የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • nwt መዝሙር 1:1-150:6
  • መዝሙር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መዝሙር
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
መዝሙር

መዝሙር

አንደኛ መጽሐፍ

(መዝሙር 1-41)

1 በክፉዎች ምክር የማይሄድ፣

በኃጢአተኞች መንገድ+ የማይቆም፣

በፌዘኞችም+ ወንበር የማይቀመጥ ሰው ደስተኛ ነው።

 2 ይልቁንም በይሖዋ ሕግ ደስ ይለዋል፤+

ሕጉንም በቀንና በሌሊት በለሆሳስ ያነበዋል።*+

 3 በጅረቶች ዳር እንደተተከለ፣

ፍሬውን በወቅቱ እንደሚሰጥ፣

ቅጠሉም እንደማይጠወልግ ዛፍ ይሆናል።

የሚሠራውም ሁሉ ይሳካለታል።+

 4 ክፉዎች እንዲህ አይደሉም፤

ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ገለባ ናቸው።

 5 ከዚህም የተነሳ ክፉዎች በፍርድ ፊት ለዘለቄታው አይቆሙም፤+

ኃጢአተኞችም በጻድቃን ጉባኤ ጸንተው አይቆሙም።+

 6 ይሖዋ የጻድቃንን መንገድ ያውቃልና፤+

የክፉዎች መንገድ ግን ይጠፋል።+

2 ብሔራት የታወኩት ለምንድን ነው?

ሕዝቦችስ ከንቱ ነገር የሚያጉተመትሙት* ለምንድን ነው?+

 2 የምድር ነገሥታት ተሰለፉ፤

ከፍተኛ ባለሥልጣናትም በአንድነት ተሰብስበው*+

በይሖዋና እሱ በቀባው ላይ*+ ተነሱ።

 3 “ሰንሰለታቸውን እንበጥስ፤

ገመዳቸውንም እናስወግድ!” ይላሉ።

 4 በሰማያት በዙፋን ላይ የተቀመጠው ይስቃል፤

ይሖዋ ይሳለቅባቸዋል።

 5 በዚያን ጊዜ በቁጣ ይናገራቸዋል፤

በሚነድ ቁጣውም ያሸብራቸዋል፤

 6 እንዲህም ይላቸዋል፦ “እኔ ራሴ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን+ ላይ

ንጉሤን ሾምኩ።”+

 7 የይሖዋን ድንጋጌ ልናገር፤

እንዲህ ብሎኛል፦ “አንተ ልጄ ነህ፤+

እኔ ዛሬ ወለድኩህ።+

 8 ጠይቀኝ፤ ብሔራትን ርስትህ፣

የምድርንም ዳርቻዎች ግዛትህ አድርጌ እሰጥሃለሁ።+

 9 በብረት በትረ መንግሥት ትሰብራቸዋለህ፤+

እንደ ሸክላ ዕቃም ታደቃቸዋለህ።”+

10 እንግዲህ እናንተ ነገሥታት አስተውሉ፤

እናንተ የምድር ፈራጆች እርማት ተቀበሉ።*

11 ይሖዋን በፍርሃት አገልግሉ፤

ለእሱ በመንቀጥቀጥም ሐሴት አድርጉ።

12 ልጁን አክብሩ፤*+ አለዚያ አምላክ* ይቆጣል፤

ከመንገዱም ትጠፋላችሁ፤+

ቁጣው ፈጥኖ ይነድዳልና።

እሱን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ ደስተኞች ናቸው።

የዳዊት ማህሌት፤* ከልጁ ከአቢሴሎም በሸሸ ጊዜ።+

3 ይሖዋ ሆይ፣ ጠላቶቼ እንዲህ የበዙት ለምንድን ነው?+

ብዙ ሰዎች በእኔ ላይ የተነሱትስ ለምንድን ነው?+

 2 ብዙዎች “አምላክ አያድነውም” እያሉ

ስለ እኔ* ይናገራሉ።+ (ሴላ)*

 3 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን በዙሪያዬ ያለህ ጋሻ ነህ፤+

አንተ ክብሬና+ ራሴን ቀና የምታደርግ ነህ።+

 4 ድምፄን ከፍ አድርጌ ይሖዋን እጣራለሁ፤

እሱም ከተቀደሰ ተራራው ይመልስልኛል።+ (ሴላ)

 5 እተኛለሁ፣ አንቀላፋለሁም፤

ይሖዋም ዘወትር ስለሚደግፈኝ

በሰላም እነቃለሁ።+

 6 በየአቅጣጫው የተሰለፉብኝን

በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አልፈራም።+

 7 ይሖዋ ሆይ፣ ተነስ! አምላኬ ሆይ፣ አድነኝ!+

የጠላቶቼን ሁሉ መንጋጋ ትመታለህና፤

የክፉዎችን ጥርስ ትሰባብራለህ።+

 8 ማዳን የይሖዋ ነው።+

በረከትህ በሕዝብህ ላይ ነው። (ሴላ)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በባለ አውታር መሣሪያዎች የሚታጀብ። የዳዊት ማህሌት።

4 ጻድቅ አምላኬ ሆይ፣+ ስጣራ መልስልኝ።

በምጨነቅበት ጊዜ ማምለጫ መንገድ* አዘጋጅልኝ።

ቸርነት አሳየኝ፤ ጸሎቴንም ስማ።

 2 እናንተ የሰው ልጆች፣ ክብሬን ወደ ውርደት የምትለውጡት እስከ መቼ ነው?

ከንቱ ነገሮችን የምትወዱት እስከ መቼ ነው? ሐሰትንስ የምትሹት እስከ መቼ ነው? (ሴላ)

 3 ይሖዋ ለእሱ ታማኝ የሆነውን ሰው ልዩ በሆነ መንገድ እንደሚይዘው እወቁ፤*

ይሖዋ በጠራሁት ጊዜ ይሰማኛል።

 4 ተቆጡ፤ ሆኖም ኃጢአት አትሥሩ።+

የምትናገሩትን በመኝታችሁ ላይ ሳላችሁ በልባችሁ ተናገሩ፤ ጸጥም በሉ። (ሴላ)

 5 የጽድቅ መሥዋዕቶች አቅርቡ፤

በይሖዋም ታመኑ።+

 6 “መልካም ነገር ማን ያሳየናል?” የሚሉ ብዙዎች አሉ።

ይሖዋ ሆይ፣ የፊትህን ብርሃን በላያችን አብራ።+

 7 የተትረፈረፈ እህል ከሰበሰቡና አዲስ የወይን ጠጅ በብዛት ካመረቱ ሰዎች ይበልጥ

ልቤ በሐሴት እንዲሞላ አደረግክ።

 8 በሰላም እተኛለሁ፤ አንቀላፋለሁም፤+

ይሖዋ ሆይ፣ ተረጋግቼ እንድኖር የምታደርገኝ አንተ ብቻ ነህና።+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በኔሂሎት።* የዳዊት ማህሌት።

5 ይሖዋ ሆይ፣ ቃሌን አዳምጥ፤+

መቃተቴን ልብ በል።

 2 ንጉሤና አምላኬ ሆይ፣ ወደ አንተ እጸልያለሁና፣

ለእርዳታ የማሰማውን ጩኸት በትኩረት አዳምጥ።

 3 ይሖዋ ሆይ፣ በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ፤+

ያሳሰበኝን ነገር በማለዳ ለአንተ እናገራለሁ፤+ በተስፋም እጠባበቃለሁ።

 4 አንተ በክፋት የምትደሰት አምላክ አይደለህምና፤+

ክፉ ሰው ከአንተ ጋር አይቀመጥም።+

 5 እብሪተኛ ሰው በፊትህ አይቆምም።

መጥፎ ምግባር ያላቸውን ሁሉ ትጠላለህ፤+

 6 ውሸት የሚናገሩትን ታጠፋለህ።+

ይሖዋ ዓመፀኞችንና አታላዮችን* ይጸየፋል።+

 7 እኔ ግን ታላቅ ከሆነው ታማኝ ፍቅርህ የተነሳ+ ወደ ቤትህ እገባለሁ፤+

አንተን በመፍራት* ቅዱስ ወደሆነው ቤተ መቅደስህ እሰግዳለሁ።+

 8 ይሖዋ ሆይ፣ ጠላቶቼ በዙሪያዬ ስላሉ በጽድቅህ ምራኝ፤

ከመንገድህ ላይ እንቅፋቶችን አስወግድልኝ።+

 9 የሚሉት ነገር ሁሉ ሊታመን አይችልም፤

ውስጣቸው በተንኮል የተሞላ ነው።

ጉሮሯቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤

በምላሳቸው ይሸነግላሉ።*+

10 አምላክ ግን ይፈርድባቸዋል፤

የገዛ ራሳቸው ዕቅድ ለጥፋት ይዳርጋቸዋል።+

ከበደላቸው ብዛት የተነሳ ይባረሩ፤

በአንተ ላይ ዓምፀዋልና።

11 አንተን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ ግን ሐሴት ያደርጋሉ፤+

ምንጊዜም በደስታ እልል ይላሉ።

ሊጎዷቸው ከሚፈልጉ ሰዎች ትጠብቃቸዋለህ፤

ስምህን የሚወዱም በአንተ ሐሴት ያደርጋሉ።

12 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ጻድቅ የሆነውን ሁሉ ትባርካለህና፤

ሞገስህ እንደ ትልቅ ጋሻ ይሆንላቸዋል።+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በሸሚኒት ቅኝት፣* በባለ አውታር መሣሪያዎች የሚታጀብ። የዳዊት ማህሌት።

6 ይሖዋ ሆይ፣ በቁጣህ አትውቀሰኝ፤

በታላቅ ቁጣህም አታርመኝ።+

 2 ይሖዋ ሆይ፣ ዝያለሁና ሞገስ አሳየኝ።*

ይሖዋ ሆይ፣ አጥንቶቼ ተንቀጥቅጠዋልና ፈውሰኝ።+

 3 አዎ፣ እጅግ ተረብሻለሁ፤*+

ይሖዋ ሆይ፣ ይህ እስከ መቼ ድረስ ነው? ብዬ እጠይቅሃለሁ።+

 4 ይሖዋ ሆይ፣ ተመለስ፤ ደግሞም ታደገኝ፤*+

ለታማኝ ፍቅርህ ስትል አድነኝ።+

 5 ሙታን አንተን አያነሱም፤*

በመቃብር* ማን ያወድስሃል?+

 6 ከመቃተቴ የተነሳ ዝያለሁ፤+

ሌሊቱን ሙሉ መኝታዬን በእንባ አርሳለሁ፤*

በለቅሶ አልጋዬን አጥለቀልቃለሁ።+

 7 በሐዘኔ ምክንያት ዓይኔ ደክሟል፤+

ከሚያጠቁኝ ሰዎች ሁሉ የተነሳ ዓይኔ ፈዟል።*

 8 እናንተ መጥፎ ምግባር ያላችሁ ሁሉ ከእኔ ራቁ፤

ይሖዋ የለቅሶዬን ድምፅ ይሰማልና።+

 9 ይሖዋ ሞገስ እንዲያሳየኝ የማቀርበውን ልመና ይሰማል፤+

ይሖዋ ጸሎቴን ይቀበላል።

10 ጠላቶቼ በሙሉ ያፍራሉ፤ ደግሞም እጅግ ይደነግጣሉ፤

በድንገት ውርደት ተከናንበው ወደ ኋላ ያፈገፍጋሉ።+

ቢንያማዊው ኩሽ የተናገረውን ቃል በተመለከተ ዳዊት ለይሖዋ ያንጎራጎረው ሙሾ።*

7 አምላኬ ይሖዋ ሆይ፣ አንተን መጠጊያ አድርጌአለሁ።+

ከሚያሳድዱኝ ሁሉ አድነኝ፤ ታደገኝም።+

 2 አለዚያ እንደ አንበሳ ይዘነጣጥሉኛል፤*+

የሚታደገኝ በሌለበት ነጥቀው ይወስዱኛል።

 3 አምላኬ ይሖዋ ሆይ፣ የሠራሁት አንዳች ጥፋት ካለ፣

አግባብ ያልሆነ ድርጊት ፈጽሜ ከሆነ፣

 4 መልካም ያደረገልኝን ሰው በድዬ ከሆነ፣+

ወይም ያላንዳች ምክንያት ጠላቴን ዘርፌ ከሆነ፣*

 5 ጠላት አሳዶ ይያዘኝ፤*

ሕይወቴን መሬት ላይ ይጨፍልቃት፤

ክብሬንም ከአፈር ይደባልቀው። (ሴላ)

 6 ይሖዋ ሆይ፣ በቁጣህ ተነስ፤

በእኔ ላይ በቁጣ በሚገነፍሉት ጠላቶቼ ላይ ተነስ፤+

ለእኔ ስትል ንቃ፤ ፍትሕ እንዲሰፍንም እዘዝ።+

 7 ብሔራት ይክበቡህ፤

አንተም ከላይ ሆነህ በእነሱ ላይ እርምጃ ትወስዳለህ።

 8 ይሖዋ በሕዝቦች ላይ ፍርድ ያስተላልፋል።+

ይሖዋ ሆይ፣ እንደ ጽድቄ፣

እንደ ንጹሕ አቋሜም* ፍረድልኝ።+

 9 እባክህ፣ የክፉ ሰዎች ክፋት እንዲያከትም አድርግ።

ጻድቁን ሰው ግን አጽና፤+

ልብንና+ ጥልቅ ስሜትን የምትመረምር*+ ጻድቅ አምላክ ነህና።+

10 ቀና ልብ ያላቸውን ሰዎች የሚያድነው+ አምላክ ጋሻዬ ነው።+

11 አምላክ ጻድቅ ፈራጅ ነው፤+

በየቀኑም ፍርዱን ያውጃል።*

12 ማንም ሰው ንስሐ የማይገባ ከሆነ፣+ አምላክ ሰይፉን ይስላል፤+

ደጋኑን ወጥሮ ያነጣጥራል።+

13 ገዳይ የሆኑ መሣሪያዎቹን ያሰናዳል፤

የሚንበለበሉ ፍላጻዎቹን ያዘጋጃል።+

14 ክፋትን ያረገዘውን ሰው ተመልከት፤

ችግርን ይፀንሳል፤ ሐሰትንም ይወልዳል።+

15 ጉድጓድ ይምሳል፤ ጥልቅ አድርጎም ይቆፍረዋል፤

ሆኖም በቆፈረው ጉድጓድ ውስጥ ራሱ ይወድቃል።+

16 የሚያመጣው ችግር በራሱ ላይ ይመለሳል፤+

የዓመፅ ድርጊቱ በገዛ አናቱ ላይ ይወርዳል።

17 ይሖዋን ለፍትሑ አወድሰዋለሁ፤+

ለልዑሉ አምላክ+ ለይሖዋ ስም የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በጊቲት።* የዳዊት ማህሌት።

8 ጌታችን ይሖዋ ሆይ፣ ስምህ በመላው ምድር ላይ ምንኛ የከበረ ነው፤

ግርማህ ከሰማያትም በላይ ከፍ ከፍ እንዲል አድርገሃል!*+

 2 ከባላጋራዎችህ የተነሳ፣

ከልጆችና ከሕፃናት አፍ በሚወጡ ቃላት+ ብርታትህን አሳየህ፤

ይህም ጠላትንና ተበቃይን ዝም ለማሰኘት ነው።

 3 የጣቶችህን ሥራ ሰማያትን፣

አንተ የሠራሃቸውን ጨረቃንና ከዋክብትን ስመለከት፣+

 4 ታስበው ዘንድ ሟች ሰው ምንድን ነው?

ትንከባከበውስ ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?+

 5 ከመላእክት* በጥቂቱ አሳነስከው፤

የክብርና የግርማ ዘውድም ደፋህለት።

 6 በእጆችህ ሥራዎች ላይ ሥልጣን ሰጠኸው፤+

ሁሉንም ነገር ከእግሩ በታች አደረግክለት፦

 7 መንጎቹንና ከብቶቹን ሁሉ፣

እንዲሁም የዱር አራዊትን፣+

 8 የሰማይ ወፎችንና የባሕር ዓሣዎችን፣

በባሕር ውስጥ የሚርመሰመሱትን ሁሉ ከእግሩ በታች አደረግክለት።

 9 ጌታችን ይሖዋ ሆይ፣ ስምህ በመላው ምድር ላይ ምንኛ የከበረ ነው!

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በሙትላቤን።* የዳዊት ማህሌት።

א [አሌፍ]

9 ይሖዋ ሆይ፣ በሙሉ ልቤ አወድስሃለሁ፤

ስለ ድንቅ ሥራዎችህ ሁሉ እናገራለሁ።+

 2 በአንተ ደስ ይለኛል፤ ሐሴትም አደርጋለሁ፤

ልዑል አምላክ ሆይ፣ ለስምህ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።+

ב [ቤት]

 3 ጠላቶቼ ወደ ኋላ ሲያፈገፍጉ+

ተሰናክለው ከፊትህ ይጠፋሉ።

 4 ለማቀርበው ትክክለኛ ክስ ትሟገትልኛለህና፤

በዙፋንህ ላይ ተቀምጠህ በጽድቅ ትፈርዳለህ።+

ג [ጊሜል]

 5 ብሔራትን ገሠጽክ፤+ ክፉውንም አጠፋህ፤

ስማቸውን ለዘላለም ደመሰስክ።

 6 ጠላቶች ለዘላለም ጠፍተዋል፤

ከተሞቻቸውን አፈራርሰሃል፤

መታሰቢያቸውም ሁሉ ይደመሰሳል።+

ה [ሄ]

 7 ይሖዋ ግን በዙፋኑ ላይ ለዘላለም ተቀምጧል፤+

ዙፋኑንም ለፍትሕ ሲል አጽንቷል።+

 8 ዓለምን* በጽድቅ ይዳኛል፤+

ለብሔራት ትክክለኛ የፍርድ ውሳኔዎች ያስተላልፋል።+

ו [ዋው]

 9 ይሖዋ ለተጨቆኑ አስተማማኝ መጠጊያ ይሆናል፤+

በመከራ ጊዜ አስተማማኝ መጠጊያ ነው።+

10 ስምህን የሚያውቁ በአንተ ይታመናሉ፤+

ይሖዋ ሆይ፣ አንተን የሚሹትን ፈጽሞ አትተዋቸውም።+

ז [ዛየን]

11 በጽዮን ለሚኖረው ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤

ሥራውንም በሕዝቦች መካከል አስታውቁ።+

12 ደማቸውን የሚበቀለው እሱ ያስታውሳቸዋልና፤+

የተጎሳቆሉ ሰዎች የሚያሰሙትን ጩኸት አይረሳም።+

ח [ኼት]

13 ይሖዋ ሆይ፣ ቸርነት አሳየኝ፤

ከሞት ደጆች የምታነሳኝ አምላክ ሆይ፣+ የሚጠሉኝ ሰዎች የሚያደርሱብኝን እንግልት ተመልከት፤

14 ያን ጊዜ የሚያስመሰግኑ ተግባሮችህን በጽዮን ሴት ልጅ ደጆች አውጃለሁ፤+

በማዳን ሥራህም ሐሴት አደርጋለሁ።+

ט [ቴት]

15 ብሔራት፣ ራሳቸው በቆፈሩት ጉድጓድ ውስጥ ገቡ፤

የገዛ እግራቸው በስውር ባስቀመጡት መረብ ተያዘ።+

16 ይሖዋ በሚወስደው የፍርድ እርምጃ ይታወቃል።+

ክፉ ሰው በገዛ እጁ በሠራው ነገር ተጠመደ።+

ሂጋዮን።* (ሴላ)

י [ዮድ]

17 ክፉ ሰው፣ አምላክን የሚረሱ ብሔራትም ሁሉ

ወደ መቃብር* ይሄዳሉ።

18 ድሃ ግን ለዘላለም ተረስቶ አይቀርም፤+

የየዋሆችም ተስፋ ፈጽሞ ከንቱ ሆኖ አይቀርም።+

כ [ካፍ]

19 ይሖዋ ሆይ፣ ተነስ! ሟች የሆነ ሰው እንዲያይል አትፍቀድ።

ብሔራት በፊትህ ይፈረድባቸው።+

20 ይሖዋ ሆይ፣ ፍርሃት ልቀቅባቸው፤+

ሕዝቦች ሟች መሆናቸውን ይወቁ። (ሴላ)

ל [ላሜድ]

10 ይሖዋ ሆይ፣ ርቀህ የምትቆመው ለምንድን ነው?

በመከራ ጊዜ ራስህን የምትሰውረው ለምንድን ነው?+

 2 ክፉ ሰው በእብሪት ተነሳስቶ ምስኪኑን ያሳድዳል፤+

ይሁንና በወጠነው ሴራ ይያዛል።+

 3 ክፉው ሰው በራስ ወዳድነት ምኞቱ ይኩራራልና፤*+

ስግብግብ የሆነውንም ሰው ይባርካል፤*

נ [ኑን]

ይሖዋንም ያቃልላል።

 4 ክፉው ሰው ከትዕቢቱ የተነሳ ምንም ምርምር አያደርግም፤

“አምላክ የለም” ብሎ ያስባል።+

 5 መንገዱ ሁልጊዜ የተሳካ ነው፤+

ሆኖም ፍርድህ እሱ ሊገነዘበው ከሚችለው በላይ ነው፤+

በጠላቶቹ ሁሉ ላይ ያፌዛል።*

 6 በልቡ እንዲህ ይላል፦ “ፈጽሞ አልናወጥም፤*

ከትውልድ እስከ ትውልድ

ምንም መከራ አይደርስብኝም።”+

פ [ፔ]

 7 አፉ በእርግማን፣ በውሸትና በዛቻ የተሞላ ነው፤+

ከምላሱ ሥር ችግርና ጉዳት የሚያስከትል ነገር አለ።+

 8 በመንደሮቹ አጠገብ አድብቶ ይጠብቃል፤

ከተደበቀበት ቦታ ወጥቶ ንጹሑን ሰው ይገድላል።+

ע [አይን]

ዓይኖቹ ያልታደለውን ሰለባ ይጠባበቃሉ።+

 9 በጎሬው ውስጥ እንዳለ* አንበሳ በተደበቀበት ቦታ አድፍጦ ይጠብቃል።+

ምስኪኑን ሰው ለመያዝ ይጠባበቃል።

ምስኪኑን ሰው መረቡ ውስጥ አስገብቶ ይይዘዋል።+

10 ሰለባው ይደቅቃል፤ ደግሞም ይወድቃል፤

ያልታደሉ ሰዎች መዳፉ ውስጥ ይወድቃሉ።

11 በልቡ እንዲህ ይላል፦ “አምላክ ረስቷል።+

ፊቱን አዙሯል።

ፈጽሞ ልብ አይልም።”+

ק [ኮፍ]

12 ይሖዋ ሆይ፣ ተነስ።+ አምላክ ሆይ፣ እጅህን አንሳ።+

ምስኪኖችን አትርሳ።+

13 ክፉው ሰው አምላክን ያቃለለው ለምንድን ነው?

በልቡ “ተጠያቂ አታደርገኝም” ይላል።

ר [ረሽ]

14 አንተ ግን ችግርንና መከራን ትመለከታለህ።

ደግሞም አይተህ እርምጃ ትወስዳለህ።+

ያልታደለው ሰለባ ወደ አንተ ይጮኻል፤+

አንተ አባት ለሌለው ልጅ* ረዳቱ ነህ።+

ש [ሺን]

15 ክፉና መጥፎ የሆነውን ሰው ክንድ ስበር፤+

ከዚያ በኋላ ክፋቱን በምትፈልግበት ጊዜ

ጨርሶ አታገኘውም።

16 ይሖዋ ለዘላለም ንጉሥ ነው።+

ብሔራት ከምድር ጠፍተዋል።+

ת [ታው]

17 ይሖዋ ሆይ፣ የዋሆች የሚያቀርቡትን ልመና ግን ትሰማለህ።+

ልባቸውን ታጸናለህ፤+ ደግሞም ትኩረት ትሰጣቸዋለህ።+

18 በምድር ላይ ያለ ሟች የሆነ ሰው ከእንግዲህ እንዳያሸብራቸው፣+

አባት ለሌለው ልጅና ለተደቆሱ ሰዎች ፍትሕ ታሰፍናለህ።+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት መዝሙር።

11 ይሖዋን መጠጊያዬ አድርጌዋለሁ።+

ታዲያ እንዴት እንዲህ ትሉኛላችሁ?*

“እንደ ወፍ ወደ ተራራህ ብረር!*

 2 ክፉዎች ደጋናቸውን እንዴት እንደወጠሩ ተመልከት፤

በጨለማ፣ ልበ ቀና የሆኑትን ለመውጋት፣

ፍላጻቸውን በአውታሩ ላይ ደግነዋል።

 3 መሠረቶቹ* ከተናዱ፣

ጻድቁ ሰው ምን ማድረግ ይችላል?”

 4 ይሖዋ ቅዱስ በሆነው ቤተ መቅደሱ ውስጥ ነው።+

የይሖዋ ዙፋን በሰማያት ነው።+

የገዛ ዓይኖቹ ይመለከታሉ፤ ንቁ የሆኑት* ዓይኖቹ የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።+

 5 ይሖዋ ጻድቁንም ሆነ ክፉውን ይመረምራል፤+

ዓመፅን* የሚወድን ማንኛውንም ሰው ይጠላል።*+

 6 በክፉዎች ላይ ወጥመድ* ያዘንባል፤

እሳትና ድኝ+ እንዲሁም የሚለበልብ ነፋስ ጽዋቸው ይሆናል።

 7 ይሖዋ ጻድቅ ነውና፤+ የጽድቅ ሥራዎችን ይወዳል።+

ቅን የሆኑ ሰዎች ፊቱን ያያሉ።*+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በሸሚኒት ቅኝት።* የዳዊት ማህሌት።

12 ይሖዋ ሆይ፣ አንድም ታማኝ ሰው ስለሌለ አድነኝ፤

ከሰው ልጆች መካከል ታማኞች ጠፍተዋል።

 2 እርስ በርሳቸው ውሸት ይነጋገራሉ፤

በከንፈራቸው ይሸነግላሉ፤* አታላይ በሆነ ልብም* ይናገራሉ።+

 3 ይሖዋ የሚሸነግልን ከንፈር ሁሉ፣

ጉራ የሚነዛውንም ምላስ ይቆርጣል፤+

 4 እነሱ “በምላሳችን እንረታለን።

አንደበታችንን እንዳሻን እንጠቀምበታለን፤

በእኛ ላይ ጌታ ሊሆን የሚችል ማን ነው?” ይላሉ።+

 5 “የተጎሳቆሉት ሰዎች በመጨቆናቸው፣

ድሆችም በመቃተታቸው፣+

እርምጃ ለመውሰድ እነሳለሁ” ይላል ይሖዋ።

“በንቀት ዓይን ከሚመለከቷቸው* ሁሉ እታደጋቸዋለሁ።”

 6 የይሖዋ ቃል የጠራ ነው፤+

ከሸክላ በተሠራ ምድጃ* እንደተጣራ ብር ሰባት ጊዜ የነጠረ ነው።

 7 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ትጋርዳቸዋለህ፤+

እያንዳንዳቸውን ከዚህ ትውልድ ለዘላለም ትጠብቃቸዋለህ።

 8 የሰው ልጆች ብልሹ ምግባርን ስለሚያስፋፉ፣

ክፉዎች እንዳሻቸው ይፈነጫሉ።+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት ማህሌት።

13 ይሖዋ ሆይ፣ የምትረሳኝ እስከ መቼ ነው? ለዘላለም?

ፊትህን ከእኔ የምትሰውረው እስከ መቼ ነው?+

 2 ልቤ በየዕለቱ በሐዘን እየተደቆሰ፣

በጭንቀት ተውጬ የምኖረው* እስከ መቼ ነው?

ጠላቴ በእኔ ላይ የሚያይለው እስከ መቼ ነው?+

 3 ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ ወደ እኔ ተመልከት፤ መልስም ስጠኝ።

በሞት እንዳላንቀላፋ ዓይኖቼን አብራልኝ፤

 4 እንዲህ ከሆነ ጠላቴ “አሸነፍኩት!” አይልም፤

ባላጋራዎቼ በእኔ ውድቀት ሐሴት እንዲያደርጉ አትፍቀድ።+

 5 እኔ በበኩሌ በታማኝ ፍቅርህ እታመናለሁ፤+

ልቤ በማዳን ሥራህ ሐሴት ያደርጋል።+

 6 በእጅጉ ስለካሰኝ+ ለይሖዋ እዘምራለሁ።

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት መዝሙር።

14 ሞኝ* ሰው በልቡ

“ይሖዋ የለም” ይላል።+

ሥራቸው ብልሹ ነው፤ ተግባራቸውም አስጸያፊ ነው፤

መልካም የሚሠራ ማንም የለም።+

 2 ሆኖም ጥልቅ ማስተዋል ያለውና ይሖዋን የሚፈልግ ሰው ይኖር እንደሆነ ለማየት፣

ይሖዋ ከሰማይ ሆኖ ወደ ሰው ልጆች ይመለከታል።+

 3 ሁሉም መንገድ ስተዋል፤+

ሁሉም ብልሹ ናቸው።

መልካም የሚሠራ ማንም የለም፤

አንድ እንኳ የለም።

 4 ከክፉ አድራጊዎቹ መካከል አንዳቸውም አያስተውሉም?

ምግብ እንደሚበሉ ሕዝቤን ይውጣሉ።

ይሖዋን አይጠሩም።

 5 ይሁንና በታላቅ ሽብር ይዋጣሉ፤+

ይሖዋ ከጻድቅ ትውልድ ጋር ነውና።

 6 እናንተ ክፉ አድራጊዎች የችግረኛውን ሰው ዕቅድ ለማጨናገፍ ትሞክራላችሁ፤

ይሖዋ ግን መጠጊያው ነው።+

 7 የእስራኤል መዳን ምነው ከጽዮን በመጣ!+

ይሖዋ የተማረከውን ሕዝቡን በሚመልስበት ጊዜ፣

ያዕቆብ ደስ ይበለው፤ እስራኤል ሐሴት ያድርግ።

የዳዊት ማህሌት።

15 ይሖዋ ሆይ፣ በድንኳንህ ውስጥ በእንግድነት የሚስተናገድ ማን ነው?

በተቀደሰ ተራራህ የሚኖር ማን ነው?+

 2 ያለነቀፋ* የሚመላለስ፣+

ትክክል የሆነውን የሚያደርግ፣+

በልቡም እውነትን የሚናገር ሰው ነው።+

 3 በአንደበቱ ስም አያጠፋም፤+

በባልንጀራው ላይ መጥፎ ነገር አይሠራም፤+

የወዳጆቹንም ስም አያጎድፍም።*+

 4 ነውረኛ የሆነን ሰው ሁሉ ይንቃል፤+

ይሖዋን የሚፈሩትን ግን ያከብራል።

ጉዳት ላይ ሊጥለው ቢችልም እንኳ ቃሉን* አያጥፍም።+

 5 ገንዘቡን በወለድ አያበድርም፤+

ንጹሕ የሆነውን ሰው ለመወንጀልም ጉቦ አይቀበልም።+

እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ሰው ሁሉ ፈጽሞ አይናወጥም።*+

የዳዊት ሚክታም።*

16 አምላክ ሆይ፣ አንተን መጠጊያ አድርጌአለሁና ጠብቀኝ።+

 2 ይሖዋን እንዲህ አልኩት፦ “አንተ ይሖዋ ነህ፤ ለእኔ የጥሩ ነገሮች ምንጭ አንተ ነህ።

 3 ደግሞም በምድር ላይ ያሉት ቅዱሳን፣

ክብር የተላበሱት አገልጋዮች እጅግ ደስ ያሰኙኛል።”+

 4 ሌሎች አማልክትን የሚከተሉ ሐዘናቸውን ያበዛሉ።+

እንደ እነሱ ደምን የመጠጥ መባ አድርጌ አላቀርብም፤

በከንፈሬም ስማቸውን አላነሳም።+

 5 ይሖዋ ድርሻዬ፣ ዕጣ ፋንታዬና+ ጽዋዬ+ ነው።

ርስቴን ትጠብቅልኛለህ።

 6 ለእኔ ርስት አድርገህ ለመስጠት የለካኸው ቦታ ያማረ ነው።

አዎ፣ ባገኘሁት ርስት ረክቻለሁ።+

 7 ምክር የሰጠኝን ይሖዋን አወድሳለሁ።+

በሌሊትም እንኳ በውስጤ ያለው ሐሳብ* ያርመኛል።+

 8 ይሖዋን ሁልጊዜ በፊቴ አደርገዋለሁ።+

እሱ በቀኜ ስላለ ፈጽሞ አልናወጥም።*+

 9 ስለዚህ ልቤ ሐሴት ያደርጋል፤ ሁለንተናዬ* ደስ ይለዋል።

ያለስጋትም እኖራለሁ።*

10 መቃብር* ውስጥ አትተወኝምና።*+

ታማኝ አገልጋይህ ጉድጓድ እንዲያይ* አትፈቅድም።+

11 የሕይወትን መንገድ አሳወቅከኝ።+

በፊትህ* ብዙ ደስታ አለ፤+

በቀኝህ ለዘላለም ደስታ* አለ።

የዳዊት ጸሎት።

17 ይሖዋ ሆይ፣ ፍትሕ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና ስማ፤

እርዳታ ለማግኘት የማሰማውን ጩኸት በጥሞና አዳምጥ፤

ያለምንም ማታለል ያቀረብኩትን ጸሎት ስማ።+

 2 ለእኔ ስትል ፍትሐዊ ውሳኔ አድርግ፤+

ዓይኖችህ ትክክለኛ የሆነውን ነገር ይዩ።

 3 ልቤን መረመርክ፤ በሌሊት በሚገባ አጤንከኝ፤+

ደግሞም አጠራኸኝ፤+

አንዳች መጥፎ ነገር እንዳላሰብኩ ታውቃለህ፤

አንደበቴም አልበደለም።

 4 የሰዎችን ሥራ በተመለከተ ደግሞ፣

የከንፈርህን ቃል በማክበር ከዘራፊዎች መንገድ ርቄአለሁ።+

 5 እግሮቼ እንዳይደነቃቀፉ፣

አረማመዴ በመንገድህ ላይ ይጽና።+

 6 አምላክ ሆይ፣ መልስ ስለምትሰጠኝ አንተን እጣራለሁ።+

ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል።* ቃሌን ስማ።+

 7 በቀኝ እጅህ እንድትጠብቃቸው የሚሹትን፣

በአንተ ላይ ከሚያምፁ ሰዎች የምታድን ሆይ፣

ታማኝ ፍቅርህን ድንቅ በሆነ መንገድ አሳይ።+

 8 እንደ ዓይንህ ብሌን ጠብቀኝ፤+

በክንፎችህ ጥላ ሰውረኝ።+

 9 ጥቃት ከሚሰነዝሩብኝ ክፉዎች፣

ከሚከቡኝና ሊገድሉኝ ከሚፈልጉ ጠላቶቼ* ጠብቀኝ።+

10 ደንታ ቢሶች ሆነዋል፤*

በአፋቸው በእብሪት ይናገራሉ፤

11 መፈናፈኛ አሳጡን፤+

እኛን መጣል* የሚችሉበትን አጋጣሚ ነቅተው ይጠባበቃሉ።

12 እያንዳንዳቸው ያደነውን ለመዘነጣጠል እንደሚጓጓ አንበሳ፣

በስውር እንደሚያደባ ደቦል አንበሳ ናቸው።

13 ይሖዋ ሆይ፣ ተነስተህ ፊት ለፊት ግጠመው፤+ ደግሞም ጣለው፤

በሰይፍህ ከክፉው ሰው ታደገኝ፤*

14 ይሖዋ ሆይ፣ ከዚህ ዓለም* ሰዎች በእጅህ ታደገኝ፤

እነዚህ ሰዎች ድርሻቸው አሁን ያለው ሕይወት ነው፤+

አንተ በሰጠሃቸው መልካም ነገሮች አጥግበሃቸዋል፤+

ደግሞም ለብዙ ወንዶች ልጆቻቸው ርስት ያስተላልፋሉ።

15 እኔ ግን ፊትህን በጽድቅ አያለሁ፤

በምነቃበት ጊዜ አንተን በማየት እደሰታለሁ።+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የይሖዋ አገልጋይ የሆነው ዳዊት፣ ይሖዋ ከጠላቶቹ ሁሉ እጅና ከሳኦል እጅ ባዳነው ቀን ለይሖዋ የዘመረው መዝሙር፦+

18 ብርታቴ ይሖዋ ሆይ፣+ እወድሃለሁ።

 2 ይሖዋ ቋጥኜ፣ ምሽጌና ታዳጊዬ ነው።+

አምላኬ የምሸሸግበት ዓለቴ ነው፤+

ጋሻዬ፣ የመዳኔ ቀንድና* አስተማማኝ መጠጊያዬ ነው።+

 3 ውዳሴ የሚገባውን ይሖዋን እጠራለሁ፤

ከጠላቶቼም እድናለሁ።+

 4 የሞት ገመዶች ተተበተቡብኝ፤+

የማይረቡ ሰዎች የለቀቁት ድንገተኛ ጎርፍ አሸበረኝ።+

 5 የመቃብር* ገመድ ተጠመጠመብኝ፤

የሞት ወጥመድ ተጋረጠብኝ።+

 6 በጭንቅ ውስጥ ሳለሁ ይሖዋን ጠራሁት፤

እርዳታ ለማግኘት አምላኬን አጥብቄ ተማጸንኩት።

በመቅደሱ ሆኖ ድምፄን ሰማ፤+

እርዳታ ለማግኘት የማሰማውም ጩኸት ወደ ጆሮው ደረሰ።+

 7 ምድርም ትንቀጠቀጥና ትናወጥ ጀመር፤+

የተራሮች መሠረቶች ተንቀጠቀጡ፤

እሱ ስለተቆጣም ራዱ።+

 8 ከአፍንጫው ጭስ ወጣ፤

የሚባላም እሳት ከአፉ ወጣ፤+

ፍምም ከእሱ ፈለቀ።

 9 ወደ ታች ሲወርድ ሰማያት እንዲያጎነብሱ አደረገ፤+

ከእግሮቹም በታች ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበር።+

10 በኪሩብ ላይ ተቀምጦ እየበረረ መጣ።+

በመንፈስ* ክንፎች በፍጥነት ወረደ።+

11 ከዚያም በጨለማ ራሱን ሸፈነ፤+

ጥቁር ውኃና ጥቅጥቅ ያለ ደመና+

እንደ መጠለያ በዙሪያው ነበር።

12 በፊቱ ካለው ብርሃን፣

ከደመናቱ መካከል በረዶና ፍም ወጣ።

13 ከዚያም ይሖዋ በሰማያት ያንጎደጉድ ጀመር፤+

ልዑሉ አምላክ ድምፁን አሰማ፤+

ደግሞም በረዶና ፍም ነበር።

14 ፍላጻዎቹን አስፈንጥሮ በታተናቸው፤+

መብረቁን አዥጎድጉዶ ግራ አጋባቸው።+

15 ይሖዋ ሆይ፣ ከተግሣጽህ፣ ከአፍንጫህም ከሚወጣው ኃይለኛ እስትንፋስ የተነሳ+

የጅረቶች ወለል ታየ፤*+

የምድር መሠረቶችም ተገለጡ።

16 ከላይ ሆኖ እጁን ሰደደ፤

ከጥልቅ ውኃ ውስጥም አወጣኝ።+

17 ከብርቱ ጠላቴ አዳነኝ፤+

ከእኔ ይበልጥ ብርቱዎች ከሆኑት፣ ከሚጠሉኝ ሰዎች ታደገኝ።+

18 ችግር ላይ በወደቅኩበት ቀን ተነሱብኝ፤+

ይሖዋ ግን ድጋፍ ሆነልኝ።

19 ከዚያም ደህንነት ወደማገኝበት ስፍራ* አመጣኝ፤

በእኔ ስለተደሰተ ታደገኝ።+

20 ይሖዋ እንደ ጽድቄ ወሮታ ይከፍለኛል፤+

እንደ እጄ ንጽሕና ብድራት ይመልስልኛል።+

21 የይሖዋን መንገድ ጠብቄአለሁና፤

አምላኬን በመተው ክፉ ድርጊት አልፈጸምኩም።

22 ፍርዱ ሁሉ በፊቴ ነው፤

ደንቦቹን ቸል አልልም።

23 በፊቱ እንከን የለሽ ሆኜ እኖራለሁ፤+

ራሴንም ከስህተት እጠብቃለሁ።+

24 ይሖዋ እንደ ጽድቄ፣+

በፊቱ ንጹሕ እንደሆኑት እጆቼ ብድራት ይመልስልኝ።+

25 ታማኝ ለሆነ ሰው ታማኝ ትሆናለህ፤+

እንከን የለሽ ለሆነ ሰው እንከን የለሽ ትሆናለህ፤+

26 ከንጹሕ ሰው ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፤+

ጠማማ ለሆነ ሰው ግን ብልህ መሆንህን ታሳያለህ።+

27 ችግረኞችን* ታድናለህና፤+

ትዕቢተኛውን* ግን ታዋርዳለህ።+

28 ይሖዋ ሆይ፣ መብራቴን የምታበራው አንተ ነህና፤

አምላኬ ሆይ፣ ጨለማዬን ብርሃን የምታደርገው አንተ ነህ።+

29 በአንተ እርዳታ ወራሪውን ቡድን መጋፈጥ እችላለሁ፤+

በአምላክ ኃይል ቅጥር መውጣት እችላለሁ።+

30 የእውነተኛው አምላክ መንገድ ፍጹም ነው፤+

የይሖዋ ቃል የነጠረ ነው።+

እሱ መጠጊያ ለሚያደርጉት ሁሉ ጋሻቸው ነው።+

31 ደግሞስ ከይሖዋ ሌላ አምላክ ማን ነው?+

ከአምላካችንስ ሌላ ዓለት ማን ነው?+

32 ብርታትን የሚያስታጥቀኝ እውነተኛው አምላክ ነው፤+

መንገዴንም ፍጹም ያደርግልኛል።+

33 እግሮቼን እንደ ዋልያ እግሮች ያደርጋል፤

በከፍታ ቦታዎች ላይ ያቆመኛል።+

34 እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናል፤

ክንዶቼ የመዳብ ደጋን ማጠፍ ይችላሉ።

35 የመዳን ጋሻህን ትሰጠኛለህ፤+

ቀኝ እጅህ ይደግፈኛል፤

ትሕትናህም ታላቅ ያደርገኛል።+

36 ለእርምጃዬ መንገዱን ታሰፋልኛለህ፤

እግሮቼ* አያዳልጣቸውም።+

37 ጠላቶቼን አሳድጄ እደርስባቸዋለሁ፤

ተጠራርገው እስኪጠፉ ድረስ ወደ ኋላ አልመለስም።

38 እንዳያንሰራሩ አድርጌ አደቃቸዋለሁ፤+

እግሬ ሥር ይወድቃሉ።

39 ለውጊያው ብርታት ታስታጥቀኛለህ፤

ጠላቶቼ ሥሬ እንዲወድቁ ታደርጋለህ።+

40 ጠላቶቼ ከእኔ እንዲሸሹ ታደርጋለህ፤*

እኔም የሚጠሉኝን አጠፋቸዋለሁ።*+

41 እርዳታ ለማግኘት ይጮኻሉ፤ ሆኖም የሚያድናቸው የለም፤

ወደ ይሖዋም ይጮኻሉ፤ እሱ ግን አይመልስላቸውም።

42 በነፋስ ፊት እንዳለ አቧራ ፈጽሜ አደቃቸዋለሁ፤

በመንገድ ላይ እንዳለ ጭቃ አውጥቼ እጥላቸዋለሁ።

43 ስህተት ከሚለቃቅሙ ሰዎች ታድነኛለህ።+

የብሔራት መሪ አድርገህ ትሾመኛለህ።+

የማላውቀው ሕዝብ ያገለግለኛል።+

44 ስለ እኔ በሰሙት ነገር ብቻ ይታዘዙኛል፤

የባዕድ አገር ሰዎችም አንገታቸውን ደፍተው ወደ ፊቴ ይቀርባሉ።+

45 የባዕድ አገር ሰዎች ወኔ ይከዳቸዋል፤*

ከምሽጎቻቸው እየተንቀጠቀጡ ይወጣሉ።

46 ይሖዋ ሕያው ነው! ዓለቴ+ ይወደስ!

የመዳኔ አምላክ ከፍ ከፍ ይበል።+

47 እውነተኛው አምላክ ይበቀልልኛል፤+

ሕዝቦችንም ከበታቼ ያስገዛልኛል።

48 በቁጣ ከተሞሉ ጠላቶቼ ይታደገኛል፤

ከሚያጠቁኝ ሰዎች በላይ ከፍ ከፍ ታደርገኛለህ፤+

ከዓመፀኛ ሰው ታድነኛለህ።

49 ይሖዋ ሆይ፣ በብሔራት መካከል የማከብርህ ለዚህ ነው፤+

ለስምህም የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።+

50 እሱ ለንጉሡ ታላላቅ የማዳን ሥራዎች ያከናውናል፤*+

ለቀባውም ታማኝ ፍቅር ያሳያል፤+

ለዳዊትና ለዘሩ ለዘላለም ይህን ያደርጋል።+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት ማህሌት።

19 ሰማያት የአምላክን ክብር ይናገራሉ፤+

ጠፈርም የእጆቹን ሥራ ያውጃል።+

 2 በየዕለቱ ንግግራቸው ይሰማል፤

በእያንዳንዱም ሌሊት እውቀትን ይገልጣሉ።

 3 ንግግር የለም፤ ቃልም የለም፤

ድምፃቸው አይሰማም።

 4 ይሁንና ጩኸታቸው* ወደ መላው ምድር ወጣ፤

መልእክታቸውም እስከ ዓለም* ዳርቻዎች ተሰማ።+

እሱ በሰማያት ለፀሐይ ድንኳን ተክሏል፤

 5 ፀሐይም ከጫጉላ ቤት እንደሚወጣ ሙሽራ ነው፤

በጎዳናው ላይ እንደሚሮጥ ብርቱ ሰው ደስ ይለዋል።

 6 ከአንደኛው የሰማያት ዳርቻ ይወጣል፤

ዞሮም ወደ ሌላኛው ዳርቻ ይሄዳል፤+

ከሙቀቱም የሚሰወር አንዳች ነገር የለም።

 7 የይሖዋ ሕግ ፍጹም ነው፤+ ኃይልን ያድሳል።*+

የይሖዋ ማሳሰቢያ አስተማማኝ ነው፤+ ተሞክሮ የሌለውን ጥበበኛ ያደርጋል።+

 8 የይሖዋ መመሪያዎች ትክክል ናቸው፤ ልብን ደስ ያሰኛሉ፤+

የይሖዋ ትእዛዝ ንጹሕ ነው፤ ዓይንን ያበራል።+

 9 ይሖዋን መፍራት+ ንጹሕ ነው፤ ለዘላለም ይኖራል።

የይሖዋ ፍርዶች እውነት ናቸው፤ ሙሉ በሙሉ ትክክል ናቸው።+

10 ከወርቅ እንዲያውም ብዛት ካለው ምርጥ ወርቅ*

የበለጠ የሚወደዱ ናቸው፤+

ደግሞም ከማርና ከማር እንጀራ ከሚንጠባጠብ ወለላ ይበልጥ ይጣፍጣሉ።+

11 ለአገልጋይህ ማስጠንቀቂያ ሆነውለታል፤+

እነሱን መጠበቅ ትልቅ ወሮታ አለው።+

12 የራሱን ስህተት ማን ሊያስተውል ይችላል?+

ሳላውቅ የሠራኋቸውን ኃጢአቶች አትቁጠርብኝ።

13 አገልጋይህንም ከእብሪት ድርጊቶች ጠብቀው፤+

እንዲቆጣጠሩኝም አትፍቀድ።+

ያን ጊዜ እንከን የሌለብኝ እሆናለሁ፤+

ዓይን ካወጣ ኃጢአትም* ነፃ እሆናለሁ።

14 ዓለቴና+ አዳኜ+ ይሖዋ ሆይ፣ የአፌ ቃልና በልቤ የማሰላስለው ነገር

አንተን ደስ የሚያሰኝ ይሁን።+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት ማህሌት።

20 በጭንቀት ቀን ይሖዋ ይስማህ።

የያዕቆብ አምላክ ስም ይጠብቅህ።+

 2 ከቅዱሱ ስፍራ እርዳታ ይላክልህ፤+

ከጽዮንም ደግፎ ይያዝህ።+

 3 በስጦታ የምታቀርበውን መባ ሁሉ ያስብልህ፤

የሚቃጠል መባህን በሞገስ ዓይን* ይቀበልህ። (ሴላ)

 4 የልብህን ፍላጎት ያሟላልህ፤+

ዕቅድህንም* ሁሉ ያሳካልህ።

 5 በማዳን ሥራህ በደስታ እልል እንላለን፤+

በአምላካችን ስም ዓርማችንን ወደ ላይ ከፍ እናደርጋለን።+

ይሖዋ የለመንከውን ሁሉ ይፈጽምልህ።

 6 ይሖዋ የቀባውን እንደሚያድን አሁን አወቅኩ።+

በቀኝ እጁ በሚያከናውነው ታላቅ የማዳን ሥራ፣*+

ቅዱስ ከሆኑት ሰማያቱ ይመልስለታል።

 7 አንዳንዶች በሠረገሎች፣ ሌሎች ደግሞ በፈረሶች ይታመናሉ፤+

እኛ ግን የአምላካችንን የይሖዋን ስም እንጠራለን።+

 8 እነሱ ተዝለፍልፈው ወድቀዋል፤

እኛ ግን ተነስተን ቀጥ ብለን ቆመናል።+

 9 ይሖዋ ሆይ፣ ንጉሡን አድን!+

እርዳታ ለማግኘት በተጣራን ቀን ይመልስልናል።+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት ማህሌት።

21 ይሖዋ ሆይ፣ ንጉሡ በአንተ ብርታት ደስ ይለዋል፤+

በማዳን ሥራህ እጅግ ሐሴት ያደርጋል!+

 2 የልቡን ፍላጎት አሟልተህለታል፤+

የከንፈሩንም ልመና አልከለከልከውም። (ሴላ)

 3 የተትረፈረፉ በረከቶች ይዘህ ተቀበልከው፤

ምርጥ ከሆነ* ወርቅ የተሠራ አክሊልም በራሱ ላይ ደፋህለት።+

 4 ሕይወትን ለመነህ፤

አንተም ረጅም ዕድሜ* ብሎም የዘላለም ሕይወት ሰጠኸው።+

 5 የማዳን ሥራህ ታላቅ ክብር ያስገኝለታል።+

ሞገስና ግርማ አጎናጸፍከው።

 6 ለዘላለም እንዲባረክ አደረግከው፤+

ከእሱ ጋር እንዳለህ ሲያውቅ* በጣም ደስ ይለዋል።+

 7 ንጉሡ በይሖዋ ይተማመናልና፤+

በልዑሉ አምላክ ታማኝ ፍቅር የተነሳ ፈጽሞ አይናወጥም።*+

 8 እጅህ ጠላቶችህን ሁሉ ይይዛቸዋል፤

ቀኝ እጅህም የሚጠሉህን ይይዛቸዋል።

 9 በተወሰነው ጊዜ ትኩረትህን በእነሱ ላይ ስታደርግ እሳት እንደሚንቀለቀልበት ምድጃ ታደርጋቸዋለህ።

ይሖዋ በቁጣው ይውጣቸዋል፤ እሳትም ይበላቸዋል።+

10 የሆዳቸውን ፍሬ ከምድር ገጽ፣

ዘራቸውንም ከሰው ልጆች መካከል ታጠፋለህ።

11 በአንተ ላይ ክፉ ለመሥራት አስበዋልና፤+

ሊሳካ የማይችል ሴራ ጠንስሰዋል።+

12 ቀስትህን* በእነሱ ላይ* በማነጣጠር

እንዲያፈገፍጉ ታደርጋለህና።+

13 ይሖዋ ሆይ፣ በብርታትህ ተነስ።

ለኃያልነትህ የውዳሴ መዝሙር እንዘምራለን።

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ “በንጋት እንስት ርኤም።”* የዳዊት ማህሌት።

22 አምላኬ፣ አምላኬ ለምን ተውከኝ?+

እኔን ከማዳን፣ ከደረሰብኝም ሥቃይ የተነሳ የማሰማውን ጩኸት+ ከመስማት

የራቅከው ለምንድን ነው?

 2 አምላኬ ሆይ፣ በቀን ደጋግሜ እጣራለሁ፤ አንተ ግን አትመልስልኝም፤+

በሌሊትም ዝም ማለት አልቻልኩም።

 3 አንተ ግን ቅዱስ ነህ፤+

እስራኤል በሚያቀርበው ውዳሴ ተከበሃል።*

 4 አባቶቻችን እምነታቸውን በአንተ ላይ ጣሉ፤+

በአንተ ተማመኑ፤ አንተም ሁልጊዜ ትታደጋቸው ነበር።+

 5 ወደ አንተ ጮኹ፤ ደግሞም ዳኑ፤

በአንተ ተማመኑ፤ የጠበቁት ሳይፈጸም ቀርቶም አላዘኑም።*+

 6 እኔ ግን ትል እንጂ ሰው አይደለሁም፤

ሰው ያፌዘብኝ፣* ሕዝብም የናቀኝ ነኝ።+

 7 የሚያዩኝ ሁሉ ያላግጡብኛል፤+

በንቀትና በፌዝ ጭንቅላታቸውን እየነቀነቁ እንዲህ ይሉኛል፦+

 8 “ራሱን ለይሖዋ በአደራ ሰጥቷል። እስቲ እሱ ይታደገው!

በእሱ እጅግ የተወደደ ስለሆነ እሱ ያድነው!”+

 9 ከማህፀን ያወጣኸኝ አንተ ነህ፤+

በእናቴ ጡት ተማምኜ እንድኖር ያደረግከኝ አንተ ነህ።

10 ስወለድ ጀምሮ ለአንተ በአደራ ተሰጠሁ፤*

ከእናቴ ማህፀን ጀምሮ አንተ አምላኬ ነህ።

11 ችግር ሊደርስብኝ ስለሆነ ከእኔ አትራቅ፤+

ደግሞም ሌላ ረዳት የለኝም።+

12 ብዙ ወይፈኖች ከበውኛል፤+

የባሳን ኃይለኛ ኮርማዎችም በዙሪያዬ ናቸው።+

13 ያደነውን እንደሚቦጫጭቅ የሚያገሳ አንበሳ+

አፋቸውን በእኔ ላይ ከፈቱ።+

14 እንደ ውኃ ፈሰስኩ፤

አጥንቶቼ ሁሉ ከመጋጠሚያቸው ወለቁ።

ልቤ እንደ ሰም ሆነ፤+

በውስጤም ቀለጠ።+

15 ኃይሌ እንደ ገል ደረቀ፤+

ምላሴ ከላንቃዬ ጋር ተጣበቀ፤+

እንድሞትም ወደ ጉድጓድ አወረድከኝ።+

16 ውሾች ከበውኛልና፤+

እንደ ክፉ አድራጊዎች ሸንጎ በዙሪያዬ ሰፍረዋል፤+

እንደ አንበሳ ሆነው እጆቼና እግሮቼ ላይ ተረባረቡ።*+

17 አጥንቶቼን ሁሉ መቁጠር እችላለሁ።+

እነሱም አዩኝ፤ ትኩር ብለውም ተመለከቱኝ።

18 መደረቢያዎቼን እርስ በርሳቸው ተከፋፈሉ፤

በልብሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ።+

19 አንተ ግን ይሖዋ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ።+

አንተ ብርታቴ ነህ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።+

20 ከሰይፍ አድነኝ፤*

ውድ ሕይወቴን* ከውሾች መዳፍ* ታደጋት፤+

21 ከአንበሳ አፍና ከዱር በሬዎች ቀንድ አድነኝ፤+

መልስ ስጠኝ፤ ታደገኝም።

22 ስምህን ለወንድሞቼ አሳውቃለሁ፤+

በጉባኤ መካከልም አወድስሃለሁ።+

23 እናንተ ይሖዋን የምትፈሩ፣ አወድሱት!

እናንተ የያዕቆብ ዘር ሁሉ፣ ከፍ ከፍ አድርጉት!+

እናንተ የእስራኤል ዘር ሁሉ፣ ለእሱ ታላቅ አክብሮት አሳዩ።

24 እሱ የተጨቆነውን ሰው መከራ አልናቀምና፤+ ደግሞም አልተጸየፈም፤

ፊቱን ከእሱ አልሰወረም።+

ለእርዳታ ወደ እሱ በጮኸ ጊዜ ሰምቶታል።+

25 በታላቅ ጉባኤ መካከል አወድስሃለሁ፤+

እሱን በሚፈሩት ፊት ስእለቴን እፈጽማለሁ።

26 የዋሆች በልተው ይጠግባሉ፤+

ይሖዋን የሚፈልጉት እሱን ያወድሱታል።+

ለዘላለም ተደስታችሁ ኑሩ።*

27 የምድር ዳርቻዎች ሁሉ ይሖዋን አስታውሰው ወደ እሱ ይዞራሉ።

የሕዝቦች ነገዶች ሁሉ በፊትህ ይሰግዳሉ።+

28 ንግሥና የይሖዋ ነውና፤+

ብሔራትን ይገዛል።

29 በምድር ያሉ ባለጸጎች ሁሉ* ይበላሉ፤ ይሰግዳሉም፤

ወደ አፈር የሚወርዱ ሁሉ በእሱ ፊት ይንበረከካሉ፤

ከእነሱ መካከል አንዳቸውም ሕይወታቸውን* ማቆየት አይችሉም።

30 ዘሮቻቸው ያገለግሉታል፤

መጪው ትውልድ ስለ ይሖዋ ይነገረዋል።

31 መጥተው ጽድቁን ያወራሉ።

ገና ለሚወለድ ሕዝብ ያደረገውን ነገር ይናገራሉ።

የዳዊት ማህሌት።

23 ይሖዋ እረኛዬ ነው።+

የሚጎድልብኝ ነገር የለም።+

 2 በለመለመ መስክ ያሳርፈኛል፤

ውኃ ወዳለበት የእረፍት ቦታም* ይመራኛል።+

 3 ኃይሌን* ያድሳል።+

ለስሙ ሲል በጽድቅ መንገድ ይመራኛል።+

 4 ድቅድቅ ጨለማ በዋጠው ሸለቆ ውስጥ ብሄድ እንኳ+

አንተ ከእኔ ጋር ስለሆንክ፣+

ጉዳት ይደርስብኛል ብዬ አልፈራም፤+

በትርህና ምርኩዝህ ያበረታቱኛል።*

 5 በጠላቶቼ ፊት ማዕድ አዘጋጀህልኝ።+

ራሴን በዘይት ቀባህ፤+

ጽዋዬ ጢም ብሎ ሞልቷል።+

 6 ጥሩነትህና ታማኝ ፍቅርህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፤+

ዕድሜዬንም በሙሉ በይሖዋ ቤት እኖራለሁ።+

የዳዊት መዝሙር። ማህሌት።

24 ምድርና በውስጧ ያለው ነገር ሁሉ፣

ፍሬያማ የሆነችው ምድርና በእሷ ላይ የሚኖር ሁሉ የይሖዋ ነው።+

 2 እሱ በባሕሮች ላይ መሥርቷታልና፤+

በወንዞችም ላይ አጽንቶ አስቀምጧታል።

 3 ወደ ይሖዋ ተራራ መውጣት የሚችል ማን ነው?+

በቅዱስ ስፍራውስ ሊቆም የሚችል ማን ነው?

 4 ከክፋት የጸዱ እጆችና ንጹሕ ልብ ያለው፣+

በእኔ ሕይወት* በሐሰት ያልማለ፣

በማታለልም መሐላ ያልፈጸመ።+

 5 እሱ በረከትን ከይሖዋ ያገኛል፤+

ጽድቅንም* አዳኝ ከሆነው አምላኩ ይቀበላል።+

 6 እሱን የሚፈልጉ ሰዎች ትውልድ ይህ ነው፤

የያዕቆብ አምላክ ሆይ፣ ፊትህን የሚፈልጉ ሰዎች ትውልድ እንዲህ ያለ ነው። (ሴላ)

 7 እናንተ ደጆች፣ ራሳችሁን ቀና አድርጉ፤+

እናንተ ጥንታዊ በሮች፣

ክብር የተጎናጸፈው ንጉሥ ይገባ ዘንድ ተከፈቱ!*+

 8 ይህ ክብር የተጎናጸፈ ንጉሥ ማን ነው?

ብርቱና ኃያል የሆነው ይሖዋ ነው፤+

በውጊያ ኃያል የሆነው ይሖዋ ነው።+

 9 እናንተ ደጆች፣ ራሳችሁን ቀና አድርጉ፤+

እናንተ ጥንታዊ በሮች፣

ክብር የተጎናጸፈው ንጉሥ ይገባ ዘንድ ተከፈቱ!

10 ይህ ክብር የተጎናጸፈ ንጉሥ ማን ነው?

የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ነው፤ ክብር የተጎናጸፈው ንጉሥ እሱ ነው።+ (ሴላ)

የዳዊት መዝሙር።

א [አሌፍ]

25 ይሖዋ ሆይ፣ አንተን እማጸናለሁ።*

ב [ቤት]

 2 አምላኬ ሆይ፣ በአንተ እታመናለሁ፤+

ለኀፍረት እንድዳረግ አትፍቀድ።+

ጠላቶቼ በደረሰብኝ መከራ አይፈንድቁ።+

ג [ጊሜል]

 3 አንተን ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ በፍጹም አያፍርም፤+

ያላንዳች ምክንያት ክህደት የሚፈጽሙ ግን ለኀፍረት ይዳረጋሉ።+

ד [ዳሌት]

 4 ይሖዋ ሆይ፣ መንገድህን አሳውቀኝ፤+

ጎዳናህንም አስተምረኝ።+

ה [ሄ]

 5 አንተ አዳኝ አምላኬ ስለሆንክ

በእውነትህ እንድመላለስ አድርገኝ፤ አስተምረኝም።+

ז [ዋው]

ቀኑን ሙሉ አንተን ተስፋ አደርጋለሁ።

ז [ዛየን]

 6 ይሖዋ ሆይ፣ ምንጊዜም ታሳያቸው የነበሩትን*+

ምሕረትህንና ታማኝ ፍቅርህን አስታውስ።+

ח [ኼት]

 7 በወጣትነቴ የሠራኋቸውን ኃጢአቶችና በደሎች አታስብብኝ።

ይሖዋ ሆይ፣ ለጥሩነትህ ስትል+

እንደ ታማኝ ፍቅርህ መጠን አስበኝ።+

ט [ቴት]

 8 ይሖዋ ጥሩና ቀና ነው።+

ኃጢአተኞችን ሊኖሩበት የሚገባውን መንገድ የሚያስተምራቸው ለዚህ ነው።+

י [ዮድ]

 9 የዋሆችን በትክክለኛ መንገድ* ይመራቸዋል፤+

እንዲሁም ለየዋሆች መንገዱን ያስተምራል።+

כ [ካፍ]

10 የይሖዋ መንገዶች ሁሉ፣ ቃል ኪዳኑንና+ ማሳሰቢያዎቹን+ ለሚጠብቁ፣

ታማኝ ፍቅር የሚንጸባረቅባቸውና እምነት የሚጣልባቸው ናቸው።

ל [ላሜድ]

11 ይሖዋ ሆይ፣ ኃጢአቴ ታላቅ ቢሆንም እንኳ

ለስምህ ስትል ይቅር በለኝ።+

מ [ሜም]

12 ይሖዋን የሚፈራ ሰው ማን ነው?+

መምረጥ ስላለበት መንገድ ያስተምረዋል።+

נ [ኑን]

13 እሱ ጥሩ የሆነውን ነገር ያገኛል፤*+

ዘሮቹም ምድርን ይወርሳሉ።+

ס [ሳሜኽ]

14 ከይሖዋ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት የሚኖራቸው እሱን የሚፈሩ ሰዎች ናቸው፤+

ቃል ኪዳኑንም ያሳውቃቸዋል።+

ע [አይን]

15 ዓይኖቼ ሁልጊዜ ወደ ይሖዋ ያያሉ፤+

እግሮቼን ከወጥመድ ያወጣቸዋልና።+

פ [ፔ]

16 ብቸኛና ምስኪን ስለሆንኩ

ፊትህን ወደ እኔ መልስ፤ ቸርነትም አሳየኝ።

צ [ጻዴ]

17 የልቤ ጭንቀት በዝቷል፤+

ከሥቃዬ ገላግለኝ።

ר [ረሽ]

18 ጉስቁልናዬንና መከራዬን ተመልከት፤+

ኃጢአቴንም ሁሉ ይቅር በል።+

19 ጠላቶቼ ምን ያህል ብዙ እንደሆኑ ተመልከት፤

ምን ያህል አምርረው እንደሚጠሉኝም እይ።

ש [ሺን]

20 ሕይወቴን* ጠብቅ፤ አድነኝም።+

አንተን መጠጊያ ስላደረግኩ ለኀፍረት እንድዳረግ አትፍቀድ።

ת [ታው]

21 ንጹሕ አቋሜና* ቅንነቴ ይጠብቁኝ፤+

አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና።+

22 አምላክ ሆይ፣ እስራኤልን ከጭንቀቱ ሁሉ ታደገው።*

የዳዊት መዝሙር።

26 ይሖዋ ሆይ፣ በንጹሕ አቋም* ተመላልሻለሁና ፍረድልኝ፤+

ያለምንም ማወላወል በይሖዋ ታምኛለሁ።+

 2 ይሖዋ ሆይ፣ መርምረኝ፤ ፈትነኝም፤

በውስጤ ያለውን ሐሳብና* ልቤን አጥራልኝ።+

 3 ታማኝ ፍቅርህ ምንጊዜም በፊቴ ነውና፤

በእውነትህም እመላለሳለሁ።+

 4 አታላይ ከሆኑ ሰዎች ጋር አልቀራረብም፤*+

ማንነታቸውን ከሚደብቁም እርቃለሁ።*

 5 ከክፉ ሰዎች ጋር መሆን እጠላለሁ፤+

ከክፉዎችም ጋር መቀራረብ* አልፈልግም።+

 6 ንጹሕ መሆኔን ለማሳየት እጆቼን እታጠባለሁ፤

ይሖዋ ሆይ፣ መሠዊያህን እዞራለሁ፤

 7 ይህም የምስጋናን ድምፅ አሰማ ዘንድ፣+

ድንቅ ሥራዎችህንም ሁሉ አውጅ ዘንድ ነው።

 8 ይሖዋ ሆይ፣ የምትኖርበትን ቤት፣+

የክብርህንም ማደሪያ ቦታ እወዳለሁ።+

 9 ከኃጢአተኞች ጋር አታጥፋኝ፤*+

ሕይወቴንም ከዓመፀኞች* ጋር አታስወግድ፤

10 እጆቻቸው አሳፋሪ ድርጊት ይፈጽማሉ፤

ቀኝ እጃቸውም በጉቦ የተሞላ ነው።

11 እኔ ግን ንጹሕ አቋሜን ጠብቄ እመላለሳለሁ።

ታደገኝ፤* ሞገስም አሳየኝ።

12 እግሬ በደልዳላ ስፍራ ቆሟል፤+

በታላቅ ጉባኤ መካከል* ይሖዋን አወድሳለሁ።+

የዳዊት መዝሙር።

27 ይሖዋ ብርሃኔና+ አዳኜ ነው።

ማንን እፈራለሁ?+

ይሖዋ የሕይወቴ ተገን ነው።+

ማን ያሸብረኛል?

 2 ክፉዎች ሥጋዬን ለመብላት ባጠቁኝ ጊዜ፣+

ተሰናክለው የወደቁት ባላጋራዎቼና ጠላቶቼ ናቸው።

 3 ሠራዊት በዙሪያዬ ቢሰፍርም፣

ልቤ በፍርሃት አይዋጥም።+

ጦርነት ቢከፈትብኝም እንኳ

በልበ ሙሉነት እመላለሳለሁ።

 4 ይሖዋን አንድ ነገር ለመንኩት፤

ምኞቴም ይኸው ነው፦

በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በይሖዋ ቤት እኖር ዘንድ፣+

ይሖዋ ደስ የሚያሰኝ መሆኑን በትኩረት እመለከት ዘንድ፣

ቤተ መቅደሱንም በአድናቆት አይ* ዘንድ ነው።+

 5 በመዓት ቀን በመጠለያው ይሸሽገኛል፤+

ሚስጥራዊ ቦታ በሆነው ድንኳኑ ውስጥ ይሰውረኛል፤+

ከፍ ባለ ዓለት ላይ ያስቀምጠኛል።+

 6 በመሆኑም ራሴ በዙሪያዬ ካሉ ጠላቶቼ በላይ ከፍ ብሏል፤

በድንኳኑ ውስጥ በእልልታ መሥዋዕት አቀርባለሁ፤

ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።

 7 ይሖዋ ሆይ፣ በምጮኽበት ጊዜ ስማኝ፤+

ሞገስ አሳየኝ፤ መልስም ስጠኝ።+

 8 ልቤ በአንተ ቦታ ሆኖ ሲናገር

“ፊቴን ፈልጉ” ብሏል።

ይሖዋ ሆይ፣ ፊትህን እሻለሁ።+

 9 ፊትህን ከእኔ አትሰውር።+

አገልጋይህን ተቆጥተህ ፊት አትንሳው።

አንተ ረዳቴ ነህ፤+

አዳኝ አምላኬ ሆይ፣ ከእኔ አትለይ፤ አትተወኝም።

10 የገዛ አባቴና እናቴ ቢተዉኝ እንኳ+

ይሖዋ ራሱ ይቀበለኛል።+

11 ይሖዋ ሆይ፣ መንገድህን አስተምረኝ፤+

ከጠላቶቼ ጥበቃ እንዳገኝ ቀና በሆነ መንገድ ምራኝ።

12 ለጠላቶቼ* አሳልፈህ አትስጠኝ፤+

ሐሰተኛ ምሥክሮች በእኔ ላይ ተነስተዋልና፤+

ደግሞም እኔን ለማጥቃት ይዝቱብኛል።

13 በሕያዋን ምድር የይሖዋን ጥሩነት አያለሁ የሚል እምነት ባይኖረኝ ኖሮ

ምን ይውጠኝ ነበር!*+

14 ይሖዋን ተስፋ አድርግ፤+

ደፋር ሁን፤ ልብህም ይጽና።+

አዎ፣ ይሖዋን ተስፋ አድርግ።

የዳዊት መዝሙር።

28 ዓለቴ ይሖዋ ሆይ፣ ሁልጊዜ ወደ አንተ እጣራለሁ፤+

አንተም ጆሮ አትንፈገኝ።

ዝም ካልከኝ፣

ወደ ጉድጓድ* እንደሚወርዱ ሰዎች እሆናለሁ።+

 2 ወደ መቅደስህ ውስጠኛ ክፍል እጆቼን አንስቼ፣

እርዳታ ለማግኘት ወደ አንተ በምጮኽበት ጊዜ ልመናዬን ስማ።+

 3 ከክፉዎችና መጥፎ ነገር ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ጎትተህ አትውሰደኝ፤+

እነሱ በልባቸው ክፋት እያለ ከባልንጀሮቻቸው ጋር የሰላም ቃል የሚያወሩ ናቸው።+

 4 ለሠሩት ሥራ፣

እንደ ክፉ ልማዳቸው ክፈላቸው።+

ለእጃቸው ሥራ መልሰህ ክፈላቸው፤

እንዳደረጉትም መልስላቸው።+

 5 ይሖዋ ላከናወናቸው ነገሮች፣

ለእጆቹም ሥራ ትኩረት አይሰጡምና።+

እሱ ያፈርሳቸዋል፤ ደግሞም አይገነባቸውም።

 6 እርዳታ ለማግኘት ያቀረብኩትን ልመና ስለሰማ

ይሖዋ የተመሰገነ ይሁን።

 7 ይሖዋ ብርታቴና+ ጋሻዬ ነው፤+

ልቤ በእሱ ይተማመናል።+

ከእሱ እርዳታ ስላገኘሁ ልቤ ሐሴት ያደርጋል፤

በመዝሙሬም አወድሰዋለሁ።

 8 ይሖዋ ለሕዝቡ ብርታት ነው፤

ለቀባው ታላቅ መዳን የሚያስገኝ መሸሸጊያ ነው።+

 9 ሕዝብህን አድን፤ ርስትህንም ባርክ።+

ለዘላለም እረኛ ሁናቸው፤ በክንድህም ተሸከማቸው።+

የዳዊት ማህሌት።

29 እናንተ የኃያላን ልጆች፣ ለይሖዋ የሚገባውን ስጡ፤

ከክብሩና ከብርታቱ የተነሳ ለይሖዋ የሚገባውን ስጡ።+

 2 ለስሙ የሚገባውን ክብር ለይሖዋ ስጡ።

ያጌጠ የቅድስና ልብስ ለብሳችሁ* ለይሖዋ ስገዱ።*

 3 የይሖዋ ድምፅ ከውኃዎች በላይ ተሰማ፤

ክብር የተጎናጸፈው አምላክ አንጎደጎደ።+

ይሖዋ ከብዙ ውኃዎች በላይ ነው።+

 4 የይሖዋ ድምፅ ኃይለኛ ነው፤+

የይሖዋ ድምፅ ክብራማ ነው።

 5 የይሖዋ ድምፅ አርዘ ሊባኖስን ይሰብራል፤

አዎ፣ ይሖዋ አርዘ ሊባኖስን ይሰባብራል።+

 6 ሊባኖስን* እንደ ጥጃ፣

ሲሪዮንንም+ እንደ ዱር በሬ እንቦሳ እንዲዘሉ ያደርጋል።

 7 የይሖዋ ድምፅ የእሳት ነበልባል ይረጫል፤+

 8 የይሖዋ ድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል፤+

ይሖዋ የቃዴስን+ ምድረ በዳ ያናውጣል።

 9 የይሖዋ ድምፅ ርኤሞች* እንዲርበተበቱና እንዲወልዱ ያደርጋል፤

ደኖችንም ያራቁታል።+

በቤተ መቅደሱም ውስጥ ያሉ ሁሉ “ክብር ለአምላክ!” ይላሉ።

10 ይሖዋ ከሚያጥለቀልቁት ውኃዎች*+ በላይ በዙፋን ላይ ይቀመጣል፤

ይሖዋ ለዘላለም ንጉሥ ሆኖ በዙፋን ላይ ይቀመጣል።+

11 ይሖዋ ለሕዝቡ ብርታት ይሰጣል።+

ይሖዋ ሰላም በመስጠት ሕዝቡን ይባርካል።+

ማህሌት። ለቤቱ ምረቃ የተዘመረ የዳዊት መዝሙር።

30 ይሖዋ ሆይ፣ ወደ ላይ ስላነሳኸኝ* ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤

ጠላቶቼ በእኔ ሥቃይ እንዲደሰቱ አልፈቀድክም።+

 2 ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ እርዳታ ለማግኘት ወደ አንተ ጮኽኩ፤ አንተም ፈወስከኝ።+

 3 ይሖዋ ሆይ፣ ከመቃብር* አውጥተኸኛል።*+

በሕይወት አቆይተኸኛል፤ ወደ ጉድጓድ* ከመውረድ አድነኸኛል።+

 4 እናንተ የእሱ ታማኝ አገልጋዮች፣ ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤+

ለቅዱስ ስሙ*+ ምስጋና አቅርቡ፤

 5 ምክንያቱም የሚቆጣው ለአጭር ጊዜ ነው፤+

ሞገስ የሚያሳየው* ግን ለዕድሜ ልክ ነው።+

ማታ ለቅሶ ቢሆንም ጠዋት ግን እልልታ ይሆናል።+

 6 በተረጋጋሁ ጊዜ

“ፈጽሞ አልናወጥም”* አልኩ።

 7 ይሖዋ ሆይ፣ ሞገስ ባሳየኸኝ ጊዜ እንደ ተራራ አጠነከርከኝ።+

ፊትህን በሰወርክ ጊዜ ግን ተሸበርኩ።+

 8 ይሖዋ ሆይ፣ ወደ አንተ ደጋግሜ ተጣራሁ፤+

ሞገስ ለማግኘትም ይሖዋን አብዝቼ ተማጸንኩ።

 9 መሞቴና* ወደ ጉድጓድ* መውረዴ+ ምን የሚያስገኘው ጥቅም አለ?

አፈር ያወድስሃል?+ የአንተንስ ታማኝነት ይናገራል?+

10 ይሖዋ ሆይ፣ ስማኝ፤ ሞገስም አሳየኝ።+

ይሖዋ ሆይ፣ ረዳቴ ሁን።+

11 ሐዘኔን ወደ ጭፈራ ለወጥክ፤

ማቄን አውልቀህ ደስታን አለበስከኝ፤

12 ይህም እኔ* ዝም ከማለት ይልቅ ለአንተ የውዳሴ መዝሙር እዘምር ዘንድ ነው።

ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ ለዘላለም አወድስሃለሁ።

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት ማህሌት።

31 ይሖዋ ሆይ፣ አንተን መጠጊያ አድርጌአለሁ።+

ፈጽሞ አልፈር።+

ከጽድቅህ የተነሳ ታደገኝ።+

 2 ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል።*

ፈጥነህ ታደገኝ።+

እኔን ለማዳን በተራራ ላይ ያለ ምሽግ፣

የተመሸገ ስፍራም ሁንልኝ።+

 3 አንተ ቋጥኜና ምሽጌ ነህና፤+

ለስምህ ስትል+ ትመራኛለህ፤ የምሄድበትንም መንገድ ታሳየኛለህ።+

 4 አንተ መሸሸጊያዬ ስለሆንክ፣+

እነሱ በስውር ከዘረጉብኝ ወጥመድ ታስጥለኛለህ።+

 5 መንፈሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ።+

የእውነት* አምላክ የሆንከው ይሖዋ ሆይ፣+ ዋጅተኸኛል።

 6 የማይረቡና ከንቱ የሆኑ ጣዖቶችን የሚያመልኩ ሰዎችን እጠላለሁ፤

እኔ ግን በይሖዋ እታመናለሁ።

 7 በታማኝ ፍቅርህ እጅግ ሐሴት አደርጋለሁ፤

ጉስቁልናዬን አይተሃልና፤+

በጭንቀት መዋጤን* ታውቃለህ።

 8 ለጠላት አሳልፈህ አልሰጠኸኝም፤

ይልቁንም ደህንነት በማገኝበት ስፍራ አቆምከኝ።*

 9 ይሖዋ ሆይ፣ በጭንቀት ስለተዋጥኩ ሞገስ አሳየኝ።

መከራ ዓይኔንም ሆነ መላ ሰውነቴን አድክሞታል።*+

10 ሕይወቴ በሐዘን፣

ዕድሜዬም በመቃተት አልቋል።+

ከፈጸምኩት ኃጢአት የተነሳ ጉልበቴ ተሟጠጠ፤

አጥንቶቼ ደከሙ።+

11 ባላጋራዎቼ ሁሉ፣

በተለይ ደግሞ ጎረቤቶቼ ተሳለቁብኝ።+

የሚያውቁኝ ሰዎችም እጅግ ፈሩኝ፤

በአደባባይ ሲያዩኝ ከእኔ ይሸሻሉ።+

12 የሞትኩ ያህል ከልባቸው ወጣሁ፤* ደግሞም ተረሳሁ፤

እንደተሰበረ ማሰሮ ነኝ።

13 ብዙ መጥፎ ወሬ ሰምቻለሁ፤

ሽብር ከቦኛል።+

ግንባር ፈጥረው በእኔ ላይ በተነሱ ጊዜ

ሕይወቴን* ለማጥፋት ያሴራሉ።+

14 ይሖዋ ሆይ፣ እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ።+

“አንተ አምላኬ ነህ” እላለሁ።+

15 የሕይወት ዘመኔ በእጅህ ነው።

ከጠላቶቼና ከሚያሳድዱኝ እጅ ታደገኝ።+

16 ፊትህ በአገልጋይህ ላይ እንዲበራ አድርግ።+

በታማኝ ፍቅርህ አድነኝ።

17 ይሖዋ ሆይ፣ አንተን በጠራሁ ጊዜ አልፈር።+

ክፉዎች ግን ይፈሩ፤+

በመቃብር* ውስጥ ዝም ይበሉ።+

18 በትዕቢትና በንቀት በጻድቁ ላይ በእብሪት የሚናገሩ

ሐሰተኛ ከንፈሮች ዱዳ ይሁኑ።+

19 ጥሩነትህ ምንኛ ብዙ ነው!+

አንተን ለሚፈሩ ጠብቀህ አቆይተኸዋል፤+

እንዲሁም አንተን መጠጊያ ለሚያደርጉ ስትል በሰዎች ሁሉ ፊት አሳይተኸዋል።+

20 አንተ ባለህበት ሚስጥራዊ ቦታ፣

ከሰዎች ሴራ ትሸሽጋቸዋለህ፤+

በመጠለያህ ውስጥ

ከክፉ ጥቃት* ትሰውራቸዋለህ።+

21 በተከበበ ከተማ ውስጥ+ ታማኝ ፍቅሩን በአስደናቂ ሁኔታ ስላሳየኝ+

ይሖዋ የተመሰገነ ይሁን።

22 እኔ በድንጋጤ ተውጬ

“ከፊትህ መጥፋቴ ነው” አልኩ።+

አንተ ግን እርዳታ ለማግኘት በጮኽኩ ጊዜ ልመናዬን ሰማህ።+

23 እናንተ ለእሱ ታማኝ የሆናችሁ ሁሉ፣ ይሖዋን ውደዱ!+

ይሖዋ ታማኞችን ይጠብቃል፤+

ትዕቢተኛ የሆነን ሰው ግን ክፉኛ ይቀጣል።+

24 እናንተ ይሖዋን የምትጠባበቁ ሁሉ፣+

ደፋር ሁኑ፤ ልባችሁም ይጽና።+

የዳዊት መዝሙር። ማስኪል።*

32 በደሉ ይቅር የተባለለት፣ ኃጢአቱ የተሸፈነለት* ሰው+ ደስተኛ ነው።

 2 ይሖዋ በጥፋተኝነት የማይጠይቀው፣

በመንፈሱ ሽንገላ የሌለበት ሰው ደስተኛ ነው።+

 3 ዝም ባልኩ ጊዜ፣ ቀኑን ሙሉ ከመቃተቴ የተነሳ አጥንቶቼ መነመኑ።+

 4 ቀንና ሌሊት እጅህ* በእኔ ላይ ከብዳለችና።+

በበጋ ንዳድ እንደሚተን ውኃ ኃይሌ ተነነ።* (ሴላ)

 5 በመጨረሻ ኃጢአቴን ለአንተ ተናዘዝኩ፤

ስህተቴን አልሸፋፈንኩም።+

“የፈጸምኳቸውን በደሎች ለይሖዋ እናዘዛለሁ” አልኩ።+

አንተም ስህተቴንና ኃጢአቴን ይቅር አልክ።+ (ሴላ)

 6 ታማኝ የሆነ ሁሉ

አንተ በምትገኝበት ጊዜ ወደ አንተ የሚጸልየው ለዚህ ነው።+

በዚህ ጊዜ ኃይለኛ ጎርፍ እንኳ አይነካውም።

 7 አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤

ከጭንቀት ትሰውረኛለህ።+

በድል* እልልታ ትከበኛለህ።+ (ሴላ)

 8 አንተ እንዲህ ብለሃል፦ “ጥልቅ ማስተዋል እሰጥሃለሁ፤ ልትሄድበት የሚገባውንም መንገድ አስተምርሃለሁ።+

ዓይኔን በአንተ ላይ አድርጌ እመክርሃለሁ።+

 9 በልጓም ወይም በልባብ ካልተገራ በስተቀር አልገዛም ብሎ

ወደ እናንተ እንደማይቀርብ፣

ማስተዋል እንደሌለው ፈረስ ወይም በቅሎ አትሁኑ።”+

10 የክፉ ሰው ሥቃይ ብዙ ነው፤

በይሖዋ የሚታመን ሰው ግን ታማኝ ፍቅሩ ይከበዋል።+

11 ጻድቃን ሆይ፣ በይሖዋ ደስ ይበላችሁ፤ ሐሴትም አድርጉ፤

ልበ ቀና የሆናችሁ ሁሉ፣ እልል በሉ።

33 እናንተ ጻድቃን ሆይ፣ ይሖዋ ባደረጋቸው ነገሮች የተነሳ እልል በሉ።+

ቅኖች እሱን ማወደሳቸው የተገባ ነው።

 2 ይሖዋን በበገና አመስግኑት፤

አሥር አውታር ባለው መሣሪያ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩለት።

 3 አዲስ መዝሙር ዘምሩለት፤+

በባለ አውታር መሣሪያ ጥሩ አድርጋችሁ ተጫወቱ፤ እልልም በሉ።

 4 የይሖዋ ቃል ትክክል ነውና፤+

ሥራውም ሁሉ እምነት የሚጣልበት ነው።

 5 ጽድቅንና ፍትሕን ይወዳል።+

ምድር በይሖዋ ታማኝ ፍቅር ተሞልታለች።+

 6 ሰማያት በይሖዋ ቃል፣

በውስጣቸው ያሉትም ሁሉ ከአፉ በሚወጣው መንፈስ* ተሠሩ።+

 7 የባሕርን ውኃዎች እንደ ግድብ ያከማቻል፤+

የሚናወጠውንም ውኃ በማከማቻ ቦታ ይሰበስባል።

 8 መላዋ ምድር ይሖዋን ትፍራ።+

የምድር ነዋሪዎች እሱን ይፍሩ።*

 9 እሱ ተናግሯልና፣ ሆኗል፤+

እሱ አዟል፤ ደግሞም ተፈጽሟል።+

10 ይሖዋ የብሔራትን ሴራ* አክሽፏል፤+

የሕዝቦችን ዕቅድ* አጨናግፏል።+

11 ይሁንና የይሖዋ ውሳኔዎች ለዘላለም ይጸናሉ፤*+

የልቡ ሐሳብ ከትውልድ እስከ ትውልድ ጸንቶ ይኖራል።

12 ይሖዋ አምላኩ የሆነ ብሔር፣

የራሱ ንብረት አድርጎ የመረጠው ሕዝብ ደስተኛ ነው።+

13 ይሖዋ ከሰማይ ሆኖ ይመለከታል፤

የሰው ልጆችን ሁሉ ያያል።+

14 ከመኖሪያ ቦታው ሆኖ

በምድር የሚኖሩትን በትኩረት ይመለከታል።

15 የሁሉንም ልብ የሚሠራው እሱ ነው፤

ሥራቸውን ሁሉ ይመረምራል።+

16 በሠራዊት ብዛት የዳነ ንጉሥ የለም፤+

ኃያል ሰው በታላቅ ኃይሉ አይድንም።+

17 ፈረስ ያድነኛል* ብሎ መታመን ከንቱ ተስፋ ነው፤+

ታላቅ ኃይሉ ለመዳን ዋስትና አይሆንም።

18 እነሆ፣ የይሖዋ ዓይን የሚፈሩትን፣

ደግሞም ታማኝ ፍቅሩን የሚጠባበቁትን በትኩረት ይመለከታል፤+

19 ይህም እነሱን* ከሞት ለመታደግ፣

በረሃብ ወቅትም እነሱን በሕይወት ለማኖር ነው።+

20 ይሖዋን በተስፋ እንጠባበቃለን።*

እሱ ረዳታችንና ጋሻችን ነው።+

21 ልባችን በእሱ ሐሴት ያደርጋል፤

በቅዱስ ስሙ እንታመናለንና።+

22 ይሖዋ ሆይ፣ አንተን ስንጠባበቅ፣+

ታማኝ ፍቅርህ በእኛ ላይ ይሁን።+

ዳዊት በአቢሜሌክ* ፊት አእምሮውን የሳተ መስሎ በመቅረቡ+ አባሮ ባስወጣው ጊዜ የዘመረው መዝሙር።

א [አሌፍ]

34 ይሖዋን ሁልጊዜ አወድሰዋለሁ፤

ውዳሴው ምንጊዜም ከአፌ አይለይም።

ב [ቤት]

 2 በይሖዋ እኩራራለሁ፤*+

የዋሆች ሰምተው ሐሴት ያደርጋሉ።

ג [ጊሜል]

 3 ይሖዋን ከእኔ ጋር አወድሱት፤+

በኅብረት ስሙን ከፍ ከፍ እናድርግ።

ד [ዳሌት]

 4 ይሖዋን ጠየቅኩት፤ እሱም መለሰልኝ።+

ከምፈራው ነገር ሁሉ ታደገኝ።+

ה [ሄ]

 5 እሱን ተስፋ ያደረጉ በደስታ ፈኩ፤

ፊታቸው ፈጽሞ ለኀፍረት አይዳረግም።

ז [ዛየን]

 6 ይህ ችግረኛ ተጣራ፤ ይሖዋም ሰማው።

ከጭንቀቱ ሁሉ ገላገለው።+

ח [ኼት]

 7 የይሖዋ መልአክ አምላክን በሚፈሩ ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፤+

ደግሞም ይታደጋቸዋል።+

ט [ቴት]

 8 ይሖዋ ጥሩ መሆኑን ቅመሱ፤ እዩም፤+

እሱን መጠጊያ የሚያደርግ ሰው ደስተኛ ነው።

י [ዮድ]

 9 ቅዱሳን አገልጋዮቹ ሁሉ፣ ይሖዋን ፍሩ፤

እሱን የሚፈሩ የሚያጡት ነገር የለምና።+

כ [ካፍ]

10 ብርቱ ደቦል አንበሶች እንኳ የሚበሉት አጥተው ይራባሉ፤

ይሖዋን የሚሹ ግን መልካም ነገር አይጎድልባቸውም።+

ל [ላሜድ]

11 ልጆቼ ሆይ፣ ኑ፣ አዳምጡኝ፤

ይሖዋን መፍራት አስተምራችኋለሁ።+

מ [ሜም]

12 ከእናንተ መካከል በሕይወት የሚደሰት፣

ብዙ መልካም ዘመን ማየት የሚወድስ ማን ነው?+

נ [ኑን]

13 እንግዲያው ምላስህን ከክፉ ነገር ጠብቅ፤+

በከንፈሮችህም ከማታለል ተቆጠብ።+

ס [ሳሜኽ]

14 ክፉ ከሆነ ነገር ራቅ፤ መልካም የሆነውንም አድርግ፤+

ሰላምን ፈልግ፤ ተከተለውም።+

ע [አይን]

15 የይሖዋ ዓይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉ፤+

ጆሮዎቹም እርዳታ ለማግኘት የሚያሰሙትን ጩኸት ይሰማሉ።+

פ [ፔ]

16 ሆኖም የክፉዎችን መታሰቢያ ሁሉ ከምድር ለማጥፋት፣

የይሖዋ ፊት በእነሱ ላይ ነው።+

צ [ጻዴ]

17 ጻድቃን ጮኹ፤ ይሖዋም ሰማቸው፤+

ከጭንቀታቸውም ሁሉ ገላገላቸው።+

ק [ኮፍ]

18 ይሖዋ ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፤+

መንፈሳቸው የተደቆሰባቸውንም* ያድናል።+

ר [ረሽ]

19 የጻድቅ ሰው መከራ* ብዙ ነው፤+

ይሖዋ ግን ከመከራው ሁሉ ይታደገዋል።+

ש [ሺን]

20 አጥንቶቹን ሁሉ ይጠብቃል፤

አንዳቸውም ቢሆኑ አልተሰበሩም።+

ת [ታው]

21 ክፉ ሰው በአደጋ ይሞታል፤

ጻድቁን የሚጠሉ ሰዎችም ይፈረድባቸዋል።

22 ይሖዋ የአገልጋዮቹን ሕይወት* ይዋጃል፤

እሱን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ አይፈረድባቸውም።+

የዳዊት መዝሙር።

35 ይሖዋ ሆይ፣ ባላጋራዎቼን በመቃወም ተሟገትልኝ፤+

የሚዋጉኝን ተዋጋቸው።+

 2 ትንሹንና* ትልቁን ጋሻህን ያዝ፤+

ለእኔ ለመከላከልም ተነስ።+

 3 በሚያሳድዱኝ ላይ ጦርና መጥረቢያ* አንሳ።+

“የማድንህ እኔ ነኝ” በለኝ።*+

 4 ሕይወቴን* የሚሹ ይፈሩ፤ ይዋረዱም።+

እኔን ለማጥፋት የሚያሴሩ ተዋርደው ያፈግፍጉ።

 5 በነፋስ ፊት እንዳለ ገለባ ይሁኑ፤

የይሖዋ መልአክም ያባርራቸው።+

 6 የይሖዋ መልአክ ሲያሳድዳቸው

መንገዳቸው በጨለማ የተዋጠና የሚያዳልጥ ይሁን።

 7 ያላንዳች ምክንያት እኔን ለማጥመድ በስውር መረብ ዘርግተዋልና፤

ያላንዳች ምክንያት ጉድጓድ ቆፍረውልኛል።*

 8 ሳያስቡት ጥፋት ይምጣባቸው፤

በስውር ያስቀመጡት መረብም እነሱኑ ይያዛቸው፤

እዚያም ውስጥ ወድቀው ይጥፉ።+

 9 እኔ ግን በይሖዋ ሐሴት አደርጋለሁ፤*

በማዳን ሥራውም እጅግ ደስ ይለኛል።

10 አጥንቶቼ ሁሉ እንዲህ ይላሉ፦

“ይሖዋ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?

ምስኪኑን ብርቱ ከሆኑት፣

ምስኪኑንና ድሃውን ከሚዘርፏቸው ሰዎች ትታደጋለህ።”+

11 ክፉ ምሥክሮች ቀረቡ፤+

ምንም ስለማላውቀው ነገር ጠየቁኝ።

12 ለመልካም ነገር ክፉ መለሱልኝ፤+

ደግሞም ሐዘን ላይ ጣሉኝ።*

13 እኔ ግን እነሱ በታመሙ ጊዜ ማቅ ለበስኩ፤

ራሴን* በጾም አጎሳቆልኩ፤

ጸሎቴም መልስ ሳያገኝ በተመለሰ ጊዜ፣*

14 ለጓደኛዬ ወይም ለወንድሜ እንደማደርገው እየተንቆራጠጥኩ አለቀስኩ፤

እናቱ ሞታበት እንደሚያለቅስ ሰው አንገቴን በሐዘን ደፋሁ።

15 እኔ ስደናቀፍ ግን እነሱ ደስ ብሏቸው ተሰበሰቡ፤

አድብተው እኔን ለመምታት ተሰበሰቡ፤

ዘነጣጠሉኝ፤ በነገር መጎንተላቸውንም አልተዉም።

16 ፈሪሃ አምላክ የሌላቸው ሰዎች በንቀት ያፌዙብኛል፤*

በእኔ ላይ ጥርሳቸውን ያፋጫሉ።+

17 ይሖዋ ሆይ፣ ዝም ብለህ የምታየው እስከ መቼ ነው?+

ከሚሰነዝሩብኝ ጥቃት ታደገኝ፤*+

ውድ ሕይወቴን* ከደቦል አንበሶች አድናት።+

18 ያን ጊዜ በታላቅ ጉባኤ መካከል አመሰግንሃለሁ፤+

በብዙ ሕዝብ መካከል አወድስሃለሁ።

19 ያላንዳች ምክንያት ጠላቶቼ የሆኑ እኔን አይተው እንዲፈነድቁ፣

ያለምክንያት የሚጠሉኝ+ በተንኮል እንዲጠቃቀሱብኝ አትፍቀድ።+

20 የሰላም ቃል ከአፋቸው አይወጣምና፤

ከዚህ ይልቅ በምድሪቱ በሰላም በሚኖሩት ላይ ተንኮል ይሸርባሉ።+

21 እኔን ለመወንጀል አፋቸውን ይከፍታሉ፤

“እሰይ! እሰይ! ዓይናችን ይህን አየ” ይላሉ።

22 ይሖዋ ሆይ፣ ይህን ተመልክተሃል። ዝም አትበል።+

ይሖዋ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ።+

23 ለእኔ ጥብቅና ለመቆም ንቃ፤ ተነሳም፤

ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ ተሟገትልኝ።

24 ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ እንደ ጽድቅህ ፍረድልኝ፤+

በእኔ እንዲፈነድቁ አትፍቀድ።

25 በልባቸው “እሰይ! የተመኘነውን አገኘን”* አይበሉ።

ደግሞም “ዋጥነው” አይበሉ።+

26 እኔ ላይ በደረሰው ጉዳት የሚፈነድቁ ሁሉ

ይፈሩ፣ ይዋረዱም።

በእኔ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ ኀፍረትና ውርደት ይከናነቡ።

27 በእኔ ጽድቅ የሚደሰቱ ግን እልል ይበሉ፤

ሁልጊዜም እንዲህ ይበሉ፦

“በአገልጋዩ ሰላም የሚደሰተው ይሖዋ ከፍ ከፍ ይበል።”+

28 በዚህ ጊዜ ምላሴ ስለ ጽድቅህ ይናገራል፤*+

ቀኑን ሙሉም ያወድስሃል።+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የይሖዋ አገልጋይ የዳዊት መዝሙር።

36 ኃጢአት፣ ክፉውን ሰው በልቡ ውስጥ ሆኖ ያናግረዋል፤

በዓይኖቹ ፊት አምላክን መፍራት የሚባል ነገር የለም።+

 2 ስህተቱ ምን እንደሆነ ተረድቶ የሠራውን ነገር እንዳይጠላው፣

ለራሱ ባለው አመለካከት ራሱን እጅግ ይሸነግላልና።+

 3 ከአፉ የሚወጣው የክፋትና የሽንገላ ቃል ነው፤

መልካም ነገር ለማድረግ ማስተዋል የለውም።

 4 በአልጋው ላይ ሆኖ እንኳ ክፋትን ያውጠነጥናል።

ጥሩ ባልሆነ መንገድ ላይ ይቆማል፤

መጥፎ የሆነውን ነገር ገሸሽ አያደርግም።

 5 ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህ እስከ ሰማያት፣+

ታማኝነትህ እስከ ደመናት ይደርሳል።

 6 ጽድቅህ ግርማ እንደተላበሱ ተራሮች* ነው፤+

ፍርዶችህ እንደ ጥልቅ ባሕር ናቸው።+

ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ሰውንና እንስሳን ትጠብቃለህ።*+

 7 አምላክ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህ ምንኛ ክቡር ነው!+

የሰው ልጆች በክንፎችህ ጥላ ሥር ይሸሸጋሉ።+

 8 በቤትህ ውስጥ ተትረፍርፎ የሚገኘውን ነገር* እስኪረኩ ድረስ ይጠጣሉ፤+

መልካም ነገሮች ከሚፈስሱበት ወንዝህ ታጠጣቸዋለህ።+

 9 የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነው፤+

በብርሃንህ፣ ብርሃን ማየት እንችላለን።+

10 ለሚያውቁህ ታማኝ ፍቅርህን፣

ቀና ልብ ላላቸው ደግሞ ጽድቅህን ዘወትር አሳያቸው።+

11 የትዕቢተኛ እግር እንዲረግጠኝ፣

ወይም የክፉዎች እጅ እንዲያፈናቅለኝ አትፍቀድ።

12 ክፉ አድራጊዎች የት እንደወደቁ ተመልከት፤

ተመተው ወድቀዋል፤ መነሳትም አይችሉም።+

የዳዊት መዝሙር።

א [አሌፍ]

37 በክፉዎች አትበሳጭ፤*

ወይም በክፉ አድራጊዎች አትቅና።+

 2 እንደ ሣር በፍጥነት ይደርቃሉ፤+

እንደለመለመ ተክልም ይጠወልጋሉ።

ב [ቤት]

 3 በይሖዋ ታመን፤ መልካም የሆነውንም አድርግ፤+

በምድር ላይ ኑር፤ ለሰዎችም ታማኝ ሁን።+

 4 በይሖዋ ሐሴት አድርግ፤*

እሱም የልብህን መሻት ይሰጥሃል።

ג [ጊሜል]

 5 መንገድህን ለይሖዋ አደራ ስጥ፤*+

በእሱ ታመን፤ እሱም ለአንተ ሲል እርምጃ ይወስዳል።+

 6 ጽድቅህን እንደ ንጋት ብርሃን፣

የአንተንም ፍትሕ እንደ ቀትር ፀሐይ ያበራዋል።

ד [ዳሌት]

 7 በይሖዋ ፊት ዝም በል፤+

እሱንም በተስፋ* ተጠባበቅ።

የጠነሰሰውን ሴራ

በተሳካ ሁኔታ እየፈጸመ ባለ ሰው አትበሳጭ።+

ה [ሄ]

 8 ከቁጣ ተቆጠብ፤ ንዴትንም ተው፤+

ተበሳጭተህ ክፉ ነገር አትሥራ።*

 9 ክፉ አድራጊዎች ይጠፋሉና፤+

ይሖዋን ተስፋ የሚያደርጉ ግን ምድርን ይወርሳሉ።+

ו [ዋው]

10 ለጥቂት ጊዜ ነው እንጂ ክፉዎች አይኖሩም፤+

በቀድሞ ቦታቸው ትፈልጋቸዋለህ፤

እነሱ ግን በዚያ አይገኙም።+

11 የዋሆች ግን ምድርን ይወርሳሉ፤+

በብዙ ሰላምም እጅግ ደስ ይላቸዋል።+

ז [ዛየን]

12 ክፉ ሰው በጻድቁ ላይ ያሴራል፤+

በእሱ ላይ ጥርሱን ያፋጫል።

13 ይሖዋ ግን ይስቅበታል፤

የሚጠፋበት ቀን እንደሚደርስ ያውቃልና።+

ח [ኼት]

14 ክፉዎች የተጨቆነውንና ድሃውን ለመጣል፣

እንዲሁም ቀና የሆነውን መንገድ የሚከተሉትን ለማረድ

ሰይፋቸውን ይመዛሉ፤ ደጋናቸውንም ይወጥራሉ።

15 ሆኖም ሰይፋቸው የገዛ ልባቸውን ይወጋል፤+

ደጋኖቻቸው ይሰበራሉ።

ט [ቴት]

16 ብዙ ክፉ ሰዎች ካላቸው የተትረፈረፈ ሀብት ይልቅ

ጻድቅ ሰው ያለው ጥቂት ነገር ይሻላል።+

17 የክፉዎች ክንድ ይሰበራልና፤

ይሖዋ ግን ጻድቃንን ይደግፋል።

י [ዮድ]

18 ይሖዋ ነቀፋ የሌለባቸውን ሰዎች የሕይወት ጎዳና* ያውቃል፤

ርስታቸውም ለዘላለም ይኖራል።+

19 በአደጋ ወቅት ለኀፍረት አይዳረጉም፤

በረሃብ ዘመን የተትረፈረፈ ምግብ ይኖራቸዋል።

כ [ካፍ]

20 ክፉዎች ግን ይጠፋሉ፤+

የይሖዋ ጠላቶች እንደ መስክ ውበት ይከስማሉ፤

እንደ ጭስ ይበናሉ።

ל [ላሜድ]

21 ክፉ ሰው ይበደራል፤ መልሶም አይከፍልም፤

ጻድቅ ሰው ግን ለጋስ ነው፤* ደግሞም ይሰጣል።+

22 አምላክ የባረካቸው ምድርን ይወርሳሉ፤

እሱ የረገማቸው ግን ይጠፋሉ።+

מ [ሜም]

23 ይሖዋ በሰው መንገድ ደስ ሲሰኝ፣+

አካሄዱን ይመራለታል።*+

24 ቢወድቅም እንኳ አይዘረርም፤+

ይሖዋ እጁን ይዞ* ይደግፈዋልና።+

נ [ኑን]

25 በአንድ ወቅት ወጣት ነበርኩ፤ አሁን ግን አርጅቻለሁ፤

ይሁንና ጻድቅ ሰው ሲጣል፣+

ልጆቹም ምግብ* ሲለምኑ አላየሁም።+

26 ሁልጊዜ ሳይሰስት ያበድራል፤+

ልጆቹም በረከት ያገኛሉ።

ס [ሳሜኽ]

27 ከክፉ ራቅ፤ መልካሙንም አድርግ፤+

ለዘላለምም ትኖራለህ።

28 ይሖዋ ፍትሕን ይወዳልና፤

ታማኝ አገልጋዮቹንም አይተዋቸውም።+

ע [አይን]

ምንጊዜም ጥበቃ ያገኛሉ፤+

የክፉዎች ዘር ግን ይጠፋል።+

29 ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፤+

በእሷም ላይ ለዘላለም ይኖራሉ።+

פ [ፔ]

30 የጻድቅ አፍ ጥበብን ይናገራል፤*

ምላሱም ስለ ፍትሕ ያወራል።+

31 የአምላኩ ሕግ በልቡ አለ፤+

በሚሄድበት ጊዜም እግሮቹ አይብረከረኩም።+

צ [ጻዴ]

32 ክፉ ሰው ጻድቁን ለመግደል

በዓይነ ቁራኛ ይከታተለዋል።

33 ይሖዋ ግን በክፉው እጅ አይጥለውም፤+

ወይም ለፍርድ በሚቀርብበት ጊዜ ጥፋት አያገኝበትም።+

ק [ኮፍ]

34 ይሖዋን ተስፋ አድርግ፤ መንገዱንም ተከተል፤

እሱም ከፍ ከፍ ያደርግሃል፤ ምድርንም ትወርሳለህ።

ክፉዎች ሲጠፉ+ ታያለህ።+

ר [ረሽ]

35 ጨካኝ የሆነውን ክፉ ሰው፣

በበቀለበት መሬት ላይ እንደለመለመ ዛፍ ተንሰራፍቶ አየሁት።+

36 ይሁንና ሕይወቱ በድንገት አለፈ፤ በቦታውም አልነበረም፤+

አጥብቄ ፈለግኩት፤ ላገኘው ግን አልቻልኩም።+

ש [ሺን]

37 ነቀፋ የሌለበትን* ሰው ልብ በል፤

ቀና የሆነውንም ሰው+ በትኩረት ተመልከት፤

የዚህ ሰው የወደፊት ሕይወት ሰላማዊ ይሆናልና።+

38 ኃጢአተኞች ሁሉ ግን ይጠፋሉ፤

ክፉዎች ምንም ተስፋ አይኖራቸውም።+

ת [ታው]

39 ጻድቃን መዳን የሚያገኙት ከይሖዋ ነው፤+

በጭንቅ ጊዜ መሸሸጊያቸው እሱ ነው።+

40 ይሖዋ ይረዳቸዋል፤ ይታደጋቸዋልም።+

እሱን መጠጊያ ስላደረጉ፣

ከክፉዎች ይታደጋቸዋል፤ ደግሞም ያድናቸዋል።+

የዳዊት ማህሌት፤ ማስታወሻ ሆኖ የሚያገለግል።

38 ይሖዋ ሆይ፣ በቁጣህ አትውቀሰኝ፤

ተናደህም አታርመኝ።+

 2 ፍላጻዎችህ እስከ ውስጥ ድረስ ወግተውኛልና፤

እጅህም ተጭኖኛል።+

 3 ከቁጣህ የተነሳ መላ ሰውነቴ ታመመ።*

ከኃጢአቴም የተነሳ አጥንቶቼ ሰላም የላቸውም።+

 4 የፈጸምኳቸው ስህተቶች በራሴ ላይ ያንዣብባሉና፤+

እንደ ከባድ ሸክም በጣም ከብደውኛል።

 5 ከሞኝነቴ የተነሳ

ቁስሌ ሸተተ፤ ደግሞም አመረቀዘ።

 6 በጭንቀት ተዋጥኩ፤ አንገቴንም ደፋሁ፤

ቀኑን ሙሉ በሐዘን ተውጬ እመላለሳለሁ።

 7 ውስጤ ተቃጠለ፤*

መላ ሰውነቴ ታመመ።+

 8 ደነዘዝኩ፤ ፈጽሞም ደቀቅኩ፤

በጭንቀት ከተዋጠው ልቤ የተነሳ እጅግ እቃትታለሁ።*

 9 ይሖዋ ሆይ፣ ምኞቴ ሁሉ በፊትህ ነው፤

የማሰማው ሲቃም ከአንተ የተሰወረ አይደለም።

10 ልቤ በኃይል ይመታል፤ ጉልበቴ ከድቶኛል፤

የዓይኔም ብርሃን ጠፍቷል።+

11 ከቁስሌ የተነሳ ወዳጆቼና ጓደኞቼ ሸሹኝ፤

በቅርብ የሚያውቁኝ ሰዎችም ከእኔ ራቁ።

12 ሕይወቴን* የሚሹ ሰዎች ወጥመድ ዘረጉብኝ፤

እኔን መጉዳት የሚፈልጉም ስለ ጥፋት ያወራሉ፤+

ቀኑን ሙሉ ተንኮል ሲሸርቡ ይውላሉ።

13 እኔ ግን እንደ ደንቆሮ አልሰማቸውም፤+

እንደ ዱዳም አፌን አልከፍትም።+

14 መስማት እንደማይችል፣

በአፉም የመከላከያ መልስ እንደማይሰጥ ሰው ሆንኩ።

15 ይሖዋ ሆይ፣ አንተን በተስፋ ተጠባብቄአለሁና፤+

ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ አንተም መልስ ሰጥተኸኛል።+

16 “በእኔ ውድቀት አይፈንድቁ፤

ወይም እግሬ ቢንሸራተት በእኔ ላይ አይኩራሩ” ብያለሁና።

17 ልወድቅ ምንም አልቀረኝም ነበርና፤

ሥቃዬም ከእኔ አልተለየም።+

18 በደሌን ተናዘዝኩ፤+

ኃጢአቴም አስጨንቆኝ ነበር።+

19 ይሁንና ጠላቶቼ ብርቱዎችና* ኃያላን ናቸው፤*

ያላንዳች ምክንያት የሚጠሉኝ ተበራከቱ።

20 ላደረግኩት መልካም ነገር ክፉ መለሱልኝ፤

መልካም የሆነውን ነገር በመከተሌ ይቃወሙኝ ነበር።

21 ይሖዋ ሆይ፣ አትተወኝ።

አምላክ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ።+

22 አዳኜ ይሖዋ ሆይ፣

እኔን ለመርዳት ፍጠን።+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በየዱቱን።*+ የዳዊት ማህሌት።

39 እኔ “በምላሴ ኃጢአት እንዳልፈጽም+

አካሄዴን እጠብቃለሁ።

ክፉ ሰው ከእኔ ጋር እስካለ ድረስ

አፌን ለመጠበቅ ልጓም አስገባለሁ”*+ አልኩ።

 2 ዱዳ ሆንኩ፤ ደግሞም ዝም አልኩ፤+

መልካም ነገር ከመናገር እንኳ ታቀብኩ፤

ይሁንና ሥቃዬ ከባድ ነበር።*

 3 ልቤ በውስጤ ነደደ።*

ሳወጣ ሳወርድ* እንደ እሳት ነደድኩ።

በዚህ ጊዜ በአንደበቴ እንዲህ አልኩ፦

 4 “ይሖዋ ሆይ፣ መጨረሻዬ ምን እንደሚሆን፣

የዕድሜዬም ርዝማኔ ምን ያህል እንደሆነ እንዳውቅ እርዳኝ፤+

ይህም ሕይወቴ ምን ያህል አጭር እንደሆነ* አውቅ ዘንድ ነው።

 5 በእርግጥም ቀኖቼን ጥቂት* አደረግካቸው፤+

የሕይወት ዘመኔም በፊትህ ከምንም አይቆጠርም።+

አዎ፣ ሰው ሁሉ ምንም ነገር የማይነካው ቢመስልም እንኳ እንደ እስትንፋስ ነው።+ (ሴላ)

 6 በእርግጥም ሰው ሁሉ የሚመላለሰው እንደ ጥላ ነው።

ላይ ታች የሚለው* በከንቱ ነው።

ማን እንደሚጠቀምበት ሳያውቅ ንብረት ያከማቻል።+

 7 ይሖዋ ሆይ፣ ታዲያ ተስፋዬ ምንድን ነው?

ተስፋዬ አንተ ብቻ ነህ።

 8 ከፈጸምኩት በደል ሁሉ አድነኝ።+

ሞኝ ሰው እንዲሳለቅብኝ አትፍቀድ።

 9 ዱዳ ሆንኩ፤

ይህን ያደረግከው አንተ ስለሆንክ+

አፌን መክፈት አልቻልኩም።+

10 በእኔ ላይ ያመጣኸውን መቅሰፍት ከእኔ አርቅ።

እጅህ ስለመታኝ ዛልኩ።

11 ሰውን በሠራው ስህተት የተነሳ በመቅጣት ታርመዋለህ፤+

እንደ ውድ ሀብት የሚመለከታቸውን ነገሮች እንደ ብል ትበላበታለህ።

በእርግጥም ሰው ሁሉ እንደ እስትንፋስ ነው።+ (ሴላ)

12 ይሖዋ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤

ለእርዳታ የማሰማውን ጩኸት አዳምጥ።+

እንባዬን ችላ አትበል።

እኔ በአንተ ዘንድ የባዕድ አገር ሰው ነኝና፤+

እንደ አባቶቼ አልፌ የምሄድ ተጓዥ* ነኝ።+

13 ከመሞቴና ከሕልውና ውጭ ከመሆኔ በፊት፣

ፊቴ እንዲፈካ በክፉ ዓይን አትየኝ።”

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት መዝሙር። ማህሌት።

40 ተስፋዬን ሙሉ በሙሉ በይሖዋ ላይ ጣልኩ፤*

እሱም ጆሮውን ወደ እኔ አዘነበለ፤* ለእርዳታ ያሰማሁትንም ጩኸት ሰማ።+

 2 የሚያስገመግም ድምፅ ካለበት ጉድጓድ፣

ከሚያዘቅጥ ማጥም አወጣኝ።

እግሮቼንም በዓለት ላይ አቆመ፤

አረማመዴንም አጸና።

 3 ከዚያም በአፌ ላይ አዲስ መዝሙር፣+

ለአምላካችን የሚቀርብ ውዳሴ አኖረ።

ብዙዎች በፍርሃት* ተውጠው ይመለከታሉ፤

በይሖዋም ይታመናሉ።

 4 በይሖዋ የሚታመን፣ እንቢተኛ ወደሆኑት ወይም

ሐሰት* ወደሆኑት ፊቱን ያላዞረ ሰው ደስተኛ ነው።

 5 ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣

ያደረግካቸው ድንቅ ሥራዎች፣

ለእኛ ያሰብካቸው ነገሮችም ብዙ ናቸው።+

ከአንተ ጋር ሊወዳደር የሚችል ማንም የለም፤+

ስለ እነዚህ ነገሮች ላውራ፣ ልናገር ብል፣

ዘርዝሬ ልጨርሳቸው አልችልም!+

 6 መሥዋዕትንና መባን አልፈለግክም፤*+

ከዚህ ይልቅ እንድሰማ ጆሮዎቼን ከፈትክልኝ።*+

የሚቃጠል መባና የኃጢአት መባ እንዲቀርብልህ አልጠየቅክም።+

 7 በዚህ ጊዜ እንዲህ አልኩ፦ “እነሆ፣ መጥቻለሁ።

ስለ እኔ በመጽሐፍ ጥቅልል ተጽፏል።+

 8 አምላኬ ሆይ፣ ፈቃድህን ማድረግ ያስደስተኛል፤*+

ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው።+

 9 በታላቅ ጉባኤ መካከል የጽድቅን ምሥራች አውጃለሁ።+

ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ራስህ በሚገባ እንደምታውቀው፣

እነሆ፣ ከንፈሮቼን አልከለክልም።+

10 ጽድቅህን በልቤ ውስጥ አልሸሽግም።

ታማኝነትህንና ማዳንህን አውጃለሁ።

በታላቅ ጉባኤ መካከል ታማኝ ፍቅርህንና እውነትህን አልደብቅም።”+

11 ይሖዋ ሆይ፣ ምሕረትህን አትንፈገኝ።

ታማኝ ፍቅርህና እውነትህ ምንጊዜም ይጠብቁኝ።+

12 ለመቁጠር እንኳ የሚያታክት መከራ ከቦኛል።+

የፈጸምኳቸው በርካታ ስህተቶች ስለዋጡኝ መንገዴን ማየት ተስኖኛል፤+

በራሴ ላይ ካሉት ፀጉሮች እጅግ ይበዛሉ፤

ደግሞም ተስፋ ቆረጥኩ።

13 ይሖዋ ሆይ፣ እኔን ለማዳን እባክህ ፈቃደኛ ሁን።+

ይሖዋ ሆይ፣ እኔን ለመርዳት ፍጠን።+

14 ሕይወቴን* ለማጥፋት የሚሹ ሁሉ፣

ኀፍረትና ውርደት ይከናነቡ።

በእኔ ላይ በደረሰው ጉዳት ደስ የሚሰኙ

አፍረው ወደ ኋላ ይመለሱ።

15 “እሰይ! እሰይ!” የሚሉኝ

በሚደርስባቸው ኀፍረት የተነሳ ክው ይበሉ።

16 አንተን የሚፈልጉ+ ግን

በአንተ ይደሰቱ፤ ሐሴትም ያድርጉ።+

የማዳን ሥራህን የሚወዱ፣

ምንጊዜም “ይሖዋ ታላቅ ይሁን” ይበሉ።+

17 እኔ ግን ምስኪንና ድሃ ነኝ፤

ይሖዋ ትኩረት ይስጠኝ።

አንተ ረዳቴና ታዳጊዬ ነህ፤+

አምላኬ ሆይ፣ አትዘግይ።+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት ማህሌት።

41 ለተቸገረ ሰው የሚያስብ ደስተኛ ነው፤+

በመከራ ቀን ይሖዋ ይታደገዋል።

 2 ይሖዋ ይጠብቀዋል፤ በሕይወትም ያኖረዋል።

በምድር ላይ ደስተኛ ይባላል፤+

ለጠላቶቹ ምኞት* አሳልፈህ አትሰጠውም።+

 3 ታሞ በአልጋ ላይ ተኝቶ ሳለ ይሖዋ ይደግፈዋል፤+

በታመመበት ወቅት መኝታውን ሙሉ በሙሉ ትቀይርለታለህ።

 4 እኔም “ይሖዋ ሆይ፣ ሞገስ አሳየኝ።+

በአንተ ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁና+ ፈውሰኝ”*+ አልኩ።

 5 ጠላቶቼ ግን “የሚሞተውና ስሙ ከናካቴው የሚረሳው መቼ ነው?” እያሉ

ስለ እኔ ክፉ ወሬ ያወራሉ።

 6 ከእነሱ አንዱ እኔን ለማየት ቢመጣ ልቡ ውሸት ይናገራል።

እኔን የሚጎዳ ወሬ ይቃርማል፤

ከዚያም ወደ ውጭ ወጥቶ በየቦታው ያወራዋል።

 7 የሚጠሉኝ ሁሉ እርስ በርስ ይንሾካሾካሉ፤

በእኔ ላይ ክፉ ነገር ይሸርባሉ፤

 8 “ክፉ ነገር ደርሶበታል፤

ከእንግዲህ ከወደቀበት አይነሳም” ይላሉ።+

 9 ሌላው ቀርቶ ከእኔ ጋር ሰላም የነበረው፣ እምነት የጣልኩበትና+

ከማዕዴ ይበላ የነበረ ሰው ተረከዙን በእኔ ላይ አነሳ።*+

10 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን ብድራታቸውን እከፍል ዘንድ

ሞገስ አሳየኝ፤ ደግሞም አንሳኝ።

11 ጠላቴ በእኔ ላይ በድል አድራጊነት እልል ሳይል ሲቀር፣

አንተ በእኔ ደስ እንደተሰኘህ በዚህ አውቃለሁ።+

12 እኔ በበኩሌ ንጹሕ አቋሜን* በመጠበቄ ትደግፈኛለህ፤+

በፊትህም ለዘላለም ታኖረኛለህ።+

13 የእስራኤል አምላክ ይሖዋ

ከዘላለም እስከ ዘላለም ይወደስ።+

አሜን፣ አሜን።

ሁለተኛ መጽሐፍ

(መዝሙር 42-72)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የቆሬ ልጆች ማስኪል።*+

42 ርኤም* ጅረቶችን እንደምትናፍቅ፣

አምላክ ሆይ፣ አንተን እናፍቃለሁ።*

 2 አምላክን፣ ሕያው አምላክን ተጠማሁ።*+

ወደ አምላክ የምሄደውና በፊቱ የምቀርበው መቼ ይሆን?+

 3 እንባዬ ቀን ከሌት ምግብ ሆነኝ፤

ሰዎች ቀኑን ሙሉ “አምላክህ የት አለ?” እያሉ ይሳለቁብኛል።+

 4 እነዚህን ነገሮች አስታውሳለሁ፤ ነፍሴንም* አፈሳለሁ፤

በአንድ ወቅት ከብዙ ሰዎች ጋር እጓዝ ነበር፤

በእልልታና በምስጋና ድምፅ፣

በዓል በሚያከብር ሕዝብ ድምፅ፣

ከፊታቸው ሆኜ ወደ አምላክ ቤት በኩራት* እሄድ ነበር።+

 5 ተስፋ የምቆርጠው* ለምንድን ነው?+

ውስጤ የሚረበሸው ለምንድን ነው?

አምላክን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ፤+

እሱን እንደ ታላቅ አዳኜ አድርጌ ገና አወድሰዋለሁና።+

 6 አምላኬ ሆይ፣ ተስፋ ቆርጫለሁ።*+

ከዮርዳኖስ ምድርና ከሄርሞን አናት፣

ከሚዛር ተራራ*

የማስብህ ለዚህ ነው።+

 7 በፏፏቴህ ድምፅ አማካኝነት

ጥልቁ ውኃ፣ ጥልቁን ውኃ ይጣራል።

ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ ዋጠኝ።+

 8 ይሖዋ በቀን ታማኝ ፍቅሩን ያሳየኛል፤

እኔ ደግሞ በሌሊት ስለ እሱ እዘምራለሁ፤ ሕይወት ለሰጠኝ አምላክ ጸሎት አቀርባለሁ።+

 9 ዓለቴ የሆነውን አምላክ እንዲህ እለዋለሁ፦

“ለምን ረሳኸኝ?+

ጠላት ከሚያደርስብኝ ግፍ የተነሳ በሐዘን ተውጬ ለምን እሄዳለሁ?”+

10 ለእኔ ካላቸው ጥላቻ የተነሳ ሊገድሉኝ የሚሹ* ጠላቶቼ ይሳለቁብኛል፤

ቀኑን ሙሉ “አምላክህ የት አለ?” እያሉ ይሳለቁብኛል።+

11 ተስፋ የምቆርጠው* ለምንድን ነው?

ውስጤ የሚረበሸው ለምንድን ነው?

አምላክን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ፤+

እሱን እንደ ታላቅ አዳኜና አምላኬ አድርጌ ገና አወድሰዋለሁና።+

43 አምላክ ሆይ፣ ፍረድልኝ፤+

ከከዳተኛ ብሔር ጋር ያለብኝን ሙግት አንተ ተሟገትልኝ።+

አታላይና ዓመፀኛ ከሆነ ሰው ታደገኝ።

 2 አንተ አምላኬና ምሽጌ ነህና።+

ለምን ተውከኝ?

ጠላቴ ከሚያደርስብኝ ጭቆና የተነሳ ለምን አዝኜ ልመላለስ?+

 3 ብርሃንህንና እውነትህን ላክ።+

እነሱ ይምሩኝ፤+

ወደተቀደሰው ተራራህና ወደ ታላቁ የማደሪያ ድንኳንህ ይውሰዱኝ።+

 4 ከዚያም ወደ አምላክ መሠዊያ፣+

እጅግ ሐሴት ወደማደርግበት አምላክ እመጣለሁ።

ደግሞም አምላክ ሆይ፣ አምላኬ፣ በበገና አወድስሃለሁ።+

 5 ተስፋ የምቆርጠው* ለምንድን ነው?

ውስጤ የሚረበሸው ለምንድን ነው?

አምላክን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ፤+

እሱን እንደ ታላቅ አዳኜና አምላኬ አድርጌ ገና አወድሰዋለሁና።+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የቆሬ ልጆች መዝሙር።+ ማስኪል።*

44 አምላክ ሆይ፣ በገዛ ጆሯችን ሰምተናል፤

ከረጅም ጊዜ በፊት፣

በእነሱ ዘመን ያከናወንካቸውን ተግባሮች፣

አባቶቻችን ተርከውልናል።+

 2 በእጅህ ብሔራትን አባረርክ፤+

በዚያም አባቶቻችንን አሰፈርክ።+

ብሔራትን ድል አድርገህ አባረርካቸው።+

 3 ምድሪቱን የወረሱት በገዛ ሰይፋቸው አይደለም፤+

ድል ያጎናጸፋቸውም የገዛ ክንዳቸው አይደለም።+

ከዚህ ይልቅ በእነሱ ደስ ስለተሰኘህ+

ቀኝ እጅህ፣ ክንድህና የፊትህ ብርሃን ይህን አድርጓል።+

 4 አምላክ ሆይ፣ አንተ ንጉሤ ነህ፤+

ለያዕቆብ ፍጹም ድል* እዘዝ።*

 5 በአንተ ኃይል ጠላቶቻችንን እንመክታለን፤+

በእኛ ላይ የተነሱትን በስምህ እንረግጣለን።+

 6 በቀስቴ አልታመንምና፤

ሰይፌም ሊያድነኝ አይችልም።+

 7 ከጠላቶቻችን ያዳንከን፣

የሚጠሉንን ሰዎች ያዋረድካቸው አንተ ነህ።+

 8 ቀኑን ሙሉ ለአምላክ ውዳሴ እናቀርባለን፤

ስምህንም ለዘላለም እናመሰግናለን። (ሴላ)

 9 አሁን ግን ትተኸናል፤ ደግሞም አዋርደኸናል፤

ከሠራዊታችንም ጋር አብረህ አትወጣም።

10 ከጠላታችን ፊት እንድንሸሽ ታደርገናለህ፤+

የሚጠሉን ሰዎች የፈለጉትን ሁሉ ይወስዱብናል።

11 እንደ በግ እንዲበሉን ለጠላቶቻችን አሳልፈህ ሰጠኸን፤

በብሔራት መካከል በተንከን።+

12 ሕዝብህን በማይረባ ዋጋ ሸጥክ፤+

ከሽያጩ ያገኘኸው ትርፍ የለም።

13 በጎረቤቶቻችን ዘንድ መሳለቂያ አደረግከን፤

በዙሪያችን ያሉት ሁሉ እንዲያላግጡብንና እንዲዘብቱብን አደረግክ።

14 በብሔራት መካከል መቀለጃ እንድንሆን፣*

ሕዝቦችም ራሳቸውን እንዲነቀንቁብን አደረግክ።+

15 ቀኑን ሙሉ በኀፍረት ተውጫለሁ፤

ውርደትም ተከናንቤአለሁ፤

16 ይህም ከሚሳለቁና ከሚሳደቡ ሰዎች ድምፅ፣

እንዲሁም ከሚበቀለን ጠላታችን የተነሳ ነው።

17 ይህ ሁሉ በእኛ ላይ ደርሷል፤ እኛ ግን አልረሳንህም፤

ቃል ኪዳንህንም አላፈረስንም።+

18 ልባችን አልሸፈተም፤

እግራችንም ከመንገድህ አልወጣም።

19 ይሁንና ቀበሮዎች በሚኖሩበት ቦታ ሰባብረኸናል፤

በድቅድቅ ጨለማም ሸፍነኸናል።

20 የአምላካችንን ስም ረስተን፣

ወይም ወደ ባዕድ አምላክ ለመጸለይ እጃችንን ዘርግተን ከሆነ፣

21 አምላክ ይህን አይደርስበትም?

እሱ በልብ ውስጥ ያለውን ሚስጥር ያውቃል።+

22 ስለ አንተ ቀኑን ሙሉ ሞትን እንጋፈጣለን፤

እንደ እርድ በጎችም ተቆጠርን።+

23 ይሖዋ ሆይ፣ ተነስ። ለምንስ ትተኛለህ?+

ንቃ! ለዘላለም አትጣለን።+

24 ፊትህን ለምን ትሰውራለህ?

የደረሰብንን ጉስቁልናና ጭቆና የምትረሳው ለምንድን ነው?

25 ወደ አፈር ተጥለናልና፤*

ሰውነታችን ከመሬት ጋር ተጣብቋል።+

26 እኛን ለመርዳት ተነስ!+

ስለ ታማኝ ፍቅርህ ስትል ታደገን።*+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ “በአበቦች” የሚዘመር። የቆሬ ልጆች።+ ማስኪል።* የፍቅር መዝሙር።

45 መልካም የሆነ ነገር ልቤን አነሳስቶታል።

“መዝሙሬ* ስለ አንድ ንጉሥ ነው”+ እላለሁ።

አንደበቴ የተዋጣለት ገልባጭ *+ እንደሚጠቀምበት ብዕር+ ይሁን።

 2 አንተ ከሰው ልጆች ሁሉ ይልቅ ውብ ነህ።

ከከንፈሮችህ ጸጋ የተላበሱ ቃላት ይፈስሳሉ።+

አምላክ ለዘላለም የባረከህ ለዚህ ነው።+

 3 ኃያል ሆይ፣+ ሰይፍህን+ በጎንህ ታጠቅ፤

ክብርህንና ግርማህንም+ ተጎናጸፍ።

 4 በግርማህም ድል ለመቀዳጀት* ገስግስ፤+

ፈረስህን እየጋለብክ ለእውነት፣ ለትሕትናና ለጽድቅ ተዋጋ፤+

ቀኝ እጅህም የሚያስፈሩ ተግባሮችን ያከናውናል።*

 5 ፍላጻዎችህ የሾሉ ናቸው፤ ሰዎችን በፊትህ ይረፈርፋሉ፤+

የንጉሡን ጠላቶች ልብ ይወጋሉ።+

 6 አምላክ ለዘላለም ዙፋንህ ነው፤+

የመንግሥትህ በትር የቅንነት* በትረ መንግሥት ነው።+

 7 ጽድቅን ወደድክ፤+ ክፋትን ጠላህ።+

ስለዚህ አምላክ ይኸውም አምላክህ ከባልንጀሮችህ ይበልጥ በደስታ ዘይት+ ቀባህ።+

 8 ልብሶችህ ሁሉ የከርቤ፣ የእሬትና* የብርጉድ መዓዛ አላቸው፤

በዝሆን ጥርስ ካጌጠው ታላቅ ቤተ መንግሥት የሚወጣው የባለ አውታር መሣሪያዎች* ድምፅ ያስደስትሃል።

 9 ከተከበሩት እመቤቶችህ መካከል የነገሥታት ልጆች ይገኛሉ።

እቴጌይቱ* በኦፊር ወርቅ+ አጊጣ በቀኝህ ቆማለች።

10 ልጄ ሆይ፣ አዳምጪ፣ ልብ በዪ፣ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤

ሕዝብሽንና የአባትሽን ቤት እርሺ።

11 ንጉሡም በውበትሽ ተማርኳል፤

እሱ ጌታሽ ነውና፣

እጅ ንሺው።

12 የጢሮስ ሴት ልጅ ስጦታ ይዛ ትመጣለች፤

እጅግ ባለጸጋ የሆኑትም በአንቺ ዘንድ ሞገስ ለማግኘት ጥረት ያደርጋሉ።

13 የንጉሡ ሴት ልጅ እጅግ ተውባ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ተቀምጣለች፤*

ልብሷ በወርቅ ያጌጠ* ነው።

14 ያጌጠ ልብሷን* ለብሳ ወደ ንጉሡ ትወሰዳለች።

ወዳጆቿ የሆኑ ደናግል አጃቢዎቿን ወደ ፊትህ ያቀርቧቸዋል።

15 በደስታና በሐሴት ይመሯቸዋል፤

ወደ ንጉሡ ቤተ መንግሥት ይገባሉ።

16 በአባቶችህ ፋንታ ወንዶች ልጆችህ ይተካሉ።

በምድር ሁሉ ላይ መኳንንት አድርገህ ትሾማቸዋለህ።+

17 ለሚመጡት ትውልዶች ሁሉ ስምህን አሳውቃለሁ።+

በመሆኑም ሕዝቦች ለዘላለም ያወድሱሃል።

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የቆሬ ልጆች መዝሙር።+ በአላሞት ቅኝት።*

46 አምላክ መጠጊያችንና ብርታታችን፣+

በጭንቅ ጊዜ ፈጥኖ የሚደርስልን ረዳታችን ነው።+

 2 በመሆኑም በምድር ላይ ነውጥ ቢከሰት፣

ተራሮች ተንደው ወደ ጥልቁ ባሕር ቢሰምጡ አንፈራም፤+

 3 ውኃዎቹ ቢያስገመግሙና አረፋ ቢደፍቁ፣+

ተራሮችም ከውኃዎቹ ነውጥ የተነሳ ቢንቀጠቀጡ አንሸበርም። (ሴላ)

 4 የአምላክን ከተማ+ ደስ የሚያሰኙ ጅረቶች ያሉት ወንዝ አለ፤

ከተማዋም የልዑሉ አምላክ የተቀደሰ ታላቅ ማደሪያ ነች።

 5 አምላክ በከተማዋ ውስጥ ነው፤+ እሷም አትንኮታኮትም።

ጎህ ሲቀድ አምላክ ይደርስላታል።+

 6 ብሔራት ሁከት ፈጠሩ፤ መንግሥታት ተገለበጡ፤

እሱ ድምፁን ከፍ አድርጎ አሰማ፤ ምድርም ቀለጠች።+

 7 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ከእኛ ጋር ነው፤+

የያዕቆብ አምላክ አስተማማኝ መጠጊያችን ነው። (ሴላ)

 8 ኑና የይሖዋን ሥራዎች እዩ፤

በምድርም ላይ አስደናቂ ነገሮችን እንዴት እንዳከናወነ ተመልከቱ።

 9 ጦርነትን ከመላው ምድር ላይ ያስወግዳል።+

ቀስትን ይሰባብራል፤ ጦርንም ያነክታል፤

የጦር ሠረገሎችን* በእሳት ያቃጥላል።

10 “አርፋችሁ ተቀመጡ፤ እኔ አምላክ እንደሆንኩም እወቁ።

በብሔራት መካከል ከፍ ከፍ እላለሁ፤+

በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።”+

11 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ከእኛ ጋር ነው፤+

የያዕቆብ አምላክ አስተማማኝ መጠጊያችን ነው።+ (ሴላ)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የቆሬ ልጆች+ ማህሌት።

47 እናንተ ሕዝቦች ሁሉ፣ እጆቻችሁን አጨብጭቡ።

በድል አድራጊነት ለአምላክ እልል በሉ።

 2 ልዑሉ ይሖዋ እጅግ የሚያስፈራ ነውና፤+

በመላው ምድር ላይ ታላቅ ንጉሥ ነው።+

 3 ሕዝቦችን ለእኛ ያስገዛል፤

ብሔራትም ከእግራችን በታች እንዲሆኑ ያደርጋል።+

 4 የሚወደውን የያዕቆብን+ መመኪያ

ርስታችን አድርጎ ይመርጥልናል።+ (ሴላ)

 5 አምላክ በእልልታ አረገ፤

ይሖዋ በቀንደ መለከት* ድምፅ ወደ ላይ ወጣ።

 6 ለአምላክ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ።

ለንጉሣችን የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ።

 7 አምላክ የምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፤+

የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤ ማስተዋልም ይኑራችሁ።

 8 አምላክ በብሔራት ላይ ነግሦአል።+

በቅዱስ ዙፋኑ ላይ ተቀምጧል።

 9 የሕዝቡ መሪዎች ከአብርሃም አምላክ ሕዝብ ጋር

አንድ ላይ ተሰብስበዋል።

የምድር ገዢዎች* የአምላክ ናቸውና።

እሱ እጅግ ከፍ ከፍ ብሏል።+

መዝሙር። የቆሬ ልጆች+ ማህሌት።

48 ይሖዋ ታላቅ ነው፤

በአምላካችን ከተማ፣ በቅዱስ ተራራው እጅግ ሊወደስ ይገባዋል።

 2 በከፍታ ቦታ ላይ ተውባ የምትታየው፣ የምድር ሁሉ ደስታ፣+

በስተ ሰሜን ርቃ የምትገኘው የጽዮን ተራራ ነች፤

ደግሞም የታላቁ ንጉሥ ከተማ ነች።+

 3 አምላክ በማይደፈሩ ማማዎቿ ውስጥ

አስተማማኝ መጠጊያ መሆኑን አስመሥክሯል።+

 4 እነሆ፣ ነገሥታት ተሰብስበዋልና፤*

አንድ ላይ ሆነው ገሰገሱ።

 5 ከተማዋን ባዩአት ጊዜ ተገረሙ።

ደንግጠውም ፈረጠጡ።

 6 በዚያም በፍርሃት ተንቀጠቀጡ፤

እንደምትወልድ ሴት ጭንቅ ያዛቸው።

 7 የተርሴስን መርከቦች በምሥራቅ ነፋስ ሰባበርክ።

 8 የሰማነውን ነገር፣ በሠራዊት ጌታ በይሖዋ ከተማ

ይኸውም በአምላካችን ከተማ አሁን በገዛ ዓይናችን አይተናል።

አምላክ ለዘላለም ያጸናታል።+ (ሴላ)

 9 አምላክ ሆይ፣ በቤተ መቅደስህ ውስጥ ሆነን

ስለ ታማኝ ፍቅርህ እናሰላስላለን።+

10 አምላክ ሆይ፣ እንደ ስምህ ሁሉ ውዳሴህም

እስከ ምድር ዳርቻ ይደርሳል።+

ቀኝ እጅህ በጽድቅ ተሞልቷል።+

11 ከፍርድህ የተነሳ የጽዮን ተራራ+ ደስ ይበላት፤

የይሁዳ ከተሞችም* ሐሴት ያድርጉ።+

12 በጽዮን ዙሪያ ሂዱ፤ በዙሪያዋም ተጓዙ፤

ማማዎቿን ቁጠሩ።+

13 የመከላከያ ግንቦቿን*+ ልብ ብላችሁ ተመልከቱ።

ለመጪዎቹ ትውልዶች መናገር ትችሉ ዘንድ፣

የማይደፈሩ ማማዎቿን በሚገባ አጢኑ።

14 ይህ አምላክ፣ ለዘላለም አምላካችን ነውና።+

እስከ ወዲያኛው* ይመራናል።+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የቆሬ ልጆች+ ማህሌት።

49 እናንተ ሕዝቦች ሁሉ፣ ይህን ስሙ።

በዓለም ላይ* የምትኖሩ ሁሉ፣ ልብ በሉ፤

 2 ታናናሾችም ሆናችሁ ታላላቆች፣*

ባለጸጎችና ድሆች፣ ሁላችሁም ስሙ።

 3 አፌ ጥበብን ይናገራል፤

በልቤም የማሰላስለው ነገር+ ማስተዋልን ይገልጣል።

 4 ጆሮዬን ወደ ምሳሌ አዘነብላለሁ፤

እንቆቅልሼንም በበገና እፈታለሁ።

 5 በአስቸጋሪ ወቅት፣

እኔን ለመጣል የሚፈልጉ ሰዎች ክፋት* በከበበኝ ጊዜ ለምን እፈራለሁ?+

 6 በሀብታቸው የሚመኩትን፣+

በታላቅ ብልጽግናቸው የሚኩራሩትንም+ ለምን እፈራለሁ?

 7 አንዳቸውም ቢሆኑ ሌላውን ሰው መዋጀት፣

ወይም ለእሱ ቤዛ የሚሆን ነገር ለአምላክ መክፈል ጨርሶ አይችሉም፤+

 8 (ለሕይወታቸው* የሚከፈለው የቤዛ* ዋጋ እጅግ ውድ ስለሆነ

መቼም ቢሆን ከአቅማቸው በላይ ነው)፤

 9 ለዘላለም እንዲኖርና ወደ ጉድጓድ* እንዳይወርድ ቤዛ ሊከፍሉ አይችሉም።+

10 ጥበበኞች እንኳ ሲሞቱ ያያል፤

ሞኞችና ማመዛዘን የሚጎድላቸው ሰዎች አብረው ይጠፋሉ፤+

ሀብታቸውንም ለሌሎች ትተውት ያልፋሉ።+

11 ምኞታቸው ቤቶቻቸው ለዘላለም እንዲኖሩ፣

ድንኳናቸውም ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ነው።

ርስታቸውን በራሳቸው ስም ሰይመዋል።

12 ይሁንና የሰው ልጅ የተከበረ ቢሆንም እንኳ በሕይወት አይዘልቅም፤+

ከሚጠፉ እንስሳት ምንም አይሻልም።+

13 የሞኞች መንገድ ይህ ነው፤+

እነሱ በሚናገሩት ከንቱ ቃል ተደስተው የሚከተሏቸው ሰዎች መንገድም ይኸው ነው። (ሴላ)

14 ለእርድ እንደሚነዱ በጎች ወደ መቃብር* እንዲወርዱ ተፈርዶባቸዋል።

ሞት እረኛቸው ይሆናል፤

በማለዳ ቅኖች ይገዟቸዋል።+

ደብዛቸው ይጠፋል፤+

በቤተ መንግሥት ፋንታ መቃብር* መኖሪያቸው ይሆናል።+

15 ሆኖም አምላክ ከመቃብር* እጅ ይዋጀኛል፤*+

እሱ ይይዘኛልና። (ሴላ)

16 ሰው ሀብታም ሲሆንና

የቤቱ ክብር ሲጨምር አትፍራው፤

17 በሚሞትበት ጊዜ ከእሱ ጋር አንዳች ነገር ሊወስድ አይችልምና፤+

ክብሩም አብሮት አይወርድም።+

18 በሕይወት ዘመኑ ራሱን* ሲያወድስ ይኖራልና።+

(ስትበለጽግ ሰዎች ያወድሱሃል።)+

19 መጨረሻ ላይ ግን ከአባቶቹ ትውልድ ጋር ይቀላቀላል።

ከዚያ በኋላ ፈጽሞ ብርሃን አያዩም።

20 የተከበረ ቢሆንም እንኳ ይህን የማይረዳ ሰው

ከሚጠፉ እንስሳት ምንም አይሻልም።+

የአሳፍ+ ማህሌት።

50 የአማልክት አምላክ የሆነው ይሖዋ+ ተናግሯል፤

ከፀሐይ መውጫ አንስቶ እስከ መግቢያው* ድረስ

ምድርን ይጠራል።

 2 በውበቷ ፍጹም ከሆነችው ከጽዮን፣+ አምላክ ያበራል።

 3 አምላካችን ይመጣል፤ ፈጽሞም ዝም ሊል አይችልም።+

በፊቱ የሚባላ እሳት አለ፤+

በዙሪያውም ሁሉ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ ይነፍሳል።+

 4 በሕዝቡ ላይ ለመፍረድ፣+

በላይ ያሉትን ሰማያትና ምድርን ይጠራል፤+

 5 “በመሥዋዕት አማካኝነት ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን የሚያደርጉትን፣+

ታማኝ አገልጋዮቼን ወደ እኔ ሰብስቡ” ይላል።

 6 ሰማያት ጽድቁን ያውጃሉ፤

አምላክ ራሱ ፈራጅ ነውና።+ (ሴላ)

 7 “ሕዝቤ ሆይ፣ ስማ፤ እኔም እናገራለሁ፤

እስራኤል ሆይ፣ በአንተ ላይ እመሠክርብሃለሁ።+

እኔ አምላክ፣ አዎ አምላክህ ነኝ።+

 8 በመሥዋዕቶችህም ሆነ

ዘወትር በፊቴ ባሉት የሚቃጠሉ መባዎችህ የተነሳ አልወቅስህም።+

 9 ከቤትህ ኮርማ፣

ከጉረኖህም ፍየሎች* መውሰድ አያስፈልገኝም።+

10 በጫካ ውስጥ ያሉ የዱር እንስሳት ሁሉ፣

በሺህ ተራሮች ላይ ያሉ አራዊትም እንኳ የእኔ ናቸውና።+

11 በተራሮች ላይ የሚኖሩትን ወፎች ሁሉ አውቃለሁ፤+

በመስክ ያሉ ስፍር ቁጥር የሌላቸው እንስሳት የእኔ ናቸው።

12 ብራብ እንኳ ለአንተ አልነግርህም፤

ፍሬያማ የሆነችው ምድርና በውስጧ ያለው ሁሉ የእኔ ነውና።+

13 የኮርማዎችን ሥጋ እበላለሁ?

የፍየሎችንስ ደም እጠጣለሁ?+

14 ምስጋናን ለአምላክ መሥዋዕት አድርገህ አቅርብ፤+

ስእለትህንም ለልዑሉ አምላክ ስጥ፤+

15 በጭንቅ ቀን ጥራኝ።+

እኔ እታደግሃለሁ፤ አንተም ታወድሰኛለህ።”+

16 ክፉውን ግን አምላክ እንዲህ ይለዋል፦

“ስለ ሥርዓቴ ለማውራት፣

ወይም ደግሞ ስለ ቃል ኪዳኔ ለመናገር ምን መብት አለህ?+

17 ተግሣጼን* ትጠላለህና፤

ለቃሌም ጀርባህን ትሰጣለህ።*+

18 ሌባ ስታይ ትደግፈዋለህ፤*+

ከአመንዝሮችም ጋር ትወዳጃለህ።

19 አንደበትህን ክፉ ወሬ ለመንዛት ትጠቀምበታለህ፤

ማታለያም ከምላስህ አይጠፋም።+

20 ከሌሎች ጋር ተቀምጠህ ወንድምህን ታማለህ፤+

የገዛ እናትህን ልጅ ድክመት ታወራለህ።*

21 እነዚህን ሁሉ ነገሮች ስታደርግ፣ ዝም አልኩ፤

በመሆኑም እንደ አንተ የምሆን መስሎህ ነበር።

አሁን ግን እወቅስሃለሁ፤

ከአንተ ጋር ያለኝንም ሙግት አሳውቃለሁ።+

22 እናንተ አምላክን የምትረሱ፣ እባካችሁ ይህን ልብ በሉ፤+

አለዚያ ብትንትናችሁን አወጣለሁ፤ የሚታደጋችሁም አይኖርም።

23 ምስጋናን መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርብልኝ ያከብረኛል፤+

ደግሞም ትክክለኛውን መንገድ በጥብቅ የሚከተልን ሰው፣

የአምላክን ማዳን እንዲያይ አደርገዋለሁ።”+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። ከቤርሳቤህ ጋር ግንኙነት ከፈጸመ በኋላ ነቢዩ ናታን መጥቶ ባነጋገረው ጊዜ ዳዊት ያቀረበው ማህሌት።+

51 አምላክ ሆይ፣ እንደ ታማኝ ፍቅርህ መጠን ሞገስ አሳየኝ።+

እንደ ታላቅ ምሕረትህ መተላለፌን ደምስስ።+

 2 ከበደሌ ሙሉ በሙሉ እጠበኝ፤+

ከኃጢአቴም አንጻኝ።+

 3 መተላለፌን በሚገባ አውቃለሁና፤

ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነው።*+

 4 አንተን፣ አዎ ከማንም በላይ አንተን* በደልኩ፤+

በአንተ ዓይን ክፉ የሆነውን ነገር ፈጸምኩ።+

ስለዚህ አንተ በምትናገርበት ጊዜ ጻድቅ ነህ፤

በምትፈርድበት ጊዜም ትክክል ነህ።+

 5 እነሆ፣ በደለኛ ሆኜ ተወለድኩ፤

እናቴም በኃጢአት ፀነሰችኝ።*+

 6 ከልብ የመነጨ እውነት ደስ ያሰኝሃል፤+

ልቤን* እውነተኛ ጥበብ አስተምረው።

 7 ንጹሕ እሆን ዘንድ በሂሶጵ ከኃጢአቴ አንጻኝ፤+

ከበረዶም የበለጠ እነጣ ዘንድ እጠበኝ።+

 8 ያደቀቅካቸው አጥንቶች ደስ እንዲላቸው፣+

የደስታንና የሐሴትን ድምፅ አሰማኝ።

 9 ፊትህን ከኃጢአቴ መልስ፤*+

የፈጸምኳቸውንም ስህተቶች ሁሉ አስወግድ።*+

10 አምላክ ሆይ፣ ንጹሕ ልብ ፍጠርልኝ፤+

በውስጤም ጽኑ የሆነ አዲስ መንፈስ አኑር።+

11 ከፊትህ አትጣለኝ፤

ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ አትውሰድ።

12 የአንተ ማዳን የሚያስገኘውን ደስታ መልስልኝ፤+

አንተን የመታዘዝ ፍላጎት በውስጤ እንዲቀሰቀስ አድርግ።*

13 ኃጢአተኞች ወደ አንተ እንዲመለሱ፣

ለሕግ ተላላፊዎች መንገድህን አስተምራለሁ።+

14 አምላክ ሆይ፣ የመዳኔ አምላክ፣+ አንደበቴ ጽድቅህን በደስታ ያስታውቅ ዘንድ+

የደም ባለዕዳ ከመሆን አድነኝ።+

15 ይሖዋ ሆይ፣ አፌ ምስጋናህን እንዲያውጅ

ከንፈሮቼን ክፈት።+

16 መሥዋዕት እንዲቀርብልህ አትፈልግምና፤ ቢሆንማ ኖሮ ባቀረብኩልህ ነበር፤+

ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ አያስደስትህም።+

17 አምላክን የሚያስደስተው መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፤

አምላክ ሆይ፣ የተሰበረንና የተደቆሰን ልብ ችላ አትልም።*+

18 በበጎ ፈቃድህ ለጽዮን መልካም ነገር አድርግላት፤

የኢየሩሳሌምን ግንቦች ገንባ።

19 በዚያን ጊዜ የጽድቅ መሥዋዕቶች፣

የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችና ሙሉ በሙሉ የሚቀርቡ መባዎች ደስ ያሰኙሃል፤

በዚያን ጊዜ ኮርማዎች በመሠዊያህ ላይ ይቀርባሉ።+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። ማስኪል።* የዳዊት መዝሙር፤ ኤዶማዊው ዶይቅ ወደ ሳኦል ሄዶ፣ ዳዊት ወደ አሂሜሌክ ቤት መጥቶ እንደነበር በነገረው ጊዜ።+

52 አንተ ኃያል፣ መጥፎ በሆነው ተግባርህ የምትኩራራው ለምንድን ነው?+

የአምላክ ታማኝ ፍቅር ዘላቂ እንደሆነ አታውቅም?+

 2 ምላስህ እንደ ምላጭ የተሳለ ነው፤+

ጥፋትን ይሸርባል፤ ተንኮልንም ያቀነባብራል።+

 3 መልካም ከሆነው ነገር ይልቅ ክፋትን፣

ትክክል የሆነውን ነገር ከመናገር ይልቅ ሐሰትን ትወዳለህ። (ሴላ)

 4 አንተ አታላይ ምላስ!

ጎጂ ቃልን ሁሉ ትወዳለህ።

 5 በመሆኑም አምላክ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ያንኮታኩትሃል፤+

መንጭቆ ይወስድሃል፤ ከድንኳንህም ጎትቶ ያወጣሃል፤+

ከሕያዋን ምድር ይነቅልሃል።+ (ሴላ)

 6 ጻድቃንም ይህን አይተው በፍርሃት* ይዋጣሉ፤+

በእሱም ላይ ይስቃሉ።+

 7 “እንዲህ ያለ ሰው አምላክን መጠጊያው* አያደርግም፤+

ይልቁንም በታላቅ ሀብቱ ይታመናል፤+

ራሱ በሚጠነስሰውም ሴራ* ይመካል።”*

 8 እኔ ግን በአምላክ ቤት እንዳለ የለመለመ የወይራ ዛፍ እሆናለሁ፤

ለዘላለም በአምላክ ታማኝ ፍቅር እታመናለሁ።+

 9 እርምጃ ስለወሰድክ ለዘላለም አወድስሃለሁ፤+

መልካም ነውና፣ በታማኝ አገልጋዮችህ ፊት

በስምህ ተስፋ አደርጋለሁ።+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በማሃላት ቅኝት።* ማስኪል።* የዳዊት መዝሙር።

53 ሞኝ* ሰው በልቡ

“ይሖዋ የለም” ይላል።+

የዓመፅ ድርጊታቸው ብልሹና አስጸያፊ ነው፤

መልካም የሚሠራ ማንም የለም።+

 2 ሆኖም ጥልቅ ማስተዋል ያለውና ይሖዋን የሚፈልግ ሰው ይኖር እንደሆነ ለማየት+

አምላክ ከሰማይ ሆኖ ወደ ሰው ልጆች ይመለከታል።+

 3 ሁሉም ወደ ሌላ ዞር ብለዋል፤

ሁሉም ብልሹ ናቸው።

መልካም የሚሠራ ማንም የለም፤

አንድ እንኳ የለም።+

 4 ከክፉ አድራጊዎቹ መካከል አንዳቸውም አያስተውሉም?

ምግብ እንደሚበሉ ሕዝቤን ይውጣሉ።

ይሖዋን አይጠሩም።+

 5 ይሁንና በታላቅ ሽብር፣

ከዚህ በፊት ተሰምቷቸው በማያውቅ ታላቅ ፍርሃት ይዋጣሉ፤*

በአንተ ላይ ጥቃት የሚሰነዝሩትን* ሰዎች አጥንት አምላክ ይበታትነዋልና።

ይሖዋ ስላልተቀበላቸው አንተ ታዋርዳቸዋለህ።

 6 የእስራኤል መዳን ምነው ከጽዮን በመጣ!+

ይሖዋ የተማረከውን ሕዝቡን በሚመልስበት ጊዜ፣

ያዕቆብ ደስ ይበለው፤ እስራኤል ሐሴት ያድርግ።

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በባለ አውታር መሣሪያዎች የሚታጀብ። ማስኪል።* የዚፍ ሰዎች ወደ ሳኦል መጥተው “ዳዊት እኛ ጋ ተደብቋል” ባሉት ጊዜ ዳዊት የዘመረው መዝሙር።+

54 አምላክ ሆይ፣ በስምህ አድነኝ፤+

በኃይልህም ደግፈኝ።*+

 2 አምላክ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤+

ለአፌም ቃል ትኩረት ስጥ።

 3 ባዕዳን በእኔ ላይ ተነስተዋልና፤

ጨካኝ ሰዎችም ሕይወቴን* ይሻሉ።+

ስለ አምላክ ምንም ግድ የላቸውም።*+ (ሴላ)

 4 እነሆ፣ አምላክ ረዳቴ ነው፤+

ይሖዋ እኔን* ከሚደግፉ ጋር ነው።

 5 የገዛ ክፋታቸውን በጠላቶቼ ላይ ይመልስባቸዋል፤+

በታማኝነትህ አስወግዳቸው።*+

 6 ለአንተ በፈቃደኝነት መሥዋዕት አቀርባለሁ።+

ይሖዋ ሆይ፣ መልካም ነውና፣ ስምህን አወድሳለሁ።+

 7 ከጭንቅ ሁሉ ያድነኛልና፤+

ጠላቶቼንም በድል አድራጊነት እመለከታለሁ።+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በባለ አውታር መሣሪያዎች የሚታጀብ። ማስኪል።* የዳዊት መዝሙር።

55 አምላክ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤+

ምሕረት እንድታደርግልኝ የማቀርበውንም ልመና ቸል አትበል።*+

 2 ትኩረት ስጠኝ፤ መልስልኝም።+

ያሳሰበኝ ጉዳይ እረፍት ነስቶኛል፤+

ደግሞም በጣም ተጨንቄአለሁ፤

 3 ይህም ጠላት ከሚናገረው ቃል፣

ክፉውም ሰው ከሚያሳድረው ጫና የተነሳ ነው።

እነሱ በእኔ ላይ መከራ ይከምራሉና፤

በቁጣም ተሞልተው በጥላቻ ዓይን ያዩኛል።+

 4 ልቤ በውስጤ በጣም ተጨነቀ፤+

የሞት ፍርሃትም ዋጠኝ።+

 5 ፍርሃት አደረብኝ፤ ደግሞም ተንቀጠቀጥኩ፤

ብርክም ያዘኝ።

 6 እኔም እንዲህ እላለሁ፦ “ምነው እንደ ርግብ ክንፍ በኖረኝ!

በርሬ ሄጄ ያለስጋት በኖርኩ ነበር።

 7 እነሆ፣ ወደ ሩቅ ቦታ በበረርኩ፣+

በምድረ በዳም በቆየሁ ነበር።+ (ሴላ)

 8 ከአውሎ ነፋስና ከውሽንፍር ሸሽቼ

መጠለያ ወደማገኝበት ቦታ ፈጥኜ በሄድኩ ነበር።”

 9 ይሖዋ ሆይ፣ ግራ አጋባቸው፤ ዕቅዳቸውንም አጨናግፍ፤+

በከተማዋ ውስጥ ዓመፅና ብጥብጥ አይቻለሁና።

10 ቅጥሮቿ ላይ ወጥተው ቀንና ሌሊት ይዞራሉ፤

በውስጧም ተንኮልና መከራ አለ።+

11 ጥፋት በመካከሏ አለ፤

ጭቆናና ማታለል ከአደባባይዋ ፈጽሞ አይጠፉም።+

12 የሚዘልፈኝ ጠላት አይደለምና፤+

ቢሆንማ ኖሮ በቻልኩት ነበር።

በእኔ ላይ የተነሳው ባላጋራ አይደለም፤

ቢሆንማ ኖሮ ከእሱ በተሸሸግኩ ነበር።

13 ነገር ግን ይህን ያደረግከው እንደ እኔው ሰው* የሆንከው አንተ ነህ፤+

በሚገባ የማውቅህ የገዛ ጓደኛዬ ነህ።+

14 በመካከላችን የጠበቀ ወዳጅነት ነበር፤

ከብዙ ሕዝብ ጋር ወደ አምላክ ቤት አብረን እንሄድ ነበር።

15 ጥፋት በድንገት ይምጣባቸው!+

በሕይወት ሳሉ ወደ መቃብር* ይውረዱ፤

ክፋት በመካከላቸውና በውስጣቸው ያድራልና።

16 እኔ በበኩሌ አምላክን እጣራለሁ፤

ይሖዋም ያድነኛል።+

17 በማታ፣ በጠዋትና በቀትር እጨነቃለሁ፤ ደግሞም እቃትታለሁ፤*+

እሱም ድምፄን ይሰማል።+

18 በእኔ ላይ ጦርነት ከከፈቱ ሰዎች ይታደገኛል፤* ሰላም እንዳገኝም ያደርጋል፤

እጅግ ብዙ ሰዎች በእኔ ላይ ተነስተዋልና።+

19 ከጥንት ጀምሮ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው አምላክ+ ይሰማል፤

ምላሽም ይሰጣቸዋል።+ (ሴላ)

አምላክን የማይፈሩት እነዚህ ሰዎች+

ለመለወጥ ፈቃደኞች አይደሉም።

20 ከእሱ* ጋር ሰላም በነበራቸው ሰዎች ላይ ጥቃት ሰንዝሯል፤+

የገባውን ቃል ኪዳን አፍርሷል።+

21 የሚናገራቸው ቃላት ከቅቤ ይልቅ የለሰለሱ ናቸው፤+

በልቡ ውስጥ ግን ጠብ አለ።

ቃሎቹ ከዘይት ይልቅ የለሰለሱ ቢሆኑም

እንደተመዘዘ ሰይፍ ናቸው።+

22 ሸክምህን በይሖዋ ላይ ጣል፤+

እሱም ይደግፍሃል።+

ጻድቁ እንዲወድቅ* ፈጽሞ አይፈቅድም።+

23 አምላክ ሆይ፣ አንተ ግን ወደ ጥልቅ ጉድጓድ ታወርዳቸዋለህ።+

የደም ዕዳ ያለባቸውና አታላይ የሆኑ ሰዎች የዕድሜያቸውን ግማሽ እንኳ አይኖሩም።+

እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ።

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ “ራቅ ባለ ቦታ የምትገኝ ዝምተኛ ርግብ” በተባለው ቅኝት። የዳዊት መዝሙር። ሚክታም።* ፍልስጤማውያን በጌት በያዙት ጊዜ።+

56 አምላክ ሆይ፣ ሟች የሆነ ሰው ጥቃት እየሰነዘረብኝ* ስለሆነ ሞገስ አሳየኝ።

ቀኑን ሙሉ ይዋጉኛል፤ ደግሞም ያስጨንቁኛል።

 2 ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ እኔን ለመንከስ ይሞክራሉ፤

ብዙዎች በእብሪት ተነሳስተው ይዋጉኛል።

 3 ፍርሃት በሚሰማኝ ጊዜ+ በአንተ እታመናለሁ።+

 4 ቃሉን በማወድሰው አምላክ፣

አዎ፣ በአምላክ እታመናለሁ፤ አልፈራም።

ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?+

 5 ቀኑን ሙሉ የእኔን ጉዳይ ለማበላሸት ይጥራሉ፤

ሐሳባቸው እኔን መጉዳት ብቻ ነው።+

 6 እኔን ለማጥቃት ራሳቸውን ይሰውራሉ፤

ሕይወቴን* ለማጥፋት በመሻት+

እርምጃዬን አንድ በአንድ ይከታተላሉ።+

 7 ከክፋታቸው የተነሳ አስወግዳቸው።

አምላክ ሆይ፣ ብሔራትን በቁጣህ አጥፋቸው።+

 8 ከቦታ ቦታ ስንከራተት አንድ በአንድ ትከታተላለህ።+

እንባዬን በአቁማዳህ አጠራቅም።+

ደግሞስ በመጽሐፍህ ውስጥ ሰፍሮ የለም?+

 9 እርዳታ ለማግኘት በምጣራበት ቀን ጠላቶቼ ያፈገፍጋሉ።+

አምላክ ከጎኔ እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ።+

10 ቃሉን በማወድሰው አምላክ፣

ቃሉን በማወድሰው በይሖዋ፣

11 አዎ፣ በአምላክ እታመናለሁ፤ አልፈራም።+

ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?+

12 አምላክ ሆይ፣ ለአንተ በተሳልኳቸው ስእለቶች የተነሳ ግዴታ ውስጥ ገብቻለሁ፤+

ለአንተ የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ።+

13 አንተ ከሞት ታድገኸኛልና፤*+

እግሮቼንም ከእንቅፋት አድነሃል፤+

ይህም በሕያዋን ብርሃን በአምላክ ፊት እመላለስ ዘንድ ነው።+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ “ጥፋት አታምጣ” በተባለው ቅኝት። የዳዊት መዝሙር። ሚክታም።* ከሳኦል ሸሽቶ ወደ ዋሻ በገባበት ጊዜ።+

57 ሞገስ አሳየኝ፤ አምላክ ሆይ፣ ሞገስ አሳየኝ፤

አንተን መጠጊያ አድርጌአለሁና፤*+

መከራው እስኪያልፍ ድረስ በክንፎችህ ጥላ ሥር እጠለላለሁ።+

 2 ወደ ልዑሉ አምላክ፣

ለእኔ ሲል መከራውን ወደሚያስቆመው ወደ እውነተኛው አምላክ እጣራለሁ።

 3 ከሰማይ እርዳታ ልኮ ያድነኛል።+

ሊነክሰኝ የሚሞክረውን ሰው እንዳይሳካለት ያደርጋል። (ሴላ)

አምላክ ታማኝ ፍቅሩንና ታማኝነቱን ያሳያል።+

 4 አንበሶች ከበውኛል፤*+

ሊውጡኝ በሚፈልጉ ሰዎች መካከል ለመተኛት ተገድጃለሁ፤

ጥርሳቸው ጦርና ፍላጻ ነው፤

ምላሳቸውም የተሳለ ሰይፍ ነው።+

 5 አምላክ ሆይ፣ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል፤

ክብርህ በምድር ሁሉ ላይ ይሁን።+

 6 እግሮቼን ለመያዝ ወጥመድ አዘጋጅተዋል፤+

ከጭንቅ የተነሳ ጎብጫለሁ።*+

በፊቴ ጉድጓድ ቆፈሩ፤

ነገር ግን ራሳቸው ገቡበት።+ (ሴላ)

 7 ልቤ ጽኑ ነው፤

አምላክ ሆይ፣ ልቤ ጽኑ ነው።+

እዘምራለሁ፤ ደግሞም አዜማለሁ።

 8 ልቤ* ሆይ፣ ተነሳ።

ባለ አውታር መሣሪያ ሆይ፣ አንተም በገና ሆይ፣ ተነሱ።

እኔም በማለዳ እነሳለሁ።+

 9 ይሖዋ ሆይ፣ በሕዝቦች መካከል አወድስሃለሁ፤+

በብሔራት መካከል የውዳሴ መዝሙር እዘምርልሃለሁ።+

10 ታማኝ ፍቅርህ ታላቅ ነውና፤ እንደ ሰማያት ከፍ ያለ ነው፤+

ታማኝነትህም እስከ ደመናት ድረስ ነው።

11 አምላክ ሆይ፣ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል፤

ክብርህ በምድር ሁሉ ላይ ይሁን።+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ “ጥፋት አታምጣ” በተባለው ቅኝት። የዳዊት መዝሙር። ሚክታም።*

58 እናንተ የሰው ልጆች፣ ዝም ብላችሁ እያለ ስለ ጽድቅ ልትናገሩ ትችላላችሁ?+

በቅንነትስ መፍረድ ትችላላችሁ?+

 2 ይልቁንም በልባችሁ ክፋት ትጠነስሳላችሁ፤+

እጆቻችሁም በምድሪቱ ላይ ዓመፅ ያስፋፋሉ።+

 3 ክፉዎች፣ ከተወለዱበት ጊዜ* ጀምሮ መንገድ ስተዋል፤*

ከተወለዱበት ጊዜ አንስቶ ሥርዓት የሌላቸውና ውሸታሞች ናቸው።

 4 መርዛቸው እንደ እባብ መርዝ ነው፤+

ጆሮውን እንደ ደፈነ ጉበና* ደንቆሮ ናቸው።

 5 ድግምተኞቹ ምንም ያህል ችሎታ ቢኖራቸው

ጉበናው ድምፃቸውን አይሰማም።

 6 አምላክ ሆይ፣ ጥርሳቸውን ከአፋቸው አርግፍ!

ይሖዋ ሆይ፣ የእነዚህን አንበሶች* መንጋጋ ሰባብር!

 7 ፈስሶ እንደሚያልቅ ውኃ ይጥፉ።

አምላክ ደጋኑን ወጥሮ በቀስቶቹ ይጣላቸው።

 8 ሲሄድ እንደሚቀልጥ ቀንድ አውጣ ይሁኑ፤

ፀሐይን ፈጽሞ እንደማያይ ከሴት የተወለደ ጭንጋፍ ይሁኑ።

 9 በእሳት የተቀጣጠለው እሾህ ድስታችሁን ሳያሞቀው፣

አምላክ እርጥቡንም ሆነ የሚነደውን ቅርንጫፍ እንደ አውሎ ነፋስ ጠራርጎ ይወስደዋል።+

10 ጻድቅ ሰው በክፉዎች ላይ የተወሰደውን የበቀል እርምጃ በማየቱ ደስ ይለዋል፤+

እግሮቹ በእነሱ ደም ይርሳሉ።+

11 በዚህ ጊዜ ሰዎች እንዲህ ይላሉ፦ “በእርግጥ ጻድቁ ብድራት ይቀበላል።+

በእውነትም በምድር ላይ የሚፈርድ አምላክ አለ።”+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ “ጥፋት አታምጣ” በተባለው ቅኝት። የዳዊት መዝሙር። ሚክታም።* ሳኦል የዳዊትን ቤት* ከበው እንዲጠብቁና እንዲገድሉት ሰዎችን በላከ ጊዜ።+

59 አምላኬ ሆይ፣ ከጠላቶቼ ታደገኝ፤+

በእኔ ላይ ከተነሱት ሰዎች ጠብቀኝ።+

 2 ከክፉ አድራጊዎች ታደገኝ፤

ከጨካኝ* ሰዎችም አድነኝ።

 3 እነሆ፣ እኔን* ለማጥቃት አድፍጠው ይጠብቃሉ፤+

ይሖዋ ሆይ፣ ምንም ዓይነት ዓመፅም ሆነ ኃጢአት ሳይገኝብኝ

ብርቱ የሆኑ ሰዎች ያጠቁኛል።+

 4 የሠራሁት ጥፋት ባይኖርም እኔን ለማጥቃት ተጣደፉ፤ ደግሞም ተዘጋጁ።

ወደ አንተ ስጣራ ተነስ፤ ተመልከተኝም።

 5 የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ የእስራኤል አምላክ ነህና።+

ብሔራትን ሁሉ ለመመርመር ተነስ።

ተንኮለኛ ለሆኑ ከሃዲዎች ሁሉ ምሕረት አታድርግ።+ (ሴላ)

 6 በየምሽቱ ተመልሰው ይመጣሉ፤+

እንደ ውሾች እያጉረመረሙ* በከተማዋ ዙሪያ ያደባሉ።+

 7 ከአፋቸው የሚዥጎደጎደውን* ተመልከት፤

ከንፈሮቻቸው እንደ ሰይፍ ናቸው፤+

“ማን ይሰማል?” ይላሉና።+

 8 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን ትስቅባቸዋለህ፤+

ብሔራትን ሁሉ ታላግጥባቸዋለህ።+

 9 ብርታቴ ሆይ፣ አንተን እጠባበቃለሁ፤+

አምላክ አስተማማኝ መጠጊያዬ ነውና።+

10 ታማኝ ፍቅር የሚያሳየኝ አምላክ ይረዳኛል፤+

አምላክ ጠላቶቼን በድል አድራጊነት ስሜት እንዳያቸው ያደርገኛል።+

11 ሕዝቤ ይህን እንዳይረሳ አትግደላቸው።

በኃይልህ እንዲቅበዘበዙ አድርጋቸው፤

ጋሻችን ይሖዋ ሆይ፣ ለውድቀት ዳርጋቸው።+

12 ከአፋቸው ኃጢአትና ከከንፈራቸው ቃል፣

ከሚናገሩት እርግማንና የማታለያ ቃል የተነሳ

በኩራታቸው ይጠመዱ።+

13 በቁጣህ አጥፋቸው፤+

ከሕልውና ውጭ እንዲሆኑ ደምስሳቸው፤

አምላክ ያዕቆብንና መላውን ምድር በመግዛት ላይ እንደሆነ አሳውቃቸው።+ (ሴላ)

14 ምሽት ላይ ተመልሰው ይምጡ፤

እንደ ውሾች እያጉረመረሙ* በከተማዋ ዙሪያ ያድቡ።+

15 ምግብ ፍለጋ ወዲያ ወዲህ ይንከራተቱ፤+

በልተውም አይጥገቡ፤ የሚያርፉበት ቦታም ይጡ።

16 እኔ ግን ስለ ብርታትህ እዘምራለሁ፤+

በማለዳ ስለ ታማኝ ፍቅርህ በደስታ እናገራለሁ።

አንተ አስተማማኝ መጠጊያዬ፣

ደግሞም በጭንቀቴ ቀን መሸሸጊያዬ ነህና።+

17 ብርታቴ ሆይ፣ ለአንተ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ፤+

ታማኝ ፍቅር የሚያሳየኝ አምላክ አስተማማኝ መጠጊያዬ ነውና።+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ “በማስታወሻ አበባ” የሚዘመር። ሚክታም።* የዳዊት መዝሙር። ለትምህርት። ከአራምናሃራይም እና ከአራምጾባ ሰዎች ጋር በተዋጋ ጊዜ፤ ኢዮዓብም ተመልሶ በጨው ሸለቆ 12,000 ኤዶማውያንን ፈጀ።+

60 አምላክ ሆይ፣ ገሸሽ አድርገኸናል፤ መከላከያዎቻችንን ጥሰህ አልፈሃል።+

ተቆጥተኸናል፤ አሁን ግን መልሰህ ተቀበለን!

 2 ምድርን አናወጥካት፤ ሰነጣጠቅካት።

እየፈራረሰች ነውና ስንጥቆቿን ጠግን።

 3 ሕዝብህ መከራ እንዲደርስበት አደረግክ።

የወይን ጠጅ እንድንጠጣና እንድንንገዳገድ አደረግከን።+

 4 አንተን የሚፈሩ ከቀስት መሸሽና ማምለጥ እንዲችሉ

ምልክት አቁምላቸው።* (ሴላ)

 5 የምትወዳቸው ሰዎች እንዲድኑ

በቀኝ እጅህ ታደገን፤ ደግሞም መልስ ስጠን።+

 6 አምላክ በቅድስናው* እንዲህ ብሏል፦

“ሐሴት አደርጋለሁ፤ ሴኬምን ርስት አድርጌ እሰጣለሁ፤+

የሱኮትንም ሸለቆ* አከፋፍላለሁ።+

 7 ጊልያድም ሆነ ምናሴ የእኔ ናቸው፤+

ኤፍሬምም የራስ ቁሬ ነው፤*

ይሁዳ በትረ መንግሥቴ ነው።+

 8 ሞዓብ መታጠቢያ ገንዳዬ ነው።+

በኤዶም ላይ ጫማዬን እጥላለሁ።+

በፍልስጤም ላይ በድል አድራጊነት እጮኻለሁ።”+

 9 ወደተከበበችው* ከተማ ማን ይወስደኛል?

እስከ ኤዶም ድረስ ማን ይመራኛል?+

10 አምላክ ሆይ፣ ገሸሽ ያደረግከን አንተ አይደለህም?

አምላካችን ሆይ፣ ከሠራዊታችን ጋር አብረህ አትወጣም።+

11 ከጭንቅ እንድንገላገል እርዳን፤

የሰው ማዳን ከንቱ ነውና።+

12 አምላክ ኃይል ይሰጠናል፤+

ጠላቶቻችንንም ይረጋግጣቸዋል።+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በባለ አውታር መሣሪያዎች የሚታጀብ። የዳዊት መዝሙር።

61 አምላክ ሆይ፣ እርዳታ ለማግኘት የማሰማውን ጩኸት ስማ።

ጸሎቴን በትኩረት አዳምጥ።+

 2 ልቤ ተስፋ በቆረጠ* ጊዜ

ከምድር ዳርቻ ወደ አንተ እጮኻለሁ።+

ከእኔ ይልቅ ከፍ ወዳለ ዓለት ምራኝ።+

 3 አንተ መጠጊያዬ ነህና፤

ከጠላት የምትጠብቀኝ ጽኑ ግንብ ነህ።+

 4 በድንኳንህ ለዘላለም በእንግድነት እቀመጣለሁ፤+

በክንፎችህ ጥላ ሥር እጠለላለሁ።+ (ሴላ)

 5 አምላክ ሆይ፣ ስእለቴን ሰምተሃልና።

ስምህን የሚፈሩትን ሰዎች ርስት ሰጥተኸኛል።+

 6 የንጉሡን ሕይወት* ታረዝምለታለህ፤+

ዕድሜውም ከትውልድ እስከ ትውልድ ድረስ ይሆናል።

 7 በአምላክ ፊት ለዘላለም ይነግሣል፤*+

ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት እንዲጠብቁት እዘዝ።*+

 8 እኔም ስእለቴን በየቀኑ ስፈጽም፣+

ለስምህ ለዘላለም የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በየዱቱን።* የዳዊት ማህሌት።

62 ዝም ብዬ አምላክን እጠባበቃለሁ።*

መዳን የማገኘው ከእሱ ዘንድ ነው።+

 2 በእርግጥም እሱ ዓለቴና አዳኜ እንዲሁም አስተማማኝ መጠጊያዬ ነው፤+

ከልክ በላይ አልናወጥም።+

 3 አንድን ሰው ለመግደል ጥቃት የምትሰነዝሩበት እስከ መቼ ነው?+

ሁላችሁም እንዳዘመመ ግንብ፣ ሊወድቅ እንደተቃረበም የድንጋይ ቅጥር አደገኛ ናችሁ።*

 4 ካለበት ከፍ ያለ ቦታ ሊጥሉት* እርስ በርሳቸው ይማከራሉና፤

በመዋሸት ደስ ይሰኛሉ።

በአፋቸው ይባርካሉ፤ በልባቸው ግን ይራገማሉ።+ (ሴላ)

 5 ዝም ብዬ አምላክን እጠባበቃለሁ፤*+

ምክንያቱም ተስፋዬ የሚመጣው ከእሱ ዘንድ ነው።+

 6 በእርግጥም እሱ ዓለቴና አዳኜ እንዲሁም አስተማማኝ መጠጊያዬ ነው፤

በምንም ዓይነት አልናወጥም።+

 7 የእኔ መዳንና ክብር የተመካው በአምላክ ላይ ነው።

እሱ ጠንካራ ዓለቴና መጠጊያዬ ነው።+

 8 ሰዎች ሆይ፣ ሁልጊዜ በእሱ ታመኑ።

ልባችሁን በፊቱ አፍስሱ።+

አምላክ መጠጊያችን ነው።+ (ሴላ)

 9 የሰው ልጆች እስትንፋስ ናቸው፤

ሰዎች ከንቱ መመኪያ ናቸው።+

አንድ ላይ ሆነው በሚዛን ሲመዘኑ ከአየር እንኳ ይቀልላሉ።+

10 በዝርፊያ አትታመኑ፤

ወይም በስርቆት እጠቀማለሁ ብላችሁ በከንቱ ተስፋ አታድርጉ።

ሀብታችሁ ቢበዛ ልባችሁን በእሱ ላይ አትጣሉ።+

11 አምላክ አንድ ጊዜ ተናገረ፤ እኔም ይህን ሁለት ጊዜ ሰማሁ፦

ብርታት የአምላክ ነው።+

12 ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርም የአንተ ነው፤+

ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ትከፍላለህና።+

የዳዊት ማህሌት፤ በይሁዳ ምድረ በዳ በነበረበት ጊዜ።+

63 አምላክ ሆይ፣ አንተ አምላኬ ነህ፤ አንተን ዘወትር እጠባበቃለሁ።+

አንተን ተጠማሁ።*+

ውኃ በሌለበት ደረቅና የተጠማ ምድር

አንተን ከመናፈቄ የተነሳ እጅግ ዝያለሁ።*+

 2 ስለዚህ በቅዱሱ ስፍራ አንተን ተመለከትኩ፤

ብርታትህንና ክብርህን አየሁ።+

 3 ታማኝ ፍቅርህ ከሕይወት ስለሚሻል+

የገዛ ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል።+

 4 በመሆኑም በሕይወቴ ዘመን ሁሉ አወድስሃለሁ፤

በአንተም ስም እጆቼን ወደ ላይ አነሳለሁ።

 5 ምርጥ የሆነውንና ስቡን በልቼ ጠገብኩ፤*

ስለዚህ በከንፈሬ እልልታ አፌ ያወድስሃል።+

 6 መኝታዬ ላይ ሆኜ አንተን አስታውሳለሁ፤

ሌሊት* ስለ አንተ አሰላስላለሁ።+

 7 አንተ ረዳቴ ነህና፤+

በክንፎችህም ጥላ ሥር ሆኜ እልል እላለሁ።+

 8 አንተን የሙጥኝ እላለሁ፤*

ቀኝ እጅህ አጥብቆ ይይዘኛል።+

 9 ሕይወቴን ለማጥፋት* የሚሹ ሰዎች ግን

ወደ ምድር ጥልቅ ይወርዳሉ።

10 ለሰይፍ ስለት አልፈው ይሰጣሉ፤

የቀበሮዎችም ምግብ ይሆናሉ።

11 ንጉሡ ግን በአምላክ ሐሴት ያደርጋል።

በእሱ የሚምል ሰው ሁሉ ይደሰታል፤*

ሐሰትን የሚናገሩ ሰዎች አፍ ይዘጋልና።

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት ማህሌት።

64 አምላክ ሆይ፣ የማቀርበውን ልመና ስማ።+

ጠላት ከሚሰነዝርብኝ አስፈሪ ጥቃት ሕይወቴን ታደግ።

 2 ከክፉ ሰዎች ስውር ሴራ፣

ከክፉ አድራጊዎች ሸንጎ ጠብቀኝ፤+

 3 እነሱ ምላሳቸውን እንደ ሰይፍ ይስላሉ፤

መርዘኛ ቃላቸውን እንደ ቀስት ያነጣጥራሉ፤

 4 ይህን የሚያደርጉት ከተደበቁበት ቦታ ሆነው ንጹሑን ሰው ለመምታት ነው፤

ያላንዳች ፍርሃት በድንገት ይመቱታል።

 5 ክፉ ዓላማቸውን ከመፈጸም ወደኋላ አይሉም፤*

በስውር እንዴት ወጥመድ እንደሚዘረጉ ይነጋገራሉ።

“ማን ያየዋል?” ይላሉ።+

 6 ክፉ ነገር ለመሥራት አዳዲስ መንገዶች ይቀይሳሉ፤

የረቀቀ ሴራቸውን በስውር ይሸርባሉ፤+

በእያንዳንዳቸው ልብ ውስጥ ያለው ሐሳብ አይደረስበትም።

 7 ሆኖም አምላክ ይመታቸዋል፤+

እነሱም በድንገት በቀስት ይቆስላሉ።

 8 የገዛ ምላሳቸው ለውድቀት ይዳርጋቸዋል፤+

ይህን የሚመለከቱ ሁሉ ራሳቸውን ይነቀንቃሉ።

 9 በዚህ ጊዜ ሰዎች ሁሉ ይፈራሉ፤

አምላክ ያደረገውንም ነገር ያውጃሉ፤

ሥራውንም በሚገባ ያስተውላሉ።+

10 ጻድቅ ሰው በይሖዋ ሐሴት ያደርጋል፤ እሱንም መጠጊያው ያደርጋል፤+

ቀና ልብ ያላቸውም ሁሉ ይደሰታሉ።*

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት ማህሌት። መዝሙር።

65 አምላክ ሆይ፣ በጽዮን+ ውዳሴ ይቀርብልሃል፤

የተሳልነውን ለአንተ እንሰጣለን።+

 2 ጸሎት ሰሚ የሆንከው አምላክ ሆይ፣ ሁሉም ዓይነት ሰው* ወደ አንተ ይመጣል።+

 3 የፈጸምኳቸው በደሎች አሸንፈውኛል፤+

አንተ ግን መተላለፋችንን ይቅር አልክ።+

 4 በቅጥር ግቢዎችህ ይኖር ዘንድ

የመረጥከውና ያቀረብከው ሰው ደስተኛ ነው።+

እኛም በቤትህ፣

ቅዱስ በሆነው ቤተ መቅደስህ+ ውስጥ ባሉ ጥሩ ነገሮች እንረካለን።+

 5 የመዳናችን አምላክ ሆይ፣

ፍርሃት* በሚያሳድሩ የጽድቅ ተግባሮች ትመልስልናለህ፤+

በምድር ዳርቻዎች ሁሉና

ከባሕሩ ማዶ ርቀው ላሉት መታመኛቸው ነህ።+

 6 አንተ* በኃይልህ ተራሮችን አጽንተህ መሥርተሃል፤

ኃይልንም ለብሰሃል።+

 7 አንተ* የሚናወጡትን ባሕሮች፣ የሞገዶቻቸውን ድምፅ፣

የብሔራትንም ነውጥ ጸጥ ታሰኛለህ።+

 8 ርቀው በሚገኙ ስፍራዎች የሚኖሩ ሰዎች ምልክቶችህን አይተው በታላቅ አድናቆት ይዋጣሉ፤+

ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ ያሉ በደስታ እልል እንዲሉ ታደርጋለህ።

 9 ምድርን እጅግ ፍሬያማ* በማድረግና

በማበልጸግ ትንከባከባታለህ።+

የአምላክ ጅረት በውኃ የተሞላ ነው፤

ለሰዎች እህል ትሰጣለህ፤+

ምድርን ያዘጋጀኸው በዚህ መንገድ ነውና።

10 ትልሞቿን በውኃ ታረሰርሳለህ፤ የታረሰውንም መሬት* ትደለድላለህ፤

በካፊያ ታለሰልሳታለህ፤ ቡቃያዋንም ትባርካለህ።+

11 ዘመኑ ጥሩነትህን እንደ ዘውድ እንዲጎናጸፍ ታደርጋለህ፤

በጎዳናዎችህም ላይ የተትረፈረፉ ነገሮች ይፈስሳሉ።*+

12 የምድረ በዳው የግጦሽ መሬቶች ሁልጊዜ እንደረሰረሱ ናቸው፤*+

ኮረብቶቹም ደስታን ተጎናጽፈዋል።+

13 የግጦሽ መሬቶቹ በመንጎች ተሞሉ፤

ሸለቆዎቹም* በእህል ተሸፈኑ።+

በድል አድራጊነት እልል ይላሉ፤ አዎ፣ ይዘምራሉ።+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። መዝሙር። ማህሌት።

66 ምድር ሁሉ፣ በድል አድራጊነት ለአምላክ እልል ትበል።+

 2 ለክብራማ ስሙ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ።

ውዳሴውን አድምቁ።+

 3 አምላክን እንዲህ በሉት፦ “ሥራዎችህ አክብሮታዊ ፍርሃት የሚያሳድሩ ናቸው።+

ከኃይልህ ታላቅነት የተነሳ

ጠላቶችህ በፊትህ ይሽቆጠቆጣሉ።+

 4 በምድር ያሉ ሁሉ ይሰግዱልሃል፤+

ለአንተ የውዳሴ መዝሙር ይዘምራሉ፤

ለስምህም የውዳሴ መዝሙር ይዘምራሉ።”+ (ሴላ)

 5 ኑና የአምላክን ሥራዎች ተመልከቱ።

ለሰው ልጆች ያከናወናቸው ተግባሮች አክብሮታዊ ፍርሃት የሚያሳድሩ ናቸው።+

 6 እሱ ባሕሩን ደረቅ ምድር አደረገው፤+

ወንዙን በእግራቸው ተሻገሩ።+

በዚያ በእሱ እጅግ ደስ አለን።+

 7 በኃይሉ ለዘላለም ይገዛል።+

ዓይኖቹ ብሔራትን አተኩረው ያያሉ።+

ግትር የሆኑ ሰዎች ራሳቸውን ከፍ ከፍ አያድርጉ።+ (ሴላ)

 8 እናንተ ሕዝቦች ሆይ፣ አምላካችንን አወድሱ፤+

ለእሱ የሚቀርበውም የውዳሴ ድምፅ ይሰማ።

 9 እሱ በሕይወት ያኖረናል፤*+

እግራችን እንዲደናቀፍ* አይፈቅድም።+

10 አምላክ ሆይ፣ አንተ መርምረኸናልና፤+

ብር በእሳት እንደሚጠራ ሁሉ አንተም እኛን አጥርተኸናል።

11 ማጥመጃ መረብ ውስጥ አስገባኸን፤

በላያችንም* ከባድ ሸክም ጫንክብን።

12 ሟች ሰው ላያችን* ላይ እንዲጋልብ አደረግክ፤

በእሳት መካከልና በውኃ መካከል አለፍን፤

ከዚያም እረፍት ወደምናገኝበት ስፍራ አመጣኸን።

13 ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ ይዤ ወደ ቤትህ እመጣለሁ፤+

ስእለቴንም ለአንተ እፈጽማለሁ፤+

14 ይህም በጭንቅ ውስጥ በነበርኩበት ጊዜ ከንፈሮቼ ቃል የገቡት፣

አፌም የተናገረው ነው።+

15 የሰቡ እንስሳትን ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ አድርጌ

ከሚጨስ የአውራ በጎች መሥዋዕት ጋር አቀርብልሃለሁ።

ከአውራ ፍየሎችም ጋር ኮርማዎችን አቀርባለሁ። (ሴላ)

16 እናንተ አምላክን የምትፈሩ ሁሉ፣ ኑና አዳምጡ፤

ለእኔ ያደረገልኝንም* ነገር እነግራችኋለሁ።+

17 በአፌ ወደ እሱ ተጣራሁ፤

በአንደበቴም ከፍ ከፍ አደረግኩት።

18 በልቤ አንዳች መጥፎ ነገር ይዤ ቢሆን ኖሮ፣

ይሖዋ ባልሰማኝ ነበር።+

19 ሆኖም አምላክ ሰምቷል፤+

ጸሎቴን በትኩረት አዳምጧል።+

20 ጸሎቴን ከመስማት ጆሮውን ያልመለሰ፣

ደግሞም ታማኝ ፍቅሩን ያልነፈገኝ አምላክ ውዳሴ ይድረሰው።

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በባለ አውታር መሣሪያዎች የሚታጀብ። ማህሌት። መዝሙር።

67 አምላክ ሞገስ ያሳየናል፤ ደግሞም ይባርከናል፤

ፊቱን በእኛ ላይ ያበራል፤+ (ሴላ)

 2 ይህም መንገድህ በምድር ሁሉ ላይ፣+

የማዳን ሥራህም በብሔራት ሁሉ መካከል እንዲታወቅ ነው።+

 3 አምላክ ሆይ፣ ሕዝቦች ያወድሱህ፤

አዎ፣ ሕዝቦች ሁሉ ያወድሱህ።

 4 ብሔራት ሐሴት ያድርጉ፤ እልልም ይበሉ፤+

በሕዝቦች ላይ በትክክል ትፈርዳለህና።+

የምድርን ብሔራት ትመራቸዋለህ። (ሴላ)

 5 አምላክ ሆይ፣ ሕዝቦች ያወድሱህ፤

ሕዝቦች ሁሉ ያወድሱህ።

 6 ምድር ፍሬዋን ትሰጣለች፤+

አምላክ፣ አዎ፣ አምላካችን ይባርከናል።+

 7 አምላክ ይባርከናል፤

የምድር ዳርቻዎችም ሁሉ ይፈሩታል።*+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት መዝሙር። ማህሌት።

68 አምላክ ይነሳ፤ ጠላቶቹ ይበታተኑ፤

የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ።+

 2 ጭስ በኖ እንደሚጠፋ ሁሉ እነሱንም አጥፋቸው፤

ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ፣

ክፉዎችም ከአምላክ ፊት ይጥፉ።+

 3 ጻድቃን ግን ደስ ይበላቸው፤+

በአምላክ ፊት ሐሴት ያድርጉ፤

በደስታም ይፈንጥዙ።

 4 ለአምላክ ዘምሩ፤ ለስሙም የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ።+

በበረሃማ ሜዳዎች* እየጋለበ ለሚያቋርጠው ለእሱ ዘምሩ።

ስሙ ያህ* ነው!+ በፊቱ እጅግ ደስ ይበላችሁ!

 5 በተቀደሰ መኖሪያው ያለው አምላክ+

አባት ለሌላቸው ልጆች አባት፣ ለመበለቶች ደግሞ ጠባቂ* ነው።+

 6 አምላክ ብቸኛ ለሆኑ ሰዎች መኖሪያ ቤት ይሰጣቸዋል፤+

እስረኞችን ነፃ አውጥቶ ብልጽግና ያጎናጽፋቸዋል።+

ግትር የሆኑ ሰዎች* ግን ውኃ በተጠማ ምድር ይኖራሉ።+

 7 አምላክ ሆይ፣ ሕዝብህን በመራህ ጊዜ፣*+

በረሃውንም አቋርጠህ በተጓዝክ ጊዜ (ሴላ)

 8 ምድር ተናወጠች፤+

በአምላክ ፊት ሰማይ ዝናብ አወረደ፤*

ይህ የሲና ተራራ በአምላክ ይኸውም በእስራኤል አምላክ ፊት ተናወጠ።+

 9 አምላክ ሆይ፣ ብዙ ዝናብ እንዲዘንብ አደረግክ፤

ለዛለው ሕዝብህ* ብርታት ሰጠኸው።

10 ድንኳኖችህ በተተከሉበት ሰፈር ሕዝብህ ተቀመጠ፤+

አምላክ ሆይ፣ በጥሩነትህ ለድሃው የሚያስፈልገውን ሰጠኸው።

11 ይሖዋ ትእዛዝ አስተላለፈ፤

ምሥራቹን የሚያውጁ ሴቶች ታላቅ ሠራዊት ናቸው።+

12 የብዙ ሠራዊት ነገሥታት እግሬ አውጭኝ ብለው ይሸሻሉ!+

በቤት የምትቀር ሴትም ምርኮ ትካፈላለች።+

13 እናንተ በሰፈሩ ውስጥ በሚነድ እሳት* መካከል ብትተኙ እንኳ፣

በብር የተለበጡ ክንፎችና

በጠራ* ወርቅ የተለበጡ ላባዎች ያሏት ርግብ ትኖራለች።

14 ሁሉን ቻይ የሆነው ነገሥታቷን በበታተነ ጊዜ፣+

በጻልሞን በረዶ ወረደ።*

15 በባሳን የሚገኘው ተራራ+ የአምላክ ተራራ ነው፤*

በባሳን የሚገኘው ተራራ ባለ ብዙ ጫፍ ተራራ ነው።

16 እናንተ ባለ ብዙ ጫፍ ተራሮች ሆይ፣

አምላክ መኖሪያው አድርጎ የመረጠውን ተራራ+ በምቀኝነት ዓይን የምታዩት ለምንድን ነው?

አዎ፣ ይሖዋ በዚያ ለዘላለም ይኖራል።+

17 የአምላክ የጦር ሠረገሎች እልፍ አእላፋት፣ ሺህ ጊዜ ሺህ ናቸው።+

ይሖዋ ከሲና ወደ ቅዱሱ ስፍራ መጥቷል።+

18 ወደ ላይ ወጣህ፤+

ምርኮኞችን ወሰድክ፤

አምላካችን ያህ ሆይ፣ በመካከላቸው ትኖር ዘንድ

ሰዎችን፣ አዎ እልኸኛ የሆኑትን ጭምር+ እንደ ስጦታ አድርገህ ወሰድክ።+

19 ሸክማችንን በየዕለቱ የሚሸከምልን፣+

የሚያድነን እውነተኛው አምላክ ይሖዋ ይወደስ። (ሴላ)

20 እውነተኛው አምላክ፣ አዳኝ አምላካችን ነው፤+

ደግሞም ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ከሞት ይታደጋል።+

21 አዎ፣ አምላክ የጠላቶቹን ራስ፣

ኃጢአት መሥራታቸውን የማይተዉ ሰዎችንም ፀጉራም አናት ይፈረካክሳል።+

22 ይሖዋ እንዲህ ብሏል፦ “ከባሳን+ መልሼ አመጣቸዋለሁ፤

ከጥልቅ ባሕር አውጥቼ አመጣቸዋለሁ፤

23 ይህም እግርህ በደም እንዲታጠብ፣+

ውሾችህም የጠላቶችህን ደም እንዲልሱ ነው።”

24 አምላክ ሆይ፣ እነሱ የድል ሰልፍህን ያያሉ፤

ይህም አምላኬና ንጉሤ ወደ ቅዱሱ ስፍራ የሚያደርገው የድል ጉዞ ነው።+

25 ዘማሪዎቹ ከፊት ሆነው ሲጓዙ በባለ አውታር መሣሪያዎች የሚጫወቱት ሙዚቀኞች ደግሞ ከኋላ ይከተሏቸው ነበር፤+

አታሞ የሚመቱ ወጣት ሴቶችም በመካከላቸው ነበሩ።+

26 ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበበት* አምላክን አወድሱ፤

እናንተ ከእስራኤል ምንጭ የተገኛችሁ ሰዎች፣ ይሖዋን አወድሱ።+

27 የሁሉም ታናሽ የሆነው ቢንያም+ በዚያ ሰዎችን ይገዛል፤

የይሁዳ መኳንንትም ከሚንጫጩ ጭፍሮቻቸው ጋር፣

እንዲሁም የዛብሎን መኳንንትና የንፍታሌም መኳንንት በዚያ አሉ።

28 አምላካችሁ ብርቱዎች እንድትሆኑ አዟል።

ለእኛ ስትል እርምጃ የወሰድከው አምላክ ሆይ፣ ብርታትህን አሳይ።+

29 በኢየሩሳሌም ካለው ቤተ መቅደስህ+ የተነሳ፣

ነገሥታት ለአንተ ስጦታ ያመጣሉ።+

30 ሕዝቦቹ ከብር የተሠሩ ነገሮችን አምጥተው እስኪሰግዱ* ድረስ

በሸምበቆዎች መካከል የሚኖሩትን አራዊት፣

የኮርማዎችን ጉባኤና+ ጥጆቻቸውን ገሥጽ።

ይሁንና ጦርነት የሚያስደስታቸውን ሕዝቦች ይበታትናል።

31 ከነሐስ የተሠሩ ዕቃዎች* ከግብፅ ይመጣሉ፤+

ኢትዮጵያ* ለአምላክ ስጦታ ለመስጠት ትጣደፋለች።

32 እናንተ የምድር መንግሥታት ሆይ፣ ለአምላክ ዘምሩ፤+

ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤ (ሴላ)

33 ከጥንት ጀምሮ በነበሩት ሰማየ ሰማያት ላይ ለሚጋልበው ዘምሩ።+

እነሆ፣ እሱ በኃያል ድምፁ ያስገመግማል።

34 ለአምላክ ብርታት እውቅና ስጡ።+

ግርማዊነቱ በእስራኤል ላይ ነው፤

ብርታቱም በሰማያት* ውስጥ ነው።

35 አምላክ ከታላቅ መቅደሱ ሲወጣ፣* ፍርሃት* ያሳድራል።+

እሱ ለሕዝቡ ብርታትና ኃይል የሚሰጥ

የእስራኤል አምላክ ነው።+

አምላክ ይወደስ።

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ “በአበቦች” የሚዘመር። የዳዊት መዝሙር።

69 አምላክ ሆይ፣ ውኃ ሕይወቴን አደጋ ላይ ስለጣላት* አድነኝ።+

 2 መቆሚያ ስፍራ በሌለበት ጥልቅ ማጥ ውስጥ ሰምጫለሁ።+

ጥልቅ ውኃዎች ውስጥ ገባሁ፤

ኃይለኛ ጅረትም ጠርጎ ወሰደኝ።+

 3 ከመጮኼ ብዛት የተነሳ ደከምኩ፤+

ድምፄም ጎረነነ።

አምላኬን በመጠባበቅ ዓይኖቼ ፈዘዙ።+

 4 ያለምክንያት የሚጠሉኝ+

ከራሴ ፀጉር ይልቅ በዙ።

ሊያጠፉኝ የሚፈልጉ፣

ተንኮለኛ የሆኑ ጠላቶቼ እጅግ በዝተዋል።

ያልሰረቅኩትን ነገር እንድመልስ ተገደድኩ።

 5 አምላክ ሆይ፣ ሞኝነቴን ታውቃለህ፤

ጥፋቴም ከአንተ የተሰወረ አይደለም።

 6 ሉዓላዊ ጌታ የሆንከው የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ሆይ፣

አንተን ተስፋ የሚያደርጉ በእኔ የተነሳ አይፈሩ።

የእስራኤል አምላክ ሆይ፣

አንተን የሚሹ በእኔ የተነሳ አይዋረዱ።

 7 በአንተ የተነሳ ነቀፋ ይደርስብኛል፤+

ኀፍረት ፊቴን ይሸፍነዋል።+

 8 ለወንድሞቼ እንደ እንግዳ፣

ለእናቴ ልጆች እንደ ባዕድ አገር ሰው ሆንኩ።+

 9 ለቤትህ ያለኝ ቅንዓት በልቶኛል፤+

ሰዎች አንተን ይነቅፉበት የነበረው ነቀፋም በእኔ ላይ ደረሰ።+

10 በጾም ራሴን* ባዋረድኩ ጊዜ፣*

ነቀፋ ደረሰብኝ።

11 ማቅ በለበስኩ ጊዜ፣

መቀለጃ* አደረጉኝ።

12 በከተማዋ መግቢያ የሚቀመጡት የመወያያ ርዕስ አደረጉኝ፤

ሰካራሞችም ስለ እኔ ይዘፍናሉ።

13 ይሁንና ይሖዋ ሆይ፣ ጸሎቴ ተሰሚነት ሊያገኝ በሚችልበት ጊዜ

ወደ አንተ ይድረስ።+

አምላክ ሆይ፣ በታማኝ ፍቅርህ ብዛት፣

አስተማማኝ በሆነው የማዳን ሥራህም መልስልኝ።+

14 ከማጡ አውጣኝ፤

እንድሰምጥ አትፍቀድ።

ከሚጠሉኝ ሰዎችና

ከጥልቁ ውኃ ታደገኝ።+

15 ደራሽ ውኃ ጠርጎ እንዲወስደኝ አትፍቀድ፤+

ጥልቁም አይዋጠኝ፤

የጉድጓዱም አፍ በእኔ ላይ አይዘጋ።+

16 ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህ ጥሩ ስለሆነ መልስልኝ።+

እንደ ምሕረትህ ብዛት ወደ እኔ ተመልከት፤+

17 ፊትህንም ከአገልጋይህ አትሰውር።+

ጭንቅ ውስጥ ነኝና በፍጥነት መልስልኝ።+

18 ወደ እኔ ቀርበህ ታደገኝ፤*

ከጠላቶቼ የተነሳ ዋጀኝ።

19 የደረሰብኝን ነቀፋ፣ ኀፍረትና ውርደት ታውቃለህ።+

ጠላቶቼን በሙሉ ታያለህ።

20 የተሰነዘረብኝ ነቀፋ ልቤን ሰብሮታል፤ ቁስሉም የሚድን ዓይነት አይደለም።*

የሚያዝንልኝ ሰው ለማግኘት ተመኝቼ ነበር፤ ሆኖም አንድም ሰው አልነበረም፤+

የሚያጽናናኝ ሰውም ለማግኘት ስጠባበቅ ነበር፤ ሆኖም አንድም ሰው አላገኘሁም።+

21 ይልቁንም መርዝ* እንድበላ ሰጡኝ፤+

በጠማኝ ጊዜም ኮምጣጤ እንድጠጣ ሰጡኝ።+

22 ማዕዳቸው ወጥመድ፣

ብልጽግናቸውም አሽክላ* ይሁንባቸው።+

23 ዓይኖቻቸው ማየት እንዳይችሉ ይጨልሙ፤

ሰውነታቸውም* ምንጊዜም እንዲንቀጠቀጥ አድርግ።

24 ቁጣህን አውርድባቸው፤

የሚነደው ቁጣህም ድንገት ይምጣባቸው።+

25 ሰፈራቸው* ወና ይሁን፤

በድንኳኖቻቸው የሚኖር ሰው አይገኝ።+

26 አንተ የመታኸውን አሳደዋልና፤

ደግሞም አንተ ያቆሰልካቸውን ሰዎች ሥቃይ ሁልጊዜ ያወራሉ።

27 በበደላቸው ላይ በደል ጨምርባቸው፤

ከአንተም ጽድቅ ምንም ድርሻ አይኑራቸው።

28 ከሕያዋን መጽሐፍ* ይደምሰሱ፤+

በጻድቃንም መካከል አይመዝገቡ።+

29 እኔ ግን በጭንቅና በሥቃይ ላይ ነኝ።+

አምላክ ሆይ፣ የማዳን ኃይልህ ይጠብቀኝ።

30 ለአምላክ ስም የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ፤

እሱንም በምስጋና ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።

31 ይህ ከበሬ ይበልጥ ይሖዋን ያስደስተዋል፤

ቀንድና ሰኮና ካለው ወይፈን ይበልጥ ደስ ያሰኘዋል።+

32 የዋሆች ይህን ያያሉ፤ ሐሴትም ያደርጋሉ።

እናንተ አምላክን የምትፈልጉ፣ ልባችሁ ይነቃቃ።

33 ይሖዋ ድሆችን ይሰማልና፤+

በምርኮ ላይ ያለውን ሕዝቡንም አይንቅም።+

34 ሰማይና ምድር፣

ባሕርና በውስጡ የሚንቀሳቀሱ ሁሉ ያወድሱት።+

35 አምላክ ጽዮንን ያድናታልና፤+

የይሁዳንም ከተሞች መልሶ ይገነባል፤

እነሱም በዚያ ይኖራሉ፤ ደግሞም ይወርሷታል።*

36 የአገልጋዮቹ ዘሮች ይወርሷታል፤+

ስሙን የሚወዱም+ በእሷ ላይ ይኖራሉ።

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት መዝሙር፤ ማስታወሻ ሆኖ የሚያገለግል።*

70 አምላክ ሆይ፣ አድነኝ፤

ይሖዋ ሆይ፣ እኔን ለመርዳት ፍጠን።+

 2 ሕይወቴን* ለማጥፋት የሚሹ

ኀፍረትና ውርደት ይከናነቡ።

በእኔ ላይ በደረሰው ጉዳት ደስ የሚሰኙ

አፍረው ወደ ኋላ ይመለሱ።

 3 “እሰይ! እሰይ!” የሚሉ

አፍረው ወደ ኋላ ይመለሱ።

 4 አንተን የሚፈልጉ ግን

በአንተ ይደሰቱ፤ ሐሴትም ያድርጉ።+

የማዳን ሥራህን የሚወዱ፣

ምንጊዜም “አምላክ ታላቅ ይሁን!” ይበሉ።

 5 እኔ ግን ምስኪንና ድሃ ነኝ፤+

አምላክ ሆይ፣ ለእኔ ስትል ፈጥነህ እርምጃ ውሰድ።+

አንተ ረዳቴና ታዳጊዬ ነህ፤+

ይሖዋ ሆይ፣ አትዘግይ።+

71 ይሖዋ ሆይ፣ አንተን መጠጊያ አድርጌአለሁ።

ፈጽሞ ለኀፍረት አልዳረግ።+

 2 በጽድቅህ አድነኝ፤ ታደገኝም።

ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤* አድነኝም።+

 3 ምንጊዜም የምገባበት

መሸሸጊያ ዓለት ሁንልኝ።

አንተ ቋጥኜና ምሽጌ ስለሆንክ

እኔን ለማዳን ትእዛዝ ስጥ።+

 4 አምላኬ ሆይ፣ ከክፉው እጅ፣

ግፈኛ ከሆነው ጨቋኝ ሰው መዳፍ ታደገኝ።+

 5 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ተስፋዬ ነህ፤

ከልጅነቴ ጀምሮ በአንተ ታምኛለሁ።*+

 6 ከተወለድኩበት ጊዜ ጀምሮ በአንተ ታምኛለሁ፤

ከእናቴ ማህፀን ያወጣኸኝ አንተ ነህ።+

ሁልጊዜ አወድስሃለሁ።

 7 ለብዙዎች መደነቂያ ሆንኩ፤

አንተ ግን ጽኑ መጠጊያዬ ነህ።

 8 አፌ በውዳሴህ ተሞልቷል፤+

ቀኑን ሙሉ ስለ ግርማህ እናገራለሁ።

 9 በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ፤+

ጉልበቴ በሚያልቅበት ጊዜም አትተወኝ።+

10 ጠላቶቼ በእኔ ላይ ክፉ ነገር ይናገራሉ፤

ሕይወቴን* የሚሹ ሰዎችም በእኔ ላይ ሴራ ይጠነስሳሉ፤+

11 እንዲህም ይላሉ፦ “አምላክ ትቶታል።

የሚያድነው ስለሌለ አሳዳችሁ ያዙት።”+

12 አምላክ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ።

አምላኬ ሆይ፣ እኔን ለመርዳት ፍጠን።+

13 የሚቃወሙኝ* ሰዎች

ይፈሩ፤ ይጥፉም።+

የእኔን ጥፋት የሚሹ

ውርደትና ኀፍረት ይከናነቡ።+

14 እኔ ግን አንተን መጠባበቄን እቀጥላለሁ፤

በውዳሴ ላይ ውዳሴ አቀርብልሃለሁ።

15 አፌ ስለ ጽድቅህ ያወራል፤+

ከብዛታቸው የተነሳ ላውቃቸው* ባልችልም እንኳ

አንደበቴ ስለ ማዳን ሥራዎችህ ቀኑን ሙሉ ይናገራል።+

16 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣

መጥቼ ስለ ብርቱ ሥራዎችህ እናገራለሁ፤

ስለ አንተ ጽድቅ ብቻ እናገራለሁ።

17 አምላክ ሆይ፣ ከልጅነቴ ጀምሮ አስተምረኸኛል፤+

እኔም እስካሁን ድረስ ድንቅ ሥራዎችህን አስታውቃለሁ።+

18 አምላክ ሆይ፣ ሳረጅና ስሸብትም እንኳ አትጣለኝ።+

ለቀጣዩ ትውልድ ስለ ብርታትህ፣*

ገና ለሚመጡትም ሁሉ ስለ ኃያልነትህ ልናገር።+

19 አምላክ ሆይ፣ ጽድቅህ እጅግ ታላቅ ነው፤+

ታላላቅ ነገሮችን አከናውነሃል፤

አምላክ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?+

20 ብዙ ጭንቅና መከራ ብታሳየኝም እንኳ+

እንደገና እንዳንሰራራ አድርገኝ፤

ጥልቅ ከሆነው ምድር* አውጣኝ።+

21 ታላቅነቴ ገናና እንዲሆን አድርግ፤

ዙሪያዬንም ከበህ አጽናናኝ።

22 እኔም አምላኬ ሆይ፣ ከታማኝነትህ+ የተነሳ

በባለ አውታር መሣሪያ አወድስሃለሁ።

የእስራኤል ቅዱስ ሆይ፣

በበገና የውዳሴ መዝሙር እዘምርልሃለሁ።

23 ለአንተ የውዳሴ መዝሙር በምዘምርበት ጊዜ ከንፈሮቼ እልል ይላሉ፤+

ሕይወቴን አድነሃታልና።*+

24 ምላሴ ቀኑን ሙሉ ስለ ጽድቅህ ይናገራል፤*+

የእኔን መጥፋት የሚሹ ሰዎች ያፍራሉና፤ ደግሞም ይዋረዳሉ።+

ስለ ሰለሞን የተዘመረ መዝሙር።

72 አምላክ ሆይ፣ ፍርዶችህን ለንጉሡ ስጥ፤

ጽድቅህንም ለንጉሡ ልጅ አጎናጽፍ።+

 2 ስለ ሕዝብህ በጽድቅ ይሟገት፤

ለተቸገሩ አገልጋዮችህም ፍትሕ ያስፍን።+

 3 ተራሮች ለሕዝቡ ሰላም ያምጡ፤

ኮረብቶችም ጽድቅን ያስገኙ።

 4 በሕዝቡ መካከል ላሉት ችግረኞች ጥብቅና ይቁም፤*

የድሃውን ልጆች ያድን፤

ቀማኛውንም ይደምስሰው።+

 5 ፀሐይ ብርሃኗን እስከሰጠች፣

ጨረቃም በሰማይ ላይ እስካለች ድረስ፣

ከትውልድ እስከ ትውልድ+ አንተን ይፈሩሃል።

 6 እሱ በታጨደ ሣር ላይ እንደሚዘንብ ዝናብ፣

ምድርንም እንደሚያጠጣ ካፊያ ይወርዳል።+

 7 በእሱ ዘመን ጻድቅ ይለመልማል፤*+

ጨረቃም በምትኖርበት ዘመን ሁሉ ሰላም ይበዛል።+

 8 ከባሕር እስከ ባሕር ድረስ፣

ከወንዙም* እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ተገዢዎች ይኖሩታል።*+

 9 በበረሃ የሚኖሩ ሰዎች በፊቱ ይሰግዳሉ፤

ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ።+

10 የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት፣ ግብር ያመጣሉ።+

የሳባና የሴባ ነገሥታት፣ ስጦታ ይሰጣሉ።+

11 ነገሥታትም ሁሉ በፊቱ ይሰግዳሉ፤

ብሔራትም ሁሉ ያገለግሉታል።

12 እርዳታ ለማግኘት የሚጮኸውን ድሃ፣

እንዲሁም ችግረኛውንና ረዳት የሌለውን ሁሉ ይታደጋልና።

13 ለችግረኛውና ለድሃው ያዝናል፤

የድሆችንም ሕይወት* ያድናል።

14 ከጭቆናና ከግፍ ይታደጋቸዋል፤*

ደማቸውም በዓይኖቹ ፊት ክቡር ነው።

15 ረጅም ዘመን ይኑር፤ የሳባም ወርቅ ይሰጠው።+

ስለ እሱም ሁልጊዜ ጸሎት ይቅረብ፤

ቀኑንም ሙሉ ይባረክ።

16 በምድር ላይ እህል ይትረፈረፋል፤+

በተራሮችም አናት ላይ በብዛት ይኖራል።

የንጉሡም ፍሬ እንደ ሊባኖስ ዛፎች ይንዠረገጋል፤+

በከተሞቹም ውስጥ ሰዎች በምድር ላይ እንዳሉ ዕፀዋት ያብባሉ።+

17 ስሙ ለዘላለም ጸንቶ ይኑር፤+

ፀሐይም እስካለች ድረስ ስሙ ይግነን።

ሰዎች በእሱ አማካኝነት ለራሳቸው በረከት ያግኙ፤+

ብሔራት ሁሉ ደስተኛ ብለው ይጥሩት።

18 እሱ ብቻ አስደናቂ ነገሮችን የሚያደርገው፣+

የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ይወደስ።+

19 ክብራማ ስሙ ለዘላለም ይወደስ፤+

ምድርም ሁሉ በክብሩ ትሞላ።+

አሜን፣ አሜን።

20 የእሴይ ልጅ+ የዳዊት ጸሎቶች እዚህ ላይ አበቁ።

ሦስተኛ መጽሐፍ

(መዝሙር 73-89)

የአሳፍ+ ማህሌት።

73 አምላክ ለእስራኤል፣ ልባቸው ንጹሕ ለሆነ ሁሉ በእርግጥ ጥሩ ነው።+

 2 እኔ ግን እግሮቼ ከመንገድ ሊወጡ ተቃርበው ነበር፤

አዳልጦኝ ልወድቅ ምንም አልቀረኝም።+

 3 ክፉ ሰዎች ያላቸውን ሰላም በተመለከትኩ ጊዜ፣

እብሪተኛ በሆኑ ሰዎች* ቀንቼ ነበርና።+

 4 ሳይሠቃዩ ይሞታሉና፤

ሰውነታቸው ጤናማ* ነው።+

 5 እንደ ሌሎች ሰዎች ችግር አያጋጥማቸውም፤+

እንደ ሌሎች ሰዎችም መከራ አይደርስባቸውም።+

 6 ስለዚህ ትዕቢት የአንገት ጌጣቸው ነው፤+

ዓመፅም እንደ ልብስ ይሸፍናቸዋል።

 7 ከብልጽግናቸው* የተነሳ ዓይናቸው ፈጧል፤

ልባቸው ካሰበው በላይ አግኝተዋል።

 8 በሌሎች ላይ ያፌዛሉ፤ ክፉ ነገርም ይናገራሉ፤+

ሌሎችን ለመጨቆን በእብሪት ይዝታሉ።+

 9 የሰማይን ያህል ከፍ ያሉ ይመስል በእብሪት ይናገራሉ፤

በአንደበታቸው እንዳሻቸው እየተናገሩ በምድር ላይ ይንጎራደዳሉ።

10 በመሆኑም ሕዝቡ ወደ እነሱ ይሄዳል፤

ከእነሱ የተትረፈረፈ ውኃም ይጠጣል።

11 እነሱም “አምላክ እንዴት ያውቃል?+

ልዑሉ አምላክ በእርግጥ እውቀት አለው?” ይላሉ።

12 አዎ፣ ክፉዎች እንደዚህ ናቸው፤ ሁልጊዜ ሳይጨናነቁ ይኖራሉ።+

የሀብታቸውንም መጠን ያሳድጋሉ።+

13 በእርግጥም ልቤን ያነጻሁት፣

ንጹሕ መሆኔንም ለማሳየት እጄን የታጠብኩት በከንቱ ነው።+

14 ቀኑን ሙሉም ተጨነቅኩ፤+

በየማለዳውም ተቀጣሁ።+

15 እነዚህን ነገሮች ተናግሬ ቢሆን ኖሮ፣

ሕዝብህን* መክዳት ይሆንብኝ ነበር።

16 ይህን ለመረዳት በሞከርኩ ጊዜ፣

የሚያስጨንቅ ሆነብኝ፤

17 ይኸውም ወደ ታላቁ የአምላክ መቅደስ እስክገባና

የወደፊት ዕጣቸውን እስክረዳ ድረስ ነበር።

18 በእርግጥም በሚያዳልጥ መሬት ላይ ታስቀምጣቸዋለህ።+

ለጥፋት እንዲዳረጉም ትጥላቸዋለህ።+

19 እንዴት በቅጽበት ጠፉ!+

በአስደንጋጭ ሁኔታ ተደመሰሱ! የደረሰባቸው ጥፋት ቅጽበታዊ ነው!

20 ይሖዋ ሆይ፣ ሰው ከእንቅልፉ ሲነሳ እንደሚረሳው ሕልም፣

አንተም በምትነሳበት ጊዜ ምስላቸውን ታስወግዳለህ።*

21 ሆኖም ልቤ ተመሯል፤+

ውስጤንም* ውጋት ቀስፎ ይዞታል።

22 እኔም ማመዛዘን የማልችልና ማስተዋል የጎደለኝ ሆኜ ነበር፤

በአንተ ፊት ማሰብ እንደማይችል እንስሳ ሆንኩ።

23 አሁን ግን ሁልጊዜ ከአንተ ጋር ነኝ፤

አንተም ቀኝ እጄን ይዘሃል።+

24 በምክርህ ትመራኛለህ፤+

በኋላም ክብር ታጎናጽፈኛለህ።+

25 በሰማይ ማን አለኝ?

በምድርም ላይ ከአንተ ሌላ የምሻው የለም።+

26 ሰውነቴም ሆነ ልቤ ሊዝል ይችላል፤

አምላክ ግን ለዘላለም የልቤ ዓለትና ድርሻዬ ነው።+

27 ከአንተ የሚርቁ በእርግጥ ይጠፋሉ።

አንተን በመተው ብልሹ ምግባር የሚፈጽሙትን* ሁሉ ትደመስሳቸዋለህ።*+

28 እኔ ግን ወደ አምላክ መቅረብ ይበጀኛል።+

ሥራዎቹን ሁሉ እንዳውጅ+

ሉዓላዊውን ጌታ ይሖዋን መጠጊያዬ አድርጌዋለሁ።

ማስኪል።* የአሳፍ+ መዝሙር።

74 አምላክ ሆይ፣ ለዘላለም የጣልከን ለምንድን ነው?+

በመስክህ በተሰማራው መንጋ ላይ ቁጣህ የነደደው* ለምንድን ነው?+

 2 ከረጅም ዘመን በፊት የራስህ ያደረግከውን ሕዝብ፣*+

ርስትህ አድርገህ የዋጀኸውን ነገድ አስታውስ።+

የኖርክበትን የጽዮን ተራራ+ አስብ።

 3 ለዘለቄታው ወደፈራረሰው ቦታ አቅና።+

ጠላት በቅዱሱ ስፍራ ያለውን ነገር ሁሉ አጥፍቷል።+

 4 ጠላቶችህ በመሰብሰቢያ ቦታህ* ውስጥ በድል አድራጊነት ጮኹ።+

በዚያም የራሳቸውን ዓርማ ምልክት አድርገው አቆሙ።

 5 መጥረቢያቸውን ይዘው ጥቅጥቅ ያሉ ደኖችን እንደሚጨፈጭፉ ሰዎች ናቸው።

 6 በቅርጻ ቅርጾች ያጌጡትን+ ግድግዳዎች በጠቅላላ በመጥረቢያና በብረት ዘንግ አፈራረሱ።

 7 መቅደስህን በእሳት አቃጠሉ።+

ስምህ የተጠራበትን የማደሪያ ድንኳን መሬት ላይ ጥለው አረከሱት።

 8 እነሱም ሆኑ ዘሮቻቸው በልባቸው

“በምድሪቱ ላይ ያሉት የአምላክ መሰብሰቢያ* ቦታዎች በሙሉ ይቃጠሉ” ብለዋል።

 9 የምናያቸው ምልክቶች የሉም፤

አንድም የቀረ ነቢይ የለም፤

ደግሞም ይህ እስከ መቼ እንደሚቀጥል ከእኛ መካከል የሚያውቅ የለም።

10 አምላክ ሆይ፣ ባላጋራ የሚሳለቀው እስከ መቼ ነው?+

ጠላት ስምህን ለዘላለም እያቃለለ ይኖራል?+

11 እጅህን ይኸውም ቀኝ እጅህን የሰበሰብከው ለምንድን ነው?+

እጅህን ከጉያህ* አውጥተህ አጥፋቸው።

12 ይሁንና በምድር ላይ ታላቅ የማዳን ሥራ የሚፈጽመው አምላክ

ከጥንት ጀምሮ ንጉሤ ነው።+

13 በብርታትህ ባሕሩን አናወጥክ፤+

በውኃ ውስጥ ያሉትን ግዙፍ የባሕር ፍጥረታት ራስ ሰባበርክ።

14 የሌዋታንን* ራሶች አደቀቅክ፤

በበረሃ ለሚኖሩት ሰዎች ምግብ አድርገህ ሰጠሃቸው።

15 ለምንጮችና ለጅረቶች መውጫ ያበጀኸው አንተ ነህ፤+

ሳያቋርጡ የሚፈስሱትን ወንዞች አደረቅክ።+

16 ቀኑ የአንተ ነው፤ ሌሊቱም የአንተ ነው።

ብርሃንንና ፀሐይን* ሠራህ።+

17 የምድርን ወሰኖች ሁሉ ደነገግክ፤+

በጋና ክረምት እንዲፈራረቁ አደረግክ።+

18 ይሖዋ ሆይ፣ ጠላት እንደተሳለቀ፣

ሞኝ ሕዝብ ስምህን እንዴት እንዳቃለለ አስብ።+

19 የዋኖስህን ሕይወት* ለዱር አራዊት አትስጥ።

የተጎሳቆለውን ሕዝብህን ሕይወት ለዘላለም አትርሳ።

20 ቃል ኪዳንህን አስብ፤

በምድሪቱ ላይ ያሉት ጨለማ ቦታዎች የዓመፅ መናኸሪያ ሆነዋልና።

21 የተደቆሰው ሰው አዝኖ አይመለስ፤+

ችግረኛውና ድሃው ስምህን ያወድስ።+

22 አምላክ ሆይ፣ ተነስ፤ ደግሞም ለራስህ ተሟገት።

ሞኝ ሰው ቀኑን ሙሉ እንዴት እንደሚሳለቅብህ አስብ።+

23 ጠላቶችህ የሚሉትን አትርሳ።

አንተን የሚዳፈሩ ሰዎች የሚያሰሙት ሁካታ ያለማቋረጥ ወደ ላይ እየወጣ ነው።

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። “ጥፋት አታምጣ” በተባለው ቅኝት የሚዜም ማህሌት። የአሳፍ+ መዝሙር።

75 ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ አምላክ ሆይ፣ ምስጋና እናቀርብልሃለን፤

ስምህ ከእኛ ጋር ነው፤+

ሰዎችም ድንቅ ሥራዎችህን ያውጃሉ።

 2 አንተ እንዲህ ትላለህ፦ “ጊዜ ስወስን

በትክክል እፈርዳለሁ።

 3 ምድርና በላይዋ የሚኖሩ ሁሉ ሲቀልጡ፣

ምሰሶዎቿን አጽንቼ ያቆምኩት እኔ ነኝ።” (ሴላ)

 4 ጉራቸውን ለሚነዙት “ጉራ አትንዙ” እላለሁ፤

ክፉዎቹንም እንዲህ እላለሁ፦ “ኃይላችሁን* ከፍ ከፍ አታድርጉ።

 5 ኃይላችሁን* ወደ ላይ ከፍ አታድርጉ፤

ወይም በትዕቢት አትናገሩ።

 6 ክብር ከምሥራቅም ሆነ ከምዕራብ

ወይም ከደቡብ አይመጣምና።

 7 አምላክ ፈራጅ ነውና።+

አንዱን ያዋርዳል፤ ሌላውን ደግሞ ከፍ ከፍ ያደርጋል።+

 8 በይሖዋ እጅ ጽዋ አለና፤+

የወይን ጠጁ አረፋ ያወጣል፤ ደግሞም ሙሉ በሙሉ የተደባለቀ ነው።

እሱ በእርግጥ ያፈሰዋል፤

በምድርም ላይ ያሉ ክፉዎች ሁሉ ከነአተላው ይጨልጡታል።”+

 9 እኔ ግን ይህን ለዘላለም አውጃለሁ፤

ለያዕቆብ አምላክ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።

10 እሱ እንዲህ ይላልና፦ “የክፉዎችን ኃይል* በሙሉ እቆርጣለሁ፤

የጻድቅ ሰው ኃይል ግን ከፍ ከፍ ይላል።”

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በባለ አውታር መሣሪያዎች የሚታጀብ። የአሳፍ+ ማህሌት። መዝሙር።

76 አምላክ በይሁዳ የታወቀ ነው፤+

ስሙም በእስራኤል ታላቅ ነው።+

 2 መጠለያው በሳሌም+ ነው፤

መኖሪያውም በጽዮን ነው።+

 3 በዚያም የሚንበለበሉትን ፍላጻዎች፣

ጋሻን፣ ሰይፍንና የጦር መሣሪያዎችን ሰባበረ።+ (ሴላ)

 4 አንተ ደምቀህ ታበራለህ፤*

አዳኝ አራዊት ከሚኖሩባቸው ተራሮች ይልቅ ታላቅ ግርማ ተጎናጽፈሃል።

 5 ልበ ሙሉ የሆኑት ሰዎች ተዘርፈዋል።+

እንቅልፍ ጥሏቸዋል፤

ተዋጊዎቹ በሙሉ መከላከል የሚችሉበት ኃይል አልነበራቸውም።+

 6 የያዕቆብ አምላክ ሆይ፣ ከተግሣጽህ የተነሳ

ባለ ሠረገላውም ሆነ ፈረሱ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወስዷቸዋል።+

 7 አንተ ብቻ እጅግ የምትፈራ ነህ።+

ኃይለኛ ቁጣህን ማን ሊቋቋም ይችላል?+

 8 አንተ ከሰማይ ፍርድ ተናገርክ፤+

ምድር ፈርታ ዝም አለች፤+

 9 ይህም የሆነው አምላክ በምድር ላይ የሚኖሩትን የዋሆች ሁሉ ለማዳን+

ፍርድ ሊያስፈጽም በተነሳበት ጊዜ ነው። (ሴላ)

10 የሰው ቁጣ ለአንተ ውዳሴ ያመጣልና፤+

በቀረው ቁጣቸው ራስህን ታስጌጣለህ።

11 ለአምላካችሁ ለይሖዋ ተሳሉ፤ ስእለታችሁንም ፈጽሙ፤+

በዙሪያው ያሉ ሁሉ በፍርሃት ስጦታቸውን ያምጡ።+

12 እሱ የመሪዎችን ኩራት* ያስወግዳል፤

በምድር ነገሥታት ላይ ፍርሃት ያሳድራል።

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በየዱቱን።* የአሳፍ+ መዝሙር። ማህሌት።

77 ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ አምላክ እጮኻለሁ፤

ወደ አምላክ እጮኻለሁ፤ እሱም ይሰማኛል።+

 2 በጭንቀት በተዋጥኩ ቀን ይሖዋን እፈልጋለሁ።+

በሌሊት እጆቼ ያለምንም ፋታ ወደ እሱ እንደተዘረጉ ናቸው፤

ልጽናና አልቻልኩም።*

 3 አምላክን ሳስታውስ እቃትታለሁ፤+

ተጨንቄአለሁ፤ ኃይሌም ከዳኝ።*+ (ሴላ)

 4 የዓይኔ ቆብ እንዳይከደን ያዝከው፤

በጣም ተረብሻለሁ፤ መናገርም አልችልም።

 5 የድሮውን ጊዜ መለስ ብዬ አሰብኩ፤+

የጥንቶቹን ዓመታት አስታወስኩ።

 6 መዝሙሬን* በሌሊት አስታውሳለሁ፤+

በልቤ አወጣለሁ አወርዳለሁ፤+

በጥሞና እመረምራለሁ።*

 7 ይሖዋ ለዘላለም ይጥለናል?+

ዳግመኛስ ሞገስ አያሳየንም?+

 8 ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ተቋርጧል?

የተስፋ ቃሉስ ከትውልድ እስከ ትውልድ ከንቱ ሆኖ ይቀራል?

 9 አምላክ ሞገሱን ማሳየት ረስቷል?+

ወይስ ቁጣው ምሕረት ከማሳየት እንዲቆጠብ አድርጎታል? (ሴላ)

10 “እኔን የሚያስጨንቀኝ* ይህ ነው፦+

ልዑሉ አምላክ ለእኛ ያለውን አመለካከት* ለውጧል” እያልኩ ልኖር ነው?

11 ያህ ያከናወናቸውን ሥራዎች አስታውሳለሁ፤

ጥንት የፈጸምካቸውን ድንቅ ተግባሮች አስታውሳለሁ።

12 በሥራዎችህም ሁሉ ላይ አሰላስላለሁ፤

ያከናወንካቸውንም ነገሮች አውጠነጥናለሁ።+

13 አምላክ ሆይ፣ መንገዶችህ ቅዱስ ናቸው።

አምላክ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ታላቅ አምላክ ማን ነው?+

14 አንተ ድንቅ ነገሮችን የምታከናውን እውነተኛ አምላክ ነህ።+

ብርታትህን ለሕዝቦች ገልጠሃል።+

15 በኃይልህ* ሕዝብህን ይኸውም

የያዕቆብንና የዮሴፍን ልጆች ታድገሃል።*+ (ሴላ)

16 አምላክ ሆይ፣ ውኃዎቹ አዩህ፤

ውኃዎቹ ሲያዩህ ተረበሹ።+

ጥልቅ ውኃዎቹም ተናወጡ።

17 ደመናት ውኃ አዘነቡ።

በደመና የተሸፈኑት ሰማያት አንጎደጎዱ፤

ፍላጻዎችህም እዚህም እዚያም ተወነጨፉ።+

18 የነጎድጓድህ ድምፅ+ እንደ ሠረገላ ድምፅ ነበር፤

የመብረቅ ብልጭታዎች በዓለም* ላይ አበሩ፤+

ምድር ተናወጠች፤ ደግሞም ተንቀጠቀጠች።+

19 መንገድህ በባሕር ውስጥ ነበር፤+

ጎዳናህም በብዙ ውኃዎች ውስጥ ነበር፤

ይሁንና የእግርህ ዱካ ሊገኝ አልቻለም።

20 ሕዝብህን በሙሴና በአሮን እጅ+

እንደ መንጋ መራህ።+

ማስኪል።* የአሳፍ+ መዝሙር።

78 ሕዝቤ ሆይ፣ ሕጌን* አዳምጥ፤

ከአፌ ወደሚወጣው ቃል ጆሮህን አዘንብል።

 2 አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ።

በጥንት ዘመን የተነገሩትን እንቆቅልሾች አቀርባለሁ።+

 3 የሰማናቸውንና ያወቅናቸውን ነገሮች፣

አባቶቻችን ለእኛ የተረኩልንን፣+

 4 ከልጆቻቸው አንደብቀውም፤

ይሖዋ ያከናወናቸውን የሚያስመሰግኑ ሥራዎችና ብርታቱን፣+

ደግሞም የሠራቸውን አስደናቂ ነገሮች+

ለመጪው ትውልድ እንተርካለን።+

 5 እሱ ለያዕቆብ ማሳሰቢያ ሰጠ፤

በእስራኤልም ሕግ ደነገገ፤

እነዚህን ነገሮች ለልጆቻቸው እንዲያሳውቁ

አባቶቻችንን አዘዛቸው፤+

 6 ይህም ቀጣዩ ትውልድ፣

ገና የሚወለዱት ልጆች እነዚህን ነገሮች እንዲያውቁ ነው።+

እነሱም በተራቸው ለልጆቻቸው ይተርካሉ።+

 7 በዚህ ጊዜ እነሱ ትምክህታቸውን በአምላክ ላይ ይጥላሉ።

የአምላክን ሥራዎች አይረሱም፤+

ይልቁንም ትእዛዛቱን ይጠብቃሉ።+

 8 ያን ጊዜ እንደ አባቶቻቸው

እልኸኛና ዓመፀኛ ትውልድ፣+

ደግሞም ልቡ የሚወላውልና*+

መንፈሱ ለአምላክ ታማኝ ያልሆነ ትውልድ አይሆኑም።

 9 ኤፍሬማውያን ቀስት የታጠቁ ነበሩ፤

ይሁንና በጦርነት ቀን ወደ ኋላ አፈገፈጉ።

10 የአምላክን ቃል ኪዳን አልጠበቁም፤+

በሕጉም ለመመላለስ ፈቃደኛ አልሆኑም።+

11 በተጨማሪም ያደረጋቸውን ነገሮች፣

ያሳያቸውን ድንቅ ሥራዎች ረሱ።+

12 በአባቶቻቸው ፊት በግብፅ አገር፣

በጾዓን+ ምድር አስደናቂ ነገሮች አከናውኖ ነበር።+

13 በዚያ አቋርጠው እንዲሄዱ ባሕሩን ከፈለው፤

ውኃዎቹንም እንደ ግድብ አቆመ።*+

14 ቀን በደመና፣ ሌሊቱን ሙሉ ደግሞ

በእሳት ብርሃን መራቸው።+

15 በምድረ በዳ ዓለቶችን ሰነጠቀ፤

ከጥልቅ ውኃ የሚጠጡ ያህል እስኪረኩ ድረስ አጠጣቸው።+

16 ከቋጥኝ ውስጥ ወራጅ ውኃ አወጣ፤

ውኃዎችም እንደ ወንዝ እንዲፈስሱ አደረገ።+

17 እነሱ ግን በበረሃ፣ በልዑሉ አምላክ ላይ በማመፅ

በእሱ ላይ ኃጢአት መሥራታቸውን ቀጠሉ፤+

18 እንዲሁም የተመኙትን* ምግብ እንዲሰጣቸው በመጠየቅ

አምላክን በልባቸው ተገዳደሩት።*+

19 “አምላክ በምድረ በዳ ማዕድ ማዘጋጀት ይችላል?” በማለት

በአምላክ ላይ አጉረመረሙ።+

20 እነሆ፣ ውኃ እንዲፈስና ጅረቶች እንዲንዶለዶሉ

ዓለትን መታ።+

ይሁንና “ዳቦስ ሊሰጠን ይችላል?

ወይስ ለሕዝቡ ሥጋ ሊያቀርብ ይችላል?” አሉ።+

21 ይሖዋ በሰማቸው ጊዜ እጅግ ተቆጣ፤+

በያዕቆብ ላይ እሳት+ ተቀጣጠለ፤

በእስራኤልም ላይ ቁጣው ነደደ፤+

22 ምክንያቱም በአምላክ ላይ እምነት አልጣሉም፤+

እነሱን የማዳን ችሎታ እንዳለው አላመኑም።

23 ስለዚህ በላይ ያሉትን በደመና የተሸፈኑ ሰማያት አዘዘ፤

የሰማይንም በሮች ከፈተ።

24 የሚበሉት መና አዘነበላቸው፤

የሰማይንም እህል ሰጣቸው።+

25 ሰዎች የኃያላንን*+ ምግብ በሉ፤

እስኪጠግቡ ድረስ እንዲበሉ በቂ ምግብ አቀረበላቸው።+

26 የምሥራቁን ነፋስ በሰማይ አስነሳ፤

በኃይሉም የደቡብ ነፋስ እንዲነፍስ አደረገ።+

27 ሥጋንም እንደ አፈር፣

ወፎችንም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ አዘነበላቸው።

28 በሰፈሩ መካከል፣

በድንኳኖቹም ሁሉ ዙሪያ እንዲወድቁ አደረገ።

29 እነሱም በሉ፤ ከልክ በላይም ጠገቡ፤

የተመኙትን ነገር ሰጣቸው።+

30 ሆኖም ምኞታቸውን ሙሉ በሙሉ ከማርካታቸው በፊት፣

ምግባቸው ገና በአፋቸው ውስጥ እያለ

31 የአምላክ ቁጣ በእነሱ ላይ ነደደ።+

ኃያላን ሰዎቻቸውን ገደለ፤+

የእስራኤልን ወጣቶች ጣለ።

32 ይህም ሆኖ በኃጢአታቸው ገፉበት፤+

አስደናቂ በሆኑ ሥራዎቹም አላመኑም።+

33 ስለዚህ ዘመናቸው እንደ እስትንፋስ እንዲያበቃ፣+

ዕድሜያቸውም በድንገተኛ ሽብር እንዲያከትም አደረገ።

34 ሆኖም በገደላቸው ቁጥር እሱን ይሹ ነበር፤+

ተመልሰው አምላክን ይፈልጉ ነበር፤

35 ይህን የሚያደርጉት አምላክ ዓለታቸው እንደሆነ፣+

ልዑሉ አምላክም እንደሚዋጃቸው* በማስታወስ ነበር።+

36 እነሱ ግን በአፋቸው ሊያታልሉት ሞከሩ፤

በምላሳቸውም ዋሹት።

37 ልባቸው ለእሱ የጸና አልነበረም፤+

ለቃል ኪዳኑም ታማኞች አልነበሩም።+

38 እሱ ግን መሐሪ ነው፤+

በደላቸውን ይቅር ይል* ነበር፤ ደግሞም አላጠፋቸውም።+

ቁጣውን ሁሉ ከመቀስቀስ ይልቅ

ብዙ ጊዜ ስሜቱን ይገታ ነበር።+

39 ነፍሶ ዳግመኛ የማይመለስ ነፋስ፣*

ሥጋ መሆናቸውንም አስታውሷልና።+

40 በምድረ በዳ ስንት ጊዜ በእሱ ላይ ዓመፁ!+

በበረሃ ሳሉም ብዙ ጊዜ ስሜቱን ጎዱት!+

41 ደግመው ደጋግመው አምላክን ተፈታተኑት፤+

የእስራኤልንም ቅዱስ እጅግ አሳዘኑት።*

42 እነሱን ከጠላት የታደገበትን* ቀን፣

ኃይሉንም* አላስታወሱም፤+

43 በግብፅ አስደናቂ ምልክቶችን፣

በጾዓን ምድርም ተአምራቱን እንዴት እንዳሳየ አላሰቡም፤+

44 እንዲሁም ከጅረቶቻቸው መጠጣት እንዳይችሉ

የአባይን የመስኖ ቦዮች እንዴት ወደ ደም እንደለወጠ ዘነጉ።+

45 ይበሏቸው ዘንድ የተናካሽ ዝንቦችን መንጋ ሰደደባቸው፤+

ያጠፏቸውም ዘንድ እንቁራሪቶችን ላከባቸው።+

46 ሰብላቸውን ለማይጠግብ አንበጣ፣

የድካማቸውን ፍሬ ለአንበጣ መንጋ ሰጠ።+

47 የወይን ተክላቸውን በበረዶ፣

የሾላ ዛፎቻቸውንም በበረዶ ድንጋይ አጠፋ።+

48 የጋማ ከብቶቻቸውን ለበረዶ፣+

መንጎቻቸውንም ለመብረቅ ብልጭታ* ዳረገ።

49 የሚነድ ቁጣውን፣

ንዴቱን፣ መዓቱንና መቅሰፍቱን

እንዲሁም ጥፋት የሚያመጡ የመላእክት ሠራዊትን ላከባቸው።

50 ለቁጣው መንገድ ጠረገ።

ከሞት አላተረፋቸውም፤*

ለቸነፈርም አሳልፎ ሰጣቸው።

51 በመጨረሻም የግብፅን በኩሮች በሙሉ፣

በካም ድንኳኖች ውስጥ ከሚገኙትም መካከል የፍሬያቸው መጀመሪያ የሆኑትን መታ።+

52 ከዚያም ሕዝቡን እንደ በጎች እንዲወጡ አደረገ፤

በምድረ በዳም እንደ መንጋ መራቸው።+

53  በአስተማማኝ ሁኔታ መራቸው፤

አንዳች ፍርሃትም አልተሰማቸውም፤+

ባሕሩም ጠላቶቻቸውን ዋጠ።+

54 ደግሞም ቅዱስ ወደሆነው ምድሩ፣

ቀኝ እጁ የራሱ ወዳደረገው ወደዚህ ተራራማ ክልል አመጣቸው።+

55 ብሔራቱን ከፊታቸው አባረረ፤+

በመለኪያ ገመድም ርስት አከፋፈላቸው፤+

የእስራኤልን ነገዶች በቤቶቻቸው እንዲኖሩ አደረገ።+

56 እነሱ ግን ልዑሉን አምላክ ተገዳደሩት፤* በእሱም ላይ ዓመፁ፤+

ማሳሰቢያዎቹን ችላ አሉ።+

57 በተጨማሪም ጀርባቸውን ሰጡ፤ እንደ አባቶቻቸውም ከሃዲዎች ሆኑ።+

ጅማቱ እንደረገበ ደጋን እምነት የማይጣልባቸው ነበሩ።+

58 ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎቻቸው ብዙ ጊዜ አሳዘኑት፤+

በተቀረጹ ምስሎቻቸውም ለቁጣ* አነሳሱት።+

59 አምላክ ሰምቶ በጣም ተቆጣ፤+

በመሆኑም እስራኤልን እርግፍ አድርጎ ተወው።

60 በመጨረሻም በሴሎ የሚገኘውን የማደሪያ ድንኳን፣

በሰው ልጆች መካከል ይኖርበት የነበረውን ድንኳን ተወው።+

61 የብርታቱ ምልክት ተማርኮ እንዲወሰድ ፈቀደ፤

ግርማ ሞገሱን በጠላት እጅ አሳልፎ ሰጠ።+

62 ሕዝቡን ለሰይፍ አሳልፎ ሰጠ፤+

በርስቱም ላይ እጅግ ተቆጣ።

63 ወጣቶቹን እሳት በላቸው፤

ለድንግሎቹም የሠርግ ዘፈን አልተዘፈነላቸውም።*

64 ካህናቱ በሰይፍ ወደቁ፤+

የገዛ መበለቶቻቸውም አላለቀሱላቸውም።+

65 ከዚያም ይሖዋ፣ የወይን ጠጅ ስካሩ እንደለቀቀው ኃያል ሰው

ከእንቅልፍ እንደነቃ ሆኖ ተነሳ።+

66 ጠላቶቹንም አሳዶ ወደ ኋላ መለሳቸው፤+

ለዘለቄታው ውርደት አከናነባቸው።

67 የዮሴፍን ድንኳን ናቀ፤

የኤፍሬምን ነገድ አልመረጠም።

68 ከዚህ ይልቅ የይሁዳን ነገድ፣

የሚወደውን የጽዮንን ተራራ+ መረጠ።+

69 መቅደሱን እንደ ሰማያት ጽኑ አድርጎ ሠራው፤*+

ለዘላለምም እንደመሠረታት ምድር አድርጎ ገነባው።+

70 አገልጋዩን ዳዊትን መረጠ፤+

ከበጎች ጉረኖ ወስዶ፣+

71 የሚያጠቡ በጎችን ከመጠበቅም አንስቶ

በሕዝቡ በያዕቆብ፣ በርስቱም በእስራኤል ላይ

እረኛ እንዲሆን ሾመው።+

72 እሱም በንጹሕ ልብ* ጠበቃቸው፤+

በተካኑ እጆቹም መራቸው።+

የአሳፍ+ ማህሌት።

79 አምላክ ሆይ፣ ብሔራት ርስትህን+ ወረውታል፤

ቅዱስ መቅደስህንም አርክሰዋል፤+

ኢየሩሳሌምን የፍርስራሽ ክምር አድርገዋታል።+

 2 የአገልጋዮችህን ሬሳ ለሰማይ ወፎች፣

የታማኝ አገልጋዮችህንም ሥጋ ለምድር አራዊት ምግብ አድርገው ሰጥተዋል።+

 3 ደማቸውን በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውኃ አፈሰሱ፤

እነሱንም የሚቀብር አንድም ሰው አልተረፈም።+

 4 በጎረቤቶቻችን ዘንድ መሳለቂያ ሆንን፤+

በዙሪያችን ያሉትም ያፌዙብናል፤ ደግሞም ይዘብቱብናል።

 5 ይሖዋ ሆይ፣ የምትቆጣው እስከ መቼ ነው? ለዘላለም?+

ቁጣህስ እንደ እሳት የሚነደው እስከ መቼ ነው?+

 6 አንተን በማያውቁ ብሔራት፣

ስምህንም በማይጠሩ መንግሥታት ላይ ቁጣህን አፍስስ።+

 7 ያዕቆብን በልተውታልና፤

የትውልድ አገሩንም አውድመዋል።+

 8 አባቶቻችን በሠሩት ስህተት እኛን ተጠያቂ አታድርገን።+

ፈጥነህ ምሕረት አድርግልን፤+

በጭንቀት ተውጠናልና።

 9 አዳኛችን የሆንክ አምላክ ሆይ፣

ለታላቁ ስምህ ስትል እርዳን፤+

ለስምህም ስትል ታደገን፤ ኃጢአታችንንም ይቅር በለን።*+

10 ብሔራት “አምላካቸው የት አለ?” ለምን ይበሉ?+

በፈሰሰው የአገልጋዮችህ ደም የተነሳ የሚወሰድባቸውን የበቀል እርምጃ፣

ዓይናችን እያየ ብሔራት ይወቁት።+

11 እስረኛው የሚያሰማውን ሲቃ ስማ።+

ሞት የተፈረደባቸውን* በታላቅ ኃይልህ* አድናቸው።*+

12 ይሖዋ ሆይ፣ ጎረቤቶቻችን በአንተ ላይ በመሳለቃቸው+

ሰባት እጥፍ አድርገህ ብድራታቸውን ክፈላቸው።+

13 በዚህ ጊዜ እኛ ሕዝቦችህ፣ በመስክህ ያሰማራኸን መንጋ፣+

ለዘላለም ምስጋና እናቀርብልሃለን፤

ከትውልድ እስከ ትውልድም ውዳሴህን እናሰማለን።+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ “በአበቦች” የሚዘመር። ማስታወሻ። የአሳፍ+ መዝሙር። ማህሌት።

80 ዮሴፍን እንደ መንጋ የምትመራ

የእስራኤል እረኛ ሆይ፣+ አዳምጥ።

ከኪሩቤል በላይ* በዙፋን የምትቀመጥ ሆይ፣+

ብርሃን አብራ።*

 2 በኤፍሬም፣ በቢንያምና በምናሴ ፊት

ኃያልነትህን አሳይ፤+

መጥተህም አድነን።+

 3 አምላክ ሆይ፣ ወደ ቀድሞው ሁኔታችን መልሰን፤+

እንድንም ዘንድ ፊትህን በእኛ ላይ አብራ።+

 4 የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ ሕዝቦችህ የሚያቀርቡትን ጸሎት የምትጠላው* እስከ መቼ ነው?+

 5 እንባን እንደ ምግብ ትመግባቸዋለህ፤

ደግሞም እንባ ትግታቸዋለህ።

 6 ለጎረቤቶቻችን የጠብ ምክንያት አደረግከን፤

ጠላቶቻችን እንዳሻቸው ያላግጡብናል።+

 7 የሠራዊት አምላክ ሆይ፣ ወደ ቀድሞው ሁኔታችን መልሰን፤

እንድንም ዘንድ ፊትህን በእኛ ላይ አብራ።+

 8 የወይን ተክል+ ከግብፅ እንድትወጣ አደረግክ።

ብሔራትን አባረህ እሷን ተከልክ።+

 9 መሬቱን መነጠርክላት፤

እሷም ሥር ሰዳ በምድሪቱ ላይ ተንሰራፋች።+

10 ተራሮች በጥላዋ፣

የአምላክ አርዘ ሊባኖሶችም በቅርንጫፎቿ ተሸፈኑ።

11 ቅርንጫፎቿ እስከ ባሕሩ፣

ቀንበጦቿም እስከ ወንዙ* ድረስ ተዘረጉ።+

12 በዚያ የሚያልፉ ሁሉ ፍሬዋን እንዲቀጥፉ፣+

የወይን እርሻዋን የድንጋይ ቅጥሮች ያፈረስከው ለምንድን ነው?+

13 ከጫካ የወጡ የዱር አሳማዎች ያወድሟታል፤

በሜዳ ያሉ የዱር አራዊትም ይበሏታል።+

14 የሠራዊት አምላክ ሆይ፣ እባክህ ተመለስ።

ከሰማይ ወደ ታች እይ፤ ተመልከትም!

ይህችን የወይን ተክል ተንከባከባት፤+

15 ቀኝ እጅህ የተከላትን ግንድ*+ በእንክብካቤ ያዛት፤

ለራስህ ስትል ያጠነከርከውንም ልጅ* ተመልከት።+

16 እሷ ተቆርጣ በእሳት ተቃጥላለች።+

ሕዝቡ ከተግሣጽህ* የተነሳ ይጠፋል።

17 እጅህ በቀኝህ ላለው ሰው፣

ለራስህም ስትል ብርቱ ላደረግከው የሰው ልጅ ድጋፍ ትስጥ።+

18 እኛም ከአንተ አንርቅም።

ስምህን መጥራት እንድንችል በሕይወት አኑረን።

19 የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ ወደ ቀድሞው ሁኔታችን መልሰን፤

እንድንም ዘንድ ፊትህን በእኛ ላይ አብራ።+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በጊቲት።* የአሳፍ+ መዝሙር።

81 ብርታታችን ለሆነው አምላክ+ እልል በሉ።

ለያዕቆብ አምላክ በድል አድራጊነት ስሜት ጩኹ።

 2 ሙዚቃውን መጫወት ጀምሩ፤ አታሞም ምቱ፤

ደስ የሚያሰኘውን በገና ከባለ አውታር መሣሪያ ጋር ተጫወቱ።

 3 አዲስ ጨረቃ በምትታይበት፣

ሙሉ ጨረቃም ወጥታ በዓል በምናከብርበት ዕለት+ ቀንደ መለከት ንፉ።+

 4 ይህ ለእስራኤል የተሰጠ ድንጋጌ፣

የያዕቆብም አምላክ ያስተላለፈው ውሳኔ ነውና።+

 5 በግብፅ ምድር ላይ ባለፈ ጊዜ፣+

ይህን ለዮሴፍ ማሳሰቢያ አድርጎ ሰጠው።+

እኔም የማላውቀውን ድምፅ* ሰማሁ፦

 6 “ሸክሙን ከትከሻው ላይ አነሳሁለት፤+

እጆቹ ቅርጫት ከመያዝ አረፉ።

 7 በጨነቀህ ጊዜ ጠራኸኝ፤ እኔም ታደግኩህ፤+

ከነጎድጓዳማው ደመና* መለስኩልህ።+

የመሪባ* ውኃዎች ባሉበት ስፍራ ፈተንኩህ።+ (ሴላ)

 8 ሕዝቤ ሆይ፣ ስማኝ፤ እኔም እመሠክርብሃለሁ።

እስራኤል ሆይ፣ ምነው ብታዳምጠኝ!+

 9 በመካከልህ እንግዳ አምላክ አይኖርም፤

ለባዕድ አምላክም አትሰግድም።+

10 ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ፣

እኔ ይሖዋ አምላክህ ነኝ።+

አፍህን በሰፊው ክፈት፤ እኔም በምግብ እሞላዋለሁ።+

11 ሕዝቤ ግን ድምፄን አልሰማም፤

እስራኤል ለእኔ አይገዛም።+

12 በመሆኑም እልኸኛ ልባቸውን እንዲከተሉ ተውኳቸው፤

ትክክል መስሎ የታያቸውን አደረጉ።*+

13 ምነው ሕዝቤ ቢያዳምጠኝ ኖሮ!+

ምነው እስራኤል በመንገዴ ቢመላለስ ኖሮ!+

14 ጠላቶቻቸውን ወዲያውኑ ባንበረከክኋቸው፣

እጄን በባላጋራዎቻቸው ላይ በሰነዘርኩ ነበር።+

15 ይሖዋን የሚጠሉ በፊቱ ይሸማቀቃሉ፤

የሚደርስባቸውም ነገር* ዘላለማዊ ነው።

16 እሱ ግን ምርጡን ስንዴ* ይመግባችኋል፤*+

ከዓለት በሚገኝ ማርም ያጠግባችኋል።”+

የአሳፍ+ ማህሌት።

82 አምላክ በመለኮታዊ ጉባኤ መካከል ይሰየማል፤*+

በአማልክት* መካከል ይፈርዳል፦+

 2 “ፍትሕ የምታዛቡት እስከ መቼ ነው?+

ለክፉዎችስ የምታዳሉት እስከ መቼ ነው?+ (ሴላ)

 3 ለችግረኛውና አባት ለሌለው ተሟገቱ።*+

ረዳት የሌለውና ምስኪኑ ፍትሕ እንዲያገኝ አድርጉ።+

 4 ችግረኛውንና ድሃውን ታደጉ፤

ከክፉዎችም እጅ አድኗቸው።”

 5 ፈራጆቹ ምንም አያውቁም፤ ደግሞም አያስተውሉም፤+

በጨለማ ውስጥ ይመላለሳሉ፤

የምድር መሠረቶች ሁሉ ተናግተዋል።+

 6 “እኔም እንዲህ አልኩ፦ ‘እናንተ አማልክት* ናችሁ፤+

ሁላችሁም የልዑሉ አምላክ ልጆች ናችሁ።

 7 ይሁንና እናንተም ሰው እንደሚሞተው ትሞታላችሁ፤+

ደግሞም እንደ ማንኛውም ገዢ ትወድቃላችሁ!’”+

 8 አምላክ ሆይ፣ ተነስ፤ በምድርም ላይ ፍረድ፤+

ብሔራት ሁሉ የአንተ ናቸውና።

መዝሙር። የአሳፍ+ ማህሌት።

83 አምላክ ሆይ፣ ዝም አትበል፤+

አምላክ ሆይ፣ ጸጥ አትበል፤* ደግሞም ጭጭ አትበል።

 2 እነሆ፣ ጠላቶችህ እየደነፉ ነውና፤+

አንተን የሚጠሉ በእብሪት ይመላለሳሉ።*

 3 በስውር በሕዝቦችህ ላይ የተንኮል ሴራ ይሸርባሉ፤

በውድ አገልጋዮችህ* ላይ ይዶልታሉ።

 4 “የእስራኤል ስም ተረስቶ እንዲቀር፣

ኑ፣ ሕዝቡን እንደምስስ” ይላሉ።+

 5 የጋራ ዕቅድ ይነድፋሉ፤*

በአንተ ላይ ግንባር ፈጥረዋል፤*+

 6 የኤዶምና የእስማኤላውያን ድንኳኖች፣ ሞዓብና+ አጋራውያን፣+

 7 ጌባል፣ አሞንና+ አማሌቅ፣

እንዲሁም ፍልስጤም+ ከጢሮስ ነዋሪዎች+ ጋር አበሩ።

 8 አሦርም+ ከእነሱ ጋር ተባብሯል፤

ለሎጥ ልጆችም+ድጋፍ ይሰጣሉ።* (ሴላ)

 9 በምድያም እንዳደረግከው፣

በቂሾንም ጅረት* በሲሳራና በያቢን ላይ እንዳደረግከው አድርግባቸው።+

10 እነሱ በኤንዶር+ ተደመሰሱ፤

ለምድርም ፍግ ሆኑ።

11 በመካከላቸው ያሉትን ታላላቅ ሰዎች እንደ ኦሬብና ዜብ፣+

አለቆቻቸውንም* እንደ ዘባህና ጻልሙና አድርጋቸው፤+

12 እነሱ “አምላክ የሚኖርባቸውን ቦታዎች እንውረስ” ብለዋልና።

13 አምላኬ ሆይ፣ ነፋስ እያሽከረከረ እንደሚወስደው ኮሸሽላ፣*+

ነፋስ እንደሚጠርገው ገለባ አድርጋቸው።

14 ጫካን እንደሚያቃጥል እሳት፣

ተራሮችን እንደሚያነድ ነበልባል፣+

15 አንተም እንዲሁ በሞገድህ አሳዳቸው፤+

በአውሎ ነፋስህም አሸብራቸው።+

16 ይሖዋ ሆይ፣ ስምህን ይሹ ዘንድ፣

ፊታቸውን በኀፍረት ሸፍን።*

17 ለዘላለም ይፈሩ፣ ይሸበሩም፤

ውርደት ይከናነቡ፤ ደግሞም ይጥፉ፤

18 ስምህ ይሖዋ የሆነው አንተ፣+

አዎ፣ አንተ ብቻ በመላው ምድር ላይ ልዑል እንደሆንክ+ ሰዎች ይወቁ።

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በጊቲት።* የቆሬ ልጆች+ መዝሙር። ማህሌት።

84 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ሆይ፣

ታላቁ የማደሪያ ድንኳንህ ምንኛ ያማረ* ነው!+

 2 ሁለንተናዬ* የይሖዋን ቅጥር ግቢዎች

እጅግ ናፈቀ፤

አዎ፣ በጣም ከመጓጓቴ የተነሳ ዛልኩ።+

ልቤም ሆነ ሥጋዬ ሕያው ለሆነው አምላክ እልል ይላል።

 3 ንጉሤና አምላኬ የሆንከው የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣

ታላቁ መሠዊያህ ባለበት አቅራቢያ፣

ወፍ እንኳ በዚያ ቤት ታገኛለች፤

ወንጭፊትም ጫጩቶቿን የምታሳድግበት ጎጆ

ለራሷ ትሠራለች።

 4 በቤትህ የሚኖሩ ደስተኞች ናቸው!+

እነሱ ሁልጊዜ ያወድሱሃል።+ (ሴላ)

 5 አንተን የብርታታቸው ምንጭ ያደረጉ፣

ወደ ቤትህ የሚወስዱትን መንገዶች የሚናፍቅ ልብ ያላቸው ሰዎች ደስተኞች ናቸው።+

 6 በባካ* ሸለቆ* በሚያልፉበት ጊዜ፣

ስፍራውን ምንጮች የሚፈልቁበት ቦታ ያደርጉታል፤

የመጀመሪያውም ዝናብ በረከት ያለብሰዋል።*

 7 በብርታት ላይ ብርታት እያገኙ ይሄዳሉ፤+

እያንዳንዳቸውም በጽዮን፣ በአምላክ ፊት ይቀርባሉ።

 8 የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤

የያዕቆብ አምላክ ሆይ፣ አዳምጠኝ። (ሴላ)

 9 ጋሻችንና+ አምላካችን ሆይ፣ ተመልከት፤*

የተቀባውን የአገልጋይህን ፊት እይ።+

10 በሌላ ቦታ አንድ ሺህ ቀን ከመኖር በቅጥር ግቢዎችህ አንዲት ቀን መዋል ይሻላልና!+

በክፉዎች ድንኳን ከመኖር፣

በአምላኬ ቤት ደጃፍ ላይ መቆም እመርጣለሁ።

11 ይሖዋ አምላክ ፀሐይና+ ጋሻ+ ነውና፤

እሱ ሞገስና ክብር ይሰጣል።

ንጹሕ አቋም ይዘው የሚመላለሱትን

ይሖዋ አንዳች መልካም ነገር አይነፍጋቸውም።+

12 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ሆይ፣

በአንተ የሚታመን ሰው ደስተኛ ነው።+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የቆሬ ልጆች+ መዝሙር። ማህሌት።

85 ይሖዋ ሆይ፣ ለምድርህ ሞገስ አሳይተሃል፤+

የተማረኩትን የያዕቆብ ልጆች መልሰሃል።+

 2 የሕዝብህን በደል ተውክ፤

ኃጢአታቸውንም ሁሉ ይቅር አልክ።*+ (ሴላ)

 3 ንዴትህን ሁሉ ገታህ፤

ከብርቱ ቁጣህም ተመለስክ።+

 4 የመዳናችን አምላክ ሆይ፣ ወደ ቀድሞ ሁኔታችን መልሰን፤*

በእኛ የተነሳ ያደረብህን ቁጣም መልስ።+

 5 በእኛ ላይ የምትቆጣው ለዘላለም ነው?+

ቁጣህስ ከትውልድ እስከ ትውልድ ድረስ ይዘልቃል?

 6 ሕዝቦችህ በአንተ ሐሴት እንዲያደርጉ፣

ዳግመኛ እንድናንሰራራ አታደርገንም?+

 7 ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህን አሳየን፤+

ማዳንህንም ለግሰን።

 8 እውነተኛው አምላክ ይሖዋ የሚናገረውን እሰማለሁ፤

እሱ ለሕዝቡና ለታማኝ አገልጋዮቹ ስለ ሰላም ይናገራልና፤+

ብቻ እንደቀድሞው በራሳቸው ከልክ በላይ አይተማመኑ።+

 9 ክብሩ በምድራችን እንዲኖር፣

እሱን ለሚፈሩት ማዳኑ በእርግጥ ቅርብ ነው።+

10 ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት ይገናኛሉ፤

ጽድቅና ሰላም ይሳሳማሉ።+

11 ታማኝነት ከምድር ትበቅላለች፤

ጽድቅም ከሰማያት ወደ ታች ይመለከታል።+

12 አዎ፣ ይሖዋ መልካም ነገር* ይሰጣል፤+

ምድራችንም ምርቷን ትሰጣለች።+

13 ጽድቅ በፊቱ ይሄዳል፤+

ለእርምጃውም መንገድ ያዘጋጃል።

የዳዊት ጸሎት።

86 ይሖዋ ሆይ፣ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤* ደግሞም መልስልኝ፤

ጎስቋላና ድሃ ነኝና።+

 2 እኔ ታማኝ ስለሆንኩ ሕይወቴን* ጠብቃት።+

በአንተ የሚታመነውን አገልጋይህን አድነው፤

አንተ አምላኬ ነህና።+

 3 ይሖዋ ሆይ፣ ሞገስ አሳየኝ፤+

ቀኑን ሙሉ አንተን እጣራለሁና።+

 4 አገልጋይህን ደስ አሰኘው፤*

ይሖዋ ሆይ፣ የአንተን እርዳታ እሻለሁና።*

 5 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ጥሩ ነህና፤+ ይቅር ለማለትም ዝግጁ ነህ፤+

አንተን ለሚጠሩ ሁሉ የምታሳየው ታማኝ ፍቅር ወሰን የለውም።+

 6 ይሖዋ ሆይ፣ ጸሎቴን አዳምጥ፤

እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውንም ልመና በትኩረት ስማ።+

 7 አንተ መልስ ስለምትሰጠኝ፣+

በተጨነቅኩ ቀን አንተን እጣራለሁ።+

 8 ይሖዋ ሆይ፣ ከአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ የለም፤+

ከአንተ ሥራ ጋር የሚወዳደር አንድም ሥራ የለም።+

 9 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ የሠራሃቸው ብሔራት ሁሉ ይመጣሉ፤

በፊትህም ይሰግዳሉ፤+

ለስምህም ክብር ይሰጣሉ።+

10 አንተ ታላቅ ነህና፤ ድንቅ ነገሮችም ትሠራለህ፤+

አንተ አምላክ ነህ፤ ከአንተ ሌላ የለም።+

11 ይሖዋ ሆይ፣ መንገድህን አስተምረኝ።+

በእውነትህ እሄዳለሁ።+

ስምህን እፈራ ዘንድ ልቤን አንድ አድርግልኝ።*+

12 ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ በሙሉ ልቤ አወድስሃለሁ፤+

ስምህንም ለዘላለም ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፤

13 ለእኔ የምታሳየው ታማኝ ፍቅር ታላቅ ነውና፤

ሕይወቴንም* ጥልቅ ከሆነው መቃብር* አድነሃል።+

14 አምላክ ሆይ፣ እብሪተኛ ሰዎች በእኔ ላይ ተነስተዋል፤+

የጨካኞች ቡድን ሕይወቴን* ይሻታል፤

አንተንም ከምንም አልቆጠሩም።*+

15 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን መሐሪና ሩኅሩኅ፣*

ለቁጣ የዘገየህ እንዲሁም ታማኝ ፍቅርህና ታማኝነትህ* የበዛ አምላክ ነህ።+

16 ወደ እኔ ተመልከት፤ ሞገስም አሳየኝ።+

ለአገልጋይህ ብርታትህን ስጠው፤+

የሴት ባሪያህንም ልጅ አድን።

17 እኔን የሚጠሉ አይተው እንዲያፍሩ፣

የጥሩነትህን ምልክት* አሳየኝ።

ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ረዳቴና አጽናኜ ነህና።

የቆሬ ልጆች+ መዝሙር። ማህሌት።

87 የአምላክ ከተማ የተመሠረተችው በተቀደሱት ተራሮች ላይ ነው።+

 2 ይሖዋ ከያዕቆብ ድንኳኖች ሁሉ ይበልጥ

የጽዮንን በሮች ይወዳል።+

 3 የእውነተኛው አምላክ ከተማ ሆይ፣ ስለ አንቺ አስደናቂ የሆኑ ነገሮች እየተነገሩ ነው።+ (ሴላ)

 4 እኔን ከሚያውቁኝ* መካከል ረዓብንና*+ ባቢሎንን እጠቅሳለሁ፤

ኢትዮጵያን* ጨምሮ ፍልስጤምና ጢሮስም ይገኙበታል።

እንዲህም ይባላል፦ “ይህ በዚያ የተወለደ ነው።”

 5 ስለ ጽዮን ደግሞ እንዲህ ይባላል፦

“ይሄኛውም ሆነ ያኛው የተወለደው በእሷ ውስጥ ነው።”

ልዑሉ አምላክም አጽንቶ ይመሠርታታል።

 6 ይሖዋ ሕዝቡን ሲመዘግብ

“ይህ በዚያ የተወለደ ነው” ብሎ ያስታውቃል። (ሴላ)

 7 ዘማሪዎችና+ ጨፋሪዎች*+

“ምንጮቼ ሁሉ በአንቺ ውስጥ ይገኛሉ”*+ ይላሉ።

መዝሙር። የቆሬ ልጆች+ ማህሌት። ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በማሃላት ቅኝት፤* በመቀባበል የሚዘመር። የዛራዊው የሄማን+ ማስኪል።*

88 የመዳኔ አምላክ የሆንከው ይሖዋ ሆይ፣+

በቀን እጮኻለሁ፤

በሌሊትም በፊትህ እቀርባለሁ።+

 2 ጸሎቴ ወደ አንተ ይድረስ፤+

እርዳታ ለማግኘት የማሰማውን ጩኸት ለማዳመጥ ጆሮህን አዘንብል።*+

 3 ነፍሴ* በመከራ ተሞልታለችና፤+

ሕይወቴም በመቃብር* አፋፍ ላይ ነች።+

 4 አሁንም እንኳ ወደ ጉድጓድ* ከሚወርዱ ሰዎች ጋር ተቆጥሬአለሁ፤+

ምስኪን ሰው* ሆንኩ፤+

 5 ተገድለው በመቃብር ውስጥ እንደተጋደሙ፣

ከእንግዲህ ፈጽሞ እንደማታስታውሳቸውና

የአንተ እንክብካቤ* እንደተቋረጠባቸው ሰዎች፣

በሙታን መካከል ተተውኩ።

 6 አዘቅት ውስጥ ከተትከኝ፤

በጨለማ በተዋጠ ስፍራ፣ ጥልቅ በሆነ ጉድጓድ ውስጥ አኖርከኝ።

 7 በላዬ ላይ ያረፈው ቁጣህ እጅግ ከብዶኛል፤+

በኃይለኛ ማዕበልህም አጥለቀለቅከኝ። (ሴላ)

 8 የሚያውቁኝን ሰዎች ከእኔ አራቅክ፤+

በእነሱ ፊት አስጸያፊ ነገር አደረግከኝ።

ወጥመድ ውስጥ ገብቻለሁ፤ ማምለጥም አልቻልኩም።

 9 ከደረሰብኝ ጉስቁልና የተነሳ ዓይኔ ፈዘዘ።+

ይሖዋ ሆይ፣ ቀኑን ሙሉ አንተን እጣራለሁ፤+

እጆቼንም ወደ አንተ እዘረጋለሁ።

10 ለሙታን ድንቅ ሥራዎች ታከናውናለህ?

በሞት የተረቱትስ ተነስተው ሊያወድሱህ ይችላሉ?+ (ሴላ)

11 ታማኝ ፍቅርህ በመቃብር፣

ታማኝነትህስ በጥፋት ቦታ* ይታወጃል?

12 ያከናወንከው ድንቅ ሥራ በጨለማ፣

ጽድቅህስ በተረሱ ሰዎች ምድር ይታወቃል?+

13 ይሖዋ ሆይ፣ እኔ ግን እርዳታ ለማግኘት አሁንም ወደ አንተ እጮኻለሁ፤+

ጸሎቴም በየማለዳው ወደ አንተ ትደርሳለች።+

14 ይሖዋ ሆይ፣ ፊት የምትነሳኝ ለምንድን ነው?*+

ፊትህንስ ከእኔ የምትሰውረው ለምንድን ነው?+

15 እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ

የተጎሳቆልኩና ለመጥፋት የተቃረብኩ ነኝ፤+

እንዲደርሱብኝ ከፈቀድካቸው አስከፊ ነገሮች የተነሳ ደንዝዣለሁ።

16 የሚነደው ቁጣህ በላዬ ላይ ወረደ፤+

አንተ ያመጣህብኝ ሽብር አጠፋኝ።

17 ቀኑን ሙሉ እንደ ውኃ ከበበኝ፤

በሁሉም አቅጣጫ* ከቦ መውጫ አሳጣኝ።

18 ወዳጆቼንና ባልንጀሮቼን ከእኔ አራቅክ፤+

ጓደኛዬ ጨለማ ብቻ ሆኖ ቀረ።

የዛራዊው የኤታን+ ማስኪል።*

89 የይሖዋ ታማኝ ፍቅር ስለተገለጠባቸው መንገዶች ለዘላለም እዘምራለሁ።

ታማኝነትህን ለትውልዶች በሙሉ በአፌ አስታውቃለሁ።

 2 እንዲህ በማለት ተናግሬአለሁና፦ “ታማኝ ፍቅር ለዘላለም ይገነባል፤*+

ታማኝነትህንም በሰማያት አጽንተህ መሥርተሃል።”

 3 አንተም እንዲህ ብለሃል፦ “ከመረጥኩት ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ፤+

ለአገልጋዬ ለዳዊት ምያለሁ፦+

 4 ‘ዘርህ ለዘላለም ጸንቶ እንዲኖር አደርጋለሁ፤+

ዙፋንህንም ከትውልድ እስከ ትውልድ አጸናለሁ።’”+ (ሴላ)

 5 ይሖዋ ሆይ፣ ሰማያት ድንቅ ሥራህን፣

አዎ፣ በቅዱሳን ጉባኤ ታማኝነትህን ያወድሳሉ።

 6 በሰማያት ከይሖዋ ጋር ማን ሊወዳደር ይችላል?+

ከአምላክ ልጆች*+ መካከል እንደ ይሖዋ ያለ ማን ነው?

 7 አምላክ በቅዱሳን ጉባኤ መካከል እጅግ የተፈራ ነው፤+

በዙሪያው ባሉት ሁሉ መካከል ታላቅና እጅግ የሚከበር ነው።+

 8 የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ኃያል ነህ፤

ያህ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?+

አንተ በሁሉም ነገር ታማኝ መሆንህን ታሳያለህ።+

 9 የባሕሩን ሞገድ ትቆጣጠራለህ፤+

ማዕበሉም ሲነሳ አንተ ራስህ ጸጥ ታሰኘዋለህ።+

10 አንተ ረዓብን*+ እንደተገደለ ሰው አደቀቅከው።+

በብርቱ ክንድህ ጠላቶችህን በታተንካቸው።+

11 ሰማያት የአንተ ናቸው፤ ምድርም የአንተ ናት፤+

ፍሬያማ የሆነችውን ምድርና በውስጧ ያለውን ነገር ሁሉ የሠራኸው አንተ ነህ።+

12 ሰሜንንና ደቡብን የፈጠርክ አንተ ነህ፤

ታቦርና+ ሄርሞን+ ስምህን በደስታ ያወድሳሉ።

13 ክንድህ ኃያል ነው፤+

እጅህ ብርቱ ነው፤+

ቀኝ እጅህም ከፍ ከፍ ያለ ነው።+

14 ጽድቅና ፍትሕ የዙፋንህ መሠረት ናቸው፤+

ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት በፊትህ ናቸው።+

15 እልልታ የሚያውቁ ሰዎች ደስተኞች ናቸው።+

ይሖዋ ሆይ፣ እንዲህ ያሉ ሰዎች በፊትህ ብርሃን ይመላለሳሉ።

16 በስምህ ቀኑን ሙሉ ሐሴት ያደርጋሉ፤

በጽድቅህም ከፍ ከፍ ይላሉ።

17 አንተ የብርታታቸው ክብር ነህና፤+

በሞገስህም ብርታታችን* ከፍ ከፍ ብሏል።+

18 ጋሻችን ከይሖዋ ነውና፤

ንጉሣችን ከእስራኤል ቅዱስ ነው።+

19 በዚያን ጊዜ ለታማኝ አገልጋዮችህ በራእይ ተናገርክ፤ እንዲህም አልክ፦

“ለኃያል ሰው ብርታት ሰጠሁ፤+

ከሕዝቡም መካከል የተመረጠውን ከፍ ከፍ አደረግኩ።+

20 አገልጋዬን ዳዊትን አገኘሁት፤+

በተቀደሰ ዘይቴም ቀባሁት።+

21 እጄ ይደግፈዋል፤+

ክንዴም ያበረታዋል።

22 ማንኛውም ጠላት አያስገብረውም፤

የትኛውም ክፉ ሰው አይጨቁነውም።+

23 ባላጋራዎቹን ከፊቱ አደቃቸዋለሁ፤+

የሚጠሉትንም እመታቸዋለሁ።+

24 ታማኝነቴና ታማኝ ፍቅሬ ከእሱ ጋር ናቸው፤+

በስሜም ኃይሉ* ከፍ ከፍ ይላል።

25 እጁን* በባሕሩ ላይ፣

ቀኝ እጁንም በወንዞቹ ላይ አደርጋለሁ።+

26 እሱም ‘አንተ አባቴ ነህ፤

አምላኬና አዳኝ ዓለቴ ነህ’+ ብሎ ይጠራኛል።

27 እኔም በኩር እንዲሆን አደርገዋለሁ፤+

ከምድር ነገሥታትም ሁሉ በላይ አስቀምጠዋለሁ።+

28 ታማኝ ፍቅሬን ለዘላለም አሳየዋለሁ፤+

ከእሱ ጋር የገባሁት ቃል ኪዳንም ጸንቶ ይኖራል።+

29 ዘሩን ለዘላለም አጸናለሁ፤

ዙፋኑም የሰማያትን ዕድሜ ያህል ጸንቶ እንዲኖር አደርጋለሁ።+

30 ልጆቹ ሕጌን ቢተዉ፣

ድንጋጌዎቼንም* አክብረው ባይመላለሱ፣

31 ደንቦቼን ቢጥሱና

ትእዛዛቴን ባይጠብቁ፣

32 ባለመታዘዛቸው* በበትር እቀጣቸዋለሁ፤+

በደል በመፈጸማቸውም እገርፋቸዋለሁ።

33 ሆኖም ለእሱ ታማኝ ፍቅር ማሳየቴን አልተውም፤+

የገባሁትንም ቃል አላጥፍም።*

34 ቃል ኪዳኔን አላፈርስም፤+

ከአንደበቴ የወጣውንም ቃል አለውጥም።+

35 ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በቅድስናዬ ምያለሁ፤

ዳዊትን አልዋሸውም።+

36 ዘሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል፤+

ዙፋኑ በፊቴ እንዳለችው ፀሐይ ይጸናል።+

37 በሰማያት ታማኝ ምሥክር ሆና እንደምትኖረው እንደ ጨረቃ፣

ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።” (ሴላ)

38 ሆኖም አንተ ራስህ ጣልከው፤ ደግሞም ገሸሽ አደረግከው፤+

በተቀባው አገልጋይህ ላይ እጅግ ተቆጣህ።

39 ከአገልጋይህ ጋር የገባኸውን ቃል ኪዳን ወደ ጎን ገሸሽ አደረግክ፤

አክሊሉን* መሬት ላይ በመጣል አረከስከው።

40 በድንጋይ የተገነቡትን ቅጥሮቹን* ሁሉ አፈረስክ፤

ምሽጎቹን የፍርስራሽ ክምር አደረግክ።

41 በዚያ የሚያልፉ ሁሉ ዘረፉት፤

የጎረቤቶቹም መሳለቂያ ሆነ።+

42 ባላጋራዎቹ ድል እንዲጎናጸፉ አድርገሃል፤*+

ጠላቶቹ ሁሉ ደስ እንዲላቸው አደረግክ።

43 በተጨማሪም ሰይፉን መልሰህበታል፤

በጦርነትም እንዲሸነፍ አደረግክ።

44 ግርማ ሞገሱ እንዲጠፋ አደረግክ፤

ዙፋኑንም መሬት ላይ ጣልከው።

45 የወጣትነት ዕድሜውን አሳጠርክበት፤

ኀፍረትም አከናነብከው። (ሴላ)

46 ይሖዋ ሆይ፣ ራስህን የምትሰውረው እስከ መቼ ነው? ለዘላለም?+

ቁጣህስ እንደ እሳት ሲነድ ይኖራል?

47 ዕድሜዬ ምን ያህል አጭር እንደሆነ አስብ!+

ሰዎችን ሁሉ የፈጠርከው እንዲያው ለከንቱ ነው?

48 ሞትን ጨርሶ ሳያይ በሕይወት ሊኖር የሚችል ሰው ማን ነው?+

ራሱን* ከመቃብር* እጅ ማዳን ይችላል? (ሴላ)

49 ይሖዋ ሆይ፣ በታማኝነትህ ለዳዊት የማልክለት፣

በቀደሙት ዘመናት ያሳየኸው ታማኝ ፍቅር የት አለ?*+

50 ይሖዋ ሆይ፣ በአገልጋዮችህ ላይ የተሰነዘረውን ዘለፋ አስታውስ፤

ሰዎች ሁሉ የሰነዘሩብኝን ዘለፋ እንዴት እንደተሸከምኩ* አስብ፤

51 ይሖዋ ሆይ፣ ጠላቶችህ ምን ያህል እንደተሳደቡ አስታውስ፤

የቀባኸውን ሰው እርምጃ ሁሉ እንዴት እንደነቀፉ አስብ።

52 ይሖዋ ለዘላለም ይወደስ። አሜን፣ አሜን።+

አራተኛ መጽሐፍ

(መዝሙር 90-106)

የእውነተኛው አምላክ ሰው የሙሴ ጸሎት።+

90 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ከትውልድ እስከ ትውልድ መኖሪያችን* ሆነሃል።+

 2 ተራሮች ሳይወለዱ፣

ምድርንና ዓለምን ከመፍጠርህ*+ በፊት፣

ከዘላለም እስከ ዘላለም አንተ አምላክ ነህ።+

 3 ሟች የሆነ ሰው ወደ አፈር እንዲመለስ ታደርጋለህ፤

“የሰው ልጆች ሆይ፣ ወደ አፈር ተመለሱ”+ ትላለህ።

 4 በአንተ ዘንድ ሺህ ዓመት፣ እንዳለፈችው እንደ ትናንት ቀን፣+

እንደ አንድ ክፍለ ሌሊትም* ነው።

 5 ጠራርገህ ታስወግዳቸዋለህ፤+ እንደ ሕልም ይጠፋሉ፤

በማለዳ ሲታዩ እንደሚለመልም ሣር ናቸው።+

 6 ጠዋት ላይ ሣሩ ያቆጠቁጣል፤ ደግሞም ይለመልማል፤

ምሽት ላይ ግን ጠውልጎ ይደርቃል።+

 7 በቁጣህ አልቀናልና፤+

ከታላቅ ቁጣህም የተነሳ ተሸብረናል።

 8 በደላችንን በፊትህ ታኖራለህ፤*+

የደበቅናቸው ነገሮች በፊትህ ብርሃን ተጋልጠዋል።+

 9 ከኃይለኛ ቁጣህ የተነሳ ዘመናችን* ይመናመናል፤

ዕድሜያችንም ሽው ብሎ ያልፋል።*

10 የዕድሜያችን ርዝማኔ 70 ዓመት ነው፤

ለየት ያለ ጥንካሬ ካለን* ደግሞ 80+ ዓመት ቢሆን ነው።

ይህም በችግርና በሐዘን የተሞላ ነው፤

ፈጥኖ ይነጉዳል፤ እኛም እናልፋለን።+

11 የቁጣህን ኃይል መረዳት የሚችል ማን ነው?

ቁጣህ፣ አንተ መፈራት የሚገባህን ያህል ታላቅ ነው።+

12 ጥበበኛ ልብ ማግኘት እንችል ዘንድ፣

ዕድሜያችንን እንዴት መቁጠር እንዳለብን አስተምረን።+

13 ይሖዋ ሆይ፣ ተመለስ!+ ይህ ሁኔታ የሚቀጥለው እስከ መቼ ነው?+

ለአገልጋዮችህ ራራላቸው።+

14 በሕይወት ዘመናችን ሁሉ እልል እንድንልና ሐሴት እንድናደርግ፣+

በማለዳ ታማኝ ፍቅርህን አጥግበን።+

15 ባጎሳቆልከን ዘመን ልክ፣

መከራም ባየንባቸው ዓመታት መጠን+ ሐሴት እንዲሰማን አድርገን።+

16 አገልጋዮችህ ሥራህን ይዩ፤

ልጆቻቸውም ግርማህን ይመልከቱ።+

17 የአምላካችን የይሖዋ ሞገስ በእኛ ላይ ይሁን፤

የእጆቻችንን ሥራ ፍሬያማ አድርግልን።*

አዎ፣ የእጆቻችንን ሥራ ፍሬያማ አድርግልን።+

91 በልዑል አምላክ ሚስጥራዊ ቦታ የሚኖር ሰው+

ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ ጥላ ሥር ይቀመጣል።+

 2 ይሖዋን “አንተ መጠጊያዬና ምሽጌ፣+

የምታመንብህም አምላኬ ነህ”+ እለዋለሁ።

 3 እሱ ከወፍ አዳኙ ወጥመድ፣

ከአውዳሚ ቸነፈርም ይታደግሃልና።

 4 በላባዎቹ ይከልልሃል፤*

በክንፎቹም ሥር መጠጊያ ታገኛለህ።+

ታማኝነቱ+ ትልቅ ጋሻና+ መከላከያ ቅጥር* ይሆንልሃል።

 5 በሌሊት የሚያሸብሩ ነገሮችን፣

በቀንም የሚወነጨፍ ፍላጻን አትፈራም፤+

 6 በጨለማ የሚያደባ ቸነፈርም ሆነ

በቀትር የሚረፈርፍ ጥፋት አያስፈራህም።

 7 በአጠገብህ ሺህ፣

በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ፤

ወደ አንተ ግን አይደርስም።+

 8 በክፉዎች ላይ የሚደርሰውን ቅጣት* ትመለከታለህ፤

በዓይንህ ብቻ ታየዋለህ።

 9 ምክንያቱም “ይሖዋ መጠጊያዬ ነው” ብለሃል፤

ልዑሉን አምላክ መኖሪያህ* አድርገኸዋል፤+

10 ምንም ዓይነት አደጋ አይደርስብህም፤+

አንዳችም መቅሰፍት ወደ ድንኳንህ አይጠጋም።

11 በመንገድህ ሁሉ እንዲጠብቁህ+

መላእክቱን ስለ አንተ ያዛልና።+

12 እግርህን እንቅፋት እንዳይመታው+

በእጃቸው ያነሱሃል።+

13 የአንበሳውን ግልገልና ጉበናውን* ትረግጣለህ፤

ደቦል አንበሳውንና ትልቁን እባብ ከእግርህ ሥር ትጨፈልቃለህ።+

14 አምላክ እንዲህ ብሏል፦ “ስለወደደኝ፣* እታደገዋለሁ።+

ስሜን ስለሚያውቅ* እጠብቀዋለሁ።+

15 ይጠራኛል፤ እኔም እመልስለታለሁ።+

በተጨነቀ ጊዜ ከእሱ ጋር እሆናለሁ።+

እታደገዋለሁ እንዲሁም አከብረዋለሁ።

16 ረጅም ዕድሜን አጠግበዋለሁ፤+

የማዳን ሥራዎቼንም እንዲያይ* አደርገዋለሁ።”+

በሰንበት ቀን የሚዘመር መዝሙር። ማህሌት።

92 ለይሖዋ ምስጋና ማቅረብ ጥሩ ነው፤+

ልዑሉ አምላክ ሆይ፣ ለስምህም የውዳሴ መዝሙር መዘመር መልካም ነው፤

 2 ታማኝ ፍቅርህን በማለዳ፣

ታማኝነትህንም በሌሊት ማሳወቅ+ መልካም ነው፤

 3 አሥር አውታር ባለው መሣሪያና በክራር፣

ደስ በሚል የበገና ድምፅ+ ታጅቦ ማሳወቅ ጥሩ ነው።

 4 ይሖዋ ሆይ፣ ባከናወንካቸው ነገሮች እንድደሰት አድርገኸኛልና፤

ከእጅህ ሥራዎች የተነሳ እልል እላለሁ።

 5 ይሖዋ ሆይ፣ ሥራህ ምንኛ ታላቅ ነው!+

ሐሳብህም እንዴት ጥልቅ ነው!+

 6 ማመዛዘን የጎደለው ሰው ይህን ሊያውቅ አይችልም፤

ሞኝ የሆነም ሰው ይህን ሊረዳ አይችልም፦+

 7 ክፉዎች እንደ አረም* ቢበቅሉ፣

ክፉ አድራጊዎች ሁሉ ቢያብቡ እንኳ፣

ለዘላለም መጥፋታቸው የማይቀር ነው።+

 8 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን ለዘላለም ከሁሉ በላይ ነህ።

 9 ይሖዋ ሆይ፣ ጠላቶችህን በድል አድራጊነት ስሜት ተመልከት፤

ጠላቶችህ እንዴት እንደሚጠፉ እይ፤

ክፉ አድራጊዎች በሙሉ ይበተናሉ።+

10 አንተ ግን ኃይሌን* እንደ ዱር በሬ ኃይል ታደርጋለህ፤

እኔም ገላዬን ጥሩ ዘይት እቀባለሁ።+

11 ዓይኔ ጠላቶቼን በድል አድራጊነት ስሜት ያያል፤+

ጆሮዬም የሚያጠቁኝን ክፉ ሰዎች ውድቀት ይሰማል።

12 ጻድቅ ግን እንደ ዘንባባ ዛፍ ይለመልማል፤

እንደ አርዘ ሊባኖስም ትልቅ ይሆናል።+

13 በይሖዋ ቤት ተተክለዋል፤

በአምላካችን ቅጥር ግቢዎች ያብባሉ።+

14 ባረጁ* ጊዜም እንኳ ማበባቸውን ይቀጥላሉ፤+

እንደበረቱና* እንደጠነከሩ ይኖራሉ፤+

15 ይሖዋ ትክክለኛ እንደሆነ እያወጁ ይኖራሉ።

እሱ ዓለቴ ነው፤+ በእሱም ዘንድ ክፋት የለም።

93 ይሖዋ ነገሠ!+

ግርማ ተጎናጽፏል፤

ይሖዋ ብርታት ለብሷል፤

እንደ ቀበቶ ታጥቆታል።

ምድር* በጽኑ ተመሥርታለች፤

ልትናወጥ አትችልም።

 2 ዙፋንህ ከብዙ ዘመናት በፊት ጸንቶ የተመሠረተ ነው፤+

አንተ ከዘላለም እስከ ዘላለም አለህ።+

 3 ይሖዋ ሆይ፣ ወንዞቹ ጎረፉ፤

ወንዞቹ ጎረፉ፤ አስገመገሙም፤

ወንዞቹ ይጎርፋሉ፤ ደግሞም በኃይል ይላተማሉ።

 4 ከብዙ ውኃዎች ድምፅ፣

ኃይለኛ ከሆነው የባሕር ማዕበልም በላይ፣+

ይሖዋ ከፍ ባለ ቦታ ግርማ ተጎናጽፏል።+

 5 ማሳሰቢያዎችህ እጅግ አስተማማኝ ናቸው።+

ይሖዋ ሆይ፣ ቤትህ ለዘላለሙ በቅድስና ያጌጠ ነው።*+

94 የበቀል አምላክ፣ ይሖዋ ሆይ፣+

የበቀል አምላክ ሆይ፣ ብርሃንህን አብራ!

 2 የምድር ፈራጅ ሆይ፣ ተነስ።+

ለትዕቢተኞች የሚገባቸውን ብድራት ክፈላቸው።+

 3 ክፉዎች እስከ መቼ፣ ይሖዋ ሆይ፣

ክፉዎች እስከ መቼ ድረስ ይፈነጥዛሉ?+

 4 ይለፈልፋሉ፤ በእብሪት ይናገራሉ፤

ክፉ አድራጊዎች ሁሉ ስለ ራሳቸው ጉራ ይነዛሉ።

 5 ይሖዋ ሆይ፣ ሕዝብህን ያደቃሉ፤+

ርስትህንም ይጨቁናሉ።

 6 መበለቲቱንና ባዕዱን ሰው ይገድላሉ፤

አባት የሌላቸውንም ልጆች ሕይወት ያጠፋሉ።

 7 “ያህ አያይም፤+

የያዕቆብ አምላክ አያስተውለውም” ይላሉ።+

 8 እናንተ ማመዛዘን የጎደላችሁ ሰዎች፣ ይህን ልብ በሉ፤

እናንተ ሞኞች፣ አስተዋዮች የምትሆኑት መቼ ነው?+

 9 ጆሮን ያበጀው* እሱ መስማት አይችልም?

ወይስ ዓይንን የሠራው እሱ ማየት አይችልም?+

10 ብሔራትን የሚያርመው እሱ መውቀስ አይችልም?+

ለሰዎች እውቀት የሚሰጠው እሱ ነው!+

11 ይሖዋ የሰዎችን ሐሳብ ያውቃል፤

ከንቱ እንደሆነም ይረዳል።+

12 ያህ ሆይ፣ አንተ የምታርመው፣+

ከሕግህ ላይ የምታስተምረው ሰው ደስተኛ ነው፤+

13 ይህም ለክፉዎች ጉድጓድ እስኪቆፈር ድረስ፣+

በመከራ ወቅት ለእሱ ሰላም ትሰጠው ዘንድ ነው።

14 ይሖዋ ሕዝቡን አይጥልምና፤+

ርስቱንም አይተውም።+

15 ፍርድ፣ ዳግመኛ ጽድቅ የሚንጸባረቅበት ይሆናልና፤

ልበ ቅን የሆኑ ሰዎችም ሁሉ ይከተሉታል።

16 ከክፉዎች ጋር የሚሟገትልኝ ማን ነው?

ክፉ አድራጊዎችን በመቃወም ከጎኔ የሚቆም ማን ነው?

17 ይሖዋ ረዳቴ ባይሆን ኖሮ፣

በአጭር ጊዜ ውስጥ በጠፋሁ ነበር።*+

18 “እግሬ አዳለጠኝ” ባልኩ ጊዜ፣

ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህ ደገፈኝ።+

19 በጭንቀት በተዋጥኩ ጊዜ፣*

አጽናናኸኝ፤ ደግሞም አረጋጋኸኝ።*+

20 ምግባረ ብልሹ ገዢዎች* በሕግ ስም* ችግር ለመፍጠር እያሴሩ፣+

የአንተ ተባባሪ ሊሆኑ ይችላሉ?

21 በጻድቁ ላይ* ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት ይሰነዝራሉ፤+

በንጹሕ ሰው ላይ ሞት ይፈርዳሉ።*+

22 ለእኔ ግን ይሖዋ አስተማማኝ መጠጊያ ይሆንልኛል፤

አምላኬ መጠጊያ ዓለቴ ነው።+

23 ክፉ ሥራቸውን በላያቸው ይመልሳል፤+

በገዛ ክፋታቸው ያጠፋቸዋል።*

ይሖዋ አምላካችን ያጠፋቸዋል።+

95 ኑ፣ ለይሖዋ እልል እንበል!

አዳኛችን ለሆነው ዓለት በድል አድራጊነት ስሜት እልል እንበል።+

 2 ምስጋና ይዘን በፊቱ እንቅረብ፤+

በድል አድራጊነት ስሜት ለእሱ እንዘምር፤ ደግሞም እልል እንበል።

 3 ይሖዋ ታላቅ አምላክ ነውና፤

በሌሎች አማልክት ሁሉ ላይ ታላቅ ንጉሥ ነው።+

 4 ጥልቅ የሆኑት የምድር ክፍሎች በእጁ ናቸው፤

የተራሮችም ጫፍ የእሱ ነው።+

 5 እሱ የሠራው ባሕር የራሱ ነው፤+

የብሱንም የሠሩት እጆቹ ናቸው።+

 6 ኑ፣ እናምልክ፤ እንስገድም፤

ሠሪያችን በሆነው በይሖዋ ፊት እንንበርከክ።+

 7 እሱ አምላካችን ነውና፤

እኛ ደግሞ በመስኩ የተሰማራን ሕዝቦች፣

በእሱ እንክብካቤ* ሥር ያለን በጎች ነን።+

ዛሬ ድምፁን የምትሰሙ ከሆነ፣+

 8 አባቶቻችሁ በምድረ በዳ ሳሉ በመሪባ፣*

በማሳህ* ቀን እንዳደረጉት ልባችሁን አታደንድኑ፤+

 9 በዚያን ጊዜ እነሱ ፈተኑኝ፤+

ሥራዬን ቢያዩም ተገዳደሩኝ።+

10 ያን ትውልድ ለ40 ዓመት ተጸየፍኩት፤

እኔም “ይህ ሕዝብ ሁልጊዜ ልቡ ይስታል፤

መንገዴን ሊያውቅ አልቻለም” አልኩ።

11 በመሆኑም “ወደ እረፍቴ አይገቡም” ብዬ

በቁጣዬ ማልኩ።+

96 ለይሖዋ አዲስ መዝሙር ዘምሩ።+

መላዋ ምድር ለይሖዋ ትዘምር!+

 2 ለይሖዋ ዘምሩ፤ ስሙንም አወድሱ።

የማዳኑን ምሥራች በየቀኑ አውጁ።+

 3 ክብሩን በብሔራት፣

አስደናቂ ሥራዎቹንም በሕዝቦች ሁሉ መካከል አስታውቁ።+

 4 ይሖዋ ታላቅ ነው፤ ደግሞም እጅግ ሊወደስ ይገባዋል።

ከሌሎች አማልክት ሁሉ በላይ እጅግ የሚፈራ ነው።

 5 የሌሎች ሕዝቦች አማልክት ሁሉ ከንቱ ናቸው፤+

ይሖዋ ግን ሰማያትን የሠራ አምላክ ነው።+

 6 ሞገስና* ግርማ በፊቱ ናቸው፤+

ብርታትና ውበት በመቅደሱ ውስጥ አሉ።+

 7 እናንተ የሕዝብ ነገዶች፣ ለይሖዋ የሚገባውን ስጡ፤

ከክብሩና ከብርታቱ የተነሳ ለይሖዋ የሚገባውን ስጡ።+

 8 ለስሙ የሚገባውን ክብር ለይሖዋ ስጡ፤+

ስጦታ ይዛችሁ ወደ ቅጥር ግቢዎቹ ግቡ።

 9 ያጌጠ የቅድስና ልብስ ለብሳችሁ* ለይሖዋ ስገዱ፤*

ምድር ሁሉ በፊቱ ተንቀጥቀጪ!

10 በብሔራት መካከል እንዲህ ብላችሁ አስታውቁ፦ “ይሖዋ ነገሠ!+

ምድር* በጽኑ ተመሥርታለች፤ ከቦታዋ ልትንቀሳቀስ አትችልም።*

እሱ ለሕዝቦች በትክክል ይፈርዳል።”*+

11 ሰማያት ሐሴት ያድርጉ፤ ምድርም ደስ ይበላት፤

ባሕሩና በውስጡ ያለው ነገር ሁሉ የነጎድጓድ ድምፅ ያሰማ፤+

12 መስኩና በላዩ ላይ ያለው ሁሉ ሐሴት ያድርግ።+

የዱር ዛፎችም ሁሉ በይሖዋ ፊት እልል ይበሉ።+

13 እሱ እየመጣ ነውና፤*

በምድር ላይ ለመፍረድ እየመጣ ነው።

በዓለም* ላይ በጽድቅ፣

በሕዝቦችም ላይ በታማኝነት ይፈርዳል።+

97 ይሖዋ ነገሠ!+

ምድር ደስ ይበላት።+

ብዙ ደሴቶችም ሐሴት ያድርጉ።+

 2 ደመናና ድቅድቅ ጨለማ በዙሪያው አለ፤+

ጽድቅና ፍትሕ የዙፋኑ መሠረት ናቸው።+

 3 እሳት በፊቱ ይሄዳል፤+

ጠላቶቹንም በሁሉም አቅጣጫ ይፈጃል።+

 4 የመብረቅ ብልጭታዎቹ በመሬት ላይ አበሩ፤

ምድር ይህን አይታ ተንቀጠቀጠች።+

 5 ተራሮች በይሖዋ ፊት፣

በምድርም ሁሉ ጌታ ፊት እንደ ሰም ቀለጡ።+

 6 ሰማያት ጽድቁን ያውጃሉ፤

ሕዝቦችም ሁሉ ክብሩን ያያሉ።+

 7 ማንኛውንም የተቀረጸ ምስል የሚያመልኩ ሁሉ፣

ከንቱ በሆኑ አማልክታቸው የሚኩራሩ ይፈሩ።+

እናንተ አማልክት ሁሉ፣ ለእሱ ስገዱ።*+

 8 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ስላስተላለፍካቸው የፍርድ ውሳኔዎች፣

ጽዮን ሰምታ ሐሴት አደረገች፤

የይሁዳ ከተሞች* ደስ አላቸው።+

 9 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ በመላው ምድር ላይ ልዑል ነህና፤

ከሌሎች አማልክት ሁሉ በላይ እጅግ ከፍ ከፍ ብለሃል።+

10 እናንተ ይሖዋን የምትወዱ፣ ክፉ የሆነውን ነገር ጥሉ።+

እሱ የታማኝ አገልጋዮቹን ሕይወት* ይጠብቃል፤+

ከክፉዎች እጅ* ይታደጋቸዋል።+

11 ብርሃን ለጻድቃን ወጣ፤

ደስታም ለልበ ቅኖች ተዳረሰ።+

12 እናንተ ጻድቃን፣ በይሖዋ ሐሴት አድርጉ፤

ለቅዱስ ስሙም* ምስጋና አቅርቡ።

ማህሌት።

98 ለይሖዋ አዲስ መዝሙር ዘምሩ፤+

እሱ አስደናቂ ነገሮች አድርጓልና።+

ቀኝ እጁ፣ አዎ ቅዱስ ክንዱ መዳን አስገኝቷል።*+

 2 ይሖዋ ማዳኑ እንዲታወቅ አድርጓል፤+

በብሔራት ፊት ጽድቁን ገልጧል።+

 3 ለእስራኤል ቤት ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት ለማሳየት የገባውን ቃል አስታውሷል።+

የምድር ዳርቻዎች ሁሉ የአምላካችንን ማዳን* አይተዋል።+

 4 ምድር ሁሉ፣ ለይሖዋ በድል አድራጊነት እልል በሉ።

ደስ ይበላችሁ፤ ደግሞም እልል በሉ፤ የውዳሴም መዝሙር ዘምሩ።+

 5 ለይሖዋ በበገና የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤

በበገናና ደስ በሚል ዜማ ዘምሩለት።

 6 በእምቢልታና በቀንደ መለከት ድምፅ+

በንጉሡ በይሖዋ ፊት በድል አድራጊነት እልል በሉ።

 7 ባሕሩና በውስጡ ያለው ነገር ሁሉ፣

መሬትና* በላይዋ የሚኖር ሁሉ የነጎድጓድ ድምፅ ያሰሙ።

 8 ወንዞች በእጃቸው ያጨብጭቡ፤

ተራሮችም በአንድነት በይሖዋ ፊት እልል ይበሉ፤+

 9 እሱ በምድር ላይ ለመፍረድ እየመጣ ነውና።*

በዓለም* ላይ በጽድቅ፣

በሕዝቦችም ላይ በትክክል ይፈርዳል።+

99 ይሖዋ ነገሠ።+ ሕዝቦች ይንቀጥቀጡ።

እሱ ከኪሩቤል በላይ* በዙፋን ተቀምጧል።+ ምድር ትናወጥ።

 2 ይሖዋ በጽዮን ታላቅ ነው፤

ከሕዝቦችም ሁሉ በላይ ከፍ ያለ ነው።+

 3 ሕዝቦች ታላቅ ስምህን ያወድሱ፤+

ስምህ እጅግ የሚፈራና ቅዱስ ነውና።

 4 እሱ ፍትሕን የሚወድ ኃያል ንጉሥ ነው።+

አንተ ቅን የሆነውን ነገር በጽኑ መሥርተሃል።

ፍትሕንና ጽድቅን ለያዕቆብ አስፍነሃል።+

 5 ይሖዋ አምላካችንን ከፍ ከፍ አድርጉት፤+ በእግሩ ማሳረፊያ ፊት ስገዱ፤*+

እሱ ቅዱስ ነው።+

 6 ከካህናቱ መካከል ሙሴና አሮን ይገኙበታል፤+

ስሙን ከሚጠሩ መካከልም ሳሙኤል አንዱ ነው።+

እነሱ ወደ ይሖዋ ይጣሩ ነበር፤

እሱም ይመልስላቸው ነበር።+

 7 በደመና ዓምድ ውስጥ ሆኖ ያነጋግራቸው ነበር።+

ማሳሰቢያዎቹንና የሰጣቸውን ድንጋጌ ጠብቀዋል።+

 8 አምላካችን ይሖዋ ሆይ፣ አንተ መልስ ሰጠሃቸው።+

ይቅር ባይ አምላክ ሆንክላቸው፤+

ሆኖም ለሠሯቸው ኃጢአቶች ቀጣሃቸው።*+

 9 አምላካችንን ይሖዋን ከፍ ከፍ አድርጉት፤+

በቅዱስ ተራራውም+ ፊት ስገዱ፤*

አምላካችን ይሖዋ ቅዱስ ነውና።+

የምስጋና ማህሌት።

100 ምድር ሁሉ፣ በድል አድራጊነት ለይሖዋ እልል በሉ።+

 2 ይሖዋን በደስታ አገልግሉት።+

በእልልታ ወደ ፊቱ ቅረቡ።

 3 ይሖዋ፣ አምላክ መሆኑን እወቁ።*+

የሠራን እሱ ነው፤ እኛም የእሱ ንብረት ነን።*+

እኛ ሕዝቡና የማሰማሪያው በጎች ነን።+

 4 በምስጋና ወደ በሮቹ፣

በውዳሴም ወደ ቅጥር ግቢዎቹ ግቡ።+

ምስጋና አቅርቡለት፤ ስሙንም አወድሱ።+

 5 ይሖዋ ጥሩ ነውና፤+

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም፣

ታማኝነቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ጸንቶ ይኖራል።+

የዳዊት መዝሙር። ማህሌት።

101 ስለ ታማኝ ፍቅርና ስለ ፍትሕ እዘምራለሁ።

ይሖዋ ሆይ፣ ለአንተ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።

 2 በማስተዋልና ነቀፋ በሌለበት መንገድ* እመላለሳለሁ።

ወደ እኔ የምትመጣው መቼ ነው?

በቤቴ ውስጥ በንጹሕ ልብ* እመላለሳለሁ።+

 3 በዓይኖቼ ፊት የማይረባ* ነገር አላኖርም።

ከትክክለኛው መንገድ የሚወጡ ሰዎች የሚያደርጓቸውን ነገሮች እጠላለሁ፤+

ከእነሱ ጋር የሚያገናኘኝ ምንም ጉዳይ የለም።*

 4 ጠማማ ልብ ከእኔ የራቀ ነው፤

ምንም ዓይነት ክፉ ነገር አልቀበልም።*

 5 የባልንጀራውን ስም በስውር የሚያጠፋን ሰው፣+

ጸጥ አሰኘዋለሁ።*

ትዕቢተኛ ዓይንና እብሪተኛ ልብ ያለውን ሰው፣

አልታገሠውም።

 6 ከእኔ ጋር እንዲኖሩ

በምድሪቱ ወዳሉ ታማኞች እመለከታለሁ።

ነቀፋ በሌለበት መንገድ* የሚመላለስ ሰው እኔን ያገለግለኛል።

 7 አታላይ የሆነ ሰው በቤቴ አይኖርም፤

ውሸት የሚናገር ሰው በፊቴ* አይቆምም።

 8 በምድሪቱ ላይ የሚገኙትን ክፉ ሰዎች ሁሉ በየማለዳው ጸጥ አሰኛለሁ፤*

ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ ከይሖዋ ከተማ አስወግዳለሁ።+

ጭቆና የደረሰበት ሰው ተስፋ በቆረጠና* ጭንቀቱን በይሖዋ ፊት ባፈሰሰ ጊዜ ያቀረበው ጸሎት።+

102 ይሖዋ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤+

እርዳታ ለማግኘት የማሰማው ጩኸት ወደ አንተ ይድረስ።+

 2 የሚያስጨንቅ ሁኔታ ባጋጠመኝ ጊዜ ፊትህን ከእኔ አትሰውር።+

ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤*

ስጣራ ፈጥነህ መልስልኝ።+

 3 የሕይወት ዘመኔ እንደ ጭስ እየበነነ ነው፤

አጥንቶቼም እንደ ምድጃ ከስለዋል።+

 4 እህል መብላት ረስቻለሁና፤

ልቤ እንደ ሣር ጠውልጓል፤ ደርቋልም።+

 5 እጅግ ከመቃተቴ የተነሳ+

አጥንቶቼ ከቆዳዬ ጋር ተጣበቁ።+

 6 የምድረ በዳ ሻላ* መሰልኩ፤

በፍርስራሽ ክምር መካከል እንዳለች ጉጉት ሆንኩ።

 7 እንቅልፍ አጥቼ አድራለሁ፤*

በጣሪያ ላይ እንዳለች ብቸኛ ወፍ ሆንኩ።+

 8 ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ ይሳለቁብኛል።+

የሚያፌዙብኝ ሰዎች ስሜን ለእርግማን ይጠቀሙበታል።

 9 አመድን እንደ ምግብ እበላለሁና፤+

የምጠጣውም ነገር ከእንባ ጋር ተቀላቅሏል፤+

10 ይህም የሆነው ከቁጣህና ከንዴትህ የተነሳ ነው፤

እኔን ለመጣል ወደ ላይ አንስተኸኛልና።

11 የሕይወቴ ዘመን ፀሐይ ስትጠልቅ እንደሚጠፋ* ጥላ ነው፤+

እኔም እንደ ሣር ጠወለግኩ።+

12 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን ለዘላለም ትኖራለህ፤+

ዝናህም* ከትውልድ እስከ ትውልድ ይጸናል።+

13 በእርግጥ ትነሳለህ፤ ለጽዮንም ምሕረት ታሳያለህ፤+

ለእሷ ሞገስህን የምታሳይበት ጊዜ ነውና፤+

የተወሰነው ጊዜ ደርሷል።+

14 አገልጋዮችህ በድንጋዮቿ ደስ ይላቸዋልና፤+

ለአፈሯም እንኳ ልዩ ፍቅር አላቸው።+

15 ብሔራት የይሖዋን ስም፣

የምድር ነገሥታትም ሁሉ ክብርህን ይፈራሉ።+

16 ይሖዋ ጽዮንን ዳግመኛ ይገነባልና፤+

በክብሩም ይገለጣል።+

17 የድሆችን ጸሎት በትኩረት ያዳምጣል፤+

ጸሎታቸውን አይንቅም።+

18 ይህ የተጻፈው ለመጪው ትውልድ ነው፤+

በመሆኑም ወደፊት የሚመጣው* ሕዝብ ያህን ያወድሳል።

19 ይሖዋ ከፍ ካለው ቅዱስ ስፍራው ወደ ታች ይመለከታልና፤+

ከሰማይ ሆኖ ወደ ታች ምድርን ያያል፤

20 ይህም የእስረኛውን ሲቃ ለመስማት፣+

ሞት የተፈረደባቸውንም ነፃ ለማውጣት ነው፤+

21 በመሆኑም የይሖዋ ስም በጽዮን፣

ውዳሴውም በኢየሩሳሌም ይታወጃል፤+

22 ይህም የሚሆነው ሕዝቦችና መንግሥታት

ይሖዋን ለማገልገል አንድ ላይ በሚሰበሰቡበት ጊዜ ነው።+

23 ያለጊዜዬ ኃይል አሳጣኝ፤

የሕይወት ዘመኔን አሳጠረ።

24 እኔም እንዲህ አልኩ፦

“ከትውልድ እስከ ትውልድ የምትኖረው አምላኬ ሆይ፣+

በሕይወት ዘመኔ እኩሌታ አታጥፋኝ።

25 አንተ ከብዙ ዘመናት በፊት የምድርን መሠረት ጣልክ፤

ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው።+

26 እነሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ትኖራለህ፤

ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ።

እንደ ልብስ ትቀይራቸዋለህ፤ እነሱም ያልፋሉ።

27 አንተ ግን ያው ነህ፤ ዘመንህም ፍጻሜ የለውም።+

28 የአገልጋዮችህ ልጆች ያለስጋት ይኖራሉ፤

ዘራቸውም በፊትህ ጸንቶ ይኖራል።”+

የዳዊት መዝሙር።

103 ይሖዋን ላወድስ፤*

ሁለንተናዬ ቅዱስ ስሙን ያወድስ።

 2 ይሖዋን ላወድስ፤*

ያደረጋቸውን ነገሮች ሁሉ ፈጽሞ አልርሳ።+

 3 እሱ በደልሽን ሁሉ ይቅር ይላል፤+

ሕመምሽንም ሁሉ ይፈውሳል፤+

 4 ሕይወትሽን ከጉድጓድ* ያወጣል፤+

ታማኝ ፍቅሩንና ምሕረቱን ያጎናጽፍሻል፤+

 5 የወጣትነት ዕድሜሽ እንደ ንስር እንዲታደስ፣+

በሕይወት ዘመንሽ ሁሉ መልካም ነገሮች ያጠግብሻል።+

 6 ይሖዋ ለተጨቆኑ ሁሉ

በጽድቅና በፍትሕ እርምጃ ይወስዳል።+

 7 መንገዶቹን ለሙሴ፣

ያከናወናቸውንም ነገሮች ለእስራኤል ልጆች አሳወቀ።+

 8 ይሖዋ መሐሪና ሩኅሩኅ፣*+

ለቁጣ የዘገየ እንዲሁም ታማኝ ፍቅሩ* የበዛ ነው።+

 9 እሱ ሁልጊዜ ስህተት አይፈላልግም፤+

ለዘላለምም ቂም አይዝም።+

10 እንደ ኃጢአታችን አላደረገብንም፤+

ለበደላችን የሚገባውንም ብድራት አልከፈለንም።+

11 ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፣

እሱ ለሚፈሩት የሚያሳየው ታማኝ ፍቅር ታላቅ ነውና።+

12 ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ፣

በደላችንን ከእኛ አራቀ።+

13 አባት ለልጆቹ ምሕረት እንደሚያሳይ፣

ይሖዋም ለሚፈሩት ምሕረት አሳይቷል።+

14 እሱ እንዴት እንደተሠራን በሚገባ ያውቃልና፤+

አፈር መሆናችንን ያስታውሳል።+

15 ሟች የሆነ የሰው ልጅ የሕይወት ዘመኑ እንደ ሣር ነው፤+

እንደ ሜዳ አበባ ያብባል።+

16 ይሁንና ነፋስ ሲነፍስበት ደብዛው ይጠፋል፤

በዚያ ስፍራ ያልነበረ ያህል ይሆናል።*

17 ይሖዋ ግን እሱን ለሚፈሩት

ታማኝ ፍቅሩን ከዘላለም እስከ ዘላለም ያሳያል፤+

ጽድቁንም ለልጅ ልጆቻቸው ይገልጣል፤+

18 ይህን የሚያደርገው ቃል ኪዳኑን ለሚጠብቁ፣+

መመሪያዎቹን ለመፈጸም ለሚተጉ ነው።

19 ይሖዋ ዙፋኑን በሰማያት አጽንቶ መሥርቷል፤+

በሁሉም ላይ ንጉሥ ሆኖ ይገዛል።+

20 ትእዛዛቱን በማክበር ቃሉን የምትፈጽሙ፣*+

እናንተ ብርቱዎችና ኃያላን መላእክቱ ሁሉ፣+ ይሖዋን አወድሱ።

21 ፈቃዱን የምታደርጉ አገልጋዮቹ፣+

ሠራዊቱ ሁሉ፣ ይሖዋን አወድሱ።+

22 በግዛቱ* ሁሉ ያላችሁ፣

ፍጥረታቱ ሁሉ፣ ይሖዋን አወድሱ።

ሁለንተናዬ ይሖዋን ያወድስ።*

104 ይሖዋን ላወድስ።*+

ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ።+

ሞገስንና* ግርማን ለብሰሃል።+

 2 ብርሃንን እንደ ልብስ ተጎናጽፈሃል፤+

ሰማያትን እንደ ድንኳን መጋረጃ ዘርግተሃል።+

 3 የላይኛዎቹን ክፍሎች ተሸካሚዎች ከላይ ባሉት ውኃዎች ላይ* ያኖራል፤+

ደመናትን ሠረገላው ያደርጋል፤+

በነፋስ ክንፎችም ይሄዳል።+

 4 መላእክቱን መናፍስት፣

አገልጋዮቹን የሚባላ እሳት ያደርጋል።+

 5 ምድርን በመሠረቶቿ ላይ መሠረታት፤+

እሷም ለዘላለም ከቦታዋ አትናወጥም።+

 6 ጥልቅ ውኃን እንደ ልብስ አለበስካት።+

ውኃዎቹ ከተራሮቹ በላይ ቆሙ።

 7 በገሠጽካቸው ጊዜ ሸሹ፤+

የነጎድጓድህን ድምፅ ሲሰሙ በድንጋጤ ፈረጠጡ፤

 8 ተራሮች ወደ ላይ ወጡ፤+ ሸለቆዎችም ወደ ታች ወረዱ፤

ሁሉም ወዳዘጋጀህላቸው ቦታ ሄዱ።

 9 ውኃዎቹ አልፈው እንዳይሄዱ፣

እንደገናም ምድርን እንዳይሸፍኑ ወሰን አበጀህላቸው።+

10 ምንጮችን ወደ ሸለቆዎች* ይልካል፤

በተራሮች መካከል ይፈስሳሉ።

11 የዱር አራዊት ሁሉ ከዚያ ይጠጣሉ፤

የዱር አህዮችም ጥማቸውን ይቆርጣሉ።

12 የሰማይ ወፎች ከእነሱ በላይ ይሰፍራሉ፤

በለመለሙ የዛፍ ቅርንጫፎች መካከል ሆነው ይዘምራሉ።

13 ከላይ ካሉት ክፍሎቹ ሆኖ ተራሮችን ያጠጣል።+

በሥራህ ፍሬ ምድር ረካች።+

14 ሣርን ለከብት፣

አትክልትንም ለሰው ልጆች ጥቅም ያበቅላል፤+

ይህን የሚያደርገው ምድር እህል እንድታስገኝ ነው፤

15 እንዲሁም የሰውን ልብ ደስ የሚያሰኝ የወይን ጠጅ፣+

ፊትን የሚያበራ ዘይትና

የሰውን ልብ የሚያበረታ እህል እንዲገኝ ነው።+

16 የይሖዋ ዛፎች፣ እሱ የተከላቸው አርዘ ሊባኖሶች፣

ውኃ ጠጥተው ይረካሉ፤

17 በዚያ ወፎች ጎጇቸውን ይሠራሉ።

ራዛ*+ በጥድ ዛፎች ላይ ትኖራለች።

18 ረጃጅሞቹ ተራሮች፣ የተራራ ፍየሎች+ መኖሪያ ናቸው፤

ቋጥኞቹ የሽኮኮዎች+ መሸሸጊያ ናቸው።

19 ጊዜያትን ለመለየት ጨረቃን ሠራ፤

ፀሐይ የምትጠልቅበትን ጊዜ በሚገባ ታውቃለች።+

20 ጨለማን ታመጣለህ፤ ሌሊትም ይሆናል፤+

በዚህ ጊዜ በጫካ የሚኖሩ አራዊት ሁሉ ወጥተው ይንቀሳቀሳሉ።

21 ደቦል አንበሶች አደን ለማግኘት ያገሳሉ፤+

ምግባቸውንም ከአምላክ ይሻሉ።+

22 ፀሐይ ስትወጣ፣

ተመልሰው በየጎሬአቸው ይተኛሉ።

23 ሰውም ወደ ሥራው ተሰማርቶ

እስኪመሽ ድረስ ሲሠራ ይውላል።

24 ይሖዋ ሆይ፣ ሥራህ ምንኛ ብዙ ነው!+

ሁሉንም በጥበብ ሠራህ።+

ምድር በፈጠርካቸው ነገሮች ተሞልታለች።

25 ባሕሩ እጅግ ትልቅና ሰፊ ነው፤

በዚያ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ትናንሽም ሆኑ ትላልቅ ሕያዋን ነገሮች ይርመሰመሳሉ።+

26 በዚያም መርከቦች ይጓዛሉ፤

በዚያ እንዲጫወት የፈጠርከው ሌዋታንም*+ በውስጡ ይሄዳል።

27 በወቅቱ ምግባቸውን እንድትሰጣቸው፣

ሁሉም አንተን ይጠባበቃሉ።+

28 አንተ የምትሰጣቸውን ይሰበስባሉ።+

እጅህን ስትከፍት መልካም ነገሮችን ይጠግባሉ።+

29 ፊትህን ስትሰውር ይታወካሉ።

መንፈሳቸውን ከወሰድክ ይሞታሉ፤ ወደ አፈርም ይመለሳሉ።+

30 መንፈስህን ከላክ ይፈጠራሉ፤+

የምድርንም ገጽ ታድሳለህ።

31 የይሖዋ ክብር ለዘላለም ይኖራል።

ይሖዋ በሥራው ሐሴት ያደርጋል።+

32 ምድርን ሲመለከት ትንቀጠቀጣለች፤

ተራሮችን ሲነካ ይጨሳሉ።+

33 በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ለይሖዋ እዘምራለሁ፤+

በሕይወት እስካለሁ ድረስ ለአምላኬ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።+

34 ሐሳቤ እሱን የሚያስደስት ይሁን።*

እኔም በይሖዋ ሐሴት አደርጋለሁ።

35 ኃጢአተኞች ከምድር ይጠፋሉ፤

ክፉዎችም ከእንግዲህ አይገኙም።+

ይሖዋን ላወድስ።* ያህን አወድሱ!*

105 ይሖዋን አመስግኑ፤+ ስሙን ጥሩ፤

ሥራውን በሕዝቦች መካከል አስታውቁ!+

 2 ለእሱ ዘምሩ፤ የውዳሴም መዝሙር ዘምሩለት፤

አስደናቂ በሆኑት ሥራዎቹ ሁሉ ላይ አሰላስሉ።*+

 3 በቅዱስ ስሙ ተኩራሩ።+

ይሖዋን የሚፈልጉ ሰዎች፣ ልባቸው ሐሴት ያድርግ።+

 4 ይሖዋንና ብርታቱን ፈልጉ።+

ፊቱን ሁልጊዜ እሹ።

 5 ያከናወናቸውን አስደናቂ ሥራዎች፣

ተአምራቱንና የተናገረውን ፍርድ አስታውሱ፤+

 6 እናንተ የአገልጋዩ የአብርሃም ዘሮች፣+

እሱ የመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች፣+ ይህን አስታውሱ።

 7 እሱ ይሖዋ አምላካችን ነው።+

ፍርዱ በመላው ምድር ላይ ነው።+

 8 ቃል ኪዳኑን ለዘላለም፣

የገባውን ቃል* እስከ ሺህ ትውልድ ያስታውሳል፤+

 9 ከአብርሃም ጋር የገባውን ቃል ኪዳን፣+

ለይስሐቅም በመሐላ የገባውን ቃል አይረሳም፤+

10 ቃሉን ለያዕቆብ ድንጋጌ፣

ለእስራኤልም ዘላቂ ቃል ኪዳን አድርጎ አቋቋመ፤

11 “የከነአንን ምድር

ርስትህ አድርጌ እሰጥሃለሁ” አለ።+

12 ይህን የተናገረው በቁጥር ጥቂት፣

አዎ፣ በጣም ጥቂት በነበሩ ጊዜ ነው፤+ በምድሪቱም ላይ የባዕድ አገር ሰዎች ነበሩ።+

13 እነሱም ከአንዱ ብሔር ወደ ሌላው ብሔር፣

ከአንዱም መንግሥት ወደ ሌላው ሕዝብ ተንከራተቱ።+

14 ማንም እንዲጨቁናቸው አልፈቀደም፤+

ይልቁንም ለእነሱ ሲል ነገሥታትን ገሠጸ፤+

15 “የቀባኋቸውን አገልጋዮቼን አትንኩ፤

በነቢያቴም ላይ አንዳች ክፉ ነገር አታድርጉ” አላቸው።+

16 በምድሪቱ ላይ ረሃብን ጠራ፤+

የምግብ አቅርቦታቸው እንዲቋረጥ አደረገ።*

17 ባሪያ እንዲሆን የተሸጠውን ሰው፣ ዮሴፍን

ከእነሱ አስቀድሞ ላከው።+

18 እግሮቹን በእግር ብረት አሰሩ፤*+

አንገቱም ብረት ውስጥ ገባ፤*

19 የይሖዋ ቃል አጠራው፤

ይህም የሆነው የተናገረው ቃል እስኪፈጸም ድረስ ነው።+

20 ንጉሡ ልኮ አስፈታው፤+

የሕዝቦቹም ገዢ ነፃ አወጣው።

21 የቤቱ ጌታ አድርጎ ሾመው፤

የንብረቱ ሁሉ ገዢ አደረገው፤+

22 ይህም ደስ ባሰኘው* መንገድ በመኳንንቱ ላይ እንዲሠለጥን፣*

ሽማግሌዎቹንም ጥበብ እንዲያስተምር ነው።+

23 ከዚያም እስራኤል ወደ ግብፅ መጣ፤+

ያዕቆብም በካም ምድር የባዕድ አገር ሰው ሆኖ ኖረ።

24 አምላክ ሕዝቡ እየተባዛ እንዲሄድ አደረገ፤+

ከጠላቶቻቸው ይበልጥ ኃያላን አደረጋቸው፤+

25 ሕዝቡን ይጠሉ ዘንድ፣

በአገልጋዮቹም ላይ ያሴሩ ዘንድ የጠላቶቻቸው ልብ እንዲለወጥ ፈቀደ።+

26 አገልጋዩን ሙሴን፣+

የመረጠውንም አሮንን ላከ።+

27 እነሱም ምልክቶቹን በመካከላቸው፣

ተአምራቱን በካም ምድር አደረጉ።+

28 ጨለማን ላከ፤ ምድሪቱም ጨለመች፤+

እነሱ በቃሉ ላይ አላመፁም።

29 ውኃዎቻቸውን ወደ ደም ለወጠ፤

ዓሣዎቻቸውንም ገደለ።+

30 ምድራቸው፣ የነገሥታታቸውም እልፍኞች እንኳ* ሳይቀሩ

በእንቁራሪቶች ተጥለቀለቁ።+

31 ተናካሽ ዝንቦች እንዲወሯቸው፣

ትንኞችም በግዛቶቻቸው ሁሉ እንዲርመሰመሱ አዘዘ።+

32 በዝናባቸው ፋንታ በረዶ አወረደባቸው፤

በምድራቸውም ላይ መብረቅ* ላከ።+

33 ወይናቸውንና የበለስ ዛፋቸውን መታ፤

በግዛታቸው ውስጥ ያሉትንም ዛፎች አወደመ።

34 አንበጦች፣ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ኩብኩባዎችም

እንዲወሯቸው አዘዘ።+

35 እነሱ በአገሪቱ የሚገኘውን አትክልት ሁሉ በሉ፤

የምድሪቱንም ምርት ፈጁ።

36 ከዚያም በአገራቸው ያሉትን በኩራት ሁሉ፣

የፍሬያቸው* መጀመሪያ የሆኑትን መታ።+

37 ሕዝቡ ብርና ወርቅ ይዞ እንዲወጣ አደረገ፤+

ከነገዶቹም መካከል የተሰናከለ አልነበረም።

38 በወጡ ጊዜ ግብፅ ሐሴት አደረገ፤

እስራኤላውያንን* እጅግ ፈርተዋቸው ነበርና።+

39 እነሱን ለመሸፈን ደመናን ዘረጋ፤+

በሌሊትም ብርሃን እንዲሰጥ እሳትን ላከ።+

40 ሥጋ እንዲሰጣቸው በጠየቁት ጊዜ ድርጭት ላከላቸው፤+

ከሰማይም ምግብ እያወረደ ያጠግባቸው ነበር።+

41 ዓለትን ሰነጠቀ፤ ውኃም ተንዶለዶለ፤+

በበረሃ እንደ ወንዝ ፈሰሰ።+

42 ለአገልጋዩ ለአብርሃም የገባውን ቅዱስ ቃል አስታውሷልና።+

43 ስለዚህ ሕዝቡን በታላቅ ደስታ፣

የተመረጡ አገልጋዮቹንም በእልልታ አወጣቸው።+

44 የሌሎችን ብሔራት ምድር ሰጣቸው፤+

እነሱም ሌሎች ሕዝቦች ለፍተው ያፈሩትን ወረሱ፤+

45 ይህን ያደረገው ድንጋጌዎቹን እንዲጠብቁ፣+

ሕጎቹንም እንዲያከብሩ ነው።

ያህን አወድሱ!*

106 ያህን አወድሱ!*

ይሖዋ ጥሩ+ ስለሆነ ምስጋና አቅርቡለት፤

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።+

 2 የይሖዋን ታላላቅ ሥራዎች ሙሉ በሙሉ ሊያስታውቅ የሚችለው ማን ነው?

ወይስ የሚያስመሰግኑ ተግባሮቹን ሁሉ ሊያውጅ የሚችለው ማን ነው?+

 3 ፍትሐዊ ድርጊት የሚፈጽሙ፣

ምንጊዜም ትክክል የሆነውን የሚያደርጉ+ ደስተኞች ናቸው።

 4 ይሖዋ ሆይ፣ ለሕዝብህ ሞገስ* በምታሳይበት ጊዜ እኔንም አስታውሰኝ።+

ተንከባከበኝ፤ ደግሞም አድነኝ፤

 5 ይህም ለተመረጡ አገልጋዮችህ+ የምታሳየውን ጥሩነት እንድቀምስ፣

ከሕዝብህ ጋር ሐሴት እንዳደርግ፣

ከርስትህም ጋር አንተን በኩራት እንዳወድስ* ነው።

 6 እኛም እንደ አባቶቻችን ኃጢአት ሠርተናል፤+

በድለናል፤ ክፉ ነገርም አድርገናል።+

 7 አባቶቻችን በግብፅ በነበሩበት ጊዜ፣ ድንቅ ሥራዎችህን በአድናቆት አልተመለከቱም።*

የታማኝ ፍቅርህን ብዛት አላስታወሱም፤

ከዚህ ይልቅ በባሕሩ አጠገብ ይኸውም ቀይ ባሕር አጠገብ ዓመፁ።+

 8 ይሁንና ኃያልነቱ እንዲታወቅ ሲል፣+

ለስሙ ብሎ አዳናቸው።+

 9 ቀይ ባሕርን ገሠጸ፤ ባሕሩም ደረቀ፤

በበረሃ* የሚሄዱ ያህል በጥልቅ ውኃው መካከል መራቸው፤+

10 ከባላጋራዎቻቸው እጅ አዳናቸው፤+

ከጠላቶቻቸውም እጅ ታደጋቸው።+

11 ውኃው ጠላቶቻቸውን ዋጠ፤

ከእነሱ አንድ ሰው እንኳ አልዳነም።+

12 በዚያን ጊዜ በገባው ቃል አመኑ፤+

የውዳሴ መዝሙር ይዘምሩለት ጀመር።+

13 ይሁን እንጂ ያደረገውን ነገር ወዲያውኑ ረሱ፤+

እሱ የሚሰጣቸውን ምክር በትዕግሥት አልጠበቁም።

14 በምድረ በዳ በራስ ወዳድነት ምኞት ተሸነፉ፤+

በበረሃ አምላክን ተፈታተኑት።+

15 እሱም የለመኑትን ሰጣቸው፤

ነገር ግን በሚያመነምን* በሽታ መታቸው።+

16 በሰፈር ውስጥ በሙሴ፣

ደግሞም የይሖዋ ቅዱስ አገልጋይ+ በሆነው በአሮን ቀኑ።+

17 በዚህ ጊዜ ምድር ተከፍታ ዳታንን ዋጠች፤

ከአቤሮንም ጋር ያበሩትን ሰለቀጠች።+

18 እሳትም በማኅበራቸው መካከል ነደደች፤

ነበልባልም ክፉዎችን በላች።+

19 በኮሬብ ጥጃ ሠሩ፤

ከብረት ለተሠራም ሐውልት* ሰገዱ፤+

20 ሣር በሚበላ ኮርማ ምስል

ክብሬን ለወጡ።+

21 በግብፅ ታላላቅ ነገሮች ያደረገውን፣+

አዳኛቸው የሆነውን አምላክ ረሱ፤+

22 በካም ምድር አስደናቂ ሥራዎች፣+

በቀይ ባሕር የሚያስፈሩ* ነገሮች ያከናወነውን+ አምላክ ዘነጉ።

23 እንዲጠፉ ሊያዝዝ ምንም አልቀረውም ነበር፤

ሆኖም እሱ የመረጠው አገልጋዩ ሙሴ፣

አጥፊ ቁጣውን እንዲመልስ አምላክን ተማጸነ።*+

24 ከዚያም የተወደደችውን ምድር ናቁ፤+

በገባው ቃል ላይ እምነት አልነበራቸውም።+

25 በድንኳኖቻቸው ውስጥ ሆነው ማጉረምረማቸውን ቀጠሉ፤+

የይሖዋን ድምፅ አልሰሙም።+

26 በመሆኑም በምድረ በዳ ሊጥላቸው፣

ስለ እነሱ እጁን አንስቶ ማለ፤+

27 ዘራቸውን በብሔራት መካከል እንደሚጥል፣

በየአገሩ እንደሚበትናቸውም ማለ።+

28 ከዚያም በፌጎር የነበረውን ባአል አመለኩ፤*+

ለሙታን የቀረቡትን መሥዋዕቶችም* በሉ።

29 በሥራቸው አምላክን አስቆጡት፤+

በመካከላቸውም መቅሰፍት ተነሳ።+

30 ሆኖም ፊንሃስ ተነስቶ እርምጃ በወሰደ ጊዜ፣

መቅሰፍቱ ተገታ።+

31 ይህም በትውልዶች ሁሉ፣ ለዘላለም

ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት።+

32 በመሪባ* ውኃ አጠገብ አምላክን አስቆጡት፤

በእነሱም የተነሳ ሙሴ ችግር ላይ ወደቀ።+

33 መንፈሱን አስመረሩት፤

እሱም በከንፈሮቹ በችኮላ ተናገረ።+

34 ይሖዋ ባዘዛቸው መሠረት፣+

ሕዝቦቹን ከማጥፋት ወደኋላ አሉ።+

35 ይልቁንም በዚያ ከነበሩት ብሔራት ጋር ተቀላቀሉ፤+

የእነሱንም መንገድ ተከተሉ።*+

36 ጣዖቶቻቸውን አመለኩ፤+

እነሱም ወጥመድ ሆኑባቸው።+

37 ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን

ለአጋንንት መሥዋዕት አድርገው ያቀርቡ ነበር።+

38 ንጹሕ ደም፣

ይኸውም ለከነአን ጣዖቶች የሠዉአቸውን+

የገዛ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ደም አፈሰሱ፤+

ምድሪቱም በደም ተበከለች።

39 በሥራቸው ረከሱ፤

በድርጊታቸውም መንፈሳዊ ምንዝር ፈጸሙ።+

40 በመሆኑም የይሖዋ ቁጣ በሕዝቡ ላይ ነደደ፤

ርስቱንም ተጸየፈ።

41 በተደጋጋሚ ጊዜያት በብሔራት እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤+

ይህም የሚጠሏቸው ሰዎች እንዲገዟቸው ነው።+

42 ጠላቶቻቸው ጨቆኗቸው፤

ለእነሱም ሥልጣን* ተገዢ ሆኑ።

43 ብዙ ጊዜ ታደጋቸው፤+

እነሱ ግን ያምፁና ለመታዘዝ አሻፈረኝ ይሉ ነበር፤+

ከሠሩት ጥፋት የተነሳም ተዋረዱ።+

44 እሱ ግን ጭንቀታቸውን ይመለከት፣+

እርዳታ ለማግኘት የሚያሰሙትንም ጩኸት ይሰማ ነበር።+

45 ለእነሱ ሲል ቃል ኪዳኑን ያስታውስ ነበር፤

ታላቅ በሆነው* ታማኝ ፍቅሩ ተገፋፍቶ ያዝንላቸው* ነበር።+

46 የማረኳቸው ሰዎች ሁሉ

በሐዘኔታ እንዲይዟቸው ያደርግ ነበር።+

47 ይሖዋ አምላካችን ሆይ፣ አድነን፤+

ደግሞም ለቅዱስ ስምህ ምስጋና እንድናቀርብ፣

አንተንም በማወደስ ሐሴት እንድናደርግ፣*+

ከብሔራት ሰብስበን።+

48 የእስራኤል አምላክ ይሖዋ

ከዘላለም እስከ ዘላለም ይወደስ፤+

ሕዝቦችም ሁሉ “አሜን!”* ይበሉ።

ያህን አወድሱ!*

አምስተኛ መጽሐፍ

(መዝሙር 107-150)

107 ይሖዋ ጥሩ+ ስለሆነ ምስጋና አቅርቡለት፤

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።+

 2 ይሖዋ የዋጃቸው፣*

አዎ፣ ከጠላት እጅ* የዋጃቸው+ ይህን ይበሉ፤

 3 ከምሥራቅና ከምዕራብ፣*

ከሰሜንና ከደቡብ፣

ከየአገሩ አንድ ላይ የሰበሰባቸው+ ይህን ይናገሩ።

 4 በምድረ በዳ፣ በበረሃም ተቅበዘበዙ፤

ሊኖሩ ወደሚችሉበት ከተማ የሚወስድ መንገድ አላገኙም።

 5 ተርበውና ተጠምተው ነበር፤

ኃይላቸው ከመሟጠጡ የተነሳ ተዝለፈለፉ።*

 6 በተጨነቁ ጊዜ ወደ ይሖዋ ይጮኹ ነበር፤+

እሱም ከደረሰባቸው መከራ ታደጋቸው።+

 7 መኖር ወደሚችሉበት ከተማ እንዲደርሱ+

በትክክለኛው መንገድ መራቸው።+

 8 ሕዝቦች ስለ ታማኝ ፍቅሩና

ለሰው ልጆች ስላደረጋቸው አስደናቂ ሥራዎች+ ይሖዋን ያመስግኑት።+

 9 እሱ የተጠማውን* አርክቷልና፤

የተራበውንም* በመልካም ነገሮች አጥግቧል።+

10 አንዳንዶች በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ የሚኖሩ፣

በመከራ ውስጥ ያሉና በሰንሰለት የተጠፈሩ እስረኞች ነበሩ።

11 በአምላክ ቃል ላይ ዓምፀዋልና፤

የልዑሉን አምላክ ምክር ንቀዋል።+

12 ስለዚህ በደረሰባቸው መከራ ልባቸው እንዲለሰልስ አደረገ፤+

ተሰናከሉ፤ የሚረዳቸውም አንዳች ሰው አልነበረም።

13 በተጨነቁ ጊዜ እርዳታ ለማግኘት ወደ ይሖዋ ተጣሩ፤

እሱም ከደረሰባቸው መከራ አዳናቸው።

14 ከድቅድቅ ጨለማ አወጣቸው፤

የታሰሩበትንም ሰንሰለት በጠሰ።+

15 ሕዝቦች ስለ ታማኝ ፍቅሩና

ለሰው ልጆች ስላደረጋቸው አስደናቂ ሥራዎች ይሖዋን ያመስግኑት።+

16 እሱ የመዳብ በሮችን ሰብሯልና፤

የብረት መወርወሪያዎችንም ቆርጧል።+

17 ከጥፋታቸውና ከበደላቸው የተነሳ+

ሞኝ ሆኑ፤ ለመከራም ተዳረጉ።+

18 የምግብ ፍላጎታቸው ሙሉ በሙሉ ጠፋ፤*

ወደ ሞት ደጆች ቀረቡ።

19 በተጨነቁ ጊዜ እርዳታ ለማግኘት ወደ ይሖዋ ይጣሩ ነበር፤

እሱም ከደረሰባቸው መከራ ያድናቸው ነበር።

20 ቃሉን ልኮ ይፈውሳቸው፣+

ከተያዙበትም ጉድጓድ ይታደጋቸው ነበር።

21 ሕዝቦች ስለ ታማኝ ፍቅሩና

ለሰው ልጆች ስላደረጋቸው አስደናቂ ሥራዎች ይሖዋን ያመስግኑት።

22 የምስጋና መሥዋዕት ያቅርቡ፤+

በእልልታም ሥራዎቹን ያስታውቁ።

23 በባሕር ላይ በመርከቦች የሚጓዙ፣

በሰፋፊ ውኃዎች ላይ ንግድ የሚያካሂዱ፣+

24 እነሱ የይሖዋን ሥራዎች፣

በጥልቁም ውስጥ ያከናወናቸውን አስደናቂ ነገሮች+ ተመልክተዋል፤

25 እሱ በቃሉ አውሎ ነፋስ ሲያስነሳ፣+

የባሕሩንም ማዕበል ሲያናውጥ አይተዋል።

26 ወደ ሰማይ ይወጣሉ፣

ወደ ጥልቆችም ይወርዳሉ።

እየመጣባቸው ካለው መከራ የተነሳ ሐሞታቸው ፈሰሰ።*

27 እንደሰከረ ሰው ይንገዳገዳሉ፤ ደግሞም ይወላገዳሉ፤

ችሎታቸውም ሁሉ የፈየደላቸው ነገር የለም።+

28 በዚህ ጊዜ ከጭንቀታቸው የተነሳ ወደ ይሖዋ ይጮኻሉ፤+

እሱም ከደረሰባቸው መከራ ይታደጋቸዋል።

29 አውሎ ነፋሱ እንዲቆም ያደርጋል፤

የባሕሩም ሞገዶች ጸጥ ይላሉ።+

30 ሞገዶቹ ጸጥ ሲሉ ሰዎቹ ሐሴት ያደርጋሉ፤

እሱም ወዳሰቡት ወደብ ይመራቸዋል።

31 ሕዝቦች ስለ ታማኝ ፍቅሩና

ለሰው ልጆች ስላደረጋቸው አስደናቂ ሥራዎች ይሖዋን ያመስግኑት።+

32 በሕዝብ ጉባኤ መካከል ከፍ ከፍ ያድርጉት፤+

በሽማግሌዎችም ሸንጎ* ያወድሱት።

33 እሱ ወንዞችን ወደ በረሃ፣

የውኃ ምንጮችንም ወደ ደረቅ መሬት ይለውጣል፤+

34 ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሳ

ፍሬያማዋን አገር ጨዋማ የሆነ ጠፍ ምድር ያደርጋታል።+

35 በረሃውን ቄጠማ የሞላበት ኩሬ፣

ደረቁንም ምድር የውኃ ምንጭ ያደርጋል።+

36 ሊኖሩ የሚችሉበትን ከተማ እንዲመሠርቱ፣+

የተራቡ ሰዎችን በዚያ ያኖራል።+

37 መሬት ላይ ዘሩ፤ ወይንም ተከሉ፤+

መሬቱም ብዙ ምርት ሰጠ።+

38 እሱ ይባርካቸዋል፤ እነሱም እጅግ ይበዛሉ፤

የከብቶቻቸው ብዛት እንዲያንስ አያደርግም።+

39 ሆኖም ከደረሰባቸው ጭቆና፣ መከራና ሐዘን የተነሳ

ዳግመኛ ቁጥራቸው ተመናመነ፤ ተዋረዱም።

40 በታላላቅ ሰዎች ላይ የውርደት መዓት ያዘንባል፤

መንገድ በሌለበት ጠፍ መሬትም እንዲቅበዘበዙ ያደርጋል።+

41 ድሆችን ግን ከጭቆና ይጠብቃል፤*+

ቤተሰባቸውንም እንደ መንጋ ያበዛል።

42 ቅኖች ይህን አይተው ሐሴት ያደርጋሉ፤+

ዓመፀኞች ሁሉ ግን አፋቸውን ይዘጋሉ።+

43 ጥበበኛ የሆነ ሁሉ እነዚህን ነገሮች ልብ ይላል፤+

ደግሞም ይሖዋ በታማኝ ፍቅር ያከናወናቸውን ነገሮች በትኩረት ይመለከታል።+

መዝሙር። የዳዊት ማህሌት።

108 አምላክ ሆይ፣ ልቤ ጽኑ ነው።

በሁለንተናዬ እዘምራለሁ፤ ደግሞም አዜማለሁ።+

 2 ባለ አውታር መሣሪያ ሆይ፣ አንተም በገና ሆይ፣+ ተነሱ።

እኔም በማለዳ እነሳለሁ።

 3 ይሖዋ ሆይ፣ በሕዝቦች መካከል አወድስሃለሁ፤

በብሔራትም መካከል የውዳሴ መዝሙር እዘምርልሃለሁ።

 4 ታማኝ ፍቅርህ ታላቅ ነውና፤ እንደ ሰማያት ከፍ ያለ ነው፤+

ታማኝነትህም እስከ ደመናት ድረስ ነው።

 5 አምላክ ሆይ፣ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል፤

ክብርህ በምድር ሁሉ ላይ ይሁን።+

 6 የምትወዳቸው ሰዎች እንዲድኑ

በቀኝ እጅህ ታደገን፤ ደግሞም መልስ ስጠኝ።+

 7 አምላክ በቅድስናው* እንዲህ ብሏል፦

“ሐሴት አደርጋለሁ፤ ሴኬምን ርስት አድርጌ እሰጣለሁ፤+

የሱኮትንም ሸለቆ* አከፋፍላለሁ።+

 8 ጊልያድም+ ሆነ ምናሴ የእኔ ናቸው፤

ኤፍሬምም የራስ ቁሬ ነው፤*+

ይሁዳ በትረ መንግሥቴ ነው።+

 9 ሞዓብ መታጠቢያ ገንዳዬ ነው።+

በኤዶም ላይ ጫማዬን እጥላለሁ።+

በፍልስጤም ላይ በድል አድራጊነት እጮኻለሁ።”+

10 ወደተመሸገችው ከተማ ማን ይወስደኛል?

እስከ ኤዶም ድረስ ማን ይመራኛል?+

11 አምላክ ሆይ፣ ገሸሽ ያደረግከን አንተ አይደለህም?

አምላካችን ሆይ፣ ከሠራዊታችን ጋር አብረህ አትወጣም።+

12 ከጭንቅ እንድንገላገል እርዳን፤+

የሰው ማዳን ከንቱ ነውና።+

13 አምላክ ኃይል ይሰጠናል፤+

ጠላቶቻችንንም ይረጋግጣቸዋል።+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት መዝሙር። ማህሌት።

109 የማወድስህ አምላክ ሆይ፣+ ዝም አትበል።

 2 ክፉዎችና አታላዮች በእኔ ላይ አፋቸውን ይከፍታሉና።

ስለ እኔ በሐሰተኛ አንደበት ይናገራሉ፤+

 3 በዙሪያዬም ሆነው የጥላቻ ቃላት ይሰነዝሩብኛል፤

ያለምክንያት ያጠቁኛል።+

 4 ፍቅር ሳሳያቸው በምላሹ ይቃወሙኛል፤+

እኔ ግን መጸለዬን እቀጥላለሁ።

 5 ለመልካም ነገር ክፋትን፣

ላሳየኋቸው ፍቅር ጥላቻን ይመልሱልኛል።+

 6 በእሱ ላይ ክፉ ሰው እዘዝበት፤

በቀኙም ተቃዋሚ* ይቁም።

 7 ፍርድ ፊት ሲቆም በደለኛ* ሆኖ ይገኝ፤

ጸሎቱም እንኳ እንደ ኃጢአት ይቆጠርበት።+

 8 የሕይወት ዘመኑ አጭር ይሁን፤+

የበላይ ተመልካችነት ሹመቱን ሌላ ሰው ይውሰደው።+

 9 ልጆቹ* ያለአባት ይቅሩ፤

ሚስቱም መበለት ትሁን።

10 ልጆቹ* በየቦታው የሚቅበዘበዙ ለማኞች ይሁኑ፤

ከፈራረሰው መኖሪያቸው ወጥተው ምግብ ፍለጋ ይንከራተቱ።

11 ያበደረው ሰው ያለውን ነገር ሁሉ ይውሰድበት፤*

ባዕድ ሰዎችም ንብረቱን ይዝረፉት።

12 ደግነት* የሚያሳየው ሰው ከቶ አይኑር፤

ያለአባት ለቀሩት ልጆቹ የሚራራ አንድም ሰው አይገኝ።

13 ዘሩ* ይጥፋ፤+

ስማቸው በአንድ ትውልድ ውስጥ ይደምሰስ።

14 አባቶቹ የሠሩትን በደል ይሖዋ አይርሳ፤+

የእናቱም ኃጢአት አይደምሰስ።

15 ይሖዋ የሠሩትን ነገር ምንጊዜም ያስብ፤

መታሰቢያቸውንም ከምድር ገጽ ያጥፋ።+

16 ክፉው ሰው ደግነት* ለማሳየት አላሰበምና፤+

ይልቁንም የተጨቆነውን፣ ድሃውንና ልቡ በሐዘን የተደቆሰውን ሰው

ለመግደል ሲያሳድድ ነበር።+

17 ሌሎችን መርገም ወደደ፤ በመሆኑም እርግማኑ በእሱ ላይ ደረሰበት፤

ሌሎችን ለመባረክ ፍላጎት አልነበረውም፤ ስለዚህ ምንም በረከት አላገኘም።

18 እርግማንን እንደ ልብስ ለበሰ።

እንደ ውኃም ሰውነቱ ውስጥ ፈሰሰ፤

እንደ ዘይት ወደ አጥንቶቹ ዘለቀ።

19 እርግማኑ እንደሚከናነበው ልብስ፣

ሁልጊዜ እንደሚታጠቀውም ቀበቶ ይሁንለት።+

20 እኔን የሚቃወመኝ ሰው፣

በእኔም* ላይ ክፉ ነገር የሚናገሩ ሰዎች ከይሖዋ የሚያገኙት ዋጋ ይህ ነው።+

21 አንተ ግን ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣

ለስምህ ስትል እርዳኝ።+

ታማኝ ፍቅርህ ጥሩ ስለሆነ ታደገኝ።+

22 እኔ ምስኪንና ድሃ ነኝና፤+

ልቤም በውስጤ ተወግቷል።+

23 ፀሐይ ስትጠልቅ እንደሚጠፋ ጥላ አልፋለሁ፤

እንደ አንበጣ አራግፈው ጣሉኝ።

24 ከመጾሜ የተነሳ ጉልበቶቼ ከዱኝ፤

ሰውነቴ ከሳ፤ እኔም እየመነመንኩ ሄድኩ።*

25 የእነሱ መሳለቂያ ሆንኩ።+

ሲያዩኝ ራሳቸውን ይነቀንቃሉ።+

26 ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ እርዳኝ፤

በታማኝ ፍቅርህ አድነኝ።

27 ይህ የአንተ እጅ መሆኑን ይወቁ፤

ይሖዋ ሆይ፣ ይህን ያደረግከው አንተ እንደሆንክ ይገንዘቡ።

28 እነሱ ይራገሙ፤ አንተ ግን ባርክ።

እነሱ በእኔ ላይ ሲነሱ ለኀፍረት ይዳረጉ፤

አገልጋይህ ግን ሐሴት ያድርግ።

29 እኔን የሚቃወሙኝ ውርደት ይከናነቡ፤

ኀፍረታቸውንም እንደ ልብስ* ይጎናጸፉ።+

30 አንደበቴ ይሖዋን ከልብ ታወድሰዋለች፤

በብዙ ሕዝቦች ፊት አወድሰዋለሁ።+

31 በእሱ* ላይ ከሚፈርዱት ሊያድነው

በድሃው ቀኝ ይቆማልና።

የዳዊት መዝሙር። ማህሌት።

110 ይሖዋ ጌታዬን

“ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስከማደርግልህ ድረስ+

በቀኜ ተቀመጥ”+ አለው።

 2 ይሖዋ የኃይልህን በትር ከጽዮን ይዘረጋል፤

“በጠላቶችህ መካከል በድል አድራጊነት ግዛ”*+ ይላል።

 3 ወደ ጦርነት በምትዘምትበት ቀን*

ሕዝብህ በገዛ ፈቃዱ ራሱን ያቀርባል።

በቅድስና ተውበህ ሳለ፣ ከንጋት ማህፀን እንደወጣ ጤዛ ያለ የወጣቶች ሠራዊት ከጎንህ ይሰለፋል።

 4 ይሖዋ “እንደ መልከጼዴቅ፣+

አንተ ለዘላለም ካህን ነህ!” ሲል ምሏል፤+

ደግሞም ሐሳቡን አይለውጥም።*

 5 ይሖዋ በቀኝህ ይሆናል፤+

በቁጣው ቀን ነገሥታትን ያደቃል።+

 6 በብሔራት ላይ* የፍርድ እርምጃ ይወስዳል፤+

ምድሪቱንም ሬሳ በሬሳ ያደርጋል።+

ሰፊ የሆነውን አገር* የሚገዛውን መሪ* ያደቀዋል።

 7 እሱ* በመንገድ ዳር ካለው ጅረት ይጠጣል።

በመሆኑም ራሱን ቀና ያደርጋል።

111 ያህን አወድሱ!*+

א [አሌፍ]

ቅኖች በተሰበሰቡበት ማኅበርና በጉባኤ

ב [ቤት]

ይሖዋን በሙሉ ልቤ አወድሰዋለሁ።+

ג [ጊሜል]

 2 የይሖዋ ሥራ ታላቅ ነው፤+

ד [ዳሌት]

በሥራው የሚደሰቱ ሰዎች ሁሉ ያጠኑታል።+

ה [ሄ]

 3 ሥራው ግርማና ውበት የተላበሰ ነው፤

ו [ዋው]

ጽድቁም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።+

ז [ዛየን]

 4 አስደናቂ ሥራዎቹ እንዲታወሱ ያደርጋል።+

ח [ኼት]

ይሖዋ ሩኅሩኅና* መሐሪ ነው።+

ט [ቴት]

 5 ለሚፈሩት ምግብ ይሰጣል።+

י [ዮድ]

ቃል ኪዳኑን ለዘላለም ያስታውሳል።+

כ [ካፍ]

 6 የብሔራትን ርስት በመስጠት፣+

ל [ላሜድ]

ኃያል ሥራዎቹን ለሕዝቡ ገልጧል።

ס [ሜም]

 7 የእጆቹ ሥራዎች እውነትና ፍትሕ ናቸው፤+

נ [ኑን]

መመሪያዎቹ ሁሉ እምነት የሚጣልባቸው ናቸው።+

ס [ሳሜኽ]

 8 አሁንም ሆነ ለዘላለም፣ ምንጊዜም አስተማማኝ* ናቸው፤

ע [አይን]

በእውነትና በጽድቅ ላይ የተመሠረቱ ናቸው።+

פ [ፔ]

 9 ሕዝቡን ዋጀ።+

צ [ጻዴ]

ቃል ኪዳኑ ለዘላለም እንዲጸና አዘዘ።

ק [ኮፍ]

ስሙ ቅዱስና እጅግ የሚፈራ ነው።+

ר [ረሽ]

10 ይሖዋን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው።+

ש [ሺን]

መመሪያዎቹን የሚጠብቁ* ሁሉ ጥሩ ማስተዋል አላቸው።+

ת [ታው]

ውዳሴው ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።

112 ያህን አወድሱ!*+

א [አሌፍ]

ይሖዋን የሚፈራና+

ב [ቤት]

ትእዛዛቱን እጅግ የሚወድ ሰው ደስተኛ ነው።+

ג [ጊሜል]

 2 ዘሮቹ በምድር ላይ ኃያላን ይሆናሉ።

ד [ዳሌት]

ደግሞም የቅኖች ትውልድ ይባረካል።+

ה [ሄ]

 3 በቤቱ ሀብትና ንብረት አለ፤

ו [ዋው]

ጽድቁም ለዘላለም ይኖራል።

ז [ዛየን]

 4 ለቅኖች በጨለማ ውስጥ እንደ ብርሃን ያበራል።+

ח [ኼት]

ሩኅሩኅና* መሐሪ+ እንዲሁም ጻድቅ ነው።

ט [ቴት]

 5 በልግስና የሚያበድር ሰው ይሳካለታል።+

י [ዮድ]

ጉዳዩን በፍትሕ ያከናውናል።

כ [ካፍ]

 6 እሱ ፈጽሞ አይናወጥም።+

ל [ላሜድ]

ጻድቅ ለዘላለም ሲታወስ ይኖራል።+

מ [ሜም]

 7 ክፉ ወሬ አያስፈራውም።+

נ [ኑን]

በይሖዋ ስለሚተማመን ልቡ ጽኑ ነው።+

ס [ሳሜኽ]

 8 ልቡ አይናወጥም፤* አይፈራምም፤+

ע [አይን]

በመጨረሻም ጠላቶቹን በድል አድራጊነት ይመለከታል።+

פ [ፔ]

 9 በብዛት* አከፋፈለ፤ ለድሆችም ሰጠ።+

צ [ጻዴ]

ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል።+

ק [ኮፍ]

የገዛ ብርታቱ* በክብር ከፍ ከፍ ይላል።

ר [ረሽ]

10 ክፉ ሰው አይቶ ይበሳጫል።

ש [ሺን]

ጥርሱን ያፋጫል፤ ቀልጦም ይጠፋል።

ת [ታው]

የክፉዎች ምኞት ይከስማል።+

113 ያህን አወድሱ!*

እናንተ የይሖዋ አገልጋዮች፣ ውዳሴ አቅርቡ፤

የይሖዋን ስም አወድሱ።

 2 ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም፣

የይሖዋ ስም ይወደስ።+

 3 ከፀሐይ መውጫ አንስቶ እስከ መግቢያው ድረስ

የይሖዋ ስም ይወደስ።+

 4 ይሖዋ ከብሔራት ሁሉ በላይ ከፍ ያለ ነው፤+

ክብሩም ከሰማያት በላይ ነው።+

 5 ከፍ ባለ ቦታ እንደሚኖረው*

እንደ አምላካችን እንደ ይሖዋ ያለ ማን ነው?+

 6 ሰማይንና ምድርን ለማየት ወደ ታች ያጎነብሳል፤+

 7 ችግረኛውን ከአፈር ያነሳል።

ድሃውን ከአመድ ቁልል* ላይ ብድግ ያደርገዋል፤+

 8 ይህም ከታላላቅ ሰዎች፣

ይኸውም በሕዝቡ መካከል ካሉ ታላላቅ ሰዎች ጋር ያስቀምጠው ዘንድ ነው።

 9 መሃኒቱ ሴት፣ ደስተኛ የልጆች* እናት+ ሆና እንድትኖር

ቤት ይሰጣታል።

ያህን አወድሱ!*

114 እስራኤል ከግብፅ ሲወጣ፣+

የያዕቆብ ቤት ባዕድ ቋንቋ ከሚናገር ሕዝብ ተለይቶ ሲሄድ፣

 2 ይሁዳ መቅደሱ፣*

እስራኤልም ግዛቱ ሆነ።+

 3 ባሕሩ ይህን አይቶ ሸሸ፤+

ዮርዳኖስ ወደ ኋላ ተመለሰ።+

 4 ተራሮች እንደ አውራ በግ፣

ኮረብቶች እንደ ጠቦት ፈነጩ።+

 5 አንተ ባሕር ሆይ፣ የሸሸኸው ምን ሆነህ ነው?+

ዮርዳኖስ ሆይ፣ ወደ ኋላ የተመለስከው ለምንድን ነው?+

 6 ተራሮች ሆይ፣ እንደ አውራ በግ የዘለላችሁት፣

እናንተ ኮረብቶች፣ እንደ ጠቦት የፈነጫችሁት ለምንድን ነው?

 7 ምድር ሆይ፣ ከጌታ የተነሳ፣

ከያዕቆብም አምላክ የተነሳ ተንቀጥቀጪ፤+

 8 እሱ ዓለቱን ቄጠማ ወደሞላበት ኩሬ፣

ጠንካራውንም ዓለት ወደ ውኃ ምንጮች ይለውጣል።+

115 ከታማኝ ፍቅርህና ከታማኝነትህ የተነሳ+

ለእኛ ሳይሆን፣ ይሖዋ ሆይ፣ ለእኛ ሳይሆን፣*

ለስምህ ክብር ስጥ።+

 2 ብሔራት “አምላካቸው የት አለ?”

ለምን ይበሉ?+

 3 አምላካችን ያለው በሰማያት ነው፤

እሱ የወደደውን ሁሉ ያደርጋል።

 4 የእነሱ ጣዖቶች ከብርና ከወርቅ የተሠሩ፣

የሰው እጅ ሥራ ናቸው።+

 5 አፍ አላቸው፤ መናገር ግን አይችሉም፤+

ዓይን አላቸው፤ ማየት ግን አይችሉም፤

 6 ጆሮ አላቸው፤ መስማት ግን አይችሉም፤

አፍንጫ አላቸው፤ ማሽተት ግን አይችሉም፤

 7 እጅ አላቸው፤ መዳሰስ ግን አይችሉም፤

እግር አላቸው፤ መራመድ ግን አይችሉም፤+

በጉሮሯቸው የሚያሰሙት ድምፅ የለም።+

 8 የሚሠሯቸውም ሆኑ የሚታመኑባቸው ሁሉ፣

እንደ እነሱ ይሆናሉ።+

 9 እስራኤል ሆይ፣ በይሖዋ ታመኑ፤+

እሱ ረዳታቸውና ጋሻቸው ነው።+

10 የአሮን ቤት ሆይ፣+ በይሖዋ ታመኑ፤

እሱ ረዳታቸውና ጋሻቸው ነው።

11 እናንተ ይሖዋን የምትፈሩ፣ በይሖዋ ታመኑ፤+

እሱ ረዳታቸውና ጋሻቸው ነው።+

12 ይሖዋ ያስታውሰናል፤ ደግሞም ይባርከናል፤

የእስራኤልን ቤት ይባርካል፤+

የአሮንን ቤት ይባርካል።

13 ይሖዋ እሱን የሚፈሩትን፣

ታናናሾችንም ሆነ ታላላቆችን ይባርካል።

14 ይሖዋ እናንተን፣

አዎ፣ እናንተንና ልጆቻችሁን* ያበዛል።+

15 ሰማይንና ምድርን የሠራው+

ይሖዋ ይባርካችሁ።+

16 ሰማያት የይሖዋ ናቸው፤+

ምድርን ግን ለሰው ልጆች ሰጣት።+

17 ሙታንም ሆኑ ወደ ዝምታው ዓለም* የሚወርዱ ሁሉ፣+

ያህን አያወድሱም።+

18 እኛ ግን ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም፣

ያህን እናወድሳለን።

ያህን አወድሱ!*

116 ይሖዋ ድምፄን፣

እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና ስለሚሰማ እወደዋለሁ።*+

 2 ጆሮውን ወደ እኔ ያዘነብላልና፣*+

በሕይወት እስካለሁ ድረስ* እሱን እጣራለሁ።

 3 የሞት ገመዶች ተተበተቡብኝ፤

መቃብር ያዘኝ።*+

በጭንቀትና በሐዘን ተዋጥኩ።+

 4 እኔ ግን የይሖዋን ስም ጠራሁ፦+

“ይሖዋ ሆይ፣ ታደገኝ!”*

 5 ይሖዋ ሩኅሩኅና* ጻድቅ ነው፤+

አምላካችን መሐሪ ነው።+

 6 ይሖዋ ተሞክሮ የሌላቸውን ይጠብቃል።+

ተስፋ ቆርጬ ነበር፤ እሱ ግን አዳነኝ።

 7 ነፍሴ* ዳግመኛ እረፍት ታግኝ፤

ይሖዋ ደግነት አሳይቶኛልና።

 8 እኔን* ከሞት፣ ዓይኔን ከእንባ፣

እግሬንም ከእንቅፋት ታድገሃል።+

 9 በሕያዋን ምድር በይሖዋ ፊት እሄዳለሁ።

10 አመንኩ ስለዚህም ተናገርኩ፤+

እጅግ ተጎሳቁዬ ነበር።

11 በጣም ደንግጬ

“ሰው ሁሉ ውሸታም ነው”+ አልኩ።

12 ላደረገልኝ መልካም ነገር ሁሉ

ለይሖዋ ምን እመልስለታለሁ?

13 የማዳንን ጽዋ አነሳለሁ፤

የይሖዋንም ስም እጠራለሁ።

14 በሕዝቡ ሁሉ ፊት

ስእለቴን ለይሖዋ እፈጽማለሁ።+

15 የታማኝ አገልጋዮቹ ሞት

በይሖዋ ዓይን ከባድ ነገር* ነው።+

16 ይሖዋ ሆይ፣

እኔ አገልጋይህ ስለሆንኩ እለምንሃለሁ።

እኔ የሴት ባሪያህ ልጅ፣ አገልጋይህ ነኝ።

አንተ ከእስራቴ ነፃ አውጥተኸኛል።+

17 ለአንተ የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ፤+

የይሖዋን ስም እጠራለሁ።

18 በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣

ስእለቴን ለይሖዋ እፈጽማለሁ፤+

19 በይሖዋ ቤት ቅጥር ግቢዎች፣+

በኢየሩሳሌም መካከል ስእለቴን አቀርባለሁ።

ያህን አወድሱ!*+

117 ብሔራት ሁሉ፣ ይሖዋን አወድሱት፤+

ሕዝቦች* ሁሉ፣ ከፍ ከፍ አድርጉት።+

 2 ለእኛ ያሳየው ታማኝ ፍቅር ታላቅ ነውና፤+

የይሖዋ ታማኝነት+ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።+

ያህን አወድሱ!*+

118 ይሖዋ ጥሩ+ ስለሆነ ምስጋና አቅርቡለት፤

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።

 2 እስራኤል እንዲህ ይበል፦

“ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።”

 3 ከአሮን ቤት የሆኑ እንዲህ ይበሉ፦

“ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።”

 4 ይሖዋን የሚፈሩ እንዲህ ይበሉ፦

“ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።”

 5 በተጨነቅኩ ጊዜ ያህን* ተጣራሁ፤

ያህም መለሰልኝ፤ ደህንነት ወደማገኝበት ስፍራም* አመጣኝ።+

 6 ይሖዋ ከጎኔ ነው፤ አልፈራም።+

ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?+

 7 ይሖዋ ረዳቴ ሆኖ* ከጎኔ አለ፤+

የሚጠሉኝን ሰዎች በድል አድራጊነት እመለከታለሁ።+

 8 በሰው ከመታመን ይልቅ፣

ይሖዋን መጠጊያ ማድረግ ይሻላል።+

 9 በመኳንንት ከመታመን ይልቅ፣

ይሖዋን መጠጊያ ማድረግ ይሻላል።+

10 ብሔራት ሁሉ ከበቡኝ፤

እኔ ግን በይሖዋ ስም

መከትኳቸው።+

11 ከበቡኝ፤ አዎ፣ ዙሪያዬን ከበቡኝ፤

እኔ ግን በይሖዋ ስም

መከትኳቸው።

12 እንደ ንብ ከበቡኝ፤

ሆኖም በእሳት እንደተያያዘ ቁጥቋጦ ወዲያውኑ ጠፉ።

እኔም በይሖዋ ስም

መከትኳቸው።+

13 እወድቅ ዘንድ በኃይል ተገፋሁ፤*

ይሖዋ ግን ረዳኝ።

14 ያህ መጠለያዬና ብርታቴ ነው፤

አዳኝም ሆኖልኛል።+

15 በጻድቃን ድንኳኖች ውስጥ፣

የሐሴትና የመዳን* ድምፅ ይሰማል።

የይሖዋ ቀኝ እጅ ኃይሉን ያሳያል።+

16 የይሖዋ ቀኝ እጅ ከፍ ከፍ አለ፤

የይሖዋ ቀኝ እጅ ኃይሉን ያሳያል።+

17 የያህን ሥራዎች አስታውቅ ዘንድ

በሕይወት እኖራለሁ እንጂ አልሞትም።+

18 ያህ ጠንከር ያለ ተግሣጽ ሰጥቶኛል፤+

ሆኖም ለሞት አሳልፎ አልሰጠኝም።+

19 የጽድቅን በሮች ክፈቱልኝ፤+

በዚያ ገብቼ ያህን አወድሳለሁ።

20 ይህ የይሖዋ በር ነው።

ጻድቃን በዚያ በኩል ይገባሉ።+

21 መልስ ስለሰጠኸኝና

አዳኝ ስለሆንከኝ አወድስሃለሁ።+

22 ግንበኞች የናቁት ድንጋይ

የማዕዘን ራስ ድንጋይ* ሆነ።+

23 ይህ የይሖዋ ሥራ ነው፤+

ለዓይናችንም ድንቅ ነው።+

24 ይህ ይሖዋ የሠራው ቀን ነው፤

በዚህ ቀን እንደሰታለን፤ ሐሴትም እናደርጋለን።

25 ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ እንድታድነን እንለምንሃለን!

ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ ድል አቀዳጀን!

26 በይሖዋ ስም የሚመጣው የተባረከ ነው፤+

በይሖዋ ቤት ሆነን እንባርካችኋለን።

27 ይሖዋ አምላክ ነው፤

ብርሃን ይሰጠናል።+

ቅርንጫፎች በመያዝ ወደ በዓሉ ከሚጓዙት ጋር ተቀላቅላችሁ+

እስከ መሠዊያው ቀንዶች+ ድረስ ሂዱ።

28 አንተ አምላኬ ነህ፤ እኔም አወድስሃለሁ፤

አምላኬ ሆይ፣ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ።+

29 ይሖዋ ጥሩ ስለሆነ ምስጋና አቅርቡለት፤+

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።+

א [አሌፍ]

119 በመንገዳቸው ነቀፋ የሌለባቸው፣*

በይሖዋ ሕግ የሚመላለሱ ሰዎች ደስተኞች ናቸው።+

 2 ማሳሰቢያዎቹን የሚጠብቁ፣+

እሱን በሙሉ ልባቸው የሚፈልጉ ደስተኞች ናቸው።+

 3 ክፉ ነገር አያደርጉም፤

በመንገዶቹ ይሄዳሉ።+

 4 አንተ መመሪያዎችህን

በጥብቅ እንድንከተል አዘኸናል።+

 5 ሥርዓትህን እጠብቅ ዘንድ

ምነው በአቋሜ በጸናሁ!*+

 6 ይህ ቢሆንልኝ፣

ትእዛዛትህን ሁሉ በትኩረት ስመለከት አላፍርም።+

 7 የጽድቅ ፍርዶችህን በተማርኩ ጊዜ

በቀና ልብ አወድስሃለሁ።

 8 ሥርዓትህን አከብራለሁ።

አቤቱ እርግፍ አድርገህ አትተወኝ።

ב [ቤት]

 9 ወጣቶች በንጽሕና መመላለስ የሚችሉት እንዴት ነው?

በቃልህ መሠረት ራሳቸውን በመጠበቅ ነው።+

10 በሙሉ ልቤ አንተን እሻለሁ።

ከትእዛዛትህ እንድርቅ አትፍቀድ።+

11 በአንተ ላይ ኃጢአት እንዳልሠራ፣+

አንተ የተናገርከውን በልቤ ውስጥ እንደ ውድ ሀብት እሸሽጋለሁ።+

12 ይሖዋ ሆይ፣ ውዳሴ ይድረስህ፤

ሥርዓትህን አስተምረኝ።

13 የተናገርካቸውን ፍርዶች ሁሉ

በከንፈሮቼ አስታውቃለሁ።

14 ውድ ከሆኑ ሌሎች ነገሮች ሁሉ ይበልጥ፣+

በማሳሰቢያዎችህ ሐሴት አደርጋለሁ።+

15 በመመሪያዎችህ ላይ አሰላስላለሁ፤*+

ዓይኖቼንም በመንገዶችህ ላይ እተክላለሁ።+

16 ያወጣሃቸውን ደንቦች እወዳቸዋለሁ።

ቃልህን አልረሳም።+

ג [ጊሜል]

17 በሕይወት መኖርና ቃልህን መጠበቅ እችል ዘንድ፣

ለአገልጋይህ ደግነት አሳይ።+

18 በሕግህ ውስጥ ያሉትን አስደናቂ ነገሮች

አጥርቼ እንዳይ ዓይኖቼን ክፈት።

19 በምድሪቱ ላይ የባዕድ አገር ሰው ነኝ።+

ትእዛዛትህን ከእኔ አትሰውር።

20 እኔ* ፍርዶችህን

ዘወትር ከመናፈቄ የተነሳ ዛልኩ።

21 እብሪተኛ የሆኑትን፣

ከትእዛዛትህ የራቁትን የተረገሙ ሰዎች ትገሥጻለህ።+

22 ማሳሰቢያዎችህን ጠብቄአለሁና፣

ዘለፋንና ንቀትን ከእኔ አስወግድ።*

23 መኳንንትም እንኳ አንድ ላይ ተቀምጠው ስለ እኔ መጥፎ ነገር ሲያወሩ፣

አገልጋይህ በሥርዓትህ ላይ ያሰላስላል።*

24 ማሳሰቢያዎችህን እወዳቸዋለሁ፤+

መካሪዎቼ ናቸው።+

ד [ዳሌት]

25 አፈር ላይ ተደፍቻለሁ።*+

በቃልህ መሠረት በሕይወት አቆየኝ።+

26 መንገዶቼን ለአንተ ተናገርኩ፤ አንተም መለስክልኝ፤

ሥርዓትህን አስተምረኝ።+

27 አስደናቂ በሆኑት ሥራዎችህ ላይ አሰላስል ዘንድ፣*+

የመመሪያዎችህን ትርጉም እንዳስተውል አድርገኝ።

28 ከሐዘን የተነሳ እንቅልፍ አጣሁ።*

በቃልህ መሠረት አበርታኝ።

29 የአታላይነትን መንገድ ከእኔ አርቅ፤+

ሕግህንም በማሳወቅ ሞገስ አሳየኝ።

30 የታማኝነትን ጎዳና መርጫለሁ።+

ፍርዶችህ ትክክል እንደሆኑ እገነዘባለሁ።

31 ማሳሰቢያዎችህን የሙጥኝ እላለሁ።+

ይሖዋ ሆይ፣ ለሐዘን* እንድዳረግ አትፍቀድ።+

32 በልቤ ውስጥ ቦታ ስለሰጠኸው፣*

የትእዛዛትህን መንገድ በጉጉት እከተላለሁ።*

ה [ሄ]

33 ይሖዋ ሆይ፣ የሥርዓትህን መንገድ አስተምረኝ፤+

እኔም እስከ መጨረሻው እከተለዋለሁ።+

34 ሕግህን እንዳከብርና

በሙሉ ልቤ እንድጠብቅ

ማስተዋል ስጠኝ።

35 በትእዛዛትህ መንገድ ምራኝ፤*+

በእሱ ደስ እሰኛለሁና።

36 ልቤ የግል ጥቅም* ከማሳደድ+ ይልቅ

ወደ ማሳሰቢያዎችህ እንዲያዘነብል አድርግ።

37 ከንቱ ነገር እንዳያዩ ዓይኖቼን መልስ፤+

በመንገድህ ላይ በሕይወት እንድቀጥል አድርገኝ።

38 አንተ በሌሎች ትፈራ ዘንድ፣

ለአገልጋይህ የገባኸውን ቃል* ፈጽም።*

39 በጣም የምፈራውን ውርደት ከእኔ አርቅ፤

ፍርዶችህ ጥሩ ናቸውና።+

40 መመሪያዎችህን ምን ያህል እንደናፈቅኩ ተመልከት።

በጽድቅህ ሕያው ሆኜ እንድኖር አድርገኝ።

ו [ዋው]

41 ይሖዋ ሆይ፣ ቃል በገባኸው* መሠረት

ታማኝ ፍቅርህንና ማዳንህን ልቅመስ፤+

42 በዚህ ጊዜ ለሚሳለቅብኝ መልስ መስጠት እችላለሁ፤

በቃልህ እታመናለሁና።

43 የእውነትን ቃል ከአፌ አታርቅ፤

በፍርድህ ተስፋ አድርጌአለሁና።*

44 እኔ ሕግህን ዘወትር፣

አዎ፣ ለዘላለም እጠብቃለሁ።+

45 ደህንነት በማገኝበት ስፍራ* እንደ ልቤ እመላለሳለሁ፤+

መመሪያዎችህን ከልቤ እፈልጋለሁና።

46 ስለ ማሳሰቢያዎችህ በነገሥታት ፊት እናገራለሁ፤

ደግሞም አላፍርም።+

47 ትእዛዛትህ ደስ ያሰኙኛል፤

አዎ፣ እወዳቸዋለሁ።+

48 ትእዛዛትህን ስለምወዳቸው+ እጆቼን ከፍ አድርጌ ወደ አንተ እጸልያለሁ፤

በሥርዓትህም ላይ አሰላስላለሁ።*+

ז [ዛየን]

49 ለአገልጋይህ የተናገርከውን ቃል* አስታውስ፤

በዚህ ቃል ተስፋ ሰጥተኸኛል።*

50 በመከራዬ ወቅት መጽናኛ የማገኘው በዚህ ነው፤+

የተናገርከው ቃል በሕይወት አቆይቶኛልና።

51 እብሪተኞች እጅግ ይሳለቁብኛል፤

እኔ ግን ከሕግህ ንቅንቅ አልልም።+

52 ይሖዋ ሆይ፣ ከጥንት ጀምሮ የነበሩትን ፍርዶችህን አስታውሳለሁ፤+

በእነዚህም መጽናኛ አገኛለሁ።+

53 ሕግህን ከተዉ ክፉ ሰዎች የተነሳ

በቁጣ በገንኩ።+

54 በምኖርበት ቦታ* ሁሉ

ሥርዓትህ መዝሙር ሆነልኝ።

55 ይሖዋ ሆይ፣ ሕግህን እጠብቅ ዘንድ

በሌሊት ስምህን አስታውሳለሁ።+

56 ይህን ልማድ አድርጌዋለሁ፤

ምክንያቱም መመሪያዎችህን ጠብቄአለሁ።

ח [ኼት]

57 ይሖዋ ድርሻዬ ነው፤+

ሕግህን ለመጠበቅ ቃል ገብቻለሁ።+

58 በሙሉ ልቤ አንተን እማጸናለሁ፤+

በገባኸው ቃል* መሠረት ሞገስ አሳየኝ።+

59 እግሮቼን ወደ ማሳሰቢያዎችህ እመልስ ዘንድ

መንገዴን መረመርኩ።+

60 ትእዛዛትህን ለመጠበቅ ፈጠንኩ፤

ፈጽሞ አልዘገየሁም።+

61 የክፉዎች ገመድ ተተበተበብኝ፤

ሆኖም ሕግህን አልረሳሁም።+

62 ስለ ጽድቅ ፍርዶችህ አንተን ለማመስገን

እኩለ ሌሊት ላይ እነሳለሁ።+

63 አንተን ለሚፈሩ ሁሉ፣

መመሪያዎችህንም ለሚጠብቁ ባልንጀራ ነኝ።+

64 ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህ ምድርን ይሞላል፤+

ሥርዓትህን አስተምረኝ።

ט [ቴት]

65 ይሖዋ ሆይ፣ በቃልህ መሠረት

ለአገልጋይህ መልካም ነገር አድርገህለታል።

66 ማስተዋልንና እውቀትን አስተምረኝ፤+

በትእዛዛትህ ታምኛለሁና።

67 መከራ ላይ ከመውደቄ በፊት፣ መንገድ ስቼ እሄድ ነበር፤*

አሁን ግን የተናገርከውን እጠብቃለሁ።+

68 አንተ ጥሩ ነህ፤+ ሥራህም ጥሩ ነው።

ሥርዓትህን አስተምረኝ።+

69 እብሪተኞች በውሸት ስሜን ያጎድፋሉ፤

እኔ ግን በሙሉ ልቤ መመሪያዎችህን እጠብቃለሁ።

70 ልባቸው ደንዝዟል፤*+

እኔ ግን ሕግህን እወዳለሁ።+

71 ሥርዓትህን እማር ዘንድ

በመከራ ውስጥ ማለፌ ጥሩ ሆነልኝ።+

72 አንተ ያወጅከው ሕግ ጠቅሞኛል፤+

ለእኔ ከብዙ ወርቅና ብር እጅግ የተሻለ ነው።+

י [ዮድ]

73 እጆችህ ሠሩኝ፤ ደግሞም አበጁኝ።

ትእዛዛትህን እማር ዘንድ

ማስተዋል ስጠኝ።+

74 አንተን የሚፈሩ ሰዎች እኔን አይተው ሐሴት ያደርጋሉ፤

ቃልህ ተስፋዬ ነውና።*+

75 ይሖዋ ሆይ፣ ፍርዶችህ በጽድቅ ላይ የተመሠረቱ እንደሆኑና+

ከታማኝነትህ የተነሳ እንደቀጣኸኝ አውቃለሁ።+

76 ለአገልጋይህ በገባኸው ቃል* መሠረት፣

እባክህ፣ ታማኝ ፍቅርህ+ ያጽናናኝ።

77 በሕይወት መኖሬን እንድቀጥል ምሕረት አሳየኝ፤+

ሕግህን እወዳለሁና።+

78 እብሪተኞች ኀፍረት ይከናነቡ፤

ያላንዳች ምክንያት* በድለውኛልና።

እኔ ግን በመመሪያዎችህ ላይ አሰላስላለሁ።*+

79 አንተን የሚፈሩ፣ ማሳሰቢያዎችህንም የሚያውቁ፣

ወደ እኔ ይመለሱ።

80 ለኀፍረት እንዳልዳረግ፣

ልቤ ነቀፋ በሌለበት መንገድ ሥርዓትህን ይከተል።+

כ [ካፍ]

81 ማዳንህን እናፍቃለሁ፤*+

ቃልህ ተስፋዬ ነውና።*

82 አንተ የተናገርከው ቃል ሲፈጸም ለማየት ዓይኖቼ ይጓጓሉ፤+

“የምታጽናናኝ መቼ ነው?”+ እያልኩ እጠይቃለሁ።

83 ጭስ እንዳደረቀው አቁማዳ ሆኛለሁና፤

ሆኖም ሥርዓትህን አልረሳም።+

84 ባሪያህ በሕይወት የሚቆየው እስከ መቼ ነው?

ስደት በሚያደርሱብኝ ላይ የምትፈርደው መቼ ነው?+

85 ሕግህን የሚጥሱ

እብሪተኛ ሰዎች እኔን ለማጥመድ ጉድጓድ ይቆፍራሉ።

86 ትእዛዛትህ ሁሉ አስተማማኝ ናቸው።

ሰዎች ያለምክንያት ያሳድዱኛል፤ አቤቱ እርዳኝ!+

87 ከምድር ገጽ ሊያጠፉኝ ምንም ያህል አልቀራቸውም ነበር፤

እኔ ግን መመሪያዎችህን አልተውኩም።

88 የተናገርካቸውን ማሳሰቢያዎች እጠብቅ ዘንድ፣

ከታማኝ ፍቅርህ የተነሳ በሕይወት አቆየኝ።

ל [ላሜድ]

89 ይሖዋ ሆይ፣ ቃልህ በሰማያት፣

ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።+

90 ታማኝነትህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው።+

ምድር ለዘለቄታው እንድትኖር በጽኑ መሠረትካት።+

91 በፍርዶችህ መሠረት እስከ ዛሬ ጸንተው ኖረዋል፤*

ሁሉም አገልጋዮችህ ናቸውና።

92 ሕግህን ባልወድ ኖሮ፣

በደረሰብኝ ጉስቁልና በጠፋሁ ነበር።+

93 መመሪያዎችህን ፈጽሞ አልረሳም፤

ምክንያቱም በእነሱ አማካኝነት በሕይወት አቆይተኸኛል።+

94 እኔ የአንተ ነኝ፤

መመሪያዎችህን ፈልጌአለሁና+ አድነኝ።+

95 ክፉዎች እኔን ለማጥፋት ያደባሉ፤

እኔ ግን ለማሳሰቢያዎችህ ትኩረት እሰጣለሁ።

96 ፍጽምና ሁሉ ገደብ እንዳለው አይቻለሁ።

ትእዛዝህ ግን ገደብ የለውም።*

מ [ሜም]

97 ሕግህን ምንኛ ወደድኩ!+

ቀኑን ሙሉ አሰላስለዋለሁ።*+

98 ትእዛዝህ ለዘላለም ስለማይለየኝ፣

ከጠላቶቼ ይበልጥ ጥበበኛ ያደርገኛል።+

99 በማሳሰቢያዎችህ ላይ ስለማሰላስል፣*

ከአስተማሪዎቼ ሁሉ የበለጠ ጥልቅ ማስተዋል አለኝ።+

100 መመሪያዎችህን ስለማከብር፣

ከሽማግሌዎች ይበልጥ በማስተዋል እመላለሳለሁ።

101 ቃልህን እጠብቅ ዘንድ፣

በየትኛውም ክፉ መንገድ ከመሄድ እቆጠባለሁ።+

102 አንተ አስተምረኸኛልና፣

ከፍርዶችህ ፈቀቅ አልልም።

103 የተናገርከው ነገር ለምላሴ እጅግ ጣፋጭ ነው፤

ለአፌም ከማር የበለጠ ይጥማል!+

104 ከመመሪያዎችህ የተነሳ በማስተዋል እመላለሳለሁ።+

ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ሁሉ እጠላለሁ።+

נ [ኑን]

105 ቃልህ ለእግሬ መብራት፣

ለመንገዴም ብርሃን ነው።+

106 የጽድቅ ፍርዶችህን ለመጠበቅ ምያለሁ፤

ደግሞም እፈጽመዋለሁ።

107 ከፍተኛ ጉስቁልና ደርሶብኛል።+

ይሖዋ ሆይ፣ በቃልህ መሠረት በሕይወት አቆየኝ።+

108 ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ በፈቃደኝነት የማቀርበውን የውዳሴ መባ* በደስታ ተቀበል፤+

ፍርዶችህንም አስተምረኝ።+

109 ሕይወቴ ሁልጊዜ አደጋ ላይ ናት፤*

እኔ ግን ሕግህን አልረሳሁም።+

110 ክፉዎች ወጥመድ ዘረጉብኝ፤

እኔ ግን ከመመሪያዎችህ ዝንፍ አላልኩም።+

111 ማሳሰቢያዎችህ ልቤን ደስ ስለሚያሰኙ፣+

ቋሚ ንብረቴ* አደርጋቸዋለሁ።

112 ሥርዓትህን በሕይወቴ ዘመን ሁሉ፣

እስከ መጨረሻው ለመጠበቅ ቆርጫለሁ።*

ס [ሳሜኽ]

113 በግማሽ ልብ የሚመላለሱትን* እጠላለሁ፤+

ሕግህን ግን እወዳለሁ።+

114 አንተ መጠለያዬና ጋሻዬ ነህ፤+

ቃልህ ተስፋዬ ነውና።*+

115 እናንተ ክፉዎች፣

የአምላኬን ትእዛዛት መጠበቅ እንድችል ከእኔ ራቁ።+

116 በሕይወት እንድቀጥል

ቃል በገባኸው* መሠረት ደግፈኝ፤+

ተስፋዬ ሳይፈጸም ቀርቶ እንዳዝን አትፍቀድ።*+

117 እድን ዘንድ ደግፈኝ፤+

ያን ጊዜ ለሥርዓትህ ዘወትር ትኩረት እሰጣለሁ።+

118 ከሥርዓትህ የሚርቁትን ሁሉ ገሸሽ ታደርጋቸዋለህ፤+

ውሸታሞችና አታላዮች ናቸውና።

119 በምድር ላይ ያሉ ክፉዎችን ሁሉ ከላይ እንደሚሰፍ የማይረባ ቆሻሻ ታስወግዳቸዋለህ።+

ስለዚህ ማሳሰቢያዎችህን እወዳለሁ።

120 አንተን እጅግ ከመፍራቴ የተነሳ ሰውነቴ* ይንቀጠቀጣል፤

ፍርዶችህን እፈራለሁ።

ע [አይን]

121 ትክክልና ጽድቅ የሆነውን አድርጌአለሁ።

ለሚጨቁኑኝ አሳልፈህ አትስጠኝ!

122 ለአገልጋይህ ደህንነት ዋስትና ስጥ፤

እብሪተኞች እንዲጨቁኑኝ አትፍቀድ።

123 ዓይኖቼ ማዳንህንና

የገባኸውን* የጽድቅ ቃል በመጠባበቅ ደከሙ።+

124 ለአገልጋይህ ታማኝ ፍቅርህን አሳየው፤+

ሥርዓትህንም አስተምረኝ።+

125 እኔ አገልጋይህ ነኝ፤

ማሳሰቢያዎችህን እንዳውቅ ማስተዋል ስጠኝ።+

126 ይሖዋ ሆይ፣ እርምጃ የምትወስድበት ጊዜ ደርሷል፤+

ሰዎች ሕግህን ጥሰዋልና።

127 ስለዚህ እኔ ትእዛዛትህን ከወርቅ፣

ምርጥ ከሆነ* ወርቅ ይበልጥ እወዳለሁ።+

128 በመሆኑም የምታስተምረው ትምህርት* በሙሉ ትክክል እንደሆነ አምናለሁ፤+

የሐሰትን መንገድ ሁሉ እጠላለሁ።+

פ [ፔ]

129 ማሳሰቢያዎችህ ድንቅ ናቸው።

ስለዚህ እጠብቃቸዋለሁ።*

130 አንተ የምትገልጣቸው ቃላት ብርሃን ይፈነጥቃሉ፤+

ተሞክሮ የሌላቸውን አስተዋዮች ያደርጋሉ።+

131 ትእዛዛትህን ለመስማት ከመጓጓቴ የተነሳ+

አፌን ከፍቼ በረጅሙ እተነፍሳለሁ።*

132 ስምህን ለሚወዱ ሰዎች+ ከምትሰጠው ፍርድ ጋር በሚስማማ መንገድ፣

ወደ እኔ ተመለስ፤ ሞገስም አሳየኝ።+

133 በቃልህ መሠረት አካሄዴን በሰላም ምራ፤*

ማንኛውም ክፉ ነገር በእኔ ላይ አይሠልጥን።+

134 ጨቋኝ ከሆኑ ሰዎች ታደገኝ፤*

እኔም መመሪያዎችህን እጠብቃለሁ።

135 በአገልጋይህ ላይ ፊትህን አብራ፤*+

ሥርዓትህንም አስተምረኝ።

136 ሰዎች ሕግህን ስለማያከብሩ

እንባ ከዓይኖቼ እንደ ውኃ ፈሰሰ።+

צ [ጻዴ]

137 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ጻድቅ ነህ፤+

ፍርዶችህም ትክክል ናቸው።+

138 የምትሰጣቸው ማሳሰቢያዎች በጽድቅ ላይ የተመሠረቱና

ሙሉ በሙሉ አስተማማኝ ናቸው።

139 ጠላቶቼ ቃልህን ስለረሱ

ቅንዓቴ ይበላኛል።+

140 ቃልህ እጅግ የጠራ ነው፤+

አገልጋይህም ይወደዋል።+

141 እኔ በሌሎች ዘንድ የተናቅኩና የማልረባ ነኝ፤+

ሆኖም መመሪያዎችህን አልረሳሁም።

142 ጽድቅህ የዘላለም ጽድቅ ነው፤+

ሕግህም እውነት ነው።+

143 ጭንቀትና ችግር ቢደርስብኝም

ትእዛዛትህን ምንጊዜም እወዳለሁ።

144 ማሳሰቢያህ ለዘላለም ጽድቅ ነው።

በሕይወት መኖሬን እንድቀጥል ማስተዋል ስጠኝ።+

ק [ኮፍ]

145 በሙሉ ልቤ እጣራለሁ። ይሖዋ ሆይ፣ መልስልኝ።

ሥርዓትህን እጠብቃለሁ።

146 አንተን እጣራለሁ፤ አቤቱ አድነኝ!

ማሳሰቢያዎችህን እጠብቃለሁ።

147 ጎህ ሳይቀድ* ተነስቼ እርዳታ ለማግኘት እጮኻለሁ፤+

ቃልህ ተስፋዬ ነውና።*

148 በተናገርከው ቃል ላይ ማሰላሰል* እንድችል፣

ክፍለ ሌሊቶቹ ከማብቃታቸው በፊት እነቃለሁ።+

149 ከታማኝ ፍቅርህ የተነሳ ድምፄን ስማ።+

ይሖዋ ሆይ፣ ከአንተ ፍትሕ ጋር በሚስማማ መንገድ በሕይወት አቆየኝ።

150 አሳፋሪ በሆነ ድርጊት* የተጠመዱ ሰዎች ወደ እኔ ቀርበዋል፤

ከሕግህም ርቀዋል።

151 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ቅርብ ነህ፤+

ትእዛዛትህም ሁሉ እውነት ናቸው።+

152 በቀድሞው ዘመን ስለ ማሳሰቢያዎችህ ተምሬአለሁ፤

ለዘላለም ይጸኑ ዘንድ እንደመሠረትካቸው ተረድቻለሁ።+

ר [ረሽ]

153 የደረሰብኝን ጉስቁልና ተመልከት፤ ደግሞም ታደገኝ፤+

ሕግህን አልረሳሁምና።

154 ተሟገትልኝ፤* ደግሞም ታደገኝ፤+

በገባኸው * ቃል መሠረት በሕይወት አቆየኝ።

155 ክፉዎች ሥርዓትህን ስላልፈለጉ

መዳን ከእነሱ ርቋል።+

156 ይሖዋ ሆይ፣ ምሕረትህ ታላቅ ነው።+

ከአንተ ፍትሕ ጋር በሚስማማ መንገድ በሕይወት አቆየኝ።

157 አሳዳጆቼና ጠላቶቼ ብዙ ናቸው፤+

እኔ ግን ከማሳሰቢያዎችህ ፈቀቅ አላልኩም።

158 ከዳተኛ የሆኑ ሰዎችን ተጸየፍኩ፤

ምክንያቱም አንተ የተናገርከውን አይጠብቁም።+

159 መመሪያዎችህን ምን ያህል እንደምወድ ተመልከት!

ይሖዋ ሆይ፣ ከታማኝ ፍቅርህ የተነሳ በሕይወት አቆየኝ።+

160 የቃልህ ፍሬ ነገር እውነት ነው፤+

በጽድቅ ላይ የተመሠረተው ፍርድህ ሁሉ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።

ש [ሲን] ወይም [ሺን]

161 መኳንንት ያለምክንያት ያሳድዱኛል፤+

ልቤ ግን ለቃልህ ጥልቅ አክብሮት አለው።+

162 ብዙ ምርኮ እንዳገኘ ሰው፣

እኔም አንተ በተናገርከው ነገር ሐሴት አደርጋለሁ።+

163 ውሸትን እጠላለሁ፤ ደግሞም እጸየፈዋለሁ፤+

ሕግህን ግን እወዳለሁ።+

164 በጽድቅ ላይ ከተመሠረቱት ፍርዶችህ የተነሳ

በቀን ሰባት ጊዜ አወድስሃለሁ።

165 ሕግህን የሚወዱ ብዙ ሰላም አላቸው፤+

ሊያደናቅፋቸው የሚችል ምንም ነገር የለም።*

166 ይሖዋ ሆይ፣ የማዳን ሥራህን ተስፋ አደርጋለሁ፤

ትእዛዛትህንም እፈጽማለሁ።

167 ማሳሰቢያዎችህን እጠብቃለሁ፤*

ደግሞም እጅግ እወዳቸዋለሁ።+

168 መመሪያዎችህንና ማሳሰቢያዎችህን እጠብቃለሁ፤

የማደርገውን ነገር ሁሉ ታውቃለህና።+

ת [ታው]

169 ይሖዋ ሆይ፣ እርዳታ ለማግኘት የማሰማው ጩኸት ወደ አንተ ይድረስ።+

እንደ ቃልህ ማስተዋል ስጠኝ።+

170 ሞገስ ለማግኘት የማቀርበው ልመና ወደ አንተ ይድረስ።

ቃል በገባኸው* መሠረት አድነኝ።

171 ሥርዓትህን ስለምታስተምረኝ

ከንፈሮቼ ውዳሴን ያፍልቁ።+

172 አንደበቴ ስለተናገርከው ቃል ይዘምር፤+

ትእዛዛትህ ሁሉ ጽድቅ ናቸውና።

173 መመሪያዎችህን ለመታዘዝ ስለምመርጥ፣+

እጅህ እኔን ለመርዳት ዝግጁ ይሁን።+

174 ይሖዋ ሆይ፣ ማዳንህን እናፍቃለሁ፤

ሕግህንም እወዳለሁ።+

175 አወድስህ ዘንድ በሕይወት ልኑር፤*+

አንተ ያወጣሃቸው ፍርዶች ይርዱኝ።

176 እንደጠፋ በግ ተቅበዘበዝኩ።+ አገልጋይህን ፈልገው፤

ትእዛዛትህን አልረሳሁምና።+

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር።*

120 በተጨነቅኩ ጊዜ ይሖዋን ተጣራሁ፤+

እሱም መለሰልኝ።+

 2 ይሖዋ ሆይ፣ ከሐሰተኛ ከንፈር፣

ደግሞም ከአታላይ አንደበት ታደገኝ።*

 3 አንተ አታላይ አንደበት፣

አምላክ ምን ያደርግህ ይሆን? እንዴትስ ይቀጣህ ይሆን?*+

 4 ሹል በሆኑ የተዋጊ ፍላጻዎችና+

በክትክታ እንጨት ፍም+ ይቀጣሃል።

 5 በመሼቅ+ የባዕድ አገር ሰው ሆኜ ስለኖርኩ ወዮልኝ!

በቄዳር+ ድንኳኖች መካከል ኖሬአለሁ።

 6 ሰላም ከሚጠሉ ሰዎች ጋር

ለረጅም ጊዜ ኖሬአለሁ።*+

 7 እኔ ለሰላም ቆሜአለሁ፤

እነሱ ግን በተናገርኩ ቁጥር ለጦርነት ይነሳሉ።

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር።

121 ዓይኖቼን ወደ ተራሮች አነሳለሁ።+

እርዳታ የማገኘው ከየት ነው?

 2 እኔን የሚረዳኝ

ሰማይንና ምድርን የሠራው ይሖዋ ነው።+

 3 እሱ እግርህ እንዲንሸራተት* ፈጽሞ አይፈቅድም።+

ጠባቂህ በጭራሽ አያንቀላፋም።

 4 እነሆ፣ እስራኤልን የሚጠብቀው፣

ፈጽሞ አያንቀላፋም፤ ደግሞም አይተኛም።+

 5 ይሖዋ ይጠብቅሃል።

ይሖዋ በቀኝህ ሆኖ+ ይጋርድሃል።+

 6 ቀን ፀሐይ አይመታህም፤+

ሌሊትም ጨረቃ አይጎዳህም።+

 7 ይሖዋ ከማንኛውም ጉዳት ይጠብቅሃል።+

እሱ ሕይወትህን* ይጠብቃል።+

 8 ይሖዋ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም፣

በምታደርገው ነገር ሁሉ ይጠብቅሃል።*

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር። የዳዊት መዝሙር።

122 “ወደ ይሖዋ ቤት እንሂድ”

ባሉኝ ጊዜ እጅግ ደስ አለኝ።+

 2 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ አሁን በበሮችሽ ገብተን

ከውስጥ ቆመናል።+

 3 ኢየሩሳሌም አንድ ወጥ ሆና

እንደተገነባች ከተማ ናት።+

 4 ለእስራኤል በተሰጠው ማሳሰቢያ መሠረት፣

ነገዶቹ ይኸውም የያህ* ነገዶች፣

ለይሖዋ ስም ምስጋና ለማቅረብ

ወደዚያ ወጥተዋል።+

 5 በዚያ የፍርድ ዙፋኖች፣

የዳዊት ቤት ዙፋኖች+ ተቀምጠዋልና።+

 6 ለኢየሩሳሌም ሰላም ጸልዩ።+

አንቺ ከተማ ሆይ፣ አንቺን የሚወዱ ከስጋት ነፃ ይሆናሉ።

 7 በመከላከያ ግንቦችሽ* ውስጥ ሰላም ለዘለቄታው ይኑር፤

በማይደፈሩ ማማዎችሽ ውስጥ የተረጋጋ ሁኔታ ይስፈን።

 8 እንግዲህ ለወንድሞቼና ለወዳጆቼ ስል

“በውስጥሽ ሰላም ይስፈን” እላለሁ።

 9 ለአምላካችን ለይሖዋ ቤት ስል+

ለአንቺ መልካም ነገር እሻለሁ።

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር።

123 በሰማያት ዙፋን ላይ የተቀመጥክ ሆይ፣

ዓይኖቼን ወደ አንተ አነሳለሁ።+

 2 የአገልጋዮች ዓይን ወደ ጌታቸው እጅ፣

የሴት አገልጋይም ዓይን ወደ እመቤቷ እጅ እንደሚመለከት ሁሉ፣

የእኛም ዓይኖች ሞገስ እስኪያሳየን ድረስ+

ወደ አምላካችን ወደ ይሖዋ ይመለከታሉ።+

 3 ንቀት እጅግ በዝቶብናልና፣+

ሞገስ አሳየን፤ ይሖዋ ሆይ፣ ሞገስ አሳየን።

 4 ከልክ በላይ በራሳቸው የሚተማመኑ ሰዎችን ፌዝ፣

የእብሪተኞችንም ንቀት ጠግበናል።*

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር። የዳዊት መዝሙር።

124 “ይሖዋ ከእኛ ጋር ባይሆን ኖሮ፣”+

እስራኤል እንዲህ ይበል፦

 2 “ይሖዋ ከእኛ ጋር ባይሆን ኖሮ፣+

ሰዎች እኛን ለማጥቃት በተነሱ ጊዜ፣+

 3 ቁጣቸው በእኛ ላይ በነደደ ጊዜ፣+

በሕይወት ሳለን በዋጡን ነበር።+

 4 በዚያን ጊዜ ውኃ ጠራርጎ በወሰደን፣

ጎርፍም ባጥለቀለቀን ነበር።*+

 5 ኃይለኛ ውኃ በዋጠን ነበር።*

 6 ለጥርሳቸው ሲሳይ እንድንሆን አሳልፎ ስላልሰጠን

ይሖዋ ይወደስ።

 7 ከአዳኝ ወጥመድ

እንዳመለጠች ወፍ ነን፤*+

ወጥመዱ ተሰበረ፤

እኛም አመለጥን።+

 8 ሰማይንና ምድርን የሠራው

የይሖዋ ስም ረዳታችን ነው።”+

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር።

125 በይሖዋ የሚታመኑ፣+

ፈጽሞ ሳይናወጥ ለዘላለም ጸንቶ እንደሚኖረው

እንደ ጽዮን ተራራ ናቸው።+

 2 ተራሮች በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንዳሉ ሁሉ፣+

ይሖዋም ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም

በሕዝቡ ዙሪያ ይሆናል።+

 3 ጻድቃን ትክክል ያልሆነ ነገር መሥራት እንዳይጀምሩ፣*+

የክፋት በትር ለጻድቃን በተሰጠ ምድር ላይ አይኖርም።+

 4 ይሖዋ ሆይ፣ ለጥሩ ሰዎች፣

ለልበ ቅኖች+ መልካም ነገር አድርግ።+

 5 ወደ ጠማማ መንገዳቸው ዞር የሚሉትን፣

ይሖዋ ከክፉ አድራጊዎች ጋር ያስወግዳቸዋል።+

በእስራኤል ሰላም ይስፈን።

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር።

126 ይሖዋ የጽዮንን ምርኮኞች መልሶ በሰበሰበ ጊዜ፣+

ሕልም የምናይ መስሎን ነበር።

 2 በዚያን ጊዜ አፋችን በሳቅ፣

አንደበታችንም በእልልታ ተሞላ።+

ያን ጊዜ ብሔራት እንዲህ አሉ፦

“ይሖዋ ታላላቅ ነገሮች አደረገላቸው።”+

 3 ይሖዋ ታላላቅ ነገሮች አደረገልን፤+

እኛም እጅግ ተደሰትን።

 4 ይሖዋ ሆይ፣ በኔጌብ እንዳሉ ጅረቶች፣*

የተማረኩብንን ሰዎች መልሰህ ሰብስብ።*

 5 በእንባ የሚዘሩ፣

በእልልታ ያጭዳሉ።

 6 ዘር ቋጥሮ የወጣው ሰው፣

የሄደው እያለቀሰ ቢሆንም እንኳ

ነዶውን ተሸክሞ

እልል እያለ ይመለሳል።+

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር። የሰለሞን መዝሙር።

127 ይሖዋ ቤትን ካልገነባ፣

ግንበኞቹ የሚደክሙት በከንቱ ነው።+

ይሖዋ ከተማን ካልጠበቀ፣+

ጠባቂው ንቁ ሆኖ መጠበቁ ከንቱ ድካም ነው።

 2 በማለዳ መነሳታችሁ፣

እስከ ምሽት ድረስ መሥራታችሁ፣

እንዲሁም የዕለት ጉርሳችሁን ለማግኘት መልፋታችሁ ከንቱ ነው፤

ምክንያቱም አምላክ የሚወዳቸውን ሰዎች ይንከባከባቸዋል፤ እንቅልፍም ይሰጣቸዋል።+

 3 እነሆ፣ ልጆች* ከይሖዋ የተገኙ ውርሻ ናቸው፤+

የማህፀንም ፍሬ ከእሱ የሚገኝ ስጦታ ነው።+

 4 አንድ ሰው በወጣትነቱ የወለዳቸው ወንዶች ልጆች፣

በኃያል ሰው እጅ እንዳሉ ፍላጻዎች ናቸው።+

 5 ኮሮጆውን በእነዚህ የሞላ ሰው ደስተኛ ነው።+

እነሱ ፈጽሞ አያፍሩም፤

በከተማዋ በር ከጠላቶቻቸው ጋር ይነጋገራሉና።

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር።

128 ይሖዋን የሚፈሩ፣

በመንገዱም የሚሄዱ ሁሉ ደስተኞች ናቸው።+

 2 በእጅህ ደክመህ ያፈራኸውን ትበላለህ።

ደስተኛ ትሆናለህ፤ ደግሞም ትበለጽጋለህ።+

 3 ሚስትህ በቤትህ ውስጥ፣ ፍሬ እንደሚያፈራ ወይን ትሆናለች፤+

ወንዶች ልጆችህ በማዕድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ዛፍ ቡቃያዎች ይሆናሉ።

 4 እነሆ፣ ይሖዋን የሚፈራ ሰው

እንደዚህ የተባረከ ይሆናል።+

 5 ይሖዋ ከጽዮን ይባርክሃል።

በሕይወት ዘመንህ ሁሉ የኢየሩሳሌምን ብልጽግና ለማየት ያብቃህ፤+

 6 ደግሞም የልጅ ልጅ ለማየት ያብቃህ።

በእስራኤል ሰላም ይስፈን።

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር።

129 “ከወጣትነቴ ጀምሮ ሁልጊዜ ያጠቁኝ ነበር”፤+

እስራኤል እንዲህ ይበል፦

 2 “ከወጣትነቴ ጀምሮ ሁልጊዜ ያጠቁኝ ነበር፤+

ሆኖም ሊያሸንፉኝ አልቻሉም።+

 3 አራሾች ጀርባዬን አረሱት፤+

ትልማቸውንም አስረዘሙት።”*

 4 ይሖዋ ግን ጻድቅ ነው፤+

የክፉዎችን ገመድ በጣጥሷል።+

 5 ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ፣

ኀፍረት ይከናነባሉ፤ ተዋርደውም ወደኋላቸው ይመለሳሉ።+

 6 ከመነቀሉ በፊት እንደሚጠወልግ፣

በጣሪያ ላይ እንደበቀለ ሣር ይሆናሉ፤

 7 እንዲህ ዓይነቱ ሣር የአጫጁን እጅ፣

ነዶ የሚሰበስበውንም ሰው ክንዶች ሊሞላ አይችልም።

 8 በዚያ የሚያልፉ ሰዎች

“የይሖዋ በረከት በእናንተ ላይ ይሁን፤

በይሖዋ ስም እንባርካችኋለን” አይሉም።

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር።

130 ይሖዋ ሆይ፣ ከጥልቅ ውስጥ አንተን እጣራለሁ።+

 2 ይሖዋ ሆይ፣ ድምፄን ስማ።

ጆሮዎችህ እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና በትኩረት ያዳምጡ።

 3 ያህ* ሆይ፣ አንተ ስህተትን የምትከታተል* ቢሆን ኖሮ፣

ይሖዋ ሆይ፣ ማን ሊቆም ይችል ነበር?+

 4 በአንተ ዘንድ በእርግጥ ይቅርታ አለና፤+

ይህም ሰዎች አንተን እንዲፈሩ* ያደርጋል።+

 5 ይሖዋን ተስፋ አደርጋለሁ፤ ሁለንተናዬ በእሱ ተስፋ ያደርጋል፤*

ቃሉን በትዕግሥት እጠብቃለሁ።

 6 ንጋትን ከሚጠባበቁ፣

አዎ፣ ንጋትን ከሚጠባበቁ ጠባቂዎች ይበልጥ

ይሖዋን በጉጉት እጠባበቃለሁ።*+

 7 እስራኤል ይሖዋን በትዕግሥት ይጠባበቅ፤

ይሖዋ በፍቅሩ ታማኝ ነውና፤+

ሕዝቡንም ለመዋጀት ታላቅ ኃይል አለው።

 8 እስራኤልን ከበደላቸው ሁሉ ይዋጃል።

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር። የዳዊት መዝሙር።

131 ይሖዋ ሆይ፣ ልቤ አይኩራራም፤

ዓይኖቼም አይታበዩም፤+

እጅግ ታላላቅ ነገሮችን ወይም

ከአቅሜ በላይ የሆኑ ነገሮችን አልመኝም።+

 2 ይልቁንም እናቱ ላይ እንደተቀመጠ ጡት የጣለ ሕፃን

ነፍሴን አረጋጋኋት፤* ደግሞም ጸጥ አሰኘኋት።+

ጡት እንደጣለ ሕፃን ረካሁ።*

 3 እስራኤል ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም

ይሖዋን በትዕግሥት ይጠባበቅ።+

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር።

132 ይሖዋ ሆይ፣ ዳዊትን፣

የደረሰበትንም መከራ ሁሉ አስታውስ፤+

 2 ለይሖዋ እንዴት እንደማለ፣

ኃያል ለሆነው ለያዕቆብ አምላክ እንዴት እንደተሳለ አስብ፦+

 3 “ወደ ድንኳኔ፣ ወደ ቤቴ አልገባም።+

ወደ መኝታዬ፣ ወደ አልጋዬ አልወጣም፤

 4 ዓይኖቼ እንዲያንቀላፉ፣

ሽፋሽፍቶቼም እንዲያሸልቡ አልፈቅድም፤

 5 ይህም ለይሖዋ ስፍራ፣

ኃያል ለሆነው የያዕቆብ አምላክም ያማረ መኖሪያ እስከማገኝ ድረስ ነው።”+

 6 እነሆ፣ በኤፍራታ+ ስለ እሷ ሰማን፤

በጫካ በተሞላው ምድር አገኘናት።+

 7 ወደ መኖሪያው እንግባ፤+

በእግሩ ማሳረፊያ ፊት እንስገድ።+

 8 ይሖዋ ሆይ፣ ተነስ፤

አንተና የብርታትህ ታቦት፣+ ወደ ማረፊያ ስፍራህ ሂዱ።+

 9 ካህናትህ ጽድቅን ይልበሱ፤

ታማኝ አገልጋዮችህም እልል ይበሉ።

10 ለአገልጋይህ ለዳዊት ስትል፣

የቀባኸውን ሰው ገሸሽ አታድርግ።+

11 ይሖዋ ለዳዊት ምሏል፤

የገባውን ቃል ፈጽሞ አያጥፍም፦

“ከዘሮችህ መካከል አንዱን*

በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ።+

12 ወንዶች ልጆችህ ቃል ኪዳኔንና

የማስተምራቸውን ማሳሰቢያዎች ቢጠብቁ፣+

የእነሱም ልጆች

ለዘላለም በዙፋንህ ላይ ይቀመጣሉ።”+

13 ይሖዋ ጽዮንን መርጧታልና፤+

የራሱ መኖሪያ እንድትሆን ፈልጓል፤+ እንዲህም ብሏል፦

14 “ይህች ለዘላለም ማረፊያ ስፍራዬ ነች፤

በእሷ እኖራለሁ፤+ ይህ ምኞቴ ነውና።

15 የተትረፈረፈ የምግብ አቅርቦት እንዲኖራት በማድረግ እባርካታለሁ፤

ድሆቿን እህል አጠግባለሁ።+

16 ካህናቷ መዳንን እንዲለብሱ አደርጋለሁ፤+

ታማኝ ሕዝቦቿም እልል ይላሉ።+

17 በዚያ የዳዊትን ብርታት እጨምራለሁ።*

ለቀባሁት አገልጋዬ መብራት አዘጋጅቻለሁ።+

18 ጠላቶቹን ኀፍረት አከናንባለሁ፤

በራሱ ላይ ያለው አክሊል* ግን ያብባል።”+

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር። የዳዊት መዝሙር።

133 እነሆ፣ ወንድሞች በአንድነት አብረው ቢኖሩ

ምንኛ መልካም ነው! ምንኛስ ደስ ያሰኛል!+

 2 በራስ ላይ ፈስሶ እስከ ጢም እንደሚዘልቅ፣

በአሮን ጢም+ ላይ እንደሚወርድ፣

እስከ ልብሱ ኮሌታ ድረስ እንደሚፈስ

ጥሩ ዘይት ነው።+

 3 በጽዮን ተራሮች+ ላይ እንደሚወርድ፣

እንደ ሄርሞን+ ጤዛ ነው።

በዚያ ይሖዋ በረከቱን ይኸውም

የዘላለም ሕይወትን አዟል።

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር።

134 በሌሊት በይሖዋ ቤት የምታገለግሉ፣+

እናንተ የይሖዋ አገልጋዮች ሁሉ፣

ይሖዋን አወድሱ።+

 2 እጆቻችሁን በቅድስና* ወደ ላይ አንሱ፤+

ይሖዋንም አወድሱ።

 3 ሰማይንና ምድርን የሠራው ይሖዋ፣

ከጽዮን ይባርክህ።

135 ያህን አወድሱ!*

የይሖዋን ስም አወድሱ፤

እናንተ የይሖዋ አገልጋዮች፣ ውዳሴ አቅርቡ፤+

 2 በይሖዋ ቤት፣

በአምላካችን ቤት ቅጥር ግቢዎች የቆማችሁ ሁሉ አወድሱት።+

 3 ይሖዋ ጥሩ ነውና፣+ ያህን አወድሱ።

ደስ የሚያሰኝ ነውና፣ ለስሙ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ።

 4 ያህ ያዕቆብን የራሱ፣

እስራኤልን ልዩ ንብረቱ* አድርጎ መርጧልና።+

 5 ይሖዋ ታላቅ መሆኑን በሚገባ አውቃለሁና፤

ጌታችን ከሌሎች አማልክት ሁሉ የላቀ ነው።+

 6 በሰማይና በምድር፣ በባሕሮችና በጥልቆች ውስጥ

ይሖዋ ደስ ያሰኘውን ነገር ሁሉ ያደርጋል።+

 7 ደመና* ከምድር ዳርቻዎች ወደ ላይ እንዲወጣ ያደርጋል፤

በዝናብ ጊዜ መብረቅን ያበርቃል፤*

ነፋሱን ከግምጃ ቤቱ ያወጣል።+

 8 በግብፅ የተወለደውን

የሰውም ሆነ የእንስሳ በኩር ገደለ።+

 9 ግብፅ ሆይ፣ በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ሁሉ ላይ፣+

በመካከልሽ ምልክቶችንና ተአምራትን አደረገ።+

10 ብዙ ብሔራትን መታ፤+

ኃያላን ነገሥታትንም ገደለ፤+

11 የአሞራውያንን ንጉሥ ሲሖንን፣+

የባሳንን ንጉሥ ኦግን፣+

የከነአንንም መንግሥታት ሁሉ ድል አደረገ።

12 ምድራቸውን ርስት አድርጎ፣

አዎ፣ ርስት አድርጎ ለሕዝቡ ለእስራኤል ሰጠ።+

13 ይሖዋ ሆይ፣ ስምህ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።

ይሖዋ ሆይ፣ ዝናህ* ከትውልድ እስከ ትውልድ ይዘልቃል።+

14 ይሖዋ ለሕዝቡ ይሟገታልና፤*+

ለአገልጋዮቹም ይራራል።*+

15 የብሔራት ጣዖቶች ከብርና ከወርቅ የተሠሩ፣

የሰው እጅ ሥራ ናቸው።+

16 አፍ አላቸው፤ መናገር ግን አይችሉም፤+

ዓይን አላቸው፤ ማየት ግን አይችሉም፤

17 ጆሮ አላቸው፤ መስማት ግን አይችሉም።

በአፋቸው ውስጥ እስትንፋስ የለም።+

18 የሚሠሯቸውም ሆኑ የሚታመኑባቸው ሁሉ፣+

እንደ እነሱ ይሆናሉ።+

19 የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ይሖዋን አወድሱ።

የአሮን ቤት ሆይ፣ ይሖዋን አወድሱ።

20 የሌዊ ቤት ሆይ፣ ይሖዋን አወድሱ።+

እናንተ ይሖዋን የምትፈሩ፣ ይሖዋን አወድሱ።

21 በኢየሩሳሌም የሚኖረው ይሖዋ፣+

ከጽዮን ይወደስ።+

ያህን አወድሱ!+

136 ይሖዋ ጥሩ+ ስለሆነ ምስጋና አቅርቡለት፤

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።+

 2 ለአማልክት አምላክ+ ምስጋና አቅርቡ፤

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።

 3 ለጌቶች ጌታ ምስጋና አቅርቡ፤

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።

 4 እሱ ብቻ አስደናቂ የሆኑ ታላላቅ ነገሮች ይሠራል፤+

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።+

 5 ሰማያትን በጥበብ ሠራ፤*+

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።

 6 ምድርን በውኃዎች ላይ ዘረጋ፤+

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።

 7 ታላላቅ ብርሃናትን ሠራ፤+

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና፤

 8 ፀሐይ በቀን እንዲያይል* አደረገ፤+

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና፤

 9 ጨረቃና ከዋክብት በሌሊት እንዲያይሉ* አደረገ፤+

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።

10 የግብፅን በኩር ቀሰፈ፤+

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።

11 እስራኤልን ከመካከላቸው አወጣ፤+

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና፤

12 በኃያል እጅና በተዘረጋ ክንድ ይህን አድርጓል፤+

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።

13 ቀይ ባሕርን ለሁለት ከፈለ፤*+

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።

14 እስራኤል በመካከሉ እንዲያልፍ አደረገ፤+

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።

15 ፈርዖንንና ሠራዊቱን ቀይ ባሕር ውስጥ ወረወረ፤+

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።

16 ሕዝቡን በምድረ በዳ መራ፤+

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።

17 ታላላቅ ነገሥታትን መታ፤+

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።

18 ኃያላን ነገሥታትን ገደለ፤

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና፤

19 የአሞራውያንን ንጉሥ ሲሖንን+ ገደለ፤

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና፤

20 የባሳንንም ንጉሥ ኦግን+ ገደለ፤

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።

21 ምድራቸውን ርስት አድርጎ ሰጠ፤+

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና፤

22 ለአገልጋዩ ለእስራኤል ርስት አድርጎ አወረሰ፤

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።

23 መንፈሳችን ተደቁሶ በነበረበት ጊዜ አስታወሰን፤+

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።+

24 ከጠላቶቻችን እጅ ይታደገን ነበር፤+

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።

25 ሕይወት ላለው* ሁሉ ምግብ ይሰጣል፤+

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።

26 ለሰማያት አምላክ ምስጋና አቅርቡ፤

ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።

137 በባቢሎን ወንዞች አጠገብ፣+ በዚያ ተቀምጠን ነበር።

ጽዮንን ባስታወስናት ጊዜ አለቀስን።+

 2 በመካከሏ* በሚገኙ የአኻያ ዛፎች ላይ

በገናዎቻችንን ሰቀልን።+

 3 የማረኩን ሰዎች በዚያ እንድንዘምርላቸው ጠየቁን፤+

የሚያፌዙብን ሰዎች በመዝሙር እንድናዝናናቸው

“ከጽዮን መዝሙሮች አንዱን ዘምሩልን” አሉን።

 4 የይሖዋን መዝሙር

በባዕድ ምድር እንዴት ልንዘምር እንችላለን?

 5 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ አንቺን ብረሳ፣

ቀኝ እጄ ትክዳኝ።*+

 6 ሳላስታውስሽ ብቀር፣

ኢየሩሳሌምን ለደስታዬ ምክንያት

ከሆኑት ነገሮች በላይ ባላደርግ፣+

ምላሴ ከላንቃዬ ጋር ትጣበቅ።

 7 ይሖዋ ሆይ፣ ኢየሩሳሌም በወደቀችበት ቀን

ኤዶማውያን ያሉትን አስታውስ፤

“አፍርሷት! ከሥረ መሠረቷ አፍርሷት!”+ ብለው ነበር።

 8 በቅርቡ የምትጠፊው አንቺ የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ፣+

በእኛ ላይ በፈጸምሽው በዚያው ድርጊት

ብድራትሽን የሚመልስ ደስተኛ ይሆናል።+

 9 ልጆችሽን ይዞ በዓለት ላይ የሚፈጠፍጥ+

ደስተኛ ይሆናል።

የዳዊት መዝሙር።

138 በሙሉ ልቤ አወድስሃለሁ።+

በሌሎች አማልክት ፊት

የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።*

 2 ከታማኝ ፍቅርህና ከታማኝነትህ የተነሳ

ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፤+

ስምህንም አወድሳለሁ።+

ቃልህና ስምህ ከሁሉም ነገር በላይ ጎልቶ እንዲታይ አድርገሃልና።*

 3 በተጣራሁ ቀን መለስክልኝ፤+

ደፋርና* ብርቱ አደረግከኝ።+

 4 ይሖዋ ሆይ፣ የምድር ነገሥታት ሁሉ ያወድሱሃል፤+

የተናገርካቸውን የተስፋ ቃሎች ይሰማሉና።

 5 ስለ ይሖዋ መንገዶች ይዘምራሉ፤

የይሖዋ ክብር ታላቅ ነውና።+

 6 ይሖዋ ከፍ ያለ ቢሆንም ትሑት የሆነውን ሰው ይመለከታል፤+

ትዕቢተኛውን ግን ወደ እሱ እንዲቀርብ አይፈቅድም።+

 7 አደገኛ በሆነ አካባቢ ባልፍም እንኳ አንተ ሕይወቴን ትጠብቃለህ።+

በጠላቶቼ ቁጣ ላይ እጅህን ትዘረጋለህ፤

ቀኝ እጅህ ያድነኛል።

 8 ይሖዋ ለእኔ ሲል ሁሉንም ነገር ይፈጽማል።

ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል፤+

የእጅህን ሥራ ቸል አትበል።+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት መዝሙር። ማህሌት።

139 ይሖዋ ሆይ፣ በሚገባ መርምረኸኛል፤ ደግሞም ታውቀኛለህ።+

 2 አንተ ስቀመጥም ሆነ ስነሳ ታውቃለህ።+

ሐሳቤን ከሩቅ ታስተውላለህ።+

 3 ስጓዝም ሆነ ስተኛ በሚገባ ታየኛለህ፤

መንገዶቼን ሁሉ ታውቃለህ።+

 4 ይሖዋ ሆይ፣ ገና ቃል ከአፌ ሳይወጣ፣

እነሆ፣ አንተ ሁሉን ነገር አስቀድመህ በሚገባ ታውቃለህ።+

 5 ከኋላም ከፊትም ከበብከኝ፤

እጅህንም በላዬ ላይ ታደርጋለህ።

 6 እንዲህ ያለው እውቀት እኔ ልረዳው ከምችለው በላይ ነው።*

በጣም ከፍ ያለ ከመሆኑ የተነሳ ልደርስበት አልችልም።*+

 7 ከመንፈስህ ወዴት ላመልጥ እችላለሁ?

ከፊትህስ ወዴት ልሸሽ እችላለሁ?+

 8 ወደ ሰማይ ብወጣ አንተ በዚያ አለህ፤

በመቃብር* አልጋዬን ባነጥፍም እነሆ፣ አንተ በዚያ ትኖራለህ።+

 9 እጅግ ርቆ በሚገኝ ባሕር አቅራቢያ ለመኖር፣

በንጋት ክንፍ ብበር፣

10 በዚያም እንኳ እጅህ ትመራኛለች፤

ቀኝ እጅህም ትይዘኛለች።+

11 “በእርግጥ ጨለማ ይሰውረኛል!” ብል፣

በዚያን ጊዜ በዙሪያዬ ያለው ሌሊት ብርሃን ይሆናል።

12 ጨለማው ለአንተ አይጨልምብህም፤

ይልቁንም ሌሊቱ እንደ ቀን ብሩህ ይሆናል፤+

ጨለማ ለአንተ እንደ ብርሃን ነው።+

13 አንተ ኩላሊቴን ሠርተሃልና፤

በእናቴ ማህፀን ውስጥ ጋርደህ አስቀመጥከኝ።*+

14 በሚያስደምም ሁኔታ ግሩምና ድንቅ ሆኜ ስለተፈጠርኩ+ አወድስሃለሁ።

ሥራዎችህ አስደናቂ ናቸው፤+

ይህን በሚገባ አውቃለሁ።*

15 በስውር በተሠራሁ ጊዜ፣

በማህፀን ውስጥ እያደግኩ በነበረበት ወቅት፣*

አጥንቶቼ ከአንተ አልተሰወሩም ነበር።+

16 ፅንስ እያለሁ እንኳ ዓይኖችህ አዩኝ፤

የአካሌ ክፍሎች በሙሉ በመጽሐፍህ ተጻፉ፤

አንዳቸውም ወደ ሕልውና ከመምጣታቸው በፊት፣

የተሠሩባቸውን ቀኖች በተመለከተ በዝርዝር ተጻፈ።

17 ሐሳቦችህ ለእኔ ምንኛ ውድ ናቸው!+

አምላክ ሆይ፣ ቁጥራቸው ምንኛ ብዙ ነው!+

18 ልቆጥራቸው ብሞክር ከአሸዋ ይልቅ ይበዛሉ።+

ከእንቅልፌ ስነቃም ገና ከአንተው ጋር ነኝ።*+

19 አምላክ ሆይ፣ ምነው ክፉውን በገደልከው!+

በዚያን ጊዜ ጨካኞች* ከእኔ ይርቁ ነበር፤

20 እነሱ በተንኮል ተነሳስተው በአንተ ላይ ክፉ ነገር* ይናገራሉ፤

ስምህን በከንቱ የሚያነሱ ጠላቶችህ ናቸው።+

21 ይሖዋ ሆይ፣ አንተን የሚጠሉትን እጠላ የለም?+

በአንተ ላይ የሚያምፁትንስ እጸየፍ የለም?+

22 እጅግ ጠላኋቸው፤+

ለእኔ የለየላቸው ጠላቶች ሆነዋል።

23 አምላክ ሆይ፣ በሚገባ ፈትሸኝ፤ ልቤንም እወቅ።+

መርምረኝ፤ የሚያስጨንቁኝንም* ሐሳቦች እወቅ።+

24 በውስጤ ጎጂ የሆነ ዝንባሌ ካለ እይ፤+

በዘላለምም መንገድ ምራኝ።+

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት ማህሌት።

140 ይሖዋ ሆይ፣ ከክፉ ሰዎች ታደገኝ፤

ከጨካኞችም ጠብቀኝ፤+

 2 እነሱ በልባቸው ክፉ ነገር ይጠነስሳሉ፤+

ደግሞም ቀኑን ሙሉ ጠብ ይጭራሉ።

 3 እንደ እባብ ምላሳቸውን ያሾላሉ፤+

ከከንፈራቸው ኋላ የእፉኝት መርዝ አለ።+ (ሴላ)

 4 ይሖዋ ሆይ፣ ከክፉዎች እጅ አድነኝ፤+

እኔን ጠልፈው ለመጣል ከሚያሴሩ

ጨካኝ ሰዎች ጠብቀኝ።

 5 ትዕቢተኞች በስውር ወጥመድ አስቀመጡብኝ፤

ከመንገዱ አጠገብ የመረባቸውን ገመድ ዘረጉብኝ።+

አሽክላም አስቀመጡብኝ።+ (ሴላ)

 6 ይሖዋን እንዲህ እለዋለሁ፦ “አንተ አምላኬ ነህ።

ይሖዋ ሆይ፣ እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና ስማ።”+

 7 ኃያል አዳኜ የሆንከው ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣

በጦርነት ቀን ራሴን ትከልላለህ።+

 8 ይሖዋ ሆይ፣ የክፉዎች ምኞት እንዲሳካ አታድርግ።

ራሳቸውን ከፍ ከፍ እንዳያደርጉ፣ ሴራቸው እንዲሰምር አትፍቀድ።+ (ሴላ)

 9 ዙሪያዬን የከበቡኝን ሰዎች ራስ፣

የገዛ ከንፈራቸው የተናገረው ክፋት ይሸፍነው።+

10 የእሳት ፍም በላያቸው ይውረድ።+

መነሳት እንዳይችሉ ወደ እሳት፣

ወደ ጥልቅ ጉድጓዶች* ይወርወሩ።+

11 ስም አጥፊ በምድር* ላይ አንዳች ቦታ አያግኝ።+

ጨካኞችን ክፋት አሳዶ ይምታቸው።

12 ይሖዋ ለችግረኛው እንደሚሟገትና

ለድሃው ፍትሕ እንደሚያሰፍን አውቃለሁ።+

13 በእርግጥ ጻድቃን ለስምህ ምስጋና ያቀርባሉ፤

ቅኖችም በፊትህ ይኖራሉ።+

የዳዊት ማህሌት።

141 ይሖዋ ሆይ፣ አንተን እጣራለሁ።+

እኔን ለመርዳት ፈጥነህ ድረስልኝ።+

አንተን ስጣራ በትኩረት ስማኝ።+

 2 ጸሎቴ በአንተ ፊት እንደተዘጋጀ ዕጣን ይሁን፤+

የተዘረጉት እጆቼ ምሽት ላይ እንደሚቀርብ የእህል መባ ይሁኑ።+

 3 ይሖዋ ሆይ፣ ለአፌ ጠባቂ አድርግ፤

በከንፈሮቼም በር ላይ ዘበኛ አቁም።+

 4 ከክፉ ሰዎች ጋር መጥፎ ድርጊት እንዳልፈጽም፣

ልቤ ወደ ክፉ ነገር እንዲያዘነብል አትፍቀድ፤+

ጣፋጭ ከሆነው ምግባቸው አልቋደስ።

 5 ጻድቅ ቢመታኝ፣ የታማኝ ፍቅር መግለጫ አድርጌ እቆጥረዋለሁ፤+

ቢወቅሰኝ በራስ ላይ እንደሚፈስ ዘይት አድርጌ አየዋለሁ፤+

ራሴም ይህን ፈጽሞ እንቢ አይልም።+

መከራ በገጠማቸው ወቅትም እንኳ መጸለዬን እቀጥላለሁ።

 6 ፈራጆቻቸው ከገደል አፋፍ ቢጣሉም፣

ሕዝቡ ለምናገራቸው ቃላት ትኩረት ይሰጣል፤ ደስ የሚያሰኙ ናቸውና።

 7 ሰው ሲያርስና ጓል ሲከሰክስ አፈሩ እንደሚበታተን ሁሉ፣

አጥንቶቻችንም በመቃብር* አፍ ላይ ተበታተኑ።

 8 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ዓይኖቼ ግን ወደ አንተ ይመለከታሉ።+

አንተን መጠጊያዬ አድርጌአለሁ።

ሕይወቴን አትውሰድ።*

 9 ከዘረጉብኝ ወጥመድ፣

ክፉ አድራጊዎች ካስቀመጡብኝ አሽክላም ጠብቀኝ።

10 ክፉዎች አንድ ላይ የገዛ ወጥመዳቸው ውስጥ ይወድቃሉ፤+

እኔ ግን አንድም ነገር ሳይነካኝ አልፋለሁ።

ማስኪል።* ዳዊት ዋሻ ውስጥ በነበረበት ጊዜ+ የዘመረው መዝሙር። ጸሎት።

142 ድምፄን አውጥቼ እርዳታ ለማግኘት ወደ ይሖዋ እጣራለሁ፤+

ሞገስ እንዲያሳየኝ ይሖዋን እማጸናለሁ።

 2 የሚያሳስበኝን ነገር በፊቱ አፈስሳለሁ፤

የውስጤን ጭንቀት በፊቱ እናገራለሁ፤+

 3 መንፈሴ* በውስጤ ሲዝል፣ እሱን እማጸናለሁ።

በዚህ ጊዜ ጎዳናዬን ትመለከታለህ።+

በምሄድበት መንገድ ላይ

በስውር ወጥመድ ዘረጉብኝ።

 4 ቀኝ እጄን ተመልከት፤

ስለ እኔ ግድ የሚሰጠው* ሰው እንደሌለ እይ።+

ሸሽቼ ማምለጥ የምችልበት ቦታ የለም፤+

ስለ እኔ* የሚያስብ ማንም የለም።

 5 ይሖዋ ሆይ፣ እርዳታ ለማግኘት ወደ አንተ እጣራለሁ።

ደግሞም “አንተ መጠጊያዬ ነህ፤+

በሕያዋን ምድር ያለኸኝ አንተ ብቻ* ነህ” እላለሁ።

 6 መንፈሴ እጅግ ተደቁሷልና፣

እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና ስማ።

ከእኔ ይልቅ ብርቱ ስለሆኑ

ከሚያሳድዱኝ ሰዎች ታደገኝ።+

 7 ስምህን አወድስ ዘንድ

ከእስር ቤት አውጣኝ።*

ደግነት ስለምታሳየኝ

ጻድቃን በዙሪያዬ ይሰብሰቡ።

የዳዊት ማህሌት።

143 ይሖዋ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤+

እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና አዳምጥ።

እንደ ታማኝነትህና እንደ ጽድቅህ መጠን መልስልኝ።

 2 ሕያው የሆነ ማንኛውም ሰው በፊትህ ጻድቅ ሊሆን ስለማይችል፣+

አገልጋይህን ለፍርድ አታቅርበው።

 3 ጠላት ያሳድደኛልና፤*

ሕይወቴንም አድቆ ከአፈር ደባልቋታል።

ከረጅም ጊዜ በፊት እንደሞቱ ሰዎች በጨለማ ቦታ እንድኖር አድርጎኛል።

 4 መንፈሴ* በውስጤ ዛለ፤+

ልቤ በውስጤ ደነዘዘ።+

 5 የጥንቱን ዘመን አስታውሳለሁ፤

ባከናወንካቸው ነገሮች ሁሉ ላይ አሰላስላለሁ፤+

የእጆችህን ሥራ በታላቅ ጉጉት አውጠነጥናለሁ።*

 6 እጆቼን ወደ አንተ እዘረጋለሁ፤

እንደ ደረቅ ምድር አንተን ተጠማሁ።*+ (ሴላ)

 7 ይሖዋ ሆይ፣ ፈጥነህ መልስልኝ።+

ጉልበቴ* ተሟጠጠ።+

ፊትህን ከእኔ አትሰውር፤+

አለዚያ ወደ ጉድጓድ* እንደሚወርዱ ሰዎች እሆናለሁ።+

 8 በአንተ ታምኛለሁና፣

በማለዳ ታማኝ ፍቅርህን ልስማ።

ፊቴን ወደ አንተ አዞራለሁና፣*

ልሄድበት የሚገባውን መንገድ አሳውቀኝ።+

 9 ይሖዋ ሆይ፣ ከጠላቶቼ ታደገኝ።

የአንተን ጥበቃ እሻለሁ።+

10 አንተ አምላኬ ስለሆንክ፣

ፈቃድህን እንድፈጽም አስተምረኝ።+

መንፈስህ ጥሩ ነው፤

በደልዳላ መሬት* ይምራኝ።

11 ይሖዋ ሆይ፣ ለስምህ ስትል በሕይወት አቆየኝ።

በጽድቅህ ከጭንቅ ታደገኝ።*+

12 በታማኝ ፍቅርህ ጠላቶቼን አስወግዳቸው፤*+

አገልጋይህ ነኝና፣+

የሚያጎሳቁሉኝን* ሰዎች ሁሉ አጥፋቸው።+

የዳዊት መዝሙር።

144 እጆቼን ለውጊያ፣

ጣቶቼንም ለጦርነት የሚያሠለጥነው፣+

ዓለቴ የሆነው ይሖዋ+ ይወደስ።

 2 እሱ ታማኝ ፍቅር የሚያሳየኝ አምላኬና ምሽጌ፣

አስተማማኝ መጠጊያዬና ታዳጊዬ፣

ጋሻዬና መጠለያዬ፣+

ሕዝቦችን ከበታቼ የሚያስገዛልኝ አምላኬ ነው።+

 3 ይሖዋ ሆይ፣ ታስተውለው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?

ቦታ ትሰጠውስ ዘንድ ሟች የሆነው የሰው ልጅ ምንድን ነው?+

 4 ሰው እንደ እስትንፋስ ነው፤+

ዘመኑ እንደሚያልፍ ጥላ ነው።+

 5 ይሖዋ ሆይ፣ ሰማያትህን ወደ ታች ዝቅ አድርገህ* ውረድ፤+

ተራሮችን ዳስሰህ እንዲጨሱ አድርግ።+

 6 መብረቅ ልከህ ጠላትን በትን፤+

ፍላጻዎችህን ወርውረህ ግራ አጋባቸው።+

 7 እጆችህን ከላይ ዘርጋ፤

ከሚያጥለቀልቅ ውኃ ታደገኝ፤ ደግሞም አድነኝ፤

ከባዕድ አገር ሰዎች እጅ* አስጥለኝ፤+

 8 እነሱ በአፋቸው ውሸት ይናገራሉ፤

ደግሞም በውሸት ለመማል ቀኝ እጃቸውን ወደ ላይ ያነሳሉ።*

 9 አምላክ ሆይ፣ አዲስ መዝሙር እዘምርልሃለሁ።+

አሥር አውታር ባለው መሣሪያ የታጀበ የውዳሴ መዝሙር እዘምርልሃለሁ፤

10 እሱ ነገሥታትን ድል* ያጎናጽፋል፤+

አገልጋዩን ዳዊትን ከገዳይ ሰይፍ ይታደጋል።+

11 ከባዕድ አገር ሰዎች እጅ ታደገኝ፤ አድነኝም፤

እነሱ በአፋቸው ውሸት ይናገራሉ፤

ደግሞም በውሸት ለመማል ቀኝ እጃቸውን ወደ ላይ ያነሳሉ።

12 ያን ጊዜ ወንዶች ልጆቻችን በፍጥነት እንደሚያድጉ ችግኞች፣

ሴቶች ልጆቻችን ደግሞ ቤተ መንግሥት ለማስጌጥ እንደተቀረጹ የማዕዘን ዓምዶች ይሆናሉ።

13 ጎተራዎቻችን በልዩ ልዩ የእህል ዓይነቶች ጢም ብለው ይሞላሉ፤

በመስክ ያሉት መንጎቻችን ተራብተው ሺዎች ደግሞም አሥር ሺዎች ይሆናሉ።

14 የከበዱት ከብቶቻችን ጉዳት አይደርስባቸውም ወይም አይጨነግፉም፤

በአደባባዮቻችን ላይ የጭንቅ ዋይታ አይሰማም።

15 ይህ የሚሆንለት ሕዝብ ደስተኛ ነው!

አምላኩ ይሖዋ የሆነለት ሕዝብ ደስተኛ ነው!+

የዳዊት የውዳሴ መዝሙር።

א [አሌፍ]

145 ንጉሡ አምላኬ ሆይ፣+ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤

ለዘላለም ስምህን አወድሳለሁ።+

ב [ቤት]

 2 ቀኑን ሙሉ አወድስሃለሁ፤+

ለዘላለም ስምህን አወድሳለሁ።+

ג [ጊሜል]

 3 ይሖዋ ታላቅ ነው፤ እጅግ ሊወደስም ይገባዋል፤+

ታላቅነቱ አይመረመርም።*+

ד [ዳሌት]

 4 ትውልዶች ሁሉ ሥራህን ያወድሳሉ፤

ስላከናወንካቸው ታላላቅ ነገሮች ይናገራሉ።+

ה [ሄ]

 5 ታላቅ ውበት ስለተጎናጸፈው ግርማህ ይናገራሉ፤+

እኔም ስለ ድንቅ ሥራዎችህ አሰላስላለሁ።

ו [ዋው]

 6 እጅግ አስደናቂ ስለሆነው ሥራህ* ይናገራሉ፤

እኔም ስለ ታላቅነትህ አውጃለሁ።

ז [ዛየን]

 7 የጥሩነትህን ብዛት ሲያስታውሱ በስሜት ያወራሉ፤+

ከጽድቅህም የተነሳ እልል ይላሉ።+

ח [ኼት]

 8 ይሖዋ ሩኅሩኅና* መሐሪ፣+

እንዲሁም ለቁጣ የዘገየ ነው፤ ታማኝ ፍቅሩም ታላቅ ነው።+

ט [ቴት]

 9 ይሖዋ ለሁሉም ጥሩ ነው፤+

ምሕረቱም በሥራው ሁሉ ላይ ይታያል።

י [ዮድ]

10 ይሖዋ ሆይ፣ ሥራዎችህ ሁሉ ከፍ ከፍ ያደርጉሃል፤+

ታማኝ አገልጋዮችህም ያወድሱሃል።+

כ [ካፍ]

11 የንግሥናህን ክብር ያውጃሉ፤+

ስለ ኃያልነትህም ይናገራሉ፤+

ל [ላሜድ]

12 ይህም ለሰዎች ታላላቅ ሥራዎችህንና+

የንግሥናህን ታላቅ ክብር+ ያስታውቁ ዘንድ ነው።

מ [ሜም]

13 ንግሥናህ ዘላለማዊ ነው፤

ግዛትህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ጸንቶ ይኖራል።+

ס [ሳሜኽ]

14 ይሖዋ ሊወድቁ የተቃረቡትን ሁሉ ይደግፋል፤+

ያጎነበሱትንም ሁሉ ቀና ያደርጋል።+

ע [አይን]

15 ዓይን ሁሉ አንተን በተስፋ ይመለከታል፤

አንተም ምግባቸውን በወቅቱ ትሰጣቸዋለህ።+

פ [ፔ]

16 አንተ እጅህን ትዘረጋለህ፤

የሕያዋን ፍጥረታትንም ሁሉ ፍላጎት ታሟላለህ።+

צ [ጻዴ]

17 ይሖዋ በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ፣+

በሥራውም ሁሉ ታማኝ ነው።+

ק [ኮፍ]

18 ይሖዋ ለሚጠሩት ሁሉ፣

በእውነት* ለሚጠሩት+ ሁሉ ቅርብ ነው።+

ר [ረሽ]

19 የሚፈሩትን ሰዎች ፍላጎት ያረካል፤+

እርዳታ ለማግኘት የሚያሰሙትንም ጩኸት ይሰማል፤ ደግሞም ይታደጋቸዋል።+

ש [ሺን]

20 ይሖዋ የሚወዱትን ሁሉ ይጠብቃል፤+

ክፉዎችን ሁሉ ግን ይደመስሳል።+

ת [ታው]

21 አፌ የይሖዋን ውዳሴ ያስታውቃል፤+

ሕያዋን ፍጥረታት በሙሉ ቅዱስ ስሙን* ለዘላለም ያወድሱ።+

146 ያህን አወድሱ!*+

ሁለንተናዬ* ይሖዋን ያወድስ።+

 2 በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይሖዋን አወድሳለሁ።

በሕይወት እስካለሁ ድረስ ለአምላኬ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።

 3 በመኳንንትም* ሆነ

ማዳን በማይችሉ ሰዎች አትታመኑ።+

 4 መንፈሱ* ትወጣለች፤ ወደ መሬት ይመለሳል፤+

በዚያው ቀን ሐሳቡ ሁሉ ይጠፋል።+

 5 የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የሆነ፣+

በአምላኩ በይሖዋ ተስፋ የሚያደርግ ሰው ደስተኛ ነው፤+

 6 እሱ የሰማይ፣ የምድር፣

የባሕርና በውስጣቸው ያሉት ነገሮች ሁሉ ፈጣሪ ነው፤+

ደግሞም ለዘላለም ታማኝ ነው፤+

 7 ግፍ ለተፈጸመባቸው ፍትሕ ያሰፍናል፤

ለተራቡት ምግብ ይሰጣል።+

ይሖዋ እስረኞችን ነፃ ያወጣል።*+

 8 ይሖዋ የዓይነ ስውራንን ዓይን ያበራል፤+

ይሖዋ ያጎነበሱትን ቀና ያደርጋል፤+

ይሖዋ ጻድቃንን ይወዳል።

 9 ይሖዋ የባዕድ አገር ሰዎችን ይጠብቃል፤

አባት የሌለውን ልጅና መበለቲቱን ይደግፋል፤+

የክፉዎችን ዕቅድ ግን ያጨናግፋል።*+

10 ይሖዋ ለዘላለም ይነግሣል፤+

ጽዮን ሆይ፣ አምላክሽ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይገዛል።

ያህን አወድሱ!*

147 ያህን አወድሱ!*

ለአምላካችን የውዳሴ መዝሙር መዘመር ጥሩ ነው፤

እሱን ማወደስ ደስ ያሰኛል፤ ደግሞም ተገቢ ነው።+

 2 ይሖዋ ኢየሩሳሌምን ይገነባል፤+

የተበተኑትን የእስራኤል ነዋሪዎች ይሰበስባል።+

 3 የተሰበረ ልብ ያላቸውን ይጠግናል፤

ቁስላቸውን ይፈውሳል።

 4 የከዋክብትን ብዛት ይቆጥራል፤

ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል።+

 5 ጌታችን ታላቅ ነው፤ ደግሞም እጅግ ኃያል ነው፤+

ማስተዋሉም ወሰን የለውም።+

 6 ይሖዋ የዋሆችን ያነሳል፤+

ክፉዎችን ግን መሬት ላይ ይጥላል።

 7 ለይሖዋ በምስጋና ዘምሩ፤

ለአምላካችን በበገና የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤

 8 እሱ ሰማያትን በደመናት ይሸፍናል፤

ለምድር ዝናብ ይሰጣል፤+

በተራሮች ላይ ሣር እንዲበቅል ያደርጋል።+

 9 ለእንስሳት እንዲሁም የሚበሉትን ለማግኘት ለሚጮኹ የቁራ ጫጩቶች

ምግብ ይሰጣል።+

10 በፈረስ ጉልበት አይደሰትም፤+

የሰው እግር ጥንካሬም አያስደንቀውም።+

11 ከዚህ ይልቅ ይሖዋ እሱን በሚፈሩ፣

ታማኝ ፍቅሩን በሚጠባበቁ ሰዎች ይደሰታል።+

12 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ይሖዋን ከፍ ከፍ አድርጊ።

ጽዮን ሆይ፣ አምላክሽን አወድሺ።

13 እሱ የከተማሽን በሮች መወርወሪያዎች ያጠናክራል፤

በውስጥሽ ያሉትን ወንዶች ልጆች ይባርካል።

14 በክልልሽ ውስጥ ሰላም ያሰፍናል፤+

ምርጥ በሆነ ስንዴ* ያጠግብሻል።+

15 ትእዛዙን ወደ ምድር ይልካል፤

ቃሉም በፍጥነት ይሮጣል።

16 በረዶን እንደ ሱፍ ይልካል፤+

አመዳዩን እንደ አመድ ይበትናል።+

17 የበረዶውን ድንጋይ እንደ ዳቦ ፍርፋሪ ይወረውራል።+

እሱ የሚልከውን ቅዝቃዜ ማን ሊቋቋም ይችላል?+

18 ቃሉን ይልካል፤ እነሱም ይቀልጣሉ።

ነፋሱ እንዲነፍስ ያደርጋል፤+ ውኃውም ይፈስሳል።

19 ቃሉን ለያዕቆብ፣

ሥርዓቱንና ፍርዶቹን ለእስራኤል ያስታውቃል።+

20 ይህን ለሌላ ለማንም ብሔር አላደረገም፤+

እነሱ ስለ ፍርዶቹ ምንም የሚያውቁት ነገር የለም።

ያህን አወድሱ!*+

148 ያህን አወድሱ!*

ይሖዋን ከሰማያት አወድሱት፤+

በከፍታ ቦታዎች አወድሱት።

 2 መላእክቱ ሁሉ፣ አወድሱት።+

ሠራዊቱ ሁሉ፣+ አወድሱት።

 3 ፀሐይና ጨረቃ፣ አወድሱት።

የምታብረቀርቁ ከዋክብት ሁሉ፣ አወድሱት።+

 4 ሰማየ ሰማያት፣ አወድሱት፤

ከሰማያት በላይ ያላችሁ ውኃዎች፣ አወድሱት።

 5 የይሖዋን ስም ያወድሱ፤

እሱ ስላዘዘ ተፈጥረዋልና።+

 6 ለዘላለም አጸናቸው፤+

ጊዜ የማይሽረው ድንጋጌ አውጥቷል።+

 7 ይሖዋን ከምድር አወድሱት፤

እናንተ ግዙፍ የባሕር ፍጥረታትና ጥልቅ ውኃዎች ሁሉ፣

 8 መብረቅና በረዶ፣ አመዳይና ጥቅጥቅ ያለ ደመና፣

አንተም ቃሉን የምትፈጽም አውሎ ነፋስ፣+

 9 እናንተ ተራሮችና ኮረብቶች ሁሉ፣+

እናንተ ፍሬ የምታፈሩ ዛፎችና አርዘ ሊባኖሶች ሁሉ፣+

10 እናንተ የዱር እንስሳትና+ የቤት እንስሳት ሁሉ፣

እናንተ መሬት ለመሬት የምትሳቡ ፍጥረታትና ክንፍ ያላችሁ ወፎች፣

11 እናንተ የምድር ነገሥታትና ብሔራት ሁሉ፣

እናንተ መኳንንትና የምድር ፈራጆች ሁሉ፣+

12 እናንተ ወጣት ወንዶችና ወጣት ሴቶች፣*

ሽማግሌዎችና ልጆች በኅብረት አወድሱት።

13 የይሖዋን ስም ያወድሱ፤

ስሙ ብቻውን ከሌሎች ሁሉ በላይ ነውና።+

ግርማው ከምድርና ከሰማይ በላይ ነው።+

14 ታማኝ አገልጋዮቹ ሁሉ፣

ማለትም ለእሱ ቅርብ የሆኑት የሕዝቡ የእስራኤል ልጆች ይወደሱ ዘንድ

የሕዝቡን ብርታት* ከፍ ያደርጋል።

ያህን አወድሱ!*

149 ያህን አወድሱ!*

ለይሖዋ አዲስ መዝሙር ዘምሩ፤+

በታማኝ አገልጋዮች ጉባኤ መካከል አወድሱት።+

 2 እስራኤል በታላቅ ሠሪው+ ሐሴት ያድርግ፤

የጽዮን ልጆች በንጉሣቸው ደስ ይበላቸው።

 3 ስሙን በሽብሸባ ያወድሱ፤+

በአታሞና በበገና የውዳሴ መዝሙር ይዘምሩለት።+

 4 ይሖዋ በሕዝቡ ደስ ይሰኛልና።+

እሱ የዋሆችን በማዳን ውበት ያጎናጽፋቸዋል።+

 5 ታማኝ አገልጋዮቹ በክብር ሐሴት ያድርጉ፤

በመኝታቸው ላይ ሆነው እልል ይበሉ።+

 6 አንደበታቸው አምላክን የሚያወድስ መዝሙር ይዘምር፤

እጃቸውም በሁለቱም በኩል የተሳለ ሰይፍ ይያዝ፤

 7 ይህም በብሔራት ላይ የበቀል እርምጃ እንዲወስዱ፣

ሕዝቦችንም እንዲቀጡ፣

 8 ነገሥታታቸውን በሰንሰለት፣

በመካከላቸው ያሉትን ታላላቅ ሰዎችም በእግር ብረት እንዲያስሩ፣

 9 ደግሞም በእነሱ ላይ የተላለፈውን በጽሑፍ የሰፈረ ፍርድ እንዲፈጽሙ ነው።+

ታማኝ አገልጋዮቹ ሁሉ ይህ ክብር ይገባቸዋል።

ያህን አወድሱ!*

150 ያህን አወድሱ!*+

አምላክን በተቀደሰ ስፍራው አወድሱት።+

ብርታቱን በሚያሳየው ጠፈር* አወድሱት።+

 2 ስለ ብርቱ ሥራዎቹ አወድሱት።+

ወደር የለሽ ስለሆነው ታላቅነቱ አወድሱት።+

 3 በቀንደ መለከት+ ድምፅ አወድሱት።

በባለ አውታር መሣሪያና በበገና አወድሱት።+

 4 በአታሞና+ በሽብሸባ አወድሱት።

በባለ አውታር መሣሪያና+ በዋሽንት+ አወድሱት።

 5 በሚያስተጋባ ሲምባል* አወድሱት።

ኃይለኛ ድምፅ በሚያወጣ ሲምባል+ አወድሱት።

 6 እስትንፋስ ያለው ሁሉ ያህን ያወድስ።

ያህን አወድሱ!*+

ወይም “ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያሰላስለዋል።”

ወይም “የሚያውጠነጥኑት።”

ወይም “ተማክረው።”

ወይም “በእሱ ክርስቶስ ላይ።”

ወይም “ተጠንቀቁ።”

ቃል በቃል “ሳሙት።”

ቃል በቃል “እሱ።”

መንፈሳዊ መዝሙርን ያመለክታል።

ወይም “ስለ ነፍሴ።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ቃል በቃል “ሰፊ ቦታ።”

ወይም “ለእሱ ታማኝ የሆነውን ሰው ይለያል፤ ለእሱ ታማኝ የሆነውን ሰው ለራሱ ይለያል።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ደም አፍሳሽና አታላይ የሆነን ሰው።”

ወይም “ለአንተ አክብሮታዊ ፍርሃት በማሳየት።”

ወይም “በለሰለሰ አንደበት ይናገራሉ።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ምሕረት አድርግልኝ።”

ወይም “ነፍሴ እጅግ ተረብሻለች።”

ወይም “ነፍሴን ታደጋት።”

ወይም “አያስታውሱም።”

ወይም “በሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ቃል በቃል “አልጋዬ እንዲዋኝ አደርጋለሁ።”

ወይም “አርጅቷል።”

ወይም “የሐዘን እንጉርጉሮ።”

ወይም “ነፍሴን ይዘነጣጥሏታል።”

“ያለምክንያት የሚቃወመኝን ሰው ትቼ፣ መልካም ያደረገልኝን ሰው በድዬ ከሆነ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ነፍሴን አሳዶ ይያዛት።”

እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል የሥነ ምግባር ንጽሕናን፣ ሁለት ልብ አለመሆንንና እንከን የለሽ መሆንን ያመለክታል።

ወይም “ልብንና ኩላሊትን የምትፈትን።”

ወይም “የውግዘት ቃላት ይሰነዝራል።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

“ግርማህ ከሰማያት በላይ የተነገረ!” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “እንደ አምላክ ካሉት።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ፍሬያማ የሆነችውን ምድር።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “በነፍሱ ምኞት ይኩራራልና።”

“ስግብግብ ሰው ራሱን ይባርካል” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ጉራውን ይነዛል።”

ወይም “ፈጽሞ አልንገዳገድም (አልውተረተርም)።”

ወይም “በጥሻው ውስጥ እንዳለ።”

ወይም “ወላጅ አልባ ለሆነው ልጅ።”

ወይም “ነፍሴን እንዴት እንዲህ ትሏታላችሁ?”

ቃል በቃል “ወደ ተራራችሁ ብረሩ።”

ወይም “የፍትሕ መሠረቶች።”

ወይም “የሚያበሩት።”

ጠብን፣ ድብድብንና ጉዳት ማድረስን ያመለክታል።

ወይም “ነፍሱ ትጠላዋለች፤ ሁለንተናው ይጠላዋል።”

“ፍም” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ሞገሱን ያገኛሉ።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ቃል በቃል “በለስላሳ ከንፈር ይናገራሉ።”

ቃል በቃል “በልብና በልብም።”

ወይም “ጉራ ከሚነዙባቸው።”

“መሬት ላይ በተተከለ የማቅለጫ ምድጃ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ነፍሴ በጭንቀት ተውጣ የምትኖረው።”

ወይም “ማመዛዘን የጎደለው።”

ወይም “በንጹሕ አቋም።”

ወይም “ወዳጆቹን አያሳፍርም።”

ቃል በቃል “መሐላውን።”

ወይም “ፈጽሞ አይንገዳገድም (አይውተረተርም)።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ጥልቅ ስሜቴ።” ቃል በቃል “ኩላሊቴ።”

ወይም “ፈጽሞ አልንገዳገድም (አልውተረተርም)።”

ቃል በቃል “ክብሬ።”

ወይም “ሥጋዬም ያለስጋት ይኖራል።”

ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ነፍሴን አትተዋትምና።”

“መበስበስን እንዲያይ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ቃል በቃል “ከፊትህ ጋር።”

ወይም “ፍስሐ።”

ወይም “ጎንበስ ብለህ ስማኝ።”

ወይም “በነፍስ ላይ ከተነሱ ጠላቶቼ።”

ወይም “በገዛ ራሳቸው ስብ ተሸፍነዋል።”

ወይም “መሬት ላይ መጣል።”

ወይም “ነፍሴን ታደጋት።”

ወይም “ሥርዓት።”

ወይም “ኃያል አዳኜና።” የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “የሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “በነፋስ።”

ወይም “የውኃ መውረጃ ቦዮች ታዩ።”

ወይም “ሰፊ ወደሆነ ስፍራ።”

ወይም “የተጎሳቆሉትን ሰዎች።”

ቃል በቃል “ትዕቢተኛውን ዓይን።”

ወይም “ቁርጭምጭሚቶቼ።”

ወይም “የጠላቶቼን ጀርባ ትሰጠኛለህ።”

ቃል በቃል “ጸጥ አሰኛቸዋለሁ።”

ወይም “ይጠወልጋሉ።”

ወይም “ታላላቅ ድሎችን ያጎናጽፋል።”

“መለኪያ ገመዳቸው” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ፍሬያማ እስከሆነው ምድር።”

ወይም “ነፍስን ያድሳል (ይመልሳል)።”

ወይም “ብዛት ካለው የጠራ ወርቅ።”

ወይም “ከብዙ በደልም።”

ቃል በቃል “እንደ ስብ ቆጥሮ።”

ወይም “ምክርህንም።”

ወይም “በሚቀዳጀው ታላቅ ድል።”

ወይም “ከጠራ።”

ቃል በቃል “የቀኖች ርዝማኔ።”

ቃል በቃል “በፊትህ ደስታ።”

ወይም “ፈጽሞ አይንገዳገድም (አይውተረተርም)።”

ቃል በቃል “የደጋንህን አውታር።”

ቃል በቃል “በፊታቸው።”

ቅኝት ወይም የሙዚቃ ስልት ሊሆን ይችላል።

ወይም “እስራኤል በሚያቀርበው ውዳሴ መካከል (ላይ) ነግሠሃል።”

ወይም “ኀፍረት አልደረሰባቸውም።”

ወይም “የነቀፈኝ።”

ቃል በቃል “በአንተ ላይ ተጣልኩ።”

ወይም “እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩ።”

ወይም “ነፍሴን ከሰይፍ አድናት።”

ቃል በቃል “አንድ ያለችኝን።” ነፍሱን ወይም ሕይወቱን ያመለክታል።

ቃል በቃል “እጅ።”

ቃል በቃል “ልባችሁ ለዘላለም ይኑር።”

ቃል በቃል “የሰቡት ሁሉ።”

ወይም “ነፍሳቸውን።”

“ወደ እረፍት ውኃዎች” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ነፍሴን።”

ወይም “ያጽናኑኛል።”

ወይም “በነፍሴ።” አንድ ሰው የሚምልበትን የይሖዋን ሕይወት ያመለክታል።

ወይም “ፍትሕንም።”

ወይም “ከፍ በሉ።”

ወይም “ነፍሴን ወደ አንተ አነሳለሁ።”

ወይም “ከጥንት ዘመን ጀምሮ የነበሩትን።”

ቃል በቃል “በፍርድ።”

ወይም “ነፍሱ ጥሩ የሆነውን ነገር ታገኛለች።”

ወይም “ነፍሴን።”

መዝ 7:8 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።

ቃል በቃል “ዋጀው።”

መዝ 7:8 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።

ወይም “ጥልቅ ስሜቴንና።” ቃል በቃል “ኩላሊቴንና።”

ቃል በቃል “(አታላይ ከሆኑ ሰዎች ጋር) አልቀመጥም።”

ወይም “ከግብዞችም ጋር አልቀላቀልም።”

ቃል በቃል “መቀመጥ።”

ወይም “ነፍሴን አታጥፋ።”

ወይም “ደም ከሚያፈሱ ሰዎች።”

ቃል በቃል “ዋጀኝ።”

ቃል በቃል “በሸንጎዎች መካከል።”

ወይም “በተመስጦ እመለከት።”

ወይም “ለጠላቶቼ ነፍስ።”

“በሕያዋን ምድር የይሖዋን ጥሩነት አያለሁ የሚል ጽኑ እምነት አለኝ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “መቃብር።”

“ከቅድስናው ግርማ የተነሳ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ይሖዋን አምልኩ።”

የሊባኖስን ሰንሰለታማ ተራሮች የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።

ቅርንጫፍ የሚመስሉ ቀንዶች ያሉት አጥቢ እንስሳ፤ ከአጋዘን ጋር ይመሳሰላል።

ወይም “በሰማይ ካለው ውቅያኖስ።”

ወይም “ስላወጣኸኝ።”

ወይም “ከሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ነፍሴን ከመቃብር አውጥተሃታል።”

ወይም “መቃብር።”

ቃል በቃል “ለቅዱስ መታሰቢያው።”

ወይም “በጎ ፈቃድ የሚያሳየው።”

ወይም “ፈጽሞ አልንገዳገድም (አልውተረተርም)።”

ቃል በቃል “ደሜና።”

ወይም “መቃብር።”

ወይም “ክብሬ።”

ወይም “ጎንበስ ብለህ ስማኝ።”

ወይም “ታማኝ።”

ወይም “የነፍሴን ጭንቀት።”

ወይም “ሰፊ በሆነ ስፍራ አቆምከኝ።”

ወይም “ነፍሴንና ሆዴን አድክሞታል።”

ወይም “ከአእምሯቸው ወጣሁ።”

ወይም “ነፍሴን።”

ወይም “በሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ቃል በቃል “ከምላስ ጠብ።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “የተተወለት።”

ወይም “ቁጣህ።”

ወይም “የሕይወቴ እርጥበት ተለወጠ።”

ቃል በቃል “በመዳን።”

ወይም “እስትንፋስ።”

ወይም “አክብሮታዊ ፍርሃት ያሳዩት።”

ወይም “ምክር።”

ወይም “ሐሳብ።”

ወይም “ምክር ለዘላለም ይጸናል።”

ወይም “ድል ያጎናጽፈኛል።”

ወይም “ነፍሳቸውን።”

ወይም “ነፍሳችን ይሖዋን በተስፋ ትጠባበቃለች።”

ይህ የንጉሥ አንኩስ የማዕረግ ስም እንደሆነ ይታመናል።

ወይም “ነፍሴ በይሖዋ ትኩራራለች።”

ወይም “ተስፋ የቆረጡትንም።”

ወይም “ጭንቀት።”

ወይም “ነፍስ።”

አብዛኛውን ጊዜ ቀስተኞች የሚይዙት ትንሽ ጋሻ።

ወይም “በሁለቱም በኩል ስለት ያለው መጥረቢያ፤ የውጊያ መጥረቢያ።”

ወይም “ነፍሴንም ‘የማድንሽ እኔ ነኝ’ በላት።”

ወይም “ነፍሴን።”

ወይም “ለነፍሴ ጉድጓድ ቆፍረውላታል።”

ወይም “ነፍሴ ግን በይሖዋ ሐሴት ታደርጋለች።”

ወይም “ነፍሴን ሐዘን ላይ ጣሏት።”

ወይም “ነፍሴን።”

ወይም “ወደ ጉያዬ በተመለሰ ጊዜ።”

“ፈሪሃ አምላክ የሌላቸው ሰዎች ለምግብ ብለው ያፌዛሉ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ነፍሴን ታደግ።”

ቃል በቃል “አንድ ያለችኝን።” ነፍሱን ወይም ሕይወቱን ያመለክታል።

ወይም “እሰይ! ነፍሳችን ደስ አላት።”

ወይም “ምላሴ በጽድቅህ ላይ ያሰላስላል።”

ቃል በቃል “እንደ አምላክ ተራሮች።”

ወይም “ሰውንና እንስሳን ታድናለህ።”

ቃል በቃል “ስቡን።”

ወይም “ቱግ አትበል።”

ወይም “በይሖዋ እጅግ ደስ ይበልህ።”

ወይም “ሸክምህን ወደ ይሖዋ አንከባለው።”

ወይም “በትዕግሥት።”

“ጉዳት ላይ ሊጥልህ ስለሚችል አትበሳጭ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ቃል በቃል “ነቀፋ የሌለባቸውን ሰዎች ቀናት።”

ወይም “ቸርነት ያደርጋል።”

ወይም “አካሄዱን ያጸናለታል።”

ወይም “በእጁ።”

ቃል በቃል “ዳቦ።”

ወይም “በለሆሳስ ይናገራል።”

ወይም “ንጹሕ አቋሙን የሚጠብቅን።”

ቃል በቃል “በሥጋዬ ላይ ጤነኛ ቦታ የለም።”

ቃል በቃል “መላ ወገቤ ተቃጠለ።”

ወይም “እጮኻለሁ።”

ወይም “ነፍሴን።”

ቃል በቃል “ሕያዋንና።”

“ይሁንና ከመሬት ተነስተው የሚጠሉኝ ብዙ ናቸው” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “በማሰሪያ እሸብበዋለሁ።”

ወይም “ተቀሰቀሰ።”

ቃል በቃል “ጋለ።”

ወይም “በምቃትትበት ጊዜ።”

ወይም “አላፊ ጠፊ እንደሆንኩ።”

ቃል በቃል “ጋት።”

ቃል በቃል “የሚንጫጫው።”

ወይም “ሰፋሪ።”

ወይም “ይሖዋን በትዕግሥት ጠበቅኩት።”

ወይም “ለመስማት አጎነበሰ።”

ወይም “በአክብሮታዊ ፍርሃት።”

ወይም “ውሸታም።”

ወይም “በመሥዋዕትና በመባ ደስ አልተሰኘህም።”

አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ጥንታዊ ጽሑፎች “መሥዋዕትንና መባን አልፈለግክም፤ ከዚህ ይልቅ አካል አዘጋጀህልኝ” ይላሉ። ከዕብ 10:5 ጋር አወዳድር።

ወይም “እሻለሁ።”

ወይም “ነፍሴን።”

ወይም “ፍላጎት፤ ነፍስ።” የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ነፍሴን ፈውሳት።”

ወይም “እኔን ለማጥቃት ተነሳ።”

መዝ 7:8 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ቅርንጫፍ የሚመስሉ ቀንዶች ያሉት አጥቢ እንስሳ፤ ከአጋዘን ጋር ይመሳሰላል።

ወይም “ነፍሴ አንተን ትናፍቃለች።”

ወይም “ነፍሴ ተጠማች።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “በዝግታ።”

ወይም “ነፍሴ ተስፋ የምትቆርጠው።”

ወይም “ነፍሴ ተስፋ ቆርጣለች።”

ወይም “ከትንሹ ተራራ።”

“አጥንቶቼን ያደቀቁ ያህል” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ነፍሴ ተስፋ የምትቆርጠው።”

ወይም “ነፍሴ ተስፋ የምትቆርጠው።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ታላቅ መዳን።”

ወይም “አጎናጽፍ።”

ቃል በቃል “መተረቻ እንድንሆን።”

ወይም “ነፍሳችን ወደ አፈር ተጥላለችና።”

ቃል በቃል “ዋጀን።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ቃል በቃል “ሥራዎቼ።”

ወይም “ጸሐፊ።”

ወይም “ስኬት ለማግኘት።”

ቃል በቃል “ያስተምርሃል።”

ወይም “የፍትሕ።”

በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ሽቶ ለመሥራት የሚያገለግል ጥሩ መዓዛ ያለው ንጥረ ነገር የሚገኝበትን ዛፍ ያመለክታል።

ወይም “የሙዚቃ መሣሪያዎች።”

ወይም “ንግሥቲቱ።”

ቃል በቃል “ተውባ ውስጥ ተቀምጣለች።”

ቃል በቃል “ወርቀ ዘቦ።”

“በጥልፍ ሥራ የተዋበ ቀሚሷን” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

“ጋሻዎችን” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “በአውራ በግ ቀንድ፤ በትራምፔት።”

ቃል በቃል “ጋሻዎች።”

ወይም “በቀጠሮ ተገናኝተዋልና።”

ቃል በቃል “ሴቶች ልጆችም።”

ወይም “የማይደፈሩ ግንቦቿን።”

“እስክንሞት ድረስ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “በዚህ ሥርዓት።”

ቃል በቃል “የሰው ዘር ወንዶች ልጆችም ሆናችሁ የሰው ወንዶች ልጆች።”

ቃል በቃል “ስህተት።”

ወይም “ለነፍሳቸው።”

ወይም “ሕይወታቸውን ለመቤዠት የሚከፈለው።”

ወይም “መቃብር።”

ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ነፍሴን ይዋጃታል።”

ወይም “ነፍሱን።”

ወይም “ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ።”

ቃል በቃል “አውራ ፍየሎች።”

ወይም “መመሪያዬን፤ ትምህርቴን።”

ቃል በቃል “ቃሌንም ወደ ኋላህ ትጥላለህ።”

“ከእሱ ጋር ትተባበራለህ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ስም ታጠፋለህ።”

ወይም “ከአእምሮዬ አይጠፋም።”

ቃል በቃል “አንተን ብቻ።”

ወይም “እናቴ ከፀነሰችኝ ጊዜ አንስቶ ኃጢአተኛ ነኝ።”

ወይም “የውስጥ ሰውነቴን።”

ወይም “ሰውር።”

ወይም “ደምስስ።”

ቃል በቃል “በፈቃደኝነት መንፈስ ደግፈኝ።”

ወይም “አትንቅም።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “በአክብሮታዊ ፍርሃት።”

ወይም “ምሽጉ።”

ቃል በቃል “ራሱ በሚያመጣው መከራ።”

ወይም “ይጠለላል።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ማመዛዘን የጎደለው።”

“የሚያስፈራ ነገር በሌለበት በፍርሃት ይዋጣሉ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ቃል በቃል “በዙሪያህ የሰፈሩትን።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ተሟገትልኝ።”

ወይም “ነፍሴን።”

ወይም “አምላክን በፊታቸው አላደረጉትም።”

ወይም “ነፍሴን።”

ቃል በቃል “ዝም አሰኛቸው።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “እርዳታ ለማግኘት ስጸልይም ራስህን አትሰውር።”

ወይም “እኩያዬ።”

ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “እጮኻለሁ።”

ቃል በቃል “ነፍሴን ይዋጃል።”

መዝ 55:13 እና 14 ላይ የተጠቀሰውን የቀድሞ ወዳጅ ያመለክታል።

ወይም “እንዲንገዳገድ፤ እንዲውተረተር።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “እኔን ለመንከስ እየሞከረ።”

ወይም “ነፍሴን።”

ወይም “ነፍሴን ከሞት ታድገሃታልና።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ነፍሴ አንተን መጠጊያ አድርጋለችና።”

ወይም “ነፍሴ በአንበሶች ተከባለች።”

ወይም “ነፍሴ ከጭንቅ የተነሳ ጎብጣለች።”

ቃል በቃል “ክብሬ።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ቃል በቃል “ከማህፀን።”

ወይም “ተበላሽተዋል።”

በእስያና በአፍሪካ የሚገኝ እጅግ መርዘኛ የሆነ እባብ፤ ኮብራ።

ወይም “ደቦል አንበሶች።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ቃል በቃል “ቤቱን።”

ወይም “ደም ከተጠሙ።”

ወይም “ነፍሴን።”

ወይም “እየጮኹ።”

ወይም “የሚፈልቀውን።”

ወይም “እየጮኹ።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

“አቆምክላቸው” ማለትም ሊሆን ይችላል።

“በቅዱስ ስፍራው” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ረባዳማ ሜዳ።”

ቃል በቃል “ለራሴ ምሽግ ነው።”

“ወደተመሸገችው” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “በዛለ።”

ቃል በቃል “ቀናት።”

ወይም “ይኖራል።”

ወይም “ላክ።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ነፍሴ ዝም ብላ አምላክን ትጠባበቃለች።”

“እሱ ያዘመመ ግንብ፣ ሊወድቅ የተቃረበም የድንጋይ ቅጥር የሆነ ይመስል ሁላችሁም የምታጠቁት እስከ መቼ ነው?” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ከታላቅ ክብሩ ሊያዋርዱት።”

ወይም “ነፍሴ ሆይ፣ አምላክን ዝም ብለሽ ተጠባበቂ።”

ወይም “ነፍሴ አንተን ተጠማች።”

ቃል በቃል “ሥጋዬ አንተን ከመናፈቋ የተነሳ እጅግ ዝላለች።”

ወይም “ነፍሴ ምርጥ የሆነውንና ስቡን በልታ ጠገበች።”

ወይም “በክፍለ ሌሊቶች።”

ወይም “ነፍሴ አንተን የሙጥኝ ትላለች።”

ወይም “ነፍሴን ለማጥፋት፤ እኔን ለመግደል።”

ወይም “ይኮራል።”

ወይም “ክፉ ነገር ለማድረግ አንዳቸው ሌላውን ያበረታታሉ።”

ወይም “ይኮራሉ።”

ቃል በቃል “ሥጋ ሁሉ።”

ወይም “አክብሮታዊ ፍርሃት።”

ቃል በቃል “እሱ።”

ቃል በቃል “እሱ።”

ቃል በቃል “እንድትጥለቀለቅ።”

ወይም “ጉብታዎቿንም።”

ቃል በቃል “ስብ ይንጠባጠባል።”

ቃል በቃል “ያንጠባጥባሉ።”

ወይም “ረባዳማ ሜዳዎቹም።”

ወይም “ነፍሳችንን በሕይወት ያቆያታል።”

ወይም “እንዲንገዳገድ፤ እንዲውተረተር።”

ቃል በቃል “በዳሌዎቻችንም ላይ።”

ቃል በቃል “ራሳችን።”

ወይም “ለነፍሴ ያደረገላትንም።”

ወይም “ያከብሩታል።”

“በደመናት ላይ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

“ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

ቃል በቃል “ፈራጅ።”

ወይም “ዓመፀኞች።”

ቃል በቃል “በሕዝብህ ፊት በወጣህ ጊዜ።”

ቃል በቃል “አንጠባጠበ።”

ቃል በቃል “ለርስትህ።”

“በበጎች ጉረኖ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ቢጫማ አረንጓዴ ቀለም ባለው።”

ወይም “በጻልሞን በረዶ የወረደ ያህል ነበር።”

ወይም “ግርማ የተላበሰ ተራራ ነው።”

ቃል በቃል “በጉባኤዎች።”

“እስኪረጋግጡ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

“አምባሳደሮች” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ኩሽ።”

ቃል በቃል “በደመናት።”

ቃል በቃል “መቅደስህ (ስትወጣ . . . ታሳድራለህ)።”

ወይም “አክብሮታዊ ፍርሃት።”

ወይም “ነፍሴን ሊያሰምጣት ስለደረሰ።”

ወይም “ነፍሴን።”

“ባለቀስኩና በጾምኩ ጊዜ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ቃል በቃል “መተረቻ።”

ወይም “ወደ ነፍሴ ቀርበህ ተቤዣት።”

ወይም “ተስፋዬም ተሟጠጠ።”

ወይም “መርዛማ ተክል።”

ወይም “ወጥመድ።”

ቃል በቃል “ዳሌያቸውም።”

ወይም “በግንብ የታጠረው ሰፈራቸው።”

ወይም “ከሕይወት መጽሐፍ።”

ይህ ቃል ምድሪቱን እንደሚወርሱ ያሳያል።

ወይም “ለመታሰቢያ።”

ወይም “ነፍሴን።”

ወይም “ጎንበስ ብለህ ስማኝ።”

ወይም “አንተ መመኪያዬ ነህ።”

ወይም “ነፍሴን።”

ወይም “ነፍሴን የሚቃወሟት።”

ወይም “ልቆጥራቸው።”

ቃል በቃል “ስለ ክንድህ።”

ወይም “በምድር ካሉ ጥልቅ ውኃዎች።”

ወይም “ነፍሴን ዋጅተሃታልና።”

ወይም “ያሰላስላል።”

ቃል በቃል “ይፍረድ።”

ቃል በቃል “ያቆጠቁጣል።”

ኤፍራጥስን ያመለክታል።

ወይም “ይገዛል።”

ወይም “ነፍስ።”

ወይም “ነፍሳቸውን ይዋጃል።”

ወይም “ጉራቸውን በሚነዙ ሰዎች።”

ወይም “ቦርጫቸው የሰባ።”

ቃል በቃል “ከስባቸው።”

ቃል በቃል “የወንዶች ልጆችህን ትውልድ።”

ቃል በቃል “ምስላቸውን ትንቃለህ።”

ቃል በቃል “ኩላሊቴንም።”

ወይም “ታማኞች ሳይሆኑ የሚቀሩትን።”

ቃል በቃል “ዝም ታሰኛቸዋለህ።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ቃል በቃል “የጨሰው።”

ቃል በቃል “ጉባኤ።”

ወይም “ጉባኤ በምታደርግበት ቦታ።”

ወይም “አምላክ የሚመለክባቸው።”

ወይም “ከልብስህ እጥፋት።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ብርሃን ሰጪ አካልንና ፀሐይን።”

ወይም “ነፍስ።”

ቃል በቃል “ቀንዳችሁን።”

ቃል በቃል “ቀንዳችሁን።”

ቃል በቃል “ቀንድ።”

ወይም “አንተ ብርሃን ተላብሰሃል።”

ቃል በቃል “መንፈስ።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ነፍሴ ልትጽናና አልቻለችም።”

ቃል በቃል “መንፈሴም ዛለ።”

ወይም “በባለ አውታር መሣሪያ የምጫወተውን ሙዚቃ።”

ቃል በቃል “መንፈሴ በጥሞና ይመረምራል።”

ወይም “የሚያቆስለኝ።”

ቃል በቃል “ቀኝ እጁን።”

ቃል በቃል “በክንድህ።”

ቃል በቃል “ዋጅተሃል።”

ወይም “ፍሬያማ በሆነችው ምድር።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “መመሪያዬን፤ ትምህርቴን።”

ቃል በቃል “ልቡን ያላዘጋጀና።”

ወይም “እንደ ግድግዳ አቆመ።”

ወይም “ነፍሳቸው የተመኘችውን።”

ቃል በቃል “ፈተኑት።”

ወይም “የመላእክትን።”

ወይም “እንደሚበቀልላቸው።”

ቃል በቃል “ይሸፍን።”

“መንፈስ እንደሚወጣና እንደማይመለስ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “አበሳጩት።”

ቃል በቃል “የዋጀበትን።”

ቃል በቃል “እጁንም።”

“ለኃይለኛ ትኩሳት” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ነፍሳቸውን ከሞት አላተረፈም።”

ቃል በቃል “ፈተኑት።”

ወይም “ለቅናት።”

ቃል በቃል “የእሱ ድንግሎች አልተወደሱም።”

ቃል በቃል “መቅደሱን እንደ አርያም ገነባ።”

መዝ 7:8 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።

ቃል በቃል “ሸፍንልን።”

ቃል በቃል “የሞት ወንዶች ልጆችን።”

ቃል በቃል “ክንድህ።”

“ነፃ አውጣቸው” ማለትም ሊሆን ይችላል።

“በኪሩቤል መካከል” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ብርሃንህን ግለጥ።”

ቃል በቃል “በሚያቀርቡት ጸሎት ቁጣህ የሚነደው።”

የኤፍራጥስን ወንዝ ያመለክታል።

ወይም “የወይን ተክል ዋና ግንድ።”

ወይም “ቅርንጫፍ።”

ቃል በቃል “ከፊትህ ተግሣጽ።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ቋንቋ።”

ቃል በቃል “በነጎድጓድ መሰወሪያ ቦታ።”

“ጠብ” የሚል ትርጉም አለው።

ቃል በቃል “በምክራቸው ተመላለሱ።”

ቃል በቃል “ዘመናቸውም።”

ቃል በቃል “የስንዴ ስብ።”

ቃል በቃል “ይመግበዋል።” የአምላክን ሕዝብ ያመለክታል።

ወይም “በመለኮት ጉባኤ ይሰየማል።”

ወይም “እንደ አምላክ ባሉ።”

ወይም “ፍረዱ።”

ወይም “እንደ አምላክ ያላችሁ።”

ወይም “ዱዳ አትሁን።”

ወይም “ራሳቸውን ቀና ያደርጋሉ።”

ቃል በቃል “በሸሸግካቸው።”

ቃል በቃል “በአንድ ልብ ይማከራሉ።”

ወይም “ቃል ኪዳን ተጋብተዋል።”

ቃል በቃል “ክንድ ሆኑ።”

ወይም “ደረቅ ወንዝ።”

ወይም “መሪዎቻቸውንም።”

ወይም “አረም።”

ቃል በቃል “ሙላው።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ተወዳጅ።”

ወይም “ነፍሴ።”

“ባካ” የሚለው ስም የተገኘው “ለቅሶ” የሚል ትርጉም ካለው የዕብራይስጥ ቃል ነው። የተክሉ ዓይነት በትክክል አይታወቅም።

ወይም “የባካ ቁጥቋጦዎች በሚበቅሉበት ሸለቆ።”

“አስተማሪውም ራሱን በረከት ያጎናጽፋል” ማለትም ሊሆን ይችላል።

“አምላክ ሆይ፣ ጋሻችንን ተመልከት” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ቃል በቃል “ሸፈንክ።”

ወይም “መልሰህ ሰብስበን።”

ወይም “ብልጽግና።”

ወይም “ጎንበስ ብለህ ስማኝ።”

ወይም “ነፍሴን።”

ወይም “የአገልጋይህን ነፍስ ደስ አሰኛት።”

ወይም “ነፍሴን ወደ አንተ አነሳለሁና።”

ወይም “ያልተከፋፈለ ልብ ስጠኝ።”

ወይም “ነፍሴንም።”

ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ነፍሴን።”

ወይም “አንተንም በፊታቸው አላደረጉም።”

ወይም “ቸር።”

ወይም “እውነትህ።”

ወይም “ማስረጃ።”

ወይም “ለእኔ እውቅና ከሚሰጡት።”

ይህ ቃል ግብፅን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል።

ወይም “ኩሽን።”

ወይም “ክብ ሠርተው የሚጨፍሩ።”

ወይም “ለእኔ የሁሉ ነገር ምንጭ አንቺ ነሽ።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ጎንበስ ብለህ ስማኝ።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “በሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “መቃብር።”

ወይም “አቅም እንዳጣ ሰው።”

ቃል በቃል “እጅ።”

ወይም “በአባዶን።”

ወይም “ነፍሴን ፊት የምትነሳት ለምንድን ነው?”

“በአንድ ጊዜ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ጸንቶ ይኖራል።”

ወይም “ከመላእክት።”

ግብፅን ወይም የግብፅን ፈርዖን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል።

ቃል በቃል “ቀንዳችን።”

ቃል በቃል “ቀንዱ።”

ወይም “ሥልጣኑን።”

ወይም “ፍርዶቼንም።”

ወይም “በማመፃቸው።”

ቃል በቃል “ታማኝነቴም የውሸት አይሆንም።”

ወይም “ዘውዱን።”

ወይም “የድንጋይ መጠለያዎቹን።”

ቃል በቃል “የባላጋራዎቹን ቀኝ እጅ ከፍ ከፍ አድርገሃል።”

ወይም “ነፍሱን።”

ወይም “ከሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ያከናወንካቸው የታማኝ ፍቅር መግለጫዎች የት አሉ?”

ቃል በቃል “በእቅፌ እንደተሸከምኩ።”

“መጠጊያችን” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “አምጠህ ከመውለድህ።”

ክፍለ ሌሊት ፀሐይ ከጠለቀችበት አንስቶ እስከምትወጣበት ድረስ ካለው ጊዜ ውስጥ አንድ ሦስተኛውን ይሸፍናል። በመሆኑም እንደ ወቅቱ ሁኔታ፣ አንድ ክፍለ ሌሊት የአራት ሰዓት ገደማ ርዝማኔ ሊኖረው ይችላል።

ወይም “በደላችንን ታውቃለህ።”

ወይም “ሕይወታችን።”

ወይም “እንደ እስትንፋስ ወዲያው ያከትማል።”

ወይም “ልዩ ብርታት ቢኖረን።”

ወይም “አጽናልን።”

ወይም “ማንም አጠገብህ እንዳይደርስ በላባዎቹ ይከልልሃል።”

ወይም “ምሽግ።”

ቃል በቃል “በቀል።”

“ምሽግህ፤ መጠጊያህ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

በእስያና በአፍሪካ የሚገኝ እጅግ መርዘኛ የሆነ እባብ፤ ኮብራ።

ቃል በቃል “ከእኔ ጋር ስለተቆራኘ።”

ወይም “ለስሜ እውቅና ስለሚሰጥ።”

ወይም “የእኔን ማዳን እንዲያይ።”

ወይም “ሣር።”

ቃል በቃል “ቀንዴን።”

ወይም “በሸበቱ።”

ቃል በቃል “እንደሰቡና።”

ወይም “ፍሬያማ የሆነችው ምድር።”

ወይም “ቅድስና ይገባዋል።”

ቃል በቃል “የተከለው።”

ቃል በቃል “ነፍሴ በዝምታ በኖረች ነበር።”

ወይም “እረፍት የሚነሱ ሐሳቦች በውስጤ በበዙ ጊዜ።”

ወይም “ማጽናኛዎችህ ነፍሴን አረጋጓት።”

ወይም “ፈራጆች።” ቃል በቃል “ዙፋን።”

ወይም “በአዋጅ።”

ወይም “በጻድቁ ነፍስ ላይ።”

ቃል በቃል “የንጹሑንም ሰው ደም በደለኛ (ክፉ) ያደርጉታል።”

ቃል በቃል “ጸጥ ያሰኛቸዋል።”

ቃል በቃል “በእጁ።”

“ጠብ” የሚል ትርጉም አለው።

“ፈተና፤ ፈታኝ ሁኔታ” የሚል ትርጉም አለው።

ወይም “ክብርና።”

“ከቅድስናው ግርማ የተነሳ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ይሖዋን አምልኩ።”

ወይም “ፍሬያማ የሆነችው ምድር።”

ወይም “ልትናወጥ አትችልም።”

ወይም “ይሟገታል።”

ወይም “መጥቷልና።”

ወይም “ፍሬያማ በሆነችው ምድር።”

ወይም “እሱን አምልኩ።”

ቃል በቃል “ሴት ልጆች።”

ወይም “ነፍስ።”

ወይም “ኃይል።”

ቃል በቃል “ለቅዱስ መታሰቢያውም።”

ወይም “ድል አቀዳጅቶታል።”

ወይም “የአምላካችንን ድል።”

ወይም “ፍሬያማ የሆነችው ምድርና።”

ወይም “መጥቷልና።”

ወይም “ፍሬያማ በሆነችው ምድር።”

“በኪሩቤል መካከል” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “አምልኩ።”

ቃል በቃል “ተበቀልካቸው።”

ወይም “አምልኩ።”

ወይም “እውቅና ስጡ።”

“እኛም አይደለንም” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “በንጹሕ አቋም።”

መዝ 7:8 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።

ወይም “ከንቱ።”

ወይም “ተግባራቸው ከእኔ ጋር አይጣበቅም።”

ቃል በቃል “አላውቅም።”

ወይም “አጠፋዋለሁ።”

ወይም “በንጹሕ አቋም።”

ቃል በቃል “በዓይኖቼ ፊት።”

ወይም “አጠፋቸዋለሁ።”

ወይም “በደከመና።”

ወይም “ጎንበስ ብለህ ስማኝ።”

ወይም “ገርጌሶ።” ጠፍጠፍ ያለ ረጅም መንቆር ያለው ትልቅ አሞራ።

“መነመንኩ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “እንደሚረዝም።”

ወይም “ስምህም።” ቃል በቃል “መታሰቢያህም።”

ቃል በቃል “የሚፈጠረው።”

ወይም “ነፍሴ ይሖዋን ታወድስ።”

ወይም “ነፍሴ ይሖዋን ታወድስ።”

ወይም “ከመቃብር።”

ወይም “ቸር።”

ወይም “ፍቅራዊ ደግነቱ።”

ቃል በቃል “ቦታውም ከዚያ በኋላ አያውቀውም።”

ቃል በቃል “የቃሉን ድምፅ የምትሰሙ።”

ወይም “ሉዓላዊነቱ በሰፈነበት ቦታ።”

ወይም “ነፍሴ ይሖዋን ታወድስ።”

ወይም “ነፍሴ ይሖዋን ታወድስ።”

ወይም “ክብርንና።”

ቃል በቃል “በውኃዎቹ ውስጥ።”

ወይም “ደረቅ ወንዞች።”

ባለ ረጃጅም እግር ትልቅ አሞራ።

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

“ስለ እሱ የማሰላስለው ነገር ደስ የሚያሰኝ ይሁን” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ነፍሴ ይሖዋን ታወድስ።”

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

“አስደናቂ ስለሆኑት ሥራዎቹ ሁሉ ተናገሩ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ቃል በቃል “ያዘዘውን ቃል።”

ቃል በቃል “እያንዳንዱን የዳቦ በትር ሰበረ።” ዳቦ ለማስቀመጥ የሚያገለግሉ በትሮችን ሊያመለክት ይችላል።

ቃል በቃል “አጎሳቆሉ።”

ወይም “ነፍሱ ብረት ውስጥ ገባች።”

ወይም “ነፍሱን ደስ ባሰኘው።”

ቃል በቃል “መኳንንቱን እንዲያስር።”

ወይም “ክፍሎች እንኳ።”

ወይም “የእሳት ነበልባል።”

ወይም “ዘር የመተካት ችሎታቸው።”

ቃል በቃል “እነሱን።”

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

ወይም “በጎ ፈቃድ።”

ወይም “በአንተ እንድኩራራ።”

ወይም “የድንቅ ሥራዎችህን ትርጉም መረዳት አልቻሉም።”

ወይም “በምድረ በዳ።”

ወይም “ነፍሳቸውን በሚያመነምን።”

ወይም “ቀልጦ ለተሠራ ሐውልት።”

ወይም “አክብሮታዊ ፍርሃት የሚያሳድሩ።”

ቃል በቃል “ክፍተቱ ላይ በእሱ ፊት ቆመ።”

ወይም “በፌጎር ከነበረው ባአል ጋር ራሳቸውን አቆራኙ።”

ለሞቱ ሰዎች ወይም ሕይወት ለሌላቸው አማልክት የቀረቡ መሥዋዕቶችን ያመለክታል።

ይህ ቃል “ጠብ” የሚል ትርጉም አለው።

ወይም “ተማሩ።”

ቃል በቃል “እጅ።”

ወይም “ወሰን በሌለው።”

ወይም “ይጸጸት።”

ወይም “በውዳሴህ ሐሴት እንድናደርግ።”

ወይም “ይሁን!”

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

ወይም “ይሖዋ የተቤዣቸው።”

ወይም “ኃይል።”

ወይም “ከፀሐይ መውጫና ከፀሐይ መግቢያ።”

ወይም “ነፍሳቸው ተዝለፈለፈች።”

ወይም “የተጠማችውን ነፍስ።”

ወይም “የተራበችውንም ነፍስ።”

ወይም “ነፍሳቸው ማንኛውንም ምግብ ተጸየፈች።”

ወይም “ነፍሳቸው ቀለጠች።”

ቃል በቃል “መቀመጫ።”

ወይም “ከፍ ያለ ቦታ ላይ ያስቀምጣቸዋል።” የማይደረስበት ቦታ ላይ ያደርጋቸዋል ማለት ነው።

“በቅዱስ ስፍራው” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ረባዳማ ሜዳ።”

ቃል በቃል “ለራሴ ምሽግ ነው።”

ወይም “ከሳሽ።”

ወይም “ክፉ።”

ቃል በቃል “ወንዶች ልጆቹ።”

ቃል በቃል “ወንዶች ልጆቹ።”

ወይም “አራጣ አበዳሪዎች ወጥመድ ይዘርጉበት።”

ወይም “ታማኝ ፍቅር።”

ወይም “ትውልዱ።”

ወይም “ታማኝ ፍቅር።”

ወይም “በነፍሴም።”

ቃል በቃል “ሥጋዬ ኮሰመነ፤ ስብም (ዘይትም) የለውም።”

ወይም “እጅጌ እንደሌለው ቀሚስ።”

ወይም “በነፍሱ።”

ወይም “መግዛት ጀምር።”

ወይም “ሠራዊትህ ለጦርነት በሚንቀሳቀስበት ቀን።”

ወይም “አይጸጸትም።”

ወይም “መካከል።”

ወይም “መላውን ምድር።”

ቃል በቃል “ራስ።”

መዝ 110:1 ላይ “ጌታዬ” ተብሎ የተጠቀሰውን ያመለክታል።

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

ወይም “ቸርና።”

ወይም “ጽኑ መሠረት ያላቸው።”

ቃል በቃል “እነሱን የሚጠብቁ።”

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

ወይም “ቸርና።”

ወይም “ቆራጥ ነው፤ ጽኑ ነው።”

ወይም “በልግስና።”

ቃል በቃል “የገዛ ቀንዱ።”

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

ወይም “በዙፋን ላይ እንደተቀመጠው።”

“ከቆሻሻ መጣያ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ቃል በቃል “የወንዶች ልጆች።”

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

ወይም “ቅዱስ ስፍራው።”

ወይም “የእኛ የምንለው ምንም ነገር የለም፤ ይሖዋ ሆይ፣ የእኛ የምንለው ምንም ነገር የለም።”

ቃል በቃል “ወንዶች ልጆቻችሁን።”

ቃል በቃል “ወደ ዝምታ።”

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

“ይሖዋ ስለሚሰማ ውስጤ በፍቅር ይሞላል” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ጎንበስ ብሎ ይሰማኛልና።”

ቃል በቃል “በቀኖቼ።”

ቃል በቃል “የሲኦል ጭንቅ አገኘኝ።”

ወይም “ነፍሴን ታደግ።”

ወይም “ቸርና።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ነፍሴን።”

ቃል በቃል “ክቡር።”

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

ወይም “ጎሳዎች።”

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

“ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

ወይም “ሰፊ ወደሆነ ስፍራም።”

“ከሚረዱኝ ሰዎች ጋር” ማለትም ሊሆን ይችላል።

“በኃይል ገፋኸኝ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “የድል።”

ቃል በቃል “የማዕዘኑ ራስ።”

ወይም “ንጹሕ አቋማቸውን የሚጠብቁ።”

ቃል በቃል “ምነው መንገዴ ጽኑ በሆነልኝ!”

ወይም “መመሪያዎችህን አጠናለሁ።”

ወይም “ነፍሴ . . . ከመናፈቋ የተነሳ ዛለች።”

ቃል በቃል “ከላዬ ላይ አርቅ።”

ወይም “ሥርዓትህን ያጠናል።”

ወይም “ነፍሴ አፈር ላይ ተደፍታለች።”

ወይም “አስደናቂ የሆኑትን ሥራዎችህን አጠና ዘንድ።”

ወይም “ነፍሴ እንቅልፍ አጣች።”

ወይም “ለኀፍረት።”

“ልቤ የመተማመን ስሜት እንዲያድርበት ስላደረግክ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ቃል በቃል “እሮጣለሁ።”

ወይም “እንድሄድ አድርገኝ።”

ወይም “ትርፍ።”

ወይም “የተናገርከውን ነገር።”

“ለሚፈሩህ የገባኸውን ቃል፣ ለአገልጋይህ ፈጽም” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “በተናገርከው።”

ወይም “ፍርድህን እጠባበቃለሁና።”

ወይም “ሰፊ በሆነ ስፍራ።”

ወይም “ሥርዓትህንም አጠናለሁ።”

ወይም “የሰጠኸውን ተስፋ።”

ወይም “ይህን ቃል እንድጠባበቅ አድርገኸኛል።”

ወይም “የባዕድ አገር ሰው ሆኜ በምኖርበት ቤት።”

ወይም “በተናገርከው።”

ወይም “በስህተት ኃጢአት እሠራ ነበር።”

ቃል በቃል “ልባቸው እንደ ስብ ደንድኗል።”

ወይም “ቃልህን እጠባበቃለሁና።”

ወይም “በተናገርከው።”

“በውሸት” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “መመሪያዎችህን አጠናለሁ።”

ወይም “ነፍሴ ማዳንህን ከመናፈቋ የተነሳ ዛለች።”

ወይም “ቃልህን እጠባበቃለሁና።”

የፍጥረት ሥራዎቹን በሙሉ ያመለክታል።

ቃል በቃል “በጣም ሰፊ ነው።”

ወይም “ቀኑን ሙሉ አጠናዋለሁ።”

ወይም “ማሳሰቢያዎችህን ስለማጠና።”

ቃል በቃል “በአፌ በፈቃደኝነት የማቀርበውን መባ።”

ወይም “ነፍሴ ሁልጊዜ እጄ ውስጥ ናት።”

ወይም “ዘላለማዊ ውርሻዬ።”

ቃል በቃል “ልቤን አዘንብያለሁ።”

ወይም “የተከፈለ ልብ ያላቸውን ሰዎች።”

ወይም “ቃልህን እጠባበቃለሁና።”

ወይም “በተናገርከው።”

ወይም “እንዳፍር አታድርግ።”

ቃል በቃል “ሥጋዬ።”

ወይም “የተናገርከውን።”

ወይም “ከጠራ።”

ወይም “መመሪያህ።”

ወይም “ነፍሴ ትጠብቃቸዋለች።”

ቃል በቃል “አፌን ከፍቼ አለከልካለሁ።”

ወይም “አካሄዴን አጽና።”

ቃል በቃል “ዋጀኝ።”

ወይም “ለአገልጋይህ ፈገግታ አሳይ።”

ወይም “በማለዳ ወጋገን።”

ወይም “ቃልህን እጠባበቃለሁና።”

ወይም “ቃልህን ማጥናት።”

ወይም “ጸያፍ በሆነ ምግባር።”

ወይም “ጥብቅና ቁምልኝ።”

ወይም “በተናገርከው።”

ወይም “እንቅፋትም የለባቸውም።”

ወይም “ነፍሴ ማሳሰቢያዎችህን ትጠብቃለች።”

ወይም “በተናገርከው።”

ወይም “ነፍሴ በሕይወት ትኑር።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ነፍሴን ታደጋት።”

ቃል በቃል “ደግሞስ ምን ይጨምርልህ ይሆን?”

ወይም “ነፍሴ ለረጅም ጊዜ ኖራለች።”

ወይም “እሱ እግርህ እንዲውተረተር።”

ወይም “ነፍስህን።”

ቃል በቃል “መውጣትህንና መግባትህን ይጠብቃል።”

“ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

ወይም “በተመሸጉ ቅጥሮችሽ።”

ወይም “ነፍሳችን ከልክ በላይ ጠግባለች።”

ወይም “ነፍሳችንን ጎርፍ ባጥለቀለቃት ነበር።”

ወይም “ነፍሳችንን በዋጣት ነበር።”

ወይም “ነፍሳችን ከአዳኝ ወጥመድ እንዳመለጠች ወፍ ነች።”

ወይም “እጃቸውን ወደ ክፋት እንዳያዞሩ።”

ወይም “በደቡብ እንዳሉ ደረቅ ወንዞች።”

ወይም “ቀድሞ ወደነበሩበት ሁኔታ መልስ።”

ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”

ይህ ጠላቶቻቸው የሚፈጽሙባቸውን የጭካኔ ድርጊት ያሳያል።

“ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

ወይም “በትኩረት የምትመለከት።”

ወይም “ለአንተ አክብሮታዊ ፍርሃት እንዲያድርባቸው።”

ወይም “ነፍሴ በእሱ ተስፋ ታደርጋለች።”

ወይም “ነፍሴ ይሖዋን በጉጉት ትጠባበቃለች።”

ወይም “ራሴን አረጋጋሁ።” የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ነፍሴ ጡት እንደጣለ ሕፃን ረካች።”

ቃል በቃል “ከማህፀንህ ፍሬ (አንዱን)።”

ቃል በቃል “የዳዊትን ቀንድ አበቅላለሁ።”

ወይም “ዘውድ።”

“በመቅደሱ ውስጥ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

ወይም “ውድ ሀብቱ።”

ወይም “ተን።”

“ለዝናብ መውጫ ያዘጋጃል” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ስምህ።” ቃል በቃል “መታሰቢያህ።”

ወይም “ጥብቅና ይቆማልና።”

ወይም “ይጸጸታል።”

ወይም “በማስተዋል ሠራ።”

ወይም “እንዲገዛ።”

ወይም “እንዲገዙ።”

ቃል በቃል “በታተነ።”

ቃል በቃል “ለሥጋ።”

ባቢሎንን ያመለክታል።

“ትመንምን” ማለትም ሊሆን ይችላል።

“ሌሎች አማልክትን በመቃወም ለአንተ ዜማ አሰማለሁ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

“ከስምህ ሁሉ በላይ ቃልህ ጎልቶ እንዲታይ አድርገሃል” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “በነፍሴ ደፋርና።”

ወይም “ለእኔ እጅግ አስደናቂ ነው።”

ወይም “ከመረዳት አቅሜ በላይ ነው።”

ወይም “በሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

“አበጃጅተህ ሠራኸኝ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “ነፍሴ ይህን በሚገባ ታውቃለች።”

ቃል በቃል “ጥልቅ በሆኑ የምድር ክፍሎች ውስጥ በተሸመንኩ ጊዜ።”

“ገና እየቆጠርኳቸው እገኛለሁ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “የደም ዕዳ ያለባቸው ሰዎች።”

ወይም “የመሰላቸውን።”

ወይም “እረፍት የሚነሱኝንም።”

ወይም “ውኃ ወዳለባቸው ጉድጓዶች።”

ወይም “በአገሪቱ።”

ወይም “በሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ነፍሴንም አታፍስሳት።”

የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

ወይም “ጉልበቴ።”

ቃል በቃል “ለእኔ እውቅና የሚሰጥ።”

ወይም “ስለ ነፍሴ።”

ቃል በቃል “በሕያዋን ምድር ድርሻዬ አንተ ነህ።”

ወይም “ነፍሴን ከእስር ቤት አውጣት።”

ወይም “ነፍሴን ያሳድዳታልና።”

ወይም “ጉልበቴ።”

ወይም “አጠናለሁ።”

ወይም “ነፍሴ እንደ ደረቅ ምድር አንተን ተጠማች።”

ቃል በቃል “መንፈሴ።”

ወይም “መቃብር።”

ወይም “ነፍሴን ወደ አንተ አነሳለሁና።”

ወይም “በቅንነት ምድር።”

ወይም “ነፍሴን ከጭንቅ ታደጋት።”

ቃል በቃል “ጸጥ አሰኛቸው።”

ወይም “ነፍሴን የሚያጎሳቁሏትን።”

ወይም “አጥፈህ።”

ወይም “መዳፍ።”

ቃል በቃል “ቀኝ እጃቸውም የውሸት ቀኝ እጅ ናት።”

ወይም “መዳን።”

ወይም “ከመረዳት ችሎታ በላይ ነው።”

ወይም “ኃይልህ።”

ወይም “ቸርና።”

ወይም “በቅንነት።”

ቃል በቃል “ሥጋ ሁሉ ቅዱስ ስሙን።”

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

ወይም “ነፍሴ።”

ወይም “በታላላቅ ሰዎችም።”

ወይም “እስትንፋሱ።”

ቃል በቃል “የታሰሩትን ይፈታል።”

ወይም “የክፉዎችን መንገድ ግን ያጣምማል።”

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

ቃል በቃል “በስንዴ ስብ።”

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

ቃል በቃል “ደናግል።”

ቃል በቃል “ቀንድ።”

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

ወይም “ስለ ብርታቱ በሚመሠክረው ሰማይ።”

እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል፣ እርስ በርሱ ሲጋጭ ኃይለኛ ድምፅ የሚያወጣን ክብ ቅርጽ ያለው ከብረት የተሠራ የሙዚቃ መሣሪያ ያመለክታል።

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

    የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ