፍላታል።+

 7 ባቢሎን በይሖዋ እጅ ያለች የወርቅ ጽዋ ነበረች፤

ምድርን ሁሉ አሰከረች።

ብሔራት ወይን ጠጇን ጠጥተው ሰከሩ፤+

ብሔራት ያበዱት ለዚህ ነው።+

 8 ባቢሎን በድንገት ወድቃ ተሰበረች።+

ዋይ ዋይ በሉላት!+

ለሕመሟ የሚሆን በለሳን ውሰዱላት፤ ምናልባት ትፈወስ ይሆናል።”

 9 “ባቢሎንን ለመፈወስ ሞክረን ነበር፤ እሷ ግን ልትፈወስ አልቻለችም።

ትታችኋት ሂዱ፤ እያንዳንዳችንም ወደ ገዛ ምድራችን እንሂድ።+

ፍርዷ እስከ ሰማያት ደርሷልና፤

እስከ ደመናት ድረስ ከፍ ብሏል።+

10 ይሖዋ ፍትሕ አስፍኖልናል።+

ኑ፣ የአምላካችንን የይሖዋን ሥራ በጽዮን እንናገር።”+

11 “ፍላጻዎቻችሁን አሹሉ፤+ ክብ የሆኑትን ጋሻዎች አንሱ።*

ይሖዋ የሜዶናውያንን ነገሥታት መንፈስ አነሳስቷል፤+

ምክንያቱም ባቢሎንን ለማጥፋት አስቧል።

ይህ የይሖዋ በቀል ይኸውም ስለ ቤተ መቅደሱ የሚወስደው የበቀል እርምጃ ነውና።

12 የባቢሎንን ቅጥሮች ለማጥቃት ምልክት* አቁሙ።+

ጥበቃውን አጠናክሩ፤ ጠባቂዎችን አቁሙ።

ሽምቅ ተዋጊዎችን አዘጋጁ።

ይሖዋ በባቢሎን ነዋሪዎች ላይ የጦር ስልት ነድፏልና፤

በእነሱ ላይ የተናገረውንም ቃል ይፈጽማል።”+

13 “አንቺ በብዙ ውኃዎች ላይ የምትኖሪ፣+

በሀብትም የበለጸግሽ ሆይ፣+

መጨረሻሽ ቀርቧል፤ አላግባብ የምታገኚው ትርፍ ገደቡ ላይ ደርሷል።+

14 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ሲል በራሱ* ምሏል፦

‘እንደ አንበጣ ብዛት ባላቸው ሰዎች እሞላሻለሁ፤

እነሱም በአንቺ ላይ በድል አድራጊነት ይጮኻሉ።’+

15 ምድርን በኃይሉ የሠራው፣

ፍሬያማ የሆነችውን መሬት በጥበቡ የመሠረተውና+

ሰማያትን በማስተዋሉ የዘረጋው እሱ ነው።+

16 ድምፁን ሲያሰማ

በሰማያት ያሉ ውኃዎች ይናወጣሉ፤

ደመና* ከምድር ዳርቻዎች ወደ ላይ እንዲወጣ ያደርጋል።

በዝናብ ጊዜ መብረቅን ያበርቃል፤*

ነፋሱንም ከግምጃ ቤቱ ያወጣል።+

17 እያንዳንዱ ሰው ማስተዋልና እውቀት የጎደለው ድርጊት ይፈጽማል።

እያንዳንዱ አንጥረኛ፣ በተቀረጸው ምስል የተነሳ ኀፍረት ይከናነባል፤+

ከብረት የተሠራው ምስሉ* ሐሰት ነውና፤

በውስጣቸውም መንፈስ* የለም።+

18 እነሱ ከንቱና*+ መሳለቂያ ናቸው።

የሚመረመሩበት ቀን ሲመጣ ይጠፋሉ።

19 የያዕቆብ ድርሻ ግን እንደነዚህ ነገሮች አይደለም፤

እሱ የርስቱን በትር ጨምሮ

የሁሉ ነገር ሠሪ ነውና።+

ስሙ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ነው።”+

20 “አንቺ ለእኔ እንደ ቆመጥ፣ እንደ ጦር መሣሪያም ነሽ፤

በአንቺ ብሔራትን አደቃለሁ።

በአንቺ መንግሥታትን አወድማለሁ።

21 በአንቺ ፈረሱንና ፈረሰኛውን አደቃለሁ።

በአንቺ የጦር ሠረገላውንና ነጂውን አደቃለሁ።

22 በአንቺ ወንድንና ሴትን አደቃለሁ።

በአንቺ ሽማግሌንና ልጅን አደቃለሁ።

በአንቺ ወጣቱንና ወጣቷን አደቃለሁ።

23 በአንቺ እረኛንና መንጋውን አደቃለሁ።

በአንቺ ገበሬንና ጥማድ ከብቶቹን አደቃለሁ።

በአንቺ ገዢዎችንና የበታች ገዢዎችን አደቃለሁ።

24 ደግሞም በጽዮን፣ በፊታችሁ ለሠሩት ክፋት ሁሉ

ባቢሎንንና የከለዳውያን ምድር ነዋሪዎችን በሙሉ ዋጋቸውን እከፍላቸዋለሁ”+ ይላል ይሖዋ።

25 “አንቺ ምድርን ሁሉ ያጠፋሽ፣+

አጥፊ ተራራ ሆይ፣ እነሆ እኔ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ”+ ይላል ይሖዋ።

“በአንቺ ላይ እጄን እዘረጋለሁ፤ ከቋጥኞችም ላይ አንከባልልሻለሁ፤

የተቃጠለም ተራራ አደርግሻለሁ።”

26 “ሰዎች የማዕዘን ድንጋይም ሆነ የመሠረት ድንጋይ ከአንቺ አይወስዱም፤

ምክንያቱም አንቺ ለዘላለም ባድማ ትሆኛለሽ”+ ይላል ይሖዋ።

27 “በምድሪቱ ላይ ምልክት* አቁሙ።+

በብሔራት መካከል ቀንደ መለከት ንፉ።

በእሷ ላይ እንዲዘምቱ ብሔራትን መድቡ።*

የአራራት፣+ የሚኒ እና የአሽከናዝ መንግሥታት+ እሷን እንዲወጉ ሰብስቧቸው።

በላይዋም ወታደሮችን የሚመለምል መኮንን ሹሙባት።

ፈረሶችንም እንደ ኩብኩባ ስደዱባት።

28 ብሔራትን፣ የሜዶንን+ ነገሥታት፣ ገዢዎቿን፣ የበታች ገዢዎቿን ሁሉና

በእያንዳንዳቸው ግዛት ሥር ያለውን ምድር ሁሉ

በእሷ ላይ እንዲዘምቱ መድቧቸው።*

29 ምድርም ትናወጣለች፤ ትንቀጠቀጣለችም፤

ይሖዋ የባቢሎንን ምድር አስፈሪ ቦታና ሰው አልባ ለማድረግ

በባቢሎን ላይ ያሰበው ሐሳብ ይፈጸማልና።+

30 የባቢሎን ተዋጊዎች መዋጋት አቁመዋል።

በምሽጎቻቸው ውስጥ ይቀመጣሉ።

ጉልበት ከድቷቸዋል።+

እንደ ሴት ሆነዋል።+

መኖሪያዎቿ በእሳት ነደዋል።

መቀርቀሪያዎቿ ተሰብረዋል።+

31 ከተማው በየአቅጣጫው እንደተያዘች ለባቢሎን ንጉሥ ለመንገር

አንዱ መልእክተኛ ሲሮጥ ከሌላው መልእክተኛ ጋር፣

አንዱም ወሬ ነጋሪ ሲሮጥ ከሌላው ወሬ ነጋሪ ጋር ይገናኛል፤+

32 መልካዎቹ* እንደተያዙ፣+

የደንገል ጀልባዎቹ በእሳት እንደተቃጠሉና

ወታደሮቹ እንደተሸበሩ ሊነግሩት ይሯሯጣሉ።”

33 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦

“የባቢሎን ሴት ልጅ እንደ አውድማ ናት።

ይህ በኃይል የምትረገጥበት ጊዜ ነው።

በአጭር ጊዜ ውስጥ የመከር ወቅት ይደርስባታል።”

34 “የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* ዋጠኝ፤+

ጨርሶ ግራ አጋባኝ።

እንደ ባዶ ዕቃ አደረገኝ።

እንደ ትልቅ እባብ ዋጠኝ፤+

የእኔን መልካም ነገሮች በልቶ ሆዱን ሞላ።

በውኃም ጠራርጎ አስወገደኝ።

35 የጽዮን ነዋሪ ‘በእኔና በአካሌ ላይ የተፈጸመው ግፍ በባቢሎን ላይ ይድረስ!’ ትላለች።+

ኢየሩሳሌም ‘ደሜም በከለዳውያን ምድር ነዋሪዎች ላይ ይሁን!’ ትላለች።”

36 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“እነሆ፣ እኔ እሟገትልሻለሁ፤+

ደግሞም እበቀልልሻለሁ።+

ባሕሯን አደርቃለሁ፤ የውኃ ጉድጓዶቿንም ደረቅ አደርጋለሁ።+

37 ባቢሎንም የድንጋይ ቁልል፣+

የቀበሮዎች ጎሬ፣+

አስፈሪ ቦታና ማፏጫ ትሆናለች፤

የሚኖርባትም አይገኝም።+

38 ሁሉም በአንድነት እንደ ደቦል አንበሳ ያገሳሉ።

እንደ አንበሳ ግልገሎች ያጉረመርማሉ።”

39 “ፍላጎታቸው በኃይል ሲነሳሳ እጅግ ደስ እንዲሰኙ

ድግሳቸውን አዘጋጅላቸዋለሁ፤ እንዲሰክሩም አደርጋለሁ፤+

ከዚያም ጨርሶ ላይነቁ

እስከ ወዲያኛው ያንቀላፋሉ”+ ይላል ይሖዋ።

40 “እንደ ጠቦቶች፣

እንደ አውራ በጎችም ከፍየሎች ጋር ወደሚታረዱበት ቦታ አወርዳቸዋለሁ።”

41 “ሼሻቅ* እንዴት ተማረከች!+

የምድር ሁሉ ‘ውዳሴ’ እንዴት ተያዘች!+

ባቢሎን በብሔራት መካከል ምንኛ አስፈሪ ቦታ ሆነች!

42 ባሕሩ ባቢሎንን አጥለቅልቋታል።

በማዕበሉ ብዛት ተሸፍናለች።

43 ከተሞቿ አስፈሪ ቦታ እንዲሁም ውኃ የሌለበት ምድርና በረሃ ሆነዋል።

ማንም ሰው የማይኖርበትና አንድም ሰው የማያልፍበት ምድር ሆነዋል።+

44 ትኩረቴን በባቢሎን በሚገኘው በቤል+ ላይ አደርጋለሁ፤

የዋጠውንም ከአፉ አስተፋዋለሁ።+

ብሔራት ከእንግዲህ ወደ እሱ አይጎርፉም፤

የባቢሎንም ቅጥር ይፈርሳል።+

45 ሕዝቤ ሆይ፣ ከመካከሏ ውጡ!+

ከሚነደው የይሖዋ ቁጣ+ ሕይወታችሁን* ለማትረፍ ሽሹ!+

46 በምድሪቱ ላይ በሚሰማው ወሬ ልባችሁ አይሸበር፤ በፍርሃትም አትዋጡ።

በምድሪቱ ላይ ዓመፅ ስለመኖሩ፣

ገዢም በገዢ ላይ ስለመነሳቱ፣ በአንደኛው ዓመት አንድ ወሬ ይሰማል፤

በቀጣዩ ዓመት ደግሞ ሌላ ወሬ ይናፈሳል።

47 ስለዚህ፣ እነሆ ትኩረቴን

በባቢሎን የተቀረጹ ምስሎች ላይ የማደርግበት ጊዜ ይመጣል።

ምድሪቱ በሙሉ ኀፍረት ትከናነባለች፤

የታረዱባትም ሰዎች ሁሉ በመካከሏ ይወድቃሉ።+

48 ሰማያትና ምድር እንዲሁም በውስጣቸው ያሉት ሁሉ

በባቢሎን የተነሳ እልል ይላሉ፤+

አጥፊዎች ከሰሜን ይመጡባታልና”+ ይላል ይሖዋ።

49 “ባቢሎን ተጠያቂ የሆነችው ታርደው ለወደቁት እስራኤላውያን ብቻ አይደለም፤+

ከዚህ ይልቅ ከመላው ምድር የመጡ ሰዎችም በባቢሎን ታርደው ወድቀዋል።

50 እናንተ ከሰይፍ ያመለጣችሁ፣ መንገዳችሁን ቀጥሉ፤ ፈጽሞ አትቁሙ!+

በሩቅ ቦታ ሆናችሁ ይሖዋን አስታውሱ፤

ኢየሩሳሌምንም በልባችሁ አስቡ።”+

51 “ዘለፋውን ስለሰማን በኀፍረት ተውጠናል።

ባዕድ ሰዎች* በይሖዋ ቤት ባሉት ቅዱስ ስፍራዎች ላይ ስለተነሱ

ውርደት ፊታችንን ሸፍኖታል።”+

52 “ስለዚህ፣ እነሆ ትኩረቴን

በተቀረጹ ምስሎቿ ላይ የማደርግበት ጊዜ ይመጣል” ይላል ይሖዋ፤

“በምድሪቱም ሁሉ፣ የቆሰሉት ሰዎች ያቃስታሉ።”+

53 “ባቢሎን ወደ ሰማያት ብትወጣ፣+

ከፍ ያሉ ምሽጎቿንም ብታጠናክር እንኳ፣

እሷን የሚያጠፉ ከእኔ ዘንድ ይመጡባታል”+ ይላል ይሖዋ።

54 “ስሙ! ከባቢሎን ጩኸት፣+

ከከለዳውያንም ምድር የታላቅ ጥፋት ድምፅ ይሰማል፤+

55 ይሖዋ ባቢሎንን ያጠፋልና፤

ታላቅ ድምፅዋን ጸጥ ያሰኛል፤

ሞገዳቸውም እንደ ብዙ ውኃዎች ያስተጋባል።

የድምፃቸው ጩኸት ይሰማል።

56 በባቢሎን ላይ አጥፊ ይመጣልና፤+

ተዋጊዎቿ ይያዛሉ፤+

ቀስቶቻቸው ይሰባበራሉ፤

ይሖዋ የሚበቀል አምላክ ነውና።+

በእርግጥ ብድራትን ይመልሳል።+

57 መኳንንቷንና ጥበበኞቿን፣

ገዢዎቿንና የበታች ገዢዎቿን እንዲሁም ተዋጊዎቿን አሰክራለሁ፤+

እነሱም ጨርሶ ላይነቁ

እስከ ወዲያኛው ያንቀላፋሉ”+ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ የሆነው ንጉሥ።

58 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“የባቢሎን ቅጥር ሰፊ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ይፈርሳል፤+

በሮቿ ረጃጅም ቢሆኑም በእሳት ይጋያሉ።

ሰዎቹ በከንቱ ይደክማሉ፤

ብሔራትም እሳት ለሚበላው ነገር ራሳቸውን እንዲሁ ያደክማሉ።”+

59 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት የማህሴያህ ልጅ፣ የነሪያህ+ ልጅ ሰራያህ ከንጉሡ ጋር ወደ ባቢሎን በተጓዘ ጊዜ፣ ነቢዩ ኤርምያስ ለእሱ የሰጠው ትእዛዝ ይህ ነው፤ ሰራያህ የቤተ መንግሥት አስተዳዳሪ ነበር። 60 ኤርምያስ በባቢሎን ላይ የሚመጣውን ጥፋት ሁሉ፣ ደግሞም በባቢሎን ላይ ስለሚደርሰው ነገር የተጻፈውን ይህን ቃል ሁሉ በአንድ መጽሐፍ ላይ ጻፈው። 61 በተጨማሪም ኤርምያስ ሰራያህን እንዲህ አለው፦ “ባቢሎን ስትደርስና ከተማዋን ስታይ ድምፅህን ከፍ አድርገህ ይህን ቃል ሁሉ አንብብ። 62 ከዚያም እንዲህ በል፦ ‘ይሖዋ ሆይ፣ ይህች ስፍራ እንደምትጠፋና ሰውም ሆነ እንስሳ፣ አንድም የሚኖርባት እንደማይገኝ፣ እንዲሁም ለዘላለም ባድማ እንደምትሆን ተናግረሃል።’+ 63 ይህን መጽሐፍ አንብበህ ከጨረስክ በኋላም መጽሐፉን ከድንጋይ ጋር አስረህ ኤፍራጥስ ወንዝ ውስጥ ወርውረው። 64 ከዚያም እንዲህ በል፦ ‘ባቢሎን በእሷ ላይ ከማመጣው ጥፋት የተነሳ እንዲህ ትሰምጣለች፤ ዳግመኛም አትነሳም፤+ እነሱም ይዝላሉ።’”+

የኤርምያስ ቃል እዚህ ላይ ያበቃል።

52 ሴዴቅያስ+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 21 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ11 ዓመት ገዛ። እናቱ ሀሙጣል+ ትባል ነበር፤ እሷም የሊብና ሰው የሆነው የኤርምያስ ልጅ ነበረች። 2 ሴዴቅያስም ኢዮዓቄም እንዳደረገው ሁሉ በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ።+ 3 እነዚህ ነገሮች በኢየሩሳሌምና በይሁዳ የተፈጸሙት ከይሖዋ ቁጣ የተነሳ ነው፤ በመጨረሻም ከፊቱ አስወገዳቸው።+ ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዓመፀ።+ 4 ሴዴቅያስ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት፣ በአሥረኛው ወር፣ ከወሩም በአሥረኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* ሠራዊቱን ሁሉ አስከትሎ በኢየሩሳሌም ላይ ዘመተ። በዙሪያዋም ሰፈሩ፤ ደግሞም በዙሪያዋ የአፈር ቁልል ቆለሉ።+ 5 ከተማዋም እስከ ንጉሥ ሴዴቅያስ 11ኛ ዓመት ድረስ ተከበበች።

6 በአራተኛው ወር፣ ከወሩም በዘጠነኛው ቀን+ በከተማዋ ውስጥ ረሃቡ እጅግ ከፋ፤ በምድሪቱ የሚኖሩትም ሰዎች የሚላስ የሚቀመስ አጡ።+ 7 በመጨረሻም የከተማዋ ቅጥር ተነደለ፤ ከለዳውያን ከተማዋን ከበው ሳለም ወታደሮቹ ሁሉ በንጉሡ የአትክልት ቦታ አቅራቢያ ባለው መንገድ፣ በሁለቱ ቅጥሮች መካከል በሚገኘው በር በኩል በሌሊት ከከተማዋ ወጥተው ሸሹ፤ ወደ አረባ የሚወስደውንም አቅጣጫ ይዘው ሄዱ።+ 8 ይሁንና የከለዳውያን ሠራዊት ንጉሡን አሳደደ፤ ሴዴቅያስንም+ በኢያሪኮ በረሃማ ሜዳ ላይ ደረሱበት፤ ወታደሮቹም ሁሉ ጥለውት ተበታተኑ። 9 ከዚያም ንጉሡን ይዘው በሃማት ምድር በምትገኘው በሪብላ ወደነበረው የባቢሎን ንጉሥ አመጡት፤ እሱም ፈረደበት። 10 የባቢሎንም ንጉሥ የሴዴቅያስን ወንዶች ልጆች ዓይኑ እያየ አረዳቸው፤ በተጨማሪም የይሁዳን መኳንንት ሁሉ በዚያው በሪብላ አረዳቸው። 11 ከዚያም የባቢሎን ንጉሥ፣ የሴዴቅያስን ዓይን አሳወረ፤+ በመዳብ የእግር ብረት አስሮ ወደ ባቢሎን ወሰደው፤ እስከ ዕለተ ሞቱም ድረስ በእስር ቤት አቆየው።

12 በአምስተኛው ወር፣ ከወሩም በአሥረኛው ቀን ይኸውም ንጉሥ ናቡከደነጾር* በነገሠ በ19ኛው ዓመት፣ የዘቦች አለቃና የባቢሎን ንጉሥ አገልጋይ የሆነው ናቡዛራዳን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።+ 13 እሱም የይሖዋን ቤት፣ የንጉሡን ቤትና* በኢየሩሳሌም የሚገኙ ቤቶችን በሙሉ አቃጠለ፤+ ትላልቅ ቤቶችንም ሁሉ በእሳት አጋየ። 14 ከዘቦቹ አለቃ ጋር የነበረው የከለዳውያን ሠራዊት በኢየሩሳሌም ዙሪያ ያለውን ቅጥር በሙሉ አፈረሰ።+

15 የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን ችግረኛ ከሆኑት ሰዎች መካከል የተወሰኑትንና በከተማዋ የቀሩትን በሕይወት የተረፉ ሰዎች አጋዘ። በተጨማሪም ከድተው ለባቢሎን ንጉሥ እጃቸውን የሰጡትን ሰዎችና የቀሩትን የተካኑ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ወሰደ።+ 16 ሆኖም የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን፣ በምድሪቱ ከነበሩት ያጡ የነጡ ድሆች መካከል አንዳንዶቹ የወይን አትክልት ሠራተኞች ሆነው እንዲያገለግሉና የግዳጅ አገልግሎት እንዲሰጡ በዚያው ተዋቸው።+

17 ከለዳውያን የይሖዋን ቤት የመዳብ ዓምዶች+ እንዲሁም በይሖዋ ቤት ውስጥ የነበሩትን የዕቃ ማጓጓዣ ጋሪዎችና+ የመዳብ ባሕር+ ሰባብረው መዳቡን በሙሉ ወደ ባቢሎን አጋዙ።+ 18 በተጨማሪም አመድ ማጠራቀሚያዎቹን፣ አካፋዎቹን፣ የእሳት ማጥፊያዎቹን፣ ጎድጓዳ ሳህኖቹን፣+ ጽዋዎቹንና+ ለቤተ መቅደስ አገልግሎት የሚውሉትን የመዳብ ዕቃዎች ሁሉ ወሰዱ። 19 የዘቦቹ አለቃ ከንጹሕ ወርቅና ብር የተሠሩትን ዕቃዎች+ ይኸውም ሳህኖቹን፣+ መኮስተሪያዎቹን፣ ጎድጓዳ ሳህኖቹን፣ አመድ ማጠራቀሚያዎቹን፣ መቅረዞቹን፣+ ጽዋዎቹንና ሌሎቹን ጎድጓዳ ሳህኖች ወሰደ። 20 ንጉሥ ሰለሞን ለይሖዋ ቤት ያሠራቸው ሁለቱ ዓምዶች፣ ባሕሩ፣ ከባሕሩ ሥር ያሉት 12 የመዳብ በሬዎችና+ የዕቃ ማጓጓዣ ጋሪዎቹ የተሠሩበት መዳብ ከብዛቱ የተነሳ ሊመዘን የሚችል አልነበረም።

21 ዓምዶቹ እያንዳንዳቸው 18 ክንድ* ቁመት ነበራቸው፤ የዙሪያቸው መጠን በመለኪያ ገመድ 12 ክንድ፣+ ውፍረታቸውም አራት ጣት* ሲሆን ውስጣቸው ክፍት ነበር። 22 በዓምዱም አናት ላይ ያለው ጌጥ ከመዳብ የተሠራ ነበር፤ የአንዱ ጌጥ ርዝማኔ አምስት ክንድ+ ሲሆን በዙሪያው ያሉት ሮማኖችና መረቡ በሙሉ ከመዳብ የተሠሩ ነበሩ። ሁለተኛው ዓምድ፣ ሮማኖቹን ጨምሮ ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ነበር። 23 በጎኖቹ ላይ* 96 ሮማኖች የነበሩ ሲሆን በመረቡ ዙሪያ ያሉት ሮማኖች በጠቅላላ 100 ነበሩ።+

24 በተጨማሪም የዘቦቹ አለቃ የካህናት አለቃ የሆነውን ሰራያህን፣+ ሁለተኛውን ካህን ሶፎንያስንና+ ሦስቱን የበር ጠባቂዎች ወሰዳቸው።+ 25 ደግሞም ከከተማዋ የወታደሮቹ ኃላፊ የሆነን አንድ የቤተ መንግሥት ባለሥልጣን፣ በከተማዋ ውስጥ የነበሩትን ሰባቱን የንጉሡ የቅርብ ሰዎች፣ የምድሪቱን ሕዝብ የሚያሰልፈውን የሠራዊቱን አለቃ ጸሐፊ እንዲሁም ከተማዋ ውስጥ የተገኙትን በምድሪቱ የሚኖሩ 60 ተራ ሰዎች ወሰደ። 26 የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን እነዚህን ሰዎች ይዞ፣ በሪብላ ወዳለው ወደ ባቢሎን ንጉሥ አመጣቸው። 27 የባቢሎን ንጉሥ በሃማት ምድር ባለችው በሪብላ+ ሰዎቹን መትቶ ገደላቸው። በዚህ መንገድ ይሁዳ ከምድሩ በግዞት ተወሰደ።+

28 ናቡከደነጾር* በግዞት የወሰዳቸው ሰዎች እነዚህ ናቸው፦ በሰባተኛው ዓመት 3,023 አይሁዳውያንን ወሰደ።+

29 በናቡከደነጾር* 18ኛ ዓመት+ ከኢየሩሳሌም 832 ሰዎች* ተጋዙ።

30 ናቡከደነጾር* በነገሠ በ23ኛው ዓመት፣ የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን ከአይሁዳውያን መካከል 745 ሰዎችን* በግዞት ወሰደ።+

በአጠቃላይ 4,600 ሰዎች* በግዞት ተወሰዱ።

31 ከዚያም የባቢሎን ንጉሥ ኤዊልሜሮዳክ በነገሠበት ዓመት የይሁዳን ንጉሥ ዮአኪንን+ ፈታው፤* ከእስር ቤትም አወጣው፤+ ይህም የሆነው የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በግዞት በተወሰደ በ37ኛው ዓመት፣ በ12ኛው ወር፣ ከወሩም በ25ኛው ቀን ነበር። 32 በርኅራኄም አናገረው፤ ዙፋኑንም በባቢሎን ከእሱ ጋር ከነበሩት ከሌሎች ነገሥታት ዙፋን ይበልጥ ከፍ ከፍ አደረገለት። 33 በመሆኑም ዮአኪን የእስር ቤት ልብሱን አወለቀ፤ በሕይወት ዘመኑም ሁሉ በቋሚነት ከንጉሡ ማዕድ ይመገብ ነበር። 34 የባቢሎን ንጉሥ፣ ዮአኪን እስከሞተበት ጊዜ ድረስ፣ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሳያቋርጥ ቀለቡን በየዕለቱ ይሰጠው ነበር።

“ይሖዋ ከፍ ያደርጋል” የሚል ትርጉም ሊኖረው ይችላል።

ወይም “መርጬሃለሁ።”

ቃል በቃል “ከማህፀን ከመውጣትህም በፊት።”

ወይም “ለይቼሃለሁ።”

ወይም “ወጣት።”

ቃል በቃል “ንቁ የሆነው (ዛፍ)።”

ቃል በቃል “እየተራገበ ያለ።”

ወይም “አፉ ሰፊ የሆነ ድስት።”

ቃል በቃል “ዳሌዎችህን ታጠቅ።”

ወይም “ድል አይነሱህም።”

ወይም “ታማኝ ፍቅር ታሳዪ እንደነበር።”

ወይም “ደሴቶች።”

ወይም “ፈልፍለዋል።” ከዓለት ሊሆን ይችላል።

ወይም “የሜምፊስና።”

ከአባይ ወንዝ ተገንጥሎ የሚፈሰውን ውኃ ያመለክታል።

ኤፍራጥስን ያመለክታል።

ለማጠብ የሚያገለግል ንጥረ ነገር።

ወይም “ሳሙና።”

ወይም “ነፍሷ በምኞት ስትቃጠል።”

ቃል በቃል “በወሯ።”

ወይም “ከባዕዳን አማልክት።”

ወይም “ሙሽሪትስ የሠርጓን መቀነት።”

ወይም “በንጹሐን ድሆች ነፍሳት።”

ቃል በቃል “ዓረብ።”

ቃል በቃል “ዝሙት አዳሪ የሆነች ሚስት ያላት ዓይነት ግንባር አለሽ።”

ወይም “ነፍሷን ጻድቅ አድርጋ።”

ቃል በቃል “ፊቴን አልጥልም።”

ወይም “ከባዕድ አማልክት።”

ቃል በቃል “መንገዶችሽን ለእንግዶች ዘረጋሽ።”

“ባላችሁ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ቃል በቃል “አጋሯን።”

ወይም “አሳፋሪው አምላክ።”

ወይም “ለምልክት የሚተከል ምሰሶ።”

ወይም “ደረታችሁን ምቱ።”

ወይም “መኳንንቱ ወኔ ይከዳቸዋል።”

ወይም “ሰይፍ ነፍሳችን ላይ ደርሶ።”

በሰውኛ ዘይቤ የተገለጸ ቅኔያዊ አነጋገር፤ አዘኔታን ወይም ርኅራኄን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል።

እህልን ወደ ላይ በመበተንና ለነፋስ በመስጠት ከገለባ መለየት።

ቃል በቃል “ተመልካቾች።” መቼ ጥቃት መሰንዘር እንዳለባቸው ለመወሰን ከተማዋን የሚቃኙ ሰዎችን ያመለክታል።

ቃል በቃል “አንጀቴ።”

“የውጊያ ሁካታ ድምፅ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ነፍሴ ሰምታለችና።”

ወይም “ለምልክት የሚተከለውን ምሰሶ።”

ወይም “ጥበበኞች።”

ወይም “አልጸጸትም።”

ወይም “ነፍስሽን።”

ወይም “ነፍሴ ዝላለችና።”

ቃል በቃል “እነሱ ግን አልደከሙም።”

ወይም “ነፍሴ ልትበቀል።”

“እሱ የለም” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የአምላክን ቃል ያመለክታል።

ቃል በቃል “ልብ የሚጎድላችሁ ሞኞች።”

ወይም “ነፍሴ ልትበቀል።”

ቃል በቃል “ጦርነት ቀድሱ።”

ወይም “ነፍሴ ተጸይፋሽ ከአንቺ እንዳትርቅ።”

ቃል በቃል “ጆሯቸው ስላልተገረዘ።”

ቃል በቃል “ቀናት የጠገቡት።”

ወይም “ስንጥቅ።”

ወይም “እንደነገሩ።”

ወይም “ነፍሳችሁም እረፍት ታግኝ።”

ወይም “መመሪያዬንም፤ ትምህርቴንም።”

ኢሳ 43:24 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።

ቃል በቃል “ምጥ ይዞናል።”

ነቢዩ ኤርምያስን ያመለክታል።

ቃል በቃል “እነዚህ።” ይህ ቃል የቤተ መቅደሱን ሕንፃዎች በሙሉ ያመለክታል።

ወይም “አባት የሌላቸውን ልጆችና።”

ወይም “የሚጨስ መሥዋዕት።”

ቃል በቃል “በማለዳ እየተነሳሁ።”

ከሃዲ እስራኤላውያን የሚያመልኳት አምላክ የማዕረግ ስም ነው፤ የመራባት ሴት አምላክ ልትሆን ትችላለች።

ወይም “የሚያስከፉት፤ የሚያስቆጡት።”

ወይም “ምክር።”

ቃል በቃል “በየዕለቱ በማለዳ እየተነሳሁ።”

ቃል በቃል “አንገታቸውን አደነደኑ።”

ቃል በቃል “ከአፋቸው ተቆርጧል።”

ወይም “ለአምላክ የተወሰነውን።”

ወይም “የሐዘን እንጉርጉሮ አሰሚ።”

ወይም “ፈጽሞ ወደ አእምሮዬ መጥቶ የማያውቀውን።”

የቃላት መፍቻው ላይ “ገሃነም” የሚለውን ተመልከት።

የቃላት መፍቻው ላይ “ገሃነም” የሚለውን ተመልከት።

ባለ ረጃጅም እግር ትልቅ አሞራ።

ወይም “የተወሰነ ጊዜዋን።”

“ቁርዬ” ልትሆንም ትችላለች።

ወይም “የሚፈልሱበትን።”

ወይም “መመሪያ፤ ትምህርት።”

ወይም “የውሸት።”

ወይም “እንደነገሩ።”

ወይም “በጊልያድ ሕመም ማስታገሻ ቅባት የለም?”

ወይም “ሐኪም።”

ወይም “ነፍሴ ልትበቀል።”

ወይም “የሐዘን እንጉርጉሮ አሰማለሁ።”

ወይም “መመሪያዬን፤ ትምህርቴን።”

ወይም “የሐዘን እንጉርጉሮ የሚያሰሙትን።”

በዓይንና በጆሮ መካከል ያለውን የአካል ክፍል ያመለክታል።

ወይም “ዋጋ ቢስ።”

ወይም “በገጀራው።”

ወይም “ዋጋ ቢስ።”

ኤር 10:11 በመጀመሪያ የተጻፈው በአረማይክ ነበር።

ወይም “ተን።”

“ለዝናብ መውጫ ያዘጋጃል” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ቀልጦ የተሠራው ሐውልቱ።”

ወይም “እስትንፋስ።”

ወይም “ዋጋ ቢስና።”

ወይም “እወነጭፋቸዋለሁ።”

ወይም “ስንጥቅ።”

ለኤርምያስ የተነገረ ሳይሆን አይቀርም።

ወይም “ይሁን።”

ቃል በቃል “በማለዳ እየተነሳሁ።”

ወይም “የሚጨስ መሥዋዕት።”

ወይም “ለአሳፋሪው አምላክ።”

ኤርምያስን ያመለክታል።

በቤተ መቅደሱ የሚቀርቡትን መሥዋዕቶች ያመለክታል።

ወይም “ጥልቅ ስሜትንና።” ቃል በቃል “ኩላሊትንና።”

ወይም “ነፍስህን በሚሿት።”

ወይም “ጥልቅ ስሜታቸው።” ቃል በቃል “ኩላሊታቸው።”

ወይም “ነፍሴ እጅግ የምትወዳትን።”

ወይም “እንደ ዥጉርጉር።”

“ያለቅሳል” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ቃል በቃል “ሥጋ ሁሉ።”

ወይም “ነፍሴ በስውር ታለቅሳለች።”

ወይም “እመቤቲቱን።”

ወይም “ተከበዋል።”

ወይም “ኩሻዊ።”

ወይም “አሳፋሪ።”

ወይም “ታናናሾቻቸውን።”

ወይም “ወደ ቦዮቹ፤ ወደ ውኃ ማጠራቀሚያዎቹ።”

ቅርንጫፍ የሚመስሉ ቀንዶች ያሉት አጥቢ እንስሳ፤ ከአጋዘን ጋር ይመሳሰላል።

ወይም “በበሽታ።”

ወይም “ነፍስህ ተጸይፋታለች?”

ወይም “ነፍሴ ወደዚህ ሕዝብ አታዘነብልም።”

“አራት ዓይነት ፍርድ” ማለትም ሊሆን ይችላል። ቃል በቃል “አራት ወገኖች።”

“ወደ ኋላ ማፈግፈግሽን ቀጥለሻል” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “መጸጸት።”

ወይም “ነፍሷ ትንፋሽ አጥሯት።”

“ኀፍረት ተከናንባለች፤ ተዋርዳለችም” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ቃል በቃል “አትውሰደኝ።”

ወይም “በውግዘት መልእክት።”

ወይም “የእኔ ቃል አቀባይ።”

ወይም “አያሸንፉህም።”

ይህ የአረማውያን የለቅሶ ልማድ ሲሆን ከሃዲዋ እስራኤልም ይህን ልማድ ሳትከተል አትቀርም።

ቃል በቃል “በመንገዶቻቸው ሁሉ።”

ቃል በቃል “አስከሬኖች።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

“በቁጣዬ እንደ እሳት ነደሃልና” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ቃል በቃል “ሥጋን ክንዱ የሚያደርግና።”

ወይም “ብርቱ ሰው።”

ወይም “ብርቱ ሰው።”

ወይም “አታላይ።”

“ፈውስ የለውም” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ጥልቅ ስሜትንም።” ቃል በቃል “ኩላሊትንም።”

ወይም “ፍትሐዊ ባልሆነ መንገድ።”

ቃል በቃል “እኔን።” ይሖዋን የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።

ወይም “እጥፍ ድርብ ጥፋት አምጣባቸው።”

ወይም “ለነፍሳችሁ።”

ቃል በቃል “አንገታቸውን አደነደኑ።”

ወይም “ከደቡብ።”

ቃል በቃል “ሸክላ ሠሪው በዓይኑ ፊት ትክክል መስሎ በታየው መንገድ።”

ወይም “ላመጣው ባሰብኩት ጥፋት እጸጸታለሁ።”

ወይም “ባሰብኩት መልካም ነገር እጸጸታለሁ።”

ቃል በቃል “እየሠራሁ ነው።”

ወይም “ባልተሠሩ።”

ወይም “መመሪያው፤ ትምህርቱ።”

ቃል በቃል “በምላስ እንምታው።”

ወይም “ለነፍሴ ጉድጓድ ቆፍረዋልና።”

ወይም “ፈጽሞ ወደ አእምሮዬ መጥቶ የማያውቀውን።”

ወይም “ነፍሳቸውንም።”

ወይም “ነፍሳቸውን የሚሹ።”

ቃል በቃል “ቃሌን ላለመታዘዝ አንገታቸውን አደንድነዋል።”

“ዙሪያ ገባው ሽብር” የሚል ትርጉም አለው።

ወይም “ጥልቅ ስሜትንና።” ቃል በቃል “ኩላሊትንና።”

ወይም “የድሃውን ነፍስ።”

ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

ወይም “በከባድ በሽታ።”

ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

ወይም “ነፍሳቸውን በሚሹ።”

ወይም “ነፍሱም።”

ወይም “ሕይወቱን ያተርፋል።”

ወይም “በረባዳማ ሜዳ።”

ወይም “ቤተ መንግሥት።”

ወይም “ወላጅ አልባ የሆነውን ልጅ።”

ቃል በቃል “እቀድሳለሁ።”

ኢዮአካዝ ተብሎም ይጠራል።

ቃል በቃል “ምጥ።”

ዮአኪን እና ኢኮንያን ተብሎም ይጠራል።

ወይም “ነፍስህን በሚሿት።”

ቃል በቃል “በናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

ወይም “ነፍሳቸውን ወደሚያነሱባት ምድር።”

ወይም “መሬት።”

ቃል በቃል “በቀኖቹ።”

ወይም “ወራሽ።”

ወይም “ከሃዲ ሆነዋል።”

ቃል በቃል “የክፉ አድራጊዎችን እጅ ያበረታሉ።”

ወይም “በባዶ ተስፋ እየሞሏችሁ ነው።”

ወይም “ከባድ መልእክት።” የዕብራይስጡ ቃል “ከባድ መለኮታዊ ፍርድ” ወይም “ከባድ የሆነ ነገር” የሚል ሁለት ትርጉም አለው።

ወይም “ከባድ መልእክት።”

ወይም “ከባድ መልእክት።”

ወይም “ከባዱ መልእክት።”

ወይም “ከባድ መልእክት።”

ወይም “ከባድ መልእክት።”

ወይም “ከባድ መልእክት።”

ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

ዮአኪን እና ኮንያሁ ተብሎም ይጠራል።

“ምሽግ ከሚገነቡት ሰዎች” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “በሽታ።”

ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

ወይም “ለይሁዳ ሕዝብ ሁሉና ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች በሙሉ።”

ቃል በቃል “በማለዳ እየተነሳሁ ተናገርኩ።”

ቃል በቃል “በማለዳ እየተነሳ።”

ቃል በቃል “ናቡከደረጾርን።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

ወይም “እቀጣለሁ።”

በዓይንና በጆሮ መካከል ያለውን የአካል ክፍል ያመለክታል።

ባቤል (ባቢሎን) የምትጠራበት የሚስጥር ስም ሳይሆን አይቀርም።

ቃል በቃል “በሥጋ።”

ወይም “ለመስገድ።”

ወይም “ወደ ይሖዋ ቤት ለሚመጡት፣ በይሁዳ ከተሞች ለሚኖሩት።”

ወይም “ባሰብኩት ጥፋት እጸጸታለሁ።”

ወይም “መመሪያ፤ ትምህርት።”

ቃል በቃል “በማለዳ እየተነሳሁ።”

ወይም “ቤተ መንግሥት።”

ወይም “በተናገረው ጥፋት ይጸጸታል።”

ወይም “የቤተ መቅደሱም።”

ወይም “በዛፍ የተሸፈነ ተረተር።”

ወይም “በነበረው ጥፋት አልተጸጸተም?”

ወይም “በነፍሳችን።”

ወይም “በሴዴቅያስ።” የሲሪያክና የዓረብኛ ትርጉሞች እንዲሁም በእጅ የተጻፉ ሦስት ጥንታዊ የዕብራይስጥ ቅጂዎች ይህን ስም ይጠቀማሉ።

ወይም “በበሽታ።”

ቃል በቃል “እንዲያርፍ።”

ወይም “በይሁዳ ንጉሥ ቤተ መንግሥትና።”

በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚገኘውን ከመዳብ የተሠራ ትልቅ ገንዳ ያመለክታል።

ወይም “ቤተ መንግሥትና።”

ቃል በቃል “የቀናት ዓመታት።”

ወይም “በሽታ።”

ወይም “እመቤቲቱ።”

“ምሽግ የሚገነቡት ሰዎች” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “በሽታን።”

“የፈረጡ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ቃል በቃል “በማለዳ እየተነሳሁ።”

ቃል በቃል “በናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

ወይም “በአንገት ማሠሪያ ሰንሰለት።”

ወይም “ወገቡ።”

ቃል በቃል “ታላቅ።”

ወይም “ባዕዳን።”

ወይም “ባሪያዎቻቸው አያደርጓቸውም።”

ወይም “አርምሃለሁ።”

“እንዲከበሩ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ቃል በቃል “ልቡን መያዣ አድርጎ የሚሰጥ።”

ወይም “ለአንቺ ታማኝ ፍቅር ማሳየቴን ቀጠልኩ።”

ወይም “የሚፈነድቁትን ሰዎች ጭፈራ እየጨፈርሽ።”

ወይም “ደረቅ ወንዞች።”

ወይም “መልሶ ያመጣዋል።”

ወይም “ከይሖዋ በሚያገኟቸው መልካም ነገሮች።”

ወይም “ነፍሳቸው ውኃ እንደጠገበ የአትክልት ቦታ ትሆናለች።”

ወይም “የካህናቱን ነፍስ።”

ቃል በቃል “በስብ።”

ወይም “ስለ ልጆቿ።”

ወይም “የዛለችውን ነፍስ።”

ወይም “የደከመችውንም ነፍስ።”

ቃል በቃል “ደነዘ።”

“ባላቸው” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ደንቦች ያወጣው።”

ወይም “በስብ የራሰ አመድ።” መሥዋዕት ሆነው በሚቀርቡት እንስሳት ስብ የራሰውን አመድ ያመለክታል።

ወይም “ረባዳማ ሜዳ።”

ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

ወይም “ቤተ መንግሥት።”

የአባቱን ወንድም ያመለክታል።

አንድ ሰቅል 11.4 ግራም ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

ቃል በቃል “ጉያ።”

ወይም “ከዓላማዎችህ ጋር በተያያዘ ታላቅ።”

ወይም “ከበሽታው።”

ቃል በቃል “የሥጋ።”

ቃል በቃል “ለናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

ቃል በቃል “በማለዳ እየተነሳሁ።”

የቃላት መፍቻው ላይ “ገሃነም” የሚለውን ተመልከት።

ወይም “ፈጽሞ ወደ አእምሮዬ መጥቶ አያውቅም።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ወራሽ።”

ወይም “ደንብ።”

ቃል በቃል “ዘሮች።”

ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

ቃል በቃል “ዛሬ።”

ወይም “እንደ ነፍሳቸው።”

ወይም “በበሽታና።”

ወይም “ነፍሳቸውን ለሚሹ።”

ወይም “ነፍሳቸውን ለሚሹ።”

ቃል በቃል “ዮናዳብ።” የኢዮናዳብ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

ቃል በቃል “ዮናዳብ።” የኢዮናዳብ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

ቃል በቃል “በማለዳ እየተነሳሁ ብናገርም።”

ቃል በቃል “በማለዳ እየተነሳሁ።”

ቃል በቃል “ዮናዳብ።” የኢዮናዳብ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

ቃል በቃል “የመጽሐፍ ጥቅልል።”

ቃል በቃል “በመጽሐፍ ጥቅልሉ።”

ወይም “ከመጽሐፉ።”

ወይም “ጸሐፊ።”

ወይም “የመመገቢያ ክፍል።”

ወይም “ከመጽሐፉ።”

ወይም “ከመጽሐፉ።”

ወይም “ቤተ መንግሥት።”

ወይም “የቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱ።”

ወይም “ከመጽሐፉ።”

ወይም “በመጽሐፉ።”

ከኅዳር አጋማሽ እስከ ታኅሣሥ አጋማሽ ያለውን ጊዜ ያመለክታል። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ15ን ተመልከት።

ቃል በቃል “ዘሩንና።”

ወይም “መጽሐፍ።”

ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

ዮአኪን እና ኢኮንያን ተብሎም ይጠራል።

ወይም “ነፍሳችሁን አታታሉ።”

ቃል በቃል “በእግር ብረት ቤት አኖሩት።”

ቃል በቃል “በውኃ ማጠራቀሚያው ቤት።”

ወይም “በቤተ መንግሥቱ።”

ወይም “በበሽታ።”

ቃል በቃል “ወደ ከለዳውያን የሚወጣ።”

ወይም “ነፍሱ።”

ወይም “ሕይወቱን ያተርፋል።”

ቃል በቃል “እጆች።”

ወይም “ቤተ መንግሥት።”

ወይም “የቤተ መንግሥት ባለሥልጣን።”

ወይም “ቤተ መንግሥት።”

ወይም “ቤተ መንግሥት።”

ወይም “ይህችን ነፍስ በፈጠረልን።”

ወይም “ነፍስህን ለሚሿት።”

ቃል በቃል “ወደ ባቢሎን ንጉሥ መኳንንት ብትወጣ።”

ወይም “ነፍስህ በሕይወት ትኖራለች።”

ቃል በቃል “ወደ ባቢሎን ንጉሥ መኳንንት የማትወጣ ከሆነ።”

ወይም “ነፍስህም በሕይወት ትኖራለች።”

ቃል በቃል “ለመውጣት።”

ወይም “ቤተ መንግሥት።”

ቃል በቃል “የሰላምህ ሰዎች።”

ቃል በቃል “ናቡከደረጾርና።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

በዕብራይስጡ ጽሑፍ ላይ ያሉት ቃላት በሚከተለውም መንገድ ሊቀመጡ ይችላሉ፦ “ኔርጋልሻሬጸር፣ ሳምጋርነቦ፣ ሳርሰኪም፣ ራብሳሪስ።”

ወይም “የአስማተኞች አለቃ (ኮከብ ቆጣሪ)።”

ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

ወይም “ቤተ መንግሥትና።”

“የግዳጅ አገልግሎት” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

ወይም “የቤተ መንግሥት ዋና ባለሥልጣን።”

ወይም “የአስማተኞች አለቃ (ኮከብ ቆጣሪ)።”

ወይም “ነፍስህ።”

ወይም “ሕይወትህን ታተርፋለህ።”

ቃል በቃል “ለመቆም።”

የበጋ ፍሬ በዋነኝነት የሚያመለክተው “በለስን” ሲሆን “ቴምርንም” ሊጨምር ይችላል።

ወይም “ነፍስህን ለማጥፋት።”

ወይም “ነፍስህን ለምን ያጥፋት?”

ቃል በቃል “የመንግሥት ዘር።”

“በታላቁ ኩሬ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

2ነገ 25:23 ላይ ያአዛንያህ፣ ኤር 43:2 ላይ ደግሞ አዛርያስ ተብሎ ተጠርቷል።

ወይም “አዝናለሁና።”

ወይም “ለተወሰነ ጊዜ በዚያ ለመኖር።”

ወይም “በበሽታ።”

ወይም “ነፍሳችሁን።”

ወይም “ነፍሳት ሁሉ።”

ቃል በቃል “ናቡከደረጾርን።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

ወይም “ቤተ መቅደሶችም።”

ወይም “ጉዳት ሳይደርስበት።”

ወይም “የፀሐይን ቤት (ቤተ መቅደስ)።” ሂሊዮፖሊስ ማለት ነው።

ወይም “ሐውልቶች።”

ወይም “ቤተ መቅደሶችም።”

ወይም “በሜምፊስ።”

ቃል በቃል “በማለዳ እየተነሳሁ።”

ወይም “በነፍሳችሁ።”

ወይም “አልተሸማቀቁም።”

ወይም “በበሽታ።”

ወይም “ነፍሳቸውን ቢያነሱም እንኳ።”

ከሃዲ እስራኤላውያን የሚያመልኳት አምላክ የማዕረግ ስም ነው፤ የመራባት ሴት አምላክ ልትሆን ትችላለች።

ከሃዲ እስራኤላውያን የሚያመልኳት አምላክ የማዕረግ ስም ነው፤ የመራባት ሴት አምላክ ልትሆን ትችላለች።

ከሃዲ እስራኤላውያን የሚያመልኳት አምላክ የማዕረግ ስም ነው፤ የመራባት ሴት አምላክ ልትሆን ትችላለች።

ከሃዲ እስራኤላውያን የሚያመልኳት አምላክ የማዕረግ ስም ነው፤ የመራባት ሴት አምላክ ልትሆን ትችላለች።

ወይም “ነፍሱን ይፈልጋት።”

ቃል በቃል “ለናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

ወይም “ነፍሱን ለሚፈልጓት።”

ወይም “ታላላቅ ነገሮች አገኛለሁ ብለህ ትጠብቃለህ።”

ወይም “መፈለግህን ተው።”

ወይም “በሰዎች።”

ወይም “ነፍስህን።”

ወይም “ሕይወትህ እንዲተርፍ አደርጋለሁ።”

ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

አብዛኛውን ጊዜ ቀስተኞች የሚይዙት ትንሽ ጋሻ።

ወይም “የኩሽ።”

ቃል በቃል “የመርገጥና።”

ወይም “እርድ።”

ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

ወይም “በሜምፊስ።”

ቃል በቃል “የተወሰነውን ጊዜ።”

ግብፅን ድል የሚያደርገውን ያመለክታል።

ወይም “ሜምፊስ።”

“ጠፍ መሬት ትሆናለች” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “እንጨት እንደሚሰበስቡ።”

ቴብስን ያመለክታል።

ወይም “ነፍሳቸውን ለሚሹ።”

ቃል በቃል “ለናቡከደረጾርና።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

ወይም “አርምሃለሁ።”

ተሽከርካሪ እግር።

ቀርጤስን ያመለክታል።

በሐዘንና በኀፍረት ራሳቸውን እንደሚላጩ ያመለክታል።

ወይም “ረባዳማ በሆነው ሜዳቸው።”

ወይም “ነፍሳችሁን አትርፉ!”

ወይም “ረባዳማው ሜዳ።”

ወይም “አምባውም።”

“በደረቅ መሬትም” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ወደ አምባው።”

ቃል በቃል “ቀንድ።”

የበጋ ፍሬ በዋነኝነት የሚያመለክተው “በለስን” ሲሆን “ቴምርንም” ሊጨምር ይችላል።

በቀብር ጊዜ ሐዘናቸውን ለመግለጽ የሚጫወቱትን ዋሽንት ያመለክታል።

ወይም “ይጮኻል።”

በቀብር ጊዜ ሐዘናቸውን ለመግለጽ የሚጫወቱትን ዋሽንት ያመለክታል።

ወይም “ይጮኻል።”

“የውጊያ ሁካታ ድምፅ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “በዙሪያዋም።”

ወይም “የበጎች ጉረኖ።”

ወይም “በረባዳማ ሜዳዎችሽ።”

ወይም “የመከረውን ምክርና።”

ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

በዓይንና በጆሮ መካከል ያለውን የአካል ክፍል ያመለክታል።

ወይም “በሁሉም አቅጣጫ።”

ቃል በቃል “መነሻ።”

ወይም “ነፍሳቸውን በሚሹ።”

ወይም “ለምልክት የሚተከል ምሰሶ።”

እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል “ፋንድያ” ከሚለው ቃል ጋር ዝምድና ሊኖረው የሚችል ሲሆን ንቀትን ለማመልከት ተሠርቶበታል።

ወይም “አውራ በጎችና አውራ ፍየሎች።”

ቃል በቃል “የምትረግጡ።”

ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

ወይም “ነፍሱ እስክትጠግብ ድረስ ትመገባለች።”

ወይም “ለጥፋት ለያቸው።”

ቃል በቃል “የሚረግጡትንም።”

ቃል በቃል “ጸጥ ይላሉ።”

ወይም “በሐሰተኛ ነቢያት።”

ወይም “የመከረውን ምክርና።”

የከለዳውያን ምድር የምትጠራበት የሚስጥር ስም ሳይሆን አይቀርም።

እህልን ወደ ላይ በመበተንና ለነፋስ በመስጠት ከገለባ መለየት።

ቃል በቃል “አይርገጥ።”

የከለዳውያንን ምድር ያመለክታል።

ወይም “ነፍሳችሁን።”

“የፍላጻ ኮሮጆዎቹን ሙሉ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ለምልክት የሚተከል ምሰሶ።”

ወይም “በነፍሱ።”

ወይም “ተን።”

“ለዝናብ መውጫ ያዘጋጃል” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ቀልጦ የተሠራው ሐውልቱ።”

ወይም “እስትንፋስ።”

ወይም “ዋጋ ቢስና።”

ወይም “ለምልክት የሚተከል ምሰሶ።”

ቃል በቃል “ቀድሱ።”

ቃል በቃል “ቀድሷቸው።”

ወንዝ ማቋረጥ የሚቻልበት ጥልቀት የሌለው የወንዝ ክፍል።

ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

ባቤል (ባቢሎን) የምትጠራበት የሚስጥር ስም ሳይሆን አይቀርም።

ወይም “ነፍሳችሁን።”

ወይም “እንግዶች።”

ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

ወይም “ቤተ መንግሥትና።”

አንድ ክንድ 44.5 ሴንቲ ሜትር ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

የአንዱ ጣት ውፍረት 1.85 ሴንቲ ሜትር ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

ወይም “በግልጽ የሚታዩ።”

ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

ወይም “ነፍሳት።”

ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

ወይም “ነፍሳት።”

ወይም “ነፍሳት።”

ቃል በቃል “የዮአኪንን ራስ ቀና አደረገ።”

    የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ